.
#ክፍል_
...🖌ጌድዮ መቅደስ የሱ በሽታ ተጋብቶባት ነው ካሉት ቡሀላ ሂወት አስጠልቶታል መኖር ሰልችቶታል በቃ ሰሞኑንማ በዚህ የተነሳ በሽታው ብሶበታል።....መቅደስ ግን ይህን የማይመስል ወሬ አልሰማችም ብትሰማማ ምንኛ ባዘነች ነበር ሆኖም አሁንም ከሱ አልተለየችም።
......ጌዲዮ ዶርም ውስጥ ሆኖ እንደለመደው እራሱን እየጠየቀ ብቻውን እያወራ ነው ለምን እማራለሁ? ማንን ልጠቅም? ማንን ልረዳ? ደግሞ እኔን ሰው ብሎ ማነው የኔን እርዳታ የሚፈልግ? ማንም ማንም የለም ማንም ከዛም ትምርቱን ለማቆም ወሰነ ቢሆንም ለራሱም የማይክዳቸው ሁለት እውነታዎች ከለከሉት አንድኛው ምክንያቱ መቅደስን አፍቅሯታል ሌላው አደራ አለበት አልቻለም በሁለት መንገድ ተጠመደ ከዛም ጮክ ብሎ መቅደስ ለምን አፈቀርኩሽ ለምን ቀረብሽኝ እያለ ይወቅሳት ጀመር ባዚህን ጊዜ ዶርም ውስጥ ማንም ባይኖርም በለጠው የተባለ የክፍሉ ተማሪ በር ላይ ቆሞ እየሰማው ነበር።
.......መቅደስ ስትወድቅ የተቦጫጨረው ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም አሁን ጤነኛ ነች ያው እንደተለመደው እሷ ሰአዳ ብርሀን ወይንሸት ሆነው ካፌ ቁጭ ብለው ሻይ ቡና እያሉ ነው ወይንሸት ፈፅሞ በፍቅር አታምንም እሷን የሚገዛት ገንዘብና መልክ ነው በዚህ ፀባይዋ ከሶስቱም ጋር አትስማማም በተለይ መቅደስ ሁሌ ሰው እንድትሆን ትመክራታለች እሷ ግን በቀኝ ሰምታ በግራ ታፈሰዋለች መጨፈር ሺሻ ጫት መቃም ከሹገር ዳዲዎች ጋር መውጣቱዋ የታወቀ ፀባይዋ ነው።እናም እየተጨዋወቱ እያለ ዮናስ እየተንጎባለለ መጣ...
ሁሉንም ሰላም ካላቸው ቡሀላ አብሯቸው ተቀመጠ ከዛም ግን ለምን ወጣ ብለን ምሳ አንበላም አላቸው ወይንሸት ተቅበጥብጣ እሺ አለች እነብርሀንም የግቢ ምግብ ስለሰለቻቸው ተስማሙ መቅደስ ግን ለመሄድ አልፈለገችም ቢሆንም በውለታ ስለታሰረች ፈገግ ብላ ጥያቄውን ተቀበለች።
.......ከዛም ይዟቸው ከግቢ ሲወጣ አሁንም ጌዲዮ አየ ዮናስ ተንኮሉ መቅደስ መቅደስን እየታከከ ነው የሚሄደው።ከጌዲዮ አጠገብ የነበሩ ሁለት ልጆችም አይተው ስለመቅደስና ስለዮናስ ማውራት ጀመሩ አንተ ግን መቅዲ ዮናስን አፈቀረችው አይደል? ... አረ አይመስለኝም ..ተው እንጂ ዮናስን እዚህ ግቢ የማታፈቅረው ሴት አለች ልትለኝ ባልሆነ...በርግጥ ቆንጆ የተባሉት ሁላ ያፈቅሩታል ግን እሱ የሚፈልጋቸው ግዜ ማሳለፊያ አይደል እንዴ?.....ባክህ መቅደስም ተከይፋበታለች ታስታውቃለች ጌዲዮ ለመስማት ተሳነው ከተቀመጠበትም ተነስቶ ወደለመደው ጫካ ሄደ ......
ዮናስ ምሳ ጋብዟቸው ሲያበቃ ለምን አንድ ሁለት እያልን ስንቀውጠው አናመሽም አላቸው ይህን ጊዜ ሰአዳ በሉ እኔን ሸኙኝ አለቻቸው መቅደስም አረ እኔም ጥናት አለብኝ አላመሽም አለች መቅደስ እንድትቀር ወይንሸትና ብርሀን ለመኗት እሷም አይሆንም አለች ከዛ ብርሀን መቅዲ ካላመሸች እኔም አልፈልግም አለች ከዛም በቃ ልሸኛችሁ ብሎ ወደ ግቢ ወሰዳቸውና ከወይንሸት ጋር ተመለሱ።
......ልክ እነመቅደስ ወደውስጥ ሲገቡ እነሱም መታጠፊያውን መንገድ ሲይዙ ወይንሸትና ዮናስ ተቃቅፈው እየተላፉ ሲላቸው እየተሳሳሙ መንገድ ጀመሩ ዮናስና ወይንሸት መቅደስ የማታውቀው ድብቅ ግንኙነት አላቸው ሁለቱም የጥቅም ሰው ስለሆኑ ይስማማሉ ባለፈውም መቅደስ የወደቀችው የጌዲዮ በሽታ ተላልፎባት ነው የሚለውን ወሬ ዮናስ ነው በወይንሸት አፍ ያስለኮሰው ምክንያቱም ሁለቱ እንዲለያዩ ይፈልጋል ዮናስ ጌዲዮንን በነገር ግቢውን ሊያስለቅቁት ለወይንሸት ብር ሰጥቶ አሳምኗታል።
......ይኸው በወይንሸት ስብከት በተደጋጋሚ ዮናስና መቅደስ እንዲገናኙ ሲገናኙም ጌዲዮ እንዲያይ እያደረገች ነው።
....ጌዲዮም የሚሰማው የመቅደስ እና የዮናስ የተቀናበረ የውሸት ፍቅር እውነት ነው ብሎ ሊቀበል እየተገደደ ነው።
....በተለይ ባለፈው አቅፎ ሆቴል ሲያስገባት ካየ ቡሀላ ትምርት በቃኝ እሷን እያየሁ ከምቃጠል ባቋርጥ ይሻለኛል ብሎ ከትምርቱ ሊሰናበት ወስኗል።
.........ጌዲዮ መቅደስን እንዳትጠጊኝ ስለኔ አይመለከትሽም ካላት ቀን ቡሀላ ዘወር ብላም እንዳላየችው ነው የሚያውቀው...አሁንም እራሱን ጠየቀ እውነት አፍቅራኝ ቢሆን አትንኪኝ ስላልኳት እኔን ትታ ሌላ ወንድ ጋር ባትሄድ ነበር አለ።
ከዛም ፍቅሯን መቋቋም ሲያቅተው ካይኗ ብርቅ ይሻለኛል ብሎ ትምህርቱን ሊሰናበት ወደደ መፅሀፎቹን ብቻ ሰብስቦ ለማንም ሳይናገር ወደ መጣበት ሊመለስ ግቢውን ለቆ ወጣ ልክ የግቢውን በር ሲያልፍ አደራ መብላቱን ፍቅሩን ማጣቱን አስታውሶ በቆመበት ወደቀ መቅደስም ከሩቅ አይታው እየሮጠች መጥታ በፊት እንደምታደርገው ክርቢት ምናምን አጭሳ ሰውነቱ ሲረጋጋ ሳይነቃ ልታመልጠው ልትነሳ ስትል አድርጎት የማያውቀውን ወዲያው ነቃ መቅደስ ውሀ ሆነች እንዳይመታት ሁለት ጉንጮቿን በእጆቿ ያዘች ተንቀጠቀጠች ጌዲዮ ግን በልቡ አይኖችሽ ስንቅ ይሁኑኝ ብሎ ፍዝዝ ብሎ አያት አይኖቹ እንባን አፈሰሱ መቅደስ ሳታውቅ ፍቅሯ ተሰናብቷት መንገዱን ቀጠለ መቅደስም ሁኔታው ግራ አጋብቷት ሳታውቀው በቆመችበት ባይኖቿ ሸኘችው...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል7️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
...🖌በቃ ጌዲዮ ሄደ አንድ ሁለት ተብሎ ሶስተኛ ቀን ተቆጠረ መቅደስ ግራ ገባት ከክፍል ተማሪ አንስታ እስከ ዳሬክተር እየተመላለሰች በምን ምክንያት እንደጠፋ ጠየቀች ግን መልስ ማግኘት አልቻለችም የጌዲዮ መጥፋት የዩንቨርስቲውም አሳሳቢ ዜና ሆኑዋል ምክንያቱም ጌዲዮ በጣም ተስፋ የተጣለበት ጎበዝ ተማሪ ነው።
........መቅደስ ምግብ አልበላ ውሀ አልጠጣ አለች ትኩረቷም ከትምርቷ ተነሳ ታመመች ምንም የግሏ ባይሆንም አቅፋ ስታስታምመው የራሷ ያደረገችው ያክል ስለሚሰማት ደስተኛ ነበረች ፍቅሯ የጋራ ባይመስላትም እሷ ግን አይኑ ነበር የፍቅር ምግቧ አሁን ግን ጠፋ ምክንያቱን እንኳን ሳታውቅ ተሰወረባት ብቸኝነት ተሰማት።
.......አሁን የዮናስ እና የወይንሸት ሀሳብ ተሳካላቸው የጀመረውን ጌም ለማሸነፍ አንድ እንቅፋቱን አስወገደ መቼም ከዚህ ቡሀላ ይመጣል ብሎ መገመት ከባድ ነው።
.........መቅደስ እራሱዋን አስራ ብቻዋን ዶርም ተኝታ በናፍቆት እየተብሰለሰለች ትገላበጣለች ከዛም እነሰአዳ መጡ በየቦታቸውም አረፍ አሉ ወይንሸት ግን ይህን የተወጣጠረ እርቃኑዋን ነች አትባል ለብሳለች አትባል ብቻ ለባብሳ መቀባባት ጀመረች እነብርሀን የመቅደስን ሁኔታ እያዩ ነው አያባብሏት ነገር ብዙ ብለዋት ማፅናኛ ቃል አልቆባቸዋል ደግሞ ያውቃሉ መፍትሄ እንጂ ምክር አይጠቅማትም.....
....ከዛም ሰአዳ ወደ ወይንሸት ዞራ ወይና ግን በአላህ ምናል ትንሽ እንኳን ሸፈን ያለ ነገር ብትለብሺ አለቻት እሷም አረ ይሄም እራሱ እረዝሟል ስትል ብርሀን እግዚኦ ታዲያ አንድኛሽን እርቃንሽን አትሄጂም ስትል መቅደስ በተዋጠው ድምጿ ግን የት ልትሄጂ ነው እንዲህ ሆነሽ አለቻት እሷም እእእ ፖርቲ ዛሬ እኮ እኔና ሚኪ የተዋወቅንበት አንደኛ ወራችን ነው አለች መቅደስም አይ ለወደፊትማ ሰላም ከተባባልሽው ወንድ ሁሉ ልደት ታከብሪያለሽ ብርሀን ሳቅ ብላ የት ይቀራል አለቻት።
ከዛም ወይና ወደ መቅደስ ከተኛችበት አልጋ ተጠግታ እንዳዘነ ሰው ቅልስልስ ብላ መቅዲ ግን ይሄን ጌዲዮን እረስተሽ ለምን ከዮናስ ጋር አዲስ ላይፍ አትጀምሪም እስከመች እንዲህ ተኮራምተሽ አለቻት እነብርሀንም ግራ ስለገባቸው አው እርሺው እሱ እንደሁ ጥሎሽ ሄዷል እራስሽን ማረጋጋት አለብሽ አሏት መቅደስም እናንተ ምን ነካችሁ ዮናስ እኮ ንፁህ ጓደኛዬ ነው ወይንሸትም ፈጠን ብላ እሱ ግን ያፈቅርሻል ስትላት ስልኳ ጮኸ በቃ መቅዲ አስቢበት ብላ ቦርሳዋን ይዛ ስልኳን እያናገረች ወጣች ከዛም እነብርሀን ወሬውን ሊቀጥሉ ሲሉ መቅደስ ይልቅ እኔም ስለ ጌዲ ያልጠየኩት አንድ የክፍሉ ልጅ አለ እሱ ጋር ልሂድ ብላ ተነሳች ሰአዳና ብርሀንም ተከተሏት።
...ሄደውም ሌላ ጓደኛውን አገኙ ይቅርታ ወንድም በለጠውን ፈልገን ነበር ሲሉት በሌ መቃሚያ ቤት ነው በዚህ ሰአት እዚህ አይገኝም ግን እኔም እዛው ልሄድ ድለሆነ ከፈለጋችሁ ልውሰዳችሁ አላቸው እነሱም ተስማምተው አብረውት ሄዱ።
በእውነት እዚህ መንደር መቃሚያ ቤት ቀርቶ ሱቅ እንኳን ያለ አይመስልም ብቻ እያሹለከለከ ወሰዳቸው ወደ ውስጥ ሲገቡ በጣም ተደናገጡ ውስጥ ያሉት እነመቅደስን እነሱ ደግሞ ተማሪዎቹን እያዩ ተፋጠጡ ግማሹ ጫት ይቅማል ግማሹ ሺሻ ያጨሳል ሌሎቹ ሲጋራ ቀስ ብለው ተቀመጡ ከዛም በትዝብት ቤቱን ይቃኙ ጀመር አብዛኞቹ የግቢ ተማሪዎች ናቸው ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚቅሙና የሚያጨሱም አሉ
ከዛም አንዷ መጣችና ምን ልታዘዛችሁ አለቻቸው በዚህ ሰአት ያመጣቸው በለጠውን ሊጠራ ሄዶ ነበር እናምአረ ምንም አንፈልግም አሉ ታዲያ ምን ልትሆኑ ገባችሁ ስትላቸው በለጥው ተያቸው እኔን ፈልገው ነው አላት
ከዛ አጠገባቸው መጥቶ ተቀመጠ ምን እንደፈለጉ ሲጠይቃቸው ስለጌዲዮ የምታውቀው ነገር ካለ ብለን ነው አሉት።
.......ስለሱማ እኔም በጣም ታስዝቤሻለሁ ያረግሽው ነገር እኮ ከንዳንቺ አይነት ሴት የማይጠበቅ ነገር ነው አላት መቅደስ ምን እንደምታወራ አልገባኝም አለችው ለማንኛውም ልወጣ ስለሆነ እየሄድን እናውራ አላቸው ከዛም ተነሱ
....ቀጠለ ልንገርሽ ጌዲዮ ትምርቱን የተወዉ ባንቺ ምክንያት ነው መቅደስ በጣም ደነገጠች ማፍቀሩን ባይገልፅላትም ያኔ ጌዲዮ ብቻውን ሆኖ ሲያወራ ከበር ቆሞ የሰማውን ሁሉ ነገራቸው።
.........መቅደስ እነ ብርሀንን ጠየቀች ማነው ማነው እንዲህ ያለው?? እኔኮ የወደኩት ብላ የወደቀችበትን ሁኔታ ነገረቻቸው እነሱም አንገት ደፉ ብርሀንም ሙሉ ግቢው እኮ ነው በሱ በሽታ መውደቅሽን ያወራው ስትል ታዲያ ለምን አልነገራችሁኝም ብላ ጮኸች ሌላ ህመም ጌዲዮ በሷ ሰበብ እንደሆነ አወቀች ትምርቱን የተወው...
በቃ ትምርትም አስጠላት ይኸው ክፍል ቁጭ ብላ ሀሳቧ ግን ሌላ ጋር ነው ከዛም አቋርጣ ወጣች ሰአዳም ተከተለቻት መቅደስ ግን ምን እየሆንሽ ነው ቢያንስ ለናት አባትሽ ለቤተሰቦችሽ አታስቢም የውጪ እድልሽን አሳልፈሽ እየተማርሽ ያለሽው እኮ ያስተማረሽን ህዝብና ሀገር ለመጥቀም ነው ከሁለት አጥ አትሁኚ እንጂ አላማሽን እንዴት ትዘነጊያለሽ ብላ ሰአዳ ተቆጣቻት መቅደስም እንባ ተናንቋት አቃተኛ አቃተኝ ምን ላርግ አልቻልኩም እንደውም እኔም አልማርም ስትል ሰአዳ መቅደስ ይሄ መፍትሄ አይሆንም ባይሆን ለምን አድራሻውን ፈልገን አንሄድም አለቻት ከዛም ተያይዘው አድራሻውን ለማግኘት ወደ ቢሮ ሄዱ...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...🖌መቅደስና ሰአዳ የጌዲዮን አድራሻ ለመጠየቅ ወደ ቢሮ ሄዱ ቢሮውን ሲያንኳኩ ይግቡ የሚል ድምፅ ሰሙ ከፍተውም ገቡ ሲገቡም ያጋጠማቸው አስተናጋጅ የመቅደስ አፍቃሪ መምህር ያሬድ ነው።መቅደስ በሰአቱ አልደነገጠችም ባለፈው በንዴት ተማሪ መሀል መቅደስ የሰደበችውን አስታውሳ ሰአዳ ግን ክው ነው ያለችው። መምህር ያሬድ መቅደስን ሲያይ እየተቅለሰለሰ እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ተቀመጡ ምን ልርዳችሁ አላቸው በትህትና እነሱም የጌዲዮን አድራሻ ፈልገው እንደሆነ አስረዱት መምህር ያሬድ በጌዲዮ የተነሳ በሚያፈቅራት ሴት አንደበት ተሰድቧል በሷ ሳይሆን በሱ ቂም ይዟል እሱ ከሌለ የግሌ አደርጋታለሁ ብሎም አሰበ በውስጡም እንኳን ከዚ ግቢ ከምድረ ገፅም ይጥፋ ብሎ ተመኘ በመቀጠልም ነገ ፈልጎ እንደሚጠብቃቸው ነግሮ ልክ በዚህ ሰአት መጥተው እንዲወስዱ ቀጠራቸው መቅደስ ፈፅሞ ቂም ይዟል ብላ ስላላሰበች አመስግነውት ሄዱ።.......ልክ እንደሄዱለትም በርብሮ ፈልጎ ወዲያው አገኘው ከዛም ከሌላ ሰውም እንዳያገኙት አርጎ የጌዲዮን አድራሻ ሰነድ አርቆ ደበቀው።
..........በነጋታውም ክላሱዋን አቋርጣ ባላት ሰአት ቢሮው ሄደች በለሰለሰ ድምጿ ስጠኝ ብላ ጠየቀችው መምህር ያሬድም መቅዲ የእውነት በጣም አዝናለሁ ከትላንት ጀምሮ ሌላ ስራ አልሰራሁም ማለት ይቻላል ስፈልግ ግን ላገኘው አልቻልኩም መቅደስም ሙሉ ተስፋዋ ተሟጦ አላገኘሁትም ማለት አለችው እሱም መቅዲ የቻልኩትን ሞክሪያለሁ ግን ላገኘው አልቻልኩም ምንም ማድረግ አልችልም ሲላት እንባዎቿ ካይኗ እንደጅረት ያለማቋረጥ ይፈሱ ጀመር መምህር ያሬድም ከወንበሩ ተነስቶ አጠገቧ ሄዶ አቅፎ ባስመሳይ አንደበቱ አባበላት።.....ከቢሮ ስትወጣ ላያት ከለቅሶ ቤት ተመላሽ ነው የምትመስለው............
...ከዛም እየተመላለሽ ጠይቂኝ ስላላት እየተመላለሰች ወደቢሮው ትሄዳለች እያለቀሰች ትመለሳለች አንድ ቀንም እንዲሁ እያነባች ወደ ክፍል ስትገባ እነ ብርሀን ቁጭ ብለው እያጠኑ ነበር ምንም ሳታናግራቸው ተጠቅልላ ተኛች ብርሀን ግን ቀሰቀሰቻት እና ይህ ቆይ የያሬድ ተንኮልስ ቢሆን አለቻቸው ሰአዳም እኔም ጠርጥሪያለሁ አለች መቅደስም ተነስታ ቁጭ አለች ወይን እሸት ግን ምንም መናገር አልፈለገችም ግን እውነት ቢሆንስ ብላ ለማጣጣል እንዴ ምን ልሁን ብሎ ይህንን ነውር ይፈፅማል ስትል ወዲያው መቅደስ ባለፈው ይቅርታ ስላልጠየኩት አለች እነብርሀንም አዎ የሚል መልስ ሰጧት ከዚያም ያሬድ በማይኖርበት ሰአት ሄደው ሌላ መምህር ጠየቁ ያው ያሬድ ስለደበቀው ፈልገው ቢያስፈልጉትም ሊያገኙት አልቻሉም ወይንሸት ደስ አላት ሰአዳና ብርሀን ግን ከመቅደስ ጋር አብረው አዘኑ።
.........ወይንሸት እና ዮናስ ጌዲዮ ስለጠፋ መቅደስን እንዳሰቡት የጌሙ መሀል ላይ ማቆም አልቻሉም አሁን እሷ ማንንም ማግኘት አትፈልግም ልክ እንደጌዲዮ ብቸኝነትን መርጣለች ይሁን እንጂ ሙከራቸውን አላቆሙም ባለፈው ወይንሸት ማሳመን እንደከበዳት ለዮናስ ስትነግረው ቅድሚያ ብር ስለሰጣት ዝቶባታል እሷም ከዮናስ ከተጣላች ብዙ ገቢ እንደምታጣ ስለምታቅ ሙከራዋን አጠንክራ ቀጥላለች።
መቅደስ ጌዲዮን በብዛት የምታይበት ቦታ እየሄደች በተስፋና በናፍቆት ትጠብቀዋለች የወንዶች ዶርም መግቢያውን ከሩቅ ሆና ድንገት የምታየው እየመሰላት በስስት ትጠብቀዋለች ወድቆ የምታቅፈውን ታስታውሳለች እውነት ላያት ታስለቅሳለች ለካ ፍቅር እውነትም ሀያል ነው ማለትም የማይቀር ነው።....ፍቅርን ስላልፈለጉት አይለቅም ስለፈለጉትም አይዝም በቃ በፍቅር ወጥመድ ውስጥ መውደቅ ወደድንም ጠላንም የተፈጥሮ ህግ ነው ከዚ በፊት መቅደስ ካይስኩል ጓደኛዋ ፍቅር እንዲይዛት ትፈልግ ነበር ምክንያቱም ለሷ ከማንም በላይ ብዙ ነገር ሆኖላታል ብዙ ብዙ በቃላት የማይገለፅ ፍቅርን ሰቷታል ግን ፍቅር እንዲይዛት ስለፈለገች አልያዛትም ይኸው ዛሬ ግን ተራው ደርሷት በጌዲዮ ፍቅር እንዲህ እየታመመች ነው።.............ከሩቅ ሆነው ሲያዩዋት የነበሩ የግቢው ቦዘኔ ተማሪዎች ሊያስደነግጧት ተነጋገሩና አንድኛው ተማሪ ልክ እንደጌዲዮ አጎንብሶ ወደወንዶቹ ዶርም መግቢያ ሄደ መቅደስም በተስፋ ስትመለከተው የነበረው መግቢያ ጌዲዮን ያመጣው መሰላት ልጁም ልክ እንደጌዲዮ ተንፈራፍሮ ወደቀ መቅደስም ጨርቋን ጥላ ወደሱ እሮጠች ልክ ስትደርስም ልጁ በሳቅ ወደቀ ሌሎቹም እራሷን እስክትይዝ ሳቁባት እያለቀሰች ወደማደሪያዋ ሄደች አብዛኛው ተማሪ ግን አዘነላት እነዛ ቦዘኔ ተማሪዎች በሰሩት አሳፋሪ ስራ ተበሳጩ እውነት ግን የፍቅር አምላክ ጌዲዮን ያመጣላት ይሆን???????????
........ዶርም ስትገባ ብርሀንና ሰአዳ ሁኔታዋ አንጀታቸውን በልቶት አብረዋት አለቀሱ ወይንሸትም አሁን ተንኮል ለመስራት አመቺ ግዜ ላይ እንዳለች አስባ ብርሀንን እና ሰአዳን መቅደስን ማዝናናት እንደምትፈልግ ነግራ እነሱም እንዳይከተሏት አሳመነቻቸው ከዛም በስንት ልመና መቅደስን ላዝናና በሚል ፓርቲ ወሰደቻት ሀሳቧ ግን ማዝናናት ሳይሆን በመዳኒት አደንዝዛ ከ ዮናስ ጋር አንሶላ እንዲጋፈፉ ማድረግ ነው።ከዛም እንዳሰበችው ቀኑ ሄዶ ጨለማው ሲተካ የቀረበላት ለስላሳ ላይ መዳኒት ጨመረች እራሷንም ስትስት መጨፈር ማበድ ስትጀምርላት ፈረሱም ሜዳውም ያው ብላ ለዮናስ አስረክባ ከሹገር ዳዲ ጋር ተቃቅፋ ወጣች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል9️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
...🖌ምሽቱ በጭፈራ ቅልጥ ብሏል መቅደስ እራሷን አታውቅም ከዮናስ ጋር ታብዳለች ትጨፍራለች ትዘላለች ታቅፈዋለች ብቻ የዮናስ ጓደኞች መሸነፋቸውን አመኑ መዳኒት ጠጥታ መሆኑን ማንም አልጠረጠረም ግን ውርርዱን የሚያሸንፈው አብረው እንዳደሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ሲያቀርብ ነው ለዚህም ቀደም ብለው ከ ወይንሸት ጋር ዝግጅት አርገዋል።
...........ከዛም አቅፎ ወዳልጋ ክፍል ወሰዳት ስልኩ ደጋግሞ ይጮሀል ግን ብዙ ወንዶች አድንቀው ያላገኙት ገላ መዳፉ ላይ መሆኑን እያሰበ ሊያነሳው ፍቃደኛ አልነበረም መቅደስ በዛ ሰአት ምንም ቢያረጋት እራሷን አታውቅም ተዘርራለች ሌላ አለም ውስጥ ነች እሱም ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይሄኔ ነው አለ ባንድ በኩል የውርርዱ ከፍተኛ ገንዘብ ሌላው አስደማሚው የመቅደስ ገላ ደስ አለው ከዛም ልብሱን ሲያወላልቅ ስልኩ ድጋሚ ጮኸ ተናዶ ሊዘጋው ሲያይ አሁን ካሰበው የውርርዱ ገንዘብ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ቢዝነስ ነው ዮናስ በብር ቀልድ አይወድም ሲኦል ብር አለ ቢባል እንኳ ገነትን ትቶ ሲኦል እንደሚገባ አያጠራጥርም ከዛም ይህንን ጨዋታ ለነገ ቀጠሮ ከራሱ ጋር ያዘ መቅደስንም ግቢ ድረስ አድርሷት ወደ ተጠራበት ቢዝነስ ሄደ።
.........ጠዋት ይህንን ወሬ ለወይንሸት ሲነግራት በጣም ተበሳጨች ቆይ እጅህ የገባን እድል አሻፈረኝ ብለክ ድጋሚ ትላለህ አለችው ዮናስም ከዚኛው የዛኛው ቢዝነስ ይበልጥ ነበር ስለዚህ የሚቀድመውን አስቀደምኩ አላት ወይንሸትም ታዲያ እንዴት ብዬ ነው ድጋሚ የማሳምናት በዛ ላይ ትላንትና ለምን ጥለሻት ሄድሽ ሲሉኝስ ምንድነው መልሴ ብላ ጠየቀችው እሱም ሴት ብልሀት አታጣም ይባል የለ ሴትነትሽን አንዳንዴ እንኳን ተጠቀሚበት ብሏት ሄደ።
...........የፈራችው አልቀረም ወደ ዶርም ስትገባ መቅደስ ታማ እነ ብርሀን እያስታመሙ ደረሰች ሰአዳ ልክ ስታያት ደሟ ፈልቶ ቆይ አንቺ መቼ ነው አደራሽን የምትወጪው አለቻት እሷም አይን አውጥታ ምን አረኩ አለች ይሄኔ ብርሀንም ቦግ ብላ ምን ማለት ነው የወሰድሻት እኮ ጭንቀቷን እንድትረሳ ላዝናና ብለሽ እንጂ አስክረሽ ሜዳ እንድትጥያት አይደለም።
.......ወይንሸትም ውሸቷን ጨማምራ እየውላችሁ መጀመሪያ ደና እየተዝናናን ነበር ከዛም ካልጠጣሁ ብላ አስቸገረችኝ ምንም ማረግ ስላልቻልኩ ሰጠኋት ከዛም መስከር ጀመረች ይሄን ጊዜ ዮናስን አየችው ከሱ ጋርም ካልጨፈርኩ ብላ እሪ አለችብኝ ደስታዋን ስለሆነ የምፈልገው እሺ አልኳት ከዛም ተመቻቹ መቅደስ ደንግጣ ከተኛችበት ተነሳች ምንድነው የተመቻቸነው አለቻት ወይንሸትም አስመሳይ ሳቋን በፌዝ መልክ ስቃ ማለት አንድ ላይ መደሰት መጨፈር ጀመራችሁ እሱም አብራኝ ትሁን እሸኛታለሁ ሲለኝ ያው እንደውስ ከኛ በላይ ውለታ ውሎልሽ የለ አብራችሁ እንድትሆኑ ትቼ ከፍቅረኛዬ ጋር ሌላ ጭፈራ ቤት ሄድን አለቻቸው ሁኔታው ቢያጠራጥራቸውም 50%አመኗት።
.........መቅደስ እንደበፊቱ መሆን ተስኗታል በደንብ አትበላ አትጠጣ አትማር አትተኛ ውበቷ ባይካድም ጉስቁል ብላለች።
የጌዲዮ አለመምጣት አድራሻውም መጥፋቱን ሙሉ ለሙሉ አመነች።......በዚህ ከቀጠለች ትምርቷን ማቆሟም የማይካድ ነው በርግጥ ጌዲዮ ከሄደ ሁለተኛ ሳምንቱን ያዘ
.......ወይንሸት አሁንም እኒድ እንዝናና የሚል ጥያቄ ለመቅደስ አቀረበች መቅደስም ጓደኞቿም አልተድማሙም ብንሄድ እራሱ ሁላችንም አሏት...... ፍፁም እንደትላንቱ ለማሳመን ጣረች የሚያምናት ግን አጣች።.....የዮናስም የወይንሸት እቅድ ግብ ሳይመታ ቀረ።
...........ዛሬ ደግሞ ቀኑ ሌላ ነው ለመቅደስ አፍቃሪዎች ሀዘንን አለማመንን ስቃይዋን ተረድተው ላዘኑላት እና ለራሷ ለመቅደስ ትልቅ የምስራች ቢባል ማካበድ አይሆንም...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
attach 📎
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 0️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
🖌...ነገሩ አስገራሚም አስደንጋጭም ነው አስደንጋጩ ጌዲዮ አይመጣም ብለው ለደመደሙት ነው አስገራሚው ክስተት ደግሞ የመቅደስ ህልም እውን መሆኑ ነው።
.
....ለካ ነገሮች ሲዘበራረቁ ቦታ ቦታቸውን ሊይዙ ነው የሚባለው እውነት ነው።ጌዲዮ ካመጣችው ባጃጅ ሲወርድ እውን እሱ አይመስልም በጣም ከስቶ ፊቱ ጠቁሯል ምግብ አሳይተው እንደነሱት ህፃን ብብት ብሏል ፀጉሩ ተበጥሮ የሚያውቅ አይመስልም ልብሱም ዝርክርክ ብሏል ብቻ ባጭሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳይሆን የጎዳና ተዳዳሪ መስሏል ተማሪው ተገርሞ ለወሬ ከመቸኮሉ የተነሳ ቀስ ብለው ፎቶ አንስተውት በሚሴጅ መቀባበል ጀመሩ ባንዴ ግቢው ተዳረሰ ደስ ያላቸው እንዳያቅፉት እንኳን ደና መጣህ እንዳይሉት ይፈሩታል በመምጣቱ የተበሳጩት ደግሞ ቢችሉ መልሰው ቢያባርሩት ደስታቸው ነበር።.......
በዚህ ሰአት መቅደስ እራሷን አሟት ተኝታ ነበር እነሰአዳም አሉ። የመቅደስ ስልክ ሲጮህ ዝም አለችው ከዛም ሚሴጅ ገባ ብርሀንም ለምን አታዪውም አለቻት መቅደስም እራሷን ይዛ እንዳቃታት አመልክታ አንቺ እዪው አለቻት ከዛም ስትከፍተው ጌዲዮ የመምጣቱ ዜና ነው ብርሀን ሳታስበው በደስታ ጮኸች እነሱም ደንግጠው ምን ሆንሽ አሏት እሷም ነገረቻቸው ግን አላመኗትም ከዛም ፈጠን ብላ ፎቶውን አሳየቻቸው መቅደስ ከማየቷ ከመኝታዋ ወርዳ በለሊት ልብሷ ጫማ እንኳን ሳታደርግ በረረች እነሱም ተከተሏት...
.......ወይ ፍቅር
......ዞር ብላ ግራ ቀኝም አላየችም ቀጥታ እንዳየችው በራ ዘላ ተጠመጠመችበት እራስ ምታት የተባለ ተረሳ ጌዲዮ ትርታው ጨመረ ለማንም ተሰምቶት የማያውቅ ስሜት ለሷ ስለሚሰማው እንደማግኔት ስቦት እሱም አቀፋት ብዙ ተማሪ በሁኔታቸው አለቀሰ ብርሀንና ሰአዳማ ተቃቅፈው ነው ያለቀሱት ጓደኛ መታደል ልክ እንደነሱ ነው ደስታዋ ደስታቸው ሀዘኗ ሀዘናቸው። ሌሎቹም ፎቶ እያነሱ በ ፌስቡክ ይለጥፏቸው ጀመር ግን አዎ ተቃቅፈው ላያቸው እውነት ያጓጓሉ እናም ለደቂቃም ቢሆን ናፍቆታቸውን አስታገሱ ሁለቱም የደስታ እንባ ተናነቃቸው ግን ልትለቀው ስታስብ ፈራች ከዛ እየተቅበጠበጠች ደስታዋን ለመደበቅ እየሞከረች ካንገቱ ስትላቀቅ በሳቅ ተሞልታ አይናይኑን እያየች ውይ ጌዴ ይሄን ያክል ጊዜ የት ሄደህ ነው አለችው።
.....እሱም በስስት እያያት ዝም አላት ቀጠለች በመምጣትህ ደስ ብሎኛል እንኳን ደህና መጣህ አለችው እሱም አመስግኗት ቦርሳውን ይዞ ወደ ማደሪያው ሄደ።
........ጌዲዮ እንዲህ ጉስቁል ያለው በናፍቄቷ በፍቅሯ ነው ከሄደበት ቀን ጀምሮ ካንድ ቤት ወጥቶ አያውቅም ከሷ ሌላ ምንም አይታየውም ነበር በርግጥ በፊትም ማንንም ባያናግርም እሷን ሲለይ ግን ብሶበት አንድ ክፍል ውስጥ ማልቀስ ባለቀሰና እራሱን ባስጨነቀ ቁጥር በሽታው እየተነሳበት ከመቅደስ በላይ ጌዲዮ ተጎድቷል ትላንት ግን እራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው የመጣው ቢመጣ የማንም ብትሆን አይኗን ባይ ይሻለኛል ብሎ ነው ገና በለሊት ጅማን የረገጠው።
......በውነቱ መቅደስ ስታቅፈው በህልም አለም ውስጥ ያለ ነበር የመሰለው ነገር ግን ሲለያት በውኑ መሆኑም ሲታወቀው ታፍቅረው አታፍቅረው ባይገባውም ደስታውን መቆጣጠር አቅቶ አለቀሰ።
........መቅደስም ስለቷ ሰመረ እሷም እንደሱ ማፍቀሩን ባታውቅም በደስታ ሰከረች።
.....ይሄንን የሰሙት መምህር ያሬድ ወይንሸት ዮናስም በንዴት የሚይዙት የሚጨብጡት አጡ።
.....የጅማ ዩንቨርስቲ እሁድም ስለሆነ ገና በጠዋቱ ድምቅምቅ አለ።
.......የመቅደስንና የጌዲዮን ደግሞ የመገናኘት ደስታ እነብርሀን ባንድ ለማድረግ አሰቡ በመቀጠልም ከጌዲዮ የዶርም ጓደኞች ጋር በመነጋገር ገንዘብ አዋጡ ብርሀን የሀብታም ልጅ ስለሆነች ከሴቶች ከፍተኛውን ወጪ የሸፍነችው እሷ ነች ከወንዶች ደግሞ በለጠው ወይንሸትን ሲነግሯት በጣም ስለተቃጠለች ግን እንዲያውቁባትም ስለፈለገች ብሩን አዋጣለሁ ፓርቲው ላይ ግን አልገኝም ሌላ ቀጠሮ አለኝ አለቻቸው ሰአዳም አረ ብር በሽ ነው አንፈልግም አለቻት።
......በርግጥ ለብዙ ጊዜ አብረውት ሲማሩ በዝምታውና በበሽታው የተነሳ ለማናገር ቢፈሩትም ዛሬ ግን ደፍረው ከማናገርም አልፈው ወስደው ፀጉሩን አስቆርጠው በራሳቸው ምርጫ አልብሰው አስጌጡት ጌዲዮ መጀመሪያ ሲነግሩት ውስጡ ደስተኛ አልነበረም ምክንያቱም ብዙ ጫጫታና ወከባ ያለበት ቦታ አይመቸውም ቡሀላ ግን መቅደስ እንደምትኖር ሲነግሩት እሷ ካለች የትም ይመቸኛል በሚል ሀሳብ ፍቃደኛ ሆነ።
.
.....መቅደስም ሲነግሯት ደስታዋ እጥፍ ሆነ እሷንም እንደሱ አስዋቧት
......ከዛም የሚገርም ፓርቲ ሆነላቸው በርግጥ አንድ ላይ ባይሆኑም ግን ባይን እየተሰራረቁ አንዳንዴ ደግሞ ደፍራ እየሄደች እያናገረችው ምሽቱን ቦረቁበት ግን ጌዲዮ ያመዋል ብለው ሰግተው ነበር እሱ ግን እንኳን ሊያመው የህመም ስሜትም አልተሰማውም ሁሉንም ያዝናና ዋው የሚያስብል ምርጥ ምሽት አብረው አሳለፉ...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 1️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
...🖌ዋዉ የትላንትናው ምሽት ዛሬ ቀኑን ልዩ አርጎታል መቅደስማ ሌላ ሰው ሆናለች ገና ከእንቅልፏ ስትነቃ ፊቷ በሀሴት ያበራ ነበር ሁሉም ጓደኞቿ ጨራርሰው ወደክላስ ሲሄዱ እሷ እረጋ ብላ ለሳምንታት የረሳችውን መዋቢያዋን አንስታ ትቀባባ ጀመር ሲላት እየዘለለች ሲላት ብቻዋን እየሳቀች ደስታዋ ልክ አጥቶ ነበር።
......ልክ ከዶርም ስትወጣ ጌዲዮን አገኘችው ድጋሚ እንዳዲስ ተፈራሩ እሱም ኩስትር አለ እሷም እንደበፊቱ በመርበትበት ሰላም አደርክ ብላ ጠየቀችው እሱም ፈጣሪ ይመስገን ብሏት ወሬ ሳይጨምር መንገዱን ቀጠለ እሷም ይህን ቃሉን ስለነበር የናፈቀችው ደስታዋ ጨምሮ እየዘለለች ወደ ክፍል ሄደች አስተማሪው መምህር ያሬድ ነበረ ትንሽ ደቂቃዎችም ሆኖታል ትምርት ከተጀመረ መቅደስ ምንም ሳትል ቀጥታ ገባች ያሬድም እልህ ስለነበረበት እስካሁን የት ነበርሽ ብሎ ተቆጣት እሷም የምትለው ሲጠፋባት ከጌዲዮ ጋር ነበርኩ ልትል አስባ ገና ጌዲዮ የሚለው ቃል ካፏ ሳይወጣ ያሬድ በንዴት ጌዲዮ ጌዲዮ ታዲያ ምን ይጠበስ የሚያዋጣሽ ትምርቱ ነው ያ በሽተኛ ነው ብሎ ጮኸባት ባንዴ ደስታዋን ከፊቷ አጠፋው።
......መቅደስም ይቅርታ ቲቸር መናገር ካለብህ እኔን ተናገረኝ በተረፈ ጌዲን እንድትናገረው አልፈቅድልህም ብላ መሬቱን እየደበደበች ሄዳ ወንበሯ ላይ ቁጭ አለች
........ዮናስ ጌዲን ማስፈራራት ፈልጎ ስለነበር ከጓደኞቹ ጋር መንገዱ ላይ ቆሞ ጠበቀው አጠገባቸውም ሲደርስ ና አለው ጌዲዮም አንገት እንደደፋ እኔን ነው አላቸው በተኮሳተረ ድምፅ አዎ አንተን ነው ና ጌዲዮም ያለምንም ፍራቻ አጠገባቸው ሄዶ ምን ፈለጋችሁ አላቸው ዮናስም ከት ብሎ ስቆ ወገኛ ከንዳንተ አይነቱ በሽተኝ ደሞ ምን ይፈለጋል ሲለው ጌዲያ ቆጣ ብሎ ታዲያ ለምን አስቆማችሁኝ አለ ዮናስም ላስጠነቅቅህ ስማ ከመቅደስ ስር ስር እላለሁ ብትል እደፋሀለሁ ታቃለህ እደፋሀለሁ ጌዲዮም በፌዝ መልክ እያየው ውይ ታዲያ ብትንቀኝም ከኔ ትልቅ ነገር ፈልገሀል እኔም አንድ ነገር ልንገርህ ጀግና ፊትለፊት ተዋግቶ ድል ያደርጋል እንጂ እንዳንተ ኋላ ኋላ ብሎ አይደለም እሺ መቅደስን የግልህ ማድረግ ካለብህ በፍቅር ነው የሚያስፈልጓትን የምትፈልጋቸውን ነገሮች በማጥፋት አይደለም እንደው በዚ መንገድ የግልህ ብታረጋት እንኳን መሰረት የሌለው ቤት አይቆምም እና እውነቱን ያወቀች ቀን የውሸት ማንነትህ ገደል ይዞህ እንደሚገባ አትጠራጠር አለው ዮናስም ደሙ ፈልቶ ስማ አንተ ደነዝ እንድትመክረኝ ሳይሆን እንድትጠነቀቅ ነው ያስቆምኩህ አሻፈረኝ ካልክ ግን በነብስህ ፍረድ ሲለው ጌዲዮ ከበፊቱም በላይ በመኮሳተር
........አንተ የፍቅር ትርጉሙ አልገባህም መኖር ካለብኝ ለፍቅር ነው ፍቅር ማለት ደግሞ ስለሌላ መኖር ነው አየህ በዚች ምድር ላይ ለሁለት ነገሮች ነው የምኖረው አንድ ለናቴ ዛሬ ደግሞ ለሁለተኛዋ እናቴ ለፍቅሬ በነዚ ሁለት ነገሮች ለመጣብኝ ከነብስ በላይም ካለ አሳልፌ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ዙሪያ ጥምጥም ከምትሄድ ፊትለፊት ሞክረኝ ደግሞ አትርሳ መቅዲ የማታውቃቸው ያንተ ድብቅ ሚስጥሮች እንዳሉ እናም ወንድም ከኔ በላይ አንተ ፍራ እሺ ብሎት እየተውረገረገ መንገዱን ቀጠለ ዮናስ በጓደኞቹ ፊት አፈረ እነሱም እሱን ለማባበል ይሄ በሽተኛ ፋራ ቆይ እንሰራለታለን ይሄ ገገማ እያሉ የስድብ ናዳ አወረዱበት።
.......አሁን ጌዲዮ አንድ ነገር ገባው መቅደስና ዮናስ የፍቅር ግንኙነት እንደሌላቸው የባለፈው ውሳኔውም ትክክል እንዳልነበር ተረዳ ግን አሁንም መቅደስ እሱን እንደምታፈቅረው ማወቅ ቢፈልግም ግልፅ አልሆነለትም
.......መቅደስና ጓደኞቿ ከመመገቢያ ክፍል እየወጡ ሳለ ጌዲ ደግሞ ገና ሊበላ እየገባ ፊትለፊት ተገናኙ መቼስ ጅብ በቀደደው ውሻ ይሾልክበታል ነው ውሻ በቀደደው ጅብ ይሾልክበታል የሚባለው ብቻ የሆነው ሆኖ እንደተገናኙ ብርሀን ሀይ ጌዲ ሰላም ነው አለችው ከዛም መቅደስ በከፈተችው መንገድ ሁሉም ሰላም አሉት የሚሄድበትን እያዩ የሚያወሩት ሲያጡ የት እየሄድክ ነው ብለው ጠየቁት እሱም ምሳ ልበላ አላቸው እሺ መልካም ምሳ ብለውት ከመለያየታቸው ጌዲዮ አዙሮ ጣለው መቅደስ እየሮጠች ወደሱ መጣች በጣም እየተወራጨ ነበር እንደምንም ብላ አረጋጋችው ከግማሽ ሰአት ቡሀላ እግሮቿ ላይ አስተኝታ ባፍ ባፍንጫው የደፈቀውን አረፋ በገዛ ልብሷ እየጠረገችለት ነቃ ገና ከመንቃቱም አናግሯት የማያውቀውን ከግሮቿ ሳይነሳ መቅዲ አላት እሷም እራሱን እየደባበሰች ወዬ ጌዲ አለችው
የእውነት ፈተንሽኝ ታውቂያለሽ ከዚ በፊት ወድቄ ስነቃ አለሜ ጨልማ ሂወት ጠቁራብኝ ተስፋዬ ተሟጦ ነበር አሁን ግን እንዲህ ሲላት ታይቶ የማይታወቅ ምንም እንኳ ባይስቅ ፈገግታ ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር አሁን ግን ምን አለችው መልሱን ለመስማት ጓጉታ ባንቺ የተነሳ ጭራሽ መውደቄን ወደድኩ ምን ብዬ እንደማመሰግንሽ አላቅም ለውለታሽ የሚመጥን ቃል የለኝም እውነት ግን እግዚአብሔር አንቺን ሲፈጥር ብዙ ጥበቡን አፍስሶብሻል አላት
መቅደስ ይህንን የተስፋ ቃል በመስማቷ ቀኑን ሙሉ በደስታ ጮቤ ስትረግጥ ዋለች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 2️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
...🖌መቅደስ ምንም እንኳ ከጌዲዮ ፍቅር ባትጀምርም አሁን ካይኗ ስር በመሆኑ ደስታዋ ተመልሷል ጌዲዮም እንደዛው......
.......አሁን ወሩ የፈተና ነው ጎበዝ ተማሪዎች በጥናት ተጠምደዋል እንደወይንሸት ያሉት ደግሞ እንዴት አስተማሪዎቻቸውን ማማለል እንዳለባቸው ብቻ ሁሉም በየፊናው እየተዘጋጁ ነው።
...............ጌዲዮም እንደለመደው ጫካ በመሄድ ማጥናቱን ተያይዞታል በነገራችን ላይ መቅደስ አሁንም ሳያያት ትከተለዋለች እናም ዛሬም ሳያያት ከኋላ ኋላው ሄዳ ከቅርብ እርቀት ሆና እያየችው ነው ግን ይህን የምታደርገው አንድ ቀን በህልሟ ጫካ ውስጥ ወድቆ አውሬዎች ሊበሉት ሲሉ በላብ ተጠምቃ ከንቅልፏ ባና ከዛ ወዲ እውን እንዳይሆን እየፈራች ከግቢ ሲወጣ አብራው ትወጣለች............
........እናም ብዙ ቆየ በተስፋ ስትጠባበቀው ቆይታ የሆነ ሰአት ላይ በጫካው የጦጣዎች ትርኢት ተመለከተች ከዛም ቀልቧን ሳቡት ከዛፍ ዛፍ ሲዘሉ ሲቦርቁ ስታይ ለግዜው ጌዲን ለጥናቱ ተወችው ከዛም ስልኳን አውጥታ መቅረፅ ጀመረች ጌዲዮ በዛን ሰአት ጥናቱን ጨርሶ መፅሀፎቹን ሰብስቦ ተነሳ ተነስቶ እንደዞረም መቅደስን አያት ብታየው በተደበቀች ነበር ግን አላየችውም በጦጣዎቹ ሁኔታ እየሳቀች ካሜራዋን ደቅና እየቀረፀች ነው
ጌዲዮ የልቡን ጀግና በተመስጦ እያደነቀ ለደቂቃዎች ሲያያት ቆይቶ ፊትለፊቷ ሄደ ከዛም እረጋ ባለ ድምፅ መቅዲ አላት መቅደስ በድንጋጤ ጮሀ አውቃ ፌንት እንደነቀለ ሰው እጁ ላይ ወደቀች እሱም እውነቷን መስሎት ሊያነቃት ብዙ ጣረ ከዛም የያዘውን ሀይላንድ ውሀ እላይዋ ላይ ደፋው ሆን ብላ እያለከለከች ነቃች
................እሱም ምነው ምን ሆንሽ አላት እሷም እንዴ አስደነገጥከኝ እኮ አለችው በርግጥ ከሚባለው በላይ ደንግጣለች ከዛም እንደማያቅ ሆና ቆይ እዚህ ምን ታደርጋለህ አለችው ጌዲም እኔማ በብዛት እዚህ ነው የማጠናው ይልቅ አንቺ እዚህ አስፈሪ ጫካ ብቻሽን ምን ታደርጊያለሽ አላት መቅደስም አምጣ አምጣ ምን መሰለህ የሆነ የፎቶ ኤግዚቢሽን አለብኝ እናም ለዛ ነው ስትለው ተቆጣት እንዴ ቢሆንስ ቢያንስ ከጓደኞችሽ ጋር አትመጪም ቆይ እኔ እንዳገኘሁሽ አውሬ ቢያጋጥምሽስ በሁኔታው ደስ አላት በርግጥ ማንም ቢሆን የሚያፈቅረው ሰው ሲጨነቅለት ያስደስተዋል መቅደስም ያ ደስታ ነው የተሰማት ቀጥላም እሱን ጠየቀችው እሱም ከልጅነቱ ጀምሮ የለመደው እንደሆነ ነግሯት መንገድ ጀመሩ
መቅደስም ልክ እንዳዲስ ሰው መወለጋገድ ጀመረች ጭራሽ መሄድ ያቃታትም መሰለች ጌዲዮ በጆቹ ደገፋት እሷም ይህንን ስለነበር የፈለገችው ፈገግ አለች ግቢም ሲገቡ እንደደገፋት ነበር ነገሩ ብዙውን ተማሪ አስገርሟል።
.......ዶርም ስትገባ እነ ሰአዳ ቆይ አብረን እናጠናለን ተባብለን የለም እንዴ ምነው ቆየሽ አሏት እሷም ከነሱ ምንም ስለማትደብቅ ነገረቻቸው ከዛም ጥናት ጀመሩ ወይንሸት ግን ማጥናት አልፈለገችም ቢሆንም መቅደስ በግድ ያዘቻት ከዛም በጋራ የሚያጠኑትን ሲጨርሱ በግል እንዲሰሩ ጥያቄ ሰጠቻቸውና ወይንሸትን ብቻዋን ማስጠናት ጀመረች ግን ምንም ሊገባት አልቻለም ሀሳቧ ሁሉ አብሯት የለም መቅደስ ተበሳጨች ብርሀን በሁኔታቸው እየሳቀች መቅዲ አትልፊ ወይንሸትን እኮ እንኳን አንቺ ጌዲዮ ቢያስጠናትም አይገባትም ስትል ወይንሸት በንዴት ትራስ ወረወረችባት።
.......መቅደስ ብርሀን እንደዛ ስትል አንድ ሀሳብ መጣላት...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...
...............በንጋታውም ልጠይቀው ከክፍል እስኪወጣ ምንገድ ላይ ጠበቀችው ከዛም ሁሉም ተማሪ ወቶ ሲያልቅ መጨረሻ ላይ አቀርቅሮ መጣ መቅደስ ምን እንደምትለው እየተለማመደች ነበር ግን እሱን ስታየው ሁሉም ጠፋባት እንደደረሰም አያትና ሰላም ሊላት ተጠጋ እሷ ግን ደንግጣ ስለነበረ አንደበቷ ተያይዞ እጇ እየተንቀጠቀጠ ለሰላምታ መዘርጋት አቃተው ጌዲዮም ምን ሆነሽ ነው አላት እሷም በመጠየቅና ባለመጠየቅ መሀል ሆና አይ ምንም ስትለው የሆንሽውማ ነገር አለ ለምን አትነግሪኝም አላት እሷም እእእ ጎበዝ ተማሪ አይደለክ አለችው እሱም ማለት አላት ማለትማ የፈተና ዝግጅት ስለከበደኝ እንድታስጠናኝ ነው አለችው ቁና እየተነፈሰች ጌዲዮም እንዴ እኔ አንቺን ቀለሜ አይደለሽ እንዴ አላት መቅደስም ካልተመቸህ ችግር የለውም ስትለው አረ ለዛ አይደለም ማንም አስጠናኝ ብሎኝ ስለማያቅ ገርመሽኝ ነው እንጂ ማስጠናቱን አለመፈለግ አይደለም ደስ ካለሽ ከትምህርት ሰአቴ ውጪ ማጥናት ስትፈልጊ ሁሌም ጥሪኝ ይመቸኛል አላት ጥያቄዋን በፍጥነት ስለተቀበላት መቅደስ ደስ አላት።...............
.........ይሄኔ ዮናስ ካፌ ቁጭ ብሎ እያያቸው ነበር በሚያየው ነገር ተበሳጨ የውርርዱ የመጨረሻ ወር ላይ ነው ያለው ግን ይበልጥ ያሳሰበው የውርርዱን ብር ማጣቱ ሳይሆን በማንም ተሸንፎ የማያውቀው ዮናስ ባንድ ሴት ክብሩ ሲነካ መሸነፉን ግቢው ሲያወራ ገና ካሁኑ ታይቶት ነው ከዛም የፍቅር ጥያቄ ሊያቀርብላት አሰበ።
................ጌዲም መቅደስን ይዟት ላይብረሪ ገቡና መፃህፍትን ይዘው ወጡ ከዛም ቀጥታ ወደጫካ ሄዱ እዛም አጥንተው ለነገሩ ምን አጥንተው እሱ ለፈለፈ እንጂ መቅደስ አንዱንም አልሰማችውን ከዛም እንደጨረሱ እንሂድ ሲላት አይ ለምን ትንሽ አንጫወትም ቦታው ደስ ይላል አለችው ደስ ካለሽ እሺ አላት ጌዲዮ ከማንም ጋር አፍ ለአፍ ገጥሞ አውርቶ ስለማያውቅ በመሀከላቸው ዝምታ ሰፈነ ከዛም መቅደስ እኔ እምለው እስኪ ታሪክህን አጫውተኝ ብላ ጠየቀችው እሱም መጀመሪያ አንቺ ንገሪኝና እነግርሻለሁ አላት ትንሽ አንገራግራ ቀጠለች.......
......ተወልጄ ያደኩት አ.አ ለገሀር የሚባለው ሰፈር ነው የልጅነት ጊዜዬ እንደማንኛውም ህፃን ደስ የሚል ነበረ ሁለት ወንድምና አንድ እህት አሉኝ የቤታችን የመጨረሻ ልጅ እኔ ነኝ ሁሉም ታላቆቼ ናቸው አባቴ የአ.አ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነው እናቴ ደግሞ ከፍተኛ የመንግስት ቢሮ ነው የምትሰራው ሁለቱም የተዋወቁት አባዬ መምህር እማዬ ተማሪ ሆነው ነበር አሁን ላይ ጥሩና ስኬታማ ቤተሰብ አለን ሁሉም ወንድምና እህቴ የማዕረግ ተመራቂ ናቸው እኔም ጠንካራ እንድሆን ዘውትር ያበረታቱኛል እንደውም የውጪ እድል መቶልኝ አልፈልግም ብዬ ነው ዛሬ ላይ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ትምህርቴን የምማረው ምክንያቱም ሳይማር ያስተማረኝን ህብረተሰብ እኔም ወግ ደርሶኝ ማገልገል እፈልጋለሁ ይህንን ሳደርግ ከቤት አንድም ተቃዋሚ አልገጠመኝም በቃ ይኸው አሁንም እየተማርኩ ነው እልሀለሁ አለችው ጌዲዮም ዋዉ የሚያስቀና ቤተሰብ ውስጥ ነው የበቀልሽው አላት መቅደስም አመሰግናለሁ ስትለው አረ ምንም አይደል ደግሞ ተምረሽ አንቺም ጥሩ ቦታ እንደምትደርሺ አልጠራጠርም አላት ................
.........ከዛም የሱን እንዲነግራት ስጠይቀው ነገ ዲያሪውን አገላብጦ መጥቶ እንደሚነግራት ቃል ገብቶላት ተነስተው ወደግቢ ተመለሱ .........
ልክ እንደተለያዩም ዮናስ አስቆማት እሷም ሰላም ካለችው ቡሀላ በጣም ለጥብቅ ጉዳይ እፈልግሻለሁ አላት እሷም ምን እንደሆነ ስጠይቀው ማታ እራት እየበላን እነግርሻለሁ ብሎ ትልቅ ሆቴል ከምሽቱ ሁለት ሰአት እንድትመጣ ጋበዛት በፍፁም እንዳትቀርም አስጠነቀቃት እሷም የማትረሳው ውለታው አስገድዷት ውስጧ
ቢደነግጥም ፍቃደኛ ሆነች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
➕➡️
➕➡️
➕➡️
➕➡️
➕➡️
➕➡️
አሁኑኑ ያናግሩን
@ethio3254
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 4️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
........እሱም ከፍቶ ሲያነበው ስማ አንተ በሽተኛ ነግሬህ ነበረ መቅደስ የኔ ናት ለማንኛውም እንድታምነኝ ስል ዛሬ ምሽት የፍቅር ጥያቄ አቀርብላታለሁ ከቻልክ መጥተክ መታደም ትችላለህ ዮናስ ይላል እሱም ወሬኛ ብሎ ደብዳቤውን ቀደደና ወደዶርም ሊመለስ ሲል መቅደስን በዛ በጨለማ ንግስት መስላ ከግቢ ስትወጣ ከሩቅ አያት ጌዲዮ ማመን አቃተው ባይፈልግም ፍቅር ነውና ተከትሎ መጨረሻቸውን ሊያይ ከኋላዋ ተከተላት.........
.........መቅደስ ባላት ሰአት ሆቴሉ ገባች ባይኗም ብዙ ወንበሮች ላይ ፈለገችው የለም ከዛም አንድ ወንበር ይዛ ተቀመጠች አስተናጋጅ ፊትለፊቷ መጥቶ ምን ልታዘዝ አላት እሷም ሰው እጠብቃለሁ የሚል መልስ ሰጠችው ከቆይታዎች ቡሀላ ሌላ አስተናጋጅ መጣችና መቅደስ አለቻት እሷም አዎ ነኝ ኦኬ ተከተይኝ አለቻት መቅደስም ግራ በመጋባት ወዴት ስትላት ዮናስ የተባለ ደንበኛችን ነው ይዘሻት ነይ ያለኝ አለቻት እሺ ብላ ተከተለቻት ሁለተኛ ፎቅም እንደደረሱ ስለደረስን አይንሽን ላስርሽ ነው አለቻት መቅደስ ይበልጥ ግራ በመጋባት እኮ ለምን ስትል አርጊ የተባልኩትን ነው ብላ አይኖቿን አስራ ግን ግለጭ ሳትባይ ምንም እንዳታዪ አደራ ብላት የፎቁ በረንዳ ላይ አድርሳት ተመለሰች ዮናስም ከጥቂት ደቂቃ ቡሀላ ግለጪ አላት መቅደስ የታሰረችበትን ጨርቅ ካይኖቿ ስታነሳ የምታየው ነገር ህልም መሰላት አበባ ተጎዝጉዞ ምሽቱ በሻማዎች ደምቆ አለ የተባለ መጠጥ ቀርቦ ዮናስ አንዲት ቀይ ፅጌሬዳ ይዞ ፊቷ ተንበርክኳል
.......በዛ ሰአት ጌዲዮ ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት ውስጥ ህኖም እያያቸው ነበር.....
መቅደስ ግራ ገባት ላንድም ቀን ዮናስን በዚህ መልኩ አስባው አታውቅም ዮናስ ምን እየሆንክ ነው አለችው እሱም ክሽን አድርጎ በሚያወራት አስመሳይ ግን ጣፋጭ በሆነ አንደበቱ መቅዲ ካየሁሽ ቀን ጀምሮ አፍቅሬሻለሁ የልቤ እመቤት አድርጌ ሾሜሻለሁ መቅዲ አንቺ ከማንም በላይ ለኔ ልዩ ነሽ እስከ ሂወቴ ፍፃሜ ያንቺ ብቻ ልሁን ፍቀጂልኝና የፍቅርሽ ባሪያ ልሁን አያለለ ዜማ ቢጨመርበት አንድ ክሊፕ የሚሰራውን ዜማውን አፈሰሰባት ከዛም መቅደስ ምን እንደምትል እንኳን ግራ ገብቷት እየውልክ ዮናስ ይሄን ላረግ አልችልም ብላ ከተንበረከከበት እጆቹን ይዛ አስነሳችው ዮናስ ደሙ ፈላ ግን ለምን አላት እየውልክ እኔ የኔ የምለው የማፈቅረው ሰው አለኝ አንተን ወንድሜ እንጂ ፍቅረኛዬ ላደርግህ አልችልም ዮኒ የእውነት በጣም አዝናለሁ እኔ ያንተ ልሆን አልችልም በቃ ውለታውን በዚ መልኩ ልትከፍለው እንደማትችል ነግራ በጣም አስተዛዝናው ተመልሳ ሄደች ልክ እሷ እንደተመለሰች
ጌዲዮ ፊትለፊቱ ሄደና ስማ መቅደስን እንኳን በውንህ በህልምህም የግልክ አታደርጋትም የእውነት ግን በራሴ አፈርኩ አንተን አምኜ እዚህ ድረስ መልፋት አልነበረብኝም ይህንን ትርኪ ሚርኪህን በለመድካቸው ላይ ግን ለዚህ ሁሉ ወጪ ስንት ብር ፈጀብህ እያለ የዮናስን ንዴት በእጥፍ ጨምሮ ሄደ ዮናስ መጠጡን እየገለበጠ በፍቅር እንቢ ካልሽ የበቀል ልቡን አሳበጠው........
...........ከዛም በንጋታው ጌዲዮና መቅደስ ተያይዘው ለጥናት ወደጫካው ሄዱ አጥንተውም እንደጨረሱ ታሪኩ እንዲነግራት አስገደደችው እሱም
.....እኔ ምንም ሌላ ታሪክ የለኝም ታሪኬ አንድ ግን ብዙዋ እናቴ ናት ተወልጄ ያደኩት በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ጃማ የሚባለው ገጠራማ ስፍራ ነው አባቴን አላውቀውም በልጅነቴ ነው የሞተው ከኔ በፊት እናቴ ሶስት ልጆች ሞተውባታል እኔንም ስለት ተስላ ነው ያደኩላት ግን ባድግም የአራት አመት ልጅ እያለሁ በየቦታው ይጥለኝ ጀመር እማ በሀዘን ላይ ሀዘን ተጨመረባት አስበሽዋል ሶስት ልጆቿን ባሏን ያጣች ሴት መከራ በዛላይ እኔም በሽተኛ መሆኔ አላፊው አግዳሚው አላስቀምጥ አላት ያባቴ ዘመዶችማ ለነገሩ እሷ ስላለችኝ እንጂ እንኳን ያባቴን የራሷንም ዘመዶች አላቃቸውም ምክንያቱም የሷ ቤተሰቦች እንድታገባ ሲለምኗት አሻፈረኝ ካገባሁ ልጄ ይጎዳብኛል ስላለች እስከዛሬ ድረስ ማንም የሚፈልጋት የሚጠይቃት የለም አየሽ እናቴ ለኔ ስትል ስንት ነገር እንዳጣች አባ ሲሞት ቆንጆ ወጣት ነበረች ብታገባ ኖሮ እንደ ወንድ ሞፈርና ቀንበር አንዴ ከጓሮ አንዴ ከጓዳ ባልተንከራተተች ነበር ግን ለኔ ስትል ሁለት መልክ አወጣች መከራ ትንሽ ነው ብዙ ብዙ ነገር አየች
እኔ እናቴ የማስደስታት ቀንበር ይዤ ስከተላት አልነበረም ጓሮ ሄጄ ስቆፍር እንጨት ስሰብርላት አይደለም እውነተኛው የናቴ ደስታ ደብተር እስኪቢርቶዬን አንግቤ ለትምርት ስወጣ ነው ብዙ ጊዜ ትምርት አልማርም እላታለሁ እሷ ግን ምክንያቴን ስለምታውቅ ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶም እንዳላየ ሁን ትለኛለች እዚህ ለመድረሴ የናቴ ትልቁ ምክሯ ይህ ነበር የልጆች ጨዋታን እየተጫወትኩ ሳይሆን እያየሁ እየዘመርኩ ሳይሆን እየሰማሁ ነው ያደኩት ማንም ልጅ ከኔ መጫወት ቢፈልግ እንኳን አይችልም ምክንያቱም የትኛውም እናት አባት አይፈቅድም መቅዲ እኔኮ ከሰው ጋር ስሆን አይደለም የሚያመኝ ግን ማንም አይረዳኝም ብሎ ለብዙ ግዜ ያመቀው ቁስል ስለሆነ ዛሬ ግን ፈነዳና አመመው ሳይጨርስላት እንባው ቀደመው አስተዳደጉ በሙላ አይኑ ላይ ተስሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ መቅደስም አንጀቷን በልቶት አብራው አለቀሰች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...🖌ጌዲዮ እንደምንም እንባውን ጠራርጎ ታሪኩን ቀጠለላት አየሽ እኔን ማንም ከሰው ተራ ቆጥሮኝ ስላላደኩ ዛሬም ሰው እፈራለሁ ብቸኝነቴን እመርጣለሁ ዝምታዬን እወደዋለሁ ለኔ የመኖር ምክንያቴ እናቴ ናት እሷ ናት ታሪኬ እንዳባት ሞፈር ተሸክማ እንደህት መክራ እንደወንድም ጋሻ ሆናኝ ከናት በላይ ብዙ ሆና ያኖረችኝ ታሪኬ እናቴ ብቻናት አየሽ መቅደስ አንቺ እኔን ከመደገፍሽ በፊት ከናቴ በቀር ማንም ጎንበስ ብሎ አንስትትምኝ አያውቅም ለዚም ነው አንቺን እንደናቴ ያየሁሽ አላት ሳያውቀው ለሷ ያለውን ስሜት ነገራት መቅደስ እጆቿን ከጉንጩ ሰዳ እንባዉን ጠረገችለት
ለብዙ ጊዜ ፍቅራቸውን እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ሲጨነቁ የነበሩት ጥንዶች ዛሬ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አንድ ሜዳ ላይ ተገናኙ በርግጥም እውነተኛ ፍቅር የቃላት ድርደራ አይፈልግም ለካ እውነተኛ ፍቅር ባይን ጥቅሻ ብቻ ያግባባል በቃ በዝምታ ተያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌዲዮ ከንፈሩን ከሴት ከንፈር አገናኘው መቅደስ ለብዙ ጊዜ የናፈቀችውን ጌዲን በቅፎቿ አስገባችው በቃ ያለምንም አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ያለማንም አጃቢ በከንፈራቸው ቃልኪዳን አሰሩ
የፍቅር ድግሳቸው ትተጠነሰሰ ማንም ባይገምትም የጌዲዮና የመቅደስ ፍቅር እውን ሆነ የዛኑ ቀን ነበር ግቢው ይህን እውነት የሰማው ዮናስ ጌሙን ባደባባይ ተሸነፈ መቅደስ ከሱ ቁንጅና ይልቅ የጌዲዮ መልካምነት አሸነፋት ከዮናስ ማስመሰል የጌዲዮ ፍቅር በለጠባት የውጭ ማንነቱን ሳይሆን በውስጥ መልካም ስብእናው ባደባባይ የጌዲዮ ነኝ አለች
ዮናስ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አይነት ጌም ሲሸነፍ ከፍተኛ ገንዘብና እሱ የሚያምንበትን ክብሩን አጣ የመጨረሻ እርምጃ ያለውን በቀል በውስጡ አበቀለ በክፋትም ሊጥላት አሰበ
ጌዲና መቅዲ ግን ግቢውን ያስቀና ፍቅር ጀመሩ አይቶ ካይን ያውጣችሁ የማይል ምቀኛ ብቻ ነው በፍቅራቸው አልተደነኩም የሚል ካለ ውሸታም ነው...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...🖌ጌዲና መቅዲ ባሁን ሰአት ለደቂቃ እንኳን መለያየት ይከብዳቸዋል በቀን ቀን ፍቅራቸው እየጨመረ አማላይ ጥንዶች ሆነዋል
ጌዲም በብዙ ነገር ተቀይሯል አሁን ከሰው ጋር ይውላል ከክፍል ጓደኞቹም ጋር ይጮታል አብሮ ይበላል አብሮ ይጠጣል በመዘነጥም ቢሆን የግቢውን ቆንጆዎች አስንቋል ግን ለዚህ ሁሉ መሆን መቅደስ በፍቅሯ ቃል አስገብታው ነው
አረ አሁንማ ከማድነቅ አልፈው ብዙ ሴቶች ለፍቅር እየተመኙት ነው ጌዲ ግን በፊቱ ፋሽን ሾ ሲሰሩ ቢውሉም ዘወር ብሎም አያያቸውም በርግጥም ትክክል ነው የፍቅር ጀግና የሚባለው መቶ ያሰለፈ ሳይሆ ከመቶዎቹ ላንዷ ብቻ መኖር ሲችል ነው መቅደስም ብትሆን ለማንም ቦታ የላትም ግን አንዳንድ ሰዎች ግርም ይሉኛል ወድቆ እያዩት አይጠቅምም ብለው ያላነሱት ነገር ሌላ ሰው አንስቶ ሲያዩ ለምን ቅጥል እርር እንደሚሉ አይገባኝም......
ጌዲዮ ካፌ ቁጭ ብሎ ሻይ እየጠጣ መቅደስ ከክፍል እስክትወጣ እየጠበቃት ነው አንዲትም ልጅ መጥታ አጠገቡ ተቀመጠች ጌዲዮም ይቅርታ የኔ እህት ወንበሩ ተይዟል አላት እሷም በተሞላቀቀ አፏ እኔ ሰው አይደለሁ ስትለው እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ፍቅረኛዬን እየጠበኳት ነው ስለዚህ ቦታ ቀይሪ ብሎ ሳይጨርስ ምን መቅደስን አይደል ሶ እኔ ከሷ በላይ ፍቅርን ልሰጥህ ዝግጁ ነኝ ብላ ጠረንቤዛው ላይ ያረፉትን እጆቹን ጭብጥ አርጋ ያዘችው መቅደስም እየመጣች ስለነበረ ፊትለፊት እያየቻት ነበር ጌዲዮ እጇን ከጁ አመናጭቆ አስለቀቃት በጥፊ ሳልልሽ ተነስተሽ ከፊቴ ጥፊ ብሎ ሲጮህባት ደንግጣ እየበረረች ሄደች መቅደስ ፊቷ በደስታ ተሞልቶ በፈገግታ ታጀበ እንደደረሰችም አቅፋ ሳመችውና ተቀመጠች ........
.........ጌዲዬ ዛሬ ላይብረሪ እናጥና ድብርብር ብሎኛል አለች መቅዲ ከደበረሽ ለምን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን አንመጣም አላት መቅደስም ደስ ይለኛል ነጠላዬን ላምጣና እኔዳለን አለችው።
ከግቢም ሲወጡ ዮናስ አያቸው ወዲያው ወይንሸት ጋር ደውሎ ጠራት ከዛም ይዟት ወጣ እሷም ዮኒ ምን ፈልገክ ነው እዚሁ ንገረኝ ካንድ ሰአት ቡሀላ መቅደስ አስጠናችኋለሁ ብላናለች ስትለው ዮናስ ዶማ አጠና አላጠና ያው ዶማ እኮ ነው አላት ወይንሸት ንቀቱ አናደዳት ውስጧ ገብቶ ነዘራት መልሳ ዶማ እያልከኝ ነው አለች እሱም ገብቶሻል አታድርቂኝ ሲላት አሁን ትርፍ ማውራትህን አቁመህ ምን እንደፈለክ ንገረኝ አለችው እሱም ቀለል አርጎ ወደማታ መቅደስን እኔ ጋር እንድታመጪያት ነው አላት ወይናም ዮናስ ውላችንን የጨረስን መሰለኝ የተሰጠኝን ግዳጅ ባግባቡ ተወጥቻለሁ ውርርዱን የተሸነፍከው በራስህ ድክመት ነው ታዲያ ምን ችግር አለው አዲስ ውል እንዋዋል ገንዘብም ቢሆን ከባለፈው በላይ እከፍልሻለሁ ሲላት ወይና ፊቷን አኮሳትራ
......በቃኝ ዮናስ በቃኝ አልፈልግም አለችው እሱም ምኑ ነው የበቃሽ አላት በቃ ከዚህ ቡሀላ ካንተ ጋር መስራት አልፈልግም አለችው እሱም እየቀለድሽ መሆን አለበት ዮናስ እየቀለድኩ አይደለም በሀጢያት መጨማለቅ መሮኛል አይገርምህም መቅደስን እስከዛሬ የበደልኳት እየቆጨኝ ነው ደግሜ ሌላ ስተት መስራት አልፈልግም አለችው ወይንሸት የተቀየረችበትም ምክንያት ትላንትና ተደውሎላት አባቷ በጣም እንደታመመ ሲነግሯት ስታለቅስ መቅደስ አየቻት ምን እንደሆነችም ስጠይቃት አባቷ መታመሙን ነገረቻት መቅደስም በየዋህ ልቧ አብራት እያለቀሰች እግዚአብሔር ይረዳቸዋል ደግሞ አንቺን የመሰለ መልካም ልጅ አላቸው አይደል አይዞሽ ፀልዪ እኔም እፀልይልሻለሁ ብላ ስታፅናናት በደሏ ተሰማት ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ውስጧ ሲረበሽ ነበር ለዚያም ነው ዛሬ ለዮናስ ገንዘብ አልፈልግም ያለችው ዮናስ ግን............
መቼም ጨክነሽ ባባትሽ ነብስ አትፈርጂም ሲላት ስማኝ ይኸው ካይስኩል ጀምሮ በነውር በሀጢያት በምሰበስበው ገንዘብ አሳከምኩት ግን ዳነ አልዳነም አየህ እግዚአብሔር ካላለ እኔ ስላልኩ ወይም ማንም ስላለ አባቴ አይሞትም ደግሞ ቆሽሼ ከማገኘው ገንዘብ ንፁ ፀሎቴ ይሻለኛል መቼም ከዚህ ቡሀላ ወደኋላ አትመልሰኝም መቅደስ ጥሩና ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ነው ያለችው ደግሜ ልበጠብጣት አልፈልግም ደግሞ የማላቅ አይምሰልህ ሆን ብለክ አንድ ዩኒቨርሲቲ እንዲደርሰን የጣ ድልድሉ ውስጥ እጅህን ያስገባኸው እኔ ካንተ ከማገኘው ጥቅም በላይ አንተ ከኔ የምታገኘው ጥቅም ስለሚበልጥ ነው ለፍቅር ብቀርብህም አንተ ግን ከየትም እንደተገኘ ገላ ተጫወትክብኝ መጫወትክም ሳያንስ አሳልፈህ ለሹገር ዳዲዎች ሸጥከኝ እኔ ከማገኘው መቶ ፕርሰንት ዘጠናውን አንተ እንደምትወስድ አውቃለሁ ግን አስሯ ፕርሰንት ላባቴ መኖር ምክንያት ስለመሰለችኝ የከተትከኝ ሀጢያት ውስጥ እንደተስማማኝ ሆኜ ኖርኩኝ በርግጥ የኔን ትክክለኛ ማንነት ማንም አያውቅም ግን ይሁን እስከዛሬ ያልሆንኩትን ሆኜ ብኖርም የኖርኩትም ላባቴ ቢሆንም ባርቴፊሻል ማንነቴ አባቴ ድኖ ከሚያዝንብኝ በትክክለኛው ማንነቴ የሆነውን ቢሆንም ወይና አባቷን እጅግ ከሚባለው በላይ ስለምትወደው እንባዋ እንደጎርፍ ወረደ
ዮናስም እንዳመረረች ሲረዳ ኦኬ እንደዛ ከሆነ መቅደስ ላይ ያረግሽውን ሁሉ አንድም ሳይቀረኝ እነግራታለሁ ይህ ወሬ ተማሪዎች አወቁ ማለት ሳምንት እንኳን እዚህ ግቢ አትማሪም እኔን እንደሆነ አንዴ ጠልታኛለች የሆነው ቢሆን ማንም ከቁብ አይቆጥረኝም አንቺን ግን ሲላት ሰውነቷን ድንጋጤ ወረረው ዮናስ አታደርገውም አለችው ከት ብሎ ሳቀባት ዮናስ እኮ ነኝ ጭካኔዬን ያኔ ካይስኩል ጀምሮ ከማንም በላይ ታውቂዋለሽ አላት
ወይንሸት ከመስማማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም እሺ ግን እንዴት ብዬ ለፍቅር ከመጠየቅክ በላይ ደጋግመክ ጌዲዮን እንድትጠላው ለማድረግ በመሞከርክ ላይኗ እንኳን ጠልታሀለች ታዲያ የት ምን ብዬ ነው የማመጣት አለችው
ለሱ አታስቢ ወክ እናርግ ብለሽ ውስጥ ውስጡን ትወስጂያታለሽ ከዛም እላይኛው ጫካ ጋር ስትደርሱ ሁለታችሁም የታፈናችሁ አስመስለን አንቺን በጎን ይወስዱሻል እሷ እጄ ትገባለች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 7️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226