የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማህበር ተመሰረተ
የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማህበር መመስረቱን በተመለከተ በዛሬው ዕለት መስራቾች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
የማህበሩ አባል ለመሆን በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራ እድሜው ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ እና ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ድረገጽ ሊኖረው እንደሚገባ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ማህበሩ ከስምንት ወራት በፊት ጀምሮ የታሰበበት መሆኑን እና በኤፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ኤጀንሲ ከህዳር 12 ቀን ጀምሮ እውቅና ማግኘቱ ተጠቁሟል። ማህበሩ ዓለማው ይዘት ፈጣሪዎችን በማንኛውም ድረገጻቸው ላይ ለሚገጥሟቸው ችግሮች እንዲሁም በቀረጻ ወቅት ፍቃድ ለማግኘት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ ከ3 ሚሊዮን በላይ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች መኖራቸው የተጠቆመ ሲሆን የይዘት ፈጣሪዎችን መብት በጠበቀ መልኩ አባላቱን ወክሎ የሚከራከር ማህበር መሆኑ ተነግሯል።
ራሳቸው እየጠቀሙ ማህበረሰቡን በማይነካ እና አግባብነት ባለው መልኩ ለተጠቃሚው እንዲደርስ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል።
ማንኛውም መስፈርቱን ማሟላት የሚችል ይዘት ፈጣሪ የማህበሩ አባል መሆን እንደሚችል እና አላስፈላጊ የሆኑ ከኢትዮጵያ ባህል ውጪ ይዘቶችን የሚሰሩ ማስቆም እንዲሁም ስልጠና መስጠት በተመለከተ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እቅድ እንዳላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪ ብሩክ ጫላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግሯል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

❤20😁7👍2👎1🤩1
አሜሪካ የቬንዙዌላውን የዕፅ ዝውውር ለመግታት በቅርቡ የምድር ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ትራምፕ ተናገሩ
ዩናይትድ ስቴትስ የቬንዙዌላን የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር “በየብስ” ላይ በማነጣጠር እርምጃ መውሰድ ትጀምራለች ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።ከካራካስ ጋር በተፈጠረው ውጥረት ዋሽንግተን የቬንዙዌላውን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን ከስልጣን ለማውረድ አቅዳለች በሚል ክስ እየቀረበባት ይገኛል።
ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች የአውሮፕላን ተሸካሚ ቡድንን ፣ድብቅ ተዋጊ ጄቶችን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ጨምሮ ወደ ላቲን አሜሪካ ክልል ሲያሰማሩ የቆዩ ሲሆን ዋሽንግተን የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በሚባሉት ጀልባዎች ላይ ያደረሰችው ጥቃት በዓለም አቀፍ ውሃ ክልል ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል።
በእውነት የአሜሪካ አየር ኃይል የጀርባ አጥንት ነው፤ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የቬንዙዌላ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችን ለመከላከል እየሰሩ ነው ሲሉ ትራምፕ ለአሜሪካ ኃይሎች በምስጋና በዓል ቀን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ተናግረዋል ። "በእርግጥ ከአሁን በኋላ በባህር የሚገቡ በጣም ብዙ አይደሉም" ብለዋል። ትራምፕ። "ሰዎች አደንዣዥ እፅን በባህር ማድረስ አይፈልጉም፤ እናም በመሬት ላይ ያለውን ማቆም እንጀምራለን" ሲሉ አክለዋል።
የመሬቱ ጥታት ቀላል ነው፣ በጣም በቅርቡ ይጀምራል። ወደ ሀገራችን መርዝ መላክ ይብቃ ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት አክለውም 85 በመቶው በባህር ላይ የሚደረገውን የአደንዣዥ እፅ ዝውውር አስቁመናል። የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ከመስከረም ወር ጀምሮ በካሪቢያን ባህር እና በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በሚገኙ ጀልቦች ላይ ከ20 በላይ ጥቃቶችን ሲፈፅም ቢያንስ 83 ሰዎችን ገድሏል። የላቲን አሜሪካ የህግ ባለሙያዎች እና መንግስታት የጥቃቱን ዘመቻ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጪ የተፈፀመ ግድያ ሲሉ ፈርጀውታል።
በስምዖን ደረጄ

❤11👎3👍1🔥1
ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት ሲያጭበረብሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ
በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ስም ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት እና በማሰራጨት ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሶስት ግለሰቦችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥናትና ክትትል በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል፡፡
ግለሰቦቹ የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ሀሰተኛ ክብ ማህተሞች፣ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የቀበሌ መታወቂያዎች፣ የልደት ሰርተፍከቶኬቶች፣ የመሬት ይዞታ ካርታ፣ የቀረጥ ነጻ ደረሰኞች፣ የጋብቻ የምስክር ወረቀቶች፣ መንጃ ፍቃዶችን እና ሌሎች ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ለሀሰተኛ ሰነዶች ማዘጋጃነት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የእጅ ስልኮች እና ኮምፕውተሮች እንዲሁም የተዘጋጁ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶች በኤግዚቢትነት መያዛቸው ተገልጿል፡፡ሕብረተሰቡም መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲፈፀሙ ከፀጥታ ተቋማት ጎን ሆኖ መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

❤6😱3👍2🤔1
የእስራኤል ጦር በሶርያ በፈፀመው ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉ
እስራኤል በደማስቆ ገጠራማ አካባቢ በሶሪያ ግዛት ላይ በጀመረችው የጥቃት ዘመቻ ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 13 ሰዎች ሲገደሉ 25 ቆስለዋል ሲል የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። በጦር ዘመቻው ግጭት ወቅት በርካታ የእስራኤል ወታደሮች ቆስለዋል። የሶሪያ መንግስት ሚዲያ አርብ ዕለት እንደዘገበው እስራኤል ረፋድ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ከተገደሉት መካከል ሁለት ህጻናት ይገኙበታል።
በደርዘን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ከቤቴ ጂን ከተማ ወደ አቅራቢያ እና አስተማማኝ አካባቢዎች እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል።የሶሪያ አረብ የዜና አገልግሎት (ሳና) እንደዘገበው የሁለት ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ የአምስት ሶሪያውያን አስከሬን ወደ ጎላን ብሄራዊ ሆስፒታል ተወስዷል። የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላኖችም ወይም ድሮኖች በአካባቢው መብረር መቀጠላቸውን ዘገባው አክሎ ገልጿል።
የሶሪያ ሲቪል መከላከያ ቡድን አባላት የቆሰሉትን ለመታደግ ወደ ቤት ጂን መግባት አልቻሉም የተባለ ሲሆን የእስራኤል ጦር በማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ ማነጣጠሩን ቀጥሏል። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2024 ፕሬዚደንት በሽር አል አሳድ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ እስራኤል ደቡባዊ ሶሪያ ላይ ወረራዋን ቀጥላለች። የእስራኤል ወታደራዊ ወረራ የበለጠ ድፍረት የተሞላበት ፣ ተደጋጋሚ እና ብጥብጥ የሚያስከትል ሆኗል ።

🤬20❤11😭9
በተለያዩ የአመራር እርከን ላይ ተቀምጠው ሲሰሩ የነበሩ 22 ግለሠቦች በሙስና ወንጀል ተከሰው በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጡ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተለያዩ የአመራር እርከን ላይ ተቀምጠው የሴክተር መስርያ ቤቶች ሲመሩ የነበሩ 22 ግለሠቦች በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የተወሠነባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታዉቋል።የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ታደሠ አመኑ እንደለገፁት በወረጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጐሐ ከተማ ውስጥ በአመራርነት የተለያዩ የሴክተር መስርያ ቤቶች እየመሩ እያለ የጨረታ ማስታወቂያ እና ስምምነት ሳያደርጉ የፋይናስ አሠራር ባልተከተለ መንገድ ለፀጥታ አካላት ቀለብ የሚውል ከመንግስት ካዝና ገንዘብ ወጭ በማድረግ ለግል ጥቅማቸውና ለሌሎች ሰዎች ማዋላቸው በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡
ተከሣሾች ከ2014 ዓም ጀምሮ ባላቸው የአመራር እርከንነት አምስት መቶ ስልሣ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ አምስት ብር የፋይናስ መመርያን ባልተከተለ እና በተፃረረ መንገድ በማውጣት አቶ ፍቅሬ አሰፋ ለተባለ የሆቴል ባለቤት እንዲከፈል በማድረግ አላግባብ ከመንግስት ካዝና የወጣውን ብር ለግል ጥቅማቸው አዉለዋል።እነዚሕ የአመራር አካላት በሕጋዊ መንገድ ለፀጥታ አካላት የተመደበው ብር ስራ ላይ ካዋሉ በኃላ ያደረ እዳ በማለት ገንዘቡን ከመንግስት ካዝና በማውጣት ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ያደረጉት ሙከራ በኦዲት እና በተለያዩ ማስረጃዎች ምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ከአንድ እስከ አስራ ስምንት ያሉ ተከሳሾች የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ በተለያየ የስልጣን እርከን ላይ ሆነው የተለያየ የሴክተር መስርያ ቤት ሲመሩ እንደነበረ ገልፀዋል።
ተከሣሾች ከሆቴል ቤቱ ግለሠብ ጋር ባላቸው የጥቅም ግንኙነት የተነሣ የመንግስት ገንዘብ እንዲመዘበር በማድረጋቸው በፖሊስ እና በአቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገባቸው ተጣርቶ በአቃቤ ሕግ በኩል የሙስና ወንጀል ለመከላከል የወጣውን አዋጅ 881/2007 በመጥቀስ ክስ ተመስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ወንጀሎች ችሎት ሰሞኑን በዋለው ችሎት ከስድስት ወር ቀላል እስራት አንስቶ እስከ አራት አመት ከሠባት ወር እስራት እና ከሁለት ሺህ እስከ ሶስት ሺሕ ብር መቀጮ እንዲቀጡ የተወሠነባቸው መሆኑን ኮማንደር ታደሠ አመኑ ጨምረው ገልፀዋል።
በሰመሀር አለባቸው

❤12👏5👎1😁1🙏1
ትራምፕ ከሶስተኛው ዓለም ሀገራት የሚመጡ ፍልሰተኞችን ለማስቆም ማቀዳቸውን ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ ሁለት የብሔራዊ ጥበቃ አባላት ላይ የተኩስ እሩምታ በአንድ የአፍጋኒስታን ዜጋ እንደተከፈተባቸው በተሰማ ማግስት "ከሦስተኛው ዓለም ሀገራት በሙሉ" ወደ አሜሪካ የሚደረግ ፍልሰትን ለማቆም ማቀዳቸውን ተናግረዋል ። የትራምፕ ይህው መግለጫ በዋሽንግተን ዲሲ የተኩስ እሩምታን ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከ19 “አሳሳቢ ሀገራት ካላቸው በሙሉ” ሁሉንም የአረንጓዴ ካርድ ማመልከቻዎች እንደገና እንዲመረምር አዘዋል።
ወደ አሜሪካ በሚገቡት ስደተኞች ላይ ተከታታይ እገዳዎች በትራምፕ አስተዳደር ቀጥሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ስርዓት ሙሉ በሙሉ እንዲያገግም እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የባይደን አስተዳደር ህገ-ወጥ ቅበላዎችን ለማቋረጥ ከሁሉም የሶስተኛ ዓለም አገራት ፍልሰትን በቋሚነት አስቆማለሁ” ሲሉ ትራምፕ የግል ንብረታቸው በሆነው ትሩዝ ማህበራዊ መድረክ ላይ ጽፈዋል ። ትራምፕ “ሦስተኛው ዓለም” የሚለውን ቃል የትኞቹን ሀገራት እንደሚወክሉ በግልጽ ባይናገሩም ሐረጉ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው በደቡባዊ ንቅፈ ክበብ ውስጥ ያሉ ታዳጊ ሀገራትን ነው።
ትራምፕ "ለዩናይትድ ስቴትስ የተጣራ ሀብት ያልሆኑትን ወይም ሀገራችንን የመውደድ አቅም የሌለውን ማንኛውንም ሰው እንደሚያስወግዱ" ተናግረዋል። አክለውም ሁሉም የፌደራል ጥቅማጥቅሞች እና ድጎማዎች "ዜጋ ላልሆኑ ሰዎች" መስጠት ያበቃል እናም "የአገር ውስጥ መረጋጋትን የሚጎዱ ስደተኞችን እናስወግዳለን ብለዋል። በህዝባዊ ተጠያቂነት፣ የደህንነት ስጋት ወይም ከምዕራቡ ስልጣኔ ጋር የማይጣጣም የውጭ አገር ዜጋን አንቀበልም" ሲሉ ተደምጠዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ከ19 ሀገራት ወደ አሜሪካ ለተሰደዱ ግለሰቦች የተሰጠ ግሪን ካርድ በድጋሚ እንደሚመረመር ማሳወቁ ይታወሳል። ከነዚህ ሀገራት መካከል አፍጋኒስታን፣ በርማ፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ሄይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ይገኙበታል።በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤6🤔6👎1😁1😭1
በሀሰተኛ የሞባይል ባንኪንግ ደረሰኝ የወርቅ ጌጣጌጥ ሊገዛ የሞከረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
ናታን ኃ/ማርያም የተባለ ግለሰብ የማጭበርበር ወንጀሉን የፈጸመው ህዳር 8 ቀን ከቀኑ 10፡00 ሠዓት አካባቢ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 መገናኛ ቤተልሔም ህንጻ ተብሎ ከሚጠራው የወርቅ እና የብር መሸጫ ሱቅ ውስጥ ነው።
ተጠርጣሪው ወደ ወርቅ እና ብር መሸጫ ሱቅ ውስጥ በመግባትና ትክክለኛ ሸማች በመምሰል የዋጋ ግምቱ 289,632 ብር የሚያወጣ የወርቅ የአንገት ሀብል ከመረጠ እና ዋጋ ከተነጋገረ በኋላ ሂሳቡን በሞባይል ባንኪንግ ለመክፈልም ይስማማል።
ግለሰቡ ወርቁን ከባለ ሱቁ ከተቀበለ በኋላ ብሩ ገብቶልሃል በማለት ሀሰተኛ ደረሰኝ አሳይቶ ሊሄድ ሲል የግል ተበዳይ መግባቱን ሳናረጋግጥ አትሄድም በማለታቸው ከአካባቢው ሮጦ ለመሰወር ሲሞክር በጸጥታ አካላት እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
ተጠርጣሪው ተይዞ በተደረገ ምርመራ የማስፋት ስራም ሀሰተኛ ሰነዱን አስቀድሞ በመስራትና ስልኩ ላይ ኢዲት አድርጎ ዋጋውን በማስገባት ለግል ተበዳዮች እንዳሳያቸው ፖሊስ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ በሞባይል ባንኪንግ ግብይት ሲፈጽም ገንዘብ ከተላከ በኋላ በትክክል ወደ አካውንቱ መግባቱን ማረጋገጥና የማጭበርበር ወንጀል ካጋጠመውም በአፋጣኝ ጥቆማ የመስጠት ባህሉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መልዕክቱን አስተላልፏል።
ምንጭ:- አአ ፖሊስ

😁16❤15👍2👌2
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር በጋራ እየተሰራ ነው
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የምዝገባ ስርዓት ለማቀላጠፍ እና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር ለማስተሳሰር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።ኤጀንሲው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በይበልጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽነት የተላበሰ ብልሹ አሰራርን የሚከላከል እንዲሁም ተደራሽ የማድረግ አላማ ይዞ እየሰራ መሆኑን ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ናቸው።
በዚህም እየለማ የሚገኘው ሲስተም በመጠናቅቅ ላይ ሲሆን ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) የምዝገባ ስርዓት ጋር ለማስተሳሰር እየተሰራ ነው። ሲስተሙንም ያለማው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንትሌጀንስ ኢንስቲትዩት፣የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እንዲሁም ብሔራዊ መታወቂያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ግምገማ አካሂደዋል።
የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ቴክኖሎጂው ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ በቴክኖሎጂ ውስጥ ቢካተቱ የተባሉ ሀሳቦች ተጋርተዋል።በኤጀንሲው የሚከናወኑ የኩነት ምዝገባዎች መሰረታዊ በመሆናቸው የልደት እና የሞት ኩነቶች ሲከሰቱ እና በኤጀንሲው በኩል ምዝገባ ሲከናወን ለማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ መረጃ የሚደርስበት አሰራር በቴክኖሎጅው እንዲካተት ተጠይቋል፡፡
በምህረት ታደሰ

❤9
በሆንግ ኮንግ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 128 ከፍ አለ
በሆንግ ኮንግ ታይፖ አውራጃ ውስጥ በሕዝብ መኖሪያ ቤቶች ላይ በደረሰዉ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ የ128 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ የ16 ሰዎች አስክሬን አሁንም በህንፃው ውስጥ እንደሚገኝ ተሰምቷል። ባለስልጣናት አክለው እንደተናገሩት 79 ሰዎች በአደጋው ቆስለዋል። እስካሁንም 89 አስከሬኖች የማን እንደሆኑ አልታወቁም ብለዋል።
ባለሥልጣናቱ እሳቱ ከምድር ቤት ተነስቶ ወደ ከፍተኛ ወለሎች መሸጋገሩን ተናግረዋል። የአደጋው መንስኤው እስካሁን በውል ባይታወቅም ምርመራው እየተካሄደ መሆኑንም አክለዋል። የእሳቱ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 500 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ደርሷል።ፖሊስ ማስረጃ ማሰባሰብ ለመጀመር ዛሬ ወደ ዋንግ ፉክ ፍርድ ቤት ህንጻዎች መግባት እንደሚጀምር እና በሚቀጥሉት ሶስት እና አራት ሳምንታት ውስጥ ምርመራ እንደሚካሄድ ባለስልጣናቱ ገልፀዋል ።
391 የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች እና 188 አምቡላንሶች ተሰማርተዋል። አደጋውን ለመከላከል ከ2,311 በላይ የእሳት አደጋ ተከላካዮች የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በ12 ሰዎች ላይ አደጋውን እየተቆጣጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል። አደጋውን በመቆጣጠር ሂደት ሄሊኮፕተሮች ጥቅም ላይ አልዋሉም ያሉት ባለስልጣናቱ የአየር ላይ የውሃ ጠብታዎች በህንፃዎች ውስጥ የሚነሱ የእሳት ቃጠሎዎችን ለማጥፋት ውጤታማ አይደሉም ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል ። ሰው አልባ አውሮፕላኖችም ጥቅም ላይ እንዳልዋሉ ተሰምቷል።

❤17💔12👏2😢1