Zehabesha
61.1K subscribers
4.84K photos
478 videos
14 files
6.42K links
Ethiopian News
Download Telegram
ከአቅም በላይ በሆነ ችግር የዕለቱ ዜናችን በመዘግየቱ ይቅርታ እየጠየቅን ከደቂቃዎች በኋላ እንደሚለቀቅ እንገልጻለን።
የበላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን እና የወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሰሜን ጎንደር፣ ዋግኸምራ እና ደብረብርሀን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

የበላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን የቦርድ ስብቢ አቶ በላይነህ ክንዴ በገንዘብ ርክክብ ወቅቱ እንደገለጹት፤ ወገኖቻችን በድርቅ ምክንያት የደረሰባቸውን ችግር በጋራ ለመፍታት የሰባት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ አስቸኳይ ምግብ በመግዛት በራሳቸው ትራንስፖርት እንደሚያደርሱ አስታውቀዋል።

የወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት አቶ ታደሰ ምህረቴ በበኩላቸው፤ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ለሚፈልጉ የሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የአስቸኳይ ምግብ ግዥቅ ተፈጽሞም በራሳቸው ትራንስፓርት በአካባቢው እንደሚያደርሱ አስታውቀዋል::