የልብ ቋንቋ
153K subscribers
48 photos
2 videos
228 links
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀

⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE

Contact @ethio1226
Download Telegram
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

                       #ክፍል_
2️⃣1️⃣


...
የመቅደስ ድንጋጤ አንደበቷን አሰረው ሰውነቷን አደነዘዘው የምትሆነው ግራ ገባት ብቻ ደጋግማ ጌዲ ጌዲ ትላለች ጌዲዮ ግን አውቆ ስለነበር መጨረሻ ላይ በሳቅ ተንፈራፈረ ወይኔ መቅዲ ብሞትም አትጮሂም ማለት ነው እያለ የማያቋርጠውን ሳቁን ይስቅ ጀመር....በድንጋጤ ብቻ ቢሞት መቅደስ ሞታ ነበር ሞቶ መመለስም እንዲህ ከሆነ መቅደስ ግማሽ መንገድ ሄዳ ነው የመጣችው...እንደምንም እራሷን አረጋግታ እውን ቀልድ መሆኑ ሲገባት ንዴት ፊቷን በርበሬ አለበሰው...እሱ ግን አሁንም ይስቅ ነበር ቀልደህ ልብህ ወልቋል አለችው ጌዲም እየሳቀ እንዲህ ልበቢስ መሆንሽን ባቅ ኖሮኮ እንዲህ አይነት ቀልድ አልቀልድም ነበር ሲላት መቅደስ ቦርሳዋን አንስታ ያዘዘችውም ቁርስ ሳይመጣ ጥላው ወጣች እሱም አረ ቁርሱ ቢቀር ልልበስና አብረን እኔዳለን አላት እሷ ግን እንዳልሰማች ሆና ከንዴቷ ብዛት መሬቱን አጥብቃ እየረገጠች ጥላው ሄደች።..ከዛም ቡሀላ ደጋግሞ ብዙ ጊዜ ቢደውልላትም ልታናግረው ፍቃደኛ አልሆነችም በመጨረሻም እንደተቀየመችውና እንደማታነሳው ሲገባው ወይንሸት ጋር ደወለ ወይናም ገና ከማንሳቷ አንተ ልጅቱን ምን አርገሀት ነው እንዲህ አደንዝዘህ የላካት ነው ወይስ ድንግልናዋን ዛሬ ነው የወሰድከው ብላ እየሳቀች ጠየቀችው ጌድዮም ባማረው ሳቁ አጅቦ እሱንማ እኮ ቆየሁ ከተረከብኩት ባይሆን ትዝታው ይሆናል አላት ወይናም ሳቁን ተቀብላ እየሳቀች ትዝታ እንዲህ ቢያረግማ እኔ በሽተኛ እሆን ነበር አለችው እሱም ወይናዬ ባክሽ በሆነ ነገር አስቀይሚያት እኮ ነው ስልኳንም አላነሳም አለችኝ በማሪያም አገናኚኝ አላት እሷም ውይ ጌዲዬ ገና ስወጣ ነው የደወልክልኝ አሁን ደግሞ ላይብረሪ ልገባ ነው ባይሆን ብርሀንና ሰአዳ ዶርም ስላሉ አንድኛቸው ጋር ደውል አለችው

እሱም መልሶ ሰአዳ ጋር ደወለና እንድታገናኘው ጠየቃት መቅደስ ግን አላናግረውም ስትል ብርሀን ለመነቻትና እሺ አለች ስልኩንም ተቀብላ ምን ፈለክ አለችው ጌዲም መቅዲ እግዚያብሄርን እንዲህ ያስከፋሻል አላልኩም ይቅርታ አርጊልኝ አላት ብዙም ካባበላት ቡሀላ ይቅርታ አረገችለትና ሁሌ የሚገናኙበት መናፈሻ እንደሚጠብቃት ነገራት.....
የሚገርም ነው ጌዲዮና መቅደስ ፍቅረኛሞች ከሆኑ በኋላ ብዙ ሴቶች ጌዲዮን ለፍቅር ጠይቀውታል በተለይ አደራ የተባለችው የክፍሉ ተማሪ ተፈታትናዋለች ይኸው ዛሬም ሆን ብላ መቅደስን እየጠበቀ የተቀመጠበት መናፈሻ ድረስ ሄዳ አጠገቡ ተቀመጠች ብዙ ብሏት እንቢ ስላለችው ዞርበይም አላላትም ዝም ብሏት ተቀመጠ እሷም ጌዲ ሰላም ነው አለችው እሱም እግዚያብሄር ይመስገን አላት ይቅርታ መቅደስን እየጠበክ እንደሆነ አውቃለሁ ግን በጣም ስለናፈከኝ ነው የመጣሁት አለች ጌዲዮም በግርምት ፈገግ ብሎ እኔ ናፍቄሽ አላት እሷም አዎ ብላ ተጠግታ እጁን ያዘችው መቅደስ ፊትለፊት አየቻቸው እንዳየቻቸውም ቆመች
ጌዲዮም ቀስ ብሎ እራሱን ያዘ ከዛም ሰውነቱን አንቀጠቀጠው በተቀመጠበት ወድቆ ሲንፈራፈር አደራ ሰቀጠጣት እንኳን ልታነሳው የጨበጡት እጆቿን ተፀይፋ እየጠራረገች ጥላው እየበረረች ሄደች መቅደስ ግን ከመቅፅበት እየሮጠች አጠገቡ ደርሳ ስታቅፈው እየሳቀ ነቃና ወይ የዘንድሮ ፍቅር አለ መቅደስ በድጋሚ ተናደደች ምን ለማለት ነው አለችው እሱ እንዴ እሰቢው ጤነኛ እያለሁ አፈቀርኩክ ናፈከኝ አበድኩልህ ስትል የነበረችው ልጅ ታምሜ ስወድቅ ግን ተፀይፋ ጥላኝ ሄደች ታዲያ ይሄ ፍቅር ነው መቅዲዬ ካፈቀሩ አይቀር እኮ ልክ እንዳንቺ ነው ከነ ሙሉ ማንነት የኔ እናት አንቺኮ ትለያለሽ እኔ ማለት እኮ..... በጆቹ ጉንጮቿን ጨብጦ አይን አይኗን እያየ ቀጠለ....ከድለኞች መሀል አንዱ ነኝ አንቺን የሰጠኝን ፈጣሪ በምን ቃል እንደማመሰግነው አላውቅም ብሎ ጥብቅ አርጎ ግንባሯን ስሞ አቀፋት.....መቅደስም
ጌዲዬ እኔም እኮ ያንተ በመሆኔ እድለኛ ነኝ ደግሞ ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ አትቀልድ እኔኮ ህመምክ ያስፈራኛል አለችው እሱም ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ እንደማይቀልድ በፈጣሪ ስም ምሎ ቃል ገባላት ....እንዲህ እንዲህ እያሉ ደሞ ሌላ ወራቶች አሳለፉ

ፈተና እየተፈተኑ ስለነበር አሁን በብዛት ጥናት ላይ ናቸው ሰሞኑን ግን ጌዲዮ በጣም እያመመው ነው ቢሆንም ጌዲዮ ህልሙን ለማሳካት ጠንክሮ እየተማረ ነው ዛሬ ደግሞ ከመቅደስ ጋር አብረው ሁሌ የሚያጠኑበት ጫካ ሄደው እያጠኑ ነው ጥናታቸውንም እንደጨረሱ ጌዲዮ የመቅደስ እግር ላይ ተኝቶ እንደለመደው አይናይኗን እያየ ምን እንደናፈቀኝ ታውቂያለሽ አላት እሷም ምንድነው አለችው የምመረቅበት ቀን አላት ውይ አሁንማኮ ጨረስክ ግማሽ አመት እኮ ነው የቀረህ ግን ለምን ጓጓህ ጌድዬ አለችው እንዴ መቅዲ የማዬን ደስታ ለማየት ነዋ የኔን አለም የምታሳየኝ ተምረህ ተመርቀህ ነው ትለኝ ነበር ታዲያ አለሟን ለማሳየት ለምን አልጓጓም አላት መቅደስም ፈገግ ብላ እሱማ መመረቅክ የኔም አለም እኮ ነው ስትለው ግን ምንድነው ስጦታዬ አላት እሷም ያገር ቀይ አበባ ተሸክሜ እሰጥሀለሁ አለችው በቃ አላት እህ ብችልማ ቀይ ምንጣፍም ባስነጥፍልህ ደስ ይለኛል አለችው ጌዲዮም ስቆ ሀሳብሽም በቂዬ ነው የኔ እናት ደግሞ የዛሬ አመት አንቺ ስትመረቂ እኔም በተራዬ በዛ ሁሉ ህዝብ ፊት ተንበርክኬ የኔ እመቤት አግቢኝና የፍቅርሽ ታዛዥ ባሪያሽ ሆኜ እድሜ ዘመኔን ልገዛልሽ እልሻለሁ

አላት...መቅደስ ዛሬ ላይ ሆና የቀጣዩን አመት ምርቃቷን ቀን በምትወድደውና በምታፈቅረው የጌዲዮ የጋብቻ ጥያቄ አጣምራ ደስታዋን በህሊናዋ ሳለችው...



🔻ክፍል 2️⃣2️⃣ 1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

                       #ክፍል_
2️⃣2️⃣


...
​​ከዛም ጌዲዬ ጊዜ ፊልም ቢሆን አሳልፌ የምርቃቴ ቀን ላይ አርጌው ነበር ብላ ጎንበስ ብላ በስስት ከንፈሩን ሳመችው ደሞኮ ጌዲ የምርቃትህ ቀን መጀመሪያ እኛ ቤት ነው የምንሄደው አለችው ለምን አላት እንዴ እማዬ እኮ እደግሳለሁ ብላለች ከዛም የማዬ ግብዣ እንዳለቀ ብሩክ(ታላቅ ወንድሟ) ይዞን ቀጥታ እናንተ ቤት አለችው ጌዲዮ ደስታው ተደማምሮ እቅፍ አረጋት
ከዛም ቀጥታ ግቢ ሄዱ እንደገቡም ትንሽ እንደተራመዱ ጌዲዮ አካባቢው ሁሉ ጨለመበት መቅደስን ጥብቅ አርጎ ያዛትና መቅዲ እራሴን አላት እሷም ደንግጣ ምን ሆንክብኝ አለችው እኔንጃ እራሴን መቅዲዬ ያዢኝ ሁሉም ጨለመብኝ አላት መቅደስ ላንዴ አይኗ በንባ ተሞላ እኔን ምንም አትሆንም ፀሀዩ ይሆናል አለችው ከዛም እንደምንም ብላ ወደጥግ አስቀመጠችውና ክብሪት ልትፈልግ ተነስታ ልትሄድ እጇን ከጁ ልታስለቅቅ ስትል መቅዲ የትም አትሂጂ ደግፊኝ እራሴ ሊፈርስ ነው ብሎ በፍርሀት አጥብቆ ያዛት ምንም ጌዲዮ ሁሌ ቢወድቅም እንዲህ ብሏት ግን አያውቅም አቅፋው ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ሳቅና ደስታቸው ላንዴ በሀዘን ተቀየረ ጌዲዮ እንደምንም ፊቷን ፈልጎ እንባዋን እየጠረገላት መቅዲዬ ጠንካራ ሁኚ እኔኮ ሁሉም ጨለመብኝ አላት የሱም እንባ እየወረደ መቅደስ ላንዴ በለቅሶ ሲቃ ሲጥ አለች ወዲያው የግቢው ሰው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተሰበሰበ ጌዲዮም ወዲያው እራሱን ሳተ የሷም ሆነ የሱ ጓደኞች እያለቀሱ ነበር አብዛኞቹ ግን እንዳለፈው አወዳደቁ የወደቀ መስሏቸው ይነቃል እያሉ ነበር ቢሆንም ለተከቴይ ሶስት ሰአት ቢጠብቁትም ሊነቃ አልቻለም መቅደስ ለሁለት ተይዛለች ብቻ እየቀለደብኝ ነው ውሸቱን ነው ንቃ በሉት ትላለች እሱ ግን ቀልዱን አልነበረም በመጨረሻም አንቡላንስ መጥቶ ይዞት ሄደ አንቡላንሱ እያበረረ ጅማ ጠቅላላ ሆስፒታል አደረሳቸው ወዲያው ዶክተሮቹ ተባብረው ድንገተኛ ክፍል አስገቡት አብረውት የመጡት መቅደስ ሰአዳና በለጠው ብቻ ነበሩ ለነገሩ መቅደስ አለች አትባልም እሷም ለህክምና አልጋ መያዝ እንጂ የቀራት ደንዝዛለች ብቻ በር ላይ አንዴ ቁጭ አንዴ ብድግ እያለች ነው ሌሎቹም ጓደኞቻቸው ተከታትለው እየሮጡ ሴክሬተሪዋን ጠይቀው ያሉበት ክፍል እየሮጡ ደረሱ እንደደረሱም እንዴት ነው አሁን አሏቸው በለጠውም ዶክተሮቹ ገና አልወጡም አላቸው ከዛ ሁሉም በጭንቀት ተከበው መጠበቅ ጀመሩ.......

....ከዛም ቢያንስ ካንድ ሰአት ቆይታ ቡሀላ ዶክተሮቹ ወጡ እንደወጡም ሁሉም ተሯሩጠው ከበቡዋቸው ዶክተር እንዴት ነው አሉ አንዱ ዶክተር ሲቀር ሌሎቹ ፊታቸው ሳይፈታ ጥለዋቸው ሄዱ ሁሉም ፈሩ መቅደስማ አንድኛዋን ተዝለፈለፈች ዶክተሩ ቁና ተነፈሰና ሊያወራ ሲል መቅደስ ዶክተር በፈጠረህ ክፉውን እንዳትነግረኝ ሞተ እንዳትለኝ ስትለው ወይንሸት አረ መቅደስ ሶስት ጊዜ አማትቢ አለቻት ዶክተሩም እ.እ መኖሩን አለ እኛም የተቻለንን እርዳታ አርገንለታል ግን አሁንም ሁሉም ግን ምን አሉት አልነቃም የሚያስፈልገውን ህክምና ሰተነዋል ተራ በተራ እየገባችሁ ማየት ትችላላችሁ ከሁለት ሰው በላይ ግን ውስጥ መቀመጥ አይቻልም ሌላው ከታማሚው ጋር ቀረቤታ ያላችሁ ክፍል ቁጥር 24 ቢሮ መታችሁ አናግሩኝ ብሏቸው ሄደ
.መቅደስ ቀድማ ገባች ስታየው ይባስ ሲጥ እስክትል ድረስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲዮ ከወገቡ በላይ ብዙ ገመዶች ተጠላልፈውበታል አፍና አፍንጫውም በኦክሲጅን መስጫ ታፍነዋል እጆቹም ተዘርግተው አይንቀሳቀሱም ሳቁ ጠፍቶ ከንፈሮቹ ተከድነዋን የሚያምሩት መቅደስን አይተው የማይጠግቡት አይኖቹም ተከድነዋል እጁን ጭምቅ አርጋ ይዛ እየሳመችው ጌዲዬ ፈተና እኮ አላለቀም ደሞስ ላይብረሪ እንገባለን ተባብለን አልነበር ለምን አትነሳነሳም እንሂዳ ጌዲ የው ውሸት አያምርብህም በኔ አትጨክንማ ተው ተነስ እያለች ለማይሰማት ጌዲ ብዙ አወራችው መቆየቷን የተረዱት ጓደኞቻቸው እዛው እያለች እየገቡ ጌዲዮን እግዚያብሄር ይማርህ እያሉ እሷንም እያፅናኑ ወተው ደጅ ላይ ተቀመጡ ከዛም በለጠውና መቅደስ ዶክተሩ ቢሮ ሄዱ..ሲገቡም እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ከዛም በለጠው ዶክተር ችግር አለ እንዴ ብሎ ጠየቀው ዶክተሩም እየውላችሁ አሁን እንዲህ ነው ብሎ መናገር ይከብደኛል ምክንያቱም ሙሉ ምርመራ መደረግ አለበት ላሁን ግን ጥያቄዎችን ልጠይቃችሁ ታማሚው ከዚህ በፊት እራሱን ይስት ነበር??...አዎ ግን እንደዛሬው ሆኖ አያውቅም ህክምናስ ተደርጎለት ያውቃል?? መቅደስ ይህን ጥያቄ ለመመለስ አንደበቷን ፈታች ስንቴ እንደለመንኩት እኮ ይኸው ይሄ ቀን እንዳይመጣ ፈርቼ ነበር ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች በለጠው ደግፏት ነበረ ስታለቅስ ግን አቅፎ አባበላት ዶክተሩም ቀጠለ እሺ ያለፈው አልፏል አሁን ማሰብ ያለብን ስለወደፊቱ ነው እናም ለካርድ ላልጋ እንዲሁም ለግዜው ህክምና የሚውል 7ሺ ብር ማስያዝ ይጠበቅባችኋል አላቸው ከዛም እንደወጡ በለጠው....መቅዲ እጄ ላይ ምንም ሳንቲም የለም ምን ይሻላል አላት አታስብ እቤት እደውላለሁ ብላ አባቷ ጋር ደወለች
ሄ..ሎ..ሄ...ሎ አባ ወዬ መቅዲ ደና አደለሽም እንዴ አዎ አባ ጌዲን አሞት ሆስፒታል ነን ይሄን ያክል አዎ አምስት ሰአት ሊሞላው ነው እራሱን ከሳተ ግን አልነቃም አለችው አሁንም እያለቀሰች ነው አባቷም እራሱን ይዞ በቃ አይዞሽ ምንም አይሆንም አሁን ይነቃል ደሞ ሁላችንም ስራ ነን እህትሽ ግን እረፍት ላይ ስለሆነች አሁን እልካታለሁ እሺ እሺ አባ ብትችል
ግን አሁን 7ሺ ላክልኝ አረ እልክልሻለሁ ምንም ችግር የለም ብቻ አንቺ እራስሽን አረጋጊ እሺ አባ አመሰግናለሁ..ጌዲዮ ይነቃል እየተባለ ሲጠበቅ ሳምንት ሞላው የጅማ ጠቅሌ ሆስፒታል ዶክተሮችም የጌዲዮ ነገር ካቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ወደ አ.አ ተክለ ሀይማኖት አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ተፃፈለትና ከጅማ ተነስተው አ.አ ገቡ እስካሁን ያልተነገራቸው የጌዲዮ እናትም በጣም እየደወሉ ልጄስ እያሉ ሲጠይቁ በብዙ ምክንያት መታመሙን ቢደብቋቸውም የወለደ አንጀት ነውና...



🔻ክፍል 2️⃣3️⃣ 1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ቤተሰቦች እንዴት አመሻችሁ ይቅርታ ስለዘገየን ክፍል 23 ከ 5 ደቂቃ በዃላ ይለቀቃል
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

                       #ክፍል_
2️⃣3️⃣



...🖌ጌዲ መታመሙን ተረድተው አጥብቀው
ሲለምኑ ግድ ሆነባቸውና ዛሬ እውነቱን ተናገሩአይ እናት በሞት መሀል ሆነው ነው አ.አ የደረሱት ያው እነ ብርሀን በለጠው ወይና ሰአዳ እንዱሁም ሌሎቹም መቅደስ ስትቀር ነገ ፈተና ስላለ ተመልሰው ጅማ ሄደዋል መቅደስንም ቢሆን ቤተሰቦቿ እንዲሁም የጌዲ እናት ሄዳ ፈተናዋን እንድትፈተን እየለመኗት ነው እሷ ግን ካልነቃ አልሄድም አለቻቸው የጌዲዮ እናት ለቅሷቸው መራራ ነው የመንገዱ ድካም ሳይሰማቸው ሰውነታቸው መዛሉ ሳይሰማቸው ልጃቸው እግር ላይ ተደፍተው አሁንም መራራ እንባ እያነቡ ነው መቅደስማ እንባዋ አልቆ ፈዛለች
ቡሀላም እንደምንም ለምነው የመቅደስ ቤተሰቦች የጌዲዮን እናት ይዘው እቤት ሄዱ መቅደስ አሁንም አልጋው ላይ በግንባሯ ተደፍታ እያንቀላፋች ነው የሆነ ሰአት ላይ የጌዲዮ ጣቶች ሲንቀሳቀሱ ተሰማትና ከህልሟ እንደነቃች ሆና ባተተች ስታየው አይኖቹ ግራና ቀኝ እያዩ ነው ደስታዋ አንቋት ላንዴ ጮኸች ተጣድፋ ሄዳ ግንባሩን ደጋግማ ሳመችው ከዛም ጌዲዬ ነገ እኮ ፈተና ነው አብረን እኔዳለን አይደል አለችው መንቃቱን ከነርስ የሰሙት ዶክተሮች እየተሯሯጡ መጡ ወዲያው መቅደስ አያችሁ አይደል
.......መቅደስና ጌዲዮ በብዙ ፈተና ሶስት አመት በፍቅር አሳልፈው አራተኛው አመት ግን አስጊ ሆኗል ጌዲዮ የጓጓለትን ያምስተኛ አመት ትምህርቱን መጨረስ አልቻለም ዋና የሚባለውም ፈተና አምልጦታል ከሆስፒታ ወጥቶ እንዲፈተን መቅደስ ዶክተሩን ብትለምነውም ለሂወቱ አስጊ ስለሆነ እንደማይወጣ ነግሯት እሷም አልፈተንም ብትልም ጌዲዮ በፍቅሩ ለምኗት ፈተናዋን ለመፈተን ጅማ ተመልሳ ዛሬ ወደ አ.አ መጥታለች ሙሉ የህክምናውን ወጪ ችለው እያስታመሙት ያሉት የመቅደስ ቤተሰቦች ናቸው እናቱም ከክፍለ ሀገር መጥተው አብረውት ነው ያሉት ጌዲዮ ከራሱ በላይ የናቱን ህልም አለማሳካቱ ተስፋ አስቆርጦታል መቅደስም በሱ መታመም ሌት ተቀን እያለቀሰች በድን ብትሆንም ዛሬም ትምህርቱን ቀጥሎ እንደሚመረቅ ተስፋ ትሰጠዋለች.......

......ዛሬ ውጤትህ ይመጣል ስለዚህ ለዩኒቨርስቲው አሳውቀን ብትዘገይም ትፈተናለህ እሪሰርችህንም ቢሆን ትጨርሰዋለህ አለችው መቅደስ የፍርሀትና የደስታ ስሜት እየታየባት የጌዲዮ እናትም እንዳፍሽ ያርገው አሏት የሱዋም አባት እንደዛው ጌዲዮ ግን ውስጡ ጤነኝነት እየተሰማው ስላልሆነ የሚመጣው ውጤት ጥሩ ይሆናል ብሎ መገመት ተስኖታል ብቻ ባጠቃላይ አፋቸው መልካም ቢናገርም ውስጣቸው ፈርቷል ሰአቱ ሲደርስም መቅደስና አባቷ ውጤቱን ለመስማት የዶክተሩ ቢሮ ሄዱ እንዲቀመጡም ከጋበዛቸው ቡሀላ ዶክተሩ ከምን መጀመር እንዳለበት ግራ ገብቶት አይን አይናቸውን ያያቸው ጀመር ውስጣቸው ይበልጥ ተረበሸ ዶክተር ችግር አለ እንዴ አሉት...




🔻ክፍል 2️⃣4️⃣ 1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️የልቤ ትርታ❤️❤️

    


የልቤ ትርታ ክፍል 2️⃣4️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

                       #ክፍል_
2️⃣4️⃣


...🖌እየውላቹ ይህ ዜና ለናንተ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ ግን ግዴታ መናገር ስላለብኝ ስሙኝ ጌዲዮ የጭንቅላት እጢ ታማሚ ነው መቅደስ አፏን ይዛ እየተንቀጠቀጠች ምን አለች አዎ ህክምናውን በጊዜ ጀምሮ መዳኒት ስላልወሰደም በሂወት የመኖር ጊዜውን አጥቦታል መቅደስም ሆነች አባቷ እንባቸው ድንገት እንደሚጥል በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ዱብ ዱብ ይል ጀመር መቅደስ በልህ ድምጿን ከፍ አድርጋ እና ይሞታል ልትለኝ ነው አለችው ዶክተሩም አላልኩም የምትችሉት ከሆነ አንድ እድል አላችሁ አላቸው አባቷ እንደምንም አረጋግቷት ምንድነው ንገረን ብቻ ጌዲዮ ይዳን እንጂ የሆነውን ይሁን ለመፈፀም ዝግጁ ነን አሉ ባስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት መቅደስ አይሆንም ብላ ይበልጥ ጮኸች ችግሯ ህመሟ ቢገባውም መረጋጋት ባለመቻሏ ዶክተሩ ተናደደ መቅደስ አዳምጪኝ ቀዶ ጥገናው እዚህ ሀገር አይሰጥም ይህ ማለት በዚህ አራት ወር ውስጥ ካገር ወጥቶ ቀዶ ጥገናውን ካላደረገ በሂወት መኖሩ አስጊ ነው ለህክምናው ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብሎ ሃሳቡን በቁጣ ገልፆ ቁና ተንፍሶ ላንዴ ዝም አለ መቅደስና አባቷም በህልማቸው እስኪመስላቸው ደርቀው ቀሩ ምንም ሳይናገሩም ቢሮውን ለቀው ወጡ..........

......ከወጡ ቡሀላ መቅደስ ተዝለፍልፋ ወደቀች ነርሶችም ተሯሩጠው አንስተው አስተኟት ስትነቃም ሁሉም ቤተሰቦቿ ተሰብስበው ነበር አባቷ ነግሯቸው ስለነበር ሁሉም አይናቸው በንባ ብዛት በርበሬ መስሎ ነበር እማ ሁለት ሚሊዮን ያስፈልጋል አሉ እኮ አለቻት የቤተሰቦቿን አይን አይን እያየች እህቷም እሷን ለማፅናናት ያንቺ እንዲህ መሆን እኮ ብር አይሆንም ይልቅ ብሩን እንዴት ማግኘት እንዳለብን ብናስብ ነው የሚሻለው ስትል እንዴ ከየት ነው የሚመጣው አለች መቅደስ ቀጥሎም ቅብጥብጡ ወንድሟ ሲስቱ ተነካሽ እንዴ ሁለት መቶ ሺ ማግኘት ከባድ በሆነበት ሀገር እንዴት ብለሽ ነው ሳይጨርሰው የሁላቸውም ታላቅ የሆነው በረከት ከየትም ብለን አግኝተን መታከም አለበት እናትየዋም አዎ ቤታችንንም ቢሆን ሸጠን እናሳክመዋለን ማሟያ ደግሞ ሁላችንም አካውንት ያለውን ብር እናወጣለን ካልሞላም ብድር አናጣም የሚል ተስፋ ለመቅደስ ሰተዋት ከዛን ቀን ጀምሮ በየፊናቸው ብሩን ማፈላለግ ጀመሩ ብዙ ወጪ ስላወጡ የሁሉም አካውንት ውስጥ የተገኘው ብር ስድስት መቶ ሺ ብቻ ነበር ቤቱም ያሰቡትን ብር ሊያወጣ አልቻለም........

.........ሌላ ህመም እንዳይሆንበት ስለፈሩ ነገሩን ለጌዲዮ እስካሁን አልነገሩትም እናቱ ግን ቢሰሙም ደጀ ሰላም እየሄዱ ደጅ ከመፅናት ፈጣሪን ከመለመን ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም ዘወትር የመቅደስን ቤተሰቦች ሲያዩ እንዲህም አለ ወይ ይላሉ ጌዲዮንን ለማሳደግ ያዩትን መከራ እሳቸውና ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው እንኳን የባለቤታቸው ዘመዶች የገዛ ቤተሰቦቻቸውም ሰላምታ ሰተዋቸው እንኳን አያውቁም የጌዲዮ እናት ያለፉትን አመታት ሲያስታውሱ ደም እንባ ያለቅሳሉ ቢሆንም ፈጣሪ እንደሰው አይደለም ይኸው እነመቅደስን ሰጣቸው እውነት በዚህ ሰአት ብቸኛ ቢሆኑ ኖሮ ጌዲዮ ነብሱ ባልተረፈች ነበር ግን ሳይደግስ አይጣላም ይባል የለ..........

.......ግን ምንም እንዳሰቡት ገንዘቡን ማግኘት አልቻሉም ቤቱንም የሚገዛ አጡ ቢያገኙም የሚጠሩላቸው ዋጋ ለቤቱም ለህክምናውም አይመጥንም በቲቪና በራዲዮንም ማስታወቂያ ሊያሰሩ ቢጠይቁም የጠየቋቸው ገንዘብ ከባድ ነበር በዛላይ ዶክተሩ ያለው ግዜ አጭር ስለሆነ በፍጥነት ፕሮሰስ መጀመር እንዳለበት እየነገራቸው ነው አሁንማ ሁሉም ተስፋ ቆርጠው የሚገቡበት ጠፍቷቸው ወደፈጣሪ እግዚኦ እያሉ ነው........

.........ሁኔታቸው ግራ ያጋባው ጌዲዮ ቅብጥብጡን ቅዱስ ብቻውን ሲያገኘው ቅዱሴ አለው ወዬ ጌዲ አለው የህክምናውን ውጤት ንገሩኝ ስላቸው ደና ነው አሉኝ ደና ከሆንኩ ለምን አልወጣም ስላቸው አይ ትወጣለህ ይሉኛል ሰሞኑን ደግሞ ሁላችሁም ተረብሻችኋል ምን ሆናችሁ ነው በጭንቀት ማለቄ እኮ ነው ሲለው ያው ቅዱስ እስካሁንም ያላወራው አፉን ይዘውት እንጂ ወሬ የሚባል አይደብቅም እናም ምን ባክህ የጭንቅላት እጢ አለበት ውጪ ሄዶ መታከም አለበት ለዛ ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብለውን ተፍ ተፍ እያልን ነው ብሎ ካልታከመ መሞቱ እንደማይቀርም ፍርጥርጥ አርጎ ነገረው ጌዲዮ ተስፋ ቆርጦ እና እሞታለሁ አለው አረ ላሽ ትታከማለህ ደሞ ቤታችን ሊሸጥ እየተስማማ ስለሆነ እግዚያብሄር ከረዳን ብሩ ይገኛል ጌዲዮ ከመቅፅበት ህመሙ ተነሳበት...



🔻ክፍል 2️⃣5️⃣ 1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️የልቤ ትርታ❤️❤️

    


የልቤ ትርታ ክፍል 2️⃣5️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

                       #ክፍል_
2️⃣5️⃣


...🖌ወዲያው ዶክተሮቹ ተሯሩጠው ህክምና አደረጉለት ብዙም
ሳትቆይ መቅደስ መጣች መታመሙን ስታይ ወዲያው ቅዱስ
እንደነገረው ገባትና አንተ ነገርከዋ አለችው ወንድሟ ቅዱስም
መቅዲ ሙች ጠይቆኝ ነው ሲላት አረ ነው እንዴ ድሮም
ጥፋተኛዋ እኔ ነኝ አንተን ሰው ብዬ አምኜህ መሄዴ አሁን ላባ
ሳልናገር ቀጥ ብለህ ውጣ አረ መቅዲ በጥፊ ያላልኩህም
ታላቄ ስለሆንክ ነው ቆይ ቢሞትስ አታስብም እንዴ ስትለው እሺ
ይቅርታ አርጊልኝ ሁለተኛ አይደግመኝም አላት ሁሌ እንዲህ
ትላለህ ግን ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነህ ስትለው እንደምንም
አግባብቷት ይቅርታዋን አገኘ....
......ጌዲዮ ሲነቃ መቅደስ እጆቹን ተንተርሳ ተኝታ ነበር ከዛም
እጁ ሲንቀሳቀስ ነቃች አይኖቿን በንባ ሞልታ ጌዲዬ ደናነህ
ስትለው መቅዲ እሞታለኋ አላት መቅደስ ደንዝዛ ማነው ያለው
ደሞስ ቢሉስ ሰው ፈጣሪ ነው እንዴ አትሞትም ተጋብተን ልጆች
ወልደን አርጅተን ነው የምንሞተው ጌዲዬ ትተኸኝ አትሞትም
ብላ እያለቀስች ፊቱን እየተሽከረከረች ሳመችው ጌዲዮ አለቀሰ
መቅዲ ታቂያለሽ ሁሌ ከንቅልፌ ስነሳ እንደሚጥለኝ
እንደምወድቅ አቃለሁ ግን አንድም ቀን እንኳን እሞታለሁ ብዬ
አስቤ አላውቅም መቅደስ ተስፋዋ ተሟጦ ጮኸችበት ጌዲዮ
አትሞትም አትሞትም ብላ እያለቀስች ትታው ወጣች........
.......ወዲያውም ባስ ይዛ ቀጥታ ጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው
አስተዳዳሪ የዲን ቢሮ ሄደች እንባዋ ያለማቋረጥ ይፈስ ነበር
ሰውነቷ ከስቶ አይኗ ጎርጉዶ ጉንጯ ሟምቶ በተስፋ ማጣት
ተጎሳቁላ ጭራሽ መቅደስ አትመስልም አስተዳዳሪው ደንግጦ
መቅደስ አላት አዎ መቅደስ ነኝ የኔ እንደዚህ መሆን ገረመህ
አዎ ሊገርምህ ይችላል ምክንያቱም አባይን ያላየ ምንጭ
አመሰገነ ጌዲን አላያችሁትማ ካልጋ ተጣብቆ ሞቱን
እየተጠባበቀ ነው አያችሁ የዚህን ዩኒቨርስቲ ስም አራት አመት
ሙሉ አስጠራ ዘንድሮ በመመረቂያው ሲጠፋ ግን ምን ሆኖ ነው
እንኳን አላላችሁትም እሱ ባመጣው ውጤት ለስማችሁ
ለማስጨብጨብ ግን አንደኞች ናችሁ አስተዳዳሪው እንደምንም
አረጋግተዋት ስለተፈጠረው ነገር ለመረዳት ጠየቋት እሷም
ሁኔታውን በሙሉ በዝርዝር ነገረቸው ከዛም የዩኒቨርሲቲው
ኮሚቴዎች ሰብስበው መልስ እንደሚሰጧት ነግረዋት ወጣች
ስትወጣ ወይንሸትና በለጠው አንድላይ እየሄዱ አገኟት
ስለጌዲዮ ሲጠይቋት ሁሉንም ነገረቻቸው ከዛም ተመልሳ አ.አ
መጣች.................
...........ከዛም ጉዋደኞቻቸው እንዳቅማቸው ገንዘብ ማሰባሰብ
ጀመሩ የዩንቨሪስቲው አስተዳዳሪ እንዳሉት ተሰብስበው አንድ
ሀሳብ ላይ በመድረስ ዩኒቨርስቲው ማስታወቂያ ለቀቀ በዚህም
የተነሳ ቤታቸውም ሳይሸጥ ሌላም ከባድ ወጪ ሳያወጡ
የጌዲዮን ሙሉ ህክምና ወጪ የሚችል እስፖንሰር ተገኘ........
......ወዲያውም መቅደስ ጋር ተደውሎ የምስራቹ ተነገራት
ሁሉም ተስፋ በቆረጠበት ሰአት አዲስ ተስፋ በእውነት ደግማ
የተወለደች ያክል ነው የተሰማት ደስታዋንም ለሁሉም አጋርታ
አንድ ላይ ጮቤ እረገጡ ....።
......ዶክተሩም ጋር ሄዳ ገንዘቡ ተገኘ ይድናል አይደል አለችው
መቅደስ ይድናል ብዬ ተስፋ እንጂ እውነታውን ልነግርሽ
አልችልም ምክንያቱም ጌዲዮ የመጨረሻ ከፍተኛውን ቀዶ ጥገና
ነው የሚያደርገው ለዚም ካስር ወር እስከ አንድ አመት
በህክምና ሊቆይ ይችላል አላት የዶክተሩ ንግግር ደስታዋን
ቢያደፈርሰውም ለዚህ ያበቃን ፈጣሪ ነገንም አይጥለንም ብላ
ተስፋዋን ፈጣሪን አደረገች......
አብሮት ለማስታመም ማን መሄድ እንዳለበትም አባቷና እናቷ
ሲጠይቁ መቅደስ እኔ ነኛ አለች ቅዱስ እንዴ አንቺማ አትሄጂም
ልታስታምሚው ነው ወይስ በለቅሶ ልትደፊው መቅደስ ተናዳ አረ
ባክህ ስትለው እህቷም ብሩክም ሁሉም እሷ መሄድ እንደሌለባት
እና የጌዲዮን ቃል ለማክበር መማር እንዳለባት ነገሯት ከዛም
እኔ እኔ በሚል ክርክር ብዙ ከቆዩ ቡሀላ ብሩክ እንዲሄድ ተወስኖ
ፕሮሰሱ ተጀመረላቸው........
........ከዛም የበረራው ቀን እቤት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ሁሉም
ዘመድ ጓደኛ ተሰብስቦ ቤቱ በንባ ታጠበ ጌዲዮ እቤት የመጣው
ባልጋ እየተገፋ ነው ቀና ብሎ እንኳን ቻው ሊላቸው አልቻለም
ነበር መቅደስማ ደግማም የማታየው እየመሰላት ነው በተለይ
ዶክተሩ በቀዶ ጥገና ወቅት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት
ከባድ ነው ያላት ትዝ ብሏት ለቅሶዋ እርም የምታወጣ ነበር
የሚመስለው...........
............ከዛም ጓደኞቻቸው ያሰባሰቡትን ገንዘብ አስረከቡት
ብቻ ሁሉም የበኩላቸውን እያበረከቱ ሰላም እንዲመለስ
መልካም ምኞት ተመኙለት መቅደስ ግን እንደሌሎቹ ጥቅማ
ጥቅም ሳይሆን በጀሪካን ፀበልና እምነት አርጋ ለወንድሟ አደራ
ሰጠችው.....ኤርፖርትም ስትሸኘው ያንገቷን ማህተብ አውልቃ
ሂወቴ ያላንተ ባዶ ናት እኔ የምኖረው አንተ ስትኖርልኝ ነው
ተመልሰህ ከመጣህ ይህን ማህተብ ታስርልኛለህ ያለበለዚያ
ግን እኔም ተከትዬህ በሰማይ እምነቴን ማህተቤን
ትመልስልኛለህ ብላ ባንገቱ ላይ አሰረችለት ይህን ስትለው
ጌዲዮ ከተወለደ እንደዚህ ቀን አምርሮአልቅሶ አያውቅም አለቀሰ
እጇን እንደምንም ጨብጦ አደራ እግዚያብሄር ያረገውን
ቢያረገኝም እንዳትሸነፊ ነገ አዲስ ቀን ነው ትምርትሽንም አደራ
ተምረሽ የኔን ህልም አንቺ አሳኪልኝ አላት እንኳን እናቱ እንኳን
ቤተሰቦቿ በኤርፖርቱ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉም በንባ ታጠቡ
ወንድሟም እያለቀሰ ሁሌም በዋታሳፕ በቫይበር ሁሌም
እንደሚገናኙ ቃል ገብቶላቸው በለቅሶ ተሰናበቱት........
እውነት ጌዲዮ ድኖ ይመጣ ይሆን????........



🔻ክፍል 2️⃣6️⃣ 1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

                       #ክፍል_
2️⃣6️⃣




...🖌ጌዲዮ ለህክምና ውጪ ከሄደበት ቀን አንስቶ መቅደስ
ሀሳቧን መሰብሰብ ተሳናት ቃሉን ለማክበር ስትል ወደ ግቢ
ብትመለስም ከትምርቷ ይልቅ ሀሳቧ ስለጌዲዮ ሁኔታ ወንድሟ
የሚልክላትን መረጃ ለማወቅ ነበር ጉጉቷ ያው ዶክተሩ እንዳለው
ቀዶ ጥገናው ባንድ ጊዜ የሚከናወን ስላልነበረ ቀዶ ጥገና
አለው ባላት ቁጥር በሀሳብና በጭንቀት ቀድማ የምታልቀው እሷ
ነች........
.....አረ ጌዲዮስ ቢሆን የሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ሞትን የሚፈራ
የመጀመሪያው ሰው እኔ ነኝ ብሎ እስኪያስብ ድረስ ሞትን ፈራው
ዳግም የናቱንና የመቅደስን አይኖች አለማየቱን ሲያስብ ሞትን
አብዝቶ እረገመው ከበሽታው በላይ ናፍቆት ጎዳው መለየቱ
ህመም ሆነበት የመቅደስ ፈገግታ ጨዋታዋ ሳቂታነቷ ፍቅሯን
መቋቋም አቃተው በተለይ አብራ የታመመችለት ህመሟ
ከማንም አስበልጣ ተማርኮ የማረከው ፍቅሯ እህህህህ እያረገ
ውስጥ ውስጡን ሌላ በሽታ ሆነበት......... በመመረቂያው
ወቅት ሆስፒታል መተኛቱን እረስቶ መቅደስን አግብቶ ለናቱ
የልጅ ልጅ ማሳየት አማረው ሌላ ተስፋ ምን አልባትም እውን
የማይሆን ህልም...አለቀሰ አብዝቶ አነባ..........
.......ብርሀን ሰአዳ ወይንሸትም ብትሆን መቅደስ እንድትረጋጋ
ዘና እንድትል ብዙ ጥረት እያረጉ ነው ቢሆንም እንዳሰቡት
አልሆነላቸውም ምክንያቱም ከነሱ ጋር ከመሆን ይልቅ በፊት
ጌዲዮ የሚሄድበት የሚያዘወትርበት ስፍራ እየተቀመጠች
ብቸኝነቷን መርጣለች....ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ
አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ይሄ መዘዘኛ ብሎ አይደል የዘፈነው
ጥላሁንስ ቢሆን........
.........የጌዲዮ እናት እነመቅደስ ቤት ትንሽ ከተቀመጡ ቡሀላ
ወዳገርቤት መመለስ እንደሚፈልጉ ለቤተሰቡ ሲናገሩ የመቅደስ
አባት ግራ በመጋባት ምን አጠፋን ሲሉ ጠየቋቸው የጌዲዮ
እናትም አረ ምን ቦጣችሁና የናንተን ውለታ እኮ ነብሴንም
ብሰጥ ከፍዬ አልጨርሰውም ግን ይህን መልካምነታችሁን
እግዚያብሄር ነው በሰማይ የሚከፍላችሁ ሰው የለም ባልኩበት
ወቅት ነው እናንተን አግኝቼ እውነትም የሰው መዳኒቱ ሰው ነው
ያልኩት ስትላቸው ታዲያ ምን አርገን ነው ጌዲዮ ሳይመጣ ልሂድ
የሚሉ ... አዪ እንጃ ብቻ አንድ ያለኝን ያይኔን ማረፊያ ዘሬን
መተኪያዬን ልጄን እንዳላጣው ልቤ ፈራ ታዲያ እዚህ ሆኜ
በሰቀቀን ከማልቅ ከቀያችን አንድ ገዳም አለ እዛው ሄጄ በሱባኤ
ፈጣሪ ጨክኖ እንዳይጨክንብኝ ብለምነው ይሻለኛል ብዬ
ነው..... እንደዛስ ከሆነ መልካም ፈጣሪ ጥሎ አይጥልም
ይለመናል እውነት ብላችኋል የተናቀን ያከብራል የተረሳን
ያስታውሳል አበቃለት የተባለን ታሪክ ይቀይራል አዎድ ይለመናል
........
........እንዳሉትም በንጋታው የጌዲይ እናት ወዳገርቤት ተመለሱ
አመሻሽ ላይ ስለነበር የደረሱት ቤታቸውን አዘገጃጅተው ነገውኑ
ወደገዳም ገብቼ ሱባኤዬን እጀምራለሁ ብለው አሰቡና
ኩርትምትም ብለው ጋደም አሉ የልጃቸው ነገር እያስጨነቃቸው
በሀሳብ ተውጠው በዛው እንቅልፍ ወሰዳቸው ለሊትም በራቸው
በሀይል ተንኳኳ እትዬ አስካል እትዬ አስካል የሚል ድምፅም
ሰሙ በራቸው በመንኳኳቱ ቢደነግጡም የሰሙት ድምፅ የንስሀ
አባታቸው መሆኑን ሲያውቁ ተረጋግተው በሩን ከፈቱ ስኪፍቱት
ግን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሽማግሌዎች ጎረቤቶቻቸው
እንዲሁም ለብዙ አመታት የራቋቸው የባለቤታቸውና የራሳቸው
ቤተሰቦቻቸው ደጃቸውን ሞልተውት ነበር የጌዲዮ እናት
በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ የልጃቸውን መርዶ ነጋሪዎች መሰሏቸው
አንደበታቸው ተርበተበተ ሰውነታቸው ተንቀጠቀጠ ልባቸው ሄድ
መጣ ይል ጀመር በሚቆራረጥ ድምፃቸውም ልጄ ልጄ ምን ሆነ
አባ ሲሉ የንስሀ አባታቸውን ጠየቁ ነገሩ ግን ካሰቡት ውጪ ነበር
ይሄ ሁሉ ሰው የተሰበሰበው ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሆነ ሲረዱ
ነብሳቸው አረፈች ግን ለምን ሲሉም ጠየቁ የልጃቸው
መታመምን ሰምተው እንደሆነም ሲነግሯቸው አለቀሱ በንባቸው
መስታወትም ያሳለፉትን የመከራ ሃያ አመታት ወደኋላ መለስ
ብለው አስታወሱ............
........ጌዲዮን ከልጆቻቸው ጋር አንድም ቀን እንዲጮት
ፈቅደውለት አያውቁም ለግዜር ሰላምታም ቢሆን ይፀየፏቸዋል
በዛላይ አሽሙራቸው መጥፎ ንግግራቸው ከሰው መሀል ሆነው
ሰው የተራቡበትን ጊዜያት ከማህበራዊ ኑሮ ተገለው የኖሩበት
አመታት አረ ስንት መከራ ስንት ስቃይ ግን ይህን ሁሉ ጨክነው
ነበር ጌዲዮን እዚህ ደረጃ ያደረሱት የሳቸው ቅስም እየተሰበረ
የልጃቸውን ሞራል እየጠበቁ ታዲያ ምነው ዛሬ ተስፋቸው ሊሞት
መሆኑን ሲሰሙ ለይቅርታ ሽማግሌ ሰበሰቡ የጌዲዮ እናት
አሻፈረኝ አይሆንም ይቅርታችሁን አልቀበልም አሉ...




🔻ክፍል 2️⃣7️⃣ 1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️የልቤ ትርታ❤️❤️

    


የልቤ ትርታ ክፍል 2️⃣7️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

                       #ክፍል_
2️⃣7️⃣

...🖌የንስሀ አባታቸውም ብዙ አስተማሯቸው ስለይቅርባይነት
ብዙ ነገሯቸው በስተመጨረሻም እግዚያብሄር ሊፈትነኝስ ቢሆን
ብለው አሰቡና ልጄን አትርፍልኝ እንጂ እንኳን ይሄንን ስንቱን
ችያለሁ ብለው ይቅር ለግዚያብሄር አሉ ሰላም ወረደ ገዳምም
ገብተው ፆም ፀሎታቸውን ተያያዙት.................
.........መቅደስ አዘውትራ የምትሄደው ጌዲዮ የሚያጠናበት
ጫካ ነው ነገ ትምርት ጨርሰው ወደየመጡበት ይበተናሉ
ያመጣችው ውጤት ምንም ከሷ የማይጠበቅ ነው ይሄ ወር
ደግሞ ያምስተኛ አመት ተማሪዎች የጌዲዮ ጓደኞች ምርቃት
ነው ህመሟን ጨመረው ስለምርቃቱ ጓጉቶ የነገራት
እያስታወሰች በተለይ ምን ታመጪልኛለሽ ሲላት ያገር አበባ
ያለችው ብቻ ሁሉንም እያስታወሰች በንባ እየታጠበች
ነው........
.....እውነትም አልቀረም የምርቃታቸው ቀን ደረሰ የዛ ቀን
መቅደስ በጠና ታመመች ሀኪም ቤትም እንዳትወሱዱኝ አለች
ከዛም እቤት ድረስ ዶክተር አመጡ ዶክተሩም አክሞ ሲጨርስ
በጣም በናፍቆት ተጎድታለች ምግብም ካለመመገቧ የተነሳ
እራሷን መቆጣጠር ተስኗታል በተቻላችሁ አቅም የናፈቀችውን
ሰው ብታገናኟት ጥሩ ነው ሲላቸው አይ ዶክተር ይሄማ መች
ጠፋን ለማንኛውም እናመሰግናለን አሉት..... በቃ ከዛን ጊዜ
ጀምሮ ጭራሽ ከክፍሏ አልወጣም አለች ያምስተኛ አመት
ትምርቷንም ልክ እንደጌዲዮ አቆመች ቤተሰቦቿ እግሯ ላይ
ቢወድቁም አልማርም አለች ግዜም መሄዱ አይቀርምና ጌዲዮ ሁሉንም ቀዶ ጥገና
በወዳጆቹ ፀሎትና በፈጣሪ ፍቃድ በሰላም አጠናቆ የመጨረሻው
ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቀጠሮው ደርሶ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል
አስገቡት......ብሩክ ከዚህ ቡሀላ ጌዲዮ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
አልቻለም አንድም መልስ የሚሰጠው ዶክተር አጣ ይሙት ይኑር
ምኑን አውቆት ቤተሰቦቹም አስጨነቁት ግራ ቢገባው ሞቶም
ከሆነ ቁርጤን ንገሩኝ አላቸው የህክምናው ክፍል መግባት
አይቻልም መልስ የሚሰጠው አጣ ለምን የሚል ጥያቄ
ጭንቅላቱ ውስጥ ተፈጥሮበት በከፍተኛ ሀዘን ተዋጠ ለብዙ
ሳምንታትም የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቢሸውዳቸውም በስተ
መጨረሻ ግን አልቻለም ሁሉም አፋጠጡት ስልኩን ሙሉ ለሙሉ
ኦፍ አረገው በቃ ከዚህም ቡሀላ ቤተሰቡ ሀዘን ተቀመጠ
መቅደስ ካንዴም ሁለቴ እራሷን ልታጠፋ ስትል ደርሰው አዳኗት
እንኳን የጌዲዮን የብሩክን ድምፅ ከሰሙ ወራቶች ተቆጠሩ...
.....ጌዲዮና መቅደስ ከትውውቅ ጀምሮ እስካሁን በጣም ብዙ
ፈተናና መከራ አሳልፈዋል ከምንም በላይ ግን ያለፈው ግማሽ
አመትና ይሄ አመት በሳት የተፈተኑበት ወቅት ነው ትምርቷን
አቁማ ከቤት አልወጣም ካለች ይኸው አመት ሊሞላት ነው
ብትወጣ እንኳን አምላኳን ልትለምን ቤተክርስቲያን ብቻ ነው
የጌዲዮ እናትም ገዳም ገብተው ሱባኤ ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ
የመቅደስ ቤተሰቦችም የጌዲዮ ጓደኞችም ብቻ የሚያውቁት ሁሉ
በፀሎት አልተለዩትም እንደምታስታውሱት በክፍል ሀያ አምስት
ላይ ጌዲዮ የመጨረሻውን ቀዶ ጥገና ሊያደርግ ከገባበት ወቅት
አንስቶ አስታማሚው ቅዱስ ስለሱ ሁኔታ የሚነግረው አጥቶ
ተስፋ ሲቆርጥ ቤተሰቦቹም እየደወሉ እንዴት ሆነ ሲሉት ስልኩን
ሙሉ ለሙሉ ሲያጠፋ...


🔻ክፍል 2️⃣8️⃣የመጨረሻው ክፍል 1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌     ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️የልቤ ትርታ❤️❤️

    


ሰላም ሰላም ቤተሰቦች  እንኳን አደረሳችሁ የልቤ ትርታ የመጨረሻው   ክፍል ምሽት 2:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  የልቤ ትርታ  🔸
​​         

          
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️

          
❤️ የመጨረሻው ክፍል   ❤️


...🖌እነመቅደስም መሞቱን አምነው ሀዘን
ሲቀመጡ መቅደስ እራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሀሉም በንባ
ታጥበው ነበር.............
.........ቢያንስ መቅደስ ከሶስቴ በላይ እራሷን ልታጠፋ ስትል
እየደረሱ አድነዋታል በዚህም የተነሳ ብቻዋን ጥለዋት ወተው
አያውቁም ዛሬ ግን አጋጣሚ ሆነባቸውና ቅብጥብጡን ብሩክን
አደራ ብለውት ከፊቷ እንዳይጠፋ አስጠንቅቀውት ጉዳይ
ስለነበረባቸው ሁሉም ወጡ እንደእብድ ያረጋት መቅደስ አሁንም
የጌዲዮን መሞት ስታስብ መሞት አማራት ከዛ ብዙ ኪኒን
ለመዋጥ ስታስብ ብሩክ አለ ከዛም ሱቅ ልትልከው አስባ ብሩኬ
ስትለው ወዬ አላት ሱቅ ሄደህልኝ ና አለችው አረ ላሽ በይ እነ
ማሚ ጥዬሽ እንዳልሄድ አስጠንቅቀውኛል ሲላት ሴት እኮ ነኝ
ታዲያ ልበላሽ አላሳዝንህም ስትለው ምንድነው የምገዛልሽ አላት
እ .እ. እንትን ልክ እንደፈራች ሆና መርበትበት ጀመረች ደሞ
ከዚህ ውጪ ምንም ቢሆን እንደማሄድላት ታውቃለች ከዛም ካፏ
ቀበል አርጎ እየሳቀ ሲስቱ ብዙ አትጨናነቂ ገባኝ የሴቶች
ፓንፐርስ ነዋ ሲላት ሂ ሞዛዛ ብላ በጥፊ አለችው ከዛም
አደራውን እረስቶ ሊያመጣላት ተስማማና ብር ተቀብሏት ሄደ
እንደሄደም ኪኒኑን ሰብስባ ልትውጠው ስትል የቤታቸው ስልክ
ጮኸ ዝም አለችው አሁንም ልትውጥ ስትል ጮኸ አሁንም
ዝም አለችው ከዛም አሁንም ልትውጥ ስትል ሞባይሏ ጮኸ
በንዴት አንስታ ሄሎ ስትል ሀይ መቅዲዬ ቅዱስ ነኝ በቤትስልክ
ስደውል የሚያነሳ የለም ደንዝዛ ቀረች በዛ ላይ የቅዱስ ድምፅ
ፍፁም ልክ አልነበረም መልስ ልትሰጠውም አንደበቷ አልፈታም
አለ ከዛም በዛ በተዘበራረቀ ድምፁ አሁን ኤርፖርት ነኝ ነገ ማታ
12 ሰአት ስለምንደርስ ኤርፓርት ጠብቁን አላት ጌዲስ ሞተ
አይደል ብላ ልትጠይቀው አስባ ካፏ ሳታወጣው ስልኩ ተቋረጠ
እንባ ካይኖቿ ዱብ ዱብ እያለ ብቻዋን ስታወራ ብሩክ ተመልሶ
መጣ ሲያይት ደንግጦ ምን ሆንሽ አላት መልስ አልሰጠችውም
ክፍሏ ገብታ ተኛች ማታ ቤተሰቦቿ መጡ..........
ተሰብስበው ሳሎን ቁጭ ባሉበት ያለወትሮዋ መጥታ መሀላቸው
ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም አይን አይኗን ማየት ጀመሩ
ምክንያቱም አብራቸው መሆን ካቆመች ቆየች መሬት መሬቱን
እያየች ቅዱስ ነገ ይመጣል አለቻቸው ምን አሏት አዎ 12ሰአት
ተቀበሉኝ ብሏል ስትላቸው ጌዲዮስ አሏት እኔንጃ አላቅም ብላ
ተመልሳ ወደክፍሏ ሄደች......
......መድረስ አይቀርምና የመምጫቸው ሰአት ሲደርስ ሁሉም
ተሰብስበው የኤርፖርቱ በር ላይ በሁለት ስሜት ይጠባበቁ ጀመር
ግማሹ ተሳፋሪ ወጣ ቡሀላም ቅዱስ ወደነሱ ቀረበ ግን እሱን
ሳይሆን ሁሉም የሚያዩት ባይናቸው የሚፈልጉት ጌዲዮን ነበረ
ቢሆንም አጡት አባትየው ቀስ ብሎ መቅደስን ደገፋት ሁሉም
ልባቸው ቀጥ ልትል ምንም አልቀራትም ተስፋቸው ተሟጦ
የጌዲዮን ሞት አምነው ለመጮህ እራሳቸውን ሲያዘጋጁ
በስተመጨረሻ ባልጋ እየተገፋ ቻው ብሏቸው የሄደው ጌዲዮ
ድኖ ጋቢ ለብሶ ከቅዱስ ቡሀላ እየተራመደ መጣ...........
............ሁሉም በህልም አለም ያሉ መሰላቸው መቅደስ
በጩኸት ዘለለች ሌሎቹም እየተንበረከኩ በምስጋና ላምላካቸው
መስገድ ጀመሩ መቅደስ እንደጨቅላ ፍየል እንደንቦሳ ጥጃ ከዛ
ከዚህ መሯሯጥ ጀመረች የታመነችለት ፍቅር ታመነላት ጌዲዮን
አሳልፎ ለሞት አልሰጠባትም ከሩቅ ገና ሲያያት ጌዲዮ
እየተንደረደረ ወደሷ መጣ እሷም እየሮጠች ወደሱ ስትሄድ
መሀል ላይ ተገናኙ ከዛም ሊያቅፋት ሲል ተመልሳ ወደቤተሰቦቿ
ተንደረደረች ጌዲዮ ደነገጠ እሷን እሷን እያየ እንባውን አዘራ
እሷም እያለቀሰች እየዘለለች አባ አባዬ እሱ ነው ጌዲዮ
አልሞተም እኮ እያለች እውን የሆነውን ህልሟን ትተርክ ጀመር
በሁኔታዋ እንኳን ቤተሰቦቿ ያያቸው የተመለከታቸው አለቀሰ
ከዛም ወደጌዲዮ ተመለሰች አሁንም ሳታቅፈው ተመለሰች
ጌዲዮ ደስታዋ መሆኑን ሲያውቅ ከመሬት ተንበርክኮ በንባ ታጠበ
ፈጣሪውን አመሰገነ ለሶስተኛ ጊዜ ስትመጣ አሁንም
እንዳትመለስ ሁልቱን እጆቿን ጭምቅ አርጎ ይዞ ጉንጮቹ ላይ
አረጋቸው የናፈቀው አይኗ የናፈቃት አይኑ ተፋጠጡ ፍቅር
የተራበው ልባቸው በሀሴት ጮቤ እረገጠ ከንፈራቸው
ተንቀጠቀጠ ናፍቆትና ፍቅር የጋረደው አይናቸው በዙሪያቸው
የሚመለከታቸውን ህዝብ አላስትዋሉም ጌዲዮም ቤተሰቦቿ
መኖራቸውን እረሳው ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ ሳማት የተባለ
ይመስል ያኔ የመጀመሪያ ቀን እንደሳማት ግጥም አርጎ ከንፈሯን
ጎረሰው አቤት ሲያምሩ አቤት ሲያስቀኑ መፋቀርስ እንደነሱ
ፀጉሯን እየዳበሰ እሷም አንዴ ጉንጩን አንዴ ወገቡን አጥብቃ
እየያዘችው እያገላበጠ ያለምንም ፍራት ይሳሳሙ ጀመር
ቡሀላም አለመላቀቃቸውን ቀበጡ በረከት ሲያይ ጠጋ ብሎ
እህህ እህህ አረ እኛንም ሰላም በለን ናፍቀኸናል እኮ ሲለው
ጌዲ ደንገጥ አፈር ብሎ መቅደስን ለቀቃትና ከመጣህ
ትመልስልኛለህ ብላ ያጠለቀችለትን ያንገቷን ማህተብ አውልቆ
አጠለቀላት ከዛም ግንባሯን ስሞ ሁሉንም እያቀፈ በንባ ሰላም
አላቸው..............
.............ወደቤትም እንደሄዱ እራት በሉ ቡናም እየጠጡ
እናቱን ጠየቃቸው ከዛም ገዳም እንደሆኑ እሱ ሲሄድ
እንደሚወጡ ነገሩት መቅደስ ከቅፉ አልወጣችም ነበረ በቃ
ከናንተ ጋር ናፍቆቴን ይህን ያክል ካሳለፍኩ ነገ እሄዳለሁ እሜ
እጅግ በጣም ነው የናፈቀችኝ አላቸው ከዛም የመቅደስ እናት
በቃ መቅደስም አብራህ ትሂድ ባይሆን ጓደኞቿ እሁድ
ስለሚውምመረቁ በዛውን የደስታችንን ድግስ አብሬ እደግሳለሁ
ቅዳሜ እናትህን ይዛችሁ እንድትመጡ ሲሉት እንዴ መቅዲስ
አትመረቅም አላቸው መቅደስ ቶሎ ብላ አይኗን ከመሬት ተከለች
አባቷም አይ ጌዲ እንኳን ከትምርት ከራሷም አለም ወታ ነበር
እኮ ብለው የተፈጠረውን ተራ በተራ አስረዱት ጌዲዮ የመቅደስ
ፍቅር ካቅሙ በላይ ሆኖበት ከውስጡ ሸሸጋት.......
........ከዛም አገር ቤት ሲሄዱ አገር ምድሩ ተቀበላቸው እናቱም
በልልታ ፀሎቷን የሰማት አምላኳን እያመሰገነች ልጇን ከቅፏ
አስገባችው የናቱም ያባቱም ዘመዶች ጎረቤቱም ሳይቀር ከግሩ
ተንበርክከው ይቅርታ ለመኑት እሱም ይቅር ለእግዚብሄር
አላቸውመረገጣቸው መገፋታቸው ለበጎ ሆነ አሸናፊዎቹ ተሸነፉ
ተሸናፊዎቹ አሸነፉ!!!!!...........

      
🔻 ❤️ 💝  ተፈፀመ🔻 ❤️ 💝
                


❤️ 💝 አብራችሁን በመሆን  ስለተከታተላችሁን ከልብ እያመሰገን  በቅርቡ በሌላ ታሪክ እንመለሳለን  ሀሳብ አስተያዬት እንዲሁም መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች  commnet ላይ አሳውቁን  .. አብራችሁን ለሆናችሁ በእውነት በቻናላችን ስም ከልብ እናመሠግናለን🙏🙏
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌     ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻  🔺🔺🔺🔹🔻🔻🔺
🔸ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ

📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
👇👇👇👇👇👇👇

➡️👉 የ ቻናል ማስታወቂያ
➡️ 👉የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
➡️ 👉የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
➡️ 👉የ ድርጅት ማስታወቂያ
➡️ 👉የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
➡️ 👉ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ

    

         ❤️ምርትና  አገልግሎቶን በተመጣጣኝ ዋጋ ለብዙሀኑ ተደራሽ በማድረግ በእጥፍ ያትርፉ። ከኛጋ በመስራትዎ ይደሰታሉ❤️

አሁኑኑ ያናግሩን 👇👇👇👇👇

                          @ethio3254
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔸 አዳዲስ ላፕቶፖችን አስገብተናል 
   🔺🔻🔺🔹 🔺🔻
   laptop  መግዛት ፈልገው  የት ልግዛ ብለው ተቸግረዋል ?

እርስዎ በየሱቁ መንከራተትና መድከም ሳይጠበቅብዎት ባሉበት ሁነው እሚፈልጉትን computer እኛ ቻናል  ላይ መርጠው ይላኩልን  እኛ ከ1  ዓመት ሙሉ ዋስትና ጋር በቅናሽ ዋጋ እንሸጥልዎታለን

https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0  join በማድረግ በየጊዜው ፖስት እሚደረጉ የተለያዩ ብራንድ ላፕቶፖችን ማየት ትችላላችሁ::

እንዲሁም   ያገለገለ ወይንም አዲስ laptop and projector ያላችሁ በጥሩ ዋጋ እንገዛዎታል
💠💠💠💠
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0

https://www.facebook.com/profile.php?id=100084394544041&mibextid=ZbWKwL

For more info
Inbox
@ethio3254
Call at
📞0908616263
🔸🔸🔸🔸🔸🔸

❤️ሰላም ሰላም ቤተሰቦች አዲስ ታሪክ በቅርቡ እንጀምራለን
ይጀመር እምትሉ እስኪ 
1️⃣0️⃣0️⃣ 👍like ❤️



🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን! 😀


   

 
❤️❤️
❤️❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️

    ሰላም ቤተሰቦች ምኞቴ የተሰኘ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ ታከታታይ የፍቅር ታሪክ ዛሬ እንጀምራለን 💛


   ክፍል1 ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
1️⃣

          ... ረድኤት ከረፋዱ አራት ሰዓት አከባቢ የቤታቸዉን በረንዳ በማፅዳት ላይ ሳለች የግቢያቸዉ
በር ተንኳኳ፡፡ ማን ሊሆን ይችላል? ብላ እያሰበች ወደ በሩ ተጠጋች "አባዬና እማዬ ዛሬ የስራ
ቀን ስላልሆነ ቤት ዉስጥ ናቸዉ፡፡" እና ማን ነዉ? እያለች የግቢዉን በር ጠጋ አለችና "ማን
ነዉ?" አለች "እኔ ነኝ" የሚል ለስላሳ ድምፅ ከዉጭ የተሰጣት መልስ ነበር፡፡ ድምፁን
ከዚህ በፊት ባታዉቀዉም ሰላም ያለ ሰዉ እንደሆነ በድምፁ ስለተረዳች በሩን ከፈተችለት፡፡
በጣም ቆንጅዬ ወጣት ነበር፡፡  "ደህና ነሽ" አላት፡፡ እሷም "ደህና ነኝ" ብላ
ስትመልስለት "የሚከራይ ቤት አለ ብለዉኝ ነበር... አለ እንዴ?" ሲላት የረድኤት አባት
ለረዢም ሰዓት በር ላይ እንደቆመች ስላዬ
"ማን ነዉ?" እያሉ ወደ በሩ ተጠጉ፡፡ ወጣቱንም ባዩ ጊዜ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
ወጣቱ ልጅ ለረድኤት የጠየቃትን ጥያቄ ለአባቷ ለጋሽ ሀብታሙ ደገመላቸዉ፡፡ ጋሽ ሀብታሙም አለ ወደውስጥ ግባ ልጄ፡፡ አሉት  እሺ ብሎ ገባ የሚከራየውን ቤት ገብቶ አየ ስንት እንደሚከራይ ጠየቃቸውና ተስማምተው ቢኒያም ወደ ቤት ተመለሰ ፡፡ ... ከዚህ ጊዜ በኃላ ነበር ረድኤት ቢንያምን ያወቀችዉ፡፡ ቢንያም እጅግ በጣም ዉብና
ማራኪ ልጅ ነዉ፡፡ ሚስቱ ደግሞ ኤደን ትባላለች፡፡ እጅግ ሲበዛ ዝምተኛና ቆንጂዬ ናት፡፡ ቤት
ስለምትዉልና ረድኤትም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብትሆንም ሰመርን ከቤተሰቦቿ ጋር ስለምታሳልፍ ሁሌም አብረዉ ይዉሉ ነበር፡፡
ኤዲ ምንም ያክል ዝምተኛ ብትሆንም ለባሏ ግን ፍቅርን መስጠት የምትችል፤ በተለይ
ሲጫወቱና ሰዉነቱ ላይ እየተንከባለለች ቅብጥብጥ ቅብጥ፤ ሽፍድ ስትልበት... ረድኤት "እኔ በሆንኩ" ብላ ትቀናባታለች፡፡ .

..... ቢኒያም ከስራ ሊመጣ አከባቢ ኤዲ እጅግ በጣም ተዉባ ከወትሮዉ በተለዬ ይበልጥ
አምራ የግቢዉን በር ለመክፈት ከቤቷ ወጥታ በሯ አጠገብ ትቀመጣለች፡፡ ልክ በሩ
እንደተንኳኳ ሩጣ ትሄድና ቶሎ ትከፍታለች፡፡ ቢኒያምም እቅፉ ዉስጥ አስገብቶ ሲስማት
ለተወሰነ ሰዓታት የተለያዩ ሳይሆን ለአመታት ተራርቀዉ ተነፋፍቀዉ የተገናኙ ይመስላሉ፡፡
ቢኒያም ፍቅር መስጠት ተክኖበታል፡፡
ሲያፈቅራትና ሲወዳት ምድር ላይ ሌላ ሴቶች እስከመፈጠራቸዉም ረስቶ ነዉ፡፡ ለሱ ሴት
ማለት እሷ ብቻ ናት፡፡ እንደ እናት ያከብራታል፤ ያፈቅራታል በጣም ይሳሳላታል፡፡ ፍቅራቸዉ
እንኳን አብሯቸዉ ለሚኖር ሰዉ ለአንድ ቀን በመንገድ ላይ ያያቸዉ ራሱ ይቀናባቸዋል፡፡

...ከግቢዉ ነዋሪም ጋር በጣም ተግባብቷል፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ለብቻቸዉ ባገኛቸዉ ሰዓት "አባባ
ገና ወጣት ነህ አረጁ የሚል ሰዉ ተሳስቷል፡፡ አሁን እኔ እና አንቱ ሩጫ ብንሽቀዳደም
አዝነውልኝ ካልተዉልኝ በስተቀር ትበልጡኝ የለ እንዴ! አንቱኮ ሀይሌ ገ/ስላሴን ያስንቃሉ፡፡" እያለ
ይቀልዳቸዋል፡፡ እሳቸዉም የወጣትነት ጊዜያቸዉ ታዉሷቸዉ በጨዋታዉ ከሳቁ በኃላ "አይ
ልጄ..." ብለዉ ትረካቸዉን ይጀምራሉ፡፡ ለወሬያቸዉ አክብሮ ጆሮ ስለሰጣቸዉ ከስራ
የሚመለስበትን ሰዓት እንደ ኤዲ እርሳቸዉም ይጠባበቃሉ፡፡ በተለይ ደሞ ረድኤት...!




🔻ክፍል 2️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​​​​​​         
❤️❤️ምኞቴ❤️❤️


   ክፍል2️⃣ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።

ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።

Join us
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥

👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0


            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
2️⃣

        ....የፍቅርን ሸማ ለብሶ ለኤዲ መዉደድን አጉርሶ በመኖር የተካነዉ ቢኒያም ይሄ ፍቅር
አሰጣጡ ረድኤት እንድትወደዉ አድርጓታል፡፡
ሁሌም ስለሱ ታስባለች ከቤት የሚወጣበትን ሰዓት እየጠበቀች ታየዋለች... ወደ ስራ ሲሄድ
እሷም እንደ ኤዲ ከአይኗ እስኪጠፋ ድረስ በአይኗ ትሸኘዋለች!፡፡
... ቀኑ እሁድ ቀን ነበር ረፋድ አከባቢ የረድኤት እናትና አባት ከቤታቸዉ በረንዳ ላይ በልጃቸዉ
ፍላጎት ቡና እየጠጡ ነዉ፡፡ ጨዋታዉ ደምቋል፡፡ የረድኤት እናት (እማማ በለጡ) የልጅነት
ቁንጅናቸዉ ዛሬም አለ፡፡ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታቸዉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ እሳቸዉን አይቶ ረድኤትን
"ልጃችሁ ናት?" ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ረድኤትን በካርቦን አስደግፈዉ የሳሏት እንጂ
አምጠዉ የወለዷት ብቻ አትመስልም፡፡
... ኤዲ አስከዛሬ ብቻዋን የምሰራዉን ስራ ዛሬ በቢኒ አጋዥነት ቤታቸዉ በረንዳ ላይ እቃ
ያጥባሉ፡፡ የነ ረድኤት ቤትና የነ ቢኒ ቤት ፊት ለፊት ስለሆነ ከቤት ዉጭ የሚደረጉ ነገሮች
እያንዳንዳቸዉ ይተያያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ረድኤት ቡና ማፍላቷን ረስታ በነሱ ፍቅር ተስባ
በመተዛዘናቸዉ ተደምማ ዛሬም 'ኧረ የኔ በሆነ" አይነት ስሜት ታያቸዋለች፡፡
... ቢኒ በስራቸዉ መካከል ሚስቱን ዉሃ ረጨት እያረገ ይቀልዳታል፤ በመሃል ደሞ
ስራቸዉን ረስተዉ ይተያያሉ፡፡ በስስት ያያታል ሳያወሩ በአይን ይግባባሉ፡፡ እሷን ሲመለከት
ልቡ ቦታዉን ለቆ አይኑ ላይ የመጣ ይመስላል፤ የአይኖቹ ብሌን ልብ ቅርፅ ይሰራሉ ምንም
አይነጋገሩም ግን በአይኖቻቸዉ ፍቅርን ያዜማሉ፡፡
... የሚገርመዉ ግን ሶስተኛ አይንም ነበረ፡፡ ረድኤት! ... ረድኤትም በኤዲ ቦታ ራሷን ተክታ
ቢኒን ታየዋለች የራሷ ባል አስኪመስላት በስስት ታየዋለች፡፡ በሃሳብ ተጉዛ ራሷን ከቢኒ
ጋር አርጋ ነዉ የምታስበዉ፡፡ እናቷ ሲጠሯት እንኳ አሰማም፡፡ እማማ በለጡ ተጣሩ "ረድኤት"
ዝም መልስ የለም እሷ ክንፍ አዉጥታ በራለች ዘመናትን ተሻግራ ከቢኒ ጋር ተጋብታ፤
ቆንጅዬ ልጆችን ወልዳ........... በሀሳብ ጭ.... ልጥ ብላች፡፡
እናቷ እየተጣሩ ነዉ፡፡ "ረድኤት" "ኧረ ረድኤት" ብለዉ ሲጮሁ ደንግጣ ከሃሳቧ ብትት
ከእንቅልፏ ንቅት አለች፡፡ ነገሩ የእማማ በለጡ አጠራር የልጃቸዉን ብቻ ሳይሆን
ጥንዶቹንም አስደንግጧቸዋል፡፡
ቢኒ በስስት ኤዲን እየተመለከታት "አንቺ ባትኖሪኮ ምን እንደምሆን ሳስበዉ..." ብሎ
ሳይጨርሰዉ ኤዲም "ከእኔ የተሻለች ፈጣሪ ይሰጥህ ነበር" አለችዉ፡፡
ቢኒ ሁሌም ቢሆን "ከኔ የተሻለች..." ስትል አይወድም፡፡ ምክንያቱ ደሞ ከእሷ የተሻለች
ሴት አለ ብሎ ማሰብ ስለማይፈልግ፡፡

..."ፈቲዬ አንቺ ደሞ በዚች ቃል ሁሌ ታናጅኛለሻ?" እሷም ወሬ ለማስቀየር... "የኔ ማር..."
ስትለዉ "እንደዉም ካንቺ የተሻለች አገባለሁ" ሲላት ንዴቱ ወደራሷ ዞረና "ሂድ" ብላ ዉሃ
ረጨችበትና አኮረፈች፡፡
ኤዲ ስትስቅም ስታኮርፍም በጣም ዉብ ናት፡፡ ካኮረፈች ደግሞ እንደ ህፃን ልጅ ያረጋታል ፡፡
ቢኒም ማባበል ጀመረ ቶሎ እንደማትስቅ ስለገባዉ ልመናዉን ተወና ለቅጣቱ ተዘጋጀ፡፡....
እሷ አታወራም አኩርፋለች "ዛሬ ራሴን ራሴ ነኝና የምቀጣዉ፡፡ ተመልከቺኝ ..." ብሎ እንደ
ህፃን ልጅ ተንበረከከ እጁንም ወደላይ አርገበገበ፡፡ አሁንም እንዳኮረፈች ናት ከዚያ
አጎበደደና ጆሮዉን ሲይዝ ኤዲ በሳቅ ፍርስ አለች፡፡
... ረድኤትና ቤተሰቦቿም "ምንድነዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ..




🔻ክፍል3️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

💙  ምኞቴ 🔸

​​          ❤️ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

                       #ክፍል_
3️⃣

        .... ... ረድኤትና ቤተሰቦቿም "ምንድነዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ... ቢኒ ለፍቅሩ ተንበርክኮ ያስቃታል፡፡
ይሄኔ ረድኤት በጣም ትቀናለች!፡፡ ፍቅሯ በዉስጧ መብሰልሰል ይዟል፡፡ አዉጥታ አታወራዉ..
ለማን? ግቢ ዉስጥ ያለችዉ የእድሜ እኩያዋ "ኤዲ" ናት፡፡ የወደደችዉ ወጣት ሚስት ያለውነው! " ሆ
ሆ " ብላ ለራሷዉ ተሸማቀቀች፡፡
አዉጥታ መናገር እንዳለበት አምናለች ግን እንዴት ብላ ያዉም ባለ ትዳርና በትዳሩ ደስተኛ
የሆነን ሰዉ...፡፡

...ረድኤት ሌቱን ሙሉ እንቅልፍ አልወሰዳትም ትገላበጣለች፤ ታስበዋለች፡፡ ሸለብ
ሲያደርጋት በአይነ ህሊናዋ ያንን ቆንጆ ፊትና የሚያምር ጨዋታዉን ታያለች እንደገና ብትት
ትልና ቁጭ ትላለች፡፡ ምን እንደምትሆን ግራ ገብቷታል?.... ነገር ግን አንድ ስሜት ዉስጧን
ፈንቅሎ ወጣ "ነገ ልትነገሪዉ ይገባል" የሚል ድምፅ ሹክ ያላት መሰላት፡፡ "አዎ" ስትል
አሰበች "ነገ ልነግረዉ ይገባል!" "ግን... እንዴት ነዉ የምነግረዉ?" "አፈቅረሃለሁ" ልለዉ
ትልና "ኧረ..." ትላለች፡፡ "እሺ ምን ልበለዉ!?" ... በጣም ጨንቋታል ሰማይ ከመዉጣት
በላይ ከብዷታል ... ይሄንን እያሰበች የነገዋን ንጋት በጉጉት እየጠበቀች ከሌሊቱ ስምንት
ሰዓት ገደማ እንደምንም ታግላ እንቅልፍ ሸለብ አደረጋት...!

....... ረድኤት የእቅልፍ ሰዓቷ በጣም ረፈድ አርጋ ስለተኛች የሚገርም እንቅልፍ
ላይ ናት፡፡የጠዋቱ የወፎቹ ዜማም ሆነ የሞባይል አላርሟ ሊቀሰቅሳት አልቻለችም ለሽሽሽ ብላ
ተኝታለች!፡፡...... ቢኒ ዛሬ ቀኑ ሰኞ ስለሆነ በጧት ስራ መግባት አለበት፡፡ ቁርሱንም እዚያዉ ስራ ቦታ
እንደሚበላ ለኤዲ ቀድሞ ስለነገራት ከእንቅልፏ ሊቀሰቅሳት አልፈለግም፡፡ ልብሱን ለባበሰና
ወደ ስራ ከመዉጣቱ በፊት ወደ መኝታ ቤቱ አመራ ኤዲ ተኝታለች፡፡ ተኝታ ሲያያት ቁንጅናዋ
የበለጠ አስደመመዉ፡፡ ዉብ ናት፤ በጣም ዉብ ...  ስለሷ ተናገር ቢባል ቃላት ሁሉ ያጥረዋል፡፡ እጥፍጥፍ ብላ ስተኛ
የበለጠ ታሳሳለች፡፡ በተኛችበት እንደ ማንጎ ምጥጥጥ ምጥምጥጥ እንደ ትርንጎ
ግምጥጥ ቢያደርጋት ሁሉ የሚወጣለት አይመስልም፡፡ ከእንቅልፏ እንድትነሳ ስላልፈለገ
ቀስ ብሎ በስሱ ሳም አደረጋት፡፡ ግንባሯን ሲስማት ጣፍጭ ጠረኗ አፍንጫዉን አወደዉ
"ፈጣሪ ይጠብቅሽ የኔ ቆንጆ..." ብሎ ቀስ... ብሎ  ከቤት ወጣ......

 

🔻ክፍል4️⃣  ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM