#ክፍል_
...🖌መቅደስ ምንም እንኳ ከጌዲዮ ፍቅር ባትጀምርም አሁን ካይኗ ስር በመሆኑ ደስታዋ ተመልሷል ጌዲዮም እንደዛው......
.......አሁን ወሩ የፈተና ነው ጎበዝ ተማሪዎች በጥናት ተጠምደዋል እንደወይንሸት ያሉት ደግሞ እንዴት አስተማሪዎቻቸውን ማማለል እንዳለባቸው ብቻ ሁሉም በየፊናው እየተዘጋጁ ነው።
...............ጌዲዮም እንደለመደው ጫካ በመሄድ ማጥናቱን ተያይዞታል በነገራችን ላይ መቅደስ አሁንም ሳያያት ትከተለዋለች እናም ዛሬም ሳያያት ከኋላ ኋላው ሄዳ ከቅርብ እርቀት ሆና እያየችው ነው ግን ይህን የምታደርገው አንድ ቀን በህልሟ ጫካ ውስጥ ወድቆ አውሬዎች ሊበሉት ሲሉ በላብ ተጠምቃ ከንቅልፏ ባና ከዛ ወዲ እውን እንዳይሆን እየፈራች ከግቢ ሲወጣ አብራው ትወጣለች............
........እናም ብዙ ቆየ በተስፋ ስትጠባበቀው ቆይታ የሆነ ሰአት ላይ በጫካው የጦጣዎች ትርኢት ተመለከተች ከዛም ቀልቧን ሳቡት ከዛፍ ዛፍ ሲዘሉ ሲቦርቁ ስታይ ለግዜው ጌዲን ለጥናቱ ተወችው ከዛም ስልኳን አውጥታ መቅረፅ ጀመረች ጌዲዮ በዛን ሰአት ጥናቱን ጨርሶ መፅሀፎቹን ሰብስቦ ተነሳ ተነስቶ እንደዞረም መቅደስን አያት ብታየው በተደበቀች ነበር ግን አላየችውም በጦጣዎቹ ሁኔታ እየሳቀች ካሜራዋን ደቅና እየቀረፀች ነው
ጌዲዮ የልቡን ጀግና በተመስጦ እያደነቀ ለደቂቃዎች ሲያያት ቆይቶ ፊትለፊቷ ሄደ ከዛም እረጋ ባለ ድምፅ መቅዲ አላት መቅደስ በድንጋጤ ጮሀ አውቃ ፌንት እንደነቀለ ሰው እጁ ላይ ወደቀች እሱም እውነቷን መስሎት ሊያነቃት ብዙ ጣረ ከዛም የያዘውን ሀይላንድ ውሀ እላይዋ ላይ ደፋው ሆን ብላ እያለከለከች ነቃች
................እሱም ምነው ምን ሆንሽ አላት እሷም እንዴ አስደነገጥከኝ እኮ አለችው በርግጥ ከሚባለው በላይ ደንግጣለች ከዛም እንደማያቅ ሆና ቆይ እዚህ ምን ታደርጋለህ አለችው ጌዲም እኔማ በብዛት እዚህ ነው የማጠናው ይልቅ አንቺ እዚህ አስፈሪ ጫካ ብቻሽን ምን ታደርጊያለሽ አላት መቅደስም አምጣ አምጣ ምን መሰለህ የሆነ የፎቶ ኤግዚቢሽን አለብኝ እናም ለዛ ነው ስትለው ተቆጣት እንዴ ቢሆንስ ቢያንስ ከጓደኞችሽ ጋር አትመጪም ቆይ እኔ እንዳገኘሁሽ አውሬ ቢያጋጥምሽስ በሁኔታው ደስ አላት በርግጥ ማንም ቢሆን የሚያፈቅረው ሰው ሲጨነቅለት ያስደስተዋል መቅደስም ያ ደስታ ነው የተሰማት ቀጥላም እሱን ጠየቀችው እሱም ከልጅነቱ ጀምሮ የለመደው እንደሆነ ነግሯት መንገድ ጀመሩ
መቅደስም ልክ እንዳዲስ ሰው መወለጋገድ ጀመረች ጭራሽ መሄድ ያቃታትም መሰለች ጌዲዮ በጆቹ ደገፋት እሷም ይህንን ስለነበር የፈለገችው ፈገግ አለች ግቢም ሲገቡ እንደደገፋት ነበር ነገሩ ብዙውን ተማሪ አስገርሟል።
.......ዶርም ስትገባ እነ ሰአዳ ቆይ አብረን እናጠናለን ተባብለን የለም እንዴ ምነው ቆየሽ አሏት እሷም ከነሱ ምንም ስለማትደብቅ ነገረቻቸው ከዛም ጥናት ጀመሩ ወይንሸት ግን ማጥናት አልፈለገችም ቢሆንም መቅደስ በግድ ያዘቻት ከዛም በጋራ የሚያጠኑትን ሲጨርሱ በግል እንዲሰሩ ጥያቄ ሰጠቻቸውና ወይንሸትን ብቻዋን ማስጠናት ጀመረች ግን ምንም ሊገባት አልቻለም ሀሳቧ ሁሉ አብሯት የለም መቅደስ ተበሳጨች ብርሀን በሁኔታቸው እየሳቀች መቅዲ አትልፊ ወይንሸትን እኮ እንኳን አንቺ ጌዲዮ ቢያስጠናትም አይገባትም ስትል ወይንሸት በንዴት ትራስ ወረወረችባት።
.......መቅደስ ብርሀን እንደዛ ስትል አንድ ሀሳብ መጣላት...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...
...............በንጋታውም ልጠይቀው ከክፍል እስኪወጣ ምንገድ ላይ ጠበቀችው ከዛም ሁሉም ተማሪ ወቶ ሲያልቅ መጨረሻ ላይ አቀርቅሮ መጣ መቅደስ ምን እንደምትለው እየተለማመደች ነበር ግን እሱን ስታየው ሁሉም ጠፋባት እንደደረሰም አያትና ሰላም ሊላት ተጠጋ እሷ ግን ደንግጣ ስለነበረ አንደበቷ ተያይዞ እጇ እየተንቀጠቀጠ ለሰላምታ መዘርጋት አቃተው ጌዲዮም ምን ሆነሽ ነው አላት እሷም በመጠየቅና ባለመጠየቅ መሀል ሆና አይ ምንም ስትለው የሆንሽውማ ነገር አለ ለምን አትነግሪኝም አላት እሷም እእእ ጎበዝ ተማሪ አይደለክ አለችው እሱም ማለት አላት ማለትማ የፈተና ዝግጅት ስለከበደኝ እንድታስጠናኝ ነው አለችው ቁና እየተነፈሰች ጌዲዮም እንዴ እኔ አንቺን ቀለሜ አይደለሽ እንዴ አላት መቅደስም ካልተመቸህ ችግር የለውም ስትለው አረ ለዛ አይደለም ማንም አስጠናኝ ብሎኝ ስለማያቅ ገርመሽኝ ነው እንጂ ማስጠናቱን አለመፈለግ አይደለም ደስ ካለሽ ከትምህርት ሰአቴ ውጪ ማጥናት ስትፈልጊ ሁሌም ጥሪኝ ይመቸኛል አላት ጥያቄዋን በፍጥነት ስለተቀበላት መቅደስ ደስ አላት።...............
.........ይሄኔ ዮናስ ካፌ ቁጭ ብሎ እያያቸው ነበር በሚያየው ነገር ተበሳጨ የውርርዱ የመጨረሻ ወር ላይ ነው ያለው ግን ይበልጥ ያሳሰበው የውርርዱን ብር ማጣቱ ሳይሆን በማንም ተሸንፎ የማያውቀው ዮናስ ባንድ ሴት ክብሩ ሲነካ መሸነፉን ግቢው ሲያወራ ገና ካሁኑ ታይቶት ነው ከዛም የፍቅር ጥያቄ ሊያቀርብላት አሰበ።
................ጌዲም መቅደስን ይዟት ላይብረሪ ገቡና መፃህፍትን ይዘው ወጡ ከዛም ቀጥታ ወደጫካ ሄዱ እዛም አጥንተው ለነገሩ ምን አጥንተው እሱ ለፈለፈ እንጂ መቅደስ አንዱንም አልሰማችውን ከዛም እንደጨረሱ እንሂድ ሲላት አይ ለምን ትንሽ አንጫወትም ቦታው ደስ ይላል አለችው ደስ ካለሽ እሺ አላት ጌዲዮ ከማንም ጋር አፍ ለአፍ ገጥሞ አውርቶ ስለማያውቅ በመሀከላቸው ዝምታ ሰፈነ ከዛም መቅደስ እኔ እምለው እስኪ ታሪክህን አጫውተኝ ብላ ጠየቀችው እሱም መጀመሪያ አንቺ ንገሪኝና እነግርሻለሁ አላት ትንሽ አንገራግራ ቀጠለች.......
......ተወልጄ ያደኩት አ.አ ለገሀር የሚባለው ሰፈር ነው የልጅነት ጊዜዬ እንደማንኛውም ህፃን ደስ የሚል ነበረ ሁለት ወንድምና አንድ እህት አሉኝ የቤታችን የመጨረሻ ልጅ እኔ ነኝ ሁሉም ታላቆቼ ናቸው አባቴ የአ.አ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነው እናቴ ደግሞ ከፍተኛ የመንግስት ቢሮ ነው የምትሰራው ሁለቱም የተዋወቁት አባዬ መምህር እማዬ ተማሪ ሆነው ነበር አሁን ላይ ጥሩና ስኬታማ ቤተሰብ አለን ሁሉም ወንድምና እህቴ የማዕረግ ተመራቂ ናቸው እኔም ጠንካራ እንድሆን ዘውትር ያበረታቱኛል እንደውም የውጪ እድል መቶልኝ አልፈልግም ብዬ ነው ዛሬ ላይ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ትምህርቴን የምማረው ምክንያቱም ሳይማር ያስተማረኝን ህብረተሰብ እኔም ወግ ደርሶኝ ማገልገል እፈልጋለሁ ይህንን ሳደርግ ከቤት አንድም ተቃዋሚ አልገጠመኝም በቃ ይኸው አሁንም እየተማርኩ ነው እልሀለሁ አለችው ጌዲዮም ዋዉ የሚያስቀና ቤተሰብ ውስጥ ነው የበቀልሽው አላት መቅደስም አመሰግናለሁ ስትለው አረ ምንም አይደል ደግሞ ተምረሽ አንቺም ጥሩ ቦታ እንደምትደርሺ አልጠራጠርም አላት ................
.........ከዛም የሱን እንዲነግራት ስጠይቀው ነገ ዲያሪውን አገላብጦ መጥቶ እንደሚነግራት ቃል ገብቶላት ተነስተው ወደግቢ ተመለሱ .........
ልክ እንደተለያዩም ዮናስ አስቆማት እሷም ሰላም ካለችው ቡሀላ በጣም ለጥብቅ ጉዳይ እፈልግሻለሁ አላት እሷም ምን እንደሆነ ስጠይቀው ማታ እራት እየበላን እነግርሻለሁ ብሎ ትልቅ ሆቴል ከምሽቱ ሁለት ሰአት እንድትመጣ ጋበዛት በፍፁም እንዳትቀርም አስጠነቀቃት እሷም የማትረሳው ውለታው አስገድዷት ውስጧ
ቢደነግጥም ፍቃደኛ ሆነች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
➕➡️
➕➡️
➕➡️
➕➡️
➕➡️
➕➡️
አሁኑኑ ያናግሩን
@ethio3254
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 4️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
........እሱም ከፍቶ ሲያነበው ስማ አንተ በሽተኛ ነግሬህ ነበረ መቅደስ የኔ ናት ለማንኛውም እንድታምነኝ ስል ዛሬ ምሽት የፍቅር ጥያቄ አቀርብላታለሁ ከቻልክ መጥተክ መታደም ትችላለህ ዮናስ ይላል እሱም ወሬኛ ብሎ ደብዳቤውን ቀደደና ወደዶርም ሊመለስ ሲል መቅደስን በዛ በጨለማ ንግስት መስላ ከግቢ ስትወጣ ከሩቅ አያት ጌዲዮ ማመን አቃተው ባይፈልግም ፍቅር ነውና ተከትሎ መጨረሻቸውን ሊያይ ከኋላዋ ተከተላት.........
.........መቅደስ ባላት ሰአት ሆቴሉ ገባች ባይኗም ብዙ ወንበሮች ላይ ፈለገችው የለም ከዛም አንድ ወንበር ይዛ ተቀመጠች አስተናጋጅ ፊትለፊቷ መጥቶ ምን ልታዘዝ አላት እሷም ሰው እጠብቃለሁ የሚል መልስ ሰጠችው ከቆይታዎች ቡሀላ ሌላ አስተናጋጅ መጣችና መቅደስ አለቻት እሷም አዎ ነኝ ኦኬ ተከተይኝ አለቻት መቅደስም ግራ በመጋባት ወዴት ስትላት ዮናስ የተባለ ደንበኛችን ነው ይዘሻት ነይ ያለኝ አለቻት እሺ ብላ ተከተለቻት ሁለተኛ ፎቅም እንደደረሱ ስለደረስን አይንሽን ላስርሽ ነው አለቻት መቅደስ ይበልጥ ግራ በመጋባት እኮ ለምን ስትል አርጊ የተባልኩትን ነው ብላ አይኖቿን አስራ ግን ግለጭ ሳትባይ ምንም እንዳታዪ አደራ ብላት የፎቁ በረንዳ ላይ አድርሳት ተመለሰች ዮናስም ከጥቂት ደቂቃ ቡሀላ ግለጪ አላት መቅደስ የታሰረችበትን ጨርቅ ካይኖቿ ስታነሳ የምታየው ነገር ህልም መሰላት አበባ ተጎዝጉዞ ምሽቱ በሻማዎች ደምቆ አለ የተባለ መጠጥ ቀርቦ ዮናስ አንዲት ቀይ ፅጌሬዳ ይዞ ፊቷ ተንበርክኳል
.......በዛ ሰአት ጌዲዮ ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት ውስጥ ህኖም እያያቸው ነበር.....
መቅደስ ግራ ገባት ላንድም ቀን ዮናስን በዚህ መልኩ አስባው አታውቅም ዮናስ ምን እየሆንክ ነው አለችው እሱም ክሽን አድርጎ በሚያወራት አስመሳይ ግን ጣፋጭ በሆነ አንደበቱ መቅዲ ካየሁሽ ቀን ጀምሮ አፍቅሬሻለሁ የልቤ እመቤት አድርጌ ሾሜሻለሁ መቅዲ አንቺ ከማንም በላይ ለኔ ልዩ ነሽ እስከ ሂወቴ ፍፃሜ ያንቺ ብቻ ልሁን ፍቀጂልኝና የፍቅርሽ ባሪያ ልሁን አያለለ ዜማ ቢጨመርበት አንድ ክሊፕ የሚሰራውን ዜማውን አፈሰሰባት ከዛም መቅደስ ምን እንደምትል እንኳን ግራ ገብቷት እየውልክ ዮናስ ይሄን ላረግ አልችልም ብላ ከተንበረከከበት እጆቹን ይዛ አስነሳችው ዮናስ ደሙ ፈላ ግን ለምን አላት እየውልክ እኔ የኔ የምለው የማፈቅረው ሰው አለኝ አንተን ወንድሜ እንጂ ፍቅረኛዬ ላደርግህ አልችልም ዮኒ የእውነት በጣም አዝናለሁ እኔ ያንተ ልሆን አልችልም በቃ ውለታውን በዚ መልኩ ልትከፍለው እንደማትችል ነግራ በጣም አስተዛዝናው ተመልሳ ሄደች ልክ እሷ እንደተመለሰች
ጌዲዮ ፊትለፊቱ ሄደና ስማ መቅደስን እንኳን በውንህ በህልምህም የግልክ አታደርጋትም የእውነት ግን በራሴ አፈርኩ አንተን አምኜ እዚህ ድረስ መልፋት አልነበረብኝም ይህንን ትርኪ ሚርኪህን በለመድካቸው ላይ ግን ለዚህ ሁሉ ወጪ ስንት ብር ፈጀብህ እያለ የዮናስን ንዴት በእጥፍ ጨምሮ ሄደ ዮናስ መጠጡን እየገለበጠ በፍቅር እንቢ ካልሽ የበቀል ልቡን አሳበጠው........
...........ከዛም በንጋታው ጌዲዮና መቅደስ ተያይዘው ለጥናት ወደጫካው ሄዱ አጥንተውም እንደጨረሱ ታሪኩ እንዲነግራት አስገደደችው እሱም
.....እኔ ምንም ሌላ ታሪክ የለኝም ታሪኬ አንድ ግን ብዙዋ እናቴ ናት ተወልጄ ያደኩት በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ጃማ የሚባለው ገጠራማ ስፍራ ነው አባቴን አላውቀውም በልጅነቴ ነው የሞተው ከኔ በፊት እናቴ ሶስት ልጆች ሞተውባታል እኔንም ስለት ተስላ ነው ያደኩላት ግን ባድግም የአራት አመት ልጅ እያለሁ በየቦታው ይጥለኝ ጀመር እማ በሀዘን ላይ ሀዘን ተጨመረባት አስበሽዋል ሶስት ልጆቿን ባሏን ያጣች ሴት መከራ በዛላይ እኔም በሽተኛ መሆኔ አላፊው አግዳሚው አላስቀምጥ አላት ያባቴ ዘመዶችማ ለነገሩ እሷ ስላለችኝ እንጂ እንኳን ያባቴን የራሷንም ዘመዶች አላቃቸውም ምክንያቱም የሷ ቤተሰቦች እንድታገባ ሲለምኗት አሻፈረኝ ካገባሁ ልጄ ይጎዳብኛል ስላለች እስከዛሬ ድረስ ማንም የሚፈልጋት የሚጠይቃት የለም አየሽ እናቴ ለኔ ስትል ስንት ነገር እንዳጣች አባ ሲሞት ቆንጆ ወጣት ነበረች ብታገባ ኖሮ እንደ ወንድ ሞፈርና ቀንበር አንዴ ከጓሮ አንዴ ከጓዳ ባልተንከራተተች ነበር ግን ለኔ ስትል ሁለት መልክ አወጣች መከራ ትንሽ ነው ብዙ ብዙ ነገር አየች
እኔ እናቴ የማስደስታት ቀንበር ይዤ ስከተላት አልነበረም ጓሮ ሄጄ ስቆፍር እንጨት ስሰብርላት አይደለም እውነተኛው የናቴ ደስታ ደብተር እስኪቢርቶዬን አንግቤ ለትምርት ስወጣ ነው ብዙ ጊዜ ትምርት አልማርም እላታለሁ እሷ ግን ምክንያቴን ስለምታውቅ ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶም እንዳላየ ሁን ትለኛለች እዚህ ለመድረሴ የናቴ ትልቁ ምክሯ ይህ ነበር የልጆች ጨዋታን እየተጫወትኩ ሳይሆን እያየሁ እየዘመርኩ ሳይሆን እየሰማሁ ነው ያደኩት ማንም ልጅ ከኔ መጫወት ቢፈልግ እንኳን አይችልም ምክንያቱም የትኛውም እናት አባት አይፈቅድም መቅዲ እኔኮ ከሰው ጋር ስሆን አይደለም የሚያመኝ ግን ማንም አይረዳኝም ብሎ ለብዙ ግዜ ያመቀው ቁስል ስለሆነ ዛሬ ግን ፈነዳና አመመው ሳይጨርስላት እንባው ቀደመው አስተዳደጉ በሙላ አይኑ ላይ ተስሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ መቅደስም አንጀቷን በልቶት አብራው አለቀሰች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...🖌ጌዲዮ እንደምንም እንባውን ጠራርጎ ታሪኩን ቀጠለላት አየሽ እኔን ማንም ከሰው ተራ ቆጥሮኝ ስላላደኩ ዛሬም ሰው እፈራለሁ ብቸኝነቴን እመርጣለሁ ዝምታዬን እወደዋለሁ ለኔ የመኖር ምክንያቴ እናቴ ናት እሷ ናት ታሪኬ እንዳባት ሞፈር ተሸክማ እንደህት መክራ እንደወንድም ጋሻ ሆናኝ ከናት በላይ ብዙ ሆና ያኖረችኝ ታሪኬ እናቴ ብቻናት አየሽ መቅደስ አንቺ እኔን ከመደገፍሽ በፊት ከናቴ በቀር ማንም ጎንበስ ብሎ አንስትትምኝ አያውቅም ለዚም ነው አንቺን እንደናቴ ያየሁሽ አላት ሳያውቀው ለሷ ያለውን ስሜት ነገራት መቅደስ እጆቿን ከጉንጩ ሰዳ እንባዉን ጠረገችለት
ለብዙ ጊዜ ፍቅራቸውን እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ሲጨነቁ የነበሩት ጥንዶች ዛሬ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አንድ ሜዳ ላይ ተገናኙ በርግጥም እውነተኛ ፍቅር የቃላት ድርደራ አይፈልግም ለካ እውነተኛ ፍቅር ባይን ጥቅሻ ብቻ ያግባባል በቃ በዝምታ ተያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌዲዮ ከንፈሩን ከሴት ከንፈር አገናኘው መቅደስ ለብዙ ጊዜ የናፈቀችውን ጌዲን በቅፎቿ አስገባችው በቃ ያለምንም አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ያለማንም አጃቢ በከንፈራቸው ቃልኪዳን አሰሩ
የፍቅር ድግሳቸው ትተጠነሰሰ ማንም ባይገምትም የጌዲዮና የመቅደስ ፍቅር እውን ሆነ የዛኑ ቀን ነበር ግቢው ይህን እውነት የሰማው ዮናስ ጌሙን ባደባባይ ተሸነፈ መቅደስ ከሱ ቁንጅና ይልቅ የጌዲዮ መልካምነት አሸነፋት ከዮናስ ማስመሰል የጌዲዮ ፍቅር በለጠባት የውጭ ማንነቱን ሳይሆን በውስጥ መልካም ስብእናው ባደባባይ የጌዲዮ ነኝ አለች
ዮናስ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አይነት ጌም ሲሸነፍ ከፍተኛ ገንዘብና እሱ የሚያምንበትን ክብሩን አጣ የመጨረሻ እርምጃ ያለውን በቀል በውስጡ አበቀለ በክፋትም ሊጥላት አሰበ
ጌዲና መቅዲ ግን ግቢውን ያስቀና ፍቅር ጀመሩ አይቶ ካይን ያውጣችሁ የማይል ምቀኛ ብቻ ነው በፍቅራቸው አልተደነኩም የሚል ካለ ውሸታም ነው...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...🖌ጌዲና መቅዲ ባሁን ሰአት ለደቂቃ እንኳን መለያየት ይከብዳቸዋል በቀን ቀን ፍቅራቸው እየጨመረ አማላይ ጥንዶች ሆነዋል
ጌዲም በብዙ ነገር ተቀይሯል አሁን ከሰው ጋር ይውላል ከክፍል ጓደኞቹም ጋር ይጮታል አብሮ ይበላል አብሮ ይጠጣል በመዘነጥም ቢሆን የግቢውን ቆንጆዎች አስንቋል ግን ለዚህ ሁሉ መሆን መቅደስ በፍቅሯ ቃል አስገብታው ነው
አረ አሁንማ ከማድነቅ አልፈው ብዙ ሴቶች ለፍቅር እየተመኙት ነው ጌዲ ግን በፊቱ ፋሽን ሾ ሲሰሩ ቢውሉም ዘወር ብሎም አያያቸውም በርግጥም ትክክል ነው የፍቅር ጀግና የሚባለው መቶ ያሰለፈ ሳይሆ ከመቶዎቹ ላንዷ ብቻ መኖር ሲችል ነው መቅደስም ብትሆን ለማንም ቦታ የላትም ግን አንዳንድ ሰዎች ግርም ይሉኛል ወድቆ እያዩት አይጠቅምም ብለው ያላነሱት ነገር ሌላ ሰው አንስቶ ሲያዩ ለምን ቅጥል እርር እንደሚሉ አይገባኝም......
ጌዲዮ ካፌ ቁጭ ብሎ ሻይ እየጠጣ መቅደስ ከክፍል እስክትወጣ እየጠበቃት ነው አንዲትም ልጅ መጥታ አጠገቡ ተቀመጠች ጌዲዮም ይቅርታ የኔ እህት ወንበሩ ተይዟል አላት እሷም በተሞላቀቀ አፏ እኔ ሰው አይደለሁ ስትለው እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ፍቅረኛዬን እየጠበኳት ነው ስለዚህ ቦታ ቀይሪ ብሎ ሳይጨርስ ምን መቅደስን አይደል ሶ እኔ ከሷ በላይ ፍቅርን ልሰጥህ ዝግጁ ነኝ ብላ ጠረንቤዛው ላይ ያረፉትን እጆቹን ጭብጥ አርጋ ያዘችው መቅደስም እየመጣች ስለነበረ ፊትለፊት እያየቻት ነበር ጌዲዮ እጇን ከጁ አመናጭቆ አስለቀቃት በጥፊ ሳልልሽ ተነስተሽ ከፊቴ ጥፊ ብሎ ሲጮህባት ደንግጣ እየበረረች ሄደች መቅደስ ፊቷ በደስታ ተሞልቶ በፈገግታ ታጀበ እንደደረሰችም አቅፋ ሳመችውና ተቀመጠች ........
.........ጌዲዬ ዛሬ ላይብረሪ እናጥና ድብርብር ብሎኛል አለች መቅዲ ከደበረሽ ለምን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን አንመጣም አላት መቅደስም ደስ ይለኛል ነጠላዬን ላምጣና እኔዳለን አለችው።
ከግቢም ሲወጡ ዮናስ አያቸው ወዲያው ወይንሸት ጋር ደውሎ ጠራት ከዛም ይዟት ወጣ እሷም ዮኒ ምን ፈልገክ ነው እዚሁ ንገረኝ ካንድ ሰአት ቡሀላ መቅደስ አስጠናችኋለሁ ብላናለች ስትለው ዮናስ ዶማ አጠና አላጠና ያው ዶማ እኮ ነው አላት ወይንሸት ንቀቱ አናደዳት ውስጧ ገብቶ ነዘራት መልሳ ዶማ እያልከኝ ነው አለች እሱም ገብቶሻል አታድርቂኝ ሲላት አሁን ትርፍ ማውራትህን አቁመህ ምን እንደፈለክ ንገረኝ አለችው እሱም ቀለል አርጎ ወደማታ መቅደስን እኔ ጋር እንድታመጪያት ነው አላት ወይናም ዮናስ ውላችንን የጨረስን መሰለኝ የተሰጠኝን ግዳጅ ባግባቡ ተወጥቻለሁ ውርርዱን የተሸነፍከው በራስህ ድክመት ነው ታዲያ ምን ችግር አለው አዲስ ውል እንዋዋል ገንዘብም ቢሆን ከባለፈው በላይ እከፍልሻለሁ ሲላት ወይና ፊቷን አኮሳትራ
......በቃኝ ዮናስ በቃኝ አልፈልግም አለችው እሱም ምኑ ነው የበቃሽ አላት በቃ ከዚህ ቡሀላ ካንተ ጋር መስራት አልፈልግም አለችው እሱም እየቀለድሽ መሆን አለበት ዮናስ እየቀለድኩ አይደለም በሀጢያት መጨማለቅ መሮኛል አይገርምህም መቅደስን እስከዛሬ የበደልኳት እየቆጨኝ ነው ደግሜ ሌላ ስተት መስራት አልፈልግም አለችው ወይንሸት የተቀየረችበትም ምክንያት ትላንትና ተደውሎላት አባቷ በጣም እንደታመመ ሲነግሯት ስታለቅስ መቅደስ አየቻት ምን እንደሆነችም ስጠይቃት አባቷ መታመሙን ነገረቻት መቅደስም በየዋህ ልቧ አብራት እያለቀሰች እግዚአብሔር ይረዳቸዋል ደግሞ አንቺን የመሰለ መልካም ልጅ አላቸው አይደል አይዞሽ ፀልዪ እኔም እፀልይልሻለሁ ብላ ስታፅናናት በደሏ ተሰማት ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ውስጧ ሲረበሽ ነበር ለዚያም ነው ዛሬ ለዮናስ ገንዘብ አልፈልግም ያለችው ዮናስ ግን............
መቼም ጨክነሽ ባባትሽ ነብስ አትፈርጂም ሲላት ስማኝ ይኸው ካይስኩል ጀምሮ በነውር በሀጢያት በምሰበስበው ገንዘብ አሳከምኩት ግን ዳነ አልዳነም አየህ እግዚአብሔር ካላለ እኔ ስላልኩ ወይም ማንም ስላለ አባቴ አይሞትም ደግሞ ቆሽሼ ከማገኘው ገንዘብ ንፁ ፀሎቴ ይሻለኛል መቼም ከዚህ ቡሀላ ወደኋላ አትመልሰኝም መቅደስ ጥሩና ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ነው ያለችው ደግሜ ልበጠብጣት አልፈልግም ደግሞ የማላቅ አይምሰልህ ሆን ብለክ አንድ ዩኒቨርሲቲ እንዲደርሰን የጣ ድልድሉ ውስጥ እጅህን ያስገባኸው እኔ ካንተ ከማገኘው ጥቅም በላይ አንተ ከኔ የምታገኘው ጥቅም ስለሚበልጥ ነው ለፍቅር ብቀርብህም አንተ ግን ከየትም እንደተገኘ ገላ ተጫወትክብኝ መጫወትክም ሳያንስ አሳልፈህ ለሹገር ዳዲዎች ሸጥከኝ እኔ ከማገኘው መቶ ፕርሰንት ዘጠናውን አንተ እንደምትወስድ አውቃለሁ ግን አስሯ ፕርሰንት ላባቴ መኖር ምክንያት ስለመሰለችኝ የከተትከኝ ሀጢያት ውስጥ እንደተስማማኝ ሆኜ ኖርኩኝ በርግጥ የኔን ትክክለኛ ማንነት ማንም አያውቅም ግን ይሁን እስከዛሬ ያልሆንኩትን ሆኜ ብኖርም የኖርኩትም ላባቴ ቢሆንም ባርቴፊሻል ማንነቴ አባቴ ድኖ ከሚያዝንብኝ በትክክለኛው ማንነቴ የሆነውን ቢሆንም ወይና አባቷን እጅግ ከሚባለው በላይ ስለምትወደው እንባዋ እንደጎርፍ ወረደ
ዮናስም እንዳመረረች ሲረዳ ኦኬ እንደዛ ከሆነ መቅደስ ላይ ያረግሽውን ሁሉ አንድም ሳይቀረኝ እነግራታለሁ ይህ ወሬ ተማሪዎች አወቁ ማለት ሳምንት እንኳን እዚህ ግቢ አትማሪም እኔን እንደሆነ አንዴ ጠልታኛለች የሆነው ቢሆን ማንም ከቁብ አይቆጥረኝም አንቺን ግን ሲላት ሰውነቷን ድንጋጤ ወረረው ዮናስ አታደርገውም አለችው ከት ብሎ ሳቀባት ዮናስ እኮ ነኝ ጭካኔዬን ያኔ ካይስኩል ጀምሮ ከማንም በላይ ታውቂዋለሽ አላት
ወይንሸት ከመስማማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም እሺ ግን እንዴት ብዬ ለፍቅር ከመጠየቅክ በላይ ደጋግመክ ጌዲዮን እንድትጠላው ለማድረግ በመሞከርክ ላይኗ እንኳን ጠልታሀለች ታዲያ የት ምን ብዬ ነው የማመጣት አለችው
ለሱ አታስቢ ወክ እናርግ ብለሽ ውስጥ ውስጡን ትወስጂያታለሽ ከዛም እላይኛው ጫካ ጋር ስትደርሱ ሁለታችሁም የታፈናችሁ አስመስለን አንቺን በጎን ይወስዱሻል እሷ እጄ ትገባለች...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 7️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
...
........ከዛም ቀጥታ በጣም አስፈሪና ጨለማ የሆነ ቦታ ወሰዷት ማን ይያዛት ማን ይልቁቃት ምንም አታውቅም ወዲያው አንዱ በደንብ ያዛትና አንዱ አደንዛዥ እፅ ወጋት ከዛም ከቆይታ ቡሀላ ሁለቱ ወንዶች ጥለዋት ወጡ ከመውጣታቸውም ሶስተኛው ዮናስ ዋሻ የመሰለውን አስፈሪ ቤት መብራት አበራው........
......በሰአቱ ሌላ ሰው ሆና ነበር ምንም አታስታውስም ዮናስንም እንዳየችው ዋው ምን አይነት ውበት ነው አለችው እየተቅበጠበጠች እሱም ታዲያ ስንቱ ያረገደለትን ውበት እንዴት እረግጠሽው ሄድሽ አላት እሷም ግራ በመጋባት እኔ አለችው
...አዎ አንቺ አላት ቀጥላም አረ ይሄን የመሰለ ገላ እንቢ ብል እራሱ ሀጢያት ይሆንብኛል ስትለው የወጓት እፅ መስራቱን ተረዳ........
.........ሊበቀላት ያሰበው በህዝብ መሀል ነበር ዛሬ ደግሞ የቀወጠ ፓርቲ አለ ለዛም ነው ይህንን ቀን የመረጠው....
......መጨፈር ትፈልጊያለሽ አላት እሷም አዎ በደንብ አለችው እየተሻሸችው እሺ እንደዛ ከሆነ ዛሬ ፓርቲ ስላለ አብረን ሄደን እንቀውጠዋለን አላት በደስታ ዘለለች አቀፈችውም እሱ ግን ከዛ በፊት ባንድ ነገር እንስሜ አላት እሷም ምንድነው አለችው
ቀጠለ ማንም ሰው ዮናስ ምንሽ ነው ቢልሽ ፍቅረኛዬ ነው ትያለሽ አሁንም መቅደስ ግራ በመጋባት ዮናስ ማነው አለችው እሱም እየውልሽ ዮናስ ማለት እኔ ነኝ ለዛሬ ማለትም ለፓርቲው ፍቅረኛሞች ሆነን ነው የምንታየው ገባሽ አላት እሷም በደስታ ተስማማች.....
.....ገና ተቃቅፈውም ሲገቡ ብዙ የሚያውቋት ተማሪዎች ስለነበሩ ሰላም ሊሏት ተጠጉ እሷ ግን ማንንም ልታውቅ አልቻለችም ግራ ተጋቡ መቅደስ መንታ እህት አላት እንዴ እስከማለት ደረሱ እውነትም ታስብላለች ቅብጥብጥ ብላ ዮናስ ላይ እንደማስቲሽ ተለጥፋ ለመጣው ለሄደው ትስቃለች ምንም አላሳፈረችውም አንዴ ካንገቱ አንዴ ከወገቡ እየተጠመጠመች ትስመዋለች ለማያውቃቸው አዲስ ፍቅረኛሞች ነው የሚመስሉትግን አብዛኛዎቹ የጌዲዮ ፍቅረኛ መሆኗን ስለሚያውቁ ግራ በመጋባት ጭፈራቸውን አቁመው እነሱን ያያሉ....
.......ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ግን ዮናስ እንዳሰበው ሳይሆን ተቃራኒ ሆኖ በቀሉን ከግብ ሳያደርስ ጌዲዮ ፊቱ በርበሬ መስሎ እሳት ለብሶና ጎርሶ ከፊትለፊቱ ቆመ
ዮናስ የታወቀ ተደባዳቢ ስለሆነ አልፈራውም...ከዛም ጌዲዮ መቅደስን ከቅፉ ጎትቶ አስወጣት እሷም ምንድነው ብላ ጮኸችበት ዮናስም ፈልጋ እንጂ አስገድጃት እኮ አይደለም ምን ያበሳጭሀል አለው ጌዲም የመቅደስን ጉንጮች በሁለት እጆቹ ይዞ አይናይኗን እያየ መቅዲ ምንድነው የተፈጠረው አላት እሷም ማናት መቅደስ ምንድነው የምታወራው ብላ መልሳ ከጠየቀችው ቡሀላ ወደ ዮናስ ዞራ ፍቅር ምን ፈልጎ ነው አለችው...ዮናስም መልስ ለመመለስ ሲቃጣ ሁኔታዋ ግራ ያጋባው ጌዲዮ ምን አርገሀት ነው ብሎ ከመቅፅበት በቦቅስ አፍንጫውን ሲለው ዮናስ ደም በደም ሆነ የፓርቲው ሙዚቃ ባንዴ በጩኸት ተቀየረ.........
.........ዮናስ ደሙን ጠራርጎ ሊመታው ሲል እንዳልነበር አርጎ ቀጠቀጠው ከዛም የዮናስ ጓደኞችም ተጨመሩ ቢሆንም ከጌዲዮ ቦቅስ ተቋደሱ እንጂ አላስጣሉትም ምናልባት አንድ ሁለቴ እንጂ ከዛ በላይ አልተመታም ጌዲዮ በቃ ከዚያን ቡሀላ ቆሞ የሚቀርፅና የሚጮህ እንጂ አገላጋይ ጠፋ ብዙ ተደባደቡ......
......ጌዲዮ በበሽታው ይፈራል እንጂ ከማንም ጋር ተደባባድቦም ሆነ ተሰዳድቦ አያውቅም ነበር ዛሬ ግን በዝምታው ውስጥ ወንድነት ባንገት ደፊነቱ ውስጥ ጀግንነት መያዙን አስመሰከረ ወዲያው ነበር በሼር እየተቀባበለ ያየው............
......ብርሀንና ሰአዳም ወዲያው እንዳዩት እየበረሩ ቦታው ላይ ደረሱ ሲደርሱ ግን አካባቢው በፖሊስ ተከቦ ነበረ ወዲያውም መቅደስን ጌዲዮንና ዮናስን ጥያቄ እየጠየቁዋቸው ተመለከቱ......ፓሊሶቹም የማን እንደሆነች ሲጠይቋቸው ሁለቱም የኔ የኔ ማለትና መከራከር ጀመሩ ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ፓሊሶች ወደ መቅደስ አፍጥጠው የማን ነሽ አሏት እሷም ዮናስ እንዳላት የዮናስ ፍቅረኛ ነኝ አለች ጌዲዮ በሰላሟ እንደልሆነ ቢገባውም እንዲህ ስትል ደነገጠ ጓደኞቿም በድንጋጤ አፋቸውን ይዘው ደርቀው ቀሩ...
ወዲያውም ፓሊሶቹ ጌዲዮን እስር ቤት ዮናስን ደግሞ በጣም ደም እየፈሰሰው ስለነበር ሆስፒታል ይዘዋቸው ሄዱ።
መቅደስን ደግሞ እንደምንም ብለው በጌዲ መታሰር በሀዘን ተኮራምተው ግን ምንም ማድረግ ስላልቻሉ ወደ ዶርም ይዘዋት ሄዱ...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...
መቅደስ ቁጭ ብድግ አለች ምን አርገዋት ይሆን ብላ አሰበች ባይኗ እንባ ሞላ በርግጥ አፍነው ምን አረጉኝ ብላም ተጨነቀች ይበልጥ ግን የወይንሸት ነገር አሳሰባት እነብርሀንም ምን እንደተፈጠረ ጠየቋት እሷም የምታስታውሰውን ብቻ ነገረቻቸው እነሱም ካፈኗችሁ የምታስታውሺው አለ ብለው ጠየቋት ምንም እንዳላየቻቸው ነገረቻቸው........
......ሰአዳና ብርሀንም እርስ በርስ ተያይተው ይህን ያረገው ዮናስ መሆኑን ተረዱ......መቅደስም ፈጠን ብላ ለወይና እንድረስላት አለች ስልኳንም አንስታ ወደ ጌዲዮ ልትደውል አስባ ስልኳን ስትፈልግ አጣችው ሰአዳ ነበረች የደበቀችው መቅደስም የጠፋ መስሏት ብርሀን ስልክሽን ስጪኝ ጌዲ ጋር ልደውል አለቻት ብርሀንም ቻርጅ ዘግቷል አለቻት እሺ ሰአዳ አለች እሷም ምንም ሳንቲም የለውም አለቻት ኮልሚ ባክስ መልሳ ሰአደ በማፈር ስሜት አራቴ ስለላኩበት አይልክም አለች መቅደስ አይታባቸው የማታውቀው የመረበሽና የማይሆን ምክንያታቸው ግራ አጋባት ወዲያው በቃ ተዉት ዶርሙ እሄዳለሁ ብላ ስትነሳ ሁለቱም ጮኸው አስቀመጧት መቅደስ ይበልጥ ተንቀጠቀጠች ምን እንደተፈጠረ እንዲነግሯት ለመነቻቸው አጋጣሚም ሆኖ ስልኳን ከብርሀን ትራስ ስር አየችው..........
ከዚ በላይ ሊዋሹዋት ስላልቻሉ ከመጀመሪያ ጀምሮ እየተቀረፀ ሼር የተደረገላቸውን ቪዲዮ ተራ በተራ አሳዩዋት
.......መቅደስ የወጉዋት መርፌ እንደዛ እንዳረጋት ትረዳች ግን የኔ የምትለው ዮናስ ይሄንን ማድረጉ ሰው ማመን ቀብሮ ነው የሚባለው ተረት እውነት ነው አስባላት ወዲያውም ለባብሳ ጌዲዮ ወደታሰረበት ሄዳ ሁኔታውን አስረዳች በርግጥ ፖሊሶቹ አጭበርባሪ ቢሏትም ከግቢም ቢያስወጧት ወዲያው ወይንሸት ተሸፋፍና ይህንን ሁሉ ያደረገው ዮናስ ስለመሆኑ መረጃ ይዛ መጣች ወዲያውም ፈቱላት ጌዲንም እስከዛሬ በፍቅራችሁ ጣልቃ ገብቼ ስለበጠበጥኩ ይቅርታ አለችው ጌዲዮን በጥፋቱ እስከመጨረሻ የፀና እንጂ ጥፋቱን ተረድቶ ንስሀ የገባ ክፉና ወንጀለኛ አይባልም አላት አይኗ እንባ ሲሞላ አቅፎ አባበላት ምንም ብትበጠብጪንም ዛሬ ፍቅራችንን መልሰሽልናል ትላንት ባደውዪልኝ ኖሮ መቅደስ ላይ ሊፈጠር የሚችለው አደጋ ከባድ ነበር ስለዚ በፍቅራችን ስም ላመስግንሽ አላት ወይና በደስታ እንባዋን ጠራርጋ በቃ አንተ ሂድ የዮናስ አይን ብዙ ስለሆነ ካየኝ አይለቀኝም ብላ መልሳ ተሸፋፍና ቻው ብላው ሄደች......
