Zehabesha
61.1K subscribers
4.84K photos
478 videos
14 files
6.42K links
Ethiopian News
Download Telegram
"አሸተ ደምለው ምን ተናግረው ነው ሕወሓት እንዲህ የተቆጣው?" ላላችሁን፣ የአሸተ ንግግር በዕለቱ ዜና ይዘንላችኋል።
የለንደን ፋኖ በቪየትናም ኢምባሲ። ዝርዝሩን ከዕለቱ ዜናችን ይመልከቱ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዚህች ኢትዮጵያዊት ወጣት መጨረሻ ምን ሆነ? ዝርዝሩን ከዕለቱ ዜና ተመልከቱ። https://youtu.be/4vrUXcg8K3s
ዜና አሁን የደረሰን፡ https://youtu.be/Up-xCn7ZZNQ
Zehabesha pinned «ዜና አሁን የደረሰን፡ https://youtu.be/Up-xCn7ZZNQ»
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ለቡሬ ከተማ ነዋሪዎች በዓል መዋያ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ዛሬ ባሰራጨው መረጃ መሠረት፣ "በቡሬ ከተማ የሚገኘው ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚበጁ ማህበራዊ ሀላፊነቶችን በመወጣት ላይ ይገኛል።"

"ፊቤላ ባለፉት 4 ዓመታት ከ200 በላይ የሚሆኑና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን በቋሚነት በየወሩ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ" የገለጸው ቢኬጂ ግሩፕ፣ "ፊቤላ በቋሚነት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በዓላትን መነሻ በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖችም ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። የፊታችን እሁድ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ1300 በላይ ለሚሆኑና በቡሬ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።" ሲል ገልጿል።

በተያያዘ ዜና በላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖችም ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

ፊቤላ ኢንዱስትሪያል፣ ባለፉት አራትላአመታት በቡሬ ከተማና አካባቢው ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የትምህርት ተቋማትና የውሃ መሠረተ ልማት በመገንባት፣ የጤና መድህን በመክፈል፣ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖችን ቤት ገንብቶ በማስረከብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ካሰራጨው መረጃ ላይ ተመልክተናል።
500ሺ ዶላር ስለሚያስገኘው ጉርሻ ከዕለቱ ዜና ላይ ይመልከቱ።