ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)
3.4K subscribers
4.16K photos
139 videos
2 files
1.33K links
#𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧_𝐧𝐞𝐰𝐬
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።
ጥያቄ፣ጥቆማ፣ማስታወቂያ ለማሰራት በዚ አድርሱን
👉 @Zehabesha_offical_Bot
#𝓩𝓮𝓱𝓪𝓫𝓮𝓼𝓱𝓪_𝓸𝓯𝓯𝓲𝓬𝓲𝓪𝓵
Download Telegram
የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳና ልዑካቸው በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ መቀሌ ተመልሰዋል::
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ "20ሺህ ሰራተኞችን ሊቀጥር ነዉ"በሚል እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን አስታወቀ

በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየተሰራጨ የሚገኘዉ "ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሰራተኞችን ሊቀጥር ነዉ" የሚለዉ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ሀላፊ ወ/ሮ ተወዳጅ እሸቱ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

እንደ ወ/ሮ ተወዳጅ ገለጻ ኩባንያዉ 20 ሺህ ሰራተኞቻችን ለመቅጠር የያዘዉ እቀድ የለም ያሉ ሲሆነወ የተጠቀሰዉ ቁጥርም ግነት ያለዉ መሆኑን ገልጸዋል።

እየተሰራጨ በሚገኘዉ መረጃ ኩባንያዉ " በሶማሌ ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች ነዉ የተጠቀሰውን ቁጥር ያህል ሰራተኛ ይቀጥራል የተባለዉ"።

ኩባንያዉ የዚህን ያህል ቁጥር ሰራተኛ ለመቅጠር የያዘዉ እቀድ እና ዝግጅት እንደሌለ ጠቅሰዉ ፤ በኩባንያዉ ስም ከተከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት የተሰራጨ መሆኑን ጨምረዉ ተናግረዋል።

በቅርቡ ብስራት ራዲዮ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 3 ሚሊዮን የደምበኞች ቁጥር መድረሱን መዘገቡ ይታወሳል።
ሲልቪዮ በርሉስኮኒ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሀገሪቱ የዜና ወኪል አናሳ ዘግቧል።

እ.ኤ.አ. በ 1994 እና 2011 ሶስት ግዜ የጣሊያን የመሩት እና የፎርዛ ኢታሊያ ፓርቲ ጁኒየር አጋር የሆነው የሚዲያ ባለሃብት ሲልቪዮር ቤርሉስኮኒ በደም ካንሰር ህመም ሲሰቃዩ እንደነበር አናሳ የተባለው የሃገሪቱ ዜና አውታር ገልጿል::
ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄን በመተካት ነው የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢነት የተሾሙት፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ግርማ ዋቄ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተፈቷል‼️

የ"ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ አርብ ምሽት ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ሥነ ስርዓት በኋላ በመንግሥት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር የሰነበተ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ከእስር መፈታቱ ታውቋል።
ህወሓት ከምርጫ ቦርድ መሠረዙን ተከትሎ በዚህ ስያሜ ለሚመጣ ማንኛዉም የተደራጀ ፖለቲካ ድርጅት በምርጫ ቦርድ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 69 መሠረት ስያሜዉን መዉሰድ ይችላል። ነገር ግን ምርጫ ቦርድ ለ አንድ ወር ባደረገው ስብሰባ እና ጥናት መሰረት ዉድቅ አድርጎታል።

ምርጫ ቦርድ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ለስልታዊ ትብብር ከፑቲን ጋር እንደሚሰሩ ቃል ገቡ

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር "እጅ ለእጅ" ለመያያዝ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ‼️
ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄን በመተካት ነው የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢነት የተሾሙት፡፡
ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
መረጃ‼️
በምዕራብ ጎጃም ደምበጫ ከተማ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ተከትሎ የሰው ህይወት ጠፍቷል። ይህን ተከትሎ ደምበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ላይ መንገድ መዘጋቱ እና ህዝባዊ ተቃውሞ ተደርጓል። ፍኖተ ሰላም ላይ 2 ወጣቶች ሲገደሉ ከ4 በላይ ቆስለዋል ተብሏል።
ትናንት ማታ 12:30 ጀምሮ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት እና በሀገር መከላከያ ሰራዊት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።
የሱዳን ግጭት ወደ እርስበእርስ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ገለጹ

የሱዳን ጦርነት የማይቆም ከሆነ የእርስበእርስ ግጭት እና ትርምስ እንደሚያስከትል የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ገልጸዋል።

ጦርነቱ በሱዳን ህልውና ላይ አደጋ መደቀኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ግጭት እንዲቆም እና ተፋላሚ ወገኖች ወደ ንግግር እንዲገቡ ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል ሊቀመንበሩ።

ጦርነቱ ከተጀመረ 9ኛ ሳምንቱን ይዟል።
እየሱስን ለማግኘት" ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 80 ኡጋንዳዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ አማኞቹ ኢየሱስን ለመገናኘት ለ40 ቀናት እንዲጾሙም መደረጉ ተነግሯል

የኡጋንዳው ፓስተር ኦፖሎት ድርጊት አማኞችን እስከ ሞት እንዲጾሙ ካዘዙት ኬንያው ፓስተር ፖል ማኬንዚ ጋር ተመሳሳይነት አለው ተብሏል

ኢትዮጵያ ከኢየሱስ ጋር እንደሚገናኙ ቃል የተገባላቸውን 80 የኡጋንዳ አማኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሁኔታ ማመቻቸቷ ተነግሯል።

አማኞችን አታለዋል የተባሉት ፓስተር ሲሞን ኦፖሎት በኡጋንዳ ምስራቃዊ ሶሮቲ ውስጥ ከሚገኘው የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ቤተ-ክርስቲያን ጋር ግንኙነት ያላቸው አማኞችን በማጭበርበር በደህንነት እየተፈለጉ ነው።

ኦፖሎት ተከታዮቻቸው ንብረታቸውን እንዲሸጡ እና ኢየሱስን ለመገናኘት እንዲዘጋጁ፤ ለዚህም በኢትዮጵያ ያሉት ብቻ እንደሚመረጡ መለኮታዊ ራዕይ ታይቶኛል በማለት አሳምነዋል ተብሏል። ምእመናኑ ንብረታቸውን ሸጠው ገንዘባቸውንም አደራ ሰጥተው በሞሮቶና በአሙዳት ወረዳዎች ተጉዘው ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ታውቋል።

ቡድኑ በዚህ አመት ጥር እና መጋቢት መካከል ይህንን የነፍስ ጉዞ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ኢትዮጵያ የኡጋንዳ ባለስልጣናትን በማነጋገር ዜጎቹ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን አስፈላጊ ሰነዶች እና ዝግጅቶችን ማመቻቸቷ ተነግሯል።

የየኡጋንዳ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሲሞን ፒተር ሙንዴይ ፓስተር ኦፖሎት ኢየሱስን በ41ኛው ቀን ለመገናኘት ለ40 ቀናት እንዲጾሙም አሳምኗቸዋል ብለዋል።

ኦፖሎት ለኢትዮጵያ መለኮታዊ ግንኙነት ዓለም በፍጥነት ይጠፋል ብለው ለተከታዮቻቸው ተናግረዋል ተብሏል።

ተከታዮቹ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የተማሩ ግለሰቦች መሆናቸውንም ታውቋል።

ስደተኞቹ በአድካሚ ጉዞ እና የእለት ምግብ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የአካል ጉዳታቸው መጋለጣቸውን የኡጋንዳ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ደህንነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት ወሳኝ ሚና መጫወቱንም እንዲሁ።

የኦፖሎት ድርጊት ከኬንያው ፓስተር ፖል ማኬንዚ ጋር ተመሳሳይነት አለው ተብሏል።

የኬንያው ፓስተርም ተከታዮቻቸውን ወደ መንግስተ ሰማይ ለመሄድ እስከ ሞት ድረስ እንዲጾሙ አድርገዋል።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በሳይንሳዊ መንገድ አዘጋጀሁ ያላቸውን 3 መድኃኒቶች፤ በሰዎች ላይ ሊሞክር መሆኑን አስታውቋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የባህል መድኃኒቶችን በሳይንሳዊ መንገድ እያዘጋጀ መሆኑንና በተያዘው ዓመት በሳይንሳዊ መንገድ የተቀመሙ ሦስት የባህል መድኃኒቶች በሰዎች ላይ እንደሚሞከር አስታውቋል።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ የአንኮበር ቤተ መንግሥት የሚገኝበት አከባቢ በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች ሊባል በሚችል መልኩ ለመድኃኒት ቅመማ የሚውሉ ዕፅዋት የሚገኙበት ሥፍራ እንደሆነ መለየቱን ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው፥ የዕፅዋቱን ቅመማ እና መድኃኒትነት የሚያውቁ ረጅም ዕድሜ ያላቸው አባቶች እና እናቶች አሁንም በአካባቢው መኖራቸውን እንደ ዕድል በመጠቀም አብሮ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። 

የባሕላዊ መድኃኒቶችን የአቀማመም ሥልት በማጥናት ሳይንስ በሚቀበለው መልኩ ለማድረግ የተለያዩ ምርምሮች እየተሠሩ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤  በርካታ መድኃኒቶች በቅመማ እና በሙከራ ደረጃ እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

በአይጦች እና በሌሎች ከሰው ጋር ተመሳሳይ የሰውነት ሥርዓት ባላቸው እንስሳት ላይ ሙከራቸው ተጠናቆ በሰው ላይ ሊሞከሩ የተዘጋጁ ሦስት መድኃኒቶች በያዝነው ዓመት ሙከራቸው ይጠናቀቃልም ብለዋል።

መድኃኒቶቹ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሙከራ ደረጃዎችን ሲያጠናቅቁ ወደ ምርት እንደሚገቡ የተገለጸ ሲሆን ለምን በሽታ መድኃኒትነት የተዘጋጁ እንደሆኑ በዘገባው አልተጠቀሰም
ተፈተዋል‼️
ባለፈው ሳምንት በአለርት ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው ” የአካል ጉዳተኞች መጠሊያ ጣቢያ ” ለአራት ቀናት ያህል ታስረው የቆዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተለቀቁ፡፡
‹ እነዚህ ዜጎች በአራት ቀናት ቆይታቸው ለማምለጥ ሲሉ በአጥር ጭምር የመዝለል ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበረ › የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻም ነግረዋታል፡፡
በዚህም ‹ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዳሉ › ገልፀዋል፡፡
ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ‹ በዘመቻ እንደታሰሩ › የሚገልፁት እነዚህ ዜጎች ‹ ለአራት ቀናት ያህል በቂ ምግብና ውሃ ሲቀርብላቸው እንዳልነበረ › ተናግረዋል፡፡
‹ የታሰሩበትንና ከአራት ቀናት ቆይታ በኋላም የተፈቱበትን ምክንያት እንደማያውቁ › አክለዋል፡፡
ከአራት ቀናት በኋላ የተፈቱት እሁድ ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን አሻም አረጋግጣለች፡፡
እነዚሁ ዜጎች በታሰሩበት ወቅት ቅፅር ግቢውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ሲጠብቁ እንደነበረ አሻም በስፍራው ተገኝታ ታዝባለች፡፡
ባለፈው ሳምንት የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል ‹ በአዲስ አበባ ከተማ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እንደሚያካሄድ › መግለፁ ይታወሳል፡፡
በጃፓን ላይ ከተጣለዉ የአቶሚክ ቦምብ በሶስት እጥፍ የበለጠ የኒዉክሌር ጦር በቤላሩስ ሩሲያ ልታከማች ነዉ

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት "መሳሪያዉን ለመጠቀም ዉሳኔ እንዳልሰጥ እግዚያብሄር ይጠብቀኝ " ብለዋል

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በሰጡት መግለጫ ሀገራቸው በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ከተጣሉ የአቶሚክ ቦምቦች "በሶስት እጥፍ የሚበልጡ" የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ከሩሲያ እየተቀበለች እንደሆነ ጠቁመዋል። ቤላሩስ ሊደርስባት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ወደ የጦር መሳሪያዉ አስፈላጊ እንደሆነ አስታዉቃለች።

ከቀናት በፊት ሩሲያ እንዳስታወቀችው ከሆነ ከሀምሌ ወር አንስቶ ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በቤላሩስ ምድር እንደምታሰማራ ገልፃለች። ይህን ለምዕራቡ ዓለም እንደ ማስጠንቀቂያ ተደርጎ ተወስዷል። ሉካሼንኮ እንዳስታወቁት ሚንስክ የጦር መሳሪያዎቹን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል። "ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው። የጠየቅነውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ትንሽም ቢሆን የምናገኝ ይመስለኛል” ሲሉ ተናግረዋል።

ሉካሼንኮ በምዕራባውያኑ ሀገራት አነሳሽነት ጥቃት የሚሰነዘርብን ከሆነ ምላሽ ለመስጠት መሳሪያውን ከመጠቀም ወደኋላ እንደማይሉ አስጠንቅቋል። "ለምን የኒውክሌር የጦር መሳሪያእን እንደምንፈልግ ልንገራችሁ አንድም የውጪ ወታደር በቤላሩስ ምድር ላይ እግሩን ካሰረፈ እንጠቀምበታለን" ሲሉ ተናግረዋል።

“እግዚያብሄር እነዚህን መሳሪያዎች ለመጠቀም ውሳኔ እንዳልሰጥ ይጠብቀኝ። ነገር ግን በኛ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ማመንታት እንደማይኖር እወቁት ሲሉም አክለዋል። ከሶቪየት ኅብረት መፍረራረስ በኋላ ሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን ስታንቀሳቅ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ማስገንዘቢያ

ዘ-ሐበሻ በአሜሪካን ሃገር በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚሠራ፤ ለአሜሪካ መንግስት ግብር የሚከፍል ተቋም ነው። ሚዲያችን ከተመሰረተበት እ.ኤ.አ 2008 ጀምሮ የዕምነት ተቋማትን ማስታወቂያዎች በነፃ ሲያስተዋወቅ መቆየቱ ይታወሳል። ከዚህ በኋላ ግን ማንኛውም የዕምነት ተቋም ማስታወቂያውን በዘ-ሐበሻ ማስተዋወቅ ከፈለገ የምናስከፍል መሆናችንን በትህትና እንገልጻለን።

Zehabesha LLC
“ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢነት ከለቀቅሁ በኋላ ለየትኛውም ሚዲያ ማብራሪያ አልሰጠሁም”— አቶ ግርማ ዋቄ ለኢትዮጵያ ቼክ

አቶ ግርማ ዋቄ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢነት መልቀቅቸውን ተከትሎ የእርሳቸውን ንግግር የያዙ አጫጭር ቪዲዮውች በቲክቶክ ሲጋሩ ተመልክተናል።

ከቪዲዮዎቹ ጋር “አቶ ግርማ ዝምታቸውን ሰበሩ” እና “አቶ ግርማ ዋቄ እንዲህ ብለዋል” የሚሉ ርዕሶች ይነበባሉ። በቪዲዮዎቹ የአስተያየት መስጫ ቦታ ሀሳባቸውን ያስቀመጡ በርከት ያሉ የቲክቶክ ተጠቃሚዎችም የአቶ ግርማ ንግግር አዲስ እንደመሰላቸው አስተውለናል።

ሆኖም ባለፉት ቀናት በቲክቶክ በመጋራት ላይ የሚገኙት ቪዲዮዎች የቆዩ መሆናቸውን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

ቪዲዮዎቹ የተወሰዱት አቶ ግርማ ከፋና ብሮድካስቲግ ጋር ከወራት በፊት ካደረጉት ቃለምልልስ ተቆርጠው የተወሰዴ ሲሆን ትክክለኛውን ቪዲዮው ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል:
https://youtu.be/8qtnqP1fAGk

አቶ ግርማ የተጋሩት ቪዲዮዎች የቆዩ መሆናቸውን ለኢትዮጵያ ቼክ ያረጋገጡ ሲሆን “ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢነት ከለቀቅሁ በኃላ ለየትኛውም ሚዲያ ማብራሪያ አልሰጠሁም” በማለት ገልጸዋል።

የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ላለፈው ሁለት ዓመት ተኩል ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ በሆኑት ሌተናንት ጄኔራል ይልማ መርዳሳ መተካታቸውን አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወቃል።

አቶ ግርማ ከዚህ ቀደም የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚነትን እና የአመራር ቦርድ አባልነትን ጨምሮ በተለያዩ ኃላፊነቶች ተቋሙን እንዳገለገሉ በመግለጫው ተገልጿል።
ኬንያ የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በርስ ግብይት ሲፈጽሙ በራሳቸው ገንዘብ ክፍያ መፈጸም እንዲጀምሩ ጠይቃለች‼️
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በጂቡቲ ፓርላማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው “በዶላር ላይ ጥገኝነቱ ይብቃ” ያሉት።
“ከጂቡቲ እቃ ገዝተን በዶላር የምንከፍለው ለምንድን ነው? ለምን? ምንም ምክንያት የለም” ያሉት ፕሬዝዳንት ሩቶ፥ ጂቡቲም ሆነች ኬንያ የእርስ በርስ ግብይት ሲፈጽሙ የአሜሪካ ዶላር መጠቀም አያስፈልጋቸውም ብለዋል።
"እኛ የአሜሪካን ዶላር እየተቃወምን አይደለም፤ በነጻነት ግብይት መፈጸም ስለፈለግን እንጂ” ሲሉም አብራርተዋል።
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ በአል-ቡርሃንና ሃሄቲ መካከል ቀጥተኛ ውይይት ለማድረግ ሚና እንዲኖራቸው በኢጋድ ተወስኗል- አምባሳደር መለስ ዓለም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫየሱዳንን ግጭት ለመፍታት የኢትዮጵያን ጨምሮ የአራት ሀገር መሪዎች ከተፋላሚዎች ጋር እንዲመክሩ ኢጋድ መሰወኑን አስታውቀዋል።
የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች አዲስ አበባ ላይ ፊትለፊት ተገናኘተው እንዲመክሩ ኢጋድ ታሪካዊ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ!

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ።በኢትዮጵያ በተለይም የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸው በተለያየ መልኩ ሲገለጹ ቆይቷል።የባንክ ደንበኞችም ለአገልግሎት ባመሩባቸው የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ሲጠይቁ እንዳልሰጧቸው በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተሰተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል።የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት "በኢትዮጵያ በግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል እሚባለው መረጃ ሀሰት ነው" ብለዋል።

የጥሬ ገንዘብ እትረት ገጥሟቸዋል የተባሉት አምስት ባንኮች ናቸው መባሉን ሰምተናል ፣ "ነገር ግን በሶስት ባንኮች ላይ የተወሰነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሞ ነበር፣ ብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በወሰዷቸው ማስተካከያዎች አሁን ላይ ከአንድ ባንክ በስተቀር የጥሬ ገንዘብ እጥረት ያጋጠመው ባንክ የለም" ሲሉም ምክትል ገዢው አክለዋል።

በኢትዮጵያ የገንዘብ አቅርቦቱ እና ፍላጎቱ የተጣጣመ አይደለም ያሉት አቶ ሰለሞን አሁን ያጋጠመው ክስተትም ጦርነት ውስጥ በነበርንበት የቆመው የፋይናንስ እንቅስቃሴ አሁን የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የፋይናንስ ፍላጎቱ በመጨመሩ ብቻ የተፈጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎቶችን ለዓለም አቀፍ ተቋማት በሯን ክፍት ማድረጓን ተከትሎ ይህ ሂደት የት ደረሰ? በሚል ለምክትል ገዢው ለቀረበላቸው ጥያቄም " ስራው ሰፊ ዝግጅቶችን የሚጠይቅ ነው፣ ከዓለም ባንክ ጋርም አብረን እየሰራን ነው በአንድ ዓመት ውስጥም ስራውን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው" ብለዋል።

" የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱን ተከትሎ የአገር ውስጥ ባንኮች ራሳቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ውህደት ለመፈጸም በሂደት ላይ ያሉ ባንኮች አሉ" ያሉት አቶ ሰለሞን የኢትዮጵያ ባንኮች በቴክኖሎጂ ፣ ፋይናንስ አቅም እና ሰው ሀይል የበለጠ እንዲዘጋጁም ጥሪ አቅርበዋል።

ስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው ይህ ትኩረቱን በካፒታል ማርኬት ላይ ያደረገ ሲሆን የየፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶች እና ውይይቶች እየተደረጉበት ይገኛል።በጉባኤው ላይ የባንክ ስራ አስኪያጆች፣ ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች ተሳትፈውበታል።
አየር መንገዱ 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 13 ነጥብ 7 ሚሊየን መንገደኞች ማጓጓዙን ተናግረዋል፡፡

በኮቪድ-19 ወቅት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎችን ከመመለስ በተጨማሪ ወደ ሰባት አዳዲስ መዳረሻዎች በረራ መጀመሩንም አንስተዋል፡፡

የአውሮፕላን ቁጥርን ለማሳደግ በተሰራው ስራም 12 አዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡በአየር መንገዱ የጥገና እና ምህንድስና ማዕከል ከመንገደኛ ወደ ጭነት አገልግሎት ሰጪነት የተቀየሩ ሁለት አውሮፕላኖች የካርጎ ስራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል፡፡