ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
43.8K subscribers
32.4K photos
276 videos
21 files
827 links
The best fiction is far more true than any journalism

📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ

👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56



👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Download Telegram
በስልጤ ዞን በተነሳ የእሳት አደጋ 3 ህፃናት ህይወታቸው  አለፈ

     👉 ህፃናቶቹ የታላቅ እና ታናሽ ልጆች ናቸው

በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ በሰሶ ቀበሌ በቀጠና ሁለት ልዩ ስሙ አበልቾ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በትላንትናው እለት 10:30  የእሳት አደጋ ደርሷል።

የሚቶ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ሀላፊ እና  ህዝብ ግንኙነት ተወካይ ረዳት ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ህፃናቶቹ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ እየተጫወቱ በነበረበት ሰዓት በቦታው የነበረ ገለባ በእሳት በመያያዙ በውስጡ የነበሩ የ6 ዓመት ሁለት ወንድ እና ሴት መንታ ልጆች እና የ2 ዓመት ሴት ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ህይወታቸው ያለፉት ህፃናቶች የታናሽ እና የታላቅ እህትማማች ልጆች ሲሆኑ በአያታቸው መኖሪያ ቤት ይኖራሉ።የሁለቱ መንታ ልጆች እናት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን የ2 ዓመቱ ህፃን እናት ደግሞ ለስራ ከሀገር ውጭ በመኖሯ ህፃናቶቹ በአያታቸው ቤት እንደሚኖሩ ነው  ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ  የገለፁት።

የአደጋው መንስኤ ለጊዜው ምክንያቱ ባለመታወቁ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን የህፃናቶቹ አስከሬን ለምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተልኳል።ወቅቱ በጋ እና ነፋሻማ  በመሆኑ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ  አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
💔4414😭8🔥1
ፑቲን እና ትራምፕ ልዑክ በሞስኮ  በዩክሬን ጉዳይ ውይይት ሊያደርጉ ነው

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዛሬው የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍን በሞስኮ ያገናኛሉ። ዋይት ሀውስ የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ከስምምነት ላይ ለመድረስ "በጣም ብሩህ ተስፋ" እንዳለው አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማች ያሬድ ኩሽነር በዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች የውጭ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ በመሆኑ በዉይይቱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ መድረክ የተዘጋጀው በፍሎሪዳ ለሁለት ቀናት የዩክሬይን እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ዊትኮፍ እና ኩሽነርን ጨምሮ በአሜሪካ የሚደገፈውን የሰላም ስምምነት እቅድ ለሩሲያ ይጠቅማል ተብሎ የተነገረውን የማጣራት ድርድር ተከትሎ የመጣ ነው። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ውይይቱን “ገንቢ” ሲሉ ገልጸውት “አሁንም ሊሰሩባቸው የሚገቡ አንዳንድ ከባድ ጉዳዮች አሉ” ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።

የዊትኮፍ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ በዛሬው እለት ይካሄዳል ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል። ሰኞ እለት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ከተገናኙ በኋላ ዘሌንስኪ እንደተናገሩት የኪየቭ የሰላም ድርድር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች የዩክሬንን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ እና ጠንካራ የፀጥታ ዋስትናዎችን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
24🕊2
ኢትዮጵያ ባለፋት አራት ወራት ለሽያጭ ካቀረበችው የስጋ ምርት ከ37 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ባለፋት አራት ወራት ለሽያጭ ካቀረበችው የተለያዪ የስጋ ምርቶች ከእቅድ በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊ ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ  ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬድዮ  እንደተናገሩት በዚህ ጊዜ ውስጥ 6 ሺህ 7መቶ ቶን የስጋ ምርቶችን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ።

ለውጪ ገበያ ከቀረቡት ምርቶች 35 ነጥብ 29  ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ያስረዱት ዶክተር ሳህሉ  ከእቅድ በላይ 37 ነጥብ 69 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት እንደተቻለ አስረድተዋል ።ከስጋ ዘርፋ በተገኘው ገቢ ከእቅድ በላይ 107  በመቶ አፈፃፀምን ማስመዝገብ እንደተቻለ የተገለፀ ሲሆን የበግ፣የፍየል ፣የዳልጋ ከብትን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል።

ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ  ዋነኛ  እና ነባር የስጋ ንግድ መዳረሻ ሀገራት መሆናቸው ተገልጿል።በዘርፋ ለተሰማሩ የማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በተገቢው መልኩ የእርድ እንስሳቶች  እንዲቀርብላቸው በመደረጉ ባለፋት አራት ወራት ከእቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ሲል ኢንስቲትዮቱ አስታውቋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
👎2214👍3🙏1
የኤል ቻፖ ልጅ በአሜሪካ የአደንዛዥ ዕፅ ክስ ጥፋተኛ ነኝ ሲል ተናገረ

የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ንጉስ ልጅ የሆነው ጆአኩዊን "ኤል ቻፖ" ጉዝማን ልጅ ጆአኩዊን ጉዝማን ሎፔዝ በቺካጎ ፍርድ ቤት በሁለት የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች እና የተደራጁ የወንጀል ክሶችን በሜክሲኮ ታዋቂው ሲናሎአ ካርቴል ውስጥ በፈጸመው ተግባር ጥፋተኛ ነኝ ሲል አምኗል።ጉዝማን ሎፔዝ ጥፋተኛ ነኝ ሲል በቁጭት ተናግሯል። በችሎቱ መጀመሪያ ላይ ለሰሜን ኢሊኖይ አውራጃ የዩናይትድ ስቴትስ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ ሻሮን ኮልማን ፊት ቀርቦ ምን እንደሰራ ተጠይቋል፡፡

ጉዝማን ሎፔዝ “የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ነዉ” ሲል መልሷል።በጉዝማን ሎፔዝ ላይ የጥፋተኝነት ክስ በመመስረቱ ከአሜሪካ አቃቤ ህግ ጋር በመተባበር የፈፀመውን ወንጀል የሚወክል የ80 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ በመክፈል ከህይወት ዘመን እስራት እንደሚያመልጥ ይጠበቃል ሲል ዘገባዎች አመላክተዋል።ይህም ሆኖ ግን ቢያንስ የ10 አመት እስራት እንደሚጠብቀው የፌደራል መንግስት ጠበቃ የሆኑት አንድሪው ኤርስስኪን ተናግረዋል።ጉዝማን ሎፔዝ በዳኛ ቅጣት የሚተላለፍ ሲሆን ይግባኝ ለማለት ግን እድል አይኖረውም ሲል ዘገባዎች ያስረዳሉ።

የጉዝማን ሎፔዝ ተከላካይ ጠበቃ ጄፍሪ ሊችማን ከችሎቱ በኋላ “መንግስት እስካሁን ከጆአኩዊን ጋር በጣም ፍትሃዊ ነው” ብለዋል።ሊችማን “የሜክሲኮ መንግሥት ጣልቃ አለመግባቱን አደንቃለሁ” ብለዋል።የቺካጎ ትሪቡን ዘገባ እንደሚያመለክተው በ35 ገፁ የይግባኝ ስምምነት ላይ ጉዝማን ሎፔዝና ወንድሞቹ ለባለሥልጣናቱ ጉቦ በመስጠት እና የጦር መሳሪያ እና ሌሎች መሳሪያዎችን በማሰማራት የህግ አስከባሪዎችን፣ ተቀናቃኝ አዘዋዋሪዎችን እና ሌላው ቀርቶ የራሳቸው ድርጅት አባላትን ያነጣጠረ ጥቃት እንዲፈጽሙ በማድረግ የአደንዛዣ እጽ ዝዉዉር ቡድን እንቅስቃሴ እንዳሳደጉ አምነዋል።

በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
18😁1
ባለፉት ሶስት ወራት አክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 453 ዋና ዋና ቀዶ ህክምና መስጠቱን አስታወቀ

በአክሱም ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላለፉት ሶስት ወራት የዋና ቀዶ  ህክምና አገልግሎት ያገኙ 453 ታካሚዎች መሆናቸውን ሆስፒታሉ አስታውቋል። እንዲሁም 42 ሺህ 831 ጠቅላላ በተመላላሽ የህክምና አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች በሆስፒታሉ አገልግሎት እንዳገኙ የአክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ፀጋዬ ተክለሀይማኖት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሆስፒታሉ 35ሺህ ታካሚዎች የላብራቶሪ አገልግሎት ማግኘታቸውን እንዲሁም ጠቅላላ ተኝቶ ማከሚያ ውስጥ ደግሞ 1ሺህ 544 ታካሚዎች አገልግሎት እንዳገኙ ገልጸዋል፡፡

ሆስፒታሉ በበጀት አመቱ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለማስገባት ማቀዱንም የአክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ፀጋዬ ተክለሀይማኖት ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ተናግረዋል።

በሰመሀር አለባቸው
#ዳጉ_ጆርናል
22👎1
1
የዩናይትድ ስቴትስ የጅምላ ግድያ በ2025 ዓመት ባለፉት 20 ዓመታት ከተመዘገበዉ ዝቅተኛ ሆነ

በዩናይትድ ስቴትስ በ 2025 ዓመት ከሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛው የጅምላ ግድያ ተመዝግቧል ሲል እንደዚህ ያሉ ክስተቶችን የሚከታተል የመረጃ ቋት ይፋ አድርጓል።በቅርቡ በስቶክተን ካሊፎርኒያ በተደረገ የቤተሰብ ስብሰባ ላይ አራት ሰዎችን የገደለው ተኩስ በዚህ አመት 17ኛው የጅምላ ግድያ መሆኑን አሶሺየትድ ፕሬስ ከዩኤስኤ ቱዴይ እና ከኖርዝ ኢስት ዩኒቨርሲቲ ጎን ለጎን የመረጃ ቋቱን የሚይዘው  አካል ማክሰኞ ዘግቧል።

ይህ አሃዝ ግን ገና የታህሳስ ወር ባለመጠናቀቁ ሊጨምር ቢችልም፣ ከ2019 ከነበረዉ 59 በመቶ የሚጠጋ ቅናሽ አለዉ፡፡ በ2019 ዓመት ሪከርድ የሆነው 41 የጅምላ ግድያ ተመዝግቧል። የመረጃ ቋቱ የጅምላ ግድያዎችን ለመከታተል የፖሊስ እና የኤፍቢአይ ዘገባዎችን፣ የሚዲያ ዘገባዎችን እና የፍርድ ቤት መዝገቦችን ይጠቀማል፣ እነዚህ ክስተቶች መደበኛ ወንጀለኛን ሳይጨምር አራት እና ከዚያ በላይ ሰዎች ሆን ተብሎ በ24 ሰአት ውስጥ የተገደሉበት ክስተትን የሚያካትት ነው።

የመረጃ ቋቱን የሚያስተዳድረው የኖርዝ ኢትስ ዩኒቨርሲቲ የወንጀል ተመራማሪ የሆኑት ጀምስ አላን ፎክስ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት የ2025 የተመዘገበው ውጤት ከ2024 ጋር ሲነፃፀር በ24 በመቶ ቀንሷል፣ በተጨማሪም ከ2023 ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።የቁጥሩ ማሽቆልቆል የስታቲስቲክስ ባለሙያዎች "ወደ አማካይ መመለሻ" ብለው የሚጠሩት ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል፣ ይህም ባለፉት ዓመታት ያልተለመደው ጭማሪ ወደ አማካይ የወንጀል ደረጃዎች መመለስን ያሳያል።እ.ኤ.አ. በ2025 በአሜሪካ ከተፈጸሙት የጅምላ ግድያዎች 82 በመቶ ያህሉ ከጦር መሳሪያ ጋር የተያያዙ ናቸው።የመረጃ ቋቱ በ2006 ከተከፈተ ጀምሮ 3,234 ሰዎች በጅምላ ሲገደሉ 81 በመቶ ያህሉ ተጎጂዎች ተተኩሶባቸዋል።

በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
10
የሰላሌ ዩኒቨርስቲ ከ 3ሺህ በላይ ለሚሆኑ  አቅመ ደካማ የሕብረተሠብ ክፍሎች የነፃ የሕግ አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ

የሰላሌ ዩኒቨርስቲ የሕግ አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ሶስት ሺ አራት መቶ ዘጠና ስድስት  አቅመ ደካማ የማህበረሰብ አካላት የተለያዩ የሕግ አገልግሎት ሰጥቷል።

የዩኒቨርስቲ የሕግ አገልግሎት ዲን አቶ አቤል ከተማ እንደገለፁት የነፃ የሕግ አገልግሎቱ የተሰጠው አቅመ ዳካማ ለሆኑ ፣ በእድሜ ለገፉ፣ ጥቃት ለደረሠባቸው ሴቶች ና ሕፃናት፣በከፍተኛ ሕመም ለሚገኙ እና በማረሚያ ቤት ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን ለሚከታተሉ ታራሚዎች የነፃ የሕግ አገልግሎት ነው ብለዋል።

በዚህም ለሁለት ሺህ ሠባት መቶ ሀምሳ ስድስት ወንዶች እንዲሁም ለሰባት መቶ አርባ ሴቶች አገልግሎቱ ተሰጥቷል። በነፃ አጉልግሎቱ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ከወጪ ማዳን የተቻለ ሲሆን የሰላሌ ዪኒቨርስቲ በስሩ የሚተዳደሩ አራት ቋሚ የሕግ አገልግሎት መስጫና  እና አንድ ተንቀሳቃሽ  የሕግ ማዕከል አቋቁሞ በመንቀሣቀስ በተለየ መልኩ በሕፃናት እና ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እንደዚሁም ያለ እድሜ ጋብቻ፣የቤተሰብ ግጭቶች እና ትንኮሳዎች ላይ  ሰፊ የሕግ መሰረት ያደረገ አገልግሎት መስጠቱን አቶ አቤል ከተማ ጨምረው ገልፀዋል::

ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ ከጋብቻ ውጭ የተወለዱ እና የሚጣሉ ሕፃናት ማቆያ ለመገንባት ከፍትህ አካላት ጋር የጋራ ስምምነት የተደረሠ ሲሆን ባለፈው አመት ሶስት ሕፃናት ተጥለው የተገኙትን የሠላሌ ዩኒቨርስቲ ተረክቦ በአበበች ጐበና ካምፖሱ ባለው ጊዚያዊ ማቆያ በማቆየት በሕጋዊ መንገድ ለጉዲፈቻ ተሰጥተዋል።

በዩኒቨርስቲ ውስጥ የሴት ተማሪዎች ላይ የሚደርሰውን ትንኮሳ እና ጥቃት ለመከላከልም የተቋቋመ ኮሚቴ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የተደረገው ስምምነት ከፍተኛ ውጤት እንደሚያመጣም ተመላክቷል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
13👏3🤔1👌1
ሚስቱንና ጎረቤቱን ገድሎ የተሰወረውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ህዳር 04 እና 05 ቀን 2018 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው 23 ቀበሌ መዝናናኛ ክበብ አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሽ እሱያውቃል ቢያዝን ከባለቤቱ ከወ/ሮ ሐመልማል አለምነው ጋር በትዳር ተጣምረው መኖር ከጀመሩ አራት ወራትን አስቆጥረዋል፡፡

ተጠርጣሪው ባለቤቱን ከሌላ ወንድ ጋር ስልክ ትደዋወያለሽ ከሌላ ሰው ፍቅር ጀምረሻል በሚል አጉል ጥርጣሬ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 4 ሠዓት አንገቷን አንቆ በመግደል ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በር ዘግቶባት ከአካባቢው ይሰወራል፡፡

በተጨማሪም ከአንድ ቀን በኋላ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ወደ መኖሪያ ግቢው ተመልሶ በመምጣት የ2 ልጆች አባት የሆነውን ወርቁ በቀለን ከምሽቱ 1ሰዓት በመኖሪያ ቤት ውስጥ በስምንት ጥይት ተኩሶ በመግደል ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ከአካባቢው ይሰወራል፡፡

የአቶ ወርቁ በቀለ በጥይት ተመተው መሞት መረጃ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ክትትል ክፍል የወንጀል ስፍራው ላይ በመገኘት እና መረጃ በማሰባሰብ ላይ ባሉበት ሁኔታ የገዳይ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሰው መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሙከራ ሲደረግ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የሐመልማል አለምነው አስከሬንም ሊገኝ ችሏል፡፡

ወንጀል ፈፃሚውን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ ከተማ ከተደበቀበት አልጋ ቤት ውስጥ የግድያ ወንጀሉን ከፈፀመበት ኢኮልፒ ሽጉጥ እና ከ23 ጥይቶች ጋር ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ሊያውለውም ችሏል፡፡

ግለሰቡ የወንጀል አፈፃጸሙን አስመልክቶ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም መርቶ ማሳየቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

ምንጭ:- አ.አ ፖሊስ

#ዳጉ_ጆርናል
💔2515👏3