የልብ ቋንቋ
222K subscribers
196 photos
11 videos
640 links
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀

⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE

Contact
Download Telegram
🔸🔸🔸🔸🔸🔸

❤️ሰላም ሰላም ቤተሰቦች አዲስ ታሪክ በቅርቡ እንጀምራለን
ይጀመር እምትሉ እስኪ 
1️⃣0️⃣0️⃣ 👍like ❤️



🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን! 😀


   

 
❤️❤️
❤️❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️

    ሰላም ቤተሰቦች ምኞቴ የተሰኘ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ ታከታታይ የፍቅር ታሪክ ዛሬ እንጀምራለን 💛


   ክፍል1 ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
1️⃣

          ... ረድኤት ከረፋዱ አራት ሰዓት አከባቢ የቤታቸዉን በረንዳ በማፅዳት ላይ ሳለች የግቢያቸዉ
በር ተንኳኳ፡፡ ማን ሊሆን ይችላል? ብላ እያሰበች ወደ በሩ ተጠጋች "አባዬና እማዬ ዛሬ የስራ
ቀን ስላልሆነ ቤት ዉስጥ ናቸዉ፡፡" እና ማን ነዉ? እያለች የግቢዉን በር ጠጋ አለችና "ማን
ነዉ?" አለች "እኔ ነኝ" የሚል ለስላሳ ድምፅ ከዉጭ የተሰጣት መልስ ነበር፡፡ ድምፁን
ከዚህ በፊት ባታዉቀዉም ሰላም ያለ ሰዉ እንደሆነ በድምፁ ስለተረዳች በሩን ከፈተችለት፡፡
በጣም ቆንጅዬ ወጣት ነበር፡፡  "ደህና ነሽ" አላት፡፡ እሷም "ደህና ነኝ" ብላ
ስትመልስለት "የሚከራይ ቤት አለ ብለዉኝ ነበር... አለ እንዴ?" ሲላት የረድኤት አባት
ለረዢም ሰዓት በር ላይ እንደቆመች ስላዬ
"ማን ነዉ?" እያሉ ወደ በሩ ተጠጉ፡፡ ወጣቱንም ባዩ ጊዜ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
ወጣቱ ልጅ ለረድኤት የጠየቃትን ጥያቄ ለአባቷ ለጋሽ ሀብታሙ ደገመላቸዉ፡፡ ጋሽ ሀብታሙም አለ ወደውስጥ ግባ ልጄ፡፡ አሉት  እሺ ብሎ ገባ የሚከራየውን ቤት ገብቶ አየ ስንት እንደሚከራይ ጠየቃቸውና ተስማምተው ቢኒያም ወደ ቤት ተመለሰ ፡፡ ... ከዚህ ጊዜ በኃላ ነበር ረድኤት ቢንያምን ያወቀችዉ፡፡ ቢንያም እጅግ በጣም ዉብና
ማራኪ ልጅ ነዉ፡፡ ሚስቱ ደግሞ ኤደን ትባላለች፡፡ እጅግ ሲበዛ ዝምተኛና ቆንጂዬ ናት፡፡ ቤት
ስለምትዉልና ረድኤትም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብትሆንም ሰመርን ከቤተሰቦቿ ጋር ስለምታሳልፍ ሁሌም አብረዉ ይዉሉ ነበር፡፡
ኤዲ ምንም ያክል ዝምተኛ ብትሆንም ለባሏ ግን ፍቅርን መስጠት የምትችል፤ በተለይ
ሲጫወቱና ሰዉነቱ ላይ እየተንከባለለች ቅብጥብጥ ቅብጥ፤ ሽፍድ ስትልበት... ረድኤት "እኔ በሆንኩ" ብላ ትቀናባታለች፡፡ .

..... ቢኒያም ከስራ ሊመጣ አከባቢ ኤዲ እጅግ በጣም ተዉባ ከወትሮዉ በተለዬ ይበልጥ
አምራ የግቢዉን በር ለመክፈት ከቤቷ ወጥታ በሯ አጠገብ ትቀመጣለች፡፡ ልክ በሩ
እንደተንኳኳ ሩጣ ትሄድና ቶሎ ትከፍታለች፡፡ ቢኒያምም እቅፉ ዉስጥ አስገብቶ ሲስማት
ለተወሰነ ሰዓታት የተለያዩ ሳይሆን ለአመታት ተራርቀዉ ተነፋፍቀዉ የተገናኙ ይመስላሉ፡፡
ቢኒያም ፍቅር መስጠት ተክኖበታል፡፡
ሲያፈቅራትና ሲወዳት ምድር ላይ ሌላ ሴቶች እስከመፈጠራቸዉም ረስቶ ነዉ፡፡ ለሱ ሴት
ማለት እሷ ብቻ ናት፡፡ እንደ እናት ያከብራታል፤ ያፈቅራታል በጣም ይሳሳላታል፡፡ ፍቅራቸዉ
እንኳን አብሯቸዉ ለሚኖር ሰዉ ለአንድ ቀን በመንገድ ላይ ያያቸዉ ራሱ ይቀናባቸዋል፡፡

...ከግቢዉ ነዋሪም ጋር በጣም ተግባብቷል፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ለብቻቸዉ ባገኛቸዉ ሰዓት "አባባ
ገና ወጣት ነህ አረጁ የሚል ሰዉ ተሳስቷል፡፡ አሁን እኔ እና አንቱ ሩጫ ብንሽቀዳደም
አዝነውልኝ ካልተዉልኝ በስተቀር ትበልጡኝ የለ እንዴ! አንቱኮ ሀይሌ ገ/ስላሴን ያስንቃሉ፡፡" እያለ
ይቀልዳቸዋል፡፡ እሳቸዉም የወጣትነት ጊዜያቸዉ ታዉሷቸዉ በጨዋታዉ ከሳቁ በኃላ "አይ
ልጄ..." ብለዉ ትረካቸዉን ይጀምራሉ፡፡ ለወሬያቸዉ አክብሮ ጆሮ ስለሰጣቸዉ ከስራ
የሚመለስበትን ሰዓት እንደ ኤዲ እርሳቸዉም ይጠባበቃሉ፡፡ በተለይ ደሞ ረድኤት...!




🔻ክፍል 2️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል2️⃣ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
2️⃣

