📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
ደግነት የማይከፍተው ደንዳና ልብ የለም!
እስከ 12 ሰዓት
6710 ላይ
የታሪክ ድርሳን ብለው በSMS 1 ብር
በመላክ ለልብ ህሙማን አለን እንበላቸው!!
ከ1ሺ ሰው 800ው እንኳን ቢልክ 800 ብር ነው!!!
እኛ ነፃ የሞንዎጣው ልባችን ውስጥ ነው!!
እስኪ እስክሪን ሻት እያደረግን ለአድሚኑ @Hab_G ላይ ያድርሱ አጋርነታችንን እናሳይ
💚💛❤️ 6710💚💛❤️
@yetarikdersan

ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ (አባ መላ)
ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ከኦሮሞ ገበሬ አባታቸው ከአቶ ዲነግዴ ቦተራ እና የሰባት ቤት ጉራጌ ቦዞ ሰንጌ ከሆኑት እናታቸው ከእመት ኢጁ አመዲና በሺ ስምንት መቶ አርባ ሶስት እና አርባ አራት አካባቢ ፣ በአመያና ወሊሶ አካባቢ እንደተወለዱ ነው የሚነገረው።
በተወለዱ በሰባት አመታቸው ከእናት አባታቸው ተለይተው ታላቅ እህታቸው ዘንድ ጅባትና ሜጫ አውራጃ ብደንዲ ወረዳ፣ ጎዳና ብቱቃ ገንዲ ቀበሌ እስከ አስራ አራት አመታቸው ድረስ ኖረዋል ።
በሺ ስምንት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ አመተምህረት ገደማ የሸዋን ግዛት እንደገና የማዋሃድና አንድ አድርጎ የማስተዳደር ዘመቻ፣ የራስ ጎበና ዳጨው ጦር በከፊል ወደ ጅባትና
ሜጫ ሲዘምት ፣በምርኮ ከተወሰዱት መካከል እድሜ ለጋ ልጆችም ነበሩበት ።
ወደቦዳ የዘመተው የራስ ጎበና ከፊል
ጦር ፈሊጦ ከተባለው ዋሻ አቅራቢያ እህታቸው ቤት ደርሶ ማረካቸው ።
ሀብተጊዮርጊስ ጊዮርጊስ የአስራ አራት ዓመት ልጅ እያሉ ተማርከው በቤተመንግሥት አደጉ ። ሀብቴ ዲነግዴ በቀለም ትምህርት ከማንበብ በስተቀር ፅህፈትም ሆነ ተጨማሪ ትምህርት አልነበራቸዉም።
ይሁንና በተፈጥሮ እጅግ ብልህና ንቁ አእምሮ የነበራቸው ሰው በመሆናቸው ፣በሚሰጡት አገልግሎት፣በሚመክሩት
መላም ሆነ በሚሰጡት ፍርድ በበላዮቻቸው፣ በእኩዮቻቸው ፣በአሽከሮቻቸዉም ሆነ በህዝቡ ዘንድ የተደነቁ ነበሩ ።
የሀገርም ሆነ የዉጭ ሀገር ትምህርት ያልነበራቸው ሀብቴ ዲነግዴ ፣በፖለቲካና በፍርድ አሰጣጥ በጊዜው ከነበሩ ምሁራንም በላይ ሚዛን የደፉ እንደ ነበሩ ታሪክ ፀሐፊዎች በደማቅ ቀለም አስምረዉበታል።
ዉስጥ አዋቂ ምንጮች በፅሁፍ ካኖሩልን ዝክር እንደምንረዳው ፣በጊዜው ዙፋን ችሎት አፄ ምኒልክ ፊት ቀርበው የተፈረደባቸው ባለጉዳዮች፣ ምንም እንኩዋን የንጉሡ ፍርድ የመጨረሻ ቢሆንም "ይግባኝ ለሀብቴ" ይሉ ነበርና፣ አፄ ምኒልክም "እሺ ይይላችሁ" ብለው ይፈቅዱ
እንደነበር ይነገራል ።
ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ አዋቂነታቸዉና ብልህነታቸውን
፣ትግስታቸዉንና ቻይነታቸዉን ፍንትዉ አርጎ የሚያሳይ " አባ መቻል " የተሰኘ የፈረስ ስም ቢኖራቸዉም፣ ፍትህ
አዋቂነታቸው ልቡን የነካው ፣መላ ዘያጅነታቸው መንፈሱን ያረካው ሰፊው ህዝብ "አባ መላ" እያለ በአንደበቱ
ስላለመለማቸው ይበልጡን የሚታወቁት በዚህ "አባ መላ"
በተሰኘው መጠሪያ እንደነበር ታሪክ ተንታኞች በስምምነት ያረጋግጣሉ ።
በቤተ መንግሥቱም ሰፈር እንዲሁ "ጌታ ፊታውራሪ " የሚል ስም ፀድቆላቸው አብዛኛው ቤተ ህሩያን መሳፍንት "ጌታ ፊታውራሪ " ሲሉ አክብረዉና አስከብረው ይጠሯቸው ነበር ።
እሱ ያለበት ምንም አይላላ፣
የረጋው ጎበዝ ሀብቴ አባ መላ ። ተብለው በክብር ይወደሱ ፣ባድናቆት ይወሱ ነበር ሀብቴ ዲነግዴ ።
ሀብተጊዮርጊስ በጀግንነት አቻ የሌላቸው ፣ብርቱ ተፋላሚ የጦር አበጋዝ ፣ አይበገሬ ጠላት አንበርካኪ ቆፍጣና ጄኔራል መሆናቸው ሀገር ያወቀው ፣ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው።
ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ
ፍትህን ለማስፈን ፣ፍርድን ለማደላደል የሰጧቸዉን የፍርድ ብያኔዎች እናያለን ።
ይህም ጥረት ሀብቴ ዲነግዴ ምን ያህል በሳል፣አስተዋይና ብልህ እንደሆኑ ለማየት አይኖቻችንን በሰፊው ከፍቶ ያበራልናል ።
ፊታውራሪ ሀብቴ ሚስታቸው ከወታደር ጋር ስትወሰልት ትገኝና ሚስትና ወታደር እግር ተወርች ታስረው ፊታቸው ይቀርባሉ ።
አባ መላም እንዲፈቱ ካዘዙ በኋላ ሁለቱንም ለየብቻ ያናግሩና ሚስትና ወታደር በፍቅር እንደወደቁ አውቀው ደግሰው ሚስታቸውን ለወታደራቸው
ይድራሉ። አጤ ሚኒሊክ ታሪኩን ሰምተው ኖሮ አባ መላ ጋር ሲገናኙ” እንዲያው ቆይ በሚስትህስ አልጨክን ብለህ ነው ልበል፣ ያን ባለጌ ወታደር አለመግደልህ ሲገርመኝ እንዲያው በግርፋት አትመልጠውም ኖሯል?!”
ሲሉ በአግራሞት ጠየቋቸው።
” አየ ጃንሆይ!! እንዲያው ለዚህ ሳያጥቡት ለሚገማ፣ ሳይወጉት ለሚደማ ጎደሎ ብዬ የሰው ነፍስ
ላጥፋ?!” አሉ በሳቅ ታጅበው!!