ፖሊሶቹም ወዲያው ወንጀለኛውን ዮናስን ፍለጋ ሀይል አሰማሩ ወይናም ወዲያው ከጌዲዮ ትንሽ እንደራቀች በመኪና አፋፍሰው ወሰዷት.........
ጌዲዮ ግቢ እንደደረሰ ለመቅደስ ደወለላት እሷም ቅድም ደማምቶ በዛ ላይ በሽታውም ተነስቶበት እንደነበር አይታም ተነግሯትም ስለነበር ተይዛ እያለቀሰች ነበር ስልኳም እንደጮኸ አንስታ ስታየው ጌዲ ነው በህልሟ በሀሳቡዋም መሰላት ብቻ በደመ ነብስ አንስታ ሄሎ...ሄሎ...ስትለው ተፈቶ ግቢ መናፈሻው ጋር እየጠበቃት መሆኑን ሲነግራት ህልሟን በውን ለማየት ስልኩንም ሳትዘጋ እየከነፈች ሄደች አንገቱም ላይ ተጠምጥማ ይቅርታ አውቄ አይደለም አለችው ጌዲዮ በትንፋሹዋ ተሸሽጎ እንደተረዳት ነገራት ወዲያውም የክፍል ጓደኞቹ መጥተው እያቀፉ በመፈታቱ መደሰታቸውን ገለፁለት ብርሀንና ሰአዳም መተው አቅፈው እንኳን ደስ አለህ አሉት እሱም ስለመልካም ምኞታቸው በፈገግታ አመሰገናቸው.....
ከዛም ሁለቱ ጥንዶች ተያይዘው መናፈሻው ውስጥ ገቡ ....
........ከዛም በስስትና በናፍቆት ትቅፍቅፍ ብለው ተ0ቀመጡ........
ወይንሸትን ዮናስ ጋር ወሰዷት ውይ ዮናስ ያ ውበቱ እርግፍ ብሏል ፊቱ ደረቱም ሳይቀር እዛም እዚም ታሽጓል እንዳያትም በጥፊ አጋጫት ምንም አላለችውም ደገማት የወይና ሰውነት እንደበረዶ ቀለጠ ለነገሩ መስሏት እንጂ ፖርቲው ላይ ጌዲዮ እንዲመጣ ማድረጓን እንጂ ማስፈታቷን አላወቀም ይህን ቢያውቅማ በነብስም አልተረፈች በቀጥታ መጥቶ አንገቷን አነቃት ለምን ለጌዲ እንደተናገረችም አፍጥጦ ጠየቃት እሷም የዛሬውን ማስፈታቱዋን አለማወቁ ሲገባት እኔ አይደለሁም ብላ ካደች ያሰበውን በቀል ከሷ ውጪ ማንም ስላላወቀ ክደቷ ይበልጥ አግሎት እንዳህያ እረገጣት ብዙም ከደበደባት እሷም ከዋሸች ቡሀላ እስኪ አባቴን ይንሳኝ አልተናገርኩም በይ አላርት ወይና ባባቷ በውሸት እንደማትምል ስለሚያውቅ እውነትም መማሉ ከበዳት እያለቀሰችም አዎ እኔ ነኝ አለችው ደግሞ በጥፊ ሲላት ሴትን ስለተማታህ ጀግና የምትባል መስሎክ ነው ወንድ ከሆንክ ትላንት መማታት ቢያቅትህ እንኳን እራስህን አትከላከልም ነበር ስትለው በብስጭት በቦቅስ ሲላት እስከታሰረችበት ወንበር ተዘረረች ወዲያውም ፖሊሶች በሩን በርግደውት ገቡ ያሉትንም ሁሉንም አፋፍሰው ይዘዋቸው ሄዱ...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል1️⃣ 9️⃣ ምሽት 3:20 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
...🖌መቅደስና ጌዲዮን መናፈሻው ውስጥ ተቃቅፈው ለብዙ ሰአት አልወጡም መቅደስ የቆሰለውን ፊቱን እየደባበሰች አይን አይኑን ታየዋለች እሱ ግን የወይንሸት ነገር አሳስቦታል በርግጥ መቅደስም በውስጧ እየተመላለሰችባት ነው ቡሀላም ጌዲ አለችው እሱም ወዬ መቅዲ ሲላት ትላንት ስታገት እኮ ወይንሸትም አብራ ታግታላቸ በዛ ላይ እስካሁን አልመጣችም እኔ ፈራሁ አለችው ወይና ስልክ ደውላም እንደነገረችው ቡሀላም መረጃ አቀብላ እንዳስፈታችው ለማንም እንዳይናገር በራሷ በመቅደስ ነው ያስማለችው
....ለምን አትደውዪላትም አላት አረ ብዙ ሞክረናል ስልኳ ዝግ ነው አሁንም ሞክሪ ከፍታው ይሆናል አላት ስልኳን አውጥታ ደወለች ዝግ ነው ደግማ ደጋግማ ሞከረች ቢያንስ አስሮ ከሞከረች ቡሀላ ጠራ መቅደስ ከተቀመጠችበት ተነሳች ጌዲዮን በተስፋ ያዳምጣት ጀመር ስልኩ ተነሳ ሄሎ....ሄሎ....ሄሎ.....ወይና የት ነሽ አለቻት ወይናም በሚቆራረጠው ድምጿ ከክሊኒክ እየወጣች ቢሄንም እዚሁ ነኝ እየመጣሁ ነው አለቻት መቅደስም ግን ደናነሽ ስትላት አዎ ብላ ዋሸቻት ከ15 ደቂቃ ቡሀላም ግቢ እንደምትመጣ ነገረቻትና ስልኩን ዘጋችው ጌዲዮም ችግር አለ አላት መቅደስም ድምጿ ጥሩ አይደለም ግን ደናነኝ ብላኛለች አለችው በቃ አትፍሪ ደና ትሆናለች ዶርም ሄጄ ልብሴን ቀያይሬ እመጣለሁ ሲላት ወይና እየመጣች ስለሆነ እኔ እዚሁ እጠብቅሀለሁ አለችው ግንባሯን ስሟት ሄደ።
..........ባለቻት ደቂቃ ወይና ግቢ ገባች መቅደስ ስታያት ደነገጠች ፊቷ ድልዝ ብልዝ ብሎ አልኮን ተቀብቷል አይኗ ገብቷል ጉንጯ ደግሞ አብጧል ጭራሽ ያቺ ቀበጧን ወይንሸት አትመስልም መቅደስ አቅፋ ምን እንደሆነች ጠየቀቻት ወይና ግን መልሷ ምንም አልሆንኩም ነበረ ብዙ ለመነቻት ፍንክች ዮናስ ነው አይደል ዝም መቅደስ ተናደደች እንዴ ፊትሽ እንደዚህ ባንዲራ መስሎ የምንብምንም አልሆንኩም ነው አለቻት ወይና አይኗ ግንባ ሞላ መቅዲ ይሄ ይገባኛል እንደውም እንደኔ በደል ሲያንሰኝ ነው አለቻት መቅደስ ግራ ገብቷት የተፈጠረውን እንድትነግራት ባባቷ ስም ለመነቻት እሷም ቤተክርስቲያ ሄደው እንደምትነግራት ቃል ገብታ ይዛት ሄደች......
.......ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንደገቡ ከጥላ ስር ቁጭ አሉ ወይና ከመጀመሪያ ቀን አንስቶ እስከዛሬ ያረገቻትን በንባ ጎርፍ እየታጠበች ነገረቻት ይህን ሁሉ ያረገችውም አባቷን ለማሳከም እንደሆነ እናም በግዚያብሄር ስም ይቅርታ እንድታደርግላት ከግሯ ተንበርክካ ለመነቻት መቅደስ ግን የሰማችውን ማመን ስለተሳናት ቃል ሳተነፍስ ጥላት እየተጣደፈች ወጣች አጋጣሚ ሆኖ የለቱ ጉባኤ የስብከት ፕሮግራም ላይ ደርሶ ነበር የስብከቱም ቃል ይቅር እንዳልኳችሁ ይቅር ተባባሉ ነው መቅደስ ይህን ቃል ስትሰማ ቆም ብላ አሰበች ቢሆንም ስጋዊ መንፈሷ እልህ አሲዟት መንገዷን ቀጠለች ቀጥታም ዶርም ገብታ ማንንም ሳታናግር ተጠቅልላ ተኛች ወይናም ትንሽ ቆይታ ከኋላዋ መጣች ሰአዳና ብርሀን ደነገጡ አንቺ በአላህ ምን ሆነሽ ነው አለቻት ሰአዳ ብርሀንም ቀጥላ አረ ምን ጉድ ነው በማሪያም መቅደስ ነይ እያት ብላ ልትቀሰቅሳት ስትል እንደተኛ ሰው ዝም አለቻት ወይናም ምንም አልሆንኩም አታስቡ ደናነኝ ብላ እሷም ተኛች ሁለቱም እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ሲገላበጡ አደሩ ጠዋትም........
.........መቅደስ ተነስታ ጌዲዮ ጋር ሄደች ተያይዘውም ካፌ ገቡ ምን ሄነሽ ነው ማታ ስደውል ስልክሽን ያላነሳሽው አላት እሷም ዝም አለችው ፊቷ ልክ አልነበረም መቅዲ ምን ተፈጠረ ትክክል አይደለሽም አላት እሷም አዎ አይደለሁም እንዴ ምን ሆንሽብኝ አላት እሷም የተፈጠረው ነገረችው እሱም እንዴ ታዲያ ይቅርታ ሳታረጊላት መጣሽ አላት ጌዲ ከበደኝ በሷ የተነሳ እኮ እኔና አንተም ተለያይተን ትምህርታችንንም አጥተን ነበር።
አለችው ጌዲ ፈገግ ብሎ መቅዲ እውነተኛ ፍቅር ይፈተናል በርግጥ አጥፍታለች ግን እኛ ከተፃፈልን ውጪ አልኖርንም አንኖርምም አንዳንዶቻችን የሌላውን ብርሀን ስላጨለምን የኛ ይበልጥ ይበራል ብለን እናስባለን ግን ተሳስተናል ከምንም በላይ ግን ጥፋተኝነትን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅ ጥበብ ነው ይቅርታንም መቀበል መሸነፍ ሳይሆን ትልቅ ብልህነት ነው ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም ፍቅራችንን ገደል ልትጨምረው ብትሞክርም ከገደሉ የመለሰችውም እሷ ነች አላት ግን ይህን የተናገረው እንዳትናገር ያለችውንም የነገረቻት መስሎት ነበር መቅደስ ቀበል አርጋ እንዴት ነው ከገደል የመለሰችው አላት እንዴ የዛቀን ማታ ስልክ ባትደውልልኝ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስበሽዋል በዛላይስ እኔን ለማስፈታት ካገቱሽ ልጆች መረጃ ለመሰብሰብ አንሶላ እስከመጋፈፍ እራሷን ለመስዋት ማቅረቧ ይቅርታን ሊያስደርግላት አይችልም መቅደስ ጭንቅላቷን ያዘች ቆይ ለምን አልነገረችኝም ስትል ጌዲ ደንግጦ አልነገረችሽም እንዴ አላት አዎ ብላ ከመቀመጫዋ ተነስታ ቡሀላ እንገናኛለን ብላው እየሮጠች ሄደች......
.......ዶርም ስትገባ ወይና እያለቀሰች ለመሄድ ሻንጣዋን እያዘጋጀች ነበር መቅደስም ተቆጥታ የት ልትሄጂ ነው አለቻት ወይናም አባቴ ሰው ያስፈልገዋል ልሂድለት አለቻት መቅደስም ውሸትሽን ነው ይቅርታ ስላላረኩልሽ ነዋ አለቻት ወይናን ባታረጊልኝም አልፈርድብሽም ስትላት መቅደስ ጥምጥም ብላ አቀፈቻትና ይቅርታዋን እንደተቀበለቻት ነገረቻት ወይና በደስታ ጮቤ እረገጠች ትልቅ ሸክም ቀለለላት..........
......ከዚህ ቡሀላ ወይና ከመቅደስና ከጌዲዮ ጋር በመተባበር ዮናስን ለፍርድ የሚያበቁ መረጃዎችን ሰበሰቡ ለምሳሌ ሴቶችን ለሹገር ዳዲዬች እንደሚሸጥ አደንዛዥ እፆችን ግቢ ድረስ እንደሚያዘዋውር ሌሎችም ከዛም ከጅማ ዩኒቨርስቲ ግቢ ተባረረ በመቀጠልም በፍርድ ቤት ሶስት አመት ተፈረደበት.......
...... ከዚህን ጊዜ በፍቅራቸው ማህል የገባና ከፍተኛ ክፍተት የፈጠረ ሰው የለም ያመቱ መጨረሻ ላይ ማለትም ትምህርት ሲዘጋ ጌዲዮ...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
#ከሁለት_አመት_በኋላ
...🖌መቅደስን ወሎ ድረስ ወስዶ ከናቱ ጋር አስተዋወቃት እናቱም ልክ እንደኔ ሆነሽ ልጄን ተንከባከቢልኝ ብለው አደራ ሰጧት መቅደስም ብትሆን ያለምንም ፍርሀት ቤተሰቦቿ ጋር ወስዳ አስተዋወቀችው ከዛም ሁሉም ቤተሰቦቿ በተሰበሰቡበት በሽታው ተነስቶበት ወደቀ የሚገርመው ግን አንድም ሰው አልተቃወማትም እንደውም ኮሩባት ልጃችን ገንዘብ ቤት መኪና መልክ ቁመና ዝና ሳትል ፍቅርን መረጠች ብለው ልክ እንደጌዲዮ እናት የመቅደስም ቤተሰቦች መረቋቸው እህት ወንድሞቿም ታናሻችን ብትሆኚም ሁሌ አርአያችን ነሽ ብለው ተራ በተራ እያቀፉ ሳሟት።.. ያው በሽታው ሲብስበት ፀበል ይዛው እየሄደች ታስታምመዋለች እናም በዚህ መልኩ ጌዲዮና መቅደስ ድፍን ሌላ ሁለት አመት በፍቅር ዘለቁ ከሁለት አመት ቡሀላ ምን ሊፈጠር ይችል ይሆን አብረን የምናየው ይሆናል የመቅደስና የጌዲዮ ትውውቅ ድፍን ሶስት አመት ሊሞላው አንድ ሳምንት ብቻ ነው የቀረው አሁን አመቱ አዲስ ነው የረፍት ጊዜያቸውን ጨርሰው መቅደስ ያራተኛ አመት ጌዲዮ ደግሞ ያምስተኛ አመት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ነገ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ ይጓዛሉ በተለይ ለጌዲዮ ይህ አመት ልዩ ነው ዛሬ ላይ እንዲቆም በትምርቱ ገፍቶ ሰው የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፈጣሪ በታች መሰላል የሆነችውን የናቱን አደራ የሚወጣበት ተመርቆም ለቁም ነገር የሚበቃበት ልዩ አመት ነው እንኳን ለናቱ እንኳን እራሱ መቅደስም የዚህን አመት መጨረሻ ናፍቃለች ደወለችለት
....ሄሎ ጌዲ ወዬ ፍቅር እንዴት ነህልኝ እግዚያብሄር ይመስገን ደናነኝ አንቺ እንዴት ነሽ እማ ደናነኝ አንተ ግን እያመመህ ነዋ አለችው አረ ደናነኝ ደሞ ደናነኝ ትላለሀ ቅድም እኮ ስደውል ማዘር አንስተው እንዳመመህ ነግረኛል ውይ መቅዲ እማን አታውቂያትም እና ነው እራሴንም ስል እኮ ነው አቋረጠችው በቃ እራስ ምታት ላንተ በሽታ አይደለማ ለማንኛውም ነገ መናህሪያ እንደደረስክ ደውልልኝ አባዬ አደርሳችኋለሁ ብሎኛል ለሊት ስለምትነሳ አሁን ተኛ አለችው እሺ ደናደሪልኝ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ እሺ ቻው።
.......በንጋታውም ልክ እንዳለችው ተያይዘው ባባቷ መኪና ተያይዘው ጅማ ገቡ አባቷም ምሳ ጋብዞ ግቢ አድርሷቸው ወደአ.አ ተመለሰ.......መቅደስና ጌዲዮ ግቢ እንደገቡ ከሁሉም ጓደኞቻቸው ጋር ተገናኙ ወይና ብርሀን ሰአዳ በለጠው ሌሎቹም ተሰባሰቡና ቡና ለመጠጣት ሻንጣዎቻቸውን አሳርፈው ወጡ.......
በለጠው በጓጓው ልቡ እናንተ የተገናኛችሁበትን ሶስተኛ አመት እንዴት ነው የምታከብሩት አላቸው መቅደስም እንዳምናው ነዋ አለችው በቃ ይቀወጣል አላት ብርሀንም ሙድ ስትዪዝበት የሰውንማ ለማሞቅ አንደኛ ነህ ግን ያንተ መቼ ነው ስትለው ሁሉም ሳቁበት እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ ባንድ ሳምንት አንድ ሴት እቀይራለሁ ታዲያ እኔ ለየትኛዋ ፓርቲ ላዘጋጅ ስታዪኝ ከበርቴ ቱጃር መሰልኩሽ እንዴ ጌዲዮም ቀጠለና አንድ መያዝ ነዋ አለው ወይ አንድ ትቀልዳለህ መሰል እንደዛ ሲል ሰአዳ ወሬ ቀይር አለችው ከዛም ትንሽ እንደተዝናኑም ጌዲዮ አመመው ብዙም ሳይዝናኑ ወዲያው ወደግቢ ተመለሱ።......
........ሶስተኛ አመት የትውውቅ ልደታቸውንም በደመቀ መልኩ እያከበሩት ሳለ ዛሬም ጌዲዮ አመመው ቢሆንም እስኪነቃ ጠብቀው ሻማቸውን አብርተው ሲደሰቱ ነው ያደሩት
ቢሆንም ግን መቅደስ የፍቅረኛዋ ነገር እያሳሰባት ነው ጭራሽ እንቅልፍ አልወሰዳትም ጌዲዮ ሲነቃ እንቅልፍ አልያዛትም መቅዲ ምን ሆንሽብኝ ለምን አተኚም ሲላት እንቅልፌ ስላልመጣ ነው አንተ ተኛ አለችው ፊቷ ተቀያይሮ ስለነበር ጌዲዮ ወዲያው አወቀባት ምን እያሰብሽ ነው ስለኔ ነዋ አላት አዎ ስላንተ ቆይ እስከመቼ ነው እንዲህ በሽታህን ተሸክመህ የምትኖረው መቅዲዬ እሺ ምን ላርግ ምን ላርግ አትበለኝ ይኸው ሀኪም ቤት ለመሄድ አይደል እንዴ ዛሬ ነገ እያልክ ስንት ጊዜ የሆነክ መቅዲ ብሄድም ምንም ለውጥ አይኖረውም እኮ እንዴት አወክ መቅዲዬ የኔ በሽታኮ አትጨርሰው ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ልትለኝ ነዋ አዎ ደሞኮ ሰዎች ሲያወሩ እንደሰማሁት ከሆነ እጀ ሰብ ነው ይባላል አረ ጌዲ እንደተማረ አስብ ለስሙ ነው እንዴ አራት አመት ሙሉ አገር አቀፍ ውጤት አሸንፈህ የተሸለምከው ለነገሩ ጌዲ ሀሳቧን እንድትቀይር እንጂ በንደዚህ አይነት ነገር አያምንም
.....መቅዲዬ ምንም አልሆንም ደሞ ፀበል እየሄድኩ አይደል ይሻለኛል ጌዲ ልታባብለኝ አትሞክር እኔ እንቅልፍህም ያስፈራኛል እንባ ባይኗ ሞልቶ ፈሰሰ ደግሞ የትኛው ፀበል ነው ሀኪም የሚከለክለው ሁሌ ይሻለኛል ትላለህ ግን እያባሰብህ ነው ጌዲ አንተን ካጣን እኔም ሆንኩ እናትህ አንድ ቀን አናድርም መቅደስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲም ሊያስቀይሳት ፈልጎ ማታ ወድቄ አሳፈርኩሻ አላት መቅደስ ባንዴ አራስ ነብር ሆነች ባለ በሌለ አቅሟም በጥፊ ሞላችለት ለመናገር ተስኗት ትንፋሿ ተቆራረጠ ጌዲዮም ጉንጩን ይዞ እየሳቀ አረ እየቀለድኩ ነው አመረርሽ እኮ ሲላት በንዴት ደረቱን እየወቀረች እኔ ጨንቆኛል አንተ ትቀልዳለክ ጌዲዩ በፍቅር የሚመቱትን ሁለት እጆቿን ግጥም አርጎ ይዞ አቀፋት መቅደስ ይበልጥ አለቀሰች የምታጣው የምታጣው እየመሰላት ነው ጌዲዮም ሁኔታዋ ግራ ገብቶት አረ በቃ አንቺ ደስ ካለሽ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እኔዳለን አላት እስኪ ማሪያምን በል አለችው በንባና በሳቅ መሀል ሆና ማሪያምን እኔዳለን ብሎ አባበላትና አቅፏት ተኙ።..........
.......መቅደስ ከጌዲዮ ቀድማ ነቃች ሻውር ወስዳ ለባብሳ ስትጨርስ ልትቀሰቅሰው ጌዲ አለችው መልስ አልሰጣትም አሁንም ተጣራች ዝም አላት አንተ ጌዲ ተነስ ሰአት እረፍዷል ግቢ ክላስ መግባት አለብን አለችው አሁንም መልስ አልሰጣትም ክው አለች ከወንበሯም ተነስታ ወዳልጋው አመራች በጆቿም እየደበደበች ብጠራውም ሊሰማት አልቻለም እንደበረዶ ቀለጠች ሰውነቷ ደነዘዘ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋ ጌዲ ጌዲ ደጋግማ እየተጣራች አቤት በለኝ አለች ጌዲዮ ግን...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
❤️ ❤️ የልቤ ትርታ❤️ ❤️
የልቤ ትርታ ክፍል2️⃣ 1️⃣ ምሽት 3:00 ይለቀቃል ።
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥 🫥
👇👇👇👇👇👇👇👇
🤩 🤩 🤩 🤩 🤩 🤩
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
የልቤ ትርታ ክፍል
ሰዓቱ እስኪደርስ ከታች ያለውን ቻናላችን join አድርጉ።
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
https://t.me/+HZfGuu-4yyc4OTE0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ethio Computer
አዳዲስና በመጠኑም ያገለገሉ ላፕቶፖች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
☎ 09 08 61 62 63
*new brand laptops
*dubai used laptops
*Gaming laptops
*Desk top
Contact us @Ethio1226
#ክፍል_
...
እሱም መልሶ ሰአዳ ጋር ደወለና እንድታገናኘው ጠየቃት መቅደስ ግን አላናግረውም ስትል ብርሀን ለመነቻትና እሺ አለች ስልኩንም ተቀብላ ምን ፈለክ አለችው ጌዲም መቅዲ እግዚያብሄርን እንዲህ ያስከፋሻል አላልኩም ይቅርታ አርጊልኝ አላት ብዙም ካባበላት ቡሀላ ይቅርታ አረገችለትና ሁሌ የሚገናኙበት መናፈሻ እንደሚጠብቃት ነገራት.....
የሚገርም ነው ጌዲዮና መቅደስ ፍቅረኛሞች ከሆኑ በኋላ ብዙ ሴቶች ጌዲዮን ለፍቅር ጠይቀውታል በተለይ አደራ የተባለችው የክፍሉ ተማሪ ተፈታትናዋለች ይኸው ዛሬም ሆን ብላ መቅደስን እየጠበቀ የተቀመጠበት መናፈሻ ድረስ ሄዳ አጠገቡ ተቀመጠች ብዙ ብሏት እንቢ ስላለችው ዞርበይም አላላትም ዝም ብሏት ተቀመጠ እሷም ጌዲ ሰላም ነው አለችው እሱም እግዚያብሄር ይመስገን አላት ይቅርታ መቅደስን እየጠበክ እንደሆነ አውቃለሁ ግን በጣም ስለናፈከኝ ነው የመጣሁት አለች ጌዲዮም በግርምት ፈገግ ብሎ እኔ ናፍቄሽ አላት እሷም አዎ ብላ ተጠግታ እጁን ያዘችው መቅደስ ፊትለፊት አየቻቸው እንዳየቻቸውም ቆመች
ጌዲዮም ቀስ ብሎ እራሱን ያዘ ከዛም ሰውነቱን አንቀጠቀጠው በተቀመጠበት ወድቆ ሲንፈራፈር አደራ ሰቀጠጣት እንኳን ልታነሳው የጨበጡት እጆቿን ተፀይፋ እየጠራረገች ጥላው እየበረረች ሄደች መቅደስ ግን ከመቅፅበት እየሮጠች አጠገቡ ደርሳ ስታቅፈው እየሳቀ ነቃና ወይ የዘንድሮ ፍቅር አለ መቅደስ በድጋሚ ተናደደች ምን ለማለት ነው አለችው እሱ እንዴ እሰቢው ጤነኛ እያለሁ አፈቀርኩክ ናፈከኝ አበድኩልህ ስትል የነበረችው ልጅ ታምሜ ስወድቅ ግን ተፀይፋ ጥላኝ ሄደች ታዲያ ይሄ ፍቅር ነው መቅዲዬ ካፈቀሩ አይቀር እኮ ልክ እንዳንቺ ነው ከነ ሙሉ ማንነት የኔ እናት አንቺኮ ትለያለሽ እኔ ማለት እኮ..... በጆቹ ጉንጮቿን ጨብጦ አይን አይኗን እያየ ቀጠለ....ከድለኞች መሀል አንዱ ነኝ አንቺን የሰጠኝን ፈጣሪ በምን ቃል እንደማመሰግነው አላውቅም ብሎ ጥብቅ አርጎ ግንባሯን ስሞ አቀፋት.....መቅደስም
ጌዲዬ እኔም እኮ ያንተ በመሆኔ እድለኛ ነኝ ደግሞ ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ አትቀልድ እኔኮ ህመምክ ያስፈራኛል አለችው እሱም ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ እንደማይቀልድ በፈጣሪ ስም ምሎ ቃል ገባላት ....እንዲህ እንዲህ እያሉ ደሞ ሌላ ወራቶች አሳለፉ
ፈተና እየተፈተኑ ስለነበር አሁን በብዛት ጥናት ላይ ናቸው ሰሞኑን ግን ጌዲዮ በጣም እያመመው ነው ቢሆንም ጌዲዮ ህልሙን ለማሳካት ጠንክሮ እየተማረ ነው ዛሬ ደግሞ ከመቅደስ ጋር አብረው ሁሌ የሚያጠኑበት ጫካ ሄደው እያጠኑ ነው ጥናታቸውንም እንደጨረሱ ጌዲዮ የመቅደስ እግር ላይ ተኝቶ እንደለመደው አይናይኗን እያየ ምን እንደናፈቀኝ ታውቂያለሽ አላት እሷም ምንድነው አለችው የምመረቅበት ቀን አላት ውይ አሁንማኮ ጨረስክ ግማሽ አመት እኮ ነው የቀረህ ግን ለምን ጓጓህ ጌድዬ አለችው እንዴ መቅዲ የማዬን ደስታ ለማየት ነዋ የኔን አለም የምታሳየኝ ተምረህ ተመርቀህ ነው ትለኝ ነበር ታዲያ አለሟን ለማሳየት ለምን አልጓጓም አላት መቅደስም ፈገግ ብላ እሱማ መመረቅክ የኔም አለም እኮ ነው ስትለው ግን ምንድነው ስጦታዬ አላት እሷም ያገር ቀይ አበባ ተሸክሜ እሰጥሀለሁ አለችው በቃ አላት እህ ብችልማ ቀይ ምንጣፍም ባስነጥፍልህ ደስ ይለኛል አለችው ጌዲዮም ስቆ ሀሳብሽም በቂዬ ነው የኔ እናት ደግሞ የዛሬ አመት አንቺ ስትመረቂ እኔም በተራዬ በዛ ሁሉ ህዝብ ፊት ተንበርክኬ የኔ እመቤት አግቢኝና የፍቅርሽ ታዛዥ ባሪያሽ ሆኜ እድሜ ዘመኔን ልገዛልሽ እልሻለሁ
አላት...መቅደስ ዛሬ ላይ ሆና የቀጣዩን አመት ምርቃቷን ቀን በምትወድደውና በምታፈቅረው የጌዲዮ የጋብቻ ጥያቄ አጣምራ ደስታዋን በህሊናዋ ሳለችው...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...
ከዛም ቀጥታ ግቢ ሄዱ እንደገቡም ትንሽ እንደተራመዱ ጌዲዮ አካባቢው ሁሉ ጨለመበት መቅደስን ጥብቅ አርጎ ያዛትና መቅዲ እራሴን አላት እሷም ደንግጣ ምን ሆንክብኝ አለችው እኔንጃ እራሴን መቅዲዬ ያዢኝ ሁሉም ጨለመብኝ አላት መቅደስ ላንዴ አይኗ በንባ ተሞላ እኔን ምንም አትሆንም ፀሀዩ ይሆናል አለችው ከዛም እንደምንም ብላ ወደጥግ አስቀመጠችውና ክብሪት ልትፈልግ ተነስታ ልትሄድ እጇን ከጁ ልታስለቅቅ ስትል መቅዲ የትም አትሂጂ ደግፊኝ እራሴ ሊፈርስ ነው ብሎ በፍርሀት አጥብቆ ያዛት ምንም ጌዲዮ ሁሌ ቢወድቅም እንዲህ ብሏት ግን አያውቅም አቅፋው ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ሳቅና ደስታቸው ላንዴ በሀዘን ተቀየረ ጌዲዮ እንደምንም ፊቷን ፈልጎ እንባዋን እየጠረገላት መቅዲዬ ጠንካራ ሁኚ እኔኮ ሁሉም ጨለመብኝ አላት የሱም እንባ እየወረደ መቅደስ ላንዴ በለቅሶ ሲቃ ሲጥ አለች ወዲያው የግቢው ሰው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተሰበሰበ ጌዲዮም ወዲያው እራሱን ሳተ የሷም ሆነ የሱ ጓደኞች እያለቀሱ ነበር አብዛኞቹ ግን እንዳለፈው አወዳደቁ የወደቀ መስሏቸው ይነቃል እያሉ ነበር ቢሆንም ለተከቴይ ሶስት ሰአት ቢጠብቁትም ሊነቃ አልቻለም መቅደስ ለሁለት ተይዛለች ብቻ እየቀለደብኝ ነው ውሸቱን ነው ንቃ በሉት ትላለች እሱ ግን ቀልዱን አልነበረም በመጨረሻም አንቡላንስ መጥቶ ይዞት ሄደ አንቡላንሱ እያበረረ ጅማ ጠቅላላ ሆስፒታል አደረሳቸው ወዲያው ዶክተሮቹ ተባብረው ድንገተኛ ክፍል አስገቡት አብረውት የመጡት መቅደስ ሰአዳና በለጠው ብቻ ነበሩ ለነገሩ መቅደስ አለች አትባልም እሷም ለህክምና አልጋ መያዝ እንጂ የቀራት ደንዝዛለች ብቻ በር ላይ አንዴ ቁጭ አንዴ ብድግ እያለች ነው ሌሎቹም ጓደኞቻቸው ተከታትለው እየሮጡ ሴክሬተሪዋን ጠይቀው ያሉበት ክፍል እየሮጡ ደረሱ እንደደረሱም እንዴት ነው አሁን አሏቸው በለጠውም ዶክተሮቹ ገና አልወጡም አላቸው ከዛ ሁሉም በጭንቀት ተከበው መጠበቅ ጀመሩ.......
....ከዛም ቢያንስ ካንድ ሰአት ቆይታ ቡሀላ ዶክተሮቹ ወጡ እንደወጡም ሁሉም ተሯሩጠው ከበቡዋቸው ዶክተር እንዴት ነው አሉ አንዱ ዶክተር ሲቀር ሌሎቹ ፊታቸው ሳይፈታ ጥለዋቸው ሄዱ ሁሉም ፈሩ መቅደስማ አንድኛዋን ተዝለፈለፈች ዶክተሩ ቁና ተነፈሰና ሊያወራ ሲል መቅደስ ዶክተር በፈጠረህ ክፉውን እንዳትነግረኝ ሞተ እንዳትለኝ ስትለው ወይንሸት አረ መቅደስ ሶስት ጊዜ አማትቢ አለቻት ዶክተሩም እ.እ መኖሩን አለ እኛም የተቻለንን እርዳታ አርገንለታል ግን አሁንም ሁሉም ግን ምን አሉት አልነቃም የሚያስፈልገውን ህክምና ሰተነዋል ተራ በተራ እየገባችሁ ማየት ትችላላችሁ ከሁለት ሰው በላይ ግን ውስጥ መቀመጥ አይቻልም ሌላው ከታማሚው ጋር ቀረቤታ ያላችሁ ክፍል ቁጥር 24 ቢሮ መታችሁ አናግሩኝ ብሏቸው ሄደ
.መቅደስ ቀድማ ገባች ስታየው ይባስ ሲጥ እስክትል ድረስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲዮ ከወገቡ በላይ ብዙ ገመዶች ተጠላልፈውበታል አፍና አፍንጫውም በኦክሲጅን መስጫ ታፍነዋል እጆቹም ተዘርግተው አይንቀሳቀሱም ሳቁ ጠፍቶ ከንፈሮቹ ተከድነዋን የሚያምሩት መቅደስን አይተው የማይጠግቡት አይኖቹም ተከድነዋል እጁን ጭምቅ አርጋ ይዛ እየሳመችው ጌዲዬ ፈተና እኮ አላለቀም ደሞስ ላይብረሪ እንገባለን ተባብለን አልነበር ለምን አትነሳነሳም እንሂዳ ጌዲ የው ውሸት አያምርብህም በኔ አትጨክንማ ተው ተነስ እያለች ለማይሰማት ጌዲ ብዙ አወራችው መቆየቷን የተረዱት ጓደኞቻቸው እዛው እያለች እየገቡ ጌዲዮን እግዚያብሄር ይማርህ እያሉ እሷንም እያፅናኑ ወተው ደጅ ላይ ተቀመጡ ከዛም በለጠውና መቅደስ ዶክተሩ ቢሮ ሄዱ..ሲገቡም እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ከዛም በለጠው ዶክተር ችግር አለ እንዴ ብሎ ጠየቀው ዶክተሩም እየውላችሁ አሁን እንዲህ ነው ብሎ መናገር ይከብደኛል ምክንያቱም ሙሉ ምርመራ መደረግ አለበት ላሁን ግን ጥያቄዎችን ልጠይቃችሁ ታማሚው ከዚህ በፊት እራሱን ይስት ነበር??...አዎ ግን እንደዛሬው ሆኖ አያውቅም ህክምናስ ተደርጎለት ያውቃል?? መቅደስ ይህን ጥያቄ ለመመለስ አንደበቷን ፈታች ስንቴ እንደለመንኩት እኮ ይኸው ይሄ ቀን እንዳይመጣ ፈርቼ ነበር ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች በለጠው ደግፏት ነበረ ስታለቅስ ግን አቅፎ አባበላት ዶክተሩም ቀጠለ እሺ ያለፈው አልፏል አሁን ማሰብ ያለብን ስለወደፊቱ ነው እናም ለካርድ ላልጋ እንዲሁም ለግዜው ህክምና የሚውል 7ሺ ብር ማስያዝ ይጠበቅባችኋል አላቸው ከዛም እንደወጡ በለጠው....መቅዲ እጄ ላይ ምንም ሳንቲም የለም ምን ይሻላል አላት አታስብ እቤት እደውላለሁ ብላ አባቷ ጋር ደወለች
ሄ..ሎ..ሄ...ሎ አባ ወዬ መቅዲ ደና አደለሽም እንዴ አዎ አባ ጌዲን አሞት ሆስፒታል ነን ይሄን ያክል አዎ አምስት ሰአት ሊሞላው ነው እራሱን ከሳተ ግን አልነቃም አለችው አሁንም እያለቀሰች ነው አባቷም እራሱን ይዞ በቃ አይዞሽ ምንም አይሆንም አሁን ይነቃል ደሞ ሁላችንም ስራ ነን እህትሽ ግን እረፍት ላይ ስለሆነች አሁን እልካታለሁ እሺ እሺ አባ ብትችል
ግን አሁን 7ሺ ላክልኝ አረ እልክልሻለሁ ምንም ችግር የለም ብቻ አንቺ እራስሽን አረጋጊ እሺ አባ አመሰግናለሁ..ጌዲዮ ይነቃል እየተባለ ሲጠበቅ ሳምንት ሞላው የጅማ ጠቅሌ ሆስፒታል ዶክተሮችም የጌዲዮ ነገር ካቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ወደ አ.አ ተክለ ሀይማኖት አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ተፃፈለትና ከጅማ ተነስተው አ.አ ገቡ እስካሁን ያልተነገራቸው የጌዲዮ እናትም በጣም እየደወሉ ልጄስ እያሉ ሲጠይቁ በብዙ ምክንያት መታመሙን ቢደብቋቸውም የወለደ አንጀት ነውና...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
#ክፍል_
...🖌ጌዲ መታመሙን ተረድተው አጥብቀው
ሲለምኑ ግድ ሆነባቸውና ዛሬ እውነቱን ተናገሩአይ እናት በሞት መሀል ሆነው ነው አ.አ የደረሱት ያው እነ ብርሀን በለጠው ወይና ሰአዳ እንዱሁም ሌሎቹም መቅደስ ስትቀር ነገ ፈተና ስላለ ተመልሰው ጅማ ሄደዋል መቅደስንም ቢሆን ቤተሰቦቿ እንዲሁም የጌዲ እናት ሄዳ ፈተናዋን እንድትፈተን እየለመኗት ነው እሷ ግን ካልነቃ አልሄድም አለቻቸው የጌዲዮ እናት ለቅሷቸው መራራ ነው የመንገዱ ድካም ሳይሰማቸው ሰውነታቸው መዛሉ ሳይሰማቸው ልጃቸው እግር ላይ ተደፍተው አሁንም መራራ እንባ እያነቡ ነው መቅደስማ እንባዋ አልቆ ፈዛለች
ቡሀላም እንደምንም ለምነው የመቅደስ ቤተሰቦች የጌዲዮን እናት ይዘው እቤት ሄዱ መቅደስ አሁንም አልጋው ላይ በግንባሯ ተደፍታ እያንቀላፋች ነው የሆነ ሰአት ላይ የጌዲዮ ጣቶች ሲንቀሳቀሱ ተሰማትና ከህልሟ እንደነቃች ሆና ባተተች ስታየው አይኖቹ ግራና ቀኝ እያዩ ነው ደስታዋ አንቋት ላንዴ ጮኸች ተጣድፋ ሄዳ ግንባሩን ደጋግማ ሳመችው ከዛም ጌዲዬ ነገ እኮ ፈተና ነው አብረን እኔዳለን አይደል አለችው መንቃቱን ከነርስ የሰሙት ዶክተሮች እየተሯሯጡ መጡ ወዲያው መቅደስ አያችሁ አይደል
.......መቅደስና ጌዲዮ በብዙ ፈተና ሶስት አመት በፍቅር አሳልፈው አራተኛው አመት ግን አስጊ ሆኗል ጌዲዮ የጓጓለትን ያምስተኛ አመት ትምህርቱን መጨረስ አልቻለም ዋና የሚባለውም ፈተና አምልጦታል ከሆስፒታ ወጥቶ እንዲፈተን መቅደስ ዶክተሩን ብትለምነውም ለሂወቱ አስጊ ስለሆነ እንደማይወጣ ነግሯት እሷም አልፈተንም ብትልም ጌዲዮ በፍቅሩ ለምኗት ፈተናዋን ለመፈተን ጅማ ተመልሳ ዛሬ ወደ አ.አ መጥታለች ሙሉ የህክምናውን ወጪ ችለው እያስታመሙት ያሉት የመቅደስ ቤተሰቦች ናቸው እናቱም ከክፍለ ሀገር መጥተው አብረውት ነው ያሉት ጌዲዮ ከራሱ በላይ የናቱን ህልም አለማሳካቱ ተስፋ አስቆርጦታል መቅደስም በሱ መታመም ሌት ተቀን እያለቀሰች በድን ብትሆንም ዛሬም ትምህርቱን ቀጥሎ እንደሚመረቅ ተስፋ ትሰጠዋለች.......
......ዛሬ ውጤትህ ይመጣል ስለዚህ ለዩኒቨርስቲው አሳውቀን ብትዘገይም ትፈተናለህ እሪሰርችህንም ቢሆን ትጨርሰዋለህ አለችው መቅደስ የፍርሀትና የደስታ ስሜት እየታየባት የጌዲዮ እናትም እንዳፍሽ ያርገው አሏት የሱዋም አባት እንደዛው ጌዲዮ ግን ውስጡ ጤነኝነት እየተሰማው ስላልሆነ የሚመጣው ውጤት ጥሩ ይሆናል ብሎ መገመት ተስኖታል ብቻ ባጠቃላይ አፋቸው መልካም ቢናገርም ውስጣቸው ፈርቷል ሰአቱ ሲደርስም መቅደስና አባቷ ውጤቱን ለመስማት የዶክተሩ ቢሮ ሄዱ እንዲቀመጡም ከጋበዛቸው ቡሀላ ዶክተሩ ከምን መጀመር እንዳለበት ግራ ገብቶት አይን አይናቸውን ያያቸው ጀመር ውስጣቸው ይበልጥ ተረበሸ ዶክተር ችግር አለ እንዴ አሉት...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact