ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
43.4K subscribers
28.2K photos
248 videos
21 files
731 links
The best fiction is far more true than any journalism

📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ

👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56



👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Download Telegram
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 12ሰዎች ህይወት አልፏል  

በኦሮሚያ ክልል ከግንቦት26 እስከ  ሰኔ 02 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ 12 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በ8ሰዎች ላይ ከባድ እና በ 12ሰው ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አብዛኞቹ የሞት አደጋዎች  የተከሰቱት በምስራቅ አርሲ፣ቦረና፣ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ምስራቅ ጉጂ፣ሰሜን ሸዋ፣ምእራብ ሀረርጌ ዞኖች እና ሻሸመኔ፣ጅማ ከተማዎች የተከሰቱ መሆናቸውን  የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

አብዛኛዎቹ አደጋዎች  የተከሰቱት በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሲሆን   የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት ተሽከርካሪ፣በህዝብ ማመላለሻ፣ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) እና በሞተር ሳይክል የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
                     
የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማስከርከር፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር፣ ደርቦ ማለፍ  ምልክቶችን አለማክበር ፣የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
የማላዊው ፕሬዝዳንት የሀገሪቱን ምክትልፕሬዝዳንት ይዞ የጠፋውን አውሮፕላን ለማግኘት ድጋፍ ጠየቁ

የማላዊ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ሰኞ እለት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሎስ ቺሊማን እና ዘጠኝ ሌሎች ሰዎችን ይዞ የተሰወረዉን ወታደራዊ አውሮፕላን ለማግኘት መንግስታቸው የሀገሪቱን ጎረቤቶች እና የልማት አጋሮችን እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚደንት ቻኩዌራ ስለጠፋው አውሮፕላን መረጃ ለማግኘት መንግስታቸው የአሜሪካን፣ እስራኤልን፣ ኖርዌይን እና የእንግሊዝን መንግስታትን ማነጋገሩን ተናግረዋል።እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ የልማት አጋሮች ልዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም “አውሮፕላኑን በቶሎ የማግኘት አቅማችንን የሚያጎለብት” ድጋፍን በተለያዩ መንገዶች ሰጥተዋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡“ይህ በጣም አሳዛኝ ሁኔታ እንደሆነ አውቃለሁ። ሁላችንም እንደምንፈራ እና እንደሚያሳስበን እረዳለሁ። እኔም ያሳስበኛል።

ነገር ግን ይህ አዉሮፕላን ለማግኘት ምንም አይነት ሃብት እንደማልቆጥብ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ እና በህይወት የተረፉ ሰዎችን እንደምናገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ምክትል ፕሬዝዳንቱን ያሳፈረዉ አዉሮፕላን ሰኞ እለት ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ሊሎንግዌ ተነስቶ ወደ ሰሜናዊቷ የሀገሪቱ ከተማ ምዙዙ በማምራት ላይ የነበረ ሲሆን የሀገሪቱ የቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር እና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ራልፍ ካሳምባራ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመታደም ዉጥን ነበራቸዉ፡፡

ከምክትል ፕሬዝዳንቱ በተጨማሪ በአውሮፕላኑ ውስጥ በርካታ የፓርቲያቸው ባለሥልጣናት ነበሩ።ምክትል ፕሬዝዳንቱን የያዘው አውሮፕላን መጥፋት በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት አዛዥ ከተነገራቸው በኋላ የማላዊው ፕሬዝዳንት ላዛረስ ቻክዌራ ወደ በውጭ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዟቸውን ሰርዘዋል። የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ “የተረጋገጡ መረጃዎች በተገኙ ጊዜ ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል” ብሏል።የአገሪቱ ጦር አዛዥ ጄኔራል ቫለንቲኖ ፊሪ ለፕሬዝዳንቱ ክስተቱን ባሳወቁበት ጊዜ ለአውሮፕላኑ መሰወር ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንዳልታወቀ ተናግረዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ወደ ፖለቲካው ዓለም ከመግባታቸው በፊት ዩኒሊቨር እና ኮካኮላን በመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ በከፍተኛ የመሪነት ቦታ ላይ ሠርተዋል።ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት የሆኑት የ51 ዓመቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ቺሊማ ደቡባዊ አፍሪካዊቷ አገር ማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ከአውሮፓውያኑ 2014 ጀምሮ እያገለገሉ ነው።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ኤርትራ በሌሊት ብቻ የሚሰራ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሯ ተሰማ

👉🏼 የሙሉ ሌሊት ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እስከ 105 ዶላር ድረስ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል


ኤርትረ በትናንትናው እለት የሌሊት ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሯን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ኤርትራ በሌሊት ብቻ ይሰጣል ባለችዉ የኢንተርኔት አገልግሎት እጅግ ዉድ ሊሰኝ እንደሚችል የኢንተርኔት እና የኮምፒውተር ባለሙያ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሰከንድ 512 ኪሎ ባይት ድረስ አገልግሎት ይሰጣል የተባለዉ ኢንተርኔት በቤት ስልክ መስመር የሚመጣ ሲሆን ተጠቃሚዎች ወደ ሞባይል እና ኮምፒውተሮቻቸዉ ማገናኘት እና መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ኤርትራ በትናንትናው እለት ሌሊቱን ያስጀመረችዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ባለሙያዎች ገለጻ ዘንድ ቀርፋፋ ነዉ የተሰኘዉን ነዉ።

ሁለት አይነት የኢንተርኔት ማስተላለፊያ መስመሮች ያሉ ሲሆን ኤዲኤስኤል (ADSL) በሲርናል ኢንተርኔት የሚደርስበት ሲሆን ቀርፋፋ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥበትም ነዉ። በአንጻሩ በፋይበር የሚተላለፈዉ ኢንተርኔት በብርሃን አጋዥነት አገልግሎት የሚሰጥበት ሲሆን እጅግ ፈጣኑም እንደሆነ ባለሙያዉ ገልጸዋል።

ታድያ ኤርትራ አስጀመረችዉ የተባለዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ኤዲኤስኤል (ADSL) የተሰኘዉን ነዉ። ይህ አሁንም በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም ቀርፋፋዉ አገልግሎት መሆኑን ባለሙያዉ ገልጸዋል።

ከሌሊቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከ 512 እስከ 1 ሜጋባይት ድረስ በሰከንድ ኢንተርኔት የሚያስጠቅነዉን አገልግሎት ለማግኘት ኤርትራውያን 1575 ናቅፋህ ወይንም 105 የአሜሪካ ዶላር መክፈል አለባቸው ተብሏል።

የተለያዩ አገልግሎቶች ይሰጣሉ የተባለ ሲሆን ተጠቃሚዎች እስከ 10 ጊጋ ባይት ድረስ የሆነና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን ማግኘት ካሻቸዉ ደግሞ 4200 ናቅፋህ ወይንም 280 የአሜሪካ ዶላር ከፍያ መፈጸም እንዳለባቸው ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከተሰራጨው ማስታወቂያ ላይ መታዘብ ችሏል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
በምስራቅ ጎጃም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች አንድ ሺህ አይሞሉም

በምስራቅ ጎጃም ዞን 996 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቢኖሩም  የመማር ማስተማር ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙት 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ መሆናቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታውቋል ።

በትምህርት ዘመኑ ከአንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ539 ሺህ 996 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንደሚመጡ ቢታቀድም ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት ከ13 ሺህ  የሚበልጡ አይደሉም ተብሏል ። በበጀት አመቱ 791 ት/ቤቶች ከ41 ሺህ 944 በላይ ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንደሚያስፈትኑ ቢጠበቅም 12 ት/ቤቶች በሁለት ዙር 506 ተማሪዎችን ብቻ  እንደሚያስፈትኑ ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል ።

በተጨማሪም 593 ት/ቤቶች 38 ሺህ 203 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ ቢታቀድም በ10 ት/ቤቶች  431 ተማሪዎች ብቻ በሁለት ዙር ፈተና የሚወስዱ ይሆናል ብሏል ። እንዲሁም 65 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ19 ሺህ 657 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሃገር ዓቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ ቢታሰብም 5 ት/ቤቶች 577 ተማሪዎችን ብቻ በሁለት ዙር እንደሚያስፈትኑ ተገልጿል ።

የት/ቤቶች መዘጋት የተማሪዎችንና ማህበረሰቡን ስነልቦና ከመጉዳት ባለፈ  በትውልድ ግንባታ ስራው ላይ ከፍተኛ ማነቆ የፈጠረና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የትምህርት ማህበረሰብ አባላትን ከመደበኛ ስራቸው ውጭ ማድረጉን ገልጿል ። በተለይም ከ407 በላይ ት/ቤቶች እንዲወድሙና ለመማር ማስተማር አገልግሎት እንዳይሰጡ መሆናቸውን ተከትሎ ከ290 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የት/ቤቶች ሀብትና ንብረት ወድሟል ተብሏል ።

ስለሆነም የተማሪዎችን የወደፊት ዕድል በፅኑ መሠረት ላይ ለማቆም የቀጣይ የትምህርት ስራን በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል ። በተያያዘም ዘንድሮ በሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የክልልን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ማስታወቁ ይታወሳል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
ደቡብ ኮሪያ የጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ድንበር ካቋረጡ በኋላ የማስጠንቀቂያ ተኩስ መተኮሷን አስታወቀች

የደቡብ ኮሪያ ጦር ከሰሜን ኮሪያ የመጡ ወታደሮች አገራቱን በሚለየው ዞን ድንበር ከተሻገሩ በኋላ የማስጠንቀቂያ ተኩስ መተኮሳቸዉን ገልጿል።

ክስተቱ ያጋጠመዉ እሁድ እለት ከቀኑ 12፡30 ሰዓት ላይ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ቡድን ያለውን ወታደራዊ ድንበር ማቋረጣቸዉን ተከትሎ ነዉ ሲል የዮንሃፕ የዜና ወኪል የሰራተኞች የጋራ አለቆች መግለጫ አስታዉቋል፡፡የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች ማስጠንቀቂያዎችን በማሰራጨት ወደ አየር መተኮሳቸውን የገለጹ ሲሆን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችም ወደተጠናከረው ድንበር ተመልሰዋል።

ይህ ክስተት ያጋጠመዉ ፒዮንግያንግ ከ1,000 በላይ በቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎች በድንበር ላይ ከላከች በኋላ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ተከትሎ ነዉ፡፡ ደቡብ ኮሪያ በ2018 ያቆመችውን የፕሮፓጋንዳ ስርጭቷን ቀጥላለች።ደቡብ ኮሪያ በሰሜን ኮሪያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ስርጭቱን ከስድስት ዓመታት በኋላ ለማስጀመር የወሰነችው ሰሜን ኮርያ በፊኛዎች አማካኝነት ቆሻሻ ወደ ግዛቷ መለካ መቀጠሏን ተከትሎ ነው።

የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኃያል እህት ኪም ዮ ጆንግ ስርጭቱ “የግጭት ቀውስ” ሊያስነሳ እንደሚችል ተናግራለች።በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጠችዉ መግለጫ “ይህ በጣም አደገኛ ለሆነ ሁኔታ ቅድመ ዝግጅት ነው” ስትል ተናግራለች።ሰሜን ኮሪያ ለሴኡል የድምጽ ማጉያ ስርጭቶች እጅግ በጣም ትቸገራለች ምክንያቱም እንዲህ ያለው መልእክት የፊት መስመር ወታደሮችን እና ነዋሪዎችን ተስፋ ያስቆርጣል እና በመጨረሻም የኪም ጆንግ ኡን ስልጣንን ያዳክማል በማለት ተንታኞች ተናግረዋል ።