*
ሴትዮዋ መልከ ቀና ኮማሪት ነበረች ። ታዲያ በተደራቢ ለከደንበኞቿ ጋር ገንዘብ እየተቀበለች ታድራለች ( ያው በወሲብ ንግድ መተዳደር እንበለው በዘመነኛው) ። አንድ ደንበኛዋ
ታዲያ በፍቅሯ ይወድቅና አብረው መኖር ይጀምራሉ ።
በኋላ ኑሯቸው እየደረጀ ጎጇቸው በሀብት እየተሞላ ይመጣል። አመታት
እያለፉ ሲመጡ የሰውዬው ዘመዶች እንዴት እንዳንት ያለ የከበረ ጌታ ከኮማሪት ጋር ይኖራል ብለው ይመክሩትና እንፋታ ይላታል ።
ሀብቱ ሁላ በስሩ ነበርና እሷ ሜዳ ላይ ልትቀር ሆነ ። በየደረጃው በክስ ብትሄድም መላ የሚላት እያጣች ፍርድ ሁሉ ለሱ እየሆነ በመጨረሻ ”ይግባኝ ለጃንሆይ !!”ትላለች። ጃንሆይም ሊያስማሟቸው ቢሞክሩ ባል ወይ ፍንክች የአባ ቢለዋ ልጅ!! በመጨረሻ አጤ ምኒሊክም እያዘኑ ለባል ይፈርዳሉ።
” ይግባኝ ለፊታውራሪ ሀብተ ገዮርጊስ!!” ትላለች ሰማይ የተደፋባት ከሳሽ። ” ወግጂ ይቺ ከጃንሆይ ወዲያ!!” ብሎ በዙፋን ዙሪያ ያለ ሲፎገላ ” ቆይ ቆይ !!”አሉ ጃንሆይ
ተረጋግተው ። ” አባ መላ መፍትሄ ካገኘላት ምናለ ይይላት!!” አባ መላ ግራ ቀኙን ከሰሙ ወዲያ ባልን በዚህ ቢሉ በዚያ አልበገር ይላል!!
በመጨረሻ እንዲህ ሲሉ ሴትዮይትን ጠየቋት። ”ለመሆኑ መጀመሪያ ቀን አብራችሁ ስታድሩ ስንት
ብር ከፈለሽ?” ” አምስት ብር!” ሴትዮይት መለሰች። ” አብራችሁ መኖር ከጀመራችሁ ስንት ጊዜ ሆነ?!” ” አምስት አመታችን ሰኔ ሚካኤል ላይ አለፈ!” “በጄ!” አሉ አባ መላ ” በጄ በል
እንግዲህ መጀመሪያ ቀን የከፈልካትን ብር በአምስት አመቱ ቀናት አባዝተህ ሙሉ ሂሳቧን ክፈላትና ፍቺውን መፈፀም
ትችላለህ!” ባል ፊቱ ሳምባ መሰለ !! ወዲያው ሚስቱ እግር ስር ተደፋና ” ይቅር በይኝ እናቴ መካር አሳስቶኝ ነው!!”
****
እንግሊዞች አጤ ሚኒሊክ ዘንድ
ይቀርቡና በመቅደላ ጦርነት ወቅት የኛ ወታደሮች የሞቱበት መሬት ይሰጠን! ! ወገኖቻችን ተቀብረውበታልና ይላሉ። አጤ ሚኒሊክም ጉዳዩን ወደ አባ መላ ይመሩታል። አባ መላም ነገራቸውን
ከሰሙ በኋላ ” በጄ ይሁን ብለናል! !
ፈቅደናል! !” አሉ።
እንግሊዞችም ቂጣቸውን በካልቾ እየመቱ እየፈነጠዙ ሊወጡ ሲሉ “ቆይማ!” አሉ አባ መላ ። ” እንግዲህ የአጤ ቴዎድሮስ ልጅ ልኡል አለማየሁ
የተቀበረባት ሎንዶን ለኛ የምትገባ መሆኗንም አትርሱ!!” እንግሊዞች እንደድመት ዱካቸው ሳይሰማ ሹልክ!!
ምንጭ ፤
መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ፣1999
👇
የታሪክ መጣጥፎች ለምታደርሱን ወዳጆች በነዚህ ላኩልን ...
👇👇👇👇👇👇
@Habtu_G
@Teferi_M
@MulugetaAnberber
ይህ የናንተ የታሪክ ድርሳን ገጽ ነው።
"በታሪክ እንማራለን እንጅ አንማረርም

በዛሬው ጥንቅር በተለያዩ የታሪክ መዛግብትና የምርምር ሰነዶች ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ
ፍትህን ለማስፈን ፣ፍርድን ለማደላደል የሰጧቸዉን የፍርድ ብያኔዎች ዘልቀን እንፈትሻለን።
ለወዳጅዎ ማካፈልዎን እንዳይዘነጉ!!
@yetarikdersan
ፍትህን ለማስፈን ፣ፍርድን ለማደላደል የሰጧቸዉን የፍርድ ብያኔዎች ዘልቀን እንፈትሻለን።
ለወዳጅዎ ማካፈልዎን እንዳይዘነጉ!!
@yetarikdersan
🗞በአፄ እያሱ ትዕዛዝ የተፈጸመ የግዳጅ ትዳር🗞
ተፈሪ መኮንን የሚባል አንድ ወጣት ደጃዝማች በሃረር አካባቢ ይኖር ነበር። እና ኑሮውን በሰላም በመኖር ላይ ሳለ አንድ ቀን ያልጠበቀው ነገር ገጠመው።
ተፈሪ እንደወትሮው ጸሎት ላይ
ሳለ ስልክ እንደሚፈልገው ተነገረው። የደወለለት የአጤ ምኒልክ ዙፋን ወራሽ ልጅ እያሱ ነበር። ሰላምታ ከተለዋወጡ
በሁዋላ ልጅ እያሱ በቀጥታ ተፈሪን እንዲህ አለው፣
“ስማ ተፈሪ! የእህቴን ልጅ መነን አስፋውን ልድርልህ ወስኛለሁ። የአንተ አሳብ ምንድነው?” ተፈሪ በጣም ደነገጠ። ምክንያቱም መነን ከሶስተኛ ባሏ ጋር ከተጋባች ገና አንድ አመት እንኳ አልሞላትም ነበር።
ከዚያ በፊት ካገባቻቸው ሁለት ባሎች በድምሩ አራት ልጆች መውለዷንም ያውቃል። አራት ልጆች ከወለደች በሁዋላ ሶስተኛ ባል አግብታ በመኖር ላይ ያለችን ሴት፣ “ልዳርልህ” የሚል
አሳብ ሲቀርብለት ተፈሪ መደንገጡ የሚጠበቅ ነበር። እና ድንጋጤውን ዋጥ አድርጎ ጥያቄ አቀረበ፣
“ጌታዬ! ለኔ የምታስብልኝን ሁሉ በደስታ መቀበል ፍላጎቴ ነው።
ዳሩ ግን መነን የራስ ልኡልሰገድ ሚስት ናት። እንዴት ሆኖ ነው ለኔ የምትዳረው?” ልጅ እያሱ በቁጣ ቃል ምላሽ ሰጠ፣
“እሱን ለኔ ተወው። አንተ እዚህ ውስጥ መግባት የለብህም። የጠየቅሁህ ‘መነንን ታገባታለህ ወይስ አታገባትም?’ የሚለውን ነው…”
በዚህ ጊዜ ተፈሪ መኮንን ምላሹን ሰጠ፣
“እሺ አገባታለሁ”
“እንግዲያው በ15 ቀናት ውስጥ ሽማግሌ ወደአዲሳባ ላክልን።
አንተ አዲሳባ መምጣት አያስፈልግህም። ሽማግሌዎቹ
ሚስትህን ይዘውልህ ይመጣሉ።”
ሁለቱ የባላባት ልጆች በዚህ መልኩ ስለመነን በሚነጋገሩበት ወቅት መነን ከሶስተኛ ባሏ እና ከአራት ልጆቿ ጋር በሰላም በመኖር ላይ ነበረች።
ለአራተኛ ጊዜ ለሌላ ባል እዳራለሁ ብላ
በህልምዋ እንኳ አሳቡ አልነበራትም። ከሶስተኛ ባሏ ጋር በፍቅርና በደስታ መኖር ጀምራ ነበር።
ተፈሪ መኮንን ከልጅ እያሱ ጋር የስልክ ንግግሩን ካበቃ በሁዋላ በቀጥታ ወደ ፀሎቱ ነበር የተመለሰው። ፀሎቱን እንዳበቃም ከአባቱ ወዳጆችና ነባር መኳንንቶች ጋር በጉዳዩ ላይ
መከሩበት። ጋብቻውን ከመቀበል ውጭ ምርጫ አልነበራቸውም።
መነንን እንደ ሙሽራ በማጀብ ወደ አራተኛ ባሏ የሚያመጧትም አራት ሲህ ወታደሮች ወደ አዲስአበባ ተላኩ።
ከሞቀ ትዳሯ እና ከሶስተኛ ባሏ ነጥለውም ወደ ሃረር ወስደው
ለተፈሪ መኮንን ዳሯት።
ወይዘሮ መነን ወደ ተዘጋጀላቸው አራተኛ ባል እንድትሄድ ስትጠየቅ፣ “አምላክ በዚሁ በቃሽ ይበለኝ”
ከማለት ሌላ አንዳችም ቃል እንዳልተነፈሰች ይነገራል።
በርግጥም አምላክ ፀሎቷን ሰምቶላታል። አጤ ሃይለስላሴ ተገደው እቴጌ መነንን ካገቡ በሁዋላ እስከ
ህይወታቸው ፍፃሜ በጋብቻ ኖረዋል።
እቴጌ መነንም ከአራተኛ
ባላቸው በርካታ ልጆችን ለማፍራት በቅተዋል።
(ምንጭ፣ ዘውዴ ረታ – ተፈሪ መኮንን)

‹‹እኔ ለመከራ የተፈጠርኩ ሰው ነኝ፤
የልጄን ነገር አደራ›› – እቴጌ
ጥሩወርቅ ውቤ ኃ/ማርያም (ግንቦት
1860 ዓ.ም)
የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ አሳዛኝ ሕይወትና አሟሟት (150ኛ የሙት ዓመት መታሰቢያቸውን ምክንያት
በማድረግ የተፃፈ)
እቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ የንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ሕጋዊ ሚስት ነበሩ፡፡
ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ባለቤታቸው እቴጌ ተዋበች አሊ አሉላ ከሞቱ በኋላ በሕግ ያገቡት እቴጌ
ጥሩወርቅ ውቤን ነው፡፡
እቴጌ ጥሩወርቅ የካቲት 3 ቀን 1847 ዓ.ም በደጃዝማች ካሣ ኃይሉ (በኋላ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ) ደረስጌ ላይ የተሸነፉት የደጃዝማች ወቤ ኃይለማርያም ልጅ ናቸው፡፡
ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ ሚያዚያ 6 ቀን 1860 ዓ.ም መቅደላ ላይ ከሞቱ በኋላ የእንግሊዝ ጦር
መቅደላ አምባንና አካባቢውን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ የታሰሩትን ፈትቶ (ምርኮኛና እስረኛ የነበሩትን
ኢትዮጵያውያንን) ወደእንግሊዝ ለመውሰድ የሚጭነውን ሀብት ካዘጋጀ በኋላ ሚያዚያ 14 ቀን 1860 ዓ.ም
የመልስ ጉዞ ጀመረ፡፡
በጉዞው ላይም የንጉሰ ነገሥቱ ባለቤት እቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ እና ልጃቸው ልዑልዓለማየሁ ቴዎድሮስ ነበሩ፡፡
ይሁን እንጂ እቴጌዋ ከመቅደላ ጀምሮ ጤንነት አልነበራቸውም፡፡ የእንግሊዝ ጦር መሪ ጀኔራል ሮበርት ናፒዬርም ጉዳዩን አውቆ ሐኪም መድቦላቸው ቢታከሙም ሊሻላቸው አልቻለም፡፡
ወቅቱ የበልግ ዝናብ የሚዘንብበት ጊዜ በመሆኑ ከላይ ዝናቡ ከታች ጭቃው በህመማቸው ላይ ተጨምሮ ስቃያቸውን ስላባባሰባቸው ጉዟቸውን በቃሬዛ ላይ ሆነው ለማድረግ ተገደው ነበር፡፡
ቀደም ካለው ጊዜ ጀምሮ ከንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ ጋር ወዳጅነት የነበረው እንግሊዛዊው ተጓዥና መልዕክተኛ ሆርሙዝ ራሳም እቴጌዋን ለማበርታት ‹‹አይዞዎት፣ ይበርቱ፣ ይድናሉ›› ሲላቸው … ‹‹አዬ ለመሞት ቀኔ የተወሰነ ነው፤ብሞትም አላዝንም፤ ጥንትም ስፈጠር ከልጅነቴ ጀምሮ ለመከራ የተመደብሁ ነኝ፡፡
አሁን መድኃኔዓለም ተስፋ ወደሰጠው ዓለም (መንግሥተ ሰማያት) ለመድረስ ብቻ ነው ምኞቴ፤ የልጄን ነገር አደራ›› ብለው እንደመለሱለት ጽፏል፡፡
እቴጌ ጥሩወርቅ ‹‹ጥንትም ስፈጠር ከልጅነቴ ጀምሮ ለመከራ የተመደብሁ ነኝ›› ያስባላቸው የወቅቱ ሕመማቸው ብቻ አልነበረም፡፡
አባታቸው ደጃዝማች ወቤ ኃይለማርያም ለመንገስ እየተዘጋጁ ሳለ በባለቤታቸው በደጃዝማች ካሣ ኃይሉ
(በኋላ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ) በጦር ሲሸነፉ እስራትና መጉላላት ደርሶባቸው ነበር፡፡
ደጃች ውቤ በወቅቱም ‹‹እኔን እንደዚህ ከማጉላላት ለኔ አንድ ጥይት አነሰኝ?!›› ብለው በምሬት ተናግረዋል፡፡
እቴጌዋም በአባታቸው እስራትና ሞት ብርቱ ሀዘን ወድቆባቸው ነበር፡፡
የአክስታቸው ልጆች የሆኑት ደጃዝማች ንጉሤና ደጃዝማች ተሰማ በ1852 ዓ.ም በንጉሰ ነገሥቱ ተሸንፈው ተማርከው በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ
ያጋጠማቸው ሃዘንም የበረታ ነበር፡፡
ይህም አልበቃ ብሏቸው እርሳቸውም በአካባቢው ስለነበሩ ገና በወጣትነታቸው ንጉሰ ነገሥቱን ለማግባት ተገደዱ፡፡
ወንድሞቻቻው ደጃዝማች ጓንጉልና ደጃዝማች ካሣ በንጉሰ ነገሥቱ ተማርከው ታስረው ነበር፡፡ ከእስራት
የተፈቱትም ከመቅደላ ጦርነት በኋላ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ ሚስት ሆነው ሳለ ንጉሰ ነገሥቱ የየጁዋን መልከመልካመም ሴት ወይዘሮ የተመኙን ቅምጥ አድርገው እቴጌ ጥሩወርቅን ያስቀኗቸው ነበር፡፡
በሌላ በኩል ንጉሰ ነገሥቱ መቅደላ ላይ ራሳቸውን ካጠፉ በኋላም “በንጉሰ ነገሥቱ ተበድለናል” ያለው ሰው ሁሉ
እቴጌዋን ለመጉዳት ይጋበዝ/ይዘጋጅ ነበር፡፡
ታዲያ ዳዊት ከመድገም ውጭ ሌላ ነገር ያልለመዱት ቆንጆዋና ለስላሳዋ እቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ይህን ሁሉ
መከራና ስቃይ ተሸክመው ሊዘልቁ አልቻሉም፡፡
የአባታቸው እስራትና ሞት፣ የወንድሞቻቸው እስራት፣ የአክስታቸው ልጆች አሰቃቂ ሞት፣ በባለቤታቸው ዘንድ እንደንበኛ ሚስት አለመታየት … ይህ ሁሉ መከራ ከበሽታ ጋር ተደምሮ የእቴጌዋን ሕይወት አሳጠረው፡፡
ከዛሬ 150 ዓመታት በፊት (ግንቦት 7 ቀን 1860 ዓ.ም/ ባለቤታቸው ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ
ከሞቱ ከሦስት ወራት በኋላ) አረፉ፡፡
ስርዓተ ቀብራቸውም በሸለቆት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ተፈፀመ፡፡ ከራስ
ወልደሥላሴ ጎን ተቀበሩ፡፡
መረጃው ‹‹አጤ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት›› (ተክለፃድቅ መኩሪያ) እና ከሌሎች መዛግብት
የተገኘ ሲሆን አንዳንዱ ትረካ ቃል በቃል የተወሰደ ሳይሆን መጻሕፍቱን ሳገላብጥ ያየሁትን አዛምጄ
ጽፌዋለሁ]
[ፎቶው የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ኃ/ማርያም አስክሬን
ወደ ሸለቆት ሥላሴ ገዳም ሲወሰድ የሚያሳይ ነው]
ነፍስ ይማር!
ልዑል ዓምደጽዮን ሠርፀድንግል
<"ኢትዮጵያን ለማጥፋት ለሚሰራ እና የትላንትን ሀቅ ለመካድ ለተዘጋጀ ሁሉ ዛሬም አርበኛ ነን">!!
ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን!!!
ኢትዮጵያችን ለዘለዓለም ትኑር!!!

ንግስት_ማክዳ(ንግስተ ሳባ "The Queen of Sheba")
#ከመፅሐፈ_ክብረ_ነገስት_የተወሰደ
ወገኖቼ ነገሬን አድምጡኝ፡፡ እኔ ጥበብን እሻለሁ ፡፡ ልቤም እውቀትን ትፈልጋለች ፡፡ በጥበብም ፍቅር ተነድፌአለሁ ፡፡ በጥበብ ገመዶችም ተይዣለሁ፡፡
‹‹ ጥበብ ከወርቅና ከብር መዛግብት ትሻለች ፡፡ ጥበብ በምድር ከተፈጠሩት ሁሉ ትበልጣለች፡፡ ጥበብ ከሰማይ በታች በምን ይመስሏታል ? ከማር ትጣፍጣለች ፡፡ ከወይን ታስደስታለች ፡፡ከፀሐይ ታበራለች፡፡ ከጣፈጡ ምግቦች ታጠግባለች፡፡ ከመቶ ሺህ ወርቅና ብር ታከብራለች ፡፡ ለልብ አስደሳች፣ ለአይኖች መብራት ፣ ለእግር ቅልጥፍና ፣ለደረት ጥሩር ፣ ለራስ አክሊል፣ ለአንገት የወርቅ ማርዳ፣ ለወገብም መታጠቂያ፣ ለጆሮ ማዳመጫ፣ ለልብ ብልሐት፣ ለምሑራን ትምህርት ፣ ለልበኞች መፅናኛና ለሚፈልጉት ክብር ሰጪ ናት ፡፡
”መንግስት_ያለ_ጥበብ_አይቆምም፡፡ ሐብት ያለ ጥበብ አይጠቅምም፡፡ እግርም ያለ ጥበብ በቆመበት አይጸናም፣ ልሳንም ያለ ጥበብ የተናገረው አይወደድም፡፡
ጥበብ ከንብረት ሁሉ ትሻላለች ፡፡ ወርቅና ብር የሰበሰበ ያለ ጥበብ አይጠቅመውም ፡፡
ጥበብን የሰበሰበ ከልቡ ማንም አይቀማውም፡፡ ሰነፎች የሰበሰቡትን ጠቢቦች ይበሉታል ፡፡ በበደለኞች ክፋት ቅኖች ይመሰገናሉ፡፡ በሰነፎችም ስህተት ጠቢቦች ይወደዳሉ ጥበብ ልዕልት ናት፡፡
እንደ እናት እወዳታለሁ፡፡ እሷም እንደ ሕፃኗ ታቅፈኛለች ፡፡እኔ ጥበብን ፍለጋ እክታተላለሁ፡፡ እሷም እስከ ዘላለም ትጠብቀኛለች፡፡ ዱካዋን እከታተላለሁ ፡፡ከእሷም አልጣላም ፤ እጠጋታለሁ፤እሷም የድንጋይ ግንብ ትሆነኛለች፡፡ ሐይልና ብርታትም ትሆነኛለች፡፡ እደሰትባታለሁ ፤ ብዙ ሞገስም ትሆነኛለች ፡፡ የጥበብን ዱካ ልንከተል፣ ሸኮናችንም በበሮቿ ደረጃ ሊቸነከር ይገባናል፡፡
”እንፈልጋታለን ፤እናገኛታለን፤እንወዳታለን፤ ከእኛም አትርቅም ፡፡እናገኛታለን፡፡ እንለምናት ፤እንቀበላታለን ፡፡
ሁልጊዜ እንፈልጋት ልባችንን ወደ እሷ እንመልስ ፡፡ ካሰቧት ታስባለች ፡፡ በሰነፎች ዘንድ ጥበብ አትታሰብም ፤ አያከብሯትምና እሷም አትወዳቸውም፡፡
የጥበብ_ክብር_ጠቢብን_ማክበር_ነው፡፡ የጥበብም ፍቅር ጠቢብን ማፍቀር ነው፡፡”
ንግስት_ማክዳ ስለ ንጉስ_ሰሎሞን ጠቢብነት ከነጋዴው ታምሪን ሰምታ ወደ ንጉስ ሰሎሞን ጉዞ ልታደርግ ለሕዝቧ የተናገረችው ንግግር ፡፡

🙏ውድ የታሪክ ድርሳን ቤተሰቦች🙏
ከዚህ በታች የገለጽናቸው የታሪክ መድብላትን በsoftcopy አዘጋጅተናል እና screenshoot እያደረግን ልናስነብባችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ እነኚህን አዘጋጅተናልና !!
ከዘረዘርናቸው መድብላት ውስጥ አንድናስነብባችሁ የምትሹትን መጥሐፍ ጠቁሙን እና እንጀምረው !!
ምርጫችሁን በዚህ ላኩልን
👇
@Hab_G
ለመጀመሪያ ዙር ያዘጋጀናቸው መድብላት ከዚህ በታች ዘርዝረናል!!
📚ዐፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት
በ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ
📚የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ አክሱም ዛጉዬ እስከ ዐፄ ይኩኑ አምላክ ዘመነ መንግስት
በ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ
📚አጤ ቴዎድሮስ
በ ጳውሎስ ኞኞ
📚አሉላ አባ ነጋ
በማሞ ውድነህ
📚ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
በ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ
📚የኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ
በዶክተር ላጵሶ ድሌቦ

📜ውድ የታሪክ ድርሳን ቤተሰቦች!!📜
አምስት የታሪክ መድብላትን አዘጋጅተን እንድናስነብባችሁ ምርጫ ታካሂዱ ዘንድ ጠቁመን ነበር ስለሆነም አብዛኛው ሰው የመረጠው "የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ አክሱም ዛጉዬ እስከ ዐፄ ይኩኑ አምላክ ዘመነ መንግስት" የሚለውን የተክለ ጻድቅ መኩሪያ መድብል ሆኖ ተመዝግቧል!!
በእናንተ በታሪክ ድርሳን ቤተሰቦች ምርጫ መሰረት "የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ አክሱም ዛጉዬ እስከ ዐፄ ይኩኑ አምላክ ዘመነ መንግስት" በ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ የተከተበውን እና 82 ምዕራፎች ያሉትን ድንቅ የታሪክ መድብል screenshoot እያደረግን እንድናስነብባችሁ መርጣችኋል!!
ስለሆነም በየ ምዕራፉ ከፍለን ለማስነበብ ነገ ዝግጅታችን ጨርሰን ማስነበባችን እንጀምራለን!!
ስለተሳትፏችሁ እናመሰግናለን!!
ታሪክ ዓዋቂ ትውልድን እንፈጥራለን!!
ሰናይ ንባብ……
🙏ሰላም ለኢትዮጵያ🙏