ጣፋጭ የፍቅር ታርኮች 😘💖💑💑
273 subscribers
174 photos
32 videos
3 files
152 links
♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤

➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟

ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ = https://www.facebook.com/fikrenbegtm
ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ
= +251947534345
= t.me/@yefkr_world2
Download Telegram
#የኔ ስጦታ#

አሁን የኔ በመሆንሽ በጣም ከባድ እና አስጨናቂ የህይወት ጎዳናዎች እንኳን ብሄድ ግድ አይለኝም፡፡ ምክንያቱም ከጎኔ ስላለሽ የህይወትን ብሩህ ጎን እያየው ስለሆነ አልጨነቅም፡፡ የኔ ቆንጆ ያሳለፍነውን የፍቅር ጊዜ ሳስበው ለብቻዬ እንኳን ሆኜ ፈገግ እላለሁ፡፡ አንቺ ለኔ አምላክ የሰጠኝ ስጦታዬ ነሽ፡፡ ሁሌም እወድሻለሁ፡፡


👍ከተመቻችሁ #share ማድረግ ... አይርሱ



👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Join us @yefkr_world2
Join us @yefkr_world
🔻🔻🔹🔹🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ፍቅር ያሸንፋል  🔸

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ
💟

📱ክፍል🔤

✎ ክፍል አንድ💝

ውድ ጓደኞቼ ጥሩ ያልኩትን አስተማሪ የፍቅር ታሪክ መርጬ ለናንተ በሚመች መልኩ ማቅረብ ጀምሬአለው እንደምትወዱት አልጠራጠርም እንድታነቡልኝ እጋብዛለሁ፡፡🌺

     ያስሚን ሙሐመድ  እባላለው የተወለድኩት አማራ ክልል ወሎ ክፍለ
ሀገር ደሴ የምትባል ከተማ ላይ ነው ታድያ ደሴ እናትና አባቴ ጋር ስኖር ደስተኛ ነበርኩ ቤተሰቦቼ ሀብታም ባይባሉም ሌላ ልጅ ስለሌላቸው እኔን በደምብ ይንከባከቡኛል ትምህርትም በግዜ ነበር የገባሁት ፡፡ የልጅነት ህይወቴ ብዙም የተለየ ነገር ስለሌለው ወደ የፍቅር
ህይወቴ ልግባላቹ ልክ በ16 አመቴ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆንኩ ይሄኔ ነበር የኔም የሰውነት ቅርፅ ለውጥ ያሳየው ከዛም ባለፈ እኔ በባህሪዬ ዝምተኛ ስሆን ከሰውነት ቅርፄ ጀምሮ የብዙሃን ሠው ቀልብ  የምስብና በሠዎች  አስተያየት ውብ የምባል አይነት ሴት ነበርኩ ፡፡
እኔ የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ነኝ ሆኖም ብዙ የክርስትና እምነት ተከታይ ጓደኞች አሉኝ፡፡ እናም ከነሱጋ ነበር አብዛኛውን ጊዜዬን የማሳልፈው የነበረው አንድ ዓመቱን እንዲ ሆኘ ነበር ያሳለፍኩት አዲሱን ዓመት ተቀብለን ክላስ ጀምረን መማር ጀመርኩ። ከዕታት ባንዱ ቀን ክፍላችን ውስጥ እንግዳ ፊት አየሁ ለኔ ለየት ያለብኝ ደግሞ ልክ ሳየው መደንገጤ ነበር ሁሌም በምናቤ
የምስለው አይነት ወንድ ከለሩ ቸኮሌት ቁመቱ እረዘም ያለ ፀጉሩ የሚያምር ፍሪዝ አስተያየቱ ልብ የሚሰርቅ ባጠቃላይ ውብ ቃሉ የሚያንስበት ልጅ ነው በርግጥ የኔ   የተገናኘን ቀን  እድሜዬ 17 አካባቢ ነበር እሱ ደግሞ በግምት 19  አካባቢ ይሆነል  እኛ ክፍል የገባው ደግሞ ለምን እንደሆነ ለማጣራት ወደ ክፍል ገብቼ ሳይ ለታናሽ እህቱ እቃ ለመስጠትነበር የመጣው የነበረው፡፡ ስሙ ካሌብ ይባላል የግቢያችን የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው ያን ቀን ልቤን እንደወሰደ እስካሁን አልመለሰልኝም እሱን ካየሁበት ቅፅበት ጀምሮ መሉ ሀሳቤ እሱ ነው፡፡ እናም እሱን ለማግኘት ስል መጀመርያ ማድረግ ያለብኝ እህቱን ሜሮንን ተዋወኳት ከሜሪ ጋር በጣም ተግባባን ግን ወንድሟን ማፍቀሬን ፈፅሞ አልነገርኳትም ሁሌም ስናወራ በጣም የማፈቅረው ወንድ
እንዳለ ስነግራት ሁኔታዬን አይታ ታድሎ ያስሚኔ ትለኛለች፡፡ ካሌብ መረብ ኳስ መጫወት ይወዳል ለዛም እሱን ለማየት ከሜሪ ተደብቄ ኳስ ሜዳ እሄድና አየዋለሁ ሁሌም እሱ የሚገኝበት ቦታ እሄዳለው ሳየው ደስስ ይለኛል ካላየሁት ግን እናቷን እንዳጣች ጥጃ ያረገኛል
እነጫነጫለሁ፡፡ ግን አንድ ነገር አውቃለው ከካሌብ ጋር የሀይማኖት ልዩነት አለን ቤተሰቦቼ ደግሞ በሀይማኖት ድርድር አያውቁም ያም ማለት ካሌብን  ማፍቀር እንጂ የኔ ማድረግ አልተፈቀደልኝም፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ በተከታታይ 3ቀን ካሌብዬ ትምህርት ቤት ቀረ እሱን ሳላይ ስቀር 3ቱ ቀን አመታት ሆነብኝ ያለኝ ምርጫ ስበብ ፈልጌ ሜሮን  ቤታቸው እንድትወስደኝ ዘዴ ማፈላለግ ነበር እናም ተሳክቶልኝ መፅሀፍ ፈልጌ በሚል ሰበብ  ከሜር ጋር ቤታቸው ሄድኩ ቤታቸው ያምራል የግቢው በር ተከፍቶ ስንገባ የኔ  ካሌብዬ  በረንዳው ላይ ቁጭ ብሏል ልክ ሳየው ደርቄ ቀረው ሜሪም  ግራ ገብቷት ችግር አለ ያስሚኔ  አለችኝ  ይሄኔ ነበር ማፍጠጤ የታወቀኝ ካሌብም የታላቅነት ስሜቱ እያንፀባረቀበት ኦኦኦኦኦ ሜሪዬዬ  ቆኝጂዬ ጓደኛ አለችሽ አላት እንደሱ ሲላት ይበልጥኑ የደስታ ሲቃ ተናነቀኝ በሱ ደግሞም በምወደው ሰው በካሌብ  አፍ ቆንጆ መባሌን ማመን አቃተኝ.......