እ.ኤ.አ. በ 2015 ደቡብ ኮሪያ ከረዥም ጊዜ ቆይታ በኋላ ስርጭቱን እንደገና የጀመረችበት ለመጨረሻ ጊዜ ሰሜን ኮሪያ ድንበሯን አቋርጣ መድፍ በመተኮሷ ደቡብ ኮሪያ ተኩስ እንድትመልስ አድርጋለች። በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አልደረሰም።የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ሃይል ስርጭቱ በቀን እስከ 10 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ እንዲሁም በሌሊት ደግሞ እስከ 24 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ ሊሰማ ይችላል ብሏል። በግንቦት ወር ላይ መቀመጫውን ደቡብ ኮሪያ ያደረገው የመብት ተሟጋች ቡድን ፀረ ፒዮንግያንግ በራሪ ወረቀቶችን እና የኮሪያ ፖፕ ሙዚቃ እና የሙዚቃ ቪዲዮዎችን የያዙ 20 ፊኛዎችን ድንበር አቋርጦ እንደላከ አስታውቋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ብቻ ከቡና ሽያጭ ከ2መቶ ዘጠኝ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

በ2016 በጀት ዓመት 11 ወራት ወደ ውጪ ገበያ ከተላከ የቡና ምርት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል ።በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳህለ ማርያም ገብረመድህን ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በግንቦት ወር የላከችው የቡና ምርት በመጠንም ሆነ በገቢ ከፍተኛ የሆነ ውጤት አስገኝቷል።

ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ብቻ 43ሺህ 481 ነጥብ 2 ቶን ቡናን ወደ ውጪ ሀገራት ልካ የእቅዷን 105% የሚሆነውን ውጤት ማስመዝገብ ችላለች ነው ያሉት፡፡ ከገቢም አንጻር በባለፈው የግንቦት ወር ብቻ ኢትዮጵያ 2መቶ9 ነጥብ 54 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማሳካት የቻለች ሲሆን ይህ ውጤት ከባለፉት ሶስት በጀት ዓመታት ተመሳሳይ ወራት ከተላከው ምርት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ውጤት የታየበት ነው ሲሉ አቶ ሳህለማርያም ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ውስጥ 252ሺህ 466 ነጥብ 98 ቶን የቡና ምርት በመላክ 1 ቢሊዮን 208 ሚሊዮን 73ሺህ የአሜሪካን ዶላር በማግኘት ሪከርድ የመስበሩን ግስጋሴ ኢትዮጵያ ቀጥላለች ተብሏል፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የተለያዮ ስራዎችን ለመስራት ታቅዷል ተብሏል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
​​📝 የተጠናቀቀ ስምምነት : ኑረንበርግ ጀርመናዊው አንጋፋ ተጫዋች ሚሮስላቭ ክሎዝን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ ሹሟል ።

#ዳጉ_ጆርናል
​​🚨ባለበት ይቆያል : በአርሰናል ፣ ማን ሲቲና ፣ ማንችስተር ዩናይትድ በጥብቅ ሲፈለግ የቆየው ቤንጃሚን ሴስኮ በጀርመኑ ክለብ አርቢ ሌፕዚሽ በተሻሻለው ደሞዝ ለመቆየት ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል ።

#ዳጉ_ጆርና
​​📝 የተጠናቀቀ ስምምነት ፡ ማርኮ ባሮኒ አዲሱ የላዚዮ አሰልጣኝ መሆኑ ተረጋግጧል 🦅👔

#ዳጉ_ጆርናል
​​🚨 ይፋዊ ! ሎረንት ኮሸሊኒ አዲሱ የሎረንት ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሆኗል ! 🧡👔

#ዳጉ_ጆርናል
የባለቤቱን እህት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

ግርማ ሳህሉ ነዋሪነቱ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ ካራ ሚሌ ቀበሌ ዉስጥ ሲሆን ትዳር መስርቶ ህይወቱን መርቷል። ግለሰቡ በተደጋጋሚ ከባለቤቱ ጋር በመካከላቸው ለሚፈጠር ግጭት የባለቤቱን ታላቅ እህት ተጠያቂ ሲያደርግ መቆየቱን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሚል ቱጂያን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ታላቅ እህት የሺመቤት መንግስቱ በታናሽ እህቷ ባለቤት ትዳሬን እየበጠበጥሽ ነዉ በሚል ተደጋጋሚ ክስ እና ዉንጀላ ሲቀርብባት የቆየ ሲሆን ከዚህ በዘለለም ማስፈራሪያ እና ዛቻ ሲያደርስባት ቆይቷል ብለዋል። እህት በሁለቱ ባለትዳሮች መካከል ግጭት ሲፈጠርም በሽምግልና በማስታረቅ ብትቆይም በባል ሌላ መልክ ተሰጥቶት በጥርጣሬ ይታይ ነበር ብለዋል።

ግለሰቡ ከባለቤቱ ጋር የተፈጠረዉን ግጭት ተከትሎ ሚስት እንደልማዱ ቤቷን ለቅቃ ወደ ሌላ አካባቢ ትጓዛለች። ባል ፤ በወቅቱ ሚስቱን ወደ እህቷ ቤት ሄዳ ነዉ በሚል በጥርጣሬ ወደ ሟች የሺመቤት ቤት ማቅናቱንም ገልጸዋል።

ሟች ከሱቅ እቃዎችን ሸምታ በምትመለስበት ወቅትም ገዳይ አጋጣሚዉን በመጠቀም ከኋላ አንገቷን በስለት በተደጋጋሚ ወግቷት ተሰዉሯል ብለዉናል። ሟች የሺመቤት በስለቱ የደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ ከፍተኛ ደም ፈስሷት ወደ ህክምና ቦታ በመጓዝ ላይ እያለች ህይወቷ ማለፉን ገልጸዋል።

ፖሊስ ግለሰቡን ከተሰወረበት አፈላልጎ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በቁጥጥር ስር አዉሎ ጉዳዩን ለፍርድ አቅርቧል ብለዋል። ጉዳዩን ሲመለከት የነበረዉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግንቦት 17 ቀን ባዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ግርማ ሳህሉ በ 18 አመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሚል ቱጂያን ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
ይቆያል :

በስተመጨረሻ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ጉዳይ መቋጫ ያገኘ ይመስላል ። ማንችስተር ዩናይትድ እና አሰልጣኙ ፤ በውል ማራዘሚያ ዙሪያ ውይይት ማድረግ ጀምረዋል ። ቴን ሀግ "ክለቡ ተጨማሪ ዋንጫዎችን የሚሻ ከሆነ ከእኔ ጋር ሊሰራ የግድ ይለዋል" ሲል መናገሩ የሚታወስ ነው 🔴

#ዳጉ_ጆርናል
አዲስ አበባ ከተማን ከተሽከርካሪ ጭስ ነፃ የሚያደርጋት መመሪያ ተዘጋጀ

በአዲስ አበባ የተሽከርካሪ የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ደረጃ የአፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የአየር ንብረት ለውጥና አማራጭ ኢነርጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰይድ አብደላ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከፋብሪካዎች በሚወጡ ጭሶችና በሌሎች በካይ ነገሮች የተነሳ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የአየር ብክለት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለው የአየር ብክለት መጠን እንዲባባስ ያደረጉ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ ጭስ ትልቁን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።በከተማዋ የአየር ብክለት መጠን መጨሩን ተከትሎ የጤና ስጋት እየሆነ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ሰይድ በርካቶችን ለመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

በተጨማሪም ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ እአአ በ2019 የአለም ባንክ ባጠናው ጥናት መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በየአመቱ 1ሺህ 6መቶ የሚሆኑ ሰዎች ለህልፈት እንደሚዳረጉ ይፋ ማድረጉን ዳይሬክተሩ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።ችግሩን ለመፍታት አዲስ አበባን ከተሽከርካሪ ጭስ ነፃ የሚያደርጋት መመሪያ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪውን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን በወጣው ደረጃ መሰረት አሟልተው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው በተዘጋጀው መመሪያ ተመላክቷል። የተሽከርካሪን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ሊቀንሱ የሚችሉ አማራጭ የቴክኖሎጂ ወጤቶችን ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸውም በመመሪያው ተጠቅሷል።እንደዚሁም የተሽከርካሪውን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን በየዓመቱ የማስመርመር ግዴታ እንዳለባቸው መመሪያው ያስገድዳል ሲሉ አቶ ሰይድ ተናግረዋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል