ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
43.8K subscribers
32.4K photos
275 videos
21 files
827 links
The best fiction is far more true than any journalism

📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ

👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56



👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Download Telegram
ሚስቱንና ጎረቤቱን ገድሎ የተሰወረውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ህዳር 04 እና 05 ቀን 2018 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው 23 ቀበሌ መዝናናኛ ክበብ አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሽ እሱያውቃል ቢያዝን ከባለቤቱ ከወ/ሮ ሐመልማል አለምነው ጋር በትዳር ተጣምረው መኖር ከጀመሩ አራት ወራትን አስቆጥረዋል፡፡

ተጠርጣሪው ባለቤቱን ከሌላ ወንድ ጋር ስልክ ትደዋወያለሽ ከሌላ ሰው ፍቅር ጀምረሻል በሚል አጉል ጥርጣሬ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 4 ሠዓት አንገቷን አንቆ በመግደል ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በር ዘግቶባት ከአካባቢው ይሰወራል፡፡

በተጨማሪም ከአንድ ቀን በኋላ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ወደ መኖሪያ ግቢው ተመልሶ በመምጣት የ2 ልጆች አባት የሆነውን ወርቁ በቀለን ከምሽቱ 1ሰዓት በመኖሪያ ቤት ውስጥ በስምንት ጥይት ተኩሶ በመግደል ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ከአካባቢው ይሰወራል፡፡

የአቶ ወርቁ በቀለ በጥይት ተመተው መሞት መረጃ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ክትትል ክፍል የወንጀል ስፍራው ላይ በመገኘት እና መረጃ በማሰባሰብ ላይ ባሉበት ሁኔታ የገዳይ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሰው መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሙከራ ሲደረግ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የሐመልማል አለምነው አስከሬንም ሊገኝ ችሏል፡፡

ወንጀል ፈፃሚውን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ ከተማ ከተደበቀበት አልጋ ቤት ውስጥ የግድያ ወንጀሉን ከፈፀመበት ኢኮልፒ ሽጉጥ እና ከ23 ጥይቶች ጋር ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ሊያውለውም ችሏል፡፡

ግለሰቡ የወንጀል አፈፃጸሙን አስመልክቶ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም መርቶ ማሳየቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

ምንጭ:- አ.አ ፖሊስ

#ዳጉ_ጆርናል
💔2515👏3
👉 ከአምስት ቀናት በኃላ አንድ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ

👉 ለአምስት ተከታታይ ቀናቶች በነበረው የምርመራ ውጤቶች  በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው ሁሉም ነፃ እንደነበሩ ያሳያል።

👉 በዚህም መሰረት ዛሬ ህዳር 23/ 2018 የማርበርግ ቫይረስ በተደረገው ምርመራ 221 ሰዎች የተመረመሩ ሲሆን 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል።

👉ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4 የደረሰ ሲሆን 3 ከሆስፒታሉ ወጥተዋል ።

👉አሁን ላይ አንድ ሰው በህክምና ላይ እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

👉 በአጠቃላይ እስካሁን 888 ሰዎች ተመርምረው 13 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 8ቱ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

👉 በተጨማሪም አንዱ በህክምና ላይ ያሉት ታማሚ ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ በተመሳሳይ ቦታም የህክምና ክትትላቸውን እያደረጉ እንደሚገኝ ብስራት ሬዲዮ ከጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#ዳጉ_ጆርናል
12🙏2
የተባበሩት መንግስታት በ2026 ዓመት የሰዉ ኃይሉን በመቀነስ በጀቱን በ577 ሚሊዮን ዶላር ይቀንሳል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ2026 በጀቱን 15.1 በመቶ እና ሰራተኞቹን በ18.8 በመቶ እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ ከአባል ሀገራት ያልተከፈለ ክፍያ ወደ 1.59 ትሪሊየን ዶላር ከፍ ብሏል ሲሉ አክለዋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊ የሚቀጥለውን አመት በጀት ያሳወቁ ሲሆን ከ2025 ዓመት በ577 ሚሊዮን ዶላር የቀነሰ በ 3.24 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከሴፕቴምበር ጀምሮ ቅናሹ የመጣው ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከቻይና፣ ከሩሲያ እና ከሜክሲኮ ያልተከፈለ ክፍያ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መግለጫ አመልክቷል።ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት ወጪዉ እንደተጠበቀ ይቆያል ብለዋል ።

ጉሬሬዝ “በጋዛ በተደረገው አጠቃላይ የሰብአዊ ምላሽ ላይ ተጽእኖ ከሚያስከትሉ ማናቸውም ቅነሳዎች የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲን ነፃ ለማድረግ ወስኛለሁ” ብለዋል ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበርካታ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች ውስጥ 2,681 የስራ መደቦችን ይቀንዳል ፣ “በእኛ አስተያየት ፣ በሌሎች በተሻለ ሊከናወኑ ወይም በቅልጥፍና ሊተገበር ከሚችሉ እንቅስቃሴዎች ጋር ይዛመዳሉ” ብለዋል ።

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ መደቦች ውስጥ 18 በመቶ ያህሉ ያልተከፈሉ የአባላት መዋጮ እና ሌሎች እዳዎች እየተከሰቱ ባለበት የፈጣን ችግር ምክንያት ክፍት ናቸው ሲሉ ዋና ፀሃፊው ተደምጠዋል። “እነዚያ ክፍት ቦታዎች በስትራቴጂካዊ ቅድሚያ ከሚሰጠው ፖለቲካዊ ውሳኔ ጋር አይዛመዱም ፣ ግን በቀላሉ ሰዎች በመልቀቃቸው እና በቀውስ ምክንያት ተተኪውን ለመክፈል የሚያስችል ገንዘብ የለንም” ብለዋል ።

በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
14👎4
በሚዛን አማን ከተማ 108 የጎዳና ህፃናትን ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀልና ወደ ትምህርት ገበታ የመመለስ ስራ እየተሰራ ነዉ ተባለ

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በ2018 ዓ.ም 103 ወንዶችንና 5 ሴቶችን በአጠቃላይ 108 የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናትን በመለየት ከአጎራባች ቀበሌዎች የመጡ 63 ህፃናት ወደመጡበት ወረዳ እንዲመለሱ ዞኑ እንዲያቀላቅል ዝርዝራቸዉ መላኩን የከተማዉ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል ።

የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ለማ የተቀሩት 45 ህፃናት የከተማዉ አስተዳደር ህፃናት በመሆናቸዉ ቤተሰብ ያላቸዉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀልና ቤተሰብ የሌላቸውን ከቀበሌ እና ከሚመለከተዉ የሴክተር መስሪያ ቤት ጋር በመሆን መጠለያ እንዲዘጋጅላቸው እየሰራን ነዉ ሲሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ሶስት የጎዳና ህፃናት የጀበሎ ዕቃ ተገዝቶላቸዉ ወደ ስራ መግባታቸውን ተገልጿል ። በተጨማሪም በ2017 ዓ.ም 40 ህፃናት እንደ ከተማ አስተዳደር ተለይተዉ 10ሩ ህፃናት ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል ።

ለ15 ህፃናት የሊስትሮ ቁሳቁስ በመግዛት ወደስራ ሲገቡ 12ቱ ህፃናት እዛዉ ማረፊያ ተሰጥቷቸው እየሰሩ እንደሚኖሩ አንስተዋል፡፡ የተቀሩት 10 ህፃናት ትምህርታቸዉን እንዲማሩ መደረጉን ወይዘሮ ትግስት ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
11👍4
የኢትዮጵያ ብር በሁለት ወራት ዉስጥ በዶላር ላይ ከ 11 በመቶ በላይ ተዳከመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የውጪ ምንዛሪ ጨረታ፣ የኢትዮጵያ ብር ከአሜሪካን ዶላር ጋር ያለው የምንዛሪ ተመን በከፍተኛ ደረጃ መዳከሙ ታውቋል። ይህ ለውጥ በተለይ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የገበያውን መረጋጋት ለመደገፍ በተዘጋጀው የጨረታ መድረክ ላይ የሚታይ ትልቅ ጭማሪ ነው።

ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 11ኛዉ ዙር የውጪ ምንዛሪ ጨረታ፣ ለአንድ የአሜሪካን ዶላር አማካይ የምንዛሪ ተመን ብር 154.3993 ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህ ዙር 17 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማግኘታቸውን ካፒታል ተመልክቷል።

ከአንድ ወር በፊት፣ ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 10ኛዉ ዙር ጨረታ የአንድ ዶላር አማካይ ተመን 148.1007 ብር ነበር። ይህ ማለት ብሩ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአማካይ 4.25% በዶላር ላይ መዳከምን አሳይቷል።

​ከሁለት ወራት በፊት በ9ኛው ዙር ጨረታ የተመዘገበው አማካይ ተመን 138.2 ብር እንደነበር ይታወሳል። ከዚህ ተመን ጋር ሲነፃፀር፣ የዶላር ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር በሁለት ወራት ውስጥ የ11.72% የምንዛሪ ተመን ጭማሪ ታይቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ በጨረታ ማቅረቡን የገበያውን መረጋጋት ለመደገፍ ያለመ ቢሆንም፣ የብር ተመን ፈጣን መዳከም ግን የገንዘብ ገበያው ምን ያህል ፈጣን ለውጥ እያስተናገደ እንደሆነ የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።

Via ካፒታል
#ዳጉ_ጆርናል
👎3813🤔6😭5👍2🔥1💔1
ማዱሮ ለቬንዙዌላ የቀረበዉን 'የባሪያ ሰላም' ስምምነት ነዉ ሲሉ ውድቅ አደረጉ

የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ እርምጃን ተከትሎ ውጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በካራካስ በተገኙበት በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለህዝባቸው የሰላም ጥሪ ደጋግመው ቃል ገብተዋል።ሰልፉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከብሄራዊ ደህንነት ቡድናቸው ጋር በዋይት ሀውስ ተገናኝተው በቬንዙዌላ ላይ ስለሚደረጉ "ቀጣይ እርምጃዎች" ሲወያዩ የተደረገ ነዉ ሲሉ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ማዱሮ ከሚራፍሎረስ ቤተ መንግስት በራፍ ላይ በመገኘት የቬንዙዌላ ባንዲራዎችን በማዉለብለብ ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሀገራችን ሰላም ትፈልጋለች ነገር ግን ሰላም "ከሉዓላዊነት፣ እኩልነት እና ነፃነት" ጋር ብቻ ነው ያለው።"የባሪያን ሰላም፣ የቅኝ ግዛት ሰላም አንፈልግም! ቅኝ ግዛት፣ በጭራሽ! ባርነት፣ በጭራሽ!" በማለት ተናግረዋል።

የትራምፕ አስተዳደር የፀረ አደንዛዥ እፅ ዝውውር ዘመቻ በተባለው በካሪቢያን አካባቢ ወታደራዊ መከማቸት በቬንዙዌላ ላይ ጫና እያሳደረ ይገኛል። ካራካስ እርምጃዎቹ የማዱሮን መንግስት ለመጣል ያለመ ነው ብላለች። አሜሪካ በአካባቢው 15,000 ወታደሮችን አከማችታለች እናም የአለምን ትልቁን የአውሮፕላን አጓጓዥ አሰማርታለች፣ በተጨማሪም በማዱሮ የሚመራ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ መሆኑን የገለፀውን ካርቴል ዴ ሎስ ሶልስን እንደ “አሸባሪ” ድርጅት ተሰይሟል።

ከሴፕቴምበር ወር ጀምሮ በካሪቢያን እና ፓስፊክ ውቅያኖስ የአደንዛዥ ዕፅ ጀልባዎች ላይ ቢያንስ 21 ጥቃቶችን አሜሪካ ፈጽማለች።የተሰበሰበው የአሜሪካ ሃይል ለአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ኦፕሬሽን ከሚያስፈልገው እጅግ የላቀ ነው ሲሉ ባለሙያዎች ሲናገሩ ካራካስ ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ነዳጅ ዘይትን ጨምሮ የቬንዙዌላ ግዙፍ የተፈጥሮ ሃብቶችን ለመቆጣጠር የስርዓት ለውጥ እየፈለገች ነው ብላለች ።

በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
15😁1
ትራምፕ በአሜሪካ ከሶማሊያ ሀገር የሚመጡ ሰዎችን ማየት እንደማይፈልጉ ተናገሩ

👉 ትራምፕ የሶማሊያ ስደተኞችን ቆሻሻ ማለታቸውን ኢልሃን ኦማር ተቃውማለች


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊያ ስደተኞችን በአሜሪካ ማየት እንደማይፈልጉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "ወደ መጡበት ይመለሱ" እና። "ሀገራቸው በምንም ምክንያት አይጠቅምም" ሲሉ ትራምፕ ተደምጠዋል። የካቢኔ ስብሰባ ላይ ትራምፕ እንደተናገሩት "እውነት ለመናገር ያህል በእኛ ሀገር ላያቸው አልፈልግም" ብለዋል።

ትራምፕ በጥላቻ ንግግራቸው “ቆሻሻን ወደ አገራችን ብንወስድ አሜሪካ በተሳሳተ መንገድ ትሄዳለች” ብለዋል። ይህንን አሳፋሪ አስተያየት ትራምፕ የሰጡት በሚኒሶታ ሰፊውን የሶማሊያ ማህበረሰብ የማባረር ዘመቻ ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ ነው።የግዛቱ ባለስልጣናት እቅዱን ከምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር የመጡ አሜሪካዊያን ዜጎችን ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊያጠፋ ይችላል ሲሉ አውግዘዋል።

መንትያ ከተሞች በመባል የሚታወቁት ሚኒያፖሊስ እና ሴንት ፖል በዓለም ላይ ከፍተኛው ከሶማሊያ ሀገር የሚመጡ ዜጎች በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩበት ነው። ለሰዓታት የዘለቀው የካቢኔ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ማክሰኞ እለት ትራምፕ በሰጡት አስተያየት “በእኛ ሀገር አልፈልጋቸውም። እውነት እላችኋለሁ “ በፖለቲካዊ መልኩ ትክክል ባልሆን እንኳን”  ምንም አይመስለኝም በአገራችን አልፈልጋቸውም ሲሉ ተደምጠዋል።

በመቀጠልም ኢልሀን ኦማርን ተችተዋል። የዲሞክራት ተወካይ እና የመጀመሪያዋ የሶማሊ-አሜሪካዊ በኮንግረሱ ከተመረጠችው ኢልሀን ኦማር ጋር ትራምፕ ደጋግመው ሲጋጩ ቆይተዋል። "ሁልጊዜ እመለከታታለሁ" ያሉት ትራምፕ ኢልሀን ኦማት "ሁሉንም ሰው ትጠላለች እናም እሷ ብቁ ያልሆነ ሰው ነች ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። ኢልሃን ኦማር በማህበራዊ ድህረ ገጿ ላይ በሰጠችው የአፀፋ ምላሽ "በእኔ ላይ ያለው ስሜት በጣም አሳፋሪ ነው" ብላለች። በጣም የሚፈልገውን እርዳታ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ስትል አክላለች።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
21🤬18👎8😁7😱2
በወልዲያ ከተማ መንግስት ያደረገውን የደሞዝ ጭማሪን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ አስራ ሁለት ልኳንዳ ቤቶች ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡ ተደረገ

በወልዲያ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ወደ ህጋዊ የንግድ መረብ በማምጣት ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጡ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የከተማው አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።የመምሪያው ኃላፊ አቶ አዲሱ ወንድሙ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በከተማው ያለ አግባብ ዋጋ በሚጨምሩ እና ያለ ንግድ ፍቃድ በሚሰሩ ነጋዴዎች ዙሪያ የክትትልና ቁጥጥር ተግባራት ተከናውኗል።

ለመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ መደረጉ ከተነገረ ወዲህ ነጋዴዎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ  ለነጋዴ አካላት የግንዛቤ መፍጠር ስራዎች መሰራታቸውን አቶ አዲሱ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል። ይህን ተከትሎ በምርቶች ዙሪያ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አለመታየቱን አስረድተዋል።ነገር ግን  በከተማዋ የሚገኙ አስራ ሁለት ሉካንዳ ቤቶች ከተለመደው ዋጋ በላይ በአንድ ኪሎ የበሬ ስጋ ላይ ከ1 መቶ እስከ 1 መቶ 50 ብር ድረስ ጭማሪ በማድረግ ለሽያጭ ሲያቀርቡ በመገኘታቸው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነው ያሉት ።

ነጋዴዎቹ ከ7መቶ እስከ 8 መቶ ብር ድረስ ይሸጥ የነበረን አንድ ኪሎ ስጋ  በ1 ሺህ ብር ዋጋ ለሽያጭ ሲያቀርቡ እንደነበር ተገልጿል።በዚህም የተነሳ ነጋዴዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን አቶ አዱሱ ተናግረው መንግስት ያደረገው የዋጋ ጭማሪ አላማውም ምን እንደሆነ በማስረዳት አሁን ላይ በአግባቡ እንዲነግዱ ተደርጓል ሲሉ ነግረውናል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
😁86👏1
ለኩላሊት እጥበት ህክምና አገልግሎት የጤና መድህን ሽፋን አይሰጥም ተባለ

    👉 በኢትዮጵያ 84 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና ተጠቃሚ ሆኗል


በተለያዩ አጋጣሚዎች  ለውጪ ሀገር ህክምና ፤በስራ ተቋማት ውስጥ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፤ሶስተኛ ወገን ሽፋን ያላቸው ፤ ለኩላሊት እጥበት ታካሚዎች እና ለውበት መጠበቂያ ለሚወጡ ህክምናዎች በጤና መድህን ሽፋን ማግኘት  እንደማይቻል የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት አስታውቋል ፡፡

የጤና እክል አጋጥሞት ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከም ለሚደረግ ታካሚ በጤና መድህን የተሰበሰበውን ገንዘብ አንድ ሰው ላይ ማዋል እንደሆነ እና ፍትሀዊ አገልግሎት አሰጣጥ  እንደማይሆን ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምጠው ጥላሁን ናቸው፡፡እንዲሁም ለኩላሊት ህመምተኞች ለሚደረግ የእጥበት አገልግሎት ላይም የጤና አገልግሎት የጤና መድህን ሽፋን መስጠት አስቸ ጋሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከእነዚህ ህክምናዎች ውጪ ግን ምንም አይነት የገንዘብ ገደብ ሳይደረግ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ 84 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የማህበረሰብ አቀፍ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት በ1ሺ195 ወረዳዎች ስር  ከ4ሺ347 ጤና ተቋማት ጋር  ውል በማሰር  የጤና ተቋማቱ ለማህበራዊ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች የዱቤ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡ በመጨረሻም ኦዲት ተደርጎ  ለጤና ተቋማቱ ክፍያው እንደሚፈፀምላቸው ገልፀዋል ፡፡በ2018 ዓ.ም ደግሞ የወረዳ ሽፋኑን አሳድጎ ለ1ሺ320 ወረዳ  የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ማቀዱን በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳምጠው ጥላሁን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
👎1513😢4💔1
1
የሱዳን ጦር በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት የሚገኝ ከተማን መልሶ ያዘ

የሱዳን ጦር በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ውስጥ የሚገኘውን ማብሱት ከተማን ከፓራሚሊተሪ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አር ኤስ ኤፍ) ጋር በትብብር ከሚሰሩ ሃይሎች ጋር ውጊያ ካደረገ በኋላ በድጋሚ በቁጥጥር ስር ማዋሉን እማኞች ተናግረዋል፡፡የሰራዊቱ ሃይሎች በአል-አባሲያ ታጋሊ አካባቢ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ማብስት ላይ ከሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ ኃይሎች ጋር ከተፋለሙ በኋላ ተቆጣጥረውታል ሲሉ እማኞች ለአናዶሉ ተናግረዋል።

የሱዳን ጦር አሁን ከአል-አባሲያ ታጋሊ በስተ ምዕራብ ያሉትን ሁሉንም ቦታዎች ተቆጣጥሯል።የሰራዊቱ አባላት ማብሱትን መቆጣጠሩን የሚገልጹ ቪዲዮዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አውጥተዋል።በሪፖርቱ ላይ ከሠራዊቱ የተሰጠ አስተያየት የለም።አል-አባሲያ ታጋሊ በደቡብ ኮርዶፋን ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ክፍሎች መካከል የሚያገናኝ በመሆኑ ልዩ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን በአካባቢው ወታደሮች እና ሲቪሎች እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ቁልፍ መንገዶች ላይ ለሠራዊቱ ቁጥጥር ይሰጣል ።

እሁድ እለት የሱዳን ጦር ከአርኤስኤፍ ጋር በተፈጠረ ግጭት ከአል-አባሲያ ታጋሊ በስተ ምዕራብ በርካታ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል።አርኤስኤፍ አሁን ከሱዳን 18 ግዛቶች ውስጥ አምስቱን የዳርፉር ግዛቶችን የሚቆጣጠር ሲሆን ጦሩ ካርቱምን ጨምሮ ቀሪዎቹን 13 ግዛቶች ይዟል።እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2023 በሱዳን ጦር ኃይል እና በአርኤስኤፍ መካከል የተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 40 ሺ ሰዎችን ገድሎ 12 ሚሊዮን ያህሉን ማፈናቀሉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታዉቋል።

በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
9👍3👎3
እነ ጆን ዳንኤል ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) በእስራት እንዲቀጡ ወስኖ  የታሰሩት በቂ ስለሆነ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ እና ይዲድያ ነጻነት ላይ በነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሰዓት ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ መቐለ ከተማ ለመጓዝ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ ቢሆንም የአየር ሁኔታ ለበረራ አዳጋች በመሆኑ በረራው ቢደረግ የሚያደርሰውን ከባድ አደጋ ለመከላከል ጉዞው ተሰርዞ መንገደኞች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ሲነገራቸው በረራው በግድ መደረግ አለበት አንወርድም በማለት ቀሪ ተሳፋሪዎችም እንዳይወርዱ በመክልከል አሳድመዋል በሚል በዝርዝር ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ 1ኛ ተከሳሽ ጆን ዳንኤል ላይ በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስተቱን ቲክቶክ በተባለ ማህበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርጾ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።

ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የህግ አንቀፅ ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን ችሎቱ በዛሬው ዕለት የዐቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃ እና የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ተከሶሾቹ የተከሱበት የህግ አንቀፅ ቀላል እስራትን የሚያስከትል በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ በአንድ አመት ከአራት ወር፤ 2ኛ፣ 3ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በስምንት ወር እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ በ10 ወር እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

በመሆኑም ተከሳሾቹ በእስር ላይ የቆዩበት ጊዜ ተሰልቶ ተከሳሾቹ እንዲፈቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።

Via FMC
#ዳጉ_ጆርናል
👍5225😁13👎2
በደቡብ ኦሞ ዞን በኢንቨስትመንት ስም መሬት ተረክበዉ ከአንድ ዓመት በላይ ሳያለሙ አጥረዉ ያስቀመጡ ባለሀብቶች እንዳሉ ተነገረ

በደቡብ ኦሞ ዞን በኢንቨስትመንት ስም የተላለፈ ከ13 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ወደ መሬት ባንክ ገቢ ሊደረግ መሆኑን የዞኑ የመሬት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ሳሙኤል ጃክሰን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ሰሞኑን የዞኑ ኢንቨስትመንት አስፈጻሚ ኮሚቴ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ የአልሚ ባለሀብቶችን እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ በጎበኘበት ወቅት የተረከቡትን መሬት በአግባቡ በማልማት ምርታቸውን ኤክስፖርት በማድረግ የውጪ ምንዛሪ እያስገኙ ያሉ ባለሀብቶች መኖራቸውን መመልከቱን የዞኑ ኢንቨስትመንት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ቀርማ ገልፀዋል ።

በተቃራኒው በኢንቨስትመንት ስም መሬት ተረክበው ከአንድ ዓመት በላይ ሳያለሙ አጥረው ያስቀመጡ ባለሀብቶች መኖራቸዉን ኢንጂነር ሳሙኤል ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል ።በመሆኑም በአዋጁ መሠረት ወደ 13 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ ይደረጋል ብለዋል ። አንዳንድ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ስም መሬት ከተረከቡ በኃላ ማስያዣ በማድረግ ከልማት ባንክ ገንዘብ ተበድረው ወደ ሌላ ስራ ይሰማራሉ ተብሏል ።

ከዚህ ባለፈም አንዳንድ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍ ባለመደረጉ እንዲሁም በፀጥታና መሰል ችግሮች ምክንያት ማልማት በሚገባቸው ልክ እንዳያለሙ መገደባቸው የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ ተሰማርተዉ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ያሉ ባለሀብቶች ጎን መንግስት እንደሚቆምና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ ወርቅነህ ተናግረዋል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
10👎2