Yismake Worku
20.9K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
#ቀን_ገንቢ
ምዕራፍ ፩: ክፍል ፩


የራስ ዋጋ
------------

በአንድ ሰሚናር ውስጥ ሁለት መቶና በላይ ሰዎች በታደሙበት ታዋቂው ንግግር አድረጊ ተጋብዞ በቦታው ተገኝቷል፡፡ ተናጋሪው ለለቱ ማስተላለፍ የፈለገውን መልዕክት ለማጠናከር ያግዘው ዘንድ ንግግሩን የጀመረው የሃምሣ ብር ኖት በእጁ ይዞ በማሳየት “ከመካከላችሁ ይህንን የሃምሣ ብር ኖት የሚፈልግ ማን ነው!?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ ታዳሚውም በተከታታይ ሁሉም እጁን አንድ ባንድ አወጣ፡፡ ተናገሪው ቀጠለ “ከመካከላችሁ ለአንዳችሁ መስጠት እፈልጋለሁ ነገር ግን ከዛ በፊት” አለና የሃምሳ ብር ኖቱን በእጁ በማፋተግ እንዲጨማተር ካደረገ በኋላ “አሁንስ የሚፈልገው ይኖራል!?” ሲል በድጋሜ ጥያቄ አቀረበ፡፡
አሁንም የታዳሚዎች እጅ እፈልጋለሁ በሚል ስሜት ተዘረጋ፡፡ በጣም ጥሩ አለ ተናገሪው እንደዚህ ባደርግስ ብሎ የሃምሣ ብር ኖቱን እግሩ ሥር ጥሎ በጫመው ምድሩ ጋር ካፋተገ በኋላ አሁን “እደምትመለከቱት በጣም ቆሽሿል:: ተጨማትሯልም:: አሁንስ ትትፈልጉታላችሁ!? አሁንም የፈላጊዎች እጅ በአንድነት ተነሳ፡፡ “ወገኖች አሁን በጣም ወሳኝና መሰረታዊ ትምህርት እንደቀሰማችሁ አምናለሁ፡፡ ምንም እንኳን ብሩ ላይ ማናቸውንም ነገር ባደርግበት፣ ባቆሽሸውም፣ ባጨማትረውም፤ ብሩን የራሳችሁ የማድረግ ፍላጎታችሁ እንዳለ ነው፡፡ አልቀነሰም፡፡ ምክንያቱም የብሩ ኖቱ ቢበሳቆልም ቢጎዳም እንደ ብርነቱ የሚሰጠውን ዋጋ ወይም ጠቀሜታ አልቀነሰበትምና፡፡ እስካሁንም ዋጋው ያው ሃመሳ ብር ነው፡፡” አላቸው፡፡

ብዙውን ጊዜ በሕይዎት ውጣውረድ በምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ፣ በሚፈጠሩት ክስተቶች መውደቅ መሰነሳቱ፤ መደቆሱ ያለና የሚኖር ነው፡፡ በተፈጠሩት የህይዎት ፈታኝ ክስቶቶች ዋጋ ያጣን ያህል ሊሰማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ምንም ይሁን ምን፣ ያለፍንበት የሕይዎት ጎዳና ምንም ያህል አባጣ ጎርባጣም ቢሆን እኛ ማለት እኛ ነንና የእኛነታችንን፣ የራሳችንን ዋጋ አናጣምም ማጣትም የለብንም ፡፡


#ሼር

@yismakeworku
ከ "ምሽቴ" ጋ

@yismakeworku
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 4 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፬
File Size: 24.7MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
#ቀን_ገንቢ
ምዕራፍ ፩ : ክፍል ፪


ሁለት ዘሮች
--------------


ሁለት ዘሮች ናቸው፡፡ በአካባቢው የተፈጠረ ንፋስ ከቅርፊታቸው ነጥሎ እያንሳፈፈ አጓጉዞ በላመ፣ በለሰለሰ አፈር ላይ ጎን ለጎን ቀላቀላቸው፡፡ ዘሮቹም ከለሰለሰ አፈር ላይ ማረፋቸውን በተረዱ ጊዜ በጉርብትና መንፈስ ውይይት ጀመሩ፡፡

አንደኛው ዘር፡ “በዚህ በእንደዚ ለመብቀን በተዘጋጀ ማሳ ላይ ሳርፍማ መብቀን እፈልጋለሁ፡፡ ሥሮቼንም ወደ ጥልቁ አፈር በመላክ፤ ቅርንጫፎቼን ከምድር በላይ ከፍ አድርጌ እንደ ባነር በመዘርጋት የበልግ ወራት መድረሱን፤ ልምላሜ መምጣቱን ማወጅ ይገባኛል፡፡ የጠዋቷን ፀሐይም የተፈጥሮ ስጦጣየን መመገብ ይገባኛል እፈልጋለሁም፡፡” ሲል ሀሳብን ለባልጀራው ሰነዘረለት፡፡ እናም በቅሎ ማደግ ጀመረ፡፡

ሁለተኛው ዘርም በፈንታው እንዲህ አለ፡ መጀመሪያ ሀሳቡን ህምምም.. ሲል በመደመም ጀመረ፡፡ “ስሬን ወደ ጥልቁ አፈር ብለቀው በዛ ጨለማ ውስጥ ምን እንደሚገጥመኝ ከየት አውቅና ነው! ጉንቁሎቼን ባጎነቁልስ የቀንድ አውጣ ምግብ መሆኔ አይደለምን! እንዲሁም ደግሞ አበቦቼን ባፈነድቃቸው ህፃናቶች ቆርጠው ምድር ላይ በመጣል መጫዎቻ ያደርጉኛል፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሁሉ የምጠበቅበት ምቹ ሁኔታ እስኪፈጠር መጠበቁ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም” ሲል የመብቀል የሕይወት ተልዕኮውን ገታው፡፡

ይህን ሀሳባቸውን ከተነጋገሩ ከሰዓታት በኋላ በአካባቢው ምግቧን ፍለጋ ምድርን ስትጭር የነበረች ዶሮ ለመብቀል ምቹ ሁኔታን ሲጠብቅ የነበረውን ዘር አገኘችና ተመገበችው፡፡ ሥራን ለመስራት የማይመጣን ምቹ ሁኔታን መተበቅ ስራ እንዳንሰራ ከማድረግ ውጪ የሚፈጥረው ፋይዳ የለውም፡፡ እንቅፋትም እስከመጨረሻው ስለማየውቅ በዓለማችን እስካሁን ተሰሩ ወሳይኝ የሚባሉ ስራዎች በሙሉ በችግር ውስጥ እንጅ በተደላደለ ሁኔታ እንደልሆነ አብዛኛው መረጃ ይናገራል፡፡ There is no ideal condition for everything we can do what we have to do even in adverse condition.

/ምስጋናው ግሸን/

#ሼር
@yismakeworku
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 5 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፭ / 5
File Size: 39.6MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
#ቀን_ገንቢ
ምዕራፍ ፩ : ክፍል ፫


የሰው ልጅ የልምምድ ውጤት ነው። በልምምድ እንጅ በመወለድ ብቻ ሰው መሆን አይችልም። ከማፍቀር እስከ መቆርቆር ይለማመዳል። ማፍቀርን ያህል ያህል ነገር እንኳ አውቆ አይወለድም። እርሱን ብቻ አይደለም፤ መጥላትን ሳይቀር ይለማመዳል። ከማወቅ እስከ መናቅ፣ ከመወለድ እስከ መታነቅ፤ ከመድቀቅ እስከማድቀቅ፤ ከመጋባት እስከ መፍታት፤ ከስንፈት እስከ ጥረት ... ከመርመጥመጥ እስከ መፈርጠጥ፣ ከቆመጥ እስከ ነፍጥ...ተለማምዶት እንጅ ተሰጥቶት አይደለም። ከክህደት እስከ እምነት ካልተለማመደ አይችልም።

ከራሱ ያገኘው ማንነት የለውም። ሁሉም በሂደት እና በልምምድ የመጣ ነው። መልኩን ቆላ ሲወርድና ደጋ ሲወጣ ይቀያየራል። ልቡን በየግድሙ ይጥላል። ቀልቡን መቋጠሪያ የለውም። በመለማመድ አሁን የደረሰበትን እንጅ ወደፊት የሚሄድበትን ማንም ሊያውቅ አይችልም።

~ከክቡር ድንጋይ መፅሀፍ የተወሰደ

@yismakeworku
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 6 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፮ / 6
File Size: 24.1MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
#ሼር ያደረገልን ትልቅ ተባባሪያችን ነው።

" #እባካችሁን_ከሞት_አድኑኝ😭😭😭"

ይህ ቆንጅዬ ወጣት #አማኑኤል_ጃዕፈር ይባላል!!ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ የኬሚካል ኢንጅነሪንግ 5ተኛ አመት ተማሪ ነው!!

ከዓመት በፊት ሰውነቱ ብርድ ብርድ ሲለው ለህክምና በተደጋጋሚ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል!አንዴ ብርድ ሌላ ጊዜ ኩላሊት እያሉት ከመድሀኒቱ ጋር ሳይገናኝ ስቃዩም በዝቶ በብዙ ተንከራቷል!!

አማን ህመሙ ሲብስበት ትምህርቱን አቋርጦ ወደ መቀሌ ቤተሰቦቹ ጋር ይሄዳል!የአጥንት ስፔሻሊስት
ዶ/ር ሲያየውም ህመሙ ከባድ እንደሆነና ካንሰር እንደያዘው ይነገረዋል😭
ብዙ ህልም ላለው፣ቶሎ ተመርቄ እናቴን እጦራለሁ ለሚል ወጣት ይህ ልብ የሚሰብር መርዶ ነው!!

ሪፈር ወደ አዲስ አበባ ተፅፎለት በጦርነቱ ምክንያት መንገድ ዝግ ስለሆነ ህይወቱን ለማዳን በረሀ አቋርጦ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለማረጋገጥ ሲሞክር "በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ውጪ ሄደህ ካልታከምክ ህይወትህ አደጋ ላይ ነው"ብለውት ህክምና ማረጋገጫም ሰጥተውታል!
ወንድማችን ታይላንድ ሄዶ ለመታከም ደግሞ 2,500,000ብር ያስፈልገዋል!!
እናንተ ደጋጎች እባካችሁን #እንድረስለት🙏
ምንም ማድረግ ባንችል #ሼር በማድረግ እየፀለይን
ለብዙዎች እናድርስለት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት
#አካወንት
1000183135458-አማኑኤል

#ስልክ
0930625559-አማኑኤል
0928936657-ዘነቡ

#ጎፈንድሚ
https://www.gofundme.com/f/support-amanuel-jaefer?utm_source=facebook&utm_medium=social&utm_campaign=p_cp+share-sheet

#SHARE #ሼር ያደረገልን ትልቅ ትብብር ነው።
ዛሬ ልደቴ ነው። መልካም የልደት በዓል ለኔ፣ መልካም አዲስ አመት ለእናንተ

@yismakeworku
ከቆንጆዋ ባለቤቴ ሜላት ለኔ የተላከ...


እታለም ሁሌ ማሩን ስታወራው ሞልታ አታየውም እንባዋ ይቀድማል። "የትኛው ጉኛዬ ልወሽቅህ? ከልጅነትህ ጀምሮ አሸናፊ ነህ በአስኮላውም በቤተስኪያኑም አንተን የሚያህልህ የለም። በያው ልክም እንዳንተ የተፈተነም የለም። ለኔስ እንዳው ሁሉም ቀርቶብኝ ኸፈተና ወተህ ሽሽግ ብለህ እፎይ ብለህ ብትኖርልኝ ያንን አይቼ በማግስቱ በሚስደኝ አይቆጨኝ" ትላለች እባዋን መንታ መንታ እያወረደች።

እኔም ፈተናው ሲጠናብኝ እንደሰው ብንገዳገድም እንዳልወድቅ ፍቅርህ ምርኩዝ ሆኖኝ በፅናት አለፈናል። ማሩ የተወለድከው ለሌሎች አንፀባራቂ ብርሃን፤ ለትውልዱ መስታወት፤ ለሀገርህ ምልክት፤ ለአፍሪካውያን ኩራት ልትሆን የጥበብን በትረ ሙሴ ጨብጠህ ለመጪው ትውልድ ልታቀብል ነውና ቀሪው ዘመንህ በፅሁፍህ በአለም መድረኮች ነግሰህ ሀገርህን በድጋሚ እንደምታስጠራ አምንብሃለሁ።

መልካም ልደት ጋሼ
መልካም ልደት ውድ ባለቤቴ
መልካም ልደት ማሩ
መልካም ልደት #ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
ደራሲ በመሆኑ ብቻ በሚገርም ሁኔታ በአንድ አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ የተቃጣበትን የግድያ ወጥመድ በእግዚአብሔር ሃይል ያለፈ በኔ ዘመን ያየሁት ውዱ ባለቤቴን ብቻ ነው። መልካም ልደት የኔ❤️🌺💐
ብቸኝነት ሲሰማህ ማሰብ ከቻልክ የአሳብህ ጓደኛ ነህ። ማሰብ ካልቻልክ ብቻህን ነህ። መነጠል የስጋ ሳይሆን የአሳብ ስሜት ነው። ብቸኝነትህን አሳብህ ሲጋራ የአሳብ ጓደኛ አለህ። ብቸኝነትም ጓደኝነትም ስጋ አይደለም። የአብሮነትና የመነጠል ስሜት ነው።
ከሰው ጋር ስትሆን ለብቻህ እንደሆንክ ከተሰማህ በግርግር መሀል ብቸኛ ነህ። በስጋህ ብቻህን ሆነህ ከአሳብህ ጋር አብረህ ከሆንክ አንተማ ጓደኛ አለህ። ከቻልክ የወዳጅ አስፈላጊነትን ቀንስ። ሰው ብታጣም ያጣኸው ስጋ ነው። አብሮህ የሆነ አላቂ ነው። ዛሬ የሚቀርብህ ነገ የሚርቅ ነው። ወሳኙ ጉዳይ ህሊናህን አለማጣትህ ነው። የሌላ ስጋ ሲለይ አሳብህ ካንተ ጋር ነው።
.
መለየት የስጋ ነው። ብቻህን እንዳልሆንክ ከተሰማህ የአንተ ጓደኛ ስሜትህ ነው።
@yismakeworku
ራማቶሓራ የመፅሀፍ ትረካ ክፍል 7 ነገ ጠዋት 1:00 ላይ ይለቀቃል።

እስከ ክፍል 6 ተከታትላችሁ፣ ሰባተኛውን ክፍል በጉጉት ለጠበቃችሁ ነገ እነሆ እላለሁ።

@yismakeworku
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 7 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል 7 | ፯
File Size: 26.7MB


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku