✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
17.4K subscribers
226 photos
22 videos
51 files
446 links
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮╭━─━─━─
ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት @Zemaryan
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯╰━─━─━─
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ጥያቄ> creator ለማግኝት @kidanemiherat_bot
@yita21
@Binyam
https://youtu.be/Fz4JARE6-DI
Download Telegram
ስለ ዘፈን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል??

አብዛኛውን ጊዜ ለሰው እውነቱ ሲነገረው ከመቀበል ይልቅ በአካኪ ዘራፍ አግበስብሶ ማለፉ ልማዱ ነው። ስጋዊ ህይወትና ስጋዊ አስተሳስብ ስለሚያሸንፈው ማድመጥም ሆነ መቀበልም ይቀፈዋል። #ቅዱስ #ኤፍሬም #ሶሪያዊዉ የስጋዊ ህይወት ማሸነፍ ላቃታቸው ማለትም ስጋዊህ ህይወት ላሸነፋቸው እና መግደል ላቃታቸው  መፍትሔውን ሲናገር እንዲህ ይላል፦ የስጋዊው ህይወት ማሸነፍ ምትችሉት የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት በእናንተ ውስጥ በሙላት መኖር ሲጀምር ያኔ እናንተ የስጋዊ ሕይወት ትጠየፋላችው እያለ ይናገራል። ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ በቆላ 3:16 ላይ  «የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችው» እንዳለ የእግዚአብሔር ቃል እኛ ላይ በሙላት መኖር ሲጀምርብን አብዝተን ስንጸልይ አብዝተን ስንሰግድ አብዝተን ስንፆም  የስጋዊ ህይወታችንን እንጠየፋለን ማለት ነው።

አብዛኛውን ጊዜ ዘፈን መልክ መልኩን እየቀየረ መጥቷል እያየነውም ነው። ይኼን ያነሳንበት ምክኒያት እንዳንዶቹ ስለፍቅር መዝፈን ስለሀገር መዝፈን ሀጢያት ነው ወይ የሚል ጥያቄ እያነሱ ስለምናያቸው ነው። አንድ ምሳሌ ይባላል። ምሳሌውም፦ #አዘለም_አቀፈም_ያው_ተሸከመ_ነው ይባላል። እና #ዘፈንም መልኩን ቢቀያይርና ርዕሱን ቢለዋውጥ ዘፈን ያው ዘፈን ነው። በአንድ ወቅት መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየው በriot(ርዮት) ፕሮግራም ቃለ መጠየቅ ላይ ቀርበው ስለዘፈን የሰርግ ሰፈን የሐገር ዘፈን እንዲኹም ሌሎች ሌሎችም በቤተክርስቲያን እንዴት ያዩታል ተብለው ሲጠየቁ እርሳቸውም ቤተክርስቲያንን አጥር እንዳጠረች በዚህ ጉዳይ ላይ እንደማትደራደርና ዘፈን ሀጢያት መሆኑን አስረግጠው አልፈዋል።

ዘፈን ማለት በአጭሩ የአጋንንት ግብር ነው። በአንጻሩ ስለ ሰይጣንና የግብራበሮቹ የክፋት መናፍስት ግብር ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ ሲናገር፦ በዚያም የምድረ በዳ አራዊት ያርፋሉ ጕጕቶችም በቤቶቻቸው ይሞላሉ ሰጐኖችም በዚያ ይኖራሉ በዚያም አጋንንት #ይዘፍናሉ ይላል። (ኢሳ 13:21) ለሰራዊት ጌታ ለቅዱስ እግዚአብሔር የሚቀርበውን ዝማሬና ምስጋና  የሚፈፀየፉ የአጋንንትን ግብር ማድረግ ይባስ ብሎ የአጋንንት ማህበርተኛ አንድም በክፉ ስራቸው የምንተባበር መሆን ነው። «ከአጋንንትም ጋር ማህበርተኞች እንድትሆኑ አልወድም»(1ኛ ቆሮ 10:20)

#ዘፈን የስጋ ስራ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን የሐጢያት ዋና ዋናዎች አርዕስተ ሀጢያት ብሎ እንደ ዘረዘረልን እናነባለን። ከእነዚህ ከ16ቱ ድርጊቶቹ ውስጥ አንዱ ዘፈን ወይንም ደግሞ ዘፋኝነት ነው። «የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው ርሱም #ዝሙት #ርኵሰት #መዳራት #ጣዖትን_ማምለክ #ሟርት #ጥል #ክርክር #ቅንአት #ቍጣ #ዐድመኛነት #መለያየት #መናፍቅነት #ምቀኝነት #መግደል #ስካር #ዘፋኝነት ይህንም የሚመስል ነው አስቀድሜም እንዳልኹ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።»(ገላ 5፥19-21 1ኛጴጥ 4:3) ዘፋኝነት በግልጽ መንግስተ ሰማያትን አያወርስም እያለ እንዴት ነው ሰው ወደዘፋኝነት የሚገባው።

ዘፈን የዝሙት ማቀንቀኛ ነው። በየመልኩ ሊመሰገን የሚገባው ሁሉን ያስገኘ ሁሉን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን ፈጣሪው ሳይሆን ፍጡሩን ገዢውን ሳይሆን ተገዢውን ማወደስ ማለት ትልቅ አስፀያፊ ተገባር ነው። አንዳንድ ሰው በጣም ነው ግርም የሚለው እግዚአብሔር ዘፈንን የሚፈቅድ ይመስል "ከእግዚአብሔር ጋር ዘፈን ጨርሻለሁ አሁን ይለቀቃል ከእግዚአብሔር ጋር" ሲሉ ይሰማሉ እግዚአብሔር ከሰይጣን ጋር ተባባሪ አደረጉት እኮ ይገርማል  ይህንን እንኳ ማሰብ ተስኗቸዋል እስከዚህም ድረስ ነው አስተሳሰባችን። እንደውም አለምን የፈጠረ አምላክ እንደየክብሩ ማወደስ ሲገባን በዘፈን አንድሰውን አይኑ ጥርሱ አፍንጫው እያለን ከንቱ ውዳሴ እንናገራለን። ከስልኩ እንኳ ዘፈን ለማጥፋት ያቃተው ትውልድ እኮ ነው ያለን በእውነቱ ስለዚህ ከእነዚህ አይነት ተግባር መራቅና መሸሽ ተገቢ ነው።

አንዳንድ ሰዎች ያስደንቃሉ  እኛ እኮ ለመደሰት ነው የምንዘፍነው የምንጨፍረው በማለት ሲናገሩ እናያቸዋለን። ለእነዚህ አይነት ሰዎች መጽሐፋችን እንዲህ ይለናል፦ ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር ርሱ ይጸልይ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር ርሱ ይዘምር።(ያዕ 5፥13) ስለዚህ ማናችንም ብንሆን ስንደሰት መዘመር ስናዝን ደግሞ መጸለይ እንዳለብን መጽሐፉ ነግሮናል።

ዳግም የመጋቢ ሐዲስ እሸቱን አነጋገር እንጠቀም እና እናብቃ።  መጋቢ ሐዲስ ምን አሉ ዘፈን እነ ሰርጸ እነ ማህሙድ አህመድ ሲይዙት ጽድቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ ግን ሲይዘው ሀጢያት ነው በማለት አስረግጠው አስቀምጠዋል። ይኼ ነው እውነቱ ሀጢያት ነው ለሰይጣን የምናቀርበው ግብር ነው ስለዚህ እግዚአብሔር የሰጠንን አንድበት እናመስግንበት ክፉ አናውራበት መድኃኔዓለም የሰጠንን እግር ወደጭፈራ ቤት ወደ ኃጢያት አናምራበት። ቤተክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድበት ኪዳኑን ሰዓታቱን ማሕሌቱን እንቁምበት በዚህ ስፍራ ያላችሁ ሁሉ ይህንን አንብባችሁ ትምህርት እንደምትወስዱበት አልጠራጠርም።

እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን

ይቆየን!!

ሼር በማድረግ በእንደዚህ አይነት ስፍራ ያሉትን ግንዛቤ እናስጨብጣቸው!!!

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን 👇
╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