ይማሩ - Yimaru
3.13K subscribers
11 photos
5 videos
1 file
21 links
English is Easy

To download our app:
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.yimaru.lms.app

For any help and enquiries:
Call: 0946396655
Telegram: @yimarusup
Download Telegram
Get ምንድነው?

"GET" አንድ ትርጉም ብቻ ያለው ቃል አይደለም። የሚመጣበትን አረፍተ ነገር ተመልከቱ፤ ትርጉሙን ከዚያ ይወስኑ።
Get ማግኘት | መግዛት | መድረስ | መረዳት | መሆን | ማምጣት

1. Get = ማግኘት / መቀበል
- I got a gift. (ስጦታ አገኘሁ።)

2. Get = መግዛት

I need to get some food. (ምግብ መግዛት አለብኝ።)

3. Get = መድረ

I got home at 8. (8 ሰዓት ቤት ደረስኩ።)

4. Get = መረዳት

I get it. (ገባኝ / ተረዳሁት።)

5. Get = መሆን / ሁኔታ መቀየር

I'm getting tired. (እየደከመኝ ነው።)

6. Get = መያዝ / ማምጣት

Can you get me some water? (እባክህ ውሃ አምጣልኝ።)


Quick Quiz (የ "Get"ን ትርጉም በዚህ ኣረፍተ ነገር ምንድን ነው)
1. I don't get it.
2. What time did you get home?
3. I need to get some food.
Write it in the Comment Section!!!
11
🚨 ይህ ፖስት ለአንድ ሰው ነው! 😂 🚨

That friend who says:“Like… I was like… and then she was like… so I was like…” 😭እንዴ ወንድሜ/እህቴ… LIKE ብቻ ነው? 😂

But did you know LIKE is actually a very useful English word?

❤️ I like pizza.
👉 ፒዛ እወዳለሁ።

👀 It looks like a movie.
👉 እንደ ፊልም ይመስላል።

🗣 She was like, “No wa
y!”
👉 “አይ በፍፁም!” አለች።

🍎 Fruits like apples are healthy.
👉 እንደ አፕል ያሉ ፍራፍሬዎች ጤናማ ናቸው።

So don’t stop using LIKE…Just stop using it every 3 seconds.

😂👇 ይህን ፖስት “LIKE” ብዙ ለሚጠቀም ጓደኛህ ላክለት! 😂

ምን እንደሚል እንይ… 👀😂

Yimaru Academy https://t.me/yimaru
8👏8
📚 WORD OF THE DAY

🔤 Brave /ብሬቭ/

💡 Meaning
ደፋር | ምንም ንገር ለማረግ የማይፈራ/ የማትፈራ

🗣 Example Sentence
"She is brave | እሷ ደፋር ሴት ናት።"

🔗 Related Words
Courageous | ከሬጀስ | ደፋር / ጀግና / ድፍረት ያለው

- Make a sentence using the word "Brave".
👍64🙏1
📚 WORD OF THE DAY

Lazy /ሌዚ/

💡 Meaning
መሥራት፣ ማጥናት ወይም ጥረት ማድረግ የማይፈልግ ሰው።

🗣 Example Sentence
"He is too lazy to clean his room. እሱ ክፍሉን ለማጽዳት በጣም ሰነፍ ነው።"
👍61
💬 PHRASE OF THE DAY

"Keep your chin up"

💡 Meaning
ተስፋ አትቁረጥ፤ ጠንክረህ ቀጥል

🎯 When to Use
ይህን ሐረግ አንድ ሰው ችግር ሲያጋጥመው ተስፋ እንዳይቆርጥ ለማበረታታት እንጠቀማለን።

🗣️ Example Sentence
"Keep your chin up. Things will get better. ተስፋ አትቁረጥ። ነገሮች ይሻሻላሉ።"

💬 Example Conversation
Abel: I failed my English test.
👉 አቤል፦ የእንግሊዝኛ ፈተናዬን ወደቅኩ።

Sara: Don't worry. Keep your chin up!
👉 ሳራ፦ አትጨነቅ። ተስፋ አትቁረጥ!

Abel: Thanks. I'll study harder next time.
👉 አቤል፦ አመሰግናለሁ። በሚቀጥለው ጊዜ የበለጠ እማራለሁ።
🔥3👍21
📚 WORD OF THE DAY

🔤 Sad /ሳድ/

💡 Meaning
ማዘን

🗣️ Example Sentence
"He became sad after losing his job. ሥራውን ካጣ በኋላ አዘነ።"

🔗 Related Words
Upset | የተከፋ
3🙏3
30 ቀን እንግሊዝኛን መማር የምትችሉበት ቪድዮ ክፍል 1
https://youtu.be/PpUV2j2RBYg?si=x594Bi7sRF0UxkY-
መለማመጃ ዶክዩመንት ከስር
👍52
💬 PHRASE OF THE DAY

"Step out of your comfort zone."

💡 Meaning
ከምትለምደውና ምቾት ከሚሰማህ ነገር ውጣና አዲስ ነገር ለመሞከር ድፈር።

🎯 When to Use
ይህን ሐረግ አንድ ሰው አዲስ ነገር እንዲሞክር ለማበረታታት እንጠቀማለን።

🗣️ Example Sentence
"You need to step out of your comfort zone and speak English with other people. የእንግሊዝኛ ቋንቋህን ለማሻሻል ከምቾት ዞንህ ውጣና ከሌሎች ሰዎች ጋር እንግሊዝኛ ተናገር።"

💬 Example Conversation
Abel: Why don't you speak English in front of the class?
👉 አቤል፦ በክፍል ፊት ለምን እንግሊዝኛ አትናገርም?

Sara: I'm afraid of making mistakes.
👉 ሳራ፦ ስህተት እሠራለሁ ብዬ እፈራለሁ።

Abel: Don't worry! You need to step out of your comfort zone if you want to improve.
👉 አቤል፦ አትጨነቂ! መሻሻል ከፈለግሽ ከምቾት ዞንሽ መውጣት አለብሽ።
👍5🔥5
💬 PHRASE OF THE DAY

"Give it a shot"

💡 Meaning
ሞክረው / አንድ ጊዜ ሞክረው።

🎯 When to Use
ይህን ሐረግ አንድ ሰው አንድን ነገር ለመሞከር ሲያመነታ እንዲሞክረው ለማበረታታት እንጠቀማለን።

🗣️ Example Sentence
"You’ve never tried Ethiopian food? Give it a shot! የኢትዮጵያን ምግብ ሞክረህ አታውቅም? እስቲ ሞክረው!"

💬 Example Conversation
Sara: I don't think I can speak English in front of everyone.
👉 ሳራ፦ በሁሉም ሰው ፊት እንግሊዝኛ መናገር እችላለሁ ብዬ አላስብም።

Abel: Come on! Give it a shot.
👉 አቤል፦ እስቲ! ሞክሪው።

Sara: Okay, I'll try.
👉 ሳራ፦ እሺ፣ እሞክራለሁ።
🔥2