Z Doctors 🇪🇹
94.7K subscribers
144 photos
8 videos
6 files
27 links
በግል ለማግኘት ወይም ቀርባችሁ ህክምና ማድረግ የምትፈልጉ፣ በዚህ አድራሻ ቀጠሮ ማስያዝ ትችላላችሁ።
👉 1 @Zdoctors1
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
We can’t stay quiet seeing all the love our fearless leader, Mirafe, is getting! Not only did he make us proud, he also represented the rich history of Ethiopia and kept the vibe alive during iShowSpeed’s stream. Calm, eloquent, and clear, he communicated Ethiopia’s story with confidence and ease.

We’re incredibly proud of him. And if you thought he was impressive on the stream, just imagine what it’s like to work with him at ALX. #DoHardThings
4🔥3
🔴🔴 ዛሬ ብሞትስ በል!!! 🔴🔴

ዛሬ ብንሞትስ ብላችሁ አስቡ እስኪ

🔊 ለነገ ያሳደርናቸው ብዙ ሀሳቦች አብረውን ይሞታሉ

🔊 ለነገ ያቆየናቸው ስንት ግቦች መቃብር ይወርዳሉ

🔊 ዛሬ ሳናወጣው የደበቅነው ተሰጥኦአችን አብሮን ይቀበራል

🔊 ሳይፈነጥቁ የቆዩ ብዙ ተስፋዎች ይቀጫሉ

🔊 ለሰዎች ያላሳየናቸው ስንት ደግነቶች አፈር ይበላቸዋል

🔊 ያልተነገሩ ስንት ይቅርታዎች ይሞታሉ

🔊 ነገ እደሰታለሁ ብለህ ቀን ስትጠብቅ ቀኑ ይጨልምብሀል ስለዚህ አስብ እየአንዳንዷን ቀን እንደ መጨረሻ ቀን ቁጠራት

ማድረግ ያለብህን ዛሬ እያደረክ ተደሰት just do it now አይመስልህም ?
15👏4🔥2
የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው የጉበት በሽታ ምንድን ነው ? ለግንዛቤ ያክል 👇👇

ጉበት በሆድ እቃችን ውስጥ ከሳንባችን ስር ከቀኝ ወደ ግራ አግድም የተቀመጠ አካል ሲሆን ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ፕሮቲኖችን ከማምረት ጀምሮ መርዛማ ነገሮችን በማጣራት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ምግቦች ብቻ ወደ ደም ስራችን እንዲደርሱ የሚያደርግ በጣም አስፈላጊ የሰውነት አካል ነው።

የጉበት በሽታ መንስኤዎች

የጉበት በሽታ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ቢሆንም እንደኛ ላሉ ታዳጊ ሀገራት የጉበት ቫይረሶች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ።
ሄፓታይተስ B እና C ስር የሰደደ የጉበት በሽታ (Chronic liver disease )የሚያመጡ ሲሆን A እና E ደግሞ አጣዳፊ (Acute liver disease ) ያስከትላሉ።

1.የጉበት ቫይረሶች (A,B ,C , D ,E and G)
2.የተለያዩ መድሐኒቶች
3.ከመጠን በላይ የብረትና የመዳብ ክምችት ሲኖር (Hemochromatosis, Wilson disease )
4.የሰውነታችን የመቆጣት ችግርና የራሳችንን አካል በራሱ ሲያጠቃ (Autoimmune liver disease )
5.ከጉበት ወደ አንጀት የሚውስዱ ቱቦዎች በተለያየ ምክንያት ሲዘጉ
6.አልኮል አዘውትሮ እና ለረጅም ጊዜ መጠጣት
7.እና የመሳሰሉ ምክንያቶች

ሄፓታተስ ቢ ምንድን ነው(Hepatitis B infection )

ሄፓታይተስ ቢ ጉበትን የሚያጠቃ ቫይረስ ሲሆን ለጉበት በሽታ /Chronic liver disease/ መንስኤ የሆነና የማያቋርጥ ዓለም አቀፍ ችግር ነው።

ኢትዮጵያ በጣም ከተስፋፋባቸው ሀገራት ውስጥ ትመደባለች፡፡
በኢትጵያ የአንድ ሰው የዕድሜ ልክ ሄፓታይተስ ቢ መያዝ እስከ 80% ይደርሳል::

በሄፐታይተስ ቢ ከሚያዙ አዋቂዎች 90 % ሙሉ በሙሉ ይድናሉ::
በተወለዱበት ጊዜ ወይም ከአንድ አመት በፊት ከተያዙ ሕፃናት መካከል ደግሞ 90 % የሚሆኑት ሥር የሰደደ የጉበት በሽታ ይከሰትባቸዋል፡፡

ሄፓታይተስ ቢ እንዴት ይተላለፋል?