        ....የፍቅርን ሸማ ለብሶ ለኤዲ መዉደድን አጉርሶ በመኖር የተካነዉ ቢኒያም ይሄ ፍቅር
አሰጣጡ ረድኤት እንድትወደዉ አድርጓታል፡፡
ሁሌም ስለሱ ታስባለች ከቤት የሚወጣበትን ሰዓት እየጠበቀች ታየዋለች... ወደ ስራ ሲሄድ
እሷም እንደ ኤዲ ከአይኗ እስኪጠፋ ድረስ በአይኗ ትሸኘዋለች!፡፡
... ቀኑ እሁድ ቀን ነበር ረፋድ አከባቢ የረድኤት እናትና አባት ከቤታቸዉ በረንዳ ላይ በልጃቸዉ
ፍላጎት ቡና እየጠጡ ነዉ፡፡ ጨዋታዉ ደምቋል፡፡ የረድኤት እናት (እማማ በለጡ) የልጅነት
ቁንጅናቸዉ ዛሬም አለ፡፡ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታቸዉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ እሳቸዉን አይቶ ረድኤትን
"ልጃችሁ ናት?" ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ረድኤትን በካርቦን አስደግፈዉ የሳሏት እንጂ
አምጠዉ የወለዷት ብቻ አትመስልም፡፡
... ኤዲ አስከዛሬ ብቻዋን የምሰራዉን ስራ ዛሬ በቢኒ አጋዥነት ቤታቸዉ በረንዳ ላይ እቃ
ያጥባሉ፡፡ የነ ረድኤት ቤትና የነ ቢኒ ቤት ፊት ለፊት ስለሆነ ከቤት ዉጭ የሚደረጉ ነገሮች
እያንዳንዳቸዉ ይተያያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ረድኤት ቡና ማፍላቷን ረስታ በነሱ ፍቅር ተስባ
በመተዛዘናቸዉ ተደምማ ዛሬም 'ኧረ የኔ በሆነ" አይነት ስሜት ታያቸዋለች፡፡
... ቢኒ በስራቸዉ መካከል ሚስቱን ዉሃ ረጨት እያረገ ይቀልዳታል፤ በመሃል ደሞ
ስራቸዉን ረስተዉ ይተያያሉ፡፡ በስስት ያያታል ሳያወሩ በአይን ይግባባሉ፡፡ እሷን ሲመለከት
ልቡ ቦታዉን ለቆ አይኑ ላይ የመጣ ይመስላል፤ የአይኖቹ ብሌን ልብ ቅርፅ ይሰራሉ ምንም
አይነጋገሩም ግን በአይኖቻቸዉ ፍቅርን ያዜማሉ፡፡
... የሚገርመዉ ግን ሶስተኛ አይንም ነበረ፡፡ ረድኤት! ... ረድኤትም በኤዲ ቦታ ራሷን ተክታ
ቢኒን ታየዋለች የራሷ ባል አስኪመስላት በስስት ታየዋለች፡፡ በሃሳብ ተጉዛ ራሷን ከቢኒ
ጋር አርጋ ነዉ የምታስበዉ፡፡ እናቷ ሲጠሯት እንኳ አሰማም፡፡ እማማ በለጡ ተጣሩ "ረድኤት"
ዝም መልስ የለም እሷ ክንፍ አዉጥታ በራለች ዘመናትን ተሻግራ ከቢኒ ጋር ተጋብታ፤
ቆንጅዬ ልጆችን ወልዳ........... በሀሳብ ጭ.... ልጥ ብላች፡፡
እናቷ እየተጣሩ ነዉ፡፡ "ረድኤት" "ኧረ ረድኤት" ብለዉ ሲጮሁ ደንግጣ ከሃሳቧ ብትት
ከእንቅልፏ ንቅት አለች፡፡ ነገሩ የእማማ በለጡ አጠራር የልጃቸዉን ብቻ ሳይሆን
ጥንዶቹንም አስደንግጧቸዋል፡፡
ቢኒ በስስት ኤዲን እየተመለከታት "አንቺ ባትኖሪኮ ምን እንደምሆን ሳስበዉ..." ብሎ
ሳይጨርሰዉ ኤዲም "ከእኔ የተሻለች ፈጣሪ ይሰጥህ ነበር" አለችዉ፡፡
ቢኒ ሁሌም ቢሆን "ከኔ የተሻለች..." ስትል አይወድም፡፡ ምክንያቱ ደሞ ከእሷ የተሻለች
ሴት አለ ብሎ ማሰብ ስለማይፈልግ፡፡

..."ፈቲዬ አንቺ ደሞ በዚች ቃል ሁሌ ታናጅኛለሻ?" እሷም ወሬ ለማስቀየር... "የኔ ማር..."
ስትለዉ "እንደዉም ካንቺ የተሻለች አገባለሁ" ሲላት ንዴቱ ወደራሷ ዞረና "ሂድ" ብላ ዉሃ
ረጨችበትና አኮረፈች፡፡
ኤዲ ስትስቅም ስታኮርፍም በጣም ዉብ ናት፡፡ ካኮረፈች ደግሞ እንደ ህፃን ልጅ ያረጋታል ፡፡
ቢኒም ማባበል ጀመረ ቶሎ እንደማትስቅ ስለገባዉ ልመናዉን ተወና ለቅጣቱ ተዘጋጀ፡፡....
እሷ አታወራም አኩርፋለች "ዛሬ ራሴን ራሴ ነኝና የምቀጣዉ፡፡ ተመልከቺኝ ..." ብሎ እንደ
ህፃን ልጅ ተንበረከከ እጁንም ወደላይ አርገበገበ፡፡ አሁንም እንዳኮረፈች ናት ከዚያ
አጎበደደና ጆሮዉን ሲይዝ ኤዲ በሳቅ ፍርስ አለች፡፡
... ረድኤትና ቤተሰቦቿም "ምንድነዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ..




🔻ክፍል3️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
3️⃣

        .... ... ረድኤትና ቤተሰቦቿም "ምንድነዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ... ቢኒ ለፍቅሩ ተንበርክኮ ያስቃታል፡፡
ይሄኔ ረድኤት በጣም ትቀናለች!፡፡ ፍቅሯ በዉስጧ መብሰልሰል ይዟል፡፡ አዉጥታ አታወራዉ..
ለማን? ግቢ ዉስጥ ያለችዉ የእድሜ እኩያዋ "ኤዲ" ናት፡፡ የወደደችዉ ወጣት ሚስት ያለውነው! " ሆ
ሆ " ብላ ለራሷዉ ተሸማቀቀች፡፡
አዉጥታ መናገር እንዳለበት አምናለች ግን እንዴት ብላ ያዉም ባለ ትዳርና በትዳሩ ደስተኛ
የሆነን ሰዉ...፡፡

...ረድኤት ሌቱን ሙሉ እንቅልፍ አልወሰዳትም ትገላበጣለች፤ ታስበዋለች፡፡ ሸለብ
ሲያደርጋት በአይነ ህሊናዋ ያንን ቆንጆ ፊትና የሚያምር ጨዋታዉን ታያለች እንደገና ብትት
ትልና ቁጭ ትላለች፡፡ ምን እንደምትሆን ግራ ገብቷታል?.... ነገር ግን አንድ ስሜት ዉስጧን
ፈንቅሎ ወጣ "ነገ ልትነገሪዉ ይገባል" የሚል ድምፅ ሹክ ያላት መሰላት፡፡ "አዎ" ስትል
አሰበች "ነገ ልነግረዉ ይገባል!" "ግን... እንዴት ነዉ የምነግረዉ?" "አፈቅረሃለሁ" ልለዉ
ትልና "ኧረ..." ትላለች፡፡ "እሺ ምን ልበለዉ!?" ... በጣም ጨንቋታል ሰማይ ከመዉጣት
በላይ ከብዷታል ... ይሄንን እያሰበች የነገዋን ንጋት በጉጉት እየጠበቀች ከሌሊቱ ስምንት
ሰዓት ገደማ እንደምንም ታግላ እንቅልፍ ሸለብ አደረጋት...!

....... ረድኤት የእቅልፍ ሰዓቷ በጣም ረፈድ አርጋ ስለተኛች የሚገርም እንቅልፍ
ላይ ናት፡፡የጠዋቱ የወፎቹ ዜማም ሆነ የሞባይል አላርሟ ሊቀሰቅሳት አልቻለችም ለሽሽሽ ብላ
ተኝታለች!፡፡...... ቢኒ ዛሬ ቀኑ ሰኞ ስለሆነ በጧት ስራ መግባት አለበት፡፡ ቁርሱንም እዚያዉ ስራ ቦታ
እንደሚበላ ለኤዲ ቀድሞ ስለነገራት ከእንቅልፏ ሊቀሰቅሳት አልፈለግም፡፡ ልብሱን ለባበሰና
ወደ ስራ ከመዉጣቱ በፊት ወደ መኝታ ቤቱ አመራ ኤዲ ተኝታለች፡፡ ተኝታ ሲያያት ቁንጅናዋ
የበለጠ አስደመመዉ፡፡ ዉብ ናት፤ በጣም ዉብ ...  ስለሷ ተናገር ቢባል ቃላት ሁሉ ያጥረዋል፡፡ እጥፍጥፍ ብላ ስተኛ
የበለጠ ታሳሳለች፡፡ በተኛችበት እንደ ማንጎ ምጥጥጥ ምጥምጥጥ እንደ ትርንጎ
ግምጥጥ ቢያደርጋት ሁሉ የሚወጣለት አይመስልም፡፡ ከእንቅልፏ እንድትነሳ ስላልፈለገ
ቀስ ብሎ በስሱ ሳም አደረጋት፡፡ ግንባሯን ሲስማት ጣፍጭ ጠረኗ አፍንጫዉን አወደዉ
"ፈጣሪ ይጠብቅሽ የኔ ቆንጆ..." ብሎ ቀስ... ብሎ  ከቤት ወጣ......

 

🔻ክፍል4️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​   👆👆👆👆👆 
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል4️⃣ 4:00 ይለቀቃል ።







            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
4️⃣

     ....ረድኤት ተኝታለች፡፡ ያ ስታልመዉና ስታስበዉ ያደረችዉ ቢኒ የዉስጧን ሳነግረዉ የልቧን ሳታወራዉ ሄዷል፡፡ ... እማማ በለጡ ግራ ገብቷቸዉ "ልጄ አመማት እንዴ!?" እያሉ ይጨነቃሉ፡፡ ከተኛችበት አጠገብ ተቀምጠዉ ሲያዯት በረድኤት ፊት
ላይ ላብ ይቀዳ ነበር፡፡ ለካስ እየቃዠች ነበር "ቢኒያም" "ቢኒ" "ቢኒያም"  ትላለች፡፡
እማማ በለጡ ግራ ገብቶቸዋል፡፡ኧረ በስመአብ! ብለው አማተቡና ቀስ ብለዉ ልጃቸዉን ቀሰቀሷት "ረድኤት" "ረድኤት የኔ ልጅ ተነሽ ረፍዷል" "ረድኤት" ብለዉ ራሷን ደበስበስ ሲያደርጉ በቅዠቷ ስታልመዉ የነበረዉን ሰዉ "ቢኒያም" ብላ ብትት ስትል....፡፡
 " አይዞሽ ልጄ" "ተነሺ..." "ዛሬ ምን ሆነሽ ነዉ የኔ ልጅ?" "አሁን ተነሺና ሸዋር ውሰጂ

....ረድኤት ከተኛችበት ነቅታ ከፊቷ ላይ ያለዉን ላብ ሟዠቀችዉ፡፡  በቅዠቷ ከቢኒያም ጋር
ነበር ያደረችዉ ስትነቃ አጠገቧ እናቷን ስታገኝ ደንግጣለች፡፡ "የታለ ቢኒያም?" በሚል
ፍለጋ አንገቷን እያዟዟረች መኝታ ቤቱን ትቃኛለች፡፡
ቢኒ ግን ... አጠገቧ የለም፡፡ ከአጠገቧ የተቀመጡት እናቷ እማማ በለጡ ናቸዉ፡፡ እናቷ
በቅርቡ ባይመልሷት የትም ላደርስ በህልም ሩጫ ከቢኒ ጋር ነጉዳ ነበር፡፡ ረዲ ተነስታ
ወደ ሻዋር ቤት አመራች.....
.
...... ኤዲ የቤቷን ስራ ማንጎዳጎዱን ተያይዘዋለች፡፡  ቤቷን አፅድታና አነጣጥፋ ስጨርስ ምሳ
ልሰራ ሽንኩርት እየላጠች የቤቷ በር ላይ ተሰይማለች፡፡
...ረዲ ከቤት ስትወጣ ፊት ለፊት ኤዲን ተመለከተቻት "ደህና አደርሽ ኤዲዬ እንዴት
አደርሽ?" አለቻት ይሄኔ በሆዷ "ባልሽን ልቀማሽ ነዉ ተዘጋጂ"
እያለቻት ይመስላል፡፡ ኤዲም "ደህና አደርሽ ረዲ?"አለቻት ኤዲ ጉዷን አላወቀች አገር
ሰላም ብላ ሰላምታ ትመልሳለች፡፡
ረዲም ወደ ኤዲ ጠጋ ብላ ከፈቲ ጎን እየተቀመጠች "የዛሬዉ ምሳ ምን ቢሆን ነዉ? በጠዋቱ
መስራት ጀመርሽሳ?" አለቻት፡፡ኤዲም "ቢኒ ቀዝቀዝ ያለ ነገር ስለሚዎድ ቀድሜ ልስራ
ብዬ ነዉ" አለቻት፡፡
ረዲም "ከዚያ እሱ ሊመጣ አከባቢ ተዉበሽ ልጠብቂዉ አይደል?!" ብላ ፈገግ አለች፡፡
"ኪኪኪ ባሌ አይደል? ብሽቀረቀርስ?" አለቻት፡፡ ኪኪኪኪ ሃሃሃሃ ሁለቱም ተሳሳቁ፡፡  .... ረዲ
በሂወቷ በማንም ቀንታ የማታዉቀዉን በኤዲ መቅናቷ፤ ልቧ ለማንም......
ያልሸፈተዉን
ለቢኒ  እጅ ወደላይ ማለቷ ቤታቸዉና በፍቅራቸዉ የኔ በሆነ እያለች መመኘቷ ለራሷም
ሳያስገርማት አልቀረም፡፡
በርግጥም ፍቅራቸዉ በጣም ያስቀናል፡፡

...... ኤዲ ስለቢኒ ማዉራት ያስደስታታል፡፡  ረዲ ደግሞ ስለቢኒ መስማት...ኤዲ ስለ ቢኒ
ታወራለች...ታወራለች.. ታወራለች፡፡ የሚገርመዉ ነገር ኤዲ ረዲን አላስተዋለቻትም እንጂ
የቢኒን ስም ስጠራ ረዲ ወደ ኤዲ አፍ ተጠግታ ከንፈሯን ልስማት ደርሳለች፡፡ እንደገና
"ኧረ ምን ሆኜ ነዉ?" ብላ ወደ ኀላ ፈቅቅ ፈቀቅ ትላለች፡፡ ስለሌላ ሳያወሩ የቢኒን
ስም ብቻ እያነሱ ለረዥም ሰዓት ሲያወሩ ኤዲም ስራዋን ዘንግታ ረዲም ከልቧም ተመስጣ
እየሰማች ነበር...፡፡ ኤዲ እንደገና "ኧረ ረዲ ስራዬን አስረሳሽኝኮ..." ብላ እቃ ልታመጣ ረዲን
በተቀመጥችበት ትታት ወደ ዉስጥ ገባች፡፡
...ረዲም ስለ ቢኒ የሰማችዉ ነገር እጅግ በጣም ስቧት ይበልጥ ወደደችዉ፡፡ ግን ...
የሰዉ ነዉ፡፡ ቢሆንም ግን መንገር አለብኝ፡፡ "እሱን አጥቼማ መኖር አልችልም" "ልነግረዉ
ይገባል..." እያለች እያሰበች....

 ይ





🔻ክፍል5️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​   👆👆👆👆👆 
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል  5️⃣ 3:00 ይለቀቃል ።

ቤተሰቦች Like 👍 ማንን ገደለ አንብባችሁ ስትጨርሱ ላይክና ሼር እያደረጋችሁ ባለመሆኑ ቶሎ ቶሎ እየለቀቅንላችሁ አደለም።









            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
5️⃣
ልነግረዉ
ይገባል..." እያለች እያሰበች ኤዲ ከቤት ዉስጥ ሳትወጣ ቢኒ የግቢዉን በር ክፍት
ሲያደርግ ... ረዲም የበሩን ድምፅ ስሰማ ወደ በሩ ዘወር ስትል ረዲና ቢኒ አይን ለ አይን
ተገጣጠሙ፡፡ ይሄኔ ረዲ ድንብርብሯ ይጠፋል፡፡ ልቧ ከድቷት ወደ ቢኒ ሲከንፍ ታወቃት፡፡ የምትሆነዉን
አሳጥቷታል....ቢኒም ወደ ቤቱ ሊገባ ከበሩ ላይ ረዲን እያያት እርምጃዎቹን ጀምሯል፡፡
ረዲ ምን ይዋጣት ሩጣ ዘላ አንገቱ ላይ አትጠመጠምበት እሷ ኤዲ አይደለች፡፡  "ቢኒ
አግባኝ አፈቅረሃለሁ..." እንዳትለዉ የቤቱ በር ላይ ቆማ ሚስቱ ኤዲ ብሰማትስ...፡፡
ምድር ጠበበቻት ፣ መሬት ለሁለት ስንጥቅ ብላ ብትዉጣት ደስታዋ ወደር አልነበረዉም፡፡
ነገር ግን አሁንም ሌሊት ስታልመዉ ያደረችዉን "መንገር አለብኝ ብላ ወሰነች" ....
ቢኒም ወደሷ እየተጠጋ ነዉ፡፡ "ረዲ ደህና ዋልሽ" የቢኒ ድምፅ ነበር፡፡ ደነገጠች
አቤት ድምፁ መስረቅረቁ ሰላምታ የሰጣት ሳይሆን "እወድሻለሁ" ያላት ነበር የመሰላት፡፡
እሷም "ቢኒ ደህና ዋልክ አለችው...ቢኒ ዉድ ባለቤቱን እየተጣራ ወደ ዉስጥ እየገባ ነዉ፡፡ "ኤዲዬ የኔ ማር የት ነሽ?"
....ኤዲ  "ወዬ ቢኒ እዚህ ነኝኝ" እያለች ከእቃ ቤት ወጣች፡፡
...."ደህና ዋልሽልኝ የኔ ወድ..." ግንባሯን ሳም እያረጋት
..... "እንዴት ዋልክልኝ የኔ ፍቅር?".... "ፈጣሪ ይመስገን ደህና ውዬልሻለው! ማሬ ምን ነዉ? ዛሬ ስራ አልጨረስሽም እንዴ?"
......" አዎ  አልጨረስኩም ረድኤት መጣችና ስላንተ እያወራኋት ስራዬን እርስት አላረገዉም
መሰለህ ደሞ አረፍ በል ትንሽ ነዉ የቀረኝ መጣሁ..." ብላዉ ወደ ስራዋ ስትሄድ እሱም
ስራዉን ሊያግዛት እየተከተላት...
...."ቆይ እኔም ላግዝሽ አንቺን ብቻ ማን ልፊ አለሽ የኔ ዉድ" ብሏት ተከተላት.....
...ጊዜዎች እየነጎዱ ነዉ፡፡ ረድኤትም ፍቅሯን ዛሬ ነገ እነግረዋለሁ እያለች አንዴ ሳታገኘዉ
ሌላ ጊዜ ደሞ ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ስፈራ አንድ ወር አለፋት፡፡
አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቡ የሚባሉበት ቀን እየደረሰ ነዉ፡፡ እሷም ፍቅሯን አልነገረችዉም
ማንም ሳያዉቅላት ትወደዋለች ግልፅ ሳታወጣ ታፈቅረዋለች፡፡ አንድ ነገር ደሞ ጠርጥራለች
ኤዲ መዉለድ አትችልም የሚል...፡፡ አንድ ቀን እሷና ኤዲ እያወሩ...
.. ኤዲ "እኔና ቢኒ ከተጋባን አራት አመታችንን ይዘናል"  ስትላት ረዲም "እንዴት እስካሁን
ሳትወልዱ?" ብላ ጠየቀቻት
.."ፈጣሪ አልፈቀደዉም ልጅ አልሰጠንም" ብላ መልሳላት ነበር፡፡ በሃሳቧ የመጣላት ኤዲ
የመዉለድ ችግር እንዳለባት ነዉ፡፡ "ስለዚህ ለቢኒ እንደማፈቅረዉ ብነግረዉ ኤዲን ፈትቶ
ያገባኛል ወይም ሁለተኛ ሚስቱ ያደርገኛል..." ብላ አሰበች፡፡ እንደገና መለስ ብላ "ኧረረረ ሁለተኛስ ይቅርብኝ"
እያለች እራሷ ከሃሳቧ ጋር ትሟገታለች፡፡ ....በመሀል የኤዲ ስልክ ጠራ...፡፡ ስልኳ ላይ የተደወለዉ የማታዉቀዉ ቁጥር ነዉ "<< የፍቅሬ ደሴት ነህ በልቤ ዋሻ ውስጥ ገብተህ"> > የሚለው ነበር የስልኳ ጥሪ፡፡ ኤዲም ስልኩን አነሳችዉና
"ሄሎ"አለች
"ደህና ነሽ.." ጎርነን ያለ የወንድ ድምፅ ነበር፡፡ ኤዲ ስልክ ስታወራ ረድኤት የቤታቸዉ
በር ላይ ቁጭ ብላ መፅሃፍ እያነበበች ነበር፡፡
"ደህና ነኝ ማን ልበል?
"ትናንት ቢኒያም በዚህ ቁጥር ደዉሎልኝ ነበር፡፡ የሱ ስልክ አይደለም እንዴ?"ድምፁ
ማስፈራራቱ ኮስተር ያለ ነዉ፡፡
"አይይ የቢኒያም አይደለም ግን የሱን ስልክ ቁጥር ልሰጥህ እችላለሁ" በዚህ ግዜ ጠላት
እንደመጣባት የጥንቸል ጆሮ ረድኤት አንገቷን ሰገግ አድርጋ ... ማዳመጥ ጀመረች፡፡
"እባክሽን ተባበሪኝ ለስራ ጉዳይ ፈልጌዉ ነበር"
"እሺ ፃፍ 09.. " ስትል ረድኤት ከሰዉየዉ ቀድማ ቁጥሩን መፃፍ ተያያዘችዉ፡፡
" 09 21 79...."  ኤዲ ለደዋዩ ቁጥሩን ነግራ ስጨርስ ረድኤትም እኩል ነበር የፃፈችዉ፡፡
.
ረድኤት ምንም ጊዜ ሳታጠፋ ለቢኒ መልዕክት ፃፈች ..."ቢኒ ሰላም ነው:: እንዴት ነህ ካየሁህ....




 ይ
     ቀ
         ጥ
                ላ
                      ል

🔻ክፍል6️⃣   ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
6️⃣



."ቢኒ ሰላም ነው:: እንዴት ነህ ካየሁህ
ጊዜ ጀምሮ በጣም ነዉ ያፈቀርኩህ!" ብላ ከፃፈች ቡኃላ send  የሚለዉን ተጫነችዉ፡፡
አቤት ድፍረቷ ...ለራሷም አስገርሟታል፡፡ የወራት ሸክሟን ያራገፈች መሰላት፡፡
አሁን ያስጨነቃት የሱ ምላሽ ምን እንደሚሆን ነዉ፡፡
ነገር ግን መልዕክቱ አልደረሰዉም.....

         አሁን ያስጨነቃት የሱ ምላሽ ምን እንደሚሆን ነዉ፡፡ነገር ግን መልዕክቱ አልደረሰዉም"Dear Customer, your balance is insufficient
for this service. Please recharge your account. ethio telecom"  ከቤት ወጣ...... የሚል
ሜሴጅ ስልኳ ላይ ገባ፡፡ ለካስ ስልኳ መልዕክት ሊያስልክ የሚችል ባላንስ አልነበረዉም፡፡
ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ ዉስጥ እየሮጠች ገባች፡፡
"እማዬ ስልክሽ የት ነዉ?" ብላ እማማ በለጡን ጠየቀቻቸዉ፡፡ "እንቺ..." ብለዉ እናቷ
ስልካቸዉን አቃበሏት፡፡ ወደነበረችበት ቦታ ተመልሳ ተቀመጠችና መልዕክቱን መፃፍ ጀመረች " ሰላም ነው ቢኒ በጣም አፈቅርሃለሁ!"  ከቤት ወጣ...... አይ...አለችና መልእክቱን
አጠፋችዉና ሌላ መልዕክት ፃፈች "ሰላም ነው፡፡ ቢኒ ካየሁህ ጊዜ ጀምሮ ላንተ ያለኝ
ስሜት ልዩ ነዉ፡፡ ሳልወድህ አልቀረሁም!" ብላ ፃፈች፡፡ በማታዉቀዉ ሃይል ተገፍታ እጇ
እስኪከዳት ድረስ send የሚለዉን ነካችዉ፡፡ እፎይታ ተሰማት ከማሜ "እሺ" እንጂ ሌላ
መልዕክትን አጠብቅም፡፡
ምናልባት የሱ መልስ እምቢታ ቢሆን ብላ ማሰብም አልፈለገችም፡፡
.... መልዕክቱ ማሜ ስልክ ላይ ገባ "ጢጥ ጢጥ" የሚለዉን የሞባይሉን የመልዕክት ድምፅ
ሲሰማ ስልኩን ከኪሱ አወጣ... የመልዕክቱ ላኪ ... እማማ በለጡ ይላል...ፈገግ አለ፡፡
ደንገጥም አለ ፡፡ "ኤዲ ምን ሆና ነዉ?"  ከቤት ወጣ...... "አመማት እንዴ?" "ምን ብለዉ ልከዉ ይሆን?" በሚል
ጥያቄ ራሱን አፋጠጠ፡፡ ሜሴጁን ሲከፍት ግን ያልገመተዉና ያላሰበዉ ነገር፡፡....መልዕክቱን እንዳነበበ ሰዉነቱን የማያዉቀዉ ስሜት ተሰማዉ፡፡ ምክንያቱም...ቢኒ
ከኤዲ ዉጭ ማንም ያፈቅረኛል ብሎ አስቦ አያዉቅም ነበር፡፡ ደግሞም ማንም እወድሃለሁ
ብሎት አያዉቅም፡፡ ኤዲ እንኳን እንደምታፈቅረዉ የነገረችዉ በተጋቡ በሰባተኛ ወራቸዉ
ነበር፡፡ እስከዚያ ድረስ እሱ ብቻ ነበር እወድሻለሁ፤ አፈቅርሻለሁ ሲላት የነበረዉ፡፡
...... ዛሬ ግን ቢኒ በሌላ ሰዉ "ሳልወድህ አልቀረሁም" የሚል መልዕክት ደርሶታል፡፡
መልዕክቱን ማን እንደላከዉ ብዙ ሳያስብ ነበር የገመተዉ "ረድኤት"  ከቤት ወጣ...... አለ በዉስጡ... ድሮም
አስተያየቷ አላማረዉም ነበር፡፡ እሷ ጋር አይን ለአይን በተገጣጠመበት ጊዜ ሁሉ ከረድኤት
አይኖች የፍቅር አስተያየት አስተዉሏል፡፡ በተለይ ከስራ በሚመለስበት ወቅት ሚስቱን
በእቅፉ ዉስጥ አድርጎ ቀና ሲል የረድኤት አይኖች ከሱ ላይ ሳይነቀሉ በቁጭት ከንፈሮቿን
ስትገምጣቸዉ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ አይቷታል፡፡
"እሷዉ ነች የላከችዉ" ... " እርግጠኛ ነኝ እራሷ ነች" እያለ ብቻዉን ያወራል፡፡ ግራ
ገብቶታል፤ ጭንቅ ጥብብ ብሎታል፡፡
...... ወደ ቤቱ እየሄደ ነዉ፡፡ ሃሳቡ ሁሉ የተላከለት መልዕክት ላይ ሆኗል፡፡ "አሁን እንደ
ሚስቴ በር ላይ ትጠብቀኛለች፡፡ ምን ልላት ነዉ? ኤዲ ብትሰማስ...." እያለ ይጨነቃል፡፡  ከቤት ወጣ......
ከምንም በላይ ደግሞ የኤዲ ነገር አሳስቦታል፡፡ ሌላ አግብቶ ልጅ መዉለድ እንዳለበትም
ዉስጡን አሳምኖታል፡፡ ግን... እንዴት ብሎ? ሁለተኛ እንዳያገባ አቅሙ አይፈቅድለትም፡፡
ከኤዲ ዉጭ ደግሞ... ኑሮ አይታሰብም፡፡
በነዚህ ሀሳቦች ጭንቅላቱ ተወጥሮ ጅማቱ ተገታትሯል፡፡ ጭንቅላት በሃሳብ ቢነፋ ኖሮ ...
ጭንቅላቱ በአየር እንደተሞላ ፊኛ ይሆን ነበር፡፡ በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ አስቦ ... አስቦ ...
ተጨንቆ ... መጨረሻ ላይ እንደ ፊኛዉ ጠሽሽ ማለቱ አይቀርም፡፡ወደ ቤቱ ሊገባ እርምጃዎች ቀርተዉታል........
     


🔻ክፍል  7️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💫 Notcoin ብዙ ሰው በትንሹ እስከ 20 ሺ ብር ሰርተዋል!

🚀 Tap swap ያልጀመራችሁ ሊጠናቀቅ ትንሽ ቀን ነው የቀረው

ከታች ባለው ሊንክ መሳተፍ ትችላላችሁ!

⚡️ TapSwap 👉https://t.me/tapswap_mirror_2_bot?start=r_5938888057 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​   👆👆👆👆👆 
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል 7️⃣3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0












            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
7️⃣

ወደ ቤቱ ሊገባ እርምጃዎች ቀርተዉታል.........
....

        አሁንም ሀሳብ ላይ ነዉ፡፡... በሩን ሊያንኳኳ እጁን ከፍ አደረገ እንደገና አመነታና እጁን ወደነበረበት መለሰዉ፡፡ ልቡ ለሁለት ተከፍሎ ልግባ ወይስ ልመለስ አይነት ስሜት እየተሰማዉ ባለበት ወቅት የረድኤት አባት ከኋላዉ መጡ፡፡ "ቢኒያም ደህና ነህ እንዴት ነህ?  አሉት ጋሽ ሀብታሙ ለሰዎች ሰላምታ ሲሰጡ አያሳጥሩም ሁሌም ቢሆን በሙሉዉ ነዉ፡፡ በዚህም ብዙ ጓደኞቻቸዉ ይወዷቸዋል፡፡
ቢኒ ሳያስበዉ ድንገት ከኋላዉ የጋሽ ሀብታሙን ድምፅ ሲሰማ መብረቅ ያንፀረቀበት፤ ሰማይ
የተደፋበት ነበር የመሰለዉ፡፡ "ጋሽ ሀብታሙ እ... እ... " ተንተባተበ ፈራቸዉ በግድ እንደምንም
ብሎ ሰላምታዉን መለሰ፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ግን የስከዛሬዉ ቢኒያም፤ ቀልደኛዉ፤ ተጫዋቹ፤
ለወሬያቸዉ ክብር ያለዉ ቢኒያም አልመሰላቸዉም፡፡ እስከዛሬ ቀድሞ ይቀልዳቸዉ ነበር፡፡
"ወጣቱ ሽማግሌ"  እያለ ይቀልዳቸዋል፡፡ እንደዉም እያወሩ እያለ "ወጣቱ ሽማግሌ
ምን ማለት ነዉ?" ብለዉ ጠይቀዉት ነበር፡፡ ቢኒም "እድሜው የሽማግሌ፤ ልቡ የባተለ
ነዉ፡፡" አላቸዉ፡፡ የባተለ ማለቱ ገና ወጣት ኖት፡፡ ለነገሮች አልተሸነፉም ማለቱ ነበር፡፡
በርግጥም ልክ ነበር ጋሽ ሀብታሙ ቢኒ እንደገለፃቸዉ የልብ ወጣት ናቸዉ፡፡
...ግራ መጋባቱን ባዩ ጊዜ "አስደነገጥኩህ እንዴ? ልጄ ቢኒያም" ብለዉ ጠየቁት "ኧረ ጋሽ
ሀብታሙ እንደዉ ትንሽ ሀሳብ ዉስጥ ገብቼ እንጂ እርሶ አላስደነገጡኝም" አላቸዉ፡፡...የቢኒያምን
ሀሳብ አላወቁም እንጂ ከቤታቸዉ ዛሬዉኑ ልቀቅልኝ ብለዉ ነበር አምባ ጓሮ የሚፈጥሩት፡፡
ደስ የሚለዉ ነገር ግን አላወቁበትም፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ቢኒያምን አለፍ አሉትና
የሱሪያቸዉ ኪስ ዉስጥ ግራ አጃቸዉን አስገብተዉ የበሩን ቁልፍ አወጡና በሩን ከፈቱት፡፡
ሁለቱ ቆነጃጅቶች በር በሩን እያዩ ይቁለጨለጫሉ፡፡ ኤዲና ረድኤት፡፡ ኤዲ ባሏን ትጠብቃለች፡፡
ረድኤት ደግሞ የልቧን ዘራፊ ..፡፡
...... በሩ ከፈት ሲል ከኤዲ ቀድማ ረድኤት አንገቷ እስኪሰበር ድረስ ወደ በሩ ዞረች...፡፡ጋሽ
ሀብታሙ ... ነበሩ፡፡ጋሽ ሀብታሙ ከቢኒ ቀድመዉ ነበር የገቡት ከኋላቸዉ ደግሞ ቢኒ አለ፡፡ እንደወትሮዉ ኮራ፤ ቀብረር ብሎ ሳይሆን አንገቱን ወደ መሬት ቀብሮ፤
በጣም አቀርቅሮ ጋሽ ሀብታሙን ተከትሎ ወደ ዉስጥ ዘለቀ፡፡ ረድኤት የአባቷ መምጣት
ብዙም አልገረማትም ቢኒን ከአባቷ ኋላ ስታየዉ ግን ፀሐይ ከምታበራዉ በላይ አበራች፡፡
ዉስጧ በሃሴት ተፍነከነከ፡፡ ሁሌም እንዲህ ናት፡፡ ቢኒን ስታይ መተንፈስ እንዳለባት ሁሉ
ትረሳለች፡፡... ኤዲም ከጋሽ ሀብታሙ ኋላ ዉድ ባሏን አየችዉና እየሮጠች ስትመጣ "ኧረ ቀስ ቀስ
እንዳትደፊ" አሉ ጋሽ ሀብታሙ "ደክሞት ከስራ መጥቶ እቤቱ እንኳ ሳይገባ አንቺን እንደ ልጁ ተሸክሞ  ይዉሰድ እንዴ¡ ሃሃሃሃ" መቀለዳቸዉ ነበር፡፡
ኤዲ ግን አፈረች፡፡ እንደ አመጣጧ ዘላ
ጉብ ከዚያ እጆቿን በአንገቱ ላይ ሰድዳ ጥምጥም ብላበት ልታቅፈዉ ነበር፡፡ ግን
አልቻለችም...፡፡ ቀኑን ሙሉ ስታስበዉ የነበረዉን ነገር ጋሽ ሀብታሙ በቀልዳቸዉ
ድንብርብሯን አጠፉባት...፡፡ቢኒ ፊት ቆማ ቀና ብላ አይን አይኑን አያየች እንዲያቅፋት በአይኗቿ ትማፀነዉ ነበር፡፡
ቢኒ ግን አላቀፋትም፡፡ አንዴ ኤዲን እንደገና ቀና ብሎ ደግሞ ረዲን ያያታል፡፡ ምን
እንደሚያደርግ ግራ ገብቶታል፡፡
ረድኤትም ወደነሱ ተጠጋች፡፡ ቢኒ ፈራ ይበልጥ ፈራ፡፡ "በመልዕክት የላከችዉን እዚሁ
ሚስቴ ፊት ልታፈርጠዉ ነዉ እንዴ?" ብሎ እያሰበ ቀስ ብሎ አይን አይኑን የምታየዉን ኤዲን
አቀፋት፡፡ "ሃሃሃ ይሄን ፈልጋ አይደል እስክትደፋ የምትሮጠዉ" ብለዉ...ቢኒን "በል በደንብ
እቀፋት"  ብለዉት ዘወር ሲሉ ልጃቸዉ አጠገባቸዉ ቆማለች፡፡ ረድኤት በ​​አባቷ አባባል
ብትናደድም ቻል አድርጋዉ "አባዬ..." ስትል ... ጋሽ ሀብታሙም "ምነዉ አንቺም ቢኒያምን
ማቀፍ አሰኘሽ እንዴ?" አሏት፡፡ ቢኒም "ሃሃሃ አይቀርም" ሲል ኤዲ ከታቀፈችበት እቅፍ
የቢኒን እጆች መንጭቃ ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ረድኤት ደግሞ ደስታ ሊደፋት ነዉ፡፡
ጋሽ ሀብታሙ "አንተ ቀልዱን ምር አደረከዉ? ዋ!!" ብለዉ ቢኒን አስፈራሩት...
....ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ የእማማ በለጡ ስልክ እያቃጨለ ነዉ፡፡ ከብዙ የስልክ ጥሪ ቡኃላ
እማማ በለጡ ስልኩን አነሱት፡፡
..."ሄሎ ማን ልበል?" አሉ እማማ በለጡ
..."አያውቁኝም ማዘር የረድኤት የክፍል ጓደኛነኝ፡፡ ረድኤት ሀብታሙ ትኖራለች?"
እማማ በለጡ ረድኤትን ጠሩዋትና ስልኩን ሰጧት
... "ሄሎ" ስትል ረድኤት የስልኩን ንግግር ቤተሰቦቿ እንዳይሰሙ ብሎ...
..."ሄሎ ረድኤት ... ቢኒያም ነኝ፡፡  አንዴ ወደ ዉጭ ወጥተሽ ታናግሪኝ"...
     

🔻ክፍል  8️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Ethio Computer
Hp elitebook 840 G3
  
   1tb storage

  8gb  installed memory

  6th generation

Intel  core i5

  14.1 inch screen size

.  FullHD resolution

.  Keyboard light

.  has sim  slot

price  27500


📞  0908616263
            

Inbox me @ethio3254
Join us

https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
8️⃣

     ..."አያውቁኝም ማዘር የረድኤት የክፍል ጓደኛነኝ፡፡ ረድኤት ሀብታሙ ትኖራለች?"
እማማ በለጡ ረድኤትን ጠሩዋትና ስልኩን ሰጧት
... "ሄሎ" ስትል ረድኤት የስልኩን ንግግር ቤተሰቦቿ እንዳይሰሙ ብሎ...
..."ሄሎ ረድኤት ... ቢኒያም ነኝ፡፡  አንዴ ወደ ዉጭ ወጥተሽ ታናግሪኝ"...

       ...ረድኤት በስልክ የቢኒን ድምፅ ስሰማ ደስታና ድንጋጤ ተቀላቅሎባት ልቧ በአፏ ልትወጣ ደርሳ ነበር፡፡ እየተቁነጠነጠች
...  "ሄሎ ቢኒ" አለችዉ
...  "ሰላም ነው ረዲ እንዴት ነሽ?"
ረዲ ብሎ ስሟን ሲያቆላምጥላት 'ወይዬ' ልትል እየቃጣት ቶሎ በፍጥነት ከአፏ
መለሰችዉ፡፡
...  "ደህና ነኝ ቢኒ ሰላም...." ከማለቷ ነበር የማማ በለጡ ስልክ
ጢጥ ጢጥ ብሎ ባትሪ የዘጋዉ፡፡ በጣም ተናደደች፡፡ መልሳ በራሷ ስልክም ልትደዉል
ፈለገች፡፡
"እማዬ ግን ስልክሽን ባትሪ ሲያልቅ ቻርጅ ብታረጊዉስ?" እየተበሳጨችና እየተቆጣች ነበር
እናቷን የተናገረችዉ፡፡

ቢኒ የማማ በለጡ ስልክ የዘጋዉ ባትሪ ጨርሶ እንደሆነ ያወቀዉ ጢጥ ጢጥ የሚለዉን
የባትሪ አልቋል የሚለዉን ድምፅ ሲሰማ ነዉ፡፡
..... ልጅ መዉለድ እንዳለበት ያምናል፡፡ ለኤዲ ግን እንዴት ብሎ ይንገራት፤ በምን መልኩ
ያስረዳት፡፡ በሂወቱ እንድታዝንበትና እንድትከፋበት አይፈልግም፡፡ ኤዲ ማለት ለቢኒ ፍቅርን
ያስተማረች፤ መዉደድን አልብሳ ራሷን መስዋዕት ያደረገችለት ታላቅ ሴት ናት፡፡  በማንም
ሊቀይራት አይደለም... ማንንም ሊደርብባት አይፈልግም፡፡
በርግጥ ቢኒ ለእናትና ለአባቱ አንድና ብቸኛ ልጅ ነዉ፡፡  ቤተሰቦቹም ቢሆኑ ቢኒ ገና
የአምስት አመት ህፃን ልጅ እያለ ነበር በድንገተኛ የመኪና አደጋ የሞቱት፡፡ በችግር
ከማደጉም በላይ ጥርሱ ሳቅን እየናፈቀች፤ አይኑ ፍቅርን እንዳማተረች፤ ሆዱ ምግብን
እንዳሻች ... እርሱ እንደሚለዉ "በፈጣሪ እገዛ እዚህ ደርሻለሁ"፡፡ ለኑሮዉ መቅናት ፈጣሪን
አመስግኖ ከዚያ ቀጥላ ግን... ኤዲ ነች፡፡ ኤዲ ለቢኒ እናቱም አባቱም፤ ደስታዉም፤ ሂወቱም
ናት፡፡ ደግሞም ልጅ መዉለድ አለበት፡፡ በጣም ተጨንቋል፡፡ በሃሳብ ብዛት ጭንቅላቱ እንደ
ወተት ተገፍቶ፤ እንደፊኛ ተነፍቶ ጅማቱ ወጥርጥር ብሎ "ኤዲ ወይስ ልጅ?" እያለ ያስባለል፡፡
በርግጥም ልጅ መዉለድ አለበት፤ ያለ ዘር መቅረት የለበትም፡፡ እንኳን ቢኒ ፤ ቢኒን
የሚያዉቁት ሁሉ ልጅ መዉለድ አለበት፤ አይኑን በአይኑ ማየት አለበት ብለዉ ያምናሉ፡፡
.
....ከሁሉም ሰዉ በላይ ግን ለቢኒ ኤዲ ታስባለች፡፡ ያለ ልጅ መቅረቱ ያሳስባታል፡፡ ልጅ
ልትወልድለት ባለመቻሏ "ኤዲ አንቺኮ ለቢኒ የምትገቢ አይደለሽም!፡፡" እያለች ራሷን
ትወቅሳለች፡፡
.... ቤቷ ቁጭ ብላ እያሰበች ነዉ፡፡ "ማግባት አለበት!" ትላለች፡፡ ይሄን ነገር ስትፈቅድለት
ግን... ራሷን መስዋዕት አድርጋ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ቢኒ ደሃ ነዉ፡፡ አንድ ሚስት እንጂ
ሁለተኛ መደረብ አይችልም ፡፡ ደግሞ ከቢኒ ተለይታ መኖር አትችልም፡፡ ከርሱ ዉጭ
ህይወት የላትም፡፡ በጣም ተጨንቃለች፡፡ ከምንም በላይ ኤዲን የሚያስደስታት ቢኒ ደስ
ብሎት ማየቷ ነዉ፡፡ ምንም ያክል በትዳሩ ደስተኛ ቢሆንም ትዳር ያለ ልጅ ዉበት የለዉምና
እሷን ፈትቶ ሌላ አግብቶ ልጅ መዉለድ እንዳለበት አምናለች፡፡ "ደግሞስ... ፍቅር ማለት
ለምወደዉ ሰዉ ራስን መስዋዕት አድርጎ ደስታን መፍጠር፡፡  አይደል እንዴ ?" እያለች እራሷን
በጥያቄ ታፋጠለች፡፡ ቤት እንደመጣ እነግረዋለሁ፡፡ አግባ እለዋለሁ... ብላ ወሰነች........፡፡
.
ረዲኤት ዛሬም ስለ ቢኒያም ታስባለች፡፡ የሰዉ ባል ልትቀማ፤ የሚያምር ፍቅር ልታደፈርስ
እንደሆነ ስታስበዉ ግን... መልዕክት በመላኳም ትቆጫለች፡፡ ሊቀርብኝ ይገባል፡፡ ቢኒ የኤዲ
ብቻ ነዉ፡፡
ስለዚህ እኔ በመሃላቸዉ መግባት የለብኝም ወደሚለዉ እያመዘነች ነዉ፡፡....ግን ገና
አልወሰነችም፡፡ ምክንያቱም ቢኒን ትወደዋለች መዉደድም ብቻ ሳይሆን በጣም
ታፈቅረዋለች፡፡....



🔻ክፍል 9️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                      
#ክፍል_ 9️⃣

        .... ኤዲ ለቢኒ ካላት ፍቅር  የተነሳ ስታከብረዉ ወደር የላትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ለሱ ንግግር
ቦታ ትሰጣለች፡፡
በእያንዳንዷ ክንዋኔም ላይ የቢኒ ቃል ተቀዳሚ ነዉ፡፡
... ሁለቱም በእኩል ቅጽበት "እ..." ሲሉ... ኤዲ ቀደም ብላ "ወይዬ ቢኒ ምን ልትለኝ ነበር?"
አለችዉ፡፡
ቢኒም "ኤዲዬ የኔ ቆንጆ አንቺ ሁሌም እኔን ታስቀድሚያለሽ፡፡ "የኔ ፍቅር ታዉቃለሃ?"
.....  "ምኑን ነዉ የማዉቀዉ ኤዲዬ?"
.....  "እኔና አንተ ከተጋባን አራተኛ አመታችን ነዉ፡፡"
.....  " እ... በፍቅር ክንፍ አድርገሽኝ ያበድኩልሽ ቀን! ያ ቀን እንዴት ይጠፋኛል ዉዴ!?"
.....  "እሱ አይደለም ፍቅሬ"
.....  "እና ምንድን ነዉ ....?"
.....  "ከተጋባን ቆይተናል ግን እስካሁን...."
...  "ማሬ አታስጨንቂኛ ፕሊስ ንገሪኝ?"
.....  "ቢኒ የኔ ዉድ...."
....  "ወይዬ ኤዲ የኔ ቆንጆ! ... ንገሪኛ!"
.....  "ልጅ ልወልድልህ አልቻልኩም ቢኒ"
ቢኒ በዉስጡ ያለዉን ስሜት ኤዲ አወጣችዉ፡፡ "ሁለታችንም አንድ አይነት ነገር ነበር
የምናስበዉ ማለት ነዉ?" አለ በሆዱ፡፡ ትክክለኛ ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ነዉ የሚቀዱት
ማለት ይሄኔ ነዉ፡፡
ቢኒ ኤዲን ሊጎዳት አልፈለገም....
..... "ኤዲዬ ይሄኮ ታዲያ የፈጣሪ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ፈጣሪ ባለ ጊዜ ትወልጂ ይሆናል፡፡" አላት፡፡
..... " አዎ የኔ ፍቅር ፈጣሪ ካለ እወልድ ይሆናል፡፡ ግን ደግሞ አንተ ከኔ በይበልጥ ልጅ
ማግኘት፤ ዘርህን መተካት ይኖርብሃልኮ ዉዴ!"
..... "እና ምን ላርግ ዉዴ? ልጅ ከመዉለድ በላይ አንቺ ለኔ እንደምታስፈልጊኝ ታዉቂያለሽ፡፡
ስለዚህ ማሬ...."



ረዲኤት ስለ ቢኒ ስታብሰለስል ቆይታ ሲጨንቃት  ጋደም ባለችበት እንቅልፍ ሸለብ አድርጓታል፡፡
እማማ በለጡም የረዲ የሰሞኑን ቅብዥር አላምራቸዉ ቢል ወደ ረዲ የመኝታ ክፍል ገብተዉ
ከጎኗ ቁጭ ከማለታቸዉ ነበር ... ረዲ እንደ ቅብዥር ነገር ጀምሯት "ቢኒ እወድሃለሁ"
የምትለዉ፡፡
እማማ በለጡ በቆሙበት ደርቀዉ ቀሩ፡፡እስከዛሬ ልጃቸውን ምን እዲህ እንፈሚያደርጋት ገባቸው ቢኒ የኤዲ ባል...እንዴት?... እያሉ ብቻቸውን ያወሩ ጀመር፡፡ ምን ይበሉ? ሊቀሰቅሷት አቃታቸዉና
እንደገና መለስ አሉ፡፡ "በአካል ባታገኘዉ እንኳ በህልሟ እስኪ የሷ ይሁን!" እያሉ ይመስላሉ፡፡
እማማ በለጡ በጣም ጥሩ ሴት ናቸዉ፡፡ ልጃቸዉ አንድ ከመሆኗ የተነሳ እንደ እናት ብቻ
ሳይሆን እንደ እህትም፣ እንደ ጓደኛም ሆነዉ ነዉ ያሳደጓት፡፡ ረዲን ዛሬ ጫን ያለዉ ይዟት
እንጂ አንድም ነገር ከእናቷ ደብቃ አታዉቅም፡፡ አሁን ግን ... የሰዉ ባል አፈቀርኩ ብትል
እንኳን ለእናት ለጓደኛም ለመንገር ያሸማቅቃል፡፡
እማማ በለጡ ጉዳቸዉን ሰምተዉ በእጃቸዉ መዳፋ አገጫቸዉን ይዘዉ "ጉድ... ጉድ" እያሉ
ከረዲኤት ክፍል ወጡ፡፡
እማማ በለጡ ከመዉጣታቸዉ ረዲኤት ብርግግ ብላ ስትነሳ ፊቷ በላብ ተዉጧል፡፡ በቅብዥሯ
"እወድሃለሁ" ስትለዉ የነበረዉ ቢኒያም ከአጠገቧ የለም፡፡ የሞባይሏን ሰአት ስታይ ቢኒ
ለስራ የሚወጣበት ሰዓት ደርሷል፡፡ በፍጥነት ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሂዳ እጇ ላይ
ዉሀ በማድረግ ፊቷት ውሃ ረጨት ረጨት አደረገች፡፡ በሷ ሃሳብ መታጠቧ ነበር፡፡ እየሮጠች
ወጣችና በሯ ላይ ቁጭ ብላ እየተቁለጨለጨች የነ ቢኒን ቤት በር በር ታይ ጀመር፡፡
.
....ቢኒ፡ ኤዲ መረበሿን ሲያይ አብሯት እንኳ ባይዉል ቁርስ አብሯት ለመብላት ወስኖ ነበር
ማርፈዱ፡፡ ኤዲ ግን... አዳሯን ሙሉ እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር ስላደረች ንጋቱ ላይ ለብዙ ቀን
እንቅልፍ ያልተኛች በሚመስል መልኩ ለሽሽሽ ብላለች፡፡ ቢኒም ቶሎ እንደማትነሳ
ስለተረዳ ቁርሷን ከአጠገቧ አስቀምጦ በብጣሽ ወረቀት "የኔ ቆንጆ አፈቅርሻለሁ!፡፡ ፈጣሪ
ይጠብቅሽ" የሚል ፅሁፍ አኑሮ ከመዉጣቱ... በሩ ፊት ለፊት ረዲኤትን አያት፡፡
ከግቢ የመዉጫዉን በር ተወና ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት
አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም
የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡
እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡
ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ....
"ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡
እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡


        


🔻ክፍል 1️⃣0️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                      
#ክፍል_ 1️⃣0️⃣

....
ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት
አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም
የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡
እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡
ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ....
"ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡
እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡... እማማ ሚረዱ፤ ኮሽታ ሰምተዉ የሚነቁ በአሁኑ አባባል አራዳ የሚባሉ ሴት ናቸዉ፡፡ እስከዛሬም ልጃቸዉን አላጤኗትም እንጂ ቅዠት ከመስማታቸዉ ቀድመዉ ያዉቁባት ነበር፡፡ ይሄዉ አሁን ደግሞ ስሙ ቢላቸዉ በራቸዉ ስር
መጥቶ ቢኒያም ልጃቸዉን ረድኤትን እያዋራት ነዉ፡፡
..... "ቢኒ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላዉቅም፡፡ ግን... ትቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም አንተን
ላገኝህ አልችልም፡፡ ኤዲንም ላሳዝናት አልፈልግም፡፡" አለችዉ ረዲ
ቢኒም....."ረዲ እሱን ላወራሽ አልነበረም፡፡ በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር
አመጣጤ! በይ ደህና ዋይ" ብሏት መልሷን ሳይሰማ ጥሏት ሄደ፡፡
ረድኤት በህይወቷ እንደዚች ሰዓት የተደሰተችበት ቀን የለም፡፡ ደስታ ቢገል ኑሮ ቢኒ "በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር አመጣጤ" ካላት በኃላ ትንፋሿ ፀጥ ብሎ ትሞት ነበር፡፡ ከበር እስከሚወጣ በአይኗ ከሸኘችዉ ቡኃላ ከተቀመጠችበት ተነስታ መስተዋት ፍለጋ እየሮጠች ስገባ እናቷ የመስኮቱን መስተዋት ከፍተዉ እንደማፅዳት እያደረጉ ነበር፡፡
ደነገጠች፡፡"እማዬ ስናወራ ሰምታን ይሆን እንዴ?" ብላ አሰበች፡፡ የእናቷ ነገር ደስታዋን እንዳያከስምባት ቶሎ ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ መስተዋቱ ፊት ተገተረች፡፡ 'እዉነትም ቆንጆ ነኝ!" ስትል ለራሷ አሰበች፡፡ረዲን በጣም ብዙ ወንዶች ግማሹ ለትዳር፣ ግማሹ ለአዳር፣ ሌላዉ ደግሞ ለፍቅር ጓደኝነት ሲጠይቋት አላማና ኢላማ ያላት ስነ-ስርዓት ያላት ልጅ ስለነበረች ሁሉንም ገፍታ አባራቸዋለች፡፡ ለቁጥር የሚያዳግቱ ብዙ ወንዶች ለዉበቷ ቋምጠዉላታል፤ በጣም ዉብ
ነች፡፡ብዙ ሰዎች የቁንጅናዋን ልክ ለመናገር ቃላት ደርድረዋል፡፡ እሷ ... ግን ለጊዜያዊ ስሜት የምትረታ የዋዛ አልነበረችምና አሻፈረኝ ብላለች፡፡
የቢኒ አንዷ ቃል ግን ዉስጧ ገብቷል፡፡ ልትተወዉ የነበረችዉን ሴት እንደገና የልቧን ፍም ጭሮባታል፡፡ "ቢኒንማ አልተወዉም!!" የረዲኤት ዉሳኔ ነበር፡፡

... ኤዲ ከእንቅልፏ እንደነቃች በባሏ እጅ የተከሸነዉን ጣፋጭ ቁርስ ማጣጣም ይዛለች፡፡
ቁርሷን በልታ ሳጨርስ ተኝታበት ወደነበረዉ አልጋ ዘወር ስትል ከትራሷ ስር ብጣሽ ወረቀት
አየች፡፡ አነሳችዉና ስትገልጠዉ "የኔ ፍቅር አፈቅርሻለሁ፡፡ ፈጣሪ ይጠብቅሽ!" የሚል ፅሁፍ
አነበበች፡፡ ደስታ ልቧን ፈነቀለዉ፡፡ ቢኒ እዉነትም ፍቅር ነዉ፡፡ ቁርስ ሰርቶ አካሏን
ከመጠገኑም በላይ 'አፈቅርሻለሁ' ብሎ የመንፈስ ምግብ ሰጣት፡፡ ባዲስ ንጋት ከቁርስ ጋር ፍቅር መገባት፡፡ኤዲ አዳሯን እንቅልፍ ማጣቷን ሁሉ እረሳችዉ፡፡ በደስታ ተፍነከነከች፤ በሀሴት ጮቤ
እረገጠች፡፡ በዚህ ልዩ ጧት፤ በዚህ ልዩ ቀን የጧቷን ፀሐይ ልትሻማ ከቤቷ ወጥታ ለፀሐይ ጀርባዋን ሰጥታ ቁጭ አለች፡፡
...... ረድኤት ቆንጆ መባሏ ሳያንስ ሌላ ዉበት፤ ሌላ ድምቀት ተላብሳ፤ ንጋቷን በፍቅር አድሳ እሷም እንደ ኤዲ የፀሐይን ሙቀት ልትኮመኩም ወጣች፡፡
ከመዉጣቷ ኤዲን ስላየቻት ወደሷ ሄደች፡፡ ረድኤት ላይ ዉበት ጎልቷል፤ ኤዲ ላይ ደግሞ ደስታ ነግሷል፡፡ ሁለቱም ለጨለማ ድምቀት እንደሆነችዉ ጨረቃ ደምቀዋል፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ
ቡኃላ ኤዲ፡ ረዲን...
..... "ዛሬ ወደየት ልትሄጂ ነዉ ባክሽ ተሽቀርቅረሻልሳ" አለቻት



🔻ክፍል  1️⃣1️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM