የልብ ቋንቋ
223K subscribers
200 photos
11 videos
640 links
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀

⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE

Contact
Download Telegram
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
5️⃣
ልነግረዉ
ይገባል..." እያለች እያሰበች ኤዲ ከቤት ዉስጥ ሳትወጣ ቢኒ የግቢዉን በር ክፍት
ሲያደርግ ... ረዲም የበሩን ድምፅ ስሰማ ወደ በሩ ዘወር ስትል ረዲና ቢኒ አይን ለ አይን
ተገጣጠሙ፡፡ ይሄኔ ረዲ ድንብርብሯ ይጠፋል፡፡ ልቧ ከድቷት ወደ ቢኒ ሲከንፍ ታወቃት፡፡ የምትሆነዉን
አሳጥቷታል....ቢኒም ወደ ቤቱ ሊገባ ከበሩ ላይ ረዲን እያያት እርምጃዎቹን ጀምሯል፡፡
ረዲ ምን ይዋጣት ሩጣ ዘላ አንገቱ ላይ አትጠመጠምበት እሷ ኤዲ አይደለች፡፡  "ቢኒ
አግባኝ አፈቅረሃለሁ..." እንዳትለዉ የቤቱ በር ላይ ቆማ ሚስቱ ኤዲ ብሰማትስ...፡፡
ምድር ጠበበቻት ፣ መሬት ለሁለት ስንጥቅ ብላ ብትዉጣት ደስታዋ ወደር አልነበረዉም፡፡
ነገር ግን አሁንም ሌሊት ስታልመዉ ያደረችዉን "መንገር አለብኝ ብላ ወሰነች" ....
ቢኒም ወደሷ እየተጠጋ ነዉ፡፡ "ረዲ ደህና ዋልሽ" የቢኒ ድምፅ ነበር፡፡ ደነገጠች
አቤት ድምፁ መስረቅረቁ ሰላምታ የሰጣት ሳይሆን "እወድሻለሁ" ያላት ነበር የመሰላት፡፡
እሷም "ቢኒ ደህና ዋልክ አለችው...ቢኒ ዉድ ባለቤቱን እየተጣራ ወደ ዉስጥ እየገባ ነዉ፡፡ "ኤዲዬ የኔ ማር የት ነሽ?"
....ኤዲ  "ወዬ ቢኒ እዚህ ነኝኝ" እያለች ከእቃ ቤት ወጣች፡፡
...."ደህና ዋልሽልኝ የኔ ወድ..." ግንባሯን ሳም እያረጋት
..... "እንዴት ዋልክልኝ የኔ ፍቅር?".... "ፈጣሪ ይመስገን ደህና ውዬልሻለው! ማሬ ምን ነዉ? ዛሬ ስራ አልጨረስሽም እንዴ?"
......" አዎ  አልጨረስኩም ረድኤት መጣችና ስላንተ እያወራኋት ስራዬን እርስት አላረገዉም
መሰለህ ደሞ አረፍ በል ትንሽ ነዉ የቀረኝ መጣሁ..." ብላዉ ወደ ስራዋ ስትሄድ እሱም
ስራዉን ሊያግዛት እየተከተላት...
...."ቆይ እኔም ላግዝሽ አንቺን ብቻ ማን ልፊ አለሽ የኔ ዉድ" ብሏት ተከተላት.....
...ጊዜዎች እየነጎዱ ነዉ፡፡ ረድኤትም ፍቅሯን ዛሬ ነገ እነግረዋለሁ እያለች አንዴ ሳታገኘዉ
ሌላ ጊዜ ደሞ ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ስፈራ አንድ ወር አለፋት፡፡
አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቡ የሚባሉበት ቀን እየደረሰ ነዉ፡፡ እሷም ፍቅሯን አልነገረችዉም
ማንም ሳያዉቅላት ትወደዋለች ግልፅ ሳታወጣ ታፈቅረዋለች፡፡ አንድ ነገር ደሞ ጠርጥራለች
ኤዲ መዉለድ አትችልም የሚል...፡፡ አንድ ቀን እሷና ኤዲ እያወሩ...
.. ኤዲ "እኔና ቢኒ ከተጋባን አራት አመታችንን ይዘናል"  ስትላት ረዲም "እንዴት እስካሁን
ሳትወልዱ?" ብላ ጠየቀቻት
.."ፈጣሪ አልፈቀደዉም ልጅ አልሰጠንም" ብላ መልሳላት ነበር፡፡ በሃሳቧ የመጣላት ኤዲ
የመዉለድ ችግር እንዳለባት ነዉ፡፡ "ስለዚህ ለቢኒ እንደማፈቅረዉ ብነግረዉ ኤዲን ፈትቶ
ያገባኛል ወይም ሁለተኛ ሚስቱ ያደርገኛል..." ብላ አሰበች፡፡ እንደገና መለስ ብላ "ኧረረረ ሁለተኛስ ይቅርብኝ"
እያለች እራሷ ከሃሳቧ ጋር ትሟገታለች፡፡ ....በመሀል የኤዲ ስልክ ጠራ...፡፡ ስልኳ ላይ የተደወለዉ የማታዉቀዉ ቁጥር ነዉ "<< የፍቅሬ ደሴት ነህ በልቤ ዋሻ ውስጥ ገብተህ"> > የሚለው ነበር የስልኳ ጥሪ፡፡ ኤዲም ስልኩን አነሳችዉና
"ሄሎ"አለች
"ደህና ነሽ.." ጎርነን ያለ የወንድ ድምፅ ነበር፡፡ ኤዲ ስልክ ስታወራ ረድኤት የቤታቸዉ
በር ላይ ቁጭ ብላ መፅሃፍ እያነበበች ነበር፡፡
"ደህና ነኝ ማን ልበል?
"ትናንት ቢኒያም በዚህ ቁጥር ደዉሎልኝ ነበር፡፡ የሱ ስልክ አይደለም እንዴ?"ድምፁ
ማስፈራራቱ ኮስተር ያለ ነዉ፡፡
"አይይ የቢኒያም አይደለም ግን የሱን ስልክ ቁጥር ልሰጥህ እችላለሁ" በዚህ ግዜ ጠላት
እንደመጣባት የጥንቸል ጆሮ ረድኤት አንገቷን ሰገግ አድርጋ ... ማዳመጥ ጀመረች፡፡
"እባክሽን ተባበሪኝ ለስራ ጉዳይ ፈልጌዉ ነበር"
"እሺ ፃፍ 09.. " ስትል ረድኤት ከሰዉየዉ ቀድማ ቁጥሩን መፃፍ ተያያዘችዉ፡፡
" 09 21 79...."  ኤዲ ለደዋዩ ቁጥሩን ነግራ ስጨርስ ረድኤትም እኩል ነበር የፃፈችዉ፡፡
.
ረድኤት ምንም ጊዜ ሳታጠፋ ለቢኒ መልዕክት ፃፈች ..."ቢኒ ሰላም ነው:: እንዴት ነህ ካየሁህ....




 ይ
     ቀ
         ጥ
                ላ
                      ል

🔻ክፍል6️⃣   ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
6️⃣



."ቢኒ ሰላም ነው:: እንዴት ነህ ካየሁህ
ጊዜ ጀምሮ በጣም ነዉ ያፈቀርኩህ!" ብላ ከፃፈች ቡኃላ send  የሚለዉን ተጫነችዉ፡፡
አቤት ድፍረቷ ...ለራሷም አስገርሟታል፡፡ የወራት ሸክሟን ያራገፈች መሰላት፡፡
አሁን ያስጨነቃት የሱ ምላሽ ምን እንደሚሆን ነዉ፡፡
ነገር ግን መልዕክቱ አልደረሰዉም.....