√በተበከለ ደም እና ሌሎች የሰውነት ፈሳሾች መጋለጥ
√በወሊድ ጊዜ ከእናት ወደ ልጅ
√በግብረ ሥጋ ግንኙነት
√ደህንነቱ ባልተጠበቀ መርፌ እና/ወይም ደም በመስጠት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ይተላለፋል።

በአጠቃላይ ሄፓታይተስ ቢ ከኤችአይቪ ከ 50-100 እጥፍ በበለጠ ይተላለፋል::

የሄፐታይተስ ቢ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ሀ) አጣዳፊ የሄፐታይተስ ቢ ኢንፌክሽን (Acute hepatitis B) ምልክቶች:
ድካም, ማቅለሽለሽ, ማስታወክ, የሆድ ህመም ፣ የቆዳ ,የሽንት እና የዓይን ቢጫ መሆን ናቸው።

ለ) ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ ቢ(Cirrhosis) ያለባቸው ሰዎች ደግሞ
√የሆድ እብጠት, ያልተለመደ ደም መፍሰስ፣የኩላሊት ችግር(Hepatorenal syndrome )፣የሳንባ ህመም (Hepatopulmonary syndrome )፣ እና የአዕምሮ ሁኔታ መለወጥን(Hepatic Encephalopathy ) እና የመሳሰሉትን ያስከትላል፡፡

√የጉበት ሲርሆሲስ (Cirhossis) የጉበት ካንሰርን በማምጣት ለሞት ይዳርጋል ፡፡

√ሄፓታይተስ ቢ የሲርሆሲስ በሽታ በማይኖርበት ጊዜም እንኳ የጉበት ካንሰር (Hepato cellular carcinoma) ያስከትላል፣ ስለዚህ ቢያንስ በየ 6 ወሩ የህክምና ክትትል እና የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።

የሄፓታይተስ ቢ መከላከያዎች ?

ሄፓታይተስ ቢን በክትባት መከላከል ይቻላል።

ክትባቶች መቼ ይሰጣሉ?
በብሔራዊ የክትባት መርሃ ግብር በተወለዱ፣ በ6 ፣ በ10 ፣ በ14 ሳምንታት ዕድሜ

ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ካለባት እናት የተወለደ ህፃን ክትባቱ በተቻለ ፍጥነት ከተወለደ በኋላ (በተወለደ በ24 ሰዓታት ውስጥ ማግኘት አለበት)፣ነገር ግን ክትባቱ በ24 ሰዓት ውስጥ መስጠት ካልተቻለ በተወለደ ሁለት ሳምንታት ውስጥ መስጠትም ውጤታማ ያደርገዋልና ክትባቱን መስጠት ያስፈልጋል ።

√የሄፐታይተስ ቢ ክትባቶች (ብዙ ጊዜ በ 0፣ በ1 እና 6 ወር ይሰጣሉ )
ክትባቱ ብዙ ጊዜ የሚሰጠው
-ለነፍሰጡር እናቶች
-የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ታካሚዎች እና
-ለጤና ባለሙያዎች ወዘተ…።

ለሄፐታይተስ ቢ ሕክምናው ምንድነው?
* ቴኖፎቪር(TDF) እና የመሳሰሉ Anti viral Medication ሲሆኑ።
እነማን መድሀኒት መጀመር አለባቸው ስለሚለው
በ Guidelines በግልፅ ተቀምጧል።

√ሥር የሰደደ ሄፐታይተስ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ አይድንም (no cure) ነገርግን በአብዛኛዎቹ ታካሚዎች የቫይረሱ መራባት መጠን መቀነስ እና የጉበት አሰራር መስተካከል በማምጣት የህመሙን ተፅዕኖ ይቀንሳል፡፡

ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ

በሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ መያዝን ተከትሎ ከ50 እስከ 85 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሥር በሰደደ ሄፓታይተስ ይያዛሉ;: ይሁን እንጂ ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ አብዛኛውን ጊዜ ቀስ በቀስ እያደገ የሚመጣ በመሆኑ በብዙ ታካሚዎች ግልጽ የሆነ የጉበት በሽታ ምልክት ላያመጣ ይችላል፡፡

ከ5 እስከ 30 በመቶ የሚሆኑት ሥር በሰደደ በሽታ የተያዙ ሰዎች ከ 20 እስከ 30 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ የሲርሆሲስ በሽታ ይያዛሉ፡፡

የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የመተላለፊያ መንገዶች

-የተበከሉ የሕክምና መርፌዎች ወይም መሣሪያዎች
-ከተዛማች ለጋሽ ደም መውሰድ
-በስራ ላይ የደም መጋለጥ (የመርፌ ጉዳት)
-በበሽታው ከተያዘች እናት መወለድ;
-የእንሽርት ውሀ ለረጅም ጊዜ መፍሰስ
-በበሽታው ከተያዙ አጋሮችጋር ልቅ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ
√በንቅሳት እና አካል መበሳት
√በሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የተበከሉ መሳሪያዎች መጠቀም ናቸው ።

የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ህመም ምልክቶች

አብዛኛዎቹ በአጣዳፊም ሆነ ሥር በሰደደ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የተጠቁ ታካሚዎች ምንም ምልክት ላይኖራቸው ይችላል፡፡

የአጣዳፊ ሄፓታይተስ ሲ ምልክቶች

-ማቅለሽለሽ፣
-ሽንት መጥቆር፣
-የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም፣
-መጠነኛ የሆነ ትኩሳት፣
-ብርድብርድ ማለት፣
-የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣
-ሰውነትን ማሳከክ፣
-የጡንቻ እና የመገጣጠሚያ ህመም፣
-የስሜት መረበሽ ሊኖራቸው ይችላል።
አጣዳፊ ሕመም አብዛኛውን ጊዜከ 2 እስከ 12 ሳምንታት ይቆያል፡፡

ሥር የሰደደ የሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክቶች?

√ድካም የተለመደ ምልክት ነው.
አንዳንዴ ማቅለሽለሽ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣የጡንቻ እና መገጣጠሚያ ህመም፣ክብደት መቀነስ
ምልክቶቹ እንደ ድብርት ካሉ ሌሎች በሽታዎች ጋር ስለሚመሳሰሉ ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ::

ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ህክምናው

√ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ከሰውነታችን በመድሀኒት መጥፋት የሚችል (curable) ህመም ሲሆን መድሀኒቶችን በአብዛኛው ለ12 ሳምንታት በመውሰድ መታከም ይቻላል፡፡

ለሄፐታይተስ ቢ እና ሲ ቫይረስ ምርመራ ቅድሚያ መመርመር የሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፤
√የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ ልምምዶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ በሚሆኑባቸው ቦታዎች
√ህክምና የተደረገላቸው ሰዎች
√ነፍሰጡር እናቶች
√ከሄፐታይተስ ቢ ወይም ከሄፐታይተስ ሲ ከተያዙ እናቶች የተወለዱ ልጆች
√ኤች.አይ.ቪ.በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች
√የጤና ባለሙያዎች
√ደም ወይም የደም ተዋጽኦ የተሰጣቸው ሰዎች
√የህግ ታራሚዎች
√ቤተሰብ ወይም የትዳር አጋር ህመሙ ካለባቸው
√በወሲብ ስራ የሚተዳደሩ ሰዎች
√በርካታ የወሲብ አጋሮች ያለው/ላት ወይም የአባላዘር በሽታ ያለበት/የታከመ ሰው
√የኩላሊት እጥበት ላይ ያሉ ታካሚዎች
8
የበሽታ መከላከያ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች?

የሄፐታይተስ ቢ ሆነ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ህክምና በኢትዮጵያ በተወሰኑ የመንግስት ሆስፒታሎች የሚሰጥ ሲሆን ምርመራውን አድርጎ ቫይረሱ የተገኘበት ሰው ወደ ሆስፒታሎች በመምጣት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላል።

መልካም ቀን ☕️
#share
8🔥2👏1
አንዲት ነፍሰጡር እናት የቅድመ-ወሊድ ቫይታሚኖችን (Prenatal Vitamins) እንዴት መውሰድ አለባት?

1. የቅድመ-ወሊድ ቫይታሚን መቼ መጀመር አለበት?

👍ከእርግዝና በፊት፦ የተሻለው ጊዜ እርግዝና ከመከሰቱ ከ2 እስከ 3 ወራት በፊት መጀመር ነው። ይህም በፅንሱ ላይ የሚከሰቱ የነርቭ እና የአከርካሪ አጥንት ችግሮችን (Neural tube defects) ለመከላከል ይረዳል።

👍 እርግዝና እንደታወቀ፦ አስቀድመው ካልጀመሩ፣ እርግዝና መኖሩን ካወቁበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ መውሰድ መጀመር አለብዎት።

👍 በእርግዝና ወቅት ሁሉ፦ ቫይታሚኖቹን በእርግዝና ዘመን ሁሉ እስከ መውለጃ ቀን ድረስ መቀጠል ያስፈልጋል።

2. ምን ዓይነት ቅድመ-ወሊድ ቫይታሚን(prenatal) መውሰድ አለባት? ( የምትወስጂውን prenatal ጀርባውን ተመልከቺ)

💊Folic Acid ፦ በቀን 400 mcg
💊 Iron ፦ 27 mg :- ለደም ማነስ መከላከያ እና ለፅንሱ እድገት
💊 Calcium 1000-1300mg , Vitamin D 600IU(15mcg) ፦ ለፅንሱ አጥንት እና ጥርስ ጥንካሬ።
💊 Iodine ፦ 150mcg - ለፅንሱ የአንጎል እድገት
💊 Omega 3 DHA - 200-300mcg - ለፅንሱ የአንጎል እድገት

3. Prenatal እንዴት መውሰድ ይገባል?

👉 በየቀኑ፦ እስከ ወሊድ ድረስ
👉 ከምግብ ጋር፦ ሆድ ላይ መጠነኛ መረበሽ እንዳያመጣ
👉 ከበቂ ውሃ ጋር

4. ቀላል የጎንዮሽ ጉዳቶች ሲያጋጥሙ ምን ማድረግ አለብን?

🫴 የማቅለሽለሽ ስሜት
ቫይታሚኑን ማታ ከመተኛት በፊት መውሰድ ወይም ከቀላል ምግብ ጋር መውሰድ ማቅለሽለሽን ይቀንሳል

🫴 የሆድ ድርቀት
ብዙ ውሃ መጠጣት፣ ፋይበር ያላቸውን ምግቦች (አትክልትና ፍራፍሬ) ማዘውተር እና መጠነኛ እንቅስቃሴ ማድረግ።

🫴 የቫይታሚኑን አይነት መቀየር

🫴 የሚወሰድበትን ሰዓት መቀየር

ዶ/ር ዳዊት መስፍን: የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት
7👍3💯3🔥2
ይህ ታሪክ የሚጀምረው ከአመታት በፊት በአዲስ አበባ በ Mother Teresa's Missionaries of Charity ውስጥ ነው።
​መስፍን በወቅቱ በልብ ህመም ምክንያት ለሞት ተቃርቦ የነበረ ምስኪን ታዳጊ ነበር። ሆኖም ግን፣ በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን ህይወት የታደገውና ደግነቱ በዓለም የታወቀው አሜሪካዊው ዶክተር ሪክ ሆድስ (Dr. Rick Hodes) መስፍን ላይ ተስፋ አልቆረጠም ነበር። ሪክ መስፍን ወደ አሜሪካ አትላንታ ሄዶ የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲያገኝ በማድረግ ህይወቱን ከሞት አፋፍ መለሰው።
​ነገሩ የሚገርመው እዚህ ጋር ነው! መስፍን ከህክምናው በኋላ በሪክ ሆድስ ድጋፍና ምክር ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ፤ ዛሬ እሱም እንደ ሪክ ሆድስ ጎበዝ የቀዶ ጥገና ሀኪም ለመሆን በቅቷል። አሁን በያዝነው Jan 2026፣ መስፍን እና ህይወቱን የታደገው ዶክተር ሪክ ሆድስ በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድነት ሆነው ለምስኪን ህፃናት ቀዶ ጥገና እያደረጉ ይገኛሉ።
​መስፍን በአንድ ወቅት ራሱ በታካሚነት የተረገጠበትን የቀዶ ጥገና ክፍል፤ ዛሬ ደግሞ እንደ ሪክ ሆድስ የሌሎችን ህይወት ለመታደግ ሰርጅን ሆኖ ሲገባ ማየት እጅግ አስደናቂ ነው! የዚህ ወጣት ታሪክ ውለታን መመለስ እና ለሰው ልጆች መድረስ ምን ያህል ታላቅነት እንደሆነ ያስተምረናል።
​ለካስ ደግነት እንደ ዘር ነው፤ ዛሬ የተከልከው ነገር ነገ ፍሬ ሆኖ አንተን ራሱ ይረዳሃል! ሪክ ሆድስ መስፍንን አዳነ፤ ዛሬ መስፍን ደግሞ ሪክ ሆድስን እያገዘ ሌሎችን እያዳነ ነው።
​ለሰው ልጅ ደግነት ይኑረን!
22👍3🔥2🙏2
Health comes first. The rest follows. Stay healthy.
5👍4🔥1
የረመዳን ፆምን የማያበላሹ የህክምና ተግባራት

1, የአይን ጠብታና የጆሮ ጠብታ መድሀኒቶች ፆምን አያበላሹም።

2, የአስም በሽተኞች የሚነፋ መድሃኒታቸውን (Salbutamol puff) እየፆሙ ቢወስዱ ችግር የለውም።

3, ጥርስን ማስነቀል ወይም ጥርስን ማስሞላት ፆምን አያጠፋም።

4, በምላስ ስር የሚደረጉ ኪኒኖች: የልብ በሽታን (MI) ለማከም ... ለሌሎችም በሽታዎች የሚረዱ መድሀኒቶች እስካልተዋጡ ድረስ ፆምን አያበላሹም።

5, ፆመኛ ሰው የደም ምርመራ ለማስደረግ ብሎ ደሙን ቢሰጥ ፆሙ አይፈርስም።

6, በደምስር (IV) ወይም IM የሚሰጡ ምግብን የማይተኩ መድሀኒቶች (ማስታገሻዎች ፣ ክትባቶች ፣ Antibiotics) እንዲሁም ሲቲስካን (CT Scan) ወይም MRI ለመነሳት በደምስር የሚሰጡ መድሀኒቶች (Intravenous contrast) ፆምን አያበላሹም።

7, በበሽታ ወይም በማንኛውም ምክንያት ሳያውቁ ማስታወክ ፆምን አያጠፋም።

8, ሂጃማ (ዋግምት) ፆምን ያበላሻል ወይስ አያበላሽም በሚሉት ሀሳቦች በዑለማዎች (በዲን አዋቂዎች) መካከል ብዙ ሀሳቦች የተሰጠበት ሲሆን ለመጠንቀቅ ያክል በፆም ሰዓታት ዋግምት ከመደረግ ብንቆጠብ የተሻለ ነው። የሂጃማ (የዋግምት) ድንጋጌ በዘመናዊ የህክምና መንገድ ለምንጠቀመው Phelbotomy ይውላል።

9, ነስር ያለበት ሰው በብዛት እንኳን ደም ቢፈሰው ፆሙ አይበላሽም። እየፆመ ያለ ሰው በአደጋ ወይም በሌላ ምክንያት በብዛት ደም ቢፈሰው ፆሙ ላይ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ከታመመና ከደከመ ፆሙን አጥፍቶ መመገብ ይችላል።

10, በጤናዋ ላይ ችግር የማያስከትልባት ከሆነ አንዲት ሴት የወር አበባ የሚያስቆም መድሀኒት ተጠቅማ ረመዳንን ብትፆም ችግር የለውም። አንዲት ሴት የረመዳን ቀናት ፆሞችን ፣ ለይለቱል ቀድር ፣ በሀጅና ዑምራ ላይ ያሉ አንዳንድ ተግባራት የመሳሰሉትን ዒባዳዎች እንዳያመልጧት የወር አበባን የሚያስቆም መድሀኒት መጠቀምዋ ጤናዋ ላይ ችግር የማይስከትል ከሆነ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን መድሀኒቶቹ የጎኒዮሽ ጉዳት ስላላቸውና ሴቷ ራሷን ተከሉፍ (ራሷን ማስገደድ) ውስጥ ባታስገባ የተሻለ ይሆናል። ኪኒን ተጠቅማ ግን ብትፆምና ዒባዳዎችን ብትተገብር ተቀባይነት አለው።

11, በሴት ማህፀን ወይም ብልት ውስጥ የሚከተቱ የህክምና መሳሪያዎች ፣ ምርመራዎች ፣ መድሀኒቶችና የእርግዝና መከላከያዎች ፆምን አያበላሹም።

[ እነዚህ የረመዳን ፆምን የሚመለከቱ የህክምና ብያኔዎች ቁርዓንና ሀዲስን ብሎም የአራቱ አዒማዎች መዝሀቦችን ተመርኩዘው በዘመናችን ዑለማዎች (የዲን ዓዋቂዎች) የተሰጡና የተጠናቀሩ ናቸው።]

ሼር ያድርጉት ያላወቁትን ያሳውቁ
ዶ/ር መቅሱድ ሸምሱ
#ረመዳን_የእዝነት_ወር #ረመዳን_ሙባረክ
👍75🔥2
Listen to health experts - not influencers or political figures - when making decisions about your health, including vaccination.

You wouldn’t board a plane flown by someone with no training, just because they’re popular or hold office. You’d choose a qualified pilot because the stakes are too high. The same principle applies to your health.

While the consequences of poor health decisions may not be as immediate or dramatic as an air accident, they can still be serious and long-lasting. Relying on trained health professionals and scientific experts helps ensure that your choices are based on evidence, not opinion or popularity.
Tedros Adhanom Ghebreyesus
4👍1🔥1
"ሰላም ዶክተር ልጄ የ1 ዓመቱ ነው። ፎቶ ላይ እንደሚታየው በአንገቱ ፊት ለፊት ላይ እብጠት አለው። ይህ ምን ሊሆን ይችላል? ስለዚህ ጉዳይ በደንብ ብታብራራልኝ!"
(የወላጅ ጥያቄ)

🌡ውድ ጠያቂያችን ስለ ጥያቄው በጣም እናመሰግናለን!

🌡ይህ ችግር በጣም የተለመደ እና በየቀኑ ከምናያቸው ችግሮች መካከል አንዱ ነው! ይህም ችግር Thyroglossal Duct Cyst ይባላል!

🌡በልጆች በአንገት ላይ የላይኛው ወይም መካከለኛው የፊት ክፍል ላይ ህመም የማያሳይ እብጠት ሲሆን አንዳንዴም ፈሳሽ ሊፈነዳ እና ፊስቱላ ሊፈጥር የሚችል ችግር ነው።

🌡ከአፈጣጠር ጋር የተያያዘ ችግር ሲሆን የካንሰርነት ባህሪ የሌለው እብጠት ነው።

ጥያቄ-1፡ Thyroglossal Duct cyst ምንድን ነው?

🌡አንድ ጽንስ እያደገ ሲሄድ የታይሮይድ ዕጢ ከምላስ አካባቢ በመነሳት የታችኛው የአንገት ክፍል መውረድ አለበት።

🌡የሚወርድበት መንገድ ብዙውን ጊዜ ምንም ዱካ አይተውም። መዘጋት አለበት!

🌡 የዚህ መንገድ ትንሽ ክፍል ከቀረ በፈሳሽ ሊሞላና የታይሮግሎሳል ቱቦ ሲስት (Thyroglossal Duct Cyst) ሊፈጥር ይችላል።

ጥያቄ-2፡- ለምን አሁን ታዬ? ለምን እንደ ተወለደ አልታየም?

🌡ክፍተተቱ ልጆች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ይኖራል። ከላይ በአይናችን ላናየው እንችላለን!

🌡ነገር ግን ከጊዜ በኋላ ብዙውን ጊዜ ከ1-5 ዓመት አካባቢ ፣ በተለይም ከጉንፋን ወይም ከጉሮሮ ኢንፌክሽን በኋላ ሊታወቅ ይችላል፣ ይህም እብጠቱን ሊያባብሰው ይችላል።

ጥያቄ -3 ፡- አደገኛ ነው? ካንሰርነት ባህሪ ይኖረው ይሆን?

🌡ያን ያክል አደገኛ የሚባል ችግር አይደለም።

🌡በልጆች ላይ ይህ ሁኔታ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል የካንሰርነት ባህሪ ያለው አይደለም።

🌡ለወደፊቱ ከእዚህ እብጠት የሚነሳ ካንሰር እጅግ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ሲሆን ብዙውን ጊዜ በአዋቂዎች ላይ እንጂ በትናንሽ ልጆች ላይ አይታይም።

ጥያቄ-4 ፡- ይህ እብጠት መኖር አለመኖሩን እንዴት ይታወቃል?

🌡 በአካል ምርመራ በምናደርግበት ጊዜ እንደሚከተለው ሆኖ ሊታይ ይችላል!

💊💊በአንገታቸው መሃል ላይ ለስላሳ፣ ክብ እብጠት

💊💊 ሲውጡ ወይም ምላሳቸውን ወደ ውጭ ሲያወጡ ወደ ላይ እና ወደ ታች ሲንቀሳቀስ ይታያል!

🌡🌡ብዙውን ጊዜ ኢንፌክሽን ካልፈጠረ ስቃይ እና ህመም የለውም

ጥያቄ -5 ፡ የልጄን መተንፈስ፣ አመጋገብ ወይም ንግግር ላይ ተጽዕኖ ያደርስበት ይሆን?

🌡አብዛኛውን ጊዜ ይህን አይነት ችግር አያስከትልም።

🌡እነዚህ ችግሮች የሚከሰቱት ሲስቱ ከተበከለ( if it is superinfected) ወይም በጣም ትልቅ ከሆነ ብቻ ነው።

ጥያቄ-6፥ ተጨማሪ ምርመራዎች ያስፈልጉት ይሆን?

🌡አብዛኛውን ጊዜ የአንገት አልትራሳውንድ ምርመራ በቂ ነው።
🌡 የብጠት መኖሩን እና ከሌሎች እብጠት ምክንያቶች መለየት ይቻላል!
🌡ሌላው የታይሮይድ ዕጢ በተለመደው ቦታ ላይ መሆኑን ያረጋግጣል።

🌡 የደም ምርመራ እምብዛም አያስፈልግም።

ጥያቄ -7፡- ህክምና ያስፈልገዋል?

🌡አዎ!
🌡 የመጨረሻው ሕክምና ቀዶ ጥገና ነው!
🌡 ቀዶ ጥገናው Sistrunk Procedure ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም እብጠቱን ከስሩ እና አብሮ የተያያዘውን መካከለኛ የhyoid አጥንት ክፍል የማስወገድ ሂደት ነው!
🌡ይህም እንደገና እንዳይከሰት ይከላከላል።

🌡ቀዶ ጥገናው ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው ህፃኑ ጤናማ እና ምንም አይነት ኢንፌክሽን በሌለበት ጊዜ መሆን ይኖርበታል ።

ጥያቄ - 8፡ ባይታከም ምን ሊያስከትል ይችላል?

🌡ካልታከመ የሚከተሉትን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል፡

🩺በተደጋጋሚ ኢንፌክሽን መፍጠር
🩺ሊፈነዳ ወይም ፊስቱላ ሊፈጥር ይችላል!
🩺ከጊዜ በኃላ ከዚህ እብጠት ካንሰር ሊነሳ ይችላል!

🌡ስለዚህ እብጠቱ ህመም የሌለው ቢሆንም እንኳ በቀዶ ጥገና ማስወገድ ይመከራል።

ጥያቄ - 9፡- ቀዶ ጥገናው ለአንድ ዓመት ልጅ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

🌡 አዎ!
🌡ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ከተሰራ በጣም የተለመደ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የህፃናት ቀዶ ጥገና አይነት ነው።

🌡ልጆች ከዚህ ህክምና በኋላ በፍጥነት በማገገም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።

ጥያቄ- 10 ፡- ከቀዶ ጥገና በኋላ ተመልሶ ይመጣል ወይ?

🌡ቀዶ ጥገናው በትክክል ከተደረገ በድጋሚ የመምጣት እድሉ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ነው።

💊በመጨረሻም ውድ ጠያቂያችን ይህ ችግር በልጆች ላይ የተለመደና ሊታከም የሚችል ችግር ሲሆን በተገቢው ህክምና መስተካክል የሚችል እንደሆን መረዳት ያስፈልጋል።

❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ወላጆች እንዲደርስ በቅንነት #share ያድርጉት ‼️🙏

📘በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ጥያቄ መጠየቅ ከፈለጉ ወይም በሌሎች ጉዳዬች በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።
👇👇👇👇👇👇

📲+251911441651

🌡🙏ሌሎች መረጃዎች ሲለቀቁ እንዲደርሷችሁ የtelegram አድራሻችንን ይቀላቀሉ!

http://t.me/DrSaleamlakT

ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!

አዘጋጅ :-

ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር (YK12HMC)

Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at YK12HMC) ,Addis Ababa, Ethiopia
7👍1🔥1
በማህበራዊ ድህረ ገፅ ስለ ህመማቸው ብዙ ሲዘዋወር ያየናችው እናት እጅግ ከባድ በሆነ እጢ ለረጅም አመት ሲሰቃዩ የነበሩ እናት ከነበረባቸው ዕጢ ስኬታማ የሆነ ቀዶ ህክምና በፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተከናውኗል።

ቀዶ ጥገናው በ27/06/2018 ዓ.ም ተሰርቶላቸው በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር ካሳው ENT Specialist ከነ ረዚደንት ሀኪሞቹ ክብር ይስጥልን
በስረው ላይ የተሳተፋችሁ የፈለገ ህይወት ሆስፒታል OR ቲም በሙሉ እናመሰግናለን፡፡
9👍2🔥1
Do you all still remember the Grade 9 biology, chemistry, and physics textbooks? አሁን ቀይረውት ካልሆነ ያው ሶስት መንግሥት ባይናችን ስር አለፈ 😂 but in the Ethiopian school curriculum. Honestly, I think that was one of the best things that happened to me in school. I wasn’t a bad student 😌 I was actually a good student😅 but before that, most of the time we were learning about scientists with unfamiliar names from Greece, Germany, Russia, or America ስማቸውን ለማስታወስ መከራ ስንበላ.

እና ለመጀመሪያ ግዜ those textbooks introduced Ethiopian scientists. ታሪካቸው ከየት እንደተነሱ ብዙም እሩቅ አይደለም እና their names felt familiar, and it was exciting to read about them. It gave you hope. It made you feel like maybe you could also become someone like them one day.

I remember the first time I read about Tewolde Berhan Gebre Egziabher. He became my all-time favorite. When I think about Ethiopia, he is one of the first people who comes to my mind. In a way, I feel like he represents Ethiopia for me 🇪🇹

There were also Gebisa Ejeta and Beyene Petros. I remember being confused when I saw the name Beyene Petros in the textbook ደሞ ምን አመጣው እዚ ብዬ ምክያቱም I knew his name from the elections ከ 97ቱ, so I thought he was only a politician. I asked my biology teacher about it “በየነ ጴጥሮስ ያ የምናውቀው ብዪ “ እንዴት እንደሳቀች😂, and she told me that he was actually a respected Ethiopian scientist and professor as well. That moment changed how I looked at people in politics የተማሩም ሊሆኑ ይችላሉ ለካ የምር በፊት የተማሩ ሰዎች ፖለቲከኛ የሚሆኑ አይመስለኝም ነበር😂

My biology teacher was amazing. Her name was Tarike, ስሟ ራሱ ደስ አይልም ታሪኬ🥰 and she is still one of my favorite teachers. One thing about me is that I have always loved women teachers 💅🏼Even when I didn’t like a subject (but biology was my favorite), if the teacher was a woman, I somehow understood everything better. They have their own way of teaching እና ሁሌም ይገርመኛል.

She studied biology at Jimma University top scorer 🥰, and she once told us that she had met Gebisa Ejeta. አስመራቂዋም ነበር. I was so shocked and excited when she said that. I remember thinking how lucky she was to meet someone like him. At that time, he felt like a hero to me because of his work on sorghum and agriculture ከረሀብ ነው የታደገን::. ፕሮፌሰር ያለም ፀሀይ መኮንን ሴት ማግኘት እና ማየት ብርቅ ነበር ደሞም ብርቅዬ ነች🥰🇪🇹 ከሩጫ ውጪም አለም ያውቀናል ለካ ያስባለችኝ

ብቻ those textbooks and those stories stayed with me for a long time. Even later, when I joined engineering school and became interested in architecture, I started thinking more about vernacular architecture buildings made with local materials that do not harm the environment. I became very interested in environmentally responsible design.

Part of that inspiration came from my father, but a big part of it also came from reading about Tewolde Berhan Gebre Egziabher. His ideas about respecting nature made a deep impression on me. After that, I started to think differently about the relationship between humans and the environment.

እና I proposed that idea to my professor about local designs and how we could use them without affecting our environment. እዚህ ላይ there was this amazing lecturer I don’t remember his name. He taught us only one course, but he encouraged us to design buildings that are not against the environment. I just wanted to mention him. ብቻ ያ ሰውዬ my proffesor said ተይው ይሄን የመሃይም ወሬ. He didn’t actually say those exact words, but you know… he told me it was not going to work. So we ended up doing a project on health and safety in construction areas as a group.

ለማንኛውም looking back, those Grade 9 textbooks were really special. They made science feel closer to us. They showed us that Ethiopian scientists exist and that their work matters. And for a student, that can make a big difference.
ዛሬ ምን ፈረደብን እንዳትሉ 😂
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር ለማንኛውም 😌🇪🇹
5👏2🔥1
It’s not just weight; sometimes, it’s Lipedema. 🎗️
Many people struggle with stubborn fat in their legs or arms that just won't go away with diet and exercise. Often, they are told to "just work harder," but the reality could be a chronic condition called Lipedema.
As you can see in the comparison:
Normal Fat: Distributed evenly and responds to lifestyle changes.
Lipedema Fat: Involves painful nodules, fluid retention (edema), inflammation, and fibrosis (scarring of the tissue).
Lipedema is a medical condition, not a lack of willpower. Understanding the difference is the first step toward the right treatment and self-compassion.
Have you or someone you know experienced these symptoms? Let’s spread awareness and stop the stigma.
3👍1🔥1
#Match2026 #Congratulations
The Discipline Behind the Dream: Ethiopian Doctors on the Road to the USMLE Match

Ethiopian doctors are known for their resilience and determination. Many have made remarkable sacrifices, saving from limited resources, investing close to a million birr, and dedicating their time, energy, and focus to prepare for the USMLE and secure a residency match.

I would like to sincerely congratulate the 2026 USMLE Matched applicants who have achieved this milestone after such a demanding journey. For those still in Ethiopia, I truly wish you a smooth and successful visa process without obstacles.

This path is not easy, but it remains a powerful source of motivation for others walking the same road. Once again, congratulations. 👏👏

[Tag your friends and congratulate them]

Dr. Tewodros Ayenew
MD, Assistant Professor of Internal Medicine
👍21
ወደ ባህል ሀኪም ሪፈር ፅፌ አውቃለሁ
========================
ጠቅላላ ሀኪም እያለሁ ቤኒሻንጉል ክልል የህንድ ድርጅት ውስጥ እሰራ ነበር። አካባቢው ላይ ብዙ ተሳቢና ተራማጅ እንስሳት ነበሩ። ከእነዚህ መካከል አንዱ ጊንጥ ነው። ህክምና ት/ቤት እያለሁ ጊንጥ የነደፈውን ሰው እንዴት እንደሚታከም የተማርን አይመስለኝም።

የጊንጥ ንድፊያ (Scorpion sting) እጅግ በጣም ያማል። የንብ ወይም የተርብ ንድፊያ ከጊንጥ ጋር ሲወዳደር እንደመዳሰስ ነው። የህንዶቹ ሀላፊ ጊንጥ ነድፎት እነጮኸ መጣ። Up to date መፅሀፍ ከፍቼ ህክምናውን አነበብኩ። አላርጂክ ሆኖበት ሰውነቱ ካበጠ ወይም የአየር ቱቦ ከተዘጋ ከባድ ነው። አለበለዚያ ግን የተነደፈበትን ቦታ በሳሙናና በውሀ አጥቦ ቀዝቃዛ ነገር እንዲያደርግበት መምከርና የህመም ማስታገሻ መስጠት ነው።

ማስታገሻ ብሰጠውም ህመሙ አልቀነሰለትም። በአካባቢው የባህል ሀኪም እንዳሉ ሰማን። ህንዱ "መሄድ እፈልጋለሁ" አለ። ተስማምቼ ወደ ባህል ሀኪሟ መሄድ እንደሚችል ነገርኩት። ህክምናውን ለማየት እኔም አብሬው መኪናው ላይ ወጣሁ።

የባህል ሀኪሟ ጋር ስንሄድ እንደመፋቂያ ያለ እንጨት ጉድጓድ ነገር ውስጥ እያሽከረከሩ ሲግል ጊንጥ የነደፈው ዙሪያ ሰውነቱን ተኮሱት። ስንመለስ ህንዱ "ትንሽ ቀንሶልኛል" አለ። የተካሄደው ህክምና ሌላ ህመም በመፍጠር ከዋነኛው ህመም የማዘናጋት (Distraction therapy for pain) ይሁን አይሁን አላውቅም።

ወደ ክሊኒኩ ተመልሰን ስንገባ ህንዶቹ ተሰብስበዋል። እዛ የሚሰሩት ህንዶች አለቃ በጣም ነው የሚፈሩት። አለቃቸውን ለማፅናናት የተለያየ ነገር መናገር ጀመሩ።

ወታደር ቤት ውስጥ የ'ሰር ሳንድዊች' የሚባል አነጋገር አለ። መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ 'ሰር' ማለት ነው። ለምሳሌ 'ሰር የስ ሰር' (Sir, yes sir) እዛ የነበሩት ህንዶች ግን አለቃቸውን ስለሚፈሩት ሲናገሩ የሰር ፍርፍር ነበር። አንዱ እየተርበተበተ አለቃውን ለማፅናናት "ሰር ሱኒል ሰር ዶንት ዎሪ ሰር። ስኮርፒዮን ሰር ኢዝ ፔንፉል ፈርስት ታይም ሰር። በት ኔክት ታይም ሰር ኢት ዊል ቢ ሌስ ፔንፉል ሰር" አለ።

ሚስተር ሱኒል በንዴት ጥርሱን ነክሶ አፍጦበት "ጭራሽ ኔክስት ታይም ትመኝልኛለህ?" አለው።
9😁2👍1🔥1
Health is not a luxury - it is a fundamental human right.
3🔥1