Yop Poem ️
7.71K subscribers
55 photos
5 videos
25 files
43 links
፨Yop Poem
አዳዲስ እና የቆዩ ግጥሞችና ወጎችን በቀላሉ ያገኙበታል። 🤲
እርስዎም የግጥም ተሰጥዖ ካልዎት መልቀቅ ይችላሉ።👐
Our main channale :- @Utophiainfo

ቻናላችንን #share ያድርጉ👍

for promo & cross 👉 @Yared642
Download Telegram
አንድ ሰው

እሁድ ማለዳ ላይ...
ገላዋን ታጠበች
ልብሶቿን ለበሰች
ሽቶ ተርከፍክፋ ከጎዳና ወጣች

በመንገድ ስትጓዝ...

የፀጉሯን መዘናፈል የጡቷን መኮፈስ
የረጨችው ሽቶ ካደባባይ ሲነፍስ
እሷን ያየ ሁሉ ወንዱ ተጨነቀ
በደም በውበቷ እየተደነቀ
ያስተዋላት ሁሉ ዓይኑ መንገድ ሳተ
ከዳሌ ከጡቷ ሔደ ተከተተ።

ከቦታው ስትደርስ...

ወዳጇ አልመጣም
ሰአት አልጠበቀም
ለውበቷ አልሳሳም።
ሠዓት ገላመጠች
                  ፊት ኋላዋን ቃኘች
ማኪያቶ ደገመች
ዙርያዋ ባለው ሰው እጅግ ተናደደች
እልህ ልቧን ሞላ
ፊቷ ከደም ቀላ
የሚመኛት ሁሉም
           ወንዶቹ በሞላ
                   የርሷ ልቧ ሌላ።

ሠዓቱ ረፈደ...

የጠዋት ደስታዋ ከሷ ተሰደደ
አይኖቿ ረጠቡ
አንድ ሰው አሰቡ
አንድ ሰው ተራቡ።

አንድ ሰው ነበረ እርሷን የናፈቀው
ያን ያልመጣውን ሰው
ዓይኗ የተራበው

(ኤፍሬም ስዩም)


http://T.me/Newetmusic
ሌላውን አልወቅስም
ሌላውን አልከስም
በሤራ በሥራ ፣ ቢፋጠን ውርደቴ
በየደረስኩበት ፣ ቢደገስም ሞቴ
አንድ አለመሆን ነው ፣ ዋነኛ ጠላቴ!!!

belay bekele weya

http://T.me/Newetmusic
ቢጠፋ ብርሀን
ሰማይ እና ምድር ፣ ቢጋጠሙ አንድላይ
ፀሀይዋም ብትጠልቅ ፣ እኔ አንችን እንዳላይ
ጨረቃም ብትጠፋ ፣ ከኮከቦች ጋራ
አለም ብትጨልም ፣ ቢታጣ ሚያበራ
የትም ብትሆኝ ፣ ከማይታወቅ ስፍራ
በምንም ሁኔታ ፣ አለው ካንቺ ጋራ
ስለዚህ ፍቅሬ ሆይ ፣ እንዳትፈሪ አደራ


ያሬድ ግርማ

http://T.me/Newetmusic
አሁን እኔ ብሞት ፣ ከኔ ምን ይቀራል?
ስኖር "ክፉ" ያለኝ
"ደግ ሰው ነበረ " ፣ እያለ ያወራል።
።።።
"እሱ ሰው አይደለም" ፣ ሰይጣን ነው መሠሪ"
ሲለኝ የከረመ ፣
"መልካም ሰው ነበረ ፣ መልአክ መሥሎ ኗሪ
ብሎ ቀብሬ ላይ ፣ እንባውን ይዘራል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የተናቀ ፣ ሲሞት ይከበራል ።
* * * *
የሚጠላኝ ሁላ
ተወዳጅነቴን ፣ ቀብሬ ላይ ያወሳል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የሚነቀፍ ፣ ሲሞት ይወደሳል
ሲኖር የተረሳ ፣ ሲሞት ይታወሳል!!!
።።።

Belay bekele weya


http://T.me/Newetmusic
ላ’ንዲት የገጠር ሴት…



ስትፈጭ የኖረች ሴት፣
መጁ በመጠኗ፣ ወፍጮውም በልኳ፣
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ !!
.
.
አስባው አታውቅም…
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ከና’ቷ ሆድ ወጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ለባሏ ተሰጠች……
.
ተዚያን ቀን ጀምራ፣
ተዚያን ቀን ጀምሮ፣
ድንግል ድንጋይ ወቅራ፣
ትፈጫለች ሽሮ……
.
.
አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
አታውቅም፣
ሹማምንት በ’ሷ ስም፣ ምን እንደሚሠሩ፣
አነሳኹት ‘ንጂ፣ እኔም ለነገሩ፣
ፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ፣
ምን ይጠቅማትና ጓያዋን ለማድቀቅ…
.
.
ከቶ ማንም የለ, አበባ ‘ሚሰጣት፣
ከቶ ማንም የለ፣ ከተማ ‘ሚያወጣት፣
ከቶ ማንም የለ ፣ በዳንኪራ መላ፣ ወገቧን የሚያቅፋት፣
ልፋቷም፣ ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት……
እንደ ዓባይ ፏፏቴ፣
ሽሕ ዓመት ቢንጣለል፣
ቢጎርፍም ዱቄቱ፣
እንደ ሲኦል ወለል፣ ጫፍ የለውም ቋቱ !
.
.
ከዘመናት ባንዱ
መስተዋት ፊት ቆማ፣ በተወለወለው፣
ራሷን ለማዬት፣
ከጸጉራ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለዬት፣
ያኔ ይገባታል
የተሰጣት ዕጣ፣
ከማድቀቅ ቀጥሎ፣ መድቀቅ እንዲመጣ…
.
.
የመጅ አጋፋፏ - አምሳለ ሲሲፈስ፣
ከቋት ሥስት እንጅ፣ ሢሳይ አይታፈስ፣
ትቢያ ‘ሚተነብይ ዱቄት በዙሪያዋ፣
ከባርኔጣ አይሰፋም፣ የኑሮ ጣሪያዋ፣
.
.
‹‹ስትፈጭ የኖረች ሴት››
.
.
ይህ ነው መጠሪያዋ !!




Bewketu seyoum


http://T.me/Newetmusic
ሀይሌ  
ሰፊ እና ጠንካራ ፣ ባይኖረኝም ደረት
ምጋፋበት እንኳ ፣ ቢያንሰኝም ጉልበት
ጉልበት ሀይሉ ሆኖ ፣ ቢጫነኝ ጠንካራው
ከአንተ እና አንተ ውጭ ፣ የለም የማመልከው

Yared Girma

http://T.me/Newetmusic