የፍቅር ታሪክ 🇪🇹
35K subscribers
65 photos
7 videos
322 links
🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹


➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1

Since 2011 E.C.
Download Telegram
​​​​​​​ ​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፍቅር ያሸንፋል🌺
:¨·....................:¨·.


💢ክፍል 6

ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ካሌብዬ ከሰውየው ጋር ሲያየኝ በጣም ተናዶ ጥሎኝ መሄዱ ይበልጥ አስደነገጠኝ እኔ እንኳን ከሱ ሌላ ወንድ የማማግጥበት እና ስለክብሬ እንኳ የማስብ ሴት አይደለሁም እናም ለምን ጠረጠረኝ? ብቻ ተከትዬው ቤት ገባን ከዛ ላረጋጋው ፈልጌ ካሌብዬ አልኩት እሱም ብስጭቱ ሳይለቀው አትጥሪኝ አይነት አስተያየት አየኝ ይሄኔ መታገስ አቃተኝ ምን ሆነሃል እኔኮ ቤተሰቤንና ያደኩበትን ቀዬ ትቼ የመጣሁህ አንተን ብዬ ነው ሂጃቤን ፈትቼ ፀጉሬን እያሳየው ማንነቴን አርክሼ በማላውቀው ማህበረሰብ ውስጥ የምሰራው ላንተ ስል ነው ይግባህ እንጂ እኔኮ ያለምንም እቅድ ድንግልናዬን ያስረከብኩህ ካንተ ውጪ ባዶ መሆኔን እንድታውቅ ነው ለምን አትረዳኝም ለምን ትጠራጠረኛለክ...
እያልኩ እንባ እየተናነቀኝ በጩኸት ተናገርኩ ካሌብዬ ስሜቱ እንደተረበሸ ለማወቅ አይኖቹን መመልከት በቂ ነበር ትንሽ በዝምታ ከቆየን ቀኀላ ካሌብዬም ይቅርታ ጠይቆ አባበለኝ ከዛም የጀመረውን አመት ተምሮ ቀጣይ እኔን እንደሚያስተምረኝ ቃል ገባልኝ በርግጥ ግን እኔ እሱ ቢማርልኝ እመርጣለሁ ከካሌብዬ ጋር ያለምንም ጥንቃቄ ወሲብ መፈፀማችንን ቀጠልን በሰአቱ ማገናዘብ አልቻልንም ነበርና ትንሽ አሞኝ ክሊኒክ ስሄድ እርጉዝ እንደሆንኩ ነገሩኝ ያባቴ እርግማን ወይስ የኔ እንዝላልነት
ሁለቱም መልስ ሊሆኑ ይችላሉ ብቻ ግን ለኔ ሰማይ የተደፋብኝ ያህል ተሰማኝ በሰአቱ ለካሌብ መንገር አልፈለኩም ምክንያቱም እንዳያጣኝ ስለሚፈራ ይወለድ ይል ነበር እኔ ደግሞ በኔ ስህተት
ካሌብ ትምህርቱን አቋርጦ እንዲሰቃይ አልፈልግም ለዛም ሀጥያትን መርጬ ለማሶረድ ሀኪሞቹን ለምኜ ሰውየው ይሰጠኝ በነበረው ብር በመሀፀን የሚከተት እንክብል ሰጡኝ በመጀመርያ ቀላል መስሎኝ ነበር ግን ያን ሳደርግ ከሞት አፋፍ ነበር የተመለስኩት ብዙ ደም ፈሶኝ እራሴን ሳትኩ ከዛ ሀኪም ቤት ገባሁ ይሄኔ ነበር ካሌብዬም አርግዤ እያሶረድኩ መሆኑን ያወቀው ለአንድ ሳምንት ያህል ስራ ቀረሁ ይሄኔ ያ ብር የሚሰጠኝ ሰውዬ
ለሠላም ገንዘብ ይልክልኝ ነበር በጣም የገረመኝ ደግሞ ፍቅረኛ እንዳለኝ እያወቀ ገንዘቡን መስጠቱ ነው ምክንያቱን ስጠይቀው ስለምታሳዝኚኝ ነው ይለኛል ይህ በንዲህ እንዳለ ልክ በሳምንቴ ስራ ጀመርኩ የዛኑ የጀመርኩ ቀን እራሴን አሞኝ ሰአቴ ሳይደርስ ወጥቼ ወደቤት ሄድኩ ይሄኔ ህይወቴን መሉ አስቤው ቀርቶ ላስበው የማልፈልገው ነገር ነበር ያጋጠመኝ ካሌብዬ ከሌላ ሴት ጋር ተቃቅፎ ይሄዳል ማመን አቃተኝ.......


✎ ክፍል ሰባት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ••●◉

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​​​​​​ ​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፍቅር ያሸንፋል🌺
:¨·....................:¨·.


💢ክፍል 7

ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ካሌብዬ ከኔ ሌላ ሴት በእጆቹ መንካቱ የሚያንገበግበኝ ልጅ ዛሬ ተቃቅፎ በጠራራ ፀሀይ መሄዱ እውን አልመስልሽ አለኝ ከማገናዘብ ይልቅ በስሜት መመራት ጀመርኩ እንደ እብድ እያረገኝ እርምጃዬን ጨመርኩ ልክ ካጠገባቸው ልደርስ ስል ድንጋይ አንስቶ ልጅቷን መፈንከት አማረኝ ግን እንደገና ተውኩትና ቀዝቀዝ ለማለት ሞከርኩ እርምጃዬንም ገታሁት ከዛ ካሌብዬን እቤት ሲገባ ተረጋግቼ ልጠይቀው ወይንስ ድንገት ያየሁት መስዬ ላስደንግጠው እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ድንገት እንዴ የኔ ፍቅር በዚ ሰአት ብቻሽን ለምን አልደወልሽልኝም እ አመመሽ አለኝ ካሌብዬ ደረቱ ላይ ልጥፍ እያረገኝ ይሄኔ ያሰብኩት ልክ ባለመሆኑ የደስታ ሲቃ እየተናነቀኝ ደና ነኝ ውዴ እሷ ማናት ግን አልኩት ካሌብዬም ፈገግ ብሎ እየተመለከታት የክፍሌ ልጅ ናት ሪታ ትባላለች አለኝ ፡፡ካሌብዬ ድሮም ሴት ጓደኞች ይኖሩታል ግን በኔ ቀልድ አያውቅም ባጉል ጥርጣሬዬ እራሴን እየወቀስኩ ልጅቷን ተዋወኳት . ሪታ ደስ የምትል ተጫዋች ልጅ ናት ከዛን ቀን ቡሃላም ከካሌብ ጋር ለማጥናት መምጣቷን ቀጠለች ይህ በንዲህ እንዳለም ሪታ የቤት ኪራይ ጨምረውባት አቅም ስላነሳት እስከግዜው ከኛ ጋር ደባልነት ገባች፡፡ ይህ ሆኖም ካሌብና ሪታ እረጅም ግዜአቸውን አብረው እያሳለፉ እንኳን እኔ ምንም አላስብም በካሌብዬም እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ካሌብዬና ሪታ ከትምህርት ሲወጡ እቤት ቡና አፍልተውና ምግብ ሰርተው ይጠብቁኛል ሪታ በጣም ስለምትጫወት ሁሌም ቤታችን ድምቅ ብሎ ነው የሚያመሸው እናም ዛሬም እንደወትሮዬ ሁሉ ሰዓት ደርሶ እቤት እስከምደርስ እየተጣደፍኩ ሳለ አለቃዬ መቶ ከሰኞ ቡሃላ አንድ ቀን ቀን አንድ ቀን ምሽት በፈረቃ እንደምንሰራ ተናገረ ይሄኔ ከምንም በላይ ካሌብዬን ያናደዋል ብዬ እየፈራሁ ማታ ላይ ነገርኳቸው ይሄኔ ካሌብ እንዳሰብኩትም እንዴ ፍቅር አይሆም ጭራሽ ማታ ሲል ሪታ ካፉ ነጥቃ ምን አለበት ስራ አይደል? አለች ይሄኔ ባንዴ እሺ በቃ አለ በሰአቱ ደስ ብሎኝአቀፍኩት ከዛ ግን እሷ ስትናገር ባንዴ መስማማቱ ጥርጣሬ ውስጥ ከተተኝ፡፡ ሁሌም ምሽት ተረኛ ስሆን ካሌብ እየወጣ ይቀበለኛል አንድ ቀን ታድያ ልክ ስወጣ ሆቴሉ በር ላይ አንድ ወጣት ስልክሽን ካልሰጠሽኝ ብሎ ይነዘንዘኛል ይሄኔ ካሌብ አይቶት ከሚጣሉ ብዬ ስልክ ቁጥሬን መናገር ስጀምር ከየት መጣ ሳልለቅ ካሌብ ከጎኔ ቆማል በህይወቴ እንደዛ ቀን ተሸማቅቄ አላውቅም ... አኩርፎኝእቤት ደረስን ከዛም ፊቱን አዙሮ ተኛ፡፡ ከዛ ቀን ጀምሮ ካኮረፈኝ ሳምንት ሞላው የስራ ቦታ ጓደኛዬ ሰላምም ካላናገርኩት ብላ እኔን ቀድማኝ ከስራ ወታ እኛ ቤት ሄደች ከትንሽ ደቂቃ ቡሃላ ስትመለስ ግን ጥሩ ዜና ይዛ አልተመለሰችም ነበር ካሌብዬና ሪታ ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ እንዳየች ነገረችኝ በድንጋጤ ሰማይና ምድር ተገለባበጡብኝ........


✎ ክፍል ስምንት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።



━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ••●◉


💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​​​​​​ ​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፍቅር ያሸንፋል🌺
:¨·....................:¨·.


💢ክፍል 8

ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ሰላም ከካሌብ ከሪታ ጋር ያረገውን ስትነግረኝ እራሴን ስቼ ወደኩ ይሄኔ ሁሉም ደንግጠው ከበቡኝ እናም ውሃ አደረጉልኝ ... ልክ ስነቃ የሆቴሉ አንደኛው መኝታ ክፍል ተዘርሬ ነበር እራሴን ያገኘሁት ልክ ክፍሉን ሳየው በጣም ደንግጬ እንዴ እዚ ምን አረጋለሁ ስል ወድያው ሰላምና የሆቴሉ ማናጀር ተከታትለው ገቡ ልክ ሰላምን ሳያት ተፈጥሮ የነበረውን ለማስታወስ ቻልኩ እንባዬ ጉንጮቼን እያቋረጠ ቁልቁል ይወርድ ጀመር ካሌብዬ በኔ ላይ ሴት ደርቦ እኔን በሳመበት ከንፈሩ ሌላን ሴት መሳሙን ማመን አቃተኝ፡፡ ከማንም ጋር ምንም ሳላወራ ወጥቼ ወደቤቴ መንገድ ጀመርኩ በየመንገዱ እኔና ካሌብዬ ያሳለፍነውን ሳስብና ያለፍናቸውን ብዙ ችግሮች ሳስታውስ ተስፋዬ ይለመልማል ከዛ ደግሞ እናትና አባቴን ከመተው ጀምሮ እምነት አልባ እስከመሆን መድረሴ እውነቴን ነው ወይ እስልምናዬን አጥብቄ አልያዝኩ ወይ አንደኛዬን ክርስትያን ሆኜ አልተጠመኩ ብቻ መሀል መቅረቴ እንዲሁም ትምህርት ማቆሜ እሱ ግን ብዙ ነገሮች እንደሚፈልገው እየሄዱለት እኔም እንደፈለገው እየሆንኩለት ሌላ ሴት ወደ ህይወቱ ማስገባት መቻሉ እራስ ወዳድ ነው እንድል ያረገኛል ... እቤት ልክ ስደርስ ሁለቱም በየ ፍራሻቸው ተኝተዋል እራትም
ሳልበላ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ እስከዛሬ ቡና ይፈላ ይደምቅ የነበረው ቤት በረዶ ሰራ ሰላም ያለችኝን ለማረጋገጥ ያለሰአቴ እቤት ድንገት መድረስ ጀመርኩ ታድያ አንድ የተረገመ ቀን ልክ እቤት ስገባ እሷ ፍራሽ ላይ የእጅና ጓንት ያህል ተጣብቀው ተኝተው ደረስኩ ያኔ ተስፋ ቆረጥኩ ከእምነት ፍቅር ማስቀደሜ ጥፋት መሆኑ ግልፅ ብሎ ታየኝ በድንጋጤ ፈዝዤ እያየኋቸው ሳለ ካሌብ ነቃ ልክ ሲያየኝ በድንጋጤ ተፈናጥሮ ተነሳ እኔም የሀዘኔን መርሻ እንባዬን እያዘራሁ የለበስኳትን እንደለበስኩ ወጥቼ ወደሆቴል አመራሁ ፡፡
...ከዛ ቀን ቡሃላ እዛው ሆቴል ውስጥ እያደርኩ መስራት ጀመርኩ ግን ሁሌም ሃሳቤ አንድና አንድ ነው እሱም ካሌብ ምንም ባደርግ እሱን ማሰቤን ማቆም አቃተኝ በቃ አፈቅረዋለሁ ልረሳው ከበደኝ በጣም ስጨነቅ ደግሞ እራሴን እስታለሁ ያለኝ አማራጭ መጠጣት እራሴን መርሳት ነው ሰላምን ስነግራት ከጓደኞቿ ጋር አስተዋወቀችኝ እነሱ በጣም ዱርዬና ሱሰኛ ናቸው እኔም ከስራ ቡሃላ ከነሱ ጋር ማሳለፍ ጀመርኩ፡፡ አንድ ቀን ታድያ ሰላምና ጓደኞቿ የሚያመሹበት ክለብ ተቀምጠን ስንጠጣ እኔ እንደለመድኩት ስለካሌብ እያሰብኩ ብቻዬን አወራለሁ ይሄኔ ገንዘብ የሚሰጠኝ ሰውዬ ከሰላም ጋር መቶ ካጠገቤ ተቀመጠ.........



✎ ክፍል ዘጠኝ ከ150 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።



━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ••●◉

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​​​​​​ ​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፍቅር ያሸንፋል🌺
:¨·....................:¨·.


💢ክፍል 9

ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ሰውየው ካጠገቤ መቶ ለመቀመጥ ወንበር እያመቻቸ ሁላቹም ጠጡ ሂሳብ እንዳትናንነቁ አላቸው አብረውኝ ወደተቀመጡት ፊቱን አዙሮ እነሱም በደስታ ሰውየውን በየተራ አቀፉት እኔ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አይኔን ብርጭቆዬ ላይ ተክዬ ብቻዬን ማውራቴን ቀጠልኩ በንግግሩ መልስ ያጣው በቀላል አማርኛ ሹገር ዳዲ የሚባለው ሰውዬ ቆንጆ የተከፋሽ ትመስያለሽ አለኝ አሁንም የአይኖቼን አቅጣጫ ሳልቀይር ዝም አልኩት ይሄኔ ማነህ ና ሌላ መጠጥ ታዘዛት አለና ለአንዱ አስተናጋጅ ትዛዝ ሰጠ እኔም ገልመጥ እያረኩት አመሰግናለው መቸገር አይጠበቅብህም አልኩት፡፡ እሱም በመልሴ የምፀት ቃል ፈገግ እያለ ምን መሰለሽ ቆንጆ ብሎ እጁን ወደ ትከሻዬ ላከው ይሄኔ መጠጥ ባደፋፈረው ልቤ ተማምኜ ከወንበሬ ተፈናጥሬ እየተነሳሁ እንዳትነካኝ ሰውዬ ወንዶች ስትባሉ ከሴት ጭን ውጪ የሚያስብ አእምሮ አልታደላቹም አልኩትና ጥያቸው መታጠብያ ክፍል ገባሁ፡፡
መታጠብያ ቤት ገብቼ ትንሽ እራሴን ካረጋጋው ቡሃላ ልወጣ ስል ሰላም ተከትላኝ ኖሮ መጣች እኔም አልፌአት ልሄድ ስል ያስሚን አለች እርምጃዬን ገታ አድርጌ ቆም አልኩ ተረጋጊ ውዴ ሰውዬው ላይ እንደዛ መሆን አልነበረብሽም አለችኝ ምንም ሳልመልስላት ትቻት ቦታዬ ሄድኩ ልክ ስቀመጥ ሰውየው ጠጪ አለኝ ባትለኝም እጠጣለው ብዬ ብርጭቆዬን አንስቼ ጨለጥኩትና ተነስቼ ወጣሁ ከዛም ወደ ሆቴል መንገድ ጀመርኩ፡፡ ሞቅ ስላለኝ ምንም አላውቅም ነበር ብቻዬን ስሄድ አንዴ ስስቅ አንዴ ሳለቅስ እብድ እመስል ነበር በዚ መሀል አንድ መልኩን በደምብ ያላየሁት ወጣት ሰላም አለኝ ቀናም ብዬ ሳላየው ዝም ብዬው መንገዴን ቀጠልኩ ኧረ አናግሪኝ ብቻሽን ከምሄጂ ስለሀገር ጉዳይም ቢሆን እናውራ ሲል ንግግሩ ፈገግ አስብሎኝ ቀና ብዬ አየሁት ከዛም አመሰግናለው አብረሽኝ ለመሄድ ስለተስማማሽ አለ ፈገግ እንዳልኩ እብድ አልኩት ልጁ ዮናስ ይባላል አቋሙ በጣም ያምራል በዛ ላይ ለዛ ያለው ቀልዱ ሀዘን ያስረሳል ያን ቀን ሆቴል ድረስ እያሳቀኝ ሸኝቶኝ ስልኬን ተቀብሎኝ ተለያየን፡፡ በርግጥ ከዚ ቡሃላ ምንም አይነት ወንድ መቅረብ አልፈልግም በነጋታው እራሴን አሞኝ ስለነበር ተኝቼ ዋልኩ ከዛ ወደማታ ስልኬ ጠራ አንስቼ ሀሎ ስል ሪታ ነኝ ያስሚን የካሌብ ብላ...
ንግግሯን ሳትጨርስ ስልኩን ዘጋሁባት ንዴት መላ አካሌን አንቀጠቀጠኝ ከዛ ተነስቼ ትላንት ስጠጣ ያመሸሁበት ክለብ ሄድኩ ልክ ስደርስ የማላውቀው ስልክ ተደወለ ላለማንሳት ፈልጌ ዝም አልኩት ደግሞ ሲጠራ ግን አንስቼ ማን ልበል አልኩ ቁጣ በሚመስል ድምፅ ይሄኔ ኧረ ቀስ ሆ ስልኬን በቁጣ አታሳቂያት አለኝ ዮናስ ነበር ባያየኝም ፈገግ አልኩ የት ነሽ አለኝ ከዛ ያለሁበትን ነግሬው አየጠጣሁ ነው እንዳትመጣ ብዬ ዘጋሁበት፡፡
ከደቂቃዎች ቡሃላ የትላንትናው ሰውዬ መጣ ከዛም ከጎኔ ተቀመጠ ዝም ብዬ መጠጣቴን ቀጠልኩ ከዛ ግን እንዴትና በምን እንደሰከርኩ ባላቅም ስነቃ የሚያምር አልጋ ላይ እርቃኔን ተኝቻለሁ ደንግጬ ተፈናጥሬ ስወርድ ማንም የለም የማታው ሰውዬ አስክሮ እንደደፈረኝ ገባኝ መጨረሻዬ ይህ መሆኑ ይበልጥኑ አስለቀሰኝ......


✎ ክፍል አስር ከ200 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━
••●◉Join us share ••●◉


💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​​​​​​ ​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፍቅር ያሸንፋል🌺
:¨·....................:¨·.


💢ክፍል 10

ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ



እንዴት በቶሎ ሰከርኩ ወይስ እራሴን እንዳላውቅ መጠጤ ውስጥ መዳኒት አረጉብኝ? ምንም አላውቅም ብቻ ከንቅልፌ ባልነቃ ይሻለኝ ነበር እንደዛ እያለቀስኩና ደፍሮኛል ብዬ ያሰብኩትን ሰውዬ ምን እንደማደርገው እየዛትኩ የስልኬ ጥሪ አቃጨለ በዛ ስሜት ውስጥ ሆኜ ማውራት አይደለም ደዋዩን ማየት አልፈለኩም ዘጋ ከዛ ድጋሚ ተደወለ አሁንም ዘጋ በመጨረሻ አነሳሁት ይሄኔ የኔሰካራም አስቸኳይ ጉዳይ ስለነበረኝ ነው ሳትነቂ ትቼሽ የሄድኩት አለኝ ይሄ በትክክልም የዮናስ ድምፅ ነው ግን ጆሮዬን ማመን አቃተኝና ማን ልበል አልኩ ወይ ጣጣ ሰካራም ጓደኛ መያዝኮ ችግሩ ይሄ ነው ዮናስ ነኝ ስመጣ የተፈጠረውን እነግርሻለሁ አለኝ የማወራው ስለጠፋብኝ ምንም ሳልለው ተሰናብቶኝ ስልኩን ዘጋው፡፡ በህይወቴ እንደዚ ጓጉቼ የማውቅበት ቀን ትዝ አይለኝም ዮናስን አግኝቼው ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓጓው አንድ ልቤ ደግሞ ከኔ ጋር ነው ያደርሽው ቢለኝ ሀፍረቱን መቋቋም የምችል አልመስልሽ አለኝ ብቻ ግን ሰአቱ መገስገሱን ቀጥሎ ፀሃይዋ ለመጥለቅ ትሰናዳ ጀመር እኔም ስራ የማታ ተረኛ ስለነበርኩ የመስተንግዶ ዩኒፎርሜን ለበስኩ ምሽት 12፡00 ሰአት ላይ ዮናስ ደወለ ስራ መሆኔን ስነግረው መጣ ግን ለማውራት እድል አጣሁ እሱም ይህን ተረድቶ ጠዋት እንደሚመጣ ቃል ገብቶልኝ ወደ ቤቱ ሄደ:: ልክ ሲነጋ ከእንቅልፌ ስነቃ ቶሎ ብዬ ስልኬን አየሁ መልክት ገብቶልኝ ነበር ዮኒ ነው እዛው አካባቢ የሚገኝ ካፌ ቀጠረኝ ተጣጥቤ ወደዛው አመራሁ ልክ ስደርስ ተነስቶ ሰላም አለኝና እንድቀመጥ ወምበር ስቦ ጋበዘኝ ለሴት ልጅ ክብር እንዳለው ያሳያል እኔ ግን ጉዳዬ የትላንት አዳሬን ማወቅ ነበር እናም ትኩስ ነገር አዘን ማውራት ቀጠልን፡፡ እእእእእእ አልኩ ጥያቄዬን ከምን መጀመር እንዳለብኝ ለማሰብ እየሞከርኩ የኔ ቆንጆ የምሬን
ልንገርሽ በጣም ታምሪያለሽ አለኝ ይሄኔ እንዲ ሊከዳኝ እንደንግስት ሲክበኝ የኖረው ካሌብ ትዝ አለኝና አይደል አልኩት እውነቴን ነው ትላንት ያ ሰውዬ ቀጥሮሽም ቢሆን ፈልገሽም ብትሄጂም የእንቅልፍ ኪኒን ብርጭቆሽ ውስጥ መጨመሩ አናዶኛል ሲቀጥል ገና ልጅ ነሽ እድሜሽን ከሚመጥን ሰው ጋር አትዝናኚም?አለኝ፡፡ ንግግሩ ይበልጥ ሳበኝ ኪኒን? ብዬ ቃሉን ደገምኩትና አስከትዬ ከዛስ ቆይ አንተ እንዴት... ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ እኔ ገና በግዜ ስደውልልሽ ያለሽበትን ነግረሽኝ ነበር በርግጥ ና አላልሽኝም ግን መጣሁ ስመጣና ከሰውጋ ሳይሽ ልክ ባልሆንም ከፋኝ ከዛ ሰውዬውን እህቴ ናት ስለው አንቺም ምንም ብሰክሪም እንኳን አላሳፈርሽኝም ወንድሜ ነው ብለሽ ሙጭጭ አልሽብኝ እናም ይዤሽ ያደርሽበት ሆቴል ወሰድኩሽ አለና ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ደሞ ያሳቅሽኝ አብረከኝ ሁን እፈራለው እያልሽ ስታለቅሺ አንጀቴን ነበር የበላሽኝ አለ ይሄኔ እኔም ምን እንዳረኩ እንኳ ባለማስታወሴ በሀፍረት አቀርቅሬ ፈገግ አልኩ ሳላስበው ደግሞ ምንም ሳያረገኝ ከዛ ሰውዬ ስላስጣለኝ በጣም ተደስቼና ወንድም ያገኘው ያህል ተሰምቶኝ ተነስቼ ጥምጥም አልኩበት ይሄኔ ከየት መጣ ሳልለው ካሌብዬ ከሰላም ጋር ካጠገቤ መቶ ቆመ ድንግጥ ብዬ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ይሄኔ ካሌብ አሀ ለካ አንቺም ወንድ አጊንተሽ ነው ትተሺኝ የሄድሽው አለኝ..........


✎ ክፍል አስራ አንድ ከ200 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ••●◉

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄ ​
​​​​​​​ ​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፍቅር ያሸንፋል🌺
:¨·....................:¨·.


💢ክፍል 11

ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ



በርግጥ ካሌብዬን አሁንም ቢሆን አልጠላሁትም ያም ማለት ግን በሱ ተስፋ አልቆረጥኩም ማለት አይደለም እናም ካጠገቤ መቶ ሲቆም ብደነግጥም በንግግሩ ግን በጣም ተናደኩ የከዳኝ ሳያንሰው ከዮናስ ጋር ጠረጠረኝ መጠርጠሩም ሳያንሰው ይሄን ያክል ቀን የት እንደሆንኩ እንኳ የማያውቅና ያላሳሰበው ሰው ዛሬ ደርሶ እሱው ተበዳይ ሆነ ሁኔታዬ ሲቀያየርበት ዮናስ ያስሚን ችግር አለ እነሱ ማናቸው አለኝ ይሄኔ ሰላም ቀበል አድርጋ እሱ ፍቅረኛዋ ነው እኔ ደግሞ ጓደኛዋ ስትል ንዴቴን መቆጣጠር ይሳነኝ ጀመር ግን ከመናገር ይልቅ ጥያቸው መሄድን መረጥኩ ዮናስ አላስቻለውም ጠብቂኝ ቢያንስ ልሸኝሽ አለኝ ፀጥ ብዬው እርምጃዬን ቀጠልኩ ፡፡
ዮናስም ከጎን ከጎኔ እየሄደ ባለትዳር ነበርሽ እንዴ አለኝ ዝም አልኩት እሺ ተይው አትንገሪኝ ቅድም ስታቅፊኝኮ ሀንግ ልትሰሪኝ ነው የሚመስለው የማቀፍ ልምድ እንደሌለሽ ያስታውቃል ሆ አንቀሽ ልገዪኝ ... አለና ከት ብሎ ሳቀ እውነትም ዮናስ ይለያል ከካሌብ ጋር ያሳለፍኩትን እያሰብኩ ስረበሽ እሱ ግን አስረሳኝ ጭራሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን እረስቼ መሳቅ ጀመርኩ ከዛ ወደስራዬ ገባሁ ማታ ልምጣ ሲለኝ እና ላትመጣ ነው አልኩት እውነትም ቢቀር ይደብረኛል እሱም አንድ ቀን እንደካሌብ ቢከዳኝም እስከዛው ግን አብሬው በንፁ ጓደኝነት እቀጥላለው፡፡ እየሰራው የማስበው ጠዋት ካሌብዬ እንዴት ሰላምን አግኝቷት ነው አሷ ደሞ ማን ካፌ እንዳለው አውቃ ነው ይዛው የመጣችው እንዴት ወደኛ መጡ የሚለውን ነው ሲቀጥል ሰላም እንደዛ እንደተጎዳሁ እያወቀች ከካሌብ ጎን እንዴት ትቆማለች ጭራሽ ዮናስ እንዲርቀኝ ብቻ ሰላም ሁሉም ጠባሳዎቼ ላይ አሻራዋ ይታየኝ ጀመር እቺ ልጅ ከኛ ስር ለምን አልጠፋ አለች?? ብቻ ጭንቅላቴ እንዚን ጥያቄዎች እየፈጠረ ያስጨንቀኛል ግን ምንም መልስ ስላልነበረኝ በቃ አጋጣሚዎች ናቸው ብዬ አልፈዋለው. እንደምንም መሸ ይሄኔ ተጣጥቤ ልብሴን ቀይሬ ልወጣ ስል በር ላይ ካሌብን አገኘሁት አናግሪኝ አለኝ ግን ላናግረው አልቻልኩም ምክንያቱም በሱ ምክንያት እየሆንኩ ያለሁት በጣም ይጎዳል ዝምብዬው ስሄድ ለዚ ነበር ብዙ ፈተና አልፈሽ እኔን መርጠሽ የመጣሽው ለዚ ነበር አባትሽን አልሰማ ብለሽ እኔን የመረጥሽው? አለኝ ይሄኔ እርምጃዬን ገታ አድርጌ ማሰብ ጀመርኩ ከዛም ዞር ብዬ ምን ቀረህ ወይስ ሪታ ጥላክ ሄደች አልኩት እንደምታስቢው አይደለም ሲል ሊያሳምነኝ ሞከረ እኔም ከስካሁኑ ልፋቴ አይበልጥም ይቅርታ ላርግለት ብዬ ይቅርታ አረኩለት፡፡ ከካሌብ ጋር እንደገና አብረን መኖር ጀመርን በርግጥ በሙሉ ልቤ አላመንኩትም ግን ግዜ ሁሉን ያሳየኛል በሚል ፍቅር መስጠቴን ቀጠልኩ ሪታ ከቤታችን ወታለች ግን የት እንዳለች መጠየቅ አልፈለኩም ዮናስንም ሳገኘው ስለካሌብ ሁሉንም አጫወትኩት ግን ዮኒ ለምን ቀድመሽ አልነገርሽኝም አላለኝም ወንድም ሊሆነኝ ቃል ገባልኝ ካሌብዬ ደግሞ ዮናስ ከሚባል ልጅ ራቂ ሲል አስጠንቅቆኛል እኔም ካሌብዬን ቅር ከሚለው እያልኩ ዮናስን ማግኘት ተውኩ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ተነስቼ ቁርስ እየሰራው ቤት አፀዳለው ይሄኔ የፍቅሬ እንቅፋት ሪታ በር አንኳኳች ስከፍት እሷ ናት በሩን ብጠረቅምባት ደስ ባለኝ ግን እንደምንም እራሴን ተቆጣጥሬ ምን ፈለግሽ አልኳት ካሌብን አለችኝ ካሌብዬ ተኝቷል አልኳት ፊቷ ልክ አይደለም እናም ችግር አለ አልኳት ይሄን ስል እንባዋ ዱብ ዱብ እያለ እርጉዝ ነኝ አለች ይህን ስትል ከካሌብ ነው እንደምትለኝ እርግጠኛ ሆንኩ ብዥ አለብኝ ... እኔና ካሌብ ታርቀን በፍቅር 3 ወር እንኳ ሳንቆይ ሪታ እንደገና ህይወቴ ውስጥ ጣልቃ ገባች መቋቋም አቅቶኝ እራሴን ሳትኩ......


✎ ክፍል አስራ ሁለት ከ200 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።



━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ••●◉

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​​​​​​ ​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፍቅር ያሸንፋል🌺
:¨·....................:¨·.


💢ክፍል 12

ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ ሊያልቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀረው


ሪታ እርጉዝ ነኝ ብላ ስትመጣ ራሴን ሳትኩ እሱን ብዬ የተንከራተትኩለት ፍቅረኛዬ ሌላ ሴት አስረግዞ ሳይ ዳግም በህይወት መኖር በራሱ ሞት ነው የመሰለኝ ከደቂቃዎች ቡሃላ ስነቃ ካሌብ እጆቹን አንተርሶኝ ምንጣፍ ላይ በጀርባዬ ተንጋልያለሁ ሪታ የለችም ነቅቼ ጠባብ ቤታችንን ስቃኛት ካሌብ ነቃች አለና እምባው ወረደ ያዞ እምባ አልኩ በውስጤ ዛሬ እንዲያውም የተፈጠረውን ለማስታወስ ማንንም መጠየቅ አልፈለኩም እናም በፍቅር ከምወዳቸው እጆቹ ላይ ተነሳሁ እንባዬ ሀዘኔን ያቀለው ይመስል ያለማቋረጥ እየወረደ በውሃ የራሰው ልብሴ ላይ ያርፋል እንደምንም ስሜቴን ተቆጣጥሬ ልብሴን ሰብስቤ ሻንጣዬ ውስጥ ከተትኩት ይህን ሳደርግ ካሌብ በጥሞና ይከታተለኝ ነበር ከዛም ምንም ቃል ሳልተነፍስ ወደበሩ አመራሁ፡፡
ልክ በሩጋ ስደርስ ግራ የተጋባ እያስመሰለ ምን ተፈጠረ ውዴ ድጋሚ ጥለሽኝ ልትሄጂ ነው አለኝ ቀጣፊ እምባውን እያዘነበ እስከዛሬ ቢሆን ሲያስነጥስ እንኳ እንባው ብትረግፍ ውስጤ በሀዘን ይጥለቀለቅ ነበር ዛሬ ግን እንዲ እያለቀሰና እየተማፀነኝ ፍፁም ሊያሳዝነኝ አልቻለም! ሪታስ አልኩት ይሄኔ አይኖቼን ላለማየት
እያቀረቀረ ሲጀመር ለምን እንደመጣች አላውቅላትም ሄዳለች አለኝ ይሄኔ ይበልጥ እየተናደድኩ ካሌብ ከዚ ቡሃላ ልትዋሸኝ አትችልም ይልቅ ፈጣሪ የሰጠህን ፀጋ አትግፋ ልጅህን እመንና አሳድግ እኔም ፈጣሪ ይገባሻል ያለኝን እያደረገ ነውና አርፌ እቺ አፀያፊ ህይወቴን ልኑራት ብዬ ገፍቼው ወጣሁ እንደዛ ሲሆን አይቼው አላውቅም መሬት ላይ ተደፍቶ ተንሰቀሰቀ ግን ሊያስቆመኝ አልቻለም ፡፡
ወጥቼ ሆቴል ልሄድ በየመንገዱ ብቻዬን እያወራው አለቅስ ነበር ከዛ ሆቴል ደርሼ የሰራተኞች ክፍል ገብቼ ተቀመጥኩ የሙሃሙድ ዘፈን ተከፍቶ ያቀነቅን ነበር
ተው ልመድ ገላዬ ገላዬ
ተው ልመድ ገላዬ
ትቶህ የሄደን ሰው ገላዬ
አትበል ከላላዬ...
ይላል ይሄን ሙዚቃ ስሰማ ቁስሌ የተነካ ያህል ተሰምቶኝ ተንሰቀሰኩ እእእእእ ከዛ እዛው የተቀመጥኩበት ጋር ጋደም አልኩና እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ልክ ስነቃ ሰአቱ ወደ መምሸት ተቃርቧል ከዛም እራሴን
መጠጣትና አጉል ሱሶችን መተው እንዳለብኝ አሳመንኩት ግን ስራ እስከማገኝ እዛው ሆቴል እያደርኩ መስተንግዶ መስራቴን ቀጠልኩ ሴት ልጅ ፈተናዋ ብዙ ቢሆንም የኔ ግን ልክ አጣ የሆቴሉ ባለቤት ልጅ እዛው ማደሬን ሲያይ ይፈታተነኝ ጀመር አንድ ቀን ዮናስ አጋጣሚ መጣ ከካሌብ ጋር እንደታረቅን ካወቀ ቡሃላ መቶ የማያውቀው ዮናስ ዛሬ ሳየው ልክ አባቷን እንዳየች ህፃን እምባዬ ባይኔ ሞላ የሚገርመው ፊቴን አይቶ ውስጤን ማንበብ ይችላል እናም ውጪ እፈልግሻለው ብሎኝ ወጣሁ እያለቀስኩ ካሌብ ያረገኝን ሁሉ ነገርኩት አባብሎኝ ሄደ ፡፡
ከዛ እንደቀድሞው እንገናኝ ጀመር ሁሌም እንደሚያረገው ያስቀኝና ሀዘኔን ያስረሳኛል አልፎም ስለ ወደፊት ይመክረኛል ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ማታ ተረኛ ሆኜ ቀን ላይ ከዮናስ ጋር ስንዞር ዋልን ፊልም አየን ብቻ ደስተኛ ነበርኩ የሚገርመው ምንም ያህል አብረን ብናሳልፍ ሴትነቴን ወይም ገላዬን አይመኝም ታድያ አብረን ውለን ልክ የስራ ሰአቴ ሲደርስ ወደ ሆቴል ሸኝቶኝ ተመለሰ ያን ቀን የባለቤቱ ልጅ ነበር እሱ ሲኖር ሁሉም ነገር ይቀፈኛል ዛሬም ልክ እንደዛው እየደበረኝ ሳስተናግድ ቆይቼ ሰአት ሲደርስ ልተኛ ክፍሌ ገባሁ ይሄኔ ተከትሎኝ ገባና ከውስጥ ቆለፈው ብጮሂ እገልሻለሁ አለኝና ልብሱን ለማውለቅ ቁልፉን ይፈታ ጀመር.....


✎ ክፍል አስራ ሶስት የመጨረሻው ክፍል ነገ ከ300 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል.... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

••●◉Join us share ••●◉

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​ፍቅር ያሸንፋል🌺 :¨·..........:¨·.
መጨረሻው ክፍል💖


ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ልጁ ሊደፍረኝ ይጣደፍ ጀመር ብጮሂ እገልሻለው ቢልም እኔ ግን ሞትን መርጬ ሆቴሉን በጩኸት አደባለኩት ይሄኔ ደንግጦ በፍጥነት ክፍሉን ለቆ ወጣ ወድያው የሆቴሉ ሰራተኞችና ጥበቃው እየተንጋጉ መጡና ምን ሆንሽ አሉኝ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል ጭንቀት ነው ይቅርታ ከረበሽኳቹ አልኳቸው በድንጋጤ ግምባሬ ላይ ችፍ ያለውን ላብ እየጠረኩ አንዳንዶቹ እየተነጫነጩ አንዳንዶቹ ደግሞ በሁኔታዬ አዝነው ትተውኝ ወተው ሄዱ፡፡ ልክ ሲነጋ ለዮናስ ደወልኩለት አማራጭም አልነበረኝም ሰላምና ጓደኞቿ ጋር ብሄድ ተመልሼ ወደ ሱስ እንደምገባ አውቅ ነበር ለዛ ነው ዮናስን የመረጥኩት ደውዬ ከሆቴል መውጣቴን ስነግረው ያለሁበት ድረስ መቶ እቤቱ ወሰደኝ ብቻውን ነው የሚኖረው ግን ቤቱ በጣም ያምራል ቤተሰቦቹ አሜሪካ መሆናቸውን ነገረኝ ለምን እሱ እዚ እንደሚኖር ስጠይቀው መልሱ አንድ ነበር ከሀገር መውጣት አይፈልግም፡፡ ዮናስ ጋር መኖር ከጀመርኩ 1 ወር ሞላኝ ዮናስ ግርም የሚል ሰው ነው እጅግ በጣም ቆንጆና ሀብታም በዛ ላይ እድሜው ከ27 አይበልጥም ግን ለሴት ልጅ ያለው ክብር በዛ ላይ አንድ ቀን እንኳ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮም ሆነ በመልክና ገንዘቡ ሴት ማማለል ሲፈልግ አይቼው አላውቅም አብረን መኖራችንን ቀጠልን እኔም ስራ ፈልጌ ስላጣሁ ስደት ለመሄድ ማሰብ ጀመርኩ ይሄንንም ለዮናስ ሳማክረው ደስ እንዳላለው ነገረኝ፡፡ ይልቁንም አሁን ቤተሰቦቼን መጠየቅ እንዳለብኝ መከረኝ እኔ ግን ቢያንስ እንኳ ገንዘብ ይኑረኝ ለፍቅር ብዬ የከዳሁትን አባቴን ባዶዬን አይኑን ማየት አልችልም ያሳፍረኛል ነበር መልሴ ፓስፖርት አውጥቼ ደላላ ጋር ሄድኩኝ ከዛም ወደዱባይ ለመሄድ ፕሮሰስ ጀመርኩ ይሄን ሳደርግ ዮናስ በጣም ተናዶብኛል ግን እድሜ ልክ የሚያኖረኝ የለም እሱም ቢሆን ሰው ነው አንድ ቀን ይሰለቸዋል ስለዚህ የሱን መናደድ ቦታ ሳልሰጠው መሯሯጤን ቀጠልኩ ታድያ አንድ ቀን ሙሉ ምርመራ ተመርምሬ ውጤት ለመላክ ስመረመር ውጪ መሄድ እንደማልችልና የልብ ድካም እንዳለብኝ ተነገረኝ፡፡ አሁን የምርም ፈጣሪ እንደረሳኝ አመንኩ ከዛም በጣም በንዴት ወደ መጠጥ ቤት ሄድኩኝ ልክ ገብቼ መጠጥ እንዳዘዝኩኝ ዮናስ ደወለ ገና ከማንሳቴ ጫጫታውን ሰምቶ እንዴ ደሞ ምን ሆነሽ ነው ወደተውሽው ማንነትሽ የተመለሽው አለኝ በቁጣ እኔም ከንግግሬ እምባዬ እየቀደመ ተስፋ ቆርጬ ነው ዮኒዬ ለማያውቀኝና ለረሳኝ ፈጣሪ ከዚ ቡሃላ አልጨነቅም አልኩት አሁኑኑ መጣው ብሎኝ ስልኩን ዘጋው ህይወት እንደዛ ቀን ተስፋ አስቆርጣኝ አታውቅም ከሀዘኔ ብዛት ማልቀስ በራሱ ተሳነኝ፡፡
ከተቀመጥኩ ከደቂቃዎች ቡሃላ አጋጣሚ ስዞር ሰላምና አንድ የማላውቃት ሴት ከካሌብ ጋር ክብ ሰርተው የመጠጥ አይነት ከፊታቸው ተደርድሯል እያየኋቸው መናደዴን ቀጠልኩ ከቆይታ ቡሃላ ሽንት ቤት ስሄድ ሰላም ተከትላኝ መጣች ባላያት ደስ ይለኛል እንኳን ቆሜ ላወራት ይሄኔ ከት ብላ እየሳቀች ዮኒ እቅዶቹ ሰርተውለታል አይደል አለችኝ ሁኔታዋ መስከሯን ያሳብቃሉ ምን ማለት ነው አልኳት ንዴት መላ አካላቴን እየወረረው ማለትማ አንቺን በእጁ ለማስገባት እንደለፋ አልቀረም መልአክ መስሎ...አለችና ከት ብላ ሳቀች በጣም ተናድጄ በጥፊ አልኳትና ልደግማት ስል ሰው ያዘኝ ግን ምን ለማለት ይሆን ደግሞ ከዮናስ ልታጣላኝ ነው ወይስ እውነት ያለችው ልክ ነው??? እኔና ሠላም መታጠብያ ቤት በር ላይ ግብ ግብ እንደገጠምን ወድያው ካሌብና ጓደኛዋ መጡ ልክ ሲያየኝ ፊቱ ተቀያየረ ምንድነው የመረጥሽውን መርጠሽ ሄደሻል ምን ቀርቶሽ ነው የምትከታተይኝ አለኝ በጣም ተናድጄ ቆይ አንተ ምንድነህ ካላሳበድከኝ አተወኝም ማለት ነው አልኩት ሁለታችንም በስሜት ከማውራታችን የተነሳ ሰው ፀጥ ብሎ ይሰማን ጀመር አስመሳይ ነሽ ለስሙ ስንት ፈተና አይተሻል ለስሙ ቤተሰብሽን ትተሻል ግን ያሁሉ መስዋዕት መክፈልሽ ዛሬ ሌላ ወንድ ያስመለክትሻል ብዬ አስቤም አላውቅም አንድ ቃል እንኳ ልሰሚኝ አትፈቅጂም ሁሉም ግን በግዜው ይገባሻል ሪታንም ቢሆን ሰበብ ያረግሽው አውቀሽ ነው ጭራሽ አስረገዝካት አልሽኝ ትንሽ እንዲመሳሰልልሽ ከሌላም ቢሆን ያረገዘች ሴት መፈለግ ነበረብሽ ያላረገዘን ሰው ግን ብሎ ንግግሩን ገታውና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰና ባንቺ ምክንያት ቤተሰቦቼ ተስፋ ያረጉትን ትምህርቴን አቆምኩ ደስ ይበልሽ ገና ልክ እንደዚ ጨርቄን ጥዬ አብዳለው...አለና የለበሰውን ቲሸርት እላዩ ላይቀደደው የእውነት ደነገጥኩ ግራ ገባኝ ይሄ ሁሉ ሲሆን የነበረው እኔና ካሌብን ለማለያየት ነው? እሺ ዮናስ ማነው እንዴትስ አገኘኝ ሰላም ቅድም እንዳቀደው በጁ አስገባሽ ያለችኝ እውነቷን ከሆነ አንድ ነገር አለ .... ይሄን እያሰብኩ እዛው ዞረብኝ የማስበው ነገር ካቅም በላይ ሆነብኝ ይሄኔ ጥያቸው ለመውጣት ስጣደፍ ዮናስ መጣና ያስሚንዬ ምንድነው አለኝ ምን እንደሆነማ አንተን ልጠይቅህ እስቲ ንገረኝ ካቅም በላይ ጥሩ የሆንክልኝ ለምንድን ነው አልኩት ንግግሬን ለቅሶዬ እያቆራረጠብኝ... ይሄኔ ሰላም ያለወትሮዋ እምባዋ እየወረደ ከዚ በላይ ካሌብ ሲሰቃይ ማየት አልፈልግም ሁሉም ነገር ድራማ ነበር ሪታን መሀል ያስገባትና እኔም ይበልጥ እንድትራራቁ ሳደርግ የነበረው ዮናስ አፈቅራታለው እናም በጄ አስገቡልኝ ብሎ ገንዘብ ይሰጠን ስለነበር ነው አሁን ግን በቃኝ ለካሌብ ሌላ ለያስሚን ሌላ እያወራውና እያሳየው ማራራቄ በቃኝ ፈጣሪስ ምን ይለኛል ብላ እያለቀሰች ወታ ሄደች ህልም ይሁን እውን መለየት አቃተኝ ሁሉም ሰው ግራ እንደገባው መገመት ቀላል ነበር፡፡ ወዴት እንደምሄድ ባላውቅም ልወጣ መንገድ ስጀምር ዮናስ ከፊቴ ቀድሞኝ መንገድ እየዘጋብኝ ሰክራ ነው አትስሚያት አለኝ ምንም ሳልለው እጁን አስለቅቄው መንገድ ስጀምር ሪታና ሰላም ተከታትለው ገቡ ከዛ ሪታ እግሬ ላይ ወድቃ እያለቀሰች ይቅርታ ጠየቀችኝ ፊልም የምተውን ይመስል ግራ ተጋባሁ ምንም ሳልላት ቆሜ ሁሉንም ማየት ጀመርኩ ይሄኔ ካሌብ እንደ እብድ እያረገው ሪታን ከግሬ ላይ አንስቶ ሁለቴ በጥፊ መታት ይሄኔ ካሌብዬ እረፍብዬ እጁን ያዝኩት፡፡ የኔና የካሌብ እንቅፋት ለካ መልአክ መስሎ የቀረበኝ ዮናስ ኖርዋል እምነትን መጠበቅ ግድ ቢሆንም ፍቅር ያሸንፋል ና እኔና ካሌብ ወደቀድሞ ፍቅራችን ተመልሰን መኖር ቀጥለናል ትምህርታችንንም ቀን እየሰራን ማታ መማራችንን ቀጥለናል መሀላችን ከፈጣሪ በቀር ማንንም አናስገባም ቤተሰቦቼንም ጋር እራሱ በስልክ ተጣርቀን ለበአል ደግሞ ከካሌብ ጋር ሄጄ ይቅርታ ልጠይቅ ተስማምተና.......


━━━━━━✦ተፈፀመ✦━━━━━━

••●◉Join us share @Yefkrtarik
የፍቅር ታሪክ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄
​​ ┈┈••◉◈◉●••┈
ፈ ተ ና 🌺
:¨·....................:¨·.



ሰላም👏 ውድ የቻናላችን አባላት ፈተና💔 የተሰኘውን እጅግ አጓጊና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር🌺 ታሪክ ይዤ መጥቻለው እንደምትወዱት አልጠራጠርም ይጀምር ካላችሁ ከታች የልብ ምልክቱን አንድ ጊዜ በመንካት vote❤️ በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን ከ200 vote❤️ በኋላ ይለቀቃል።

ፈተና 💔 እንዳያመልጣችሁ።

━━━━━✦🌺✦━━━━━
••●◉Join us share @Yefkrtarik
የፍቅር ጊዜ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​​​​​ ┈┈••◉◈◈◈◉●••┈
ፈ ተ ና💔
:¨·.◈............◈:¨·.


♥️ ክፍል 1

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺

ቅድስት እባላለሁ አሳዛኝ የፍቅር ታሪኬን ላጫውታችሁ ወደድኩ እኔ የምኖረው ከእናቴና ከታናናሽ ወንድሞቼ ጋር ነው ታድያ ገና የአስረኛ ክፍል አጠናቅቄ ውጤት ቀርቶብኝ የግል ለመማር
እያቀድኩ ሳለ ጎረቤታችን ኢሳያስ የሚሰራበት የግል ድርጅት ውስጥ ሰአት ተቆጣጣሪ እንደሚፈልጉ ሰማሁ ትምህርት አስጠልቶኝም ስለነበር ስራውን አነጋግሬአቸው ጀመርኩ... ስራ ቦታው የራሱ የሆነ የማይረሳ ትዝታ አለው ፈርኒቸር ቤት ነበር እናም ሰራተኞቹ እርስ በርስ ያላቸው ድጋፍ ያስቀናል ... ይሄኔ
ነበር ልኡልን እዛው ሲሰራ ያየሁት ታድያ ልኡልን ድንገት ላየው እንጨት ሲፈቀፍቅ የሚውል አይመስልም በጣም ያምራል ቀላ ብሎ እረዘም ሲል ትናንሽ አይኖቹ እንደጨረቃ ያበራሉ ፈገግታው ልብ ይሰርቃል ... ይገርማል በዛ እድሜዬ ማፍቀር ቀርቶ ስለፍቅር ማሰብ ከባድ ነበር ይሁንና ለልኡል ፍቅር ይሁን አድናቆት የማላውቀው ስሜት አለኝ ... ግን ልኡል ላይ አይኔ አረፈ ...በስራው ጎበዝና ታታሪ ነው። ታድያ አንድ ቀን ምሳ በልቼ ፀሀይ መሞቅ ጀመርኩ ይሄኔ ልኡልና ጓደኛው እያወሩ መጡ ሁሌም ቢሆን ሳየው ደስ ይለኛል እኔ መቆም ካለብኝ ቦታ እሱን ለማየት እሱ የሚሰራበት ቦታ ድረስ እሄድ ነበር ታድያ ዛሬ ለኔ አዲስና አስደሳች ቀን ነበር ልኡሌ
ከጓደኛው ጋር ሲገባ በአይኑ አወራኝ አላመንኩም በፈገግታ መለስኩለት ... ከዛን ቀን ቡሃላ ከእይኖቻችን ባለፈ የተመጠኑ ቃላቶችን መጠቀም ጀመርን.......


✎ ክፍል ሁለት ከ150 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

••●◉Join us share ••●◉

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
ቴሌግራም | t.me/Yefkrtarik
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://vm.tiktok.com/vLYd9D/
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​​​​​ ┈┈••◉◈◈◈◉●••┈
ፈ ተ ና💔
:¨·.◈............◈:¨·.

♥️ ክፍል 2

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺

ቀናቶች በሄዱ ቁጥር መግባባታችን
እየጨመረ ሄደ አንድ ቀን ከስራ ስወጣ ብቻዬን ነበር የምሄደው ሁሌም
ከጎረቤታችን ኢሳያስ ጋር ስለምሄድ ብቻዬን መሄዴ ለኔ የመጀመርያ ነበር ብቻዬን የምሄድበት ምክንያት ደግሞ ኢሳያስ ስራ ባለመግባቱ ነበር ... ታድያ ይሄን ያየው ልኡል በደስተኛ ፊት
ልሸኝሽ አለኝ እኔም ምላሼን በፈገግታ አጅቤ በአዎንታ እራሴን ነቀነኩ... ከዛ ቀን ቡሃላ ኢሳያስን እየተደበኩ ልኡል ይሸኘኝ ቀጠለ በጥቂት ቀን ውስጥ ተግባባን ... ልኡልን ወደድኩት እሱም ወደደኝ ማንም ማንንም ሳይጠይቅ ፍቅር ተጀመረ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው የብስራት ሙዚቃ....ቃል....በቃል... ሚለው ዘፈን ያኔ ቢኖር እላለው ምክንያቱም አንድ
የሚላት አዝማች አለች ማሀል ላይ
"እንደኔ በሆነ ፍቅሯ እያልኩኝ ልቤን ሳስጨንቅ አረግሽኝ በሀሴት
...................ጥልቅልቅ
ያብሮነት ጥጉ በጊዚያት ካይን አልፎ ልብን ሲላመድ እንዲ ነው ለካ መዋደድ"
ይላል ታድያ ዘፈኑ ለኛ የተዘፈነ እስኪመስለኝ ድረስ አሁን ስሰማው
ያን ህይወት ያስታውሰኛል ... አንድ ቀን ልኡል ሰፈር ድረስ ሸኝቶኝ ልክ ስደርስ ቆመን ማውራት ጀመርን ሰአቱ ሳናስበው መሽቶ ጨለምለም እያለ ነው ሰማዩ በከዋክብት ደምቋል ይሄኔ በሚያማምሩት ከዋክብት ስም ላይከዳኝ ላልከዳው ቃል ተገባባን ለመጀመርያ ግዜ ከንፈሬን ሊስመኝ ተጠጋኝ የዛን ቀን ነበር እንደሚያጨስ ያወኩት ... እውነት ለመናገር ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ባጠገቡ ማለፍ እንኳ በጣም ይቀፈኝ ነበር ልኡሌን ግን ሳልፀየፍ ሳምኩት እውነትም ፍቅር ይዞኛል ልኡል በጣም እንደሚወደኝ ያወኩት ማጨስ ማቆም እንዳለበት ስነግረው በሀሳቤ ተስማማ እናም ለአመታት የነከሰውን ሲጋራ ለማቆም 1 አለ ለማቆም ቅድምያ መቀነስ ነበረበት ይሄን ሲያደርግ ደግሞ ከፍተኛ እራስ ምታት ያመዋል ከዛም ስራ ይቀራል ይሄ ደግሞ እኔን ያስከፋኝ ጀምሯል... ስራ ሲቀር አንገናኝም
አጭሰህ ደግሞ ላይህ አልፈልግም እንኳን ልስምህ ብዬዋለው... ልኡሌ ማጨስ ለማቆም ሲጥር በመሀላችን ክፍተት ይፈጠር ጀመር... በዛ መሀል እኔም ስራ አቆምኩኝ ... የኔ ስራ ማቆም ደግሞ ይበልጥ አራራቀን ይሄኔ ልኡል መደወል ቀነሰ እኔ ስደውልለትም አያነሳም በጣም ከፋኝ ይናፍቀኝ ጀመር
ለኔ ብሎ ብዙ አጉል ሱሶችን የተወልኝ ልኡል ዛሬ ራቀኝ እኔም ቀን በቀን ማልቀስ ቀጠልኩ በዚ መልኩ ቀናት ተቆጠሩ እኔም ቢያንስ አይኑን ልየው ብዬ ወደሱ ሰፈር ሄድኩ እዛው አካባቢ የሚቀመጥበትን ስፍራ አውቀው ስለነበር ወደዛ ሄድኩ ስደርስ ግን ያልጠበኩት ነገር ነበር ያየሁት ልኡሌ ከሌላ ሴት ጋር ... የእውነቴን ያበድኩ መሰለኝ እንባዬ እየዘነበ ብቻዬን እያወራሁ ተመለስኩ ወደቤት ግን መግባት አስጠላኝ.......


꧁༺༒༻꧂


✎ ክፍል ሶስት ከ150 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @Yefkrtarik
የፍቅር ታሪክ
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