Yekatit 23 SPS
5.03K subscribers
1.79K photos
8 videos
649 files
42 links
Official school channel
Download Telegram
Forwarded from Gashawbeza Beza
ዛሬ መጋቢት 3/2016 ዓ/ም የ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስርዓተ ፆታ ክበብ ‘’ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!’’ በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን (March-8) አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
በዓሉንም ምክንያት በማድረግ የስርዓተ ፆታ ክበብ አባል ተማሪዎች እና መምህራን የተለያዩ ግጥምና የስነጽሁፍ ውጤቶችን ያቀረቡ ሲሆን በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ  ሴት ጎበዝ ተማሪዎችም የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል ።
Forwarded from Gashawbeza Beza
የአፋልጉኝ ማስታወቂያ

በፎቶ ላይ የምትመለከቱት የ 16 ዓመት ታዳጊ መናገር እና መጻፍ የማይችል ሲሆን ከቤተሰቦቹ ጋር ለህክምና ከመናገሻ ኮሎቦ የሚባል አካባቢ መጥቶ ትላንት ማክሰኞ መጋቢት 3/2016 ዓ/ም ምሽት 10:00 ስዓት አካባቢ ስለጠፋባቸው ታዳጊውን ያየ የት/ቤታችን ማህበረሰብ በስልክ ቁጥር 0912-884002 ወይም 0931585083 እንዲደውልላቸው በፈጣሪ ስም ይጠይቃሉ ።
Forwarded from Gashawbeza Beza
Forwarded from Gashawbeza Beza
Forwarded from Musse wodi raya
በፌዴራል ደረጃ ተዋቅሮ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራው የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲያካሂደው የቆየውን የመስክ ምልከታ አጠናቀቀ፡፡
*****
መጋቢት 12-2016ዓም

በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራው የድጋፍና ሱፐርቪዥን ቡድኑ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በበጀት ዓመቱ እየተሰሩ ያሉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን፣ በትምህርት ለትውልድ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ፣ በከተማ ግብርና እና ሌማት ትሩፋት ስራዎች፣ በሲቪል ምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በጤናው ዘርፍ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የተሰሩ እና እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራትን በመዘዋወር ምልከታ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም በክፍለ ከተማው አስተዳደር የተገነባውን የመረጃ ማዕከል እና የደህንነት ማስጠበቂያ ካሜራዎች ያሉበት ሁኔታ ጉብኝት አድርጓል፡፡

በሰው ተኮር ፕሮጀክቶችም ሆነ በሌማት ትሩፋት ተግባራት የነዋሪውን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ተዘዋውረን ባደረግነው ምልከታ አረጋግጠናል ሲሉ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ዳመነ ዳሮታ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ በትክክለኛው የልማት ጉዞ ላይ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል ብለዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበኩላቸው ድጋፋዊ ሱፐርቪዥኑ ጥንካሬዎቻችንንና ክፍተቶቻችንን ለይቶ የሚያሳይ በመሆኑ በእጅጉ ጠቃሚ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመስክ ምልከታው የኢፌደሪ ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ዳመነ ዳሮታ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ፣ በሚኒስትር ዴኤታ ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህግ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ፍቃዱ ጸጋዬን ጨምቶ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
Forwarded from Musse wodi raya
Forwarded from Lemlem
የፈተና መረጃ ለ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች
1. የ6ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ)
• በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
• አማርኛ
• እንግሊዘኛ
• ሒሳብ
• አካ/ሳይንስ እና
• ሞራል ሲሆኑ ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
• ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፍል ብቻ(5ኛ ክፍልን አይጨምርም)
2. 8ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ) በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
• አማርኛ
• እንግሊዘኛ
• ሒሳብ
• ሶሻል ሳይንስ
• አጠ/ሳይንስ
• የዜግነት ት/ት እና ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
• ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል ብቻ(7ኛ ክፍልን አይጨምርም)
3. 12ኛ ክፍል በተመለከተ
በ2016 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው:: እነሱም :-
ሀ/ የተፈጥሮ ሣይንስ
• እንግሊዝኛ
• ሒሳብ
• ባዮሎጅ
• ፊዚክስ
• ኬሚስትሪ
• ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት
ለ/ የማህበራዊ ሣይንስ
• እንግሊዝኛ
• ሒሳብ
• ታሪክ
• ኢኮኖሚክስ
• ጂኦግራፊ
• ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት
4. የፈተና ዝግጅትም:-
• የኢኮኖሚክስ ፈተና ከ12ኛ ክፍል ብቻ
• ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ-11ኛ በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል::
• ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት በነበረው አሠራር መሠረት ይቀጥላል::
• በመሆኑም የፈተና ወቅት እየተቃረበ በመሆኑ ተማሪዎች በዚህ መረጃ መሰረት በአግባቡ ማጥናት ይጠበቅባቹሀል::
• ት/ቤቶች እና የተማሪ ወላጆች በዚህ መረጃ መሰረት ተማሪዎቻችን አመርቂ ውጤት እንዲያመጡ የጋራ ርብርብ እናድርግ‼️
• ሁሉም ፈተናዎች በሰኔ ወር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል!
• የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት
Forwarded from Mitikkuu Cannaaloo waaqjiraa
workiishiit west.pdf
1.2 MB
Forwarded from Gashawbeza Beza
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ መምህራኖች ፣ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በሙሉ እንኳን ለ 1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ። በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት ፣የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችን ነው።
የት/ቤቱ አስተዳደር
Forwarded from Yidnek Tefera
Genetics work sheet 2016.pdf
135.8 KB
Forwarded from Liken Myhope
G-12 English Worksheet-One.docx
20.7 KB