🔻ክፍል ሁለት ከ5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።

🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

🔸🀄️🀄️ሉን! ➢🔸
❤️° @MENTA_LBOCHI°❤️
 
❤️°  @MENTA_LBOCHI°  ❤️

   
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
​​
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔻🔹🔹🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ፍቅር ያሸንፋል  🔸

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ
💟


📱ክፍል🔤

‍ ✎ ክፍል ሁለት
💝

ካሌብ ከትምህርት የቀረው አሞት እንደነበር ለማወቅ ብዙ ደቂቃ
አሎሰደብኝም ነበር አይኑን ካየሁት በኋላ ከዚ በላይ መቆየት ስለሌለብኝ ደግሞም እቤት ብዙ ከቆየው ስለምቆጣ ወጥቼ ወደቤት መሄዴን ቀጠልኩ፡፡ በየመንገዱ  ግን የማስበው ስለሱ ነበር  ሜሪዬ ቆንጂዬ ጓደኛ አለሽ ያላትን ሳስታውስ ደስታዬ እጥፍ ይሆናል እቤት እንደገባው ፊቴን አስሬ በመስታወት እያየው ግንኮእውነትም ቆንጆ ነኝ! እላለው፡፡
ከዛ ቀን ቡሃላ ካሌብዬ አወቀኝ እኔም ፍቅሬ ጨመረ ይባስ ብሎ አንድ ቀን እሱን ለማየት እንደለመድኩት ሜዳ ሄድኩ ይሄኔ
እየተጫወቱ ነበር እኔም ከሩቅ ተመስጬ ማየቴን ቀጠልኩ ይሄኔ ካሌብ የመረብ ኳሱን የመጀመሪያ ውጤት አስመዘገበ  የእውነት ማንም ባያየኝም ከልቤ ነበር የተደሰትኩት፡፡ በዚ ሰአት በቅፅፈት አንዲት ቆንጂዬ ሴት እሩጣ ተጠመጠመችበት በጣም ደንግጬ ይሁን ተናድጄ ሳይታወቀኝ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩ አይኔ እምባ አቀረረ ቀናሁ መሰለኛ ከዛ ወደነሱ ሄድኩ ለምን እንደሄድኩ ግን እኔም አልታወቀኝም ልክ ሲያየኝ ያስሚንዬ የኔ ልእልት ብሎ ጉንጬን ሳመኝና እዚ ምን ትሰርያለሽ ሲል ጠየቀኝ ይሄኔ መልስ ስላልነበረኝ ድንገት ከአፌ መቶልኝ መረብ ኳስ እወዳለው ለዛ ነው አልኩት ኦ አንድ አይነት ስሜት አለን ታዲያ እሷ ቤቲ ትባላለች ጓደኛዬ ናት ብሎኝ ካስተዋወቀኝ በኋላ  እና መረብ ኳስ ደግሞ መልመድ ከፈልግሽ  አስለምድሻለው እሺ አለኝ በጣም ከመደሰቴ የተነሳ  መቼ ነው አልኩት ከፈለግሽ ከትምህርት ቡሃላ ከፈለግሽ ብሎ ገና ሳይጨርሰው በረፍትም አልኩት እሱም በዕረፍት ሰዓት ሊያለማምደኝ እሺ አለኝ፡፡ ጓደኛዬ ናት ስላላት ልጅ ሳስብ ስናደድ ኳስ አስለምድሻለው ያለኝን
ሳስብ ስደሰት የዋልኩበት ያን ቀን መሽቶ ነጋ በኳስ ስበብ አብሬው መቆየቴ
ለኔ ትልቅ ደስታ ስለነበር እረፍት ደርሶ እስክወጣ ቸኮልኩ ከዛ ለሜሮን  አሁንም የምሄድበትን ሳልነግራት ሄድኩ ስደርስ አሁንም ያቺ ቤቲ የምትባል ሴት አለች  ከሩቅ አይቻቸው ስመለስ ካሌብ አይቶኝ ስለነበር ወደኔ እየሮጠ መጥቶ ያስሚ ብሎ ሲጠራኝ  ሄጄ መቅናቴን ለመሸሸግ እየሞከርኩ ፈገግ ብዬ ሰላም አልኩት ያን ቀን እንደኔ ደስተኛ ያለ አልመስልሽ አለኝ ምክንያቱም ስለ ቤቲ ያወኩበት ቀን ነበር የሆነውም ደግሞ እየተናደድኩኝ እና ውስጤ እየተቃጠለ እኔ የምልክ ካሌብ ቆንጆ እና ተጫዋች ፍቅረኛ አለችክ ስለው አረ 10qw  ሲለኝ ፊቴ መለዋወጥ ሲጀምር አረ ስቀልደሽ ነው ብሎኝ ቤቲ ፍቅረኛው ሳቶን ጓደኛው እንደሆነች ነገረኝ፡፡.…ካሌብ በጣም ጎበዝ ተማሪ ስለነበር ከሜሮን ጋር አብሬ ላስጠናቹ
ሲለኝ ደስተኛ ሆኜ ነበር እሺታዬን የገለፅኩት በዚ መልኩ ማፍቀሬ
እንዳይታወቅ እየተጠነቀኩ ቀናቶች እሩጫቸውን ቀጠሉ፡፡ ታድያ አንድ ቀን እነ ካሌብ ቤት እንደተለመደው ለማጥናት ስሄድ እንደድንገት ሆኖ ሜሮን አልነበረችም ነበር እናም እኔና ካሌብ  ስለነበርን ካሌብ እኔን ያስጠናኝ ጀመር፡፡
እናታቸው ደግሞ በጣም ስለምትወደኝ አልፈራትም ነበር  እዛ ቤት ስሄድ እንደቤቴ ነበር የምቆጥረው   ከዛ እሱ እያስረዳኝ እኔ ግን ሀሳቤ ግን ጥናቱጋር ሳይሆን  አይን አይኑን እያየውት ተመስጬ  ምናለ ሀይማኖታችን አንድ ሆኖ ፈጣሪ እሱን ለኔ ቢፈቅድልኝ እጣ ፈንታዬ ባረገው አልኩ በውስጤ ብዬ ልስመው ፈለጉና ወደሱ ጠጋ ስል  እሱም ገብቶታል መሰልኝ ወደ እኔ ጠጋ ሲል ሲታወቀኝ ጊዜ ሰውነቴ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ከተቀመጥኩበት ስነሳ ካሌብን እንደመደንገጥ ብሎ ይቅርታ አስቤው አይደለም ሲለኝ its ok  ብዬው እሱግ ድንጋጤው ስላልለቀቀው ወሬ ማስቀየስ ፈለኩና በላ አሁን ምን ትጠብቃለክ አስተናኝ እንጂ ቢዬው ከዛን ወደጥናታችን ተመልሰን  ከዛ ልክ ስንጨርስ ወደቤት ሄድኩ ቤት ገብቼምመኝታ ክፍሌ ውስጥ የቤት ስራ ልሰራ የሂሳብ ደብተሬን ስገልጠው አንድ ሁለት ቦታ የታጠፈ ወረቀት አገኘሁ ልቤ ድንግጥ አለና ገለጥኩት የቃልዬ ፅሁፍ ነው፡፡
"ቅድም በተፈጠረው ነገር ያስሚኒዬ ይቅርታ አርጊልኝ እኔ ለአንቺ እንደወንድምሽ ሊሆን ይችላል የምታይኝ እኔ ግን አንቺን በቃ አፍቅሬሻለው መልስሽ ምንም ይሁን ምን አፈቅርሻለሁ "ይላል በድንጋጤ ከተቀመጥኩበት ተነሳው ወረቀቱን አተኩሬ ተመለከትኩት ቤተሰቤን አሰብኩ ፍቅሬንም አሰብኩ ሳላስበው ትኩስ እምባ በጉንጮቼ ይወርድ ጀመር ይሄኔ አባዬ በሩን ከፍቶ ገባ ወረቀቱን በጄ እንደያዝኩ ደርቄ ቀረሁ...…



🔻ክፍል ሶስት ከ5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።

🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

🔸🀄️🀄️ሉን! ➢🔸
❤️° @MENTA_LBOCHI°❤️
 
❤️°  @MENTA_LBOCHI°  ❤️

   
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
​​
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔻🔹🔹🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ፍቅር ያሸንፋል  🔸

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ
💟

🔻🔻🔹🔹🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻
📱ክፍል🔤

‍ ✎ ክፍል ሶስት💝

አባዬ ገብቶ ሁኔታዬን ሲያይ በጣም ነበር የደነገጠው እንባዬን አይቶ አይኖቹ እምባ ሲያቀሩ ተመለከትኩ ከዛ መቶ ያባትነቱን እያቀፈኝ ወረቀቱን ተቀበለኝና ወደ ጠረጴዛ ላይ ወርወር አርጎት ልጄ ምን ሆነሽ ነው ውጤት ተበላሽቶብሽ ነው? ሲል ጠየቀኝ እኔም ይበልጥ ሆድ እየባሰኝ ምንም ሳልመልስለት ለቅሶዬን ቀጠልኩ አባቴ ቢማር ኖሮ ደብዳቤውን በማንበብ ለምን እንደማለቅስ ያውቅ ነበር ግን እሱ ሳይማር እኔን እያስተማረ ነው፡፡
እኔ ደግሞ የማላገኘውን ሰው አፍቅሬ መንገዴ ሊበላሽ ነው እኔ
መሆን የምፈልገው ቤተሰቦቼ እንድሆን የሚፈልጉትን ነው ግን
መሀል ላይ ምርጫ የሌለው የተፈጥሮ ግዴታ ላይ ወደኩ፡፡
አባቴ ምክንያቴን ሳያውቅ አባብሎኝ ብቻ ያ ቀን ነጋ ትምህርት ቤት
መሄድ ግድ ነውና ጠዋት ቦርሳዬን አንግቤ ወደ ትምህርት ቤት
መንገድ ጀመርኩ ይሄኔ ነበር ወደትምህርት ቤታችን መታጠፍያ ጋር
ስደርስ ድንገት ካሌብን አገኘሁት እየጠበቀኝ እንደነበር ያስታውቃል
እኔ ግን ሳየው ልቤ ለሁለት ስንጥቅ ነበር ያለው ያስሚ አለኝ
ቆም አልኩኝ የኔ ቆንጆ ናፍቀሽኝ ነው በጥዋት የመጣሁት አለኝ
ዝም አልኩ  አላስጨንቅሽም እሺ ፍቅር የጋራ ስሜት ነው
ስለዚህ ሲል አቋርጬው ትቼው መንገድ ጀመርኩ በትክክል
ማሰብ አልቻልኩም ግራ ተጋባሁ ይሄኔ ካሌብ ካንደበትሽ
መስማት አያስፈልገኝም የኔ ቆንጆ ፍቅሬን ባትቀበይም አንቺን
ማፍቀሬን ግን እቀጥላለሁ አለና አልፎኝ ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር
ግቢ ገባ፡፡
ክፍል ገብቼ መማር አቃታኝ ግን እንደምንም እረፍት ደረሰ ተደብቄ
ላየው ወደ ኳስ ሜዳ ሄድኩ ግን ብቅ እንኳ ሳይል እረፍት አለቀ
ምሳ ሰአትም ጠበኩት ግን የሚወደው መረብ ኳስ እንኳ
አስጠልቶታል ነበር ፡፡
2 ቀን በተደጋጋሚ ሳንገናኝና ካሌብን ሳላየው አደርኩ ከዛ በላይ ግን ሳላየው መቆየት አልቻልኩም ክፍላቸው ሄጄ ካጣሁት እቤታቸው ልሄድ ወሰንኩ ከዛም ልክ እረፍት ስንለቀቅ ክፍላቸው ሄድኩ ያኔ ይበልጥ የምሩን እንዳፈቀረኝ አረጋገጥኩ ፡፡
ካሌብዬ ብቻውን ተቀምጦ ትክዝ ብሎ የነበረ ልክ ስንተያይ
ሁለታችንም ደነገጥን ከዛ ማንም ማንንም ሳያናግር ተቃቀፍን እኔ
እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ ጥቂት ተቃቅፈን ከቆየን ቡሃላ
ካሌብዬ አልኩት ወዬ አለኝ አይኖቼን ለማየት ከደረቱ ቀና እያረገኝ
እወድሃለው አልኩት ይሄኔ በደስታ የሚያደርገው ጠፋው
እኔና ካሌብዬ በዚ መልኩ ፍቅር ጀመርን ሁሌም በድብቅ ቢሆንም
እንገናኛለን ሰፈሬ ድረስ ይሸኘኛል ግን የኔና የሱን ፍቅር ያወቀችው
የቃላብ እህት ሜሮን ብቻ ነች እሷም ሁሌም  ከጎናችን ሆና ትረዳናለች  ይህ
በንዲህ እንዳለ እኔ 9ኛ ክፍል ስደርስ እሱ ደግሞ 12ን ተፈትኖ
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ደረሰው ይሄኔ ሁለታችንም በጣም አዘንን
የምናደርገው ግራ ገባን  ትምርቱ ይቅርብኝ እንጂ ትቼሽ
አልሄድም አለ እኔ ደግሞ የለፋበት እንዲቋረጥ አልፈልግም  አልኩትና ተለያየን  ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ምሽት ላይ ካሌብዬ  በሜሮን
አስጠራኝ እኔም በጣም ናፍቆኝ ስለነበር እነ አባዬ ሳያዩኝ ወጣሁ
ልክ ሳየው እሩጬ ተጠመጠምኩበት ሁሌም ሳገኘው ሁሉን ነገር
እረሳለው ተጠምጥሜበት አንድ ቁጥር መስለን ያለወትሮዬ አለማችንን እየቀጨን እያለ   ፍርቅራችንን አጣጥመን  እንኳ ሳንጨርስ  ፈተና ገጠመን በምሽት ስወጣ የተጠራጠረው አባዬ ተከትሎኝ ኖሯል ለካ  ያስሚን ያስሚን ብሎ የሚጣራ ድምፅ ስሰማ የአባዬ ድምስ መሆኑን ተጠራጥሬ ዞር ስል አባዬን ሳየው የደነገጥኩት ድንጋጤ እና የተሠማኝ ፍርሀት
ሽንቴን ልለቀው ደረስኩ ወንድ ቀና ብዬ
እንዳላይ አድርጓ ሲያስጠነቅቀኝ አሳድጓኝ  ኖሮ ዛሬ ይህን ሲያይ ምን ሊያረግ ሊሆን
እንደሚችል መገመት ተሳነኝ ሁለታችንም ደርቀን ባለንበት ቀረን.......

🔻ክፍል አራት ከ5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።

🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

🔸🀄️🀄️ሉን! ➢🔸
❤️° @MENTA_LBOCHI°❤️
 
❤️°  @MENTA_LBOCHI°  ❤️

   
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
​​
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ቤተሰቦች ገባገባ በሉ
.
.
.


👇👇👇👇👇👇👇👇
Join us @yefkr_world2
Join us @yefkr_world
Forwarded from Quality Button
Notcoin በነፃ መሰብሰብ ማለትም ከ 3 ቀን በውሃላ ይቆማል። ቶሎ mine በማድረግ ኮይናችሁን ሰብስቡ። በኖትኮይን ዋጋ አሁን እየጨመረ ነው። ቡሃላ ሳይከብድ አሁኑኑ tap tap በማድረግ ይሰብስቡ
⚠️አንዴት እንደሚሰራ እና ብር ማዉጣት እንደሚቻል መጀመሪያ start በሉትና tiktok ላይ ወይ YouTube ላይ ማይት ትችላላችሁ🙌
👇👇👇👇👇👇👇
Forwarded from Notcoin
Invite your friends and get bonuses for each invited friend! 🎁

Your referral link: https://t.me/notcoin_bot?start=r_573809_35959470
Join this channel gus

👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Bitcoinjon_12
I'm on Instagram as @bnegeso. Get the app and follow me https://www.instagram.com/bnegeso

👇👇👇👇👇👇👇

🔰Join us @yefkr_world2
🔰Join us @yefkr_world
ባየሁሽ ቅጽበት ጊዜ ልቤን አሞቅሺው፣ በሁለተኛ ጊዜ ትንሽ ነበልባል አድርግሽ እና አሁን ልቤን ልክ እንደ ሲኦል ታቃጥለዋለሽ!


👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Join us @yefkr_world2
Join us @yefkr_world
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ ☞  #አደራዬ......
ፀሀፊ ☞
አብርሽ ፍቅር
#ክፍል ☞ አንድ


         ከርእሱ ልጀምርና እስኪ ስለ አደራ ምን ያህሎቻችን እናቃለን? ስንቶቻችንስ አደራችንን እየተወጣን ይሆን!!! ይቅርታ በጥያቄ ጀመርኩት መጀመሪያ  ራሴን  ሳላስተዋዉቅ........ ፊርዶስ ዩሱፍ እባላሁ ተወልጀ ያደኩት ጎጃም ደ/ማርቆስ አካባቢ ነዉ ሀገሩ፣ህዝቡ፣ አየሩ ብቻ ሁሉም ነገር ደስ ይላል። ሀገሩ ብቻ ሳይሆን እኔም ቆንጆና  ደስ የሚል ፀባይ አለኝ ማለት ባልችልም..... ብዙዎቹ ግን ፀባይም ቁንጂናም አድሎሻል ይሉኛል። አልሀምዱሊላህ...... ከሰዉ  ጋር ለመግባባት ቢሆን ብዙም አልቸገርም ቶሎ እግባባለሁ። ትምህርት የጀመርኩት በ 7 አመቴ ነዉ በትምህርቴም ጎበዝ ተማሪ ነኝ..... ደረጃም ቢሆን ከ1 እስከ3 አለቅም ሁሌም በየ አመቱ እሸለማለሁ። መምህሮች ሁሉ ይወዱኛል....... ምን መምህሮች ብቻ ተማሪዎችም በጣም ነዉ የሚወዱኝ።  አንዳንዴ መምህሮች በተለያዪ ምክንያቶች ሊቀሩ ካሰቡ ለኔ ዳስተርና ቾክ እንዳስተምር ይሰጡኛል። እኔም ክፍለ ጊዜቸዉን ሸፍኘ አስተምራለሁ። ግን እኔን የሚበልጠኝ አንድ አብርሀም የሚባል ልጅ አለ እሱ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አንደኛ ሲወጣ እኔ ደግሞ ሁለተኛ እየወጣሁ ይሄዉ ዘጠነኛ ክፍል ደረሰናል..... ግን ሁል ጊዜ እንዴት አብርሀም ይበልጠኛል አንድ ላይ እየተማርን ብየ እናደዳለሁ።  መቸም ትምህርት ነዉና እንደየልፋቱ ደረጃዉም ይለያያል።
......  ከራሴ በላይ በጣም የምወዳት አያት አለችኝ አልሀምዱሊላህ........ አያቴ ለኔ እናቴ፣ አባቴ፣ እህቴ፣ ወንድሜ በአጠቃላይ ሁሉ ነገሬ ናት ደሞ የሚገርመዉ ፊርዶስ ብላ አትጠረኝም አደራየ ነዉ የምትለኝ። ወላሂ ምክንያቱን አላቅም ሁል ጊዜ እጠይቃታለሁ ግን አንች ገና ልጅ ነሽ ስታድጊ እነግርሻለሁ አሁን ብነግርሽ  አትረጅኝም ትለኛለች። እኔም እንዴ..... አያቴ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እኮ ነኝ እና እኔ ህፃን እባላለሁ ብየ አኮርፋታለሁ። እሷም ጠጋ ብላ ፀጉሬን እያሻሸች  አደራየ የኔ ዉድ ቃል እገባልሻለሁ አንድ ቀን ሁሉንም ነገር አስረዳሻለሁ ትለኛለች በስስት አይኖቿ እየተመለከተችኝ። እኔም ፈገግ ብየ  አይ! ዉዷ አያቴ ስለ ስሜ የማላቅ ይመስልሻል?  አደራየ ምንድን ነዉ ስለ ስምሽ የምታዉቂዉ? አይ አያቴ ስለ አደራ ምንነት ብዙ  አዉቃለሁ። እኮ ምን?......ስሜን ለማወቅ  የተለያዪ ፁህፎችን አንብቤ ነበርና ለመግለፅ ብዙም አልተቸገርኩም አደራ ማለት ብየ መናገር ጀመርኩኝ.........
❖አደራ ማለት ለመግለፅ በጣም ከባድ ነዉ ከክብደቱ የተነሳ ተራራን ያንቀጠቀጠ ፣ሰማይን ያራደ፣ምድርን ያሳነ... ብቻ ምን ልበልሽ አያቴ አደራኮ ከመክበዱ የተነሳ አላህ(ሱ.ወ) አደራን ትሸከማት ዘንድ ወደ ሰማይ አቀረበ ሰማይም ጌታዋን አልችልም ይቅርታ አለች። በጣም ጠንካራ ወደ ሆነዉ ተራራም አቀረባት ተራራም ጌታየ ሆይ እኔ የመሸከም ለቅም የለኝም በማለት ደካማነቱን አሳወቀ ወደምድርም ይዟት ቀረበ ምድርም ጌታየ እኔ አልችልም ብላ ተመሳሳይ መልስ አቀረበች። ከዚህ ሁሉ በኋላ ወደ ሰዉ ልጅ ቀረበች የሰዉ ልጅም ምንም ሳይል እሽ ብሎ ተቀበላት።አላህም ይህን ክስተት እንዲህ ብሎ ነግሮናል።

እኛ አደራን በሰማያትና በምድር፣በተራራዎችም ላይ አቀረብናት። ሁሉም ግን እኛ ሀቅም የለንም አንችልም እንቢ አሉ። ሰዉም ተሸከማት። እርሱ በጣም በደለኛ ተሳሳች ነዉና።(አል አህዛብ.72)

እንግዲህ አያቴ ከዚህን ሰአት አንስቶ የሰዉ ልጅ ላይ አደራን እንዲጠብቅ ሀላፊነት የተሰጠዉ።
ዉዷ አያቴ  ብዙ ሰዉ አደራን በመጠበቅ ይታወቅ ይሆናል ብዙ ነብዮችም አላህን ከፍጡራኖቹ ጋር ካስተዋወቁ፣ የአላህንም ሀቅ ከገለፁ በኋላ ቀጣይ ተግባራቸዉ የሚሆነዉ የፍጡራን ሀቅ የሆነዉን አማናን (አደራን) በመጠበቅ ላይ ማስተማር ነዉ። ከማንም በላይ ደግሞ የመጨረሻዉ ዉድ ነብይ የሆኑት ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) በአደራ ጠባቂነታቸዉ የታወቁ ነበሩ።  ለዛም ነዉ ነብይ ከመሆናቸዉ በፊት ጀምሮ ሙሀመዱል አሚን ታማኙ ሙሀመድ የሚባሉት።

አያቴም ታለቅስ ጀመር ግንኳ እኔ  ብላ ማዉራት ስትጀምር...   በጣም እያለቀሰች ነበርና  አስቆምኳት ምንም ነገር መስማት አልፈልግም አሁን እንባሽን ታጠቢዉ ብየ ዉሀና በማስታጠቢያ ይዜላት መጣሁ...... አሷም ከታጠበች ቡሀላ ግን አደራየ የኔ ዉድ ልጂ አላህ አደራ ጠባቂዎችን ይወዳል አይደል?? ..... ዉዷ አያቴ ትጠራጠሪያለች እንዴ አወ አደራ ጠባቂወችን አላህ ይወዳል። ለዛም ነዉ የሱ ምርጥ ባሪያዎች መገለጫ ያረጋት። በዚህም ተግባራቸዉ የተነሳ ባሪያዎቹ ላይ የሚመፃደቅባቸዉ። አላህ በሁለት የቁርአን አንቀፆች ላይ እንዲህ ይላል......

👉እነዚያ እነርሱ አደራዎቻቸዉንና ቃል ኪዳናቸዉን ጠባቂዎች የኾኑት።(አል፡መዓሪጅ፡32)እና(አል ሙዕሚኑ፡8)

ደሞ ዉዷ አያቴ አደራ ቂያማ ለመቆሟና ላለመቆሟ ዋስትናም ምክንያት ናት። አደራ ጠባቂዎች በምድር ላይ እስካሉ ድረስ ቂያማ አትቆምም። ሰዎች እሷን ችላ ማለት ሲጀምሩና በምድር ላይ ለባለ አደራነት የሚበቃ ሰዉ የጠፋ ጊዜ የዛኔ ቂያማ ለመቆሟ ትልቅ ምልክት ትሆናለች። ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) ቂያማ መች እንደሆነች አንድ ሰዉ ሲጠይቃቸዉ እንዲህ አሉ.......
👉አደራ በጠፋች ጊዜ ቂያማን ተጠባበቅ ጠያቂዉም ደንገጥ ብሎ እንዴት ነዉ የምጠፋዉ? ሲል ጠየቀ
( ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ የአንድ ጉዳይ ሀላፊነት የማይገባዉ አካል ላይ ከተጣለ የዛኔ ቅያማን ተጠባበቅ ሲሉ ነገሩት።

አያቴም ይህንን ከሰማች ቡኋላ እነዛ ዉብ   አይኖቿ በአንዴ ደም ለበሱ እኔም ምን ሁነሽ ነዉ የምታለቅሽ አስቀየምኩሽ እንዴ አያቴ? በአላህ አፉ በይኝ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ንግግር አይደገመኝም.። አደራየ የኔ ዉድ እኔኮ ብዙ አደራ አለብኝ። ግን አንድንም አልተወጣሁትም እያለች... ማልቀስ ጀመረች ኧረ በአላህ አያቴ ቆይ እሽ አደራሽ ምንድን ቢሆን ነዉ እንደዚህ የሚያስለቅስሽ?

አደራየ ዉዴ ለሁሉም ነገር ግዜና ቦታ አለዉ! አሁን አልነግርሽም። ግን አደራየ ወላሂ ዛሬ ኮርቸብሻለሁ። እንዴ አያቴ ምን አድርጌ ነዉ ደግሞ የኮራሽብኝ?....ስለ አደራ ምንነትና አደራ ሲጠፍም ዉመልቂያማ የመድረሱ ምልክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ በደንብ ነግረሽኛል። አይ አያቴ የዉመልቂያማ የመድረሱ ምልክቶችኮ አደራን አለመወጣት ብቻ አይደለም ብዙ ምልክቶች አሉት። ለምሳሌ
👉 ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት
👉 ሙስና፣ማጭበርበር እና የዋጋ ንብረት እያየለ መምጣት
👉 ስስት መስፋፋት
እያልኩ ከመሀል የቤቱ ስልክ ጠራ አያቴም  በዚህ ለሊት ማን ይሆን  የደወለ ብላ ስታነሳዉ.....

#ክፍል_2 #ይቀጥላል....
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ አብርሽ ፍቅር
     #Part ☞ሁለት ➋




አያቴም በዚህ ለሊት ማን ይሆን የደወለ ብላ ስታነሳዉ..........
"እማ አሰላሙ አለይኩም ሀያት ነኝ"...... ዉአለይኩም እሰላም... ሀያቴ የኔ ዉድ በሰላም ነዉ የጠፋሽ ወላሂ ምን ሁና ነዉ የጠፋች እያልኩ እየተጨነኩ ነበር..... እየተበባሉ  በናፍቆት ያወሩ ጀመር ።
እኔም እስልኩ አጠገብ ተቀምጨ አለቅስ ጀመር..... ሀያት ማለት እናቴ ናት ነገር ግን መልኳን አላዉቀዉም። እኔን በወለደች በ 2 አመቴ ነዉ በችግር ምክንያት ወደ አረብ ሀገር ጥላኝ የሄደች።

አባቴም እንደዛዉ ግን አባቴ እንደናቴ በስልክ አዉርቸዉ ድምፁንም ሰምቸዉ አላዉቅም። በስም ብቻ ዩስፍ ከመባል ዉጭ ሌላ ነገሩን ምኑንም አላዉቅም። መልካቸዉንም ሆነ ባህሪያቸዉን ለማወቅ ለራሱ  ፎቶዎችን፤ የተለያዪ ፁህፎችን ብፈልግ ምንም ስለነሱ ፍንጭ ነገር ላገኝ አልቻልኩም።  በዛ ላይ ሰፈራችን ወጣ ያለ ስለሆነ አንድ ብቻ ሙስሊም ጓረቢት እንጂ ሌላ የለንም። አያቴም ብትሆን ከነሱ ጋር ብቻ እንጂ ከሰፈር ወጣ ብየ ሌላ ቦታ እንድጫወት አትፈቅድልኝም ብቻ አያቴ በጣም ቁጥጥር ታበዛብኛለች እየት ሄድሽ፤ከየት መጣሽ፣ ማነዉ ጓደኛሽ፤ ዛሬ ምን ተማርሽ.......የሁል ጊዜ ጥያቄዋ ነዉ። ኧረ አንዳንዴማ እንደዉም ትምህርት ቤት ሳይቀር እየሄደች መምህሮችን በትምህርቷ አደራየ እንዴት ናት ብላ ትጠይቃቸዋለች። ብቻ ይሄ ቁጥጥሮ ትምህርቴ ላይ ትኩረት እንድሰጥ አግዞኛል እንጂማ ቁጥጥር ባይኖር ዛሬ ምን ተማርሽ ብትለኝ ምን እላታለሁ የሚለዉን ሳላስብ ባልተከታተልኩ ነበር።

ደሞ ከሁሉም ግርም የሚያረኝ   ማንኛዉም ዘመድ ሲመጣ ሰላም ካልኩ ቡኋላ እጎረቢታችን ቤት መክያ የምትባል ከኔ አኳያ የምትሆን ጓደኛ አለችኝ እነሱጋ ነዉ እንድጫወት የምትልከኝ። ሌላ ሀገር ሰርግ ምናምን ከሆነ ልሂድ ብላትም እሽ አትለኝም።ብቻ ከሰዉ ጋር እንዳወራ አትፈቅድልኝም።
ቢሆንም ግን አያቴን በጣም እወዳታለሁ። ሁሉ ጊዜም በትምህርቴም  ሆነ በቂርአቴ ጠንካራ ጓበዝ እንድሆን ትመክረኛለች።ልክ እንደናትሽ በጣም ጨዋና ዝምተኛ መሆን አለብሽም ትለኛለች። ለመሆን ብፈልግም ግን አይደለሁም መናገር ያለብኝ ቦታ ላይ በደንብ እናገራለሁ ዝም ማለት ካለብኝም እላለሁ።
በቂርአቴና በትምህርቴ እንኳን አያቴ እንደምትፈልገዉ ጠንካራ ለመሆን ሁሌም እለፋለሁ።
ብቻ ብዙ ሳስብ እማየ ልጀ እንዴት ናት ስትል ከሀሳቤ ነቃሁ።

   አያቴም  ልጂሽንማ ብታያት አንዴት አድርጌ እንዳሳደኩልሽ በትምህርቷ፣ በዲኖ፣ፀባይዋ ብቻ ልጀ እንዴት አይነት ልጂ መሰለሽ አላህ መርቆ የሰጠሽ   
"አልሀምዱሊላህ....  እማ  አላህ ልፋቴን አይቶ  በሷ ሊክሰኝ ይሆናል  እሱ ምን ይሳነዋል።"
እንደሱማ አትበይ ለትንሽ ቀን ነዉ  አብሽሪ....
"እሽ እማ አጠገብሽ ናት እንዴ ፊርዶሴ ካለች እስኪ ድምጿን ልስማት።"


   አያቴም  አደራየ የኔ ዉድ አንኪ አናግሪያት እናትሽ  ናት ብላ ስልኩን ሰጠችኝ ......   ይገርማል! ወይ እናት እናት እንደዚህ በልጇ ትጨክናለች አንዴ! አስራ ሶስት አመት ሙሉ በዛ ላይ ትምህርት ቤት ስሄድ ያገኘኝ ዘመዱ ሁሉ እኔን ሲያይ አፉን ይመጥና እናትሽኳ እንዴት አይነት ቸር ሰዉ ነበረች ለሰዉ ልጂ ያላት ክብር፣ ፍቅሮ፣ ፀባዮ፣ኧረ ሁሉ ነገሮ አባትሽስ ቢሆን.... ያሁኑን አያርገዉና ይሉኛል። ወላሂ እኔ በጣም እየጨነቀኝ ነዉ ያሁኑን አያርገዉና ምን ማለት ነዉ?......ሰዉ ሲሞት ነዉ ያሁኑን አያድርገዉና የሚባል። በሂወት እያሉ ያሁኑን አያድርገዉና..... ሁሉም ነገር ይበልጥ ባደኩ ቁጥር ዉስብስብ እያለብኝ ነዉ።  እሽ አሁን ለእማ  ለምን እንደዚህ ይሉኛል ልክ እንደሞትሽ ሁሉ  ልበላት ነዉስ ለአያቴ ልንገራት እያልኩ ሳስብ  ሄሎ ሄሎ.....ልጀ ወዴት ሄድሽ አለችኝ እኔም ከእንቅልፉ ደንግጦ እንደተነሳ ሰዉ እእእእእ...እማ አለሁ ኔቶርክ ነዉ መሰል አልሰማኝ ስላለ እኮ ነዉ አሁን ግን በደንብ ይሰማል.....   "አይ ይሄ ኔትወርክ ችግር እኮ ነዉ.. ወላሂ ሁል ግዜ ለመደወል እፈልግና ኔትወርኩ እንቢ ይለኛል  መችም ፊርዶሴ አልተቀየምሽኝም አይደል?".........


አይ እማ ምን ብየ እቀየምሻለሁ  እኔኮ አሁን ህፃን ልጂ አይደለሁም ለምን ሳትደዉል ብየ አልቀየምሽም። ድሮምኮ ህፃን  ስለነበርኩ ነዉ ስለማትወጂን ነዉ ሁል ግዜ የማትደዉይ የምልሽ አሁን ግን ችግሩ ይገባኛል።ይህን ተይዉና......
እማ ግን ለምንድን ነዉ  ወደ ሀገርሽ የማትመለሽዉ እኔም አያቴም በጣም እኮ ነዉ የናፈቅንሽ እማ.... በአላህ ነይ እኔኮ ወላሂ መልክሽን እንኳን አላቀዉም እያልኩ እንባተናነቀኝ።

ኧረ በአላህ ፊርዶሴ አታልቅሽ አላህ ባለዉ ጊዜ እመጣለሁ ደሞኮ ምን ይዜ ወደ ሀገሬ እንደምመጣ ግራ ስለገባኝ ነዉ። በቃ አንች ብቻ ዱአ አድርጊ ወላሂ የኔ ልጂ ዱአ የማይሰራዉ የለም።

እሱማ ልክ ነሽ አላህስ በተከበረዉ ቁዱስ ቁርአኑ እንደዚህ ብሎን የል፦
👉 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ እንደዚህ በላቸዉ፦ እኔ ቅርብ ነኝ፤የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ግዜ እቀበለዋለሁ፤ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤እርሱ ሊምመሩ ይከጂላልና።(አል-በቀራ186)

ግንኮ እማ እኔ በሰገድኩ ቁጥር ዱአ አረጋለሁ።ግን አላህ ስለማይወደኝ ነዉ መሰል ዱአየን አይሰማኝም።
"ፊርዶሴ ግን ምን ብለሽ ዱአ አድርገሽ ነዉ አላህ ያልሰማሽ?'

ሁሌም ያረቢ እማየንና አባን ቶሎ አምጣልኝና ቢያንስ መልካቸዉም ልወቀዉ ደሞ ሁል ጊዜ ጓደኞቸን እናትና አባታቸዉ ሲያደርሷቸዉ ሳይ አለቅሳለሁ። ብቸኛ እንደሆንኩም አስባለሁ።የዛኔ አላህየ ሁሉንም አሳካላቸዉና ቶሎ ይምጡ ብየ ዱአ አረጋለሁ ግን......

እማም እያለቀሰች "ወይ የኔ ልጂ እንደዚህማ አትሁኝ አንድ ቀን እንመጣለን ኢንሻአላህ ደሞ ፊርዶሴ የአላህ መልክተኛ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዱአ እንዲህ ብለዋል፦
➥ ማንኛዉም በመሬት ላይ ያለ ሙስሊም አላህን ከለመነ የለመነዉን ያገኛል ወይም እሱ ያላወቀዉን(ያላሰበዉን) ክፉ ነገር ይወገድለታል። በሀጥያት ወይም ዝምድና በመቁረጥ ላይ ሁኖ ዱአ እስካላረገ ድረስ(ቲርሚዚ)....

እንዲህ ስታወራኝ ስልኩ ተቋረጠ እኔም በአሁኑ ሰአት ይቋረጣል እንዴ ሲያናድድ!ምናለ ትንሽ ቢጠብቀን እያልኩ ዞር ስል ዞሬም አያቴ እያለቀሰች ነዉ።ኧረ በአላህ ቆይ እሽ እኔን ለምንድን ነዉ ግራ የምታጋቡኝ? የአንች ልቅሶ፤ የእማየ አለመምጣት፤የአባየ መጥፋት፤የሰዉ ንግግሩ.....ኧረ አያቴ በአላህ ልለምንሽ የምትወጂኝ ከሆነ ካለሁበት ጭንቀት ገላግይኝ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ እባክሽ ብየ እያለቀስኩ ለመንኳት.....

#ክፍል_3 #ይቀጥላል....
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
Forwarded from ETHIO ARSENAL (🅰man.uelb 🇪🇹 x 🇬🇧)
🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ :-

                           እረፍት'

አርሰናል 2-0 ሉተን
#ኦዴጋርድ
#ሃሺኦካ (OG)

🏟 ኤምሬትስ

#COYG 🔴

SHARE ||| @ETHIO_ARSENAL
Forwarded from ETHIO ARSENAL (ቴዎድሮስ)
🇬🇧 31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ

                   ተጠናቀቀ

        🇬🇧 አርሰናል 2-0 ሉተን ታውን 🇬🇧
   ኦዴጋርድ 25'
   ሃሺኦካ (OG) 44'

🏟 ኤምሬትስ

#COYG 🔴

SHARE @ETHIO_ARSENAL
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ሶስት ➌



የምትወጂኝ ከሆነ ካለሁበት ጭንቀት ገላግይኝ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ እባክሽ ብየ እያለቀስኩ ለመንኳት......
አደራየ የጠየቅሽኝን ጥያቄዎች እኮ እመልስልሻለሁ። ግን አደራየ.......  ግን ምን ዛሬም ህፃን ነሽ ልትይኝ ነዉ?  አይደለም ግን ያልኩሽ አሁን ሰአቱ ሂዷል ይሄዉ 11፡30 ሁኖል አሁን ሰላታችንን እንስገድና አንችም የምትቀሪዉን ቀርተሽ ቁርስሽን ብይና ትምህርት ቤት መሄድ አለብሽ ደሞ አረፍደሽ የትምህርት ቤቱ የግቢዉ በር እንዳይዘጋብሽ......  የጠየቅሽኝን ጥያቄ በሰፊ ቀን አጫዉትሻለሁ.... እኔም ተናድጀ ነበርና አያቴ ዛሬ ሳትነግሪኝማ እየትም አልሄድም ትምህርቱም ቢሆን ገደል ይግባ ከኔ ጭንቀት አይበልጥም.......


  አደራየ.... የምን ጭንቀት ነዉ ደግሞ የምታወሪዉ አባትሽም ቢሆን የጠፋዉ ስኡዲ ገፀራማ ቦታ ስለሚሰራ ኔት ወርክ ስለሌለ እንጂ ረስቶሽ አይደለም በዛ ላይ ስራዎችም ስለሚደራረቡበት ሰአት ስለሌለዉ አልመቸዉ ስላለ ነዉ ይሄ ነዉ ያስጨነቀሽ.. ....  አወ እንዴት አያስጨንቀኝ ይገርማል! አባቴም ኔትወርክ ስለሌለ ነዉ የማይደዉል እናቴም ኔትወርክ ስለሌለ ነዉ ብዙ ጊዜ የማትደዉል! ...... እንዴ አያቴ! እናቴስን እሽ መቸም አንዳንዴ ኔትወርክ ሲኖር  ትደዉላለች አባቴ ግን እስከመፈጠሬ ረስቶኛል ለኔ ለአንድ ልጁ እንዴት የመደወያ  ኔትወርክ ያጣል  ከአካባቢዉ ወጣ ብሎ ቢያንስ ከሳምንት አንዴ ካልሆነ ከወር አንዴ እንዴት መደወል ያቅተዋል ታዉቅያለሽ አያቴ እኔ ወላሂ አባቴን የማስታዉሰዉ ሁል ጊዜ ቢሆንም..... ምናለ አሁን ከኔ ጋር በሆነ ብየ የምመኘዉ ግን ልክ የኔ ጓደኛቸ አባታቸዉ  ትምህርት ቤት ሲሸኛቸዉ፤ አቅፎ ሲስማቸዉ ብቻ...... ምን ልበልሽ አያቴ እኔኮ ምን አለበት አንዴ እንኳን መጥቶ በተመለሰ እነዛ ምቀኞችን ዉሸታም መሆናቸዉን በነገርኳቸዉ እያልኩ እንባየን ማፍሰስ ጀመርኩ  አደራየ ምን እያልሽ ነዉ ማነዉ ዉሸታም.....


እነዛ ናቸዋ ጎረቢት ተብየወችሽ.... እነ መክያን ማለትሽ ነዉ አወ አያቴ እነመክያ  እነሱ ደግሞ ምን ብለዉሽ ነዉ? አያቴ ምን የማይሉኝ አለ እነሱን ተያቸዉ ዝም ብለዉ ነዉ እንጂ የሚያወሩ ...  በአላህ ንገሪኝ ምንድን ብለዉሽ ነዉ?  አይ አያቴ ዝም ብለዉ ነዉ ስልሽ በቃ እሽ በአላህ ካልሽኝስ ልንገርሽ ግን አያቴ በአላህምንም ነገር እንደማትናገሪያቸዉ ቃል ግቢልኝ  ምንም ነገር አልናገርም ንገሪኝ.... ደሞ በእኔ አትተማመኝብኝም እንዴ? .......  ዉዷ አያቴ እንዴት የማልተማመንብሽ  አንችኮ ከእናትም በላይ ለኔ ዉድ ነሽ እንዴትኮ እንደምወድሽ  እእእእ ለማረሳሳት ነዉ በይ ተነቃቅተናል አሁን የጠየኩሽን መልሽልኝ እሽ በቃ ከተነቃቃንስ ልንገርሽ......


አንድ ቀን መክያን ትምህርት ቤት ስሄድ አገኘኋት እኔም አሰላሙ አለይኩም መኩ ደህና ነሽ ቤተሰቦችሽስ እንዴት ናቸዉ ብየ ጠየኳት እሷም አልሀምዱሊላህ ደህና ናቸዉ አንችስ ደህና ነሽ አያትሽስ እንዴት ናት  አናትሽስ ትደዉላለች  አባትሽስ ይደዉላል??? አለችኝ እኔም.... አልሀምዱሊላህ አያቴ ደህና ናት እናቴ አንኳን ከደወለች ትንሽ ቆየት ብላለች አባቴ ደግሞ ጭራሽ ደዉሎ አያቅም.... ምነዉ ጠይቀሽኝ የማታዉቂዉን ደዉለዉ ያቃሉ ብለሽ የጠየቅሽኝ?  በሰላም ነዉ አልኳት ፊቷም ትንሽ ቀየር ብሎብኛል መኩም ፊርዳስ እሱስ በሰላም ነዉ ግን አለችኝ እኔ ልጂሽ ጥያቄ መጠየቅ እወድ የል ግን... ምንድነዉ መኩ አልኳት  ፊርዶስ አሁን የምነግርሽን እንደማታምኝኝ አዉቃለሁ ግን ማወቅ አለብሽ እኔ ለራሱ እማየ ስታወራ ሰምቻት ነዉ እንደማታኳርፊኝ ተስፋ አደርካለሁ።  እህ ምን ቢሆን ነዉ ፊርዶሴ እንደማታምኝኝ አዉቃለሁ ያለችሽ.. ...  እህ አያቴ ቆይ ልነግርሽ አይደል...   እኔም ኧረ መኩ በአላህ ምንድን ነዉ አታስጨንቂኝ ችግር አለ? እሽ እናትሽስ ስለኔ ምን ብላ ስታወራ ሰማሻት ብየ ጠየኳት እሷም......

እሷም ወላሂ እመኝኝ ፊርዶስ  አንድ ቀን ማታ ሁሉም ተኝቶ የእማየ ስልክ ጠራ ማንነዉ ደግሞ ከመሸ የደወለ እያለች እማየ አነሳችዉ። እኔም  እንቅፌ ነቃሁ ማን ይሆን እያልኩ የተኘሁ መስየ ማዳመጥ ጀመርኩ  እማየም ስልኩን አንስታ  ዉአለይኩም እሰላም ሀዩ ስትል  አሀ....... የፊርዶስ እናት ናት እንዴ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ  እነሱም የሆድ የሆዳቸዉን ማዉራት ጀመሩ። ያዉ ጓደኞች እንደሆኑ፤አብረዉም እንዳደጉ መቸም አያትሽ ነግራሻለች...... አወ ነግራኛለች በጣም የሚዋደዱ አብሮ አደግ ጓደኛዎች እንደሆኑ....  ሌላም ብዙ ነገሮችን አጫዉተኛለች።


እሽ ይህን ካወቅሽ ያወሩትን ልንገርሽ ወቸም እንደዚህ እየተዋደዱ አይወሻሹም..... እሽ  ግን በአላህ እቸኩላለሁ ከነገርሽን ቶሎ ንገሪኝ ላዳምጥሽ ካልነገርሽኝ ቻዉ ትምህርቴ ይረፍድብኛል....  እንዴ ፊርዶስ እኔኮ እንዴት እንደምነግርሽ ግራ ስለገባኝ ነዉ።  ይህን ያህል.... ምኑ ነዉ ግራ የሚያጋባሽ ሰርፕራይዝ ባልሆነ.... ልትመጣ መሆኑን ልትነግሪኝ ነዉ እንዴ... ወላሂ ይህ ከሆነ አያስጨንቅሽ እኔ ለማንም አልናገርም ...  እኛን ሳትነግረን ሰርፕራይዝ ልታደርገን  ነዉ? ለነገሩ እኔም ጠርጥሬ   ነበር ገና ናፈቃቹህኝ ስትል እንደምትመጣ አዉቄ ነበር ።  ይህንን ነዉ አይደል የሰማሽዉ መኩየ?  ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል። አይ ፊርዶስ ! ወይ መምጣት አሁን ደስታ ለመናገር እንዲህ አድርጌ የምፈራ ይመስልሻል እና ዘሀን ለመናገር ነዉ የፈራሽ? አይደለም ፊርዶስ ግን እንዴት እንደምነግርሽ ጨንቆኝ ነዉ። አንች አንደሆንሽ መቸም ላትነግሪኝ ትምህርቴን አታስረፍጂብን በይ ደህና ዋይ....... እሽ  ፊርዶስ በቃ  አሁን ግን ወስኛለሁ እነግርሻለሁ..... እሽ እየሰማሁሽ ነዉ  ግን ሰአት የለኝም አሳጥሪዉ።   ችግር የለዉም አሳጥረዋለሁ... ... ግን ከሰማሽ ቡሀላ በአላህ ቃል ግቢልኝ መክያ ናት የነገረችኝ እንዳትይ አንችም በሂወትሽ ምንም እንዳታደርጊ፣ አያትሽንም ቢሆን ይበልጥ ዉደጃት እንጂ ፈፅሞ እንትጣያት ቃል ግቢልኝ  ምን እያልሽኝ ነዉ! እኔ ግን  ምንም የምትይዉ ግልፅ ሊሆንልኝ አልቻለም ይበልጥ ዉስብስብ እያለብኝ ነዉ። ቆይ ይህን ያህል ምንድን ነዉ? እያልኩኝ ትንሽ ካሰብኩ ቡሀላ እሽቃል እገባልሻለሁ....... ለማንም አልናገርም አያቴንም ይበልጥ እወዳታለሁ በሂወቴ ላይም ምንም ነገር አላገርም ብቻ ቶሎ ንገሪኝ አፍጥኝዉ.......  እይዉልሽ ፊርዶስ መቸም ሰዉ ነንና ቁመን አንቀርም እንኳን እኛ ወዱ(ረ.ሰ.ወ) ወደ አሂራ ሂደዋል ልክ እንደርሳቸዉ ያንችም እናትና አባት.....

በፈጣር ፍቃድ
#ክፍል_4 #ይቀጥላል....

#Share እያረጋቹ
#Join us 👇👇

@yefkr_world2
@yefkr_tube_1
@yefkr_world