         አሁን ያስጨነቃት የሱ ምላሽ ምን እንደሚሆን ነዉ፡፡ነገር ግን መልዕክቱ አልደረሰዉም"Dear Customer, your balance is insufficient
for this service. Please recharge your account. ethio telecom"  ከቤት ወጣ...... የሚል
ሜሴጅ ስልኳ ላይ ገባ፡፡ ለካስ ስልኳ መልዕክት ሊያስልክ የሚችል ባላንስ አልነበረዉም፡፡
ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ ዉስጥ እየሮጠች ገባች፡፡
"እማዬ ስልክሽ የት ነዉ?" ብላ እማማ በለጡን ጠየቀቻቸዉ፡፡ "እንቺ..." ብለዉ እናቷ
ስልካቸዉን አቃበሏት፡፡ ወደነበረችበት ቦታ ተመልሳ ተቀመጠችና መልዕክቱን መፃፍ ጀመረች " ሰላም ነው ቢኒ በጣም አፈቅርሃለሁ!"  ከቤት ወጣ...... አይ...አለችና መልእክቱን
አጠፋችዉና ሌላ መልዕክት ፃፈች "ሰላም ነው፡፡ ቢኒ ካየሁህ ጊዜ ጀምሮ ላንተ ያለኝ
ስሜት ልዩ ነዉ፡፡ ሳልወድህ አልቀረሁም!" ብላ ፃፈች፡፡ በማታዉቀዉ ሃይል ተገፍታ እጇ
እስኪከዳት ድረስ send የሚለዉን ነካችዉ፡፡ እፎይታ ተሰማት ከማሜ "እሺ" እንጂ ሌላ
መልዕክትን አጠብቅም፡፡
ምናልባት የሱ መልስ እምቢታ ቢሆን ብላ ማሰብም አልፈለገችም፡፡
.... መልዕክቱ ማሜ ስልክ ላይ ገባ "ጢጥ ጢጥ" የሚለዉን የሞባይሉን የመልዕክት ድምፅ
ሲሰማ ስልኩን ከኪሱ አወጣ... የመልዕክቱ ላኪ ... እማማ በለጡ ይላል...ፈገግ አለ፡፡
ደንገጥም አለ ፡፡ "ኤዲ ምን ሆና ነዉ?"  ከቤት ወጣ...... "አመማት እንዴ?" "ምን ብለዉ ልከዉ ይሆን?" በሚል
ጥያቄ ራሱን አፋጠጠ፡፡ ሜሴጁን ሲከፍት ግን ያልገመተዉና ያላሰበዉ ነገር፡፡....መልዕክቱን እንዳነበበ ሰዉነቱን የማያዉቀዉ ስሜት ተሰማዉ፡፡ ምክንያቱም...ቢኒ
ከኤዲ ዉጭ ማንም ያፈቅረኛል ብሎ አስቦ አያዉቅም ነበር፡፡ ደግሞም ማንም እወድሃለሁ
ብሎት አያዉቅም፡፡ ኤዲ እንኳን እንደምታፈቅረዉ የነገረችዉ በተጋቡ በሰባተኛ ወራቸዉ
ነበር፡፡ እስከዚያ ድረስ እሱ ብቻ ነበር እወድሻለሁ፤ አፈቅርሻለሁ ሲላት የነበረዉ፡፡
...... ዛሬ ግን ቢኒ በሌላ ሰዉ "ሳልወድህ አልቀረሁም" የሚል መልዕክት ደርሶታል፡፡
መልዕክቱን ማን እንደላከዉ ብዙ ሳያስብ ነበር የገመተዉ "ረድኤት"  ከቤት ወጣ...... አለ በዉስጡ... ድሮም
አስተያየቷ አላማረዉም ነበር፡፡ እሷ ጋር አይን ለአይን በተገጣጠመበት ጊዜ ሁሉ ከረድኤት
አይኖች የፍቅር አስተያየት አስተዉሏል፡፡ በተለይ ከስራ በሚመለስበት ወቅት ሚስቱን
በእቅፉ ዉስጥ አድርጎ ቀና ሲል የረድኤት አይኖች ከሱ ላይ ሳይነቀሉ በቁጭት ከንፈሮቿን
ስትገምጣቸዉ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ አይቷታል፡፡
"እሷዉ ነች የላከችዉ" ... " እርግጠኛ ነኝ እራሷ ነች" እያለ ብቻዉን ያወራል፡፡ ግራ
ገብቶታል፤ ጭንቅ ጥብብ ብሎታል፡፡
...... ወደ ቤቱ እየሄደ ነዉ፡፡ ሃሳቡ ሁሉ የተላከለት መልዕክት ላይ ሆኗል፡፡ "አሁን እንደ
ሚስቴ በር ላይ ትጠብቀኛለች፡፡ ምን ልላት ነዉ? ኤዲ ብትሰማስ...." እያለ ይጨነቃል፡፡  ከቤት ወጣ......
ከምንም በላይ ደግሞ የኤዲ ነገር አሳስቦታል፡፡ ሌላ አግብቶ ልጅ መዉለድ እንዳለበትም
ዉስጡን አሳምኖታል፡፡ ግን... እንዴት ብሎ? ሁለተኛ እንዳያገባ አቅሙ አይፈቅድለትም፡፡
ከኤዲ ዉጭ ደግሞ... ኑሮ አይታሰብም፡፡
በነዚህ ሀሳቦች ጭንቅላቱ ተወጥሮ ጅማቱ ተገታትሯል፡፡ ጭንቅላት በሃሳብ ቢነፋ ኖሮ ...
ጭንቅላቱ በአየር እንደተሞላ ፊኛ ይሆን ነበር፡፡ በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ አስቦ ... አስቦ ...
ተጨንቆ ... መጨረሻ ላይ እንደ ፊኛዉ ጠሽሽ ማለቱ አይቀርም፡፡ወደ ቤቱ ሊገባ እርምጃዎች ቀርተዉታል........
     


🔻ክፍል  7️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💫 Notcoin ብዙ ሰው በትንሹ እስከ 20 ሺ ብር ሰርተዋል!

🚀 Tap swap ያልጀመራችሁ ሊጠናቀቅ ትንሽ ቀን ነው የቀረው

ከታች ባለው ሊንክ መሳተፍ ትችላላችሁ!

⚡️ TapSwap 👉https://t.me/tapswap_mirror_2_bot?start=r_5938888057 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​   👆👆👆👆👆 
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል 7️⃣3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0












            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
7️⃣

ወደ ቤቱ ሊገባ እርምጃዎች ቀርተዉታል.........
....

        አሁንም ሀሳብ ላይ ነዉ፡፡... በሩን ሊያንኳኳ እጁን ከፍ አደረገ እንደገና አመነታና እጁን ወደነበረበት መለሰዉ፡፡ ልቡ ለሁለት ተከፍሎ ልግባ ወይስ ልመለስ አይነት ስሜት እየተሰማዉ ባለበት ወቅት የረድኤት አባት ከኋላዉ መጡ፡፡ "ቢኒያም ደህና ነህ እንዴት ነህ?  አሉት ጋሽ ሀብታሙ ለሰዎች ሰላምታ ሲሰጡ አያሳጥሩም ሁሌም ቢሆን በሙሉዉ ነዉ፡፡ በዚህም ብዙ ጓደኞቻቸዉ ይወዷቸዋል፡፡
ቢኒ ሳያስበዉ ድንገት ከኋላዉ የጋሽ ሀብታሙን ድምፅ ሲሰማ መብረቅ ያንፀረቀበት፤ ሰማይ
የተደፋበት ነበር የመሰለዉ፡፡ "ጋሽ ሀብታሙ እ... እ... " ተንተባተበ ፈራቸዉ በግድ እንደምንም
ብሎ ሰላምታዉን መለሰ፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ግን የስከዛሬዉ ቢኒያም፤ ቀልደኛዉ፤ ተጫዋቹ፤
ለወሬያቸዉ ክብር ያለዉ ቢኒያም አልመሰላቸዉም፡፡ እስከዛሬ ቀድሞ ይቀልዳቸዉ ነበር፡፡
"ወጣቱ ሽማግሌ"  እያለ ይቀልዳቸዋል፡፡ እንደዉም እያወሩ እያለ "ወጣቱ ሽማግሌ
ምን ማለት ነዉ?" ብለዉ ጠይቀዉት ነበር፡፡ ቢኒም "እድሜው የሽማግሌ፤ ልቡ የባተለ
ነዉ፡፡" አላቸዉ፡፡ የባተለ ማለቱ ገና ወጣት ኖት፡፡ ለነገሮች አልተሸነፉም ማለቱ ነበር፡፡
በርግጥም ልክ ነበር ጋሽ ሀብታሙ ቢኒ እንደገለፃቸዉ የልብ ወጣት ናቸዉ፡፡
...ግራ መጋባቱን ባዩ ጊዜ "አስደነገጥኩህ እንዴ? ልጄ ቢኒያም" ብለዉ ጠየቁት "ኧረ ጋሽ
ሀብታሙ እንደዉ ትንሽ ሀሳብ ዉስጥ ገብቼ እንጂ እርሶ አላስደነገጡኝም" አላቸዉ፡፡...የቢኒያምን
ሀሳብ አላወቁም እንጂ ከቤታቸዉ ዛሬዉኑ ልቀቅልኝ ብለዉ ነበር አምባ ጓሮ የሚፈጥሩት፡፡
ደስ የሚለዉ ነገር ግን አላወቁበትም፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ቢኒያምን አለፍ አሉትና
የሱሪያቸዉ ኪስ ዉስጥ ግራ አጃቸዉን አስገብተዉ የበሩን ቁልፍ አወጡና በሩን ከፈቱት፡፡
ሁለቱ ቆነጃጅቶች በር በሩን እያዩ ይቁለጨለጫሉ፡፡ ኤዲና ረድኤት፡፡ ኤዲ ባሏን ትጠብቃለች፡፡
ረድኤት ደግሞ የልቧን ዘራፊ ..፡፡
...... በሩ ከፈት ሲል ከኤዲ ቀድማ ረድኤት አንገቷ እስኪሰበር ድረስ ወደ በሩ ዞረች...፡፡ጋሽ
ሀብታሙ ... ነበሩ፡፡ጋሽ ሀብታሙ ከቢኒ ቀድመዉ ነበር የገቡት ከኋላቸዉ ደግሞ ቢኒ አለ፡፡ እንደወትሮዉ ኮራ፤ ቀብረር ብሎ ሳይሆን አንገቱን ወደ መሬት ቀብሮ፤
በጣም አቀርቅሮ ጋሽ ሀብታሙን ተከትሎ ወደ ዉስጥ ዘለቀ፡፡ ረድኤት የአባቷ መምጣት
ብዙም አልገረማትም ቢኒን ከአባቷ ኋላ ስታየዉ ግን ፀሐይ ከምታበራዉ በላይ አበራች፡፡
ዉስጧ በሃሴት ተፍነከነከ፡፡ ሁሌም እንዲህ ናት፡፡ ቢኒን ስታይ መተንፈስ እንዳለባት ሁሉ
ትረሳለች፡፡... ኤዲም ከጋሽ ሀብታሙ ኋላ ዉድ ባሏን አየችዉና እየሮጠች ስትመጣ "ኧረ ቀስ ቀስ
እንዳትደፊ" አሉ ጋሽ ሀብታሙ "ደክሞት ከስራ መጥቶ እቤቱ እንኳ ሳይገባ አንቺን እንደ ልጁ ተሸክሞ  ይዉሰድ እንዴ¡ ሃሃሃሃ" መቀለዳቸዉ ነበር፡፡
ኤዲ ግን አፈረች፡፡ እንደ አመጣጧ ዘላ
ጉብ ከዚያ እጆቿን በአንገቱ ላይ ሰድዳ ጥምጥም ብላበት ልታቅፈዉ ነበር፡፡ ግን
አልቻለችም...፡፡ ቀኑን ሙሉ ስታስበዉ የነበረዉን ነገር ጋሽ ሀብታሙ በቀልዳቸዉ
ድንብርብሯን አጠፉባት...፡፡ቢኒ ፊት ቆማ ቀና ብላ አይን አይኑን አያየች እንዲያቅፋት በአይኗቿ ትማፀነዉ ነበር፡፡
ቢኒ ግን አላቀፋትም፡፡ አንዴ ኤዲን እንደገና ቀና ብሎ ደግሞ ረዲን ያያታል፡፡ ምን
እንደሚያደርግ ግራ ገብቶታል፡፡
ረድኤትም ወደነሱ ተጠጋች፡፡ ቢኒ ፈራ ይበልጥ ፈራ፡፡ "በመልዕክት የላከችዉን እዚሁ
ሚስቴ ፊት ልታፈርጠዉ ነዉ እንዴ?" ብሎ እያሰበ ቀስ ብሎ አይን አይኑን የምታየዉን ኤዲን
አቀፋት፡፡ "ሃሃሃ ይሄን ፈልጋ አይደል እስክትደፋ የምትሮጠዉ" ብለዉ...ቢኒን "በል በደንብ
እቀፋት"  ብለዉት ዘወር ሲሉ ልጃቸዉ አጠገባቸዉ ቆማለች፡፡ ረድኤት በ​​አባቷ አባባል
ብትናደድም ቻል አድርጋዉ "አባዬ..." ስትል ... ጋሽ ሀብታሙም "ምነዉ አንቺም ቢኒያምን
ማቀፍ አሰኘሽ እንዴ?" አሏት፡፡ ቢኒም "ሃሃሃ አይቀርም" ሲል ኤዲ ከታቀፈችበት እቅፍ
የቢኒን እጆች መንጭቃ ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ረድኤት ደግሞ ደስታ ሊደፋት ነዉ፡፡
ጋሽ ሀብታሙ "አንተ ቀልዱን ምር አደረከዉ? ዋ!!" ብለዉ ቢኒን አስፈራሩት...
....ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ የእማማ በለጡ ስልክ እያቃጨለ ነዉ፡፡ ከብዙ የስልክ ጥሪ ቡኃላ
እማማ በለጡ ስልኩን አነሱት፡፡
..."ሄሎ ማን ልበል?" አሉ እማማ በለጡ
..."አያውቁኝም ማዘር የረድኤት የክፍል ጓደኛነኝ፡፡ ረድኤት ሀብታሙ ትኖራለች?"
እማማ በለጡ ረድኤትን ጠሩዋትና ስልኩን ሰጧት
... "ሄሎ" ስትል ረድኤት የስልኩን ንግግር ቤተሰቦቿ እንዳይሰሙ ብሎ...
..."ሄሎ ረድኤት ... ቢኒያም ነኝ፡፡  አንዴ ወደ ዉጭ ወጥተሽ ታናግሪኝ"...
     

🔻ክፍል  8️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Ethio Computer
Hp elitebook 840 G3
  
   1tb storage

  8gb  installed memory

  6th generation

Intel  core i5

  14.1 inch screen size

.  FullHD resolution

.  Keyboard light

.  has sim  slot

price  27500


📞  0908616263
            

Inbox me @ethio3254
Join us

https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
8️⃣

     ..."አያውቁኝም ማዘር የረድኤት የክፍል ጓደኛነኝ፡፡ ረድኤት ሀብታሙ ትኖራለች?"
እማማ በለጡ ረድኤትን ጠሩዋትና ስልኩን ሰጧት
... "ሄሎ" ስትል ረድኤት የስልኩን ንግግር ቤተሰቦቿ እንዳይሰሙ ብሎ...
..."ሄሎ ረድኤት ... ቢኒያም ነኝ፡፡  አንዴ ወደ ዉጭ ወጥተሽ ታናግሪኝ"...

       ...ረድኤት በስልክ የቢኒን ድምፅ ስሰማ ደስታና ድንጋጤ ተቀላቅሎባት ልቧ በአፏ ልትወጣ ደርሳ ነበር፡፡ እየተቁነጠነጠች
...  "ሄሎ ቢኒ" አለችዉ
...  "ሰላም ነው ረዲ እንዴት ነሽ?"
ረዲ ብሎ ስሟን ሲያቆላምጥላት 'ወይዬ' ልትል እየቃጣት ቶሎ በፍጥነት ከአፏ
መለሰችዉ፡፡
...  "ደህና ነኝ ቢኒ ሰላም...." ከማለቷ ነበር የማማ በለጡ ስልክ
ጢጥ ጢጥ ብሎ ባትሪ የዘጋዉ፡፡ በጣም ተናደደች፡፡ መልሳ በራሷ ስልክም ልትደዉል
ፈለገች፡፡
"እማዬ ግን ስልክሽን ባትሪ ሲያልቅ ቻርጅ ብታረጊዉስ?" እየተበሳጨችና እየተቆጣች ነበር
እናቷን የተናገረችዉ፡፡

ቢኒ የማማ በለጡ ስልክ የዘጋዉ ባትሪ ጨርሶ እንደሆነ ያወቀዉ ጢጥ ጢጥ የሚለዉን
የባትሪ አልቋል የሚለዉን ድምፅ ሲሰማ ነዉ፡፡
..... ልጅ መዉለድ እንዳለበት ያምናል፡፡ ለኤዲ ግን እንዴት ብሎ ይንገራት፤ በምን መልኩ
ያስረዳት፡፡ በሂወቱ እንድታዝንበትና እንድትከፋበት አይፈልግም፡፡ ኤዲ ማለት ለቢኒ ፍቅርን
ያስተማረች፤ መዉደድን አልብሳ ራሷን መስዋዕት ያደረገችለት ታላቅ ሴት ናት፡፡  በማንም
ሊቀይራት አይደለም... ማንንም ሊደርብባት አይፈልግም፡፡
በርግጥ ቢኒ ለእናትና ለአባቱ አንድና ብቸኛ ልጅ ነዉ፡፡  ቤተሰቦቹም ቢሆኑ ቢኒ ገና
የአምስት አመት ህፃን ልጅ እያለ ነበር በድንገተኛ የመኪና አደጋ የሞቱት፡፡ በችግር
ከማደጉም በላይ ጥርሱ ሳቅን እየናፈቀች፤ አይኑ ፍቅርን እንዳማተረች፤ ሆዱ ምግብን
እንዳሻች ... እርሱ እንደሚለዉ "በፈጣሪ እገዛ እዚህ ደርሻለሁ"፡፡ ለኑሮዉ መቅናት ፈጣሪን
አመስግኖ ከዚያ ቀጥላ ግን... ኤዲ ነች፡፡ ኤዲ ለቢኒ እናቱም አባቱም፤ ደስታዉም፤ ሂወቱም
ናት፡፡ ደግሞም ልጅ መዉለድ አለበት፡፡ በጣም ተጨንቋል፡፡ በሃሳብ ብዛት ጭንቅላቱ እንደ
ወተት ተገፍቶ፤ እንደፊኛ ተነፍቶ ጅማቱ ወጥርጥር ብሎ "ኤዲ ወይስ ልጅ?" እያለ ያስባለል፡፡
በርግጥም ልጅ መዉለድ አለበት፤ ያለ ዘር መቅረት የለበትም፡፡ እንኳን ቢኒ ፤ ቢኒን
የሚያዉቁት ሁሉ ልጅ መዉለድ አለበት፤ አይኑን በአይኑ ማየት አለበት ብለዉ ያምናሉ፡፡
.
....ከሁሉም ሰዉ በላይ ግን ለቢኒ ኤዲ ታስባለች፡፡ ያለ ልጅ መቅረቱ ያሳስባታል፡፡ ልጅ
ልትወልድለት ባለመቻሏ "ኤዲ አንቺኮ ለቢኒ የምትገቢ አይደለሽም!፡፡" እያለች ራሷን
ትወቅሳለች፡፡
.... ቤቷ ቁጭ ብላ እያሰበች ነዉ፡፡ "ማግባት አለበት!" ትላለች፡፡ ይሄን ነገር ስትፈቅድለት
ግን... ራሷን መስዋዕት አድርጋ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ቢኒ ደሃ ነዉ፡፡ አንድ ሚስት እንጂ
ሁለተኛ መደረብ አይችልም ፡፡ ደግሞ ከቢኒ ተለይታ መኖር አትችልም፡፡ ከርሱ ዉጭ
ህይወት የላትም፡፡ በጣም ተጨንቃለች፡፡ ከምንም በላይ ኤዲን የሚያስደስታት ቢኒ ደስ
ብሎት ማየቷ ነዉ፡፡ ምንም ያክል በትዳሩ ደስተኛ ቢሆንም ትዳር ያለ ልጅ ዉበት የለዉምና
እሷን ፈትቶ ሌላ አግብቶ ልጅ መዉለድ እንዳለበት አምናለች፡፡ "ደግሞስ... ፍቅር ማለት
ለምወደዉ ሰዉ ራስን መስዋዕት አድርጎ ደስታን መፍጠር፡፡  አይደል እንዴ ?" እያለች እራሷን
በጥያቄ ታፋጠለች፡፡ ቤት እንደመጣ እነግረዋለሁ፡፡ አግባ እለዋለሁ... ብላ ወሰነች........፡፡
.
ረዲኤት ዛሬም ስለ ቢኒያም ታስባለች፡፡ የሰዉ ባል ልትቀማ፤ የሚያምር ፍቅር ልታደፈርስ
እንደሆነ ስታስበዉ ግን... መልዕክት በመላኳም ትቆጫለች፡፡ ሊቀርብኝ ይገባል፡፡ ቢኒ የኤዲ
ብቻ ነዉ፡፡
ስለዚህ እኔ በመሃላቸዉ መግባት የለብኝም ወደሚለዉ እያመዘነች ነዉ፡፡....ግን ገና
አልወሰነችም፡፡ ምክንያቱም ቢኒን ትወደዋለች መዉደድም ብቻ ሳይሆን በጣም
ታፈቅረዋለች፡፡....



🔻ክፍል 9️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                      
#ክፍል_ 9️⃣

        .... ኤዲ ለቢኒ ካላት ፍቅር  የተነሳ ስታከብረዉ ወደር የላትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ለሱ ንግግር
ቦታ ትሰጣለች፡፡
በእያንዳንዷ ክንዋኔም ላይ የቢኒ ቃል ተቀዳሚ ነዉ፡፡
... ሁለቱም በእኩል ቅጽበት "እ..." ሲሉ... ኤዲ ቀደም ብላ "ወይዬ ቢኒ ምን ልትለኝ ነበር?"
አለችዉ፡፡
ቢኒም "ኤዲዬ የኔ ቆንጆ አንቺ ሁሌም እኔን ታስቀድሚያለሽ፡፡ "የኔ ፍቅር ታዉቃለሃ?"
.....  "ምኑን ነዉ የማዉቀዉ ኤዲዬ?"
.....  "እኔና አንተ ከተጋባን አራተኛ አመታችን ነዉ፡፡"
.....  " እ... በፍቅር ክንፍ አድርገሽኝ ያበድኩልሽ ቀን! ያ ቀን እንዴት ይጠፋኛል ዉዴ!?"
.....  "እሱ አይደለም ፍቅሬ"
.....  "እና ምንድን ነዉ ....?"
.....  "ከተጋባን ቆይተናል ግን እስካሁን...."
...  "ማሬ አታስጨንቂኛ ፕሊስ ንገሪኝ?"
.....  "ቢኒ የኔ ዉድ...."
....  "ወይዬ ኤዲ የኔ ቆንጆ! ... ንገሪኛ!"
.....  "ልጅ ልወልድልህ አልቻልኩም ቢኒ"
ቢኒ በዉስጡ ያለዉን ስሜት ኤዲ አወጣችዉ፡፡ "ሁለታችንም አንድ አይነት ነገር ነበር
የምናስበዉ ማለት ነዉ?" አለ በሆዱ፡፡ ትክክለኛ ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ነዉ የሚቀዱት
ማለት ይሄኔ ነዉ፡፡
ቢኒ ኤዲን ሊጎዳት አልፈለገም....
..... "ኤዲዬ ይሄኮ ታዲያ የፈጣሪ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ፈጣሪ ባለ ጊዜ ትወልጂ ይሆናል፡፡" አላት፡፡
..... " አዎ የኔ ፍቅር ፈጣሪ ካለ እወልድ ይሆናል፡፡ ግን ደግሞ አንተ ከኔ በይበልጥ ልጅ
ማግኘት፤ ዘርህን መተካት ይኖርብሃልኮ ዉዴ!"
..... "እና ምን ላርግ ዉዴ? ልጅ ከመዉለድ በላይ አንቺ ለኔ እንደምታስፈልጊኝ ታዉቂያለሽ፡፡
ስለዚህ ማሬ...."



ረዲኤት ስለ ቢኒ ስታብሰለስል ቆይታ ሲጨንቃት  ጋደም ባለችበት እንቅልፍ ሸለብ አድርጓታል፡፡
እማማ በለጡም የረዲ የሰሞኑን ቅብዥር አላምራቸዉ ቢል ወደ ረዲ የመኝታ ክፍል ገብተዉ
ከጎኗ ቁጭ ከማለታቸዉ ነበር ... ረዲ እንደ ቅብዥር ነገር ጀምሯት "ቢኒ እወድሃለሁ"
የምትለዉ፡፡
እማማ በለጡ በቆሙበት ደርቀዉ ቀሩ፡፡እስከዛሬ ልጃቸውን ምን እዲህ እንፈሚያደርጋት ገባቸው ቢኒ የኤዲ ባል...እንዴት?... እያሉ ብቻቸውን ያወሩ ጀመር፡፡ ምን ይበሉ? ሊቀሰቅሷት አቃታቸዉና
እንደገና መለስ አሉ፡፡ "በአካል ባታገኘዉ እንኳ በህልሟ እስኪ የሷ ይሁን!" እያሉ ይመስላሉ፡፡
እማማ በለጡ በጣም ጥሩ ሴት ናቸዉ፡፡ ልጃቸዉ አንድ ከመሆኗ የተነሳ እንደ እናት ብቻ
ሳይሆን እንደ እህትም፣ እንደ ጓደኛም ሆነዉ ነዉ ያሳደጓት፡፡ ረዲን ዛሬ ጫን ያለዉ ይዟት
እንጂ አንድም ነገር ከእናቷ ደብቃ አታዉቅም፡፡ አሁን ግን ... የሰዉ ባል አፈቀርኩ ብትል
እንኳን ለእናት ለጓደኛም ለመንገር ያሸማቅቃል፡፡
እማማ በለጡ ጉዳቸዉን ሰምተዉ በእጃቸዉ መዳፋ አገጫቸዉን ይዘዉ "ጉድ... ጉድ" እያሉ
ከረዲኤት ክፍል ወጡ፡፡
እማማ በለጡ ከመዉጣታቸዉ ረዲኤት ብርግግ ብላ ስትነሳ ፊቷ በላብ ተዉጧል፡፡ በቅብዥሯ
"እወድሃለሁ" ስትለዉ የነበረዉ ቢኒያም ከአጠገቧ የለም፡፡ የሞባይሏን ሰአት ስታይ ቢኒ
ለስራ የሚወጣበት ሰዓት ደርሷል፡፡ በፍጥነት ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሂዳ እጇ ላይ
ዉሀ በማድረግ ፊቷት ውሃ ረጨት ረጨት አደረገች፡፡ በሷ ሃሳብ መታጠቧ ነበር፡፡ እየሮጠች
ወጣችና በሯ ላይ ቁጭ ብላ እየተቁለጨለጨች የነ ቢኒን ቤት በር በር ታይ ጀመር፡፡
.
....ቢኒ፡ ኤዲ መረበሿን ሲያይ አብሯት እንኳ ባይዉል ቁርስ አብሯት ለመብላት ወስኖ ነበር
ማርፈዱ፡፡ ኤዲ ግን... አዳሯን ሙሉ እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር ስላደረች ንጋቱ ላይ ለብዙ ቀን
እንቅልፍ ያልተኛች በሚመስል መልኩ ለሽሽሽ ብላለች፡፡ ቢኒም ቶሎ እንደማትነሳ
ስለተረዳ ቁርሷን ከአጠገቧ አስቀምጦ በብጣሽ ወረቀት "የኔ ቆንጆ አፈቅርሻለሁ!፡፡ ፈጣሪ
ይጠብቅሽ" የሚል ፅሁፍ አኑሮ ከመዉጣቱ... በሩ ፊት ለፊት ረዲኤትን አያት፡፡
ከግቢ የመዉጫዉን በር ተወና ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት
አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም
የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡
እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡
ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ....
"ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡
እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡


        


🔻ክፍል 1️⃣0️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                      
#ክፍል_ 1️⃣0️⃣

....
ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት
አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም
የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡
እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡
ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ....
"ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡
እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡... እማማ ሚረዱ፤ ኮሽታ ሰምተዉ የሚነቁ በአሁኑ አባባል አራዳ የሚባሉ ሴት ናቸዉ፡፡ እስከዛሬም ልጃቸዉን አላጤኗትም እንጂ ቅዠት ከመስማታቸዉ ቀድመዉ ያዉቁባት ነበር፡፡ ይሄዉ አሁን ደግሞ ስሙ ቢላቸዉ በራቸዉ ስር
መጥቶ ቢኒያም ልጃቸዉን ረድኤትን እያዋራት ነዉ፡፡
..... "ቢኒ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላዉቅም፡፡ ግን... ትቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም አንተን
ላገኝህ አልችልም፡፡ ኤዲንም ላሳዝናት አልፈልግም፡፡" አለችዉ ረዲ
ቢኒም....."ረዲ እሱን ላወራሽ አልነበረም፡፡ በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር
አመጣጤ! በይ ደህና ዋይ" ብሏት መልሷን ሳይሰማ ጥሏት ሄደ፡፡
ረድኤት በህይወቷ እንደዚች ሰዓት የተደሰተችበት ቀን የለም፡፡ ደስታ ቢገል ኑሮ ቢኒ "በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር አመጣጤ" ካላት በኃላ ትንፋሿ ፀጥ ብሎ ትሞት ነበር፡፡ ከበር እስከሚወጣ በአይኗ ከሸኘችዉ ቡኃላ ከተቀመጠችበት ተነስታ መስተዋት ፍለጋ እየሮጠች ስገባ እናቷ የመስኮቱን መስተዋት ከፍተዉ እንደማፅዳት እያደረጉ ነበር፡፡
ደነገጠች፡፡"እማዬ ስናወራ ሰምታን ይሆን እንዴ?" ብላ አሰበች፡፡ የእናቷ ነገር ደስታዋን እንዳያከስምባት ቶሎ ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ መስተዋቱ ፊት ተገተረች፡፡ 'እዉነትም ቆንጆ ነኝ!" ስትል ለራሷ አሰበች፡፡ረዲን በጣም ብዙ ወንዶች ግማሹ ለትዳር፣ ግማሹ ለአዳር፣ ሌላዉ ደግሞ ለፍቅር ጓደኝነት ሲጠይቋት አላማና ኢላማ ያላት ስነ-ስርዓት ያላት ልጅ ስለነበረች ሁሉንም ገፍታ አባራቸዋለች፡፡ ለቁጥር የሚያዳግቱ ብዙ ወንዶች ለዉበቷ ቋምጠዉላታል፤ በጣም ዉብ
ነች፡፡ብዙ ሰዎች የቁንጅናዋን ልክ ለመናገር ቃላት ደርድረዋል፡፡ እሷ ... ግን ለጊዜያዊ ስሜት የምትረታ የዋዛ አልነበረችምና አሻፈረኝ ብላለች፡፡
የቢኒ አንዷ ቃል ግን ዉስጧ ገብቷል፡፡ ልትተወዉ የነበረችዉን ሴት እንደገና የልቧን ፍም ጭሮባታል፡፡ "ቢኒንማ አልተወዉም!!" የረዲኤት ዉሳኔ ነበር፡፡

... ኤዲ ከእንቅልፏ እንደነቃች በባሏ እጅ የተከሸነዉን ጣፋጭ ቁርስ ማጣጣም ይዛለች፡፡
ቁርሷን በልታ ሳጨርስ ተኝታበት ወደነበረዉ አልጋ ዘወር ስትል ከትራሷ ስር ብጣሽ ወረቀት
አየች፡፡ አነሳችዉና ስትገልጠዉ "የኔ ፍቅር አፈቅርሻለሁ፡፡ ፈጣሪ ይጠብቅሽ!" የሚል ፅሁፍ
አነበበች፡፡ ደስታ ልቧን ፈነቀለዉ፡፡ ቢኒ እዉነትም ፍቅር ነዉ፡፡ ቁርስ ሰርቶ አካሏን
ከመጠገኑም በላይ 'አፈቅርሻለሁ' ብሎ የመንፈስ ምግብ ሰጣት፡፡ ባዲስ ንጋት ከቁርስ ጋር ፍቅር መገባት፡፡ኤዲ አዳሯን እንቅልፍ ማጣቷን ሁሉ እረሳችዉ፡፡ በደስታ ተፍነከነከች፤ በሀሴት ጮቤ
እረገጠች፡፡ በዚህ ልዩ ጧት፤ በዚህ ልዩ ቀን የጧቷን ፀሐይ ልትሻማ ከቤቷ ወጥታ ለፀሐይ ጀርባዋን ሰጥታ ቁጭ አለች፡፡
...... ረድኤት ቆንጆ መባሏ ሳያንስ ሌላ ዉበት፤ ሌላ ድምቀት ተላብሳ፤ ንጋቷን በፍቅር አድሳ እሷም እንደ ኤዲ የፀሐይን ሙቀት ልትኮመኩም ወጣች፡፡
ከመዉጣቷ ኤዲን ስላየቻት ወደሷ ሄደች፡፡ ረድኤት ላይ ዉበት ጎልቷል፤ ኤዲ ላይ ደግሞ ደስታ ነግሷል፡፡ ሁለቱም ለጨለማ ድምቀት እንደሆነችዉ ጨረቃ ደምቀዋል፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ
ቡኃላ ኤዲ፡ ረዲን...
..... "ዛሬ ወደየት ልትሄጂ ነዉ ባክሽ ተሽቀርቅረሻልሳ" አለቻት



🔻ክፍል  1️⃣1️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የክረምት መባቻ ወግ


ወንድ ልጅ ግን በክረምት ገንዘብና ጺም አይጣ!

በነገራችን ላይ፥ ንግድ ባንክ ባለፈው ብር እንደ መስኖ ጠልፈው ያስቀሩ ሰዎችን ፎቶ መበተኑ በቂ አይደለም ፤ በፎቶው ላይ የሚታዩ ሰዎችን ለምንጠቁም ሰዎች የክረምቱን የሚያወጣ ጉርሻ ቢለቅልን አሪፍ ነው፤ ህግ የማስከበር ዘመቻውንም ያቀላጥፈዋል !

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ጃንጥላ እሚይዝ ወንድ ፋራ ነው ብሎ ያወጀው ዠዝባ ማን ነው? ባለፈው ጃንጥላ ልገዛ ስጠይቅ ፥ ሻጩ “ለእናትህ ነው ለሚስትህ ?” ብሎ ጠየቀኝ ፤

" ለአናቴና ለሚስቴ በህይወት እንድቆይላቸው እሱን አራት ሄክታር ጃንጥላ ስጠኝ ፤
ሰገጤ ላለመባል የተነከረ ባቄላ መስየ ቤቴ እንድገባ ፈልገህ ከሆነ ትልቅ ስተት ሰርተሀል ፤
ቢመቸኝ ፥ እንኳን ጃንጥላ እጀታ ያለው ድንኳን እዘረጋለሁ ፤ “ልለው ፈልጌ ተውኩት፤

እሚገርመው፥ የሆነ ዘመን እርድና በሌላው ዘመን ላይ ስግጥና ይሆናል፤ ነዋይ ደበበ ’ ጥላ ይዤ ልከተልሽ?” የሚል ዘፈን ሁሉ ነበረው፤

እኔ ሲመስለኝ ወንዶች ጃንጥላ መያዝ የለባቸውም ብሎ የደነገገው ሰውየ “አስጠልይኝ “ በሚል ሰበብ ከሴቶች ጋራ መተሻሸት የሚፈልግ ይመስለኛል ፤

ጃንጥላ በመያዝ ራሳችንን ችለን እንቁም! ሳይፈቀድልን በሴቶች ራዳር ውስጥ አንግባ! አመሰግናለሁ!

ክረምት መባቻ ላይ ትዝ እምትለኝን የወዳጄን ገጠመኝ አካፍየ ምሳየን ላብስል፤

ከአያሌ አመታት በፊት ጌትነት እንየውና ጉዋደኞቹ ለአንድ የገጠር ቀበሌ ህዝብ መስክ ለይ ተውኔት ያሳያሉ፤ ህዝቡ መስኩን ከበብ አድርጎ ያያቸዋል፤ ተውኔቱ የታሪኩ አማካኝ ላይ ሲደርስ ዝናብ ማካፋት ጀመረ፤ ግማሹ ተመልካች ከተቀመጠበት ፥ተነስቶ እየተግበሰበሰ፥ ባቅራቢያ በሚገኘው ዋርካ ዛፍ ስር ተጠለለ፤ የኪነጥበብ ፍቅራቸው የዝናቡን ዱላ ያስረሳቸው ሰዎች ብቻ ሜዳው ላይ ቀሩ፤ ትንሽ ቆይቶ በረዶ ብቻ ሳይሆን በራሪ ኮከብ የቀላለቀለ ዝናብ አካባቢውን ይወቅጠው ጀመር ፤ ተዋናዮች ከዚህ በላይ ለኪነጥበብ መስዋእትነት መክፈል አልፈለጉም፤ እየሮጡ ዋርካው ስር የተጠለሉትን ሰዎች ተቀላቀሉ፤

ከተጠለሉት ተመልካቾች መካከል አንድ ወዝ የጠገበ ከዘራ የያዘ ጎረምሳ ፥ወደ ተዋናዮች እያየ

“ ጎበዝ ! ዛሬ ሰንጢ ይዘንባል እንጂ አምስት ብራችንን የከሰከስንበትን ትያትር መጨረሻ ሳናይ አንሄድም”

ይሄኔ ጌትነት እንዲህ አለ፤

“ በመጨረሻም ሙሽራውና ሙሽራይቱ ወንድምና እህት መሆናቸውን ይደርሱበታል፤ አሁን በሰላም ወደ ቤታችሁ መሄድ ትችላላችሁ “

በውቀቱ ስዩም
❤️" ብትመጣም ባትመጣም "❤️

እስካለህ ሸንግለኝ
እስካለን ደልለኝ
ትመጣለህ ? ስልህ
" እ . መ . ጣ . ለ . ሁ " በለኝ

( ብትክደኝ እንኳ .. )
( ብትክደኝ እንኳ .. )

አንተን ለመጠበቅ መኖሬን አትርሳ
ለጥያቄዬ መልስ መቅረትን አታንሳ
ረሳሁሽ እንዳትል ብትረሳኝ ባትረሳኝ
ሳቅ ያበደረኝን ተስፋዬን አትንሳኝ !

( እኔ ምን ቸገረኝ .. )
እኔ ምን ቸገረኝ .. ብትቀር ባትቀር
( ብቻ ግን አደራ )
" ተይኝ" እንዳትለኝ ከጠብቂኝ በቀር
😍😍
( ከእልፍ ደዌ መሐል )
ነገን እንድናፍቅ ልቤን ተስፋ አክሞት
( ብትመጣም ባትመጣም )
" እ መ ጣ ለ ሁ ! " በለኝ እየሳቅኩ እንድሞት..
😍😍😍
               ሊና
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​   👆👆👆👆👆 
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል 1️⃣1️⃣ 3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0












            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                      
#ክፍል_ 1️⃣1️⃣


..... "ዛሬ ወደየት ልትሄጂ ነዉ ባክሽ ተሽቀርቅረሻልሳ" አለቻት
ረድኤትም ..... "ኤዲዬ አንቺምኮ አምሮብሻል ምን ተገኝቶ ነዉ?"
....."እኔማ የዉበቴም የድምቀቴም ምክንያት ባሌ ነዉ፡፡......" ብላ ስለ ቁርሱ፤ ስለ ወረቀቱ
ምንም ሳታስቀር ለረዲ ነገረቻት፡፡
ኤዲና ረድኤት በደንብ ተግባብተዋል፡፡ ብዙ ሚስጥሮችን አብረዉ እየተጋሩ ነዉ፡፡ ረዲ ለኤዲ
'ባልሽን ልቀማሽ ነዉ ተዘጋጂ!" የሚለዉ ሲቀር፡፡
.....ኤዲም "አንቺስ የዚህ ዉበት ምንጭ ማን ይሆን ረዲ?" አለቻት፡፡ ባልሽ ቢኒያም ነዉ
አትላት ነገር... እ እ እያለች ስትደናገጥ የረድኤት አባት ከቤት ዉስጥ ወጡና "እንዴት አደርሽ
ኤደን" ብለዉ ጨዋታቸዉን አቋረጧቸዉ፡፡
...... "ደህና አደሩ አባባ" ብላ መለሰችላቸዉ፡፡ አባባ  ትንሽ
ቀለድለድ ካደረጉ ቡኃላ
... "ኤዲ" አሏት፡፡
..."አቤት አባባ" አለቻችዉ፡፡
..."ኧረ እቺን ጓደኛሽን ምከሪያት እስኪ"
..."ማንን? ረድኤትን?" ስትላቸዉ
..."መቼም በለጡን ምከሪያት አልልሽ የኔ ልጅ" ሲሉ ሁሉም ተሳሳቁ፡፡ አባባ
ቀልዳቸዉና ምራቸዉ አያስታዉቅም፡፡ ቁም ነገር እያወሩ በመሃል ይቀልዳሉ፡፡ በቀልዱም
መሃል ያመራሉ፡፡ ሁሌም ፀባያቸዉ እንዲህ ነዉ፡፡ ቀጠል አደረጉና....
..."ባል እየተንጋጋ ይመጣል እሷ ግን አሻፈረኝ አለች፡፡ ሁሌም ልማር ነዉ የምትለዉ፡፡
አግብቶስ ትምህርት የከለከላል እንዴ የኔ ልጅ?" ብለዉ ጠየቋት ኤዲን፡፡ ረድኤት አንዴ ኤዲን፤
አንዴ አባቷን እያየች የሚሉትን ትሰማለች፡፡
..."አይ አይከለከልም፡፡ እንደዉም ሴት ልጅ በጊዜ ስታገባ ነዉ ጥሩዉ" አለቻቸዉ
..."ተባረኪ የኔ ልጅ" አሏት ደስ ብሏቸዉ "...እንደዉም እንደ ቢኒያም አይነት ባል ፈልጊማ ኤዲ፡፡ ሳልጠይቃት ነዉ የምድራት" ሲሉ ሁሉም ተሳሳቁ፡፡ ረዲ "እሱ እራሱ ቢኒ በመጣ"አለች በዉስጧ፡፡
..... ጨዋታዉ እንደቀጠለ ነዉ፡፡ እማማ በለጡም አራተኛ ተጨምረዉ ወሬዉን
አድምቀዉታል፡፡
.
ቢኒ በንግግሩ ኤዲን እንዳስደሰታት አዉቋል፡፡ ይበልጥ ወደ እሱ እንድትቀርብ ያደረገዉም ዘዴ ነዉ፡፡ ከኤዲ ጋር በተነጋገሩት መሰረት ሁለተኛ ማግባት እንዳለበት ወስነዋል፡፡ ሌላ ሴት
ፍለጋ መኳተን አልፈለገም፡፡ እዚሁ እፊቱ በሱ ፍቅር የተራበችዉን ረድኤትን ሊያገባት ነዉ፡፡"ግን... በምን መልኩ? አባቷስ እሺ ብለዉ ይድሩልኝ ይሆን?" እያ ያስብ ጀመር፡፡...
.
......"ረዲዬ..." አሏት እማማ በለጡ ልጃቸዉን
..."ወይዬ እማዬ...." ቤት አብረዉ ቁጭ ብለዉ ነበር፡፡ አባባ ስለሌሉ ረድኤትን
የሚያዋርባት ምቹ ጊዜ አግኝተዋል እማማ በለጡ፡፡
... "አባትሽ ሁለት ሚስት እንደነበረዉ ታዉቂያለሽ?"
ረድኤትም "ኧረ እማዬ አላዉቅም፡፡" አለች መልሱን ለማሳጠር ያክል፡፡ ምክንያቱም ወደ እሷ ቀስ እያሉ እንደሚመጡ አላጣችዉም፡፡
.... "ይሄዉልሽ የኔ ልጅ! አባትሽ መጀመሪያ ሌላ ሚስት ነበረችዉ..."
"ካንቺ በፊት?" ብላ ሊቀጥሉት የነበረዉን ወሬ አቋረጠቻቸዉ፡፡ በዚያም ላይ ደንግጣለች፡፡ረድኤት እስካሁን ድረስ እናቷ የአባቷ ሁለተኛ ሚስት እንደነበረች አታዉቅምና፡፡
...."አዎ ከኔ በፊት ሌላ ሚስት ነበረችዉ"
...."እና ምን ሆነች ማሚ? ፈቷት ነዉ ወይስ...?"
...."አይ አልፈታትም ነበር፡፡ ሙታ ነዉ ፈጣሪ ነብሷን ይማራትና" አሉ
...."እንዴት?... ለምን?... ማለቴ ...በምን ምክንያት ሞተች

          


🔻ክፍል  1️⃣2️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Ethiobot
laptop ከ16500ብር ጀምሮ እኛ ጋ በቅናሽ ዋጋ ያገኛሉ ብንልዎትስ?
እንግዲያውስ እሚፈልጉትን laptop telegram channel ላይ መርጠው ከ1 ዓመት ሙሉ ዋስትና ጋር እንሰጥዎታለን።
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                      
#ክፍል_ 1️⃣2️⃣

 
...."እንዴት?... ለምን?... ማለቴ ...በምን ምክንያት ሞተች?" እየተንተባተበች ነበር
የጠየቀቻቸዉ፡፡
...."ይሄዉልሽ ልጄ አባትሽና ሚስቱ በጣም ነበር የሚዋደዱት፡፡ ፍቅራቸዉ እጅግ ያስቀና
ነበር፡፡ ግን ምን ይደረግ ልጅ መዉለድ አልቻለችም፡፡ ከዚያ አባትሽ ሀብታም ስለነበር
ሁለተኛ እኔን አገባኝና አንቺን ወለድኩለት፡፡ ከመጀመሪያ ሚስቱ ጋር የነበረዉ ፍቅር ቀነሰ፡፡
ዉሎዉ፤ አዳሩ ከእኔና ካንቺ ልጁ ጋር ሆነ፡፡ የመጀመሪያ ሚስቱን ፈታት እንዴ? እስከሚባል
ድረስ ረሳት፡፡ እሷም በፍቅር ተጎዳች፡፡ እኔ በመዉለዴ ቅናት አብሰከሰካት፤ ብቸኝነት አጠቃት ይሄን ሰበብ አድርጎ ነዉ መሰለኝ በጣም ታመመች፡፡ ብዙም ሳትቆይ ሞተች፡፡አባትሽም ከሞተች ቡኃላ ነበር የመሞቷ ስበብ እሱ መሆኑን ያወቀዉ፡፡" በሀዘን ተዉጠዉ ነበር የሚነግሯት በፈጣሪ" አለች ረድኤት "እንዴት እስከዛሬ ሳላዉቅ ግን ማሚ?ይሄን ያክል ድብቅ ነሽ ማለት ነው...ጊዜዉ እየነጎደ ነዉ፡፡ ረድኤትም የዩንቨርሲቲ መግቢያዋ ቀርቧል፡፡ ቀናቶች ናቸዉ የቀሩት፡፡የቢኒ ጉዳይ አልተቋጨም፡፡ አሁንም ቢሆን እሱን ከማሰብ ስለሱ ከማለም አልቦዘነችም፡፡
ከጭንቅላቷ ጋር አብሮ የተሰራ ይመስል ሁሌም ስሙን ትደጋግማለች፡፡ ልቧ ላይ ግን ላይለቅ፤ ላይገፈፍ ታትሟል፡፡... ኤዲና ቢኒ እያወሩ ነዉ፡፡ በባለፈዉ ምሽት ሁለተኛ ማግባት እንዳለበት ተስማምተዋል፡፡ኤዲ የሆነ ነገር አስባለች ግን ደግሞ ለቢኒያም መንገር ፈራች፡፡ከስንት ፍርሃትና ትግል ቡኃላ
..."ቢኒ" አለችዉ
..."ወይዬ ፍቅሬ🌺" አላት፡፡ አቤት አጠራር ፤ አቤት ፍቅር
..."ለምን እኔ እራሴ አልድርህም"
..."እንደዉም ከአንቺ ጋር የምትስማማዋን አምጭልኝ" አላት፡፡ እየቀለደ ነበር፡፡
..."ቢኒ አትቀልዳ...ከምሬኮ ነዉ፡፡ እኔዉ ልዳርህ ፍቅሬ" አለችዉ፡፡ ቢኒያም ግራ ገባዉ፡፡
በዉስጡ "ይቺ ልጅ ከምሯ ነዉ እንዴ?" እያለ
..."ማንን ነዉ የምትድሪልኝ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ ኤዲም ፈራ ተባ እያለች..." በጣም ቆንጅዬ ልጅ ናት በዚያ ላይ ስርዓቷ ጥግ ድረስ ነዉ፡፡ እንደዉም ላንተ
የምትሆንህ እሷ ናት፡፡"ቢኒ ተደናገጠ፡፡ ነገሩ እሱ ብቻ ሳይሆን ንግግራቸዉን የሚሰማ ሰዉ ቢኖር ይደነግጣል፡፡እንዴት ተቀናቀኟን እሱዋለዉ ትመርጣለች፡፡ በዚያ ላይ ቆንጆ ብላ እያሞገሰች፤ ስለ ፀባይዋ እየመሰከረች፡፡
..."ማን ናት እሷ😘 ኤዲዬ"
..."ረድኤት!" አለችዉ፡፡ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ ምላሱ ተሳሰረበት የሚናገረዉ ጠፋዉ፡፡
..."እዉነትሽን ነዉ?" አላት፡፡ በመጠራጠር አይነት ስሜት..."አዎ! ደሞኮ በጣም ምርጥ ልጅ ናት ፍቅሬ" አለችዉ፡፡ በዉስጡ 'አንቺ ሳታዉቂ መጀመራችንን አታዉቂ?" አሞግሻት' እያለ ..."እሷስ እሺ የምትል ይመስልሻል?" አላት ወሬያቸዉ ቀጥሏ ረድኤት ተክዛ በሃሳብ ተዉጣ ቁጭ ብላለች፡፡ ዛሬም መንታ መንገድ ላይ ነች፡፡ ቢኒን ልተወዉ ወይስ እንደምንም ብዬ ላግባዉ፡፡ እማማ በለጡ የረድኤትን በሀሳብ መዋጥ
ተመለከቱና ጠጋ ብለዉ "ልጄ ምን ሁነሽብኝ ነዉ? ሰሞኑን ሁኔታሽ ልክ አይደለም" አሏት
ረዲም "ምንም አልሆንኩምመ እማዬ" ብላ መለሰችላቸዉ፡፡"የሆነ ነገርማ ደብቀሽኛል፡፡ በፊትኮ እንዲህ አልነበርሽም የኔ ልጅ" እንደ መንቃት እያለች
ተንጠራራችና ወገቧን ነቅነቅ አድርጋ"ያዉ እማዬ አሁንስ እንደ በፊቱ ሆንኩልሽ?" አለቻቸዉ፡፡ እማማ በለጡ ጣታቸዉን አገጫቸዉ ላይ ጣል አድርገዉ
..."የኔ ልጅ በህልምሽ ቢኒያም፣ ቢኒ የምትይዉ ማንን ነዉ?"..."ምን?... ማ እኔ?... ኧረ እኔ አላልኩም እማዬ" አለች፡፡ ተደናግጣ ነበር፡፡ እማማ በለጡም
ቀስ እያሉ ሊያዉጣጧት ፈልገዉ
..."አንድ ቀን'ኮ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ነዉ የምትይዉ" አሏት
..."እኔንጃ እማዬ ግን..."
..."ግን ምን የኔ ልጅ?" ይበልጥ ለማወቅ ጓጉተዋል
..."ቢኒያም የሚባል ልጅ ሳልወድ አልቀርም!"
..."ምን?" አሉ እማማ በለጡ ያላወቁ በመምሰል "የኤዲን ባል ቢኒያምን ነዋ?"
..."አይ..." ብላ ንግግሯን ሳጨርስ ረዲ
..."አዎ እሱኑ ነዉ፡፡ አትዋሺኝ የኔ ልጅ፡፡ ባለፈዉም እንዳማረብሽ ሲነግርሽ ሰምቻለሁ፡፡
ለመሆኑ ኤዲ ታዉቃለች?"ብለወ ጠየቋት፡፡ ረድኤት እናቷን ፈራቻቸዉ

          


🔻ክፍል  1️⃣3️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔸 አዳዲስ ላፕቶፖችን አስገብተናል 
   🔺🔻🔺🔹 🔺🔻
   laptop  መግዛት ፈልገው  የት ልግዛ ብለው ተቸግረዋል ?

እርስዎ በየሱቁ መንከራተትና መድከም ሳይጠበቅብዎት ባሉበት ሁነው እሚፈልጉትን computer እኛ ቻናል  ላይ መርጠው ይላኩልን  እኛ ከ1  ዓመት ሙሉ ዋስትና ጋር በቅናሽ ዋጋ እንሸጥልዎታለን

https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0  join በማድረግ በየጊዜው ፖስት እሚደረጉ የተለያዩ ብራንድ ላፕቶፖችን ማየት ትችላላችሁ::

እንዲሁም   ያገለገለ ወይንም አዲስ laptop and projector ያላችሁ በጥሩ ዋጋ እንገዛዎታለን
💠💠💠💠
Telegram channel
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0

Facebook page
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100084394544041&mibextid=ZbWKwL

For more info
Inbox
@ethio3254
Call at
📞0908616263
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                      
#ክፍል_ 1️⃣3️⃣


ረድኤት እናቷን ፈራቻቸዉ፡፡ ንግግራቸዉ ወደ ቁጣ እየተቀየረ ይመስላል፡፡
..."አይ አታዉቅም" አለች
..."የኔ ልጅ!" አሉ እማማ "ባለፈዉ ያባትሽ ሚስት በእኔ ምክንያት እንደሞተች
ነግሬሻለኃ?"
..."አዎ እማዬ ነግረሽኛል"
..."ስለዚህ የኔ ልጅ ኤዲም ባንቺ ምክንያት መጎዳት የለባትም፡፡ አንቺና ቢኒያም እንደሆናችሁ ሳጨርሱ አቀሩም፡፡ እኔ ለቢኒያም የምድርሽ የእናንተን መስማማት አይቼ ሳይሆን የኤዲን ፍቃደኝነት ጠይቄ ነዉ!"አሉት፡፡ ረድኤት ደስም አላት ግራ ተጋባችም፡፡ ቢኒያምን ልታገባዉ ነዉ ግን ደግሞ ኤዲ ባትፈቅድስ
..."እና ለኤዲ  ልትነግሪያት ነዉ እማዬ?"
..."አዎ ቀስ ብዬ እነግራታለሁ፡፡ አንቺ አታስቢ የኔ ልጅ" ብለዋት ከተቀመጡበት ተነስተዉ
ወደ ዉስጥ ገቡ፡፡ አባባ ሀብታሙ ከዘራቸዉን ይዘዉ ዉጭ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ እንደ አጋጣሚ ኤዲ ከቤት ስትወጣ ፊት ለፊት አየቻቸዉና "አባባ ሀብታሙ ሰላም ኖት" አለቻቸዉ፡፡ እርሳቸዉም "ደህና ነኝ ፈጣሪ ይመስገን ሰላም ነሽ ወይ ኤዲ" ብለዉ መለሱላት፡፡
ከዚያም አጠገባቸዉ ቀረበችና ስለ ረዲ አንዳንድ ነገር ለማወቅ "አባባ ረዲን አትድሯትም እንዴ እድሜዋኮ እየሄደ ነዉ፡፡"አለቻቸዉ፡፡አባባ ሀብታሙም የሷን ጥያቄ ወደ ጎን አሉና "አንቺና ቢኒያም ከተጋባችሁ ምን ያህል ጊዜ ሆናችሁ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡ኤዲ ይሄን ጥያቄ ከመለሰች ቡኋላ ቀጣዩ ጥያቄ ምን እንደሚሆን አዉቃለች፡፡ ለጥያቄያቸዉ
መልስ መስጠት ስላለባት ብቻ "አራተኛ አመታችንን ይዘናል" አለቻችዉ፡፡"ታዲያ ልጃችሁን ቤተሰቦችሽ ዘንድ አርጋችሁት ነዉ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡
..."አይይ አባባ..." አለቻቸዉ በረጅሙ የብሶት ትንፋሽ እየተነፈሰች፡፡ ተራርቀዉ
መቀመጣቸዉ እንጂ ትንፋሿ እንደ በርሃ ወበቅ ይጋረፋል፡፡
..."ምን ነዉ? የኔ ልጅ?" አሏት ጭንቀቷን ሲያዩ
..."አይ ምንም" አለችና አቀረቀረች ኤዲ፡፡ አባባ የሆነ ነገር እንዳለ ጠረጠሩ፡፡እሳቸዉም የልጅ ፍቅር ስላላቸዉ ጭንቀቷ ይገባቸዋል፡፡
"ልጅ አልወለድኩም አባባ..." አለቻቸዉ፡
አባባ ሁኔታዋን ሲያይዋት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይታይባታል፡፡ እሷ ግን እንደምንም እየታገለች ፈገግ ለማለት ትሞክራለች፡፡ ምክንያቱም ልጃቸዉን ለባሏ ልትጠይቃቸዉ ነዉና፡፡ ከረጅም ዝምታና ፀጥታ ቡኃላ አባባ ተንፈስ አሉና "ባልሽ ቢኒያም ግን በጣም ጎበዝ ነዉ አደነቅኩት" አሏት፡፡ እሷም ለምን? እንዴት? በምን ምክንያት አደነቁት? ብላ አልጠየቀቻቸዉም፡፡ ቢኒ የሚደነቅ ጥሩ ሰዉ እንደሆነ ታዉቃለችና፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጠኛ እየሆነች ነዉ፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያም ረድኤትን ለትዳር ቢጠይቅ እምቢ እንደማይሉና በደስታ እንደሚድሩት
ከአባባ ሀብታሙ ሁኔታ መረዳት ችላለች፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያምን ይወዱታል፡፡ ደስ
አላት፡፡ ባሏን እሷዉ ልድረዉ ነዉ፡፡...ቢኒ ከስራ እንደመጣ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም፡፡
"ቢኒ ለረድኤት ቤተሰቦች ሽማግሌ መላክ አለብህ" አለችዉ፡፡
..."እንዴ ፈጠንሽሳ?" አላት ቢኒ
..."አዎ ፍቅሬ ሌላ የኔን ቢጤ ደሃ ካገባህኮ እኔን መፍታትህ አይቀርም፡፡ እኔ ደግሞ አንተ
እንድትፈታኝ አልፈልግም፡፡ ሁሌም በፍቅርህ መኖር እፈልጋለሁ" አለችዉ እየተቅለሰለሰች፡፡
ይሄን ከማለቷ ብዙም ሳይቆዩ የቢኒያም ስልክ መልዕክት (ሜሴጅ) ገባ "ጢጢጥ
ጢጢጥ" ሜሴጁ ሲገባ የቢኒ ስልክ ያሰማዉ ድምፅ ነበር፡፡ ቢኒ ስልኩን አነሳና
የላኪዉን ስም ሲያይ በማማ በለጡ ስልክ ነዉ የተላከዉ "ረድኤት መሆን አለባት" አለ
በዉስጡ፡፡ ኤዲ እያየችዉ ነበር፡፡ ደንገጥ ብሎ ስታየዉ ፊቷ ክስም ይላል፡፡ እንደገና ፈገግ
ሲል እሷም አብራ ትፈካለች፡፡ ኤዲ ሁሌም ቢሆን በቢኒያም ደስታ ደስ ይላታል፡፡
"የኔ ፍቅር ምንድን ነዉ መልዕክቱ?" አለችዉ....ኤዲ ቢኒ ፈገግ ስላለበት ጉዳይ ለማወቅ ጓጓች፡፡ ቢኒ አሁንም እንደፈገገ ነዉ፡፡
" ንገረኛ ዉዴ?" አለችዉ፡፡ በአይኖቿ እየተማጸነች፡፡ ቢኒያም ሊነግራት ነበር ነገር ግን
ከረድኤት ጋር ከዚህ በፊት እንደተደዋወሉና በስልኩ መልዕክት እንደላከችለት ቀድሞ ለኤዲ
አልነገራትም ነበር፡፡ ትቆጣ ይሆን እንዴ? ፈራ፡፡ ከሷ መደበቅ ስላልፈለገና ኤዲ ብትቆጣም
ብታኮርፍም ልትንሽ ሰዓታቶች እንደሆነ ስላወቀ ስልኩን ለኤዲ አቀበላት፡

          


🔻ክፍል  1️⃣4️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​   👆👆👆👆👆 
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል 1️⃣4️⃣ 3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM