"እውነተኛ ክርስቲያን አባቱ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሰደባል እንጂ አይሳደብም፡፡ የጠፉትን ፍለጋ ይደክማል እንጂ ይባስ ብሎ አይገፈትርም፡፡ በወንድሙ ውድቀት ያለቅሳል እንጂ አይደሰትም፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን አባቱ ሌላ ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና በጊዜውም ያለ ጊዜውም ሊሆን ይገባል፡፡ ባገኘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባጣንም ጊዜ፤ ባለጤና በሆንን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በታመምንም ጊዜ፤ ሲሳካልን ብቻ ሳይሆን ባልተሳካልንም ጊዜ ማመስገን መለማመድ አለብን፡፡ የምስጋናችን ምንጭ የሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን ስለ አምላካችን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ ስንለማመድ በክብር ላይ ክብር ይጨመርልናል፤ እንደ አባታችን ኢዮብ የዲያብሎስን አፍ እንዘጋለን፡፡
ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን?” እንኪያስ "በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"በሌላ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለች መዝናኛ አድርገው ይዝናኑባታል፡፡ እኛ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለች የመለያያ ድንበር አድርገን እንጋጭባታለን፡፡"
🎤መጋቤ ሐዲስ እሸቱ
ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል …
‹ሰው እግዚአብሔር ሲለየው፤ ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል›። በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲም ካርዱ የወጣ ሞባይል ማለት ነው። ጥሪ የማይቀበል….
...እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት ግን የሰዉ አስተሳሰብ ነው።...
የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል።
ጃፓንና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው። ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው።
… እንደምታዩኝ እኔ ዐይነ ስውር ነኝ። ቀላል አይደለም.... እንክዋን ዘውትር ዓይን አጥቶ አንድ ቀን መብራት ሲሄድ ስንት እንደምታማርሩ ታውቅታላችሁ።
እኔ ግን ዓይኔ ባለማየቱ አንድ ቀን እንኳን አልቅሼ አላውቅም። ከሞት ወዲያ መብራት አለ። ከመቃብር በላይ መብራት አለ። ... ወደ መቃብር ሲወርድ ማንም ዓይነ ስውር ነው። ማንም ዐይኑ እያየ የተቀበረ የለም።
ተስፋችን ግን ምንድን ነው? ከሞት ወዲያ ሕይወት አለ። ከሞት ወዲያ ብርሃን አለ...
አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ። የማይረባ ነገር ስናይ (ዓይናችንን) የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር... መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር።
…አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሐሜት እንሰማ ነበር? የምንፈልገውን (ብቻ) አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር።
ችግሩ ብዙ ነው፡፡ ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ።
... እባካችሁ ሰው እንሁን… የንጉሠ ነገሥቱ የክርስቶስ አልጋ ወራሾች ነን... የደስታችሁ ልኬት የደስታችሁ ሚዛን ምግብና መጠጥ አይሁን፤ መኪናና ቤት ዝናንም አታርጉ።
እኛ መለኪያችን ጽድቅ ነው። መከኪያችን መንግሥተ ሰማያት ነው። ያ የምንገባበት ቤት ደግም የተዋበ፣ የደመቀ፣ መብራት ውሀ የማይሄድበት፤ 24 ሰዓት ክርስቶስ የሚያበራበት፤ 24 ሰዓት የሕይወት ውሀ የሚጠጣበት፤ ሀብታም፤ ደሀ፣ ተራ ሰው የማይባልበት፣ እገሌ ግባ እገሌ ውጣ የማይባልበት
ቦታ ነው.....።
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
@yeberhanljoche

ኦርቶዶክስ ነዎት እንግድያውስ ስለሀይማኖቶ ጥያቄ አልዎት እንግድያውስ ግሩፓችንን ይቀላቀሉ መጠየቅም መመለስም ይቻላል 🙏
Jõïñ
T.me/yemenfesawi_wiyyt_group
Jõïñ
T.me/yemenfesawi_wiyyt_group
Telegram
መንፈሳዊ ህይወታችን ግሩፕ 🗣👥 ዘE/O/T/C
⌛️ሰላም የተዋህዶ ልጆች እንደምን ከረማችሁ
📌ማሳሰቢያ
፩❗️ፖለቲካ አይፈቀድም
፪ በዚህ ግሩፕ ውስጥ ሌላ እምነት ተከታይ ካላችሁ ስርዓት ባለው መንገድ ጠይቁ .
፫ ለምትጠይቁት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው እዚሁ ግሩፕ ውስጥ ነው

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተባረከው የሐምሌ ወር ቀኑ ዐሥራ አራት ሰዓት ነው ከዚህ በኋላ እያነሰ ይሔዳል።
እንደ ኃጢአታችን በዛት እንደ በደላችን ክፋት ስይሆን እግዚአብሔር አምላክ የንስሐ ወርንና ወርሐ ክረምትን ጨመረልን ተመስገን።
በዚህም ወር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መልካም ሥራዎችን ሠርተን ከቅዱሳን በረከት ተሳትፈን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጇች ለመሆን ራሳችንን እንሥራ።
ሐምሌ አንድ ቀን በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት በምትሰራ ሴት መሞት ምክንያት ተአምር አደረገ::
ነገሩ እንዲህ ነው፦ አንድ ጎልማሳ ከሐዋርያው ቶማስ እጅ የተባረከ እንጀራ ተቀበሎ ሊበላውም ሲል እጆቹ በደረቁ ጊዜ ተአምር ተደረገ::
የህንን ያዩትም ሰዋች ሔደው ለሐዋርያው ቶማስ ነገሩት። ሐዋርያውም እጁ ወደ ደረቀበት ሰው ሔዶ ልጄ አትፍራ ንገረኝ የእግዚአብሔር ቸርነት በግልጽ በዝቷልና አትፍራ ተናገር አለው::
ያም ሰው ከእግሩ ሥር ወድቆ አባቴ ይቅር በለኝ መጠጥ ቤት ወደ ምትሰራ ሴት አዘውትሪ እገባ ነበር፤ አዘውትሪም እጎበኛታለው ቤቷ ገብቼም እበላለሁ እጠጣለሁ ነገር ግን ከዚህ ክፉ ሥራ በአንተ ምክርና ጸሎት ራኩኝ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ተመለሰሼ ክርስቲያን ተባልኩኝ ደስም አለኝ።
ያቺ ሴት ግን ወዳለሁበት እየመጣች አብሬያት እተኛ ዘንድ ነዘነዘችኝ ተይኝ ብላት ይልቁንም ከዚህ ክፉ ሥራ ርቃ ክርስቲያን እንድትሆን ብጠይቃት እምቢ አለችኝ አስቸገችኝ በዚህ ግዜ ሰይፍ አንስቺ አረድኳት አለው::
ሐዋርያውም የቀደሞ ክፉ ሥራውን ትቶ በዚህ መንገድ መሔዱን አድንቆ ነገር ግን በሠራው ሥራ በጣም አዝኖ ለምን ይህን የአውሬ ሥራን ሠራህ ብሎ ገሰጸው::
ሐዋርያውም በውኃ ላይ ጸሎትን ጸልዮ ጎልማሳውን በእግዚብሔር ታመነህ እጆችህን ታጠብ አለው ሲታጠብም ያ የደረቀ እጁ ዳነ::
ሐዋርያውም ያን ሰው ወደሴቲቷ በድን ና ምራኝ አለው ያም ሰው መርቶ አሳየው:: በድኗንም አውጥተው በአልጋ ላይ አኖሯት::
ሐዋርያውም እጁን በላይዋ ጭኖ ጸለየ ጸሎቱንም ሲፈጽም ጎልማሳውን ሒድ ይዘህ እኔ ቀድሞ በእጄ ገደልኩሽ አሁን ግን በሃይማኖት በእኔ እጅ ክርስቶስ ያስነሣሽ በላት አለው::
እንዳዘዘው ቢያደርግ ፈጥና ተነሳች:: በሐዋርያው እግር በታች ሰገደች ሐዋርያውም የት እንደነበርሽ እዚህ ላለን ለሁላችን ንገሪን አላት::
ነፍሴ ከሥጋዬ በተለየች ጊዜ አንድ ልብሱ የቆሸሸ ሽታውም የሚከረፋ ጠቋራ ተቀበለኝ የእሳት ጉድጎድና መንኰራኵር ወደ አለበት ቦታ ወሰደኝ።
ደግሞም እድፍንና ትልን የተመላ ጉድጎድን አየሁ ነፍሳትም በውስጡ ይንከባለላሉ ይሰቃያሉ::
ያ የሚመራኝ እዚህ የሚገቡና የሚመጡ እኒህ ነገረ ሰሪዎች ሐሰተኞች አመንዝራዎችና ቀማኞች ሌቦች ነፍስ ገዳዮች ድሆችንና በሽተኞችን የማይጎበኙ የእግዚአብሔርንም ሕግ የማያስታውሱ እንደ ሥራቸው የሚቀጡ ናቸው አለኝ አለችው::
ሐዋርያውም እዛ ያሉትን ሰዎች ሁሉ የኃጢአት ዋጋዋን አስረዳቸው ብዙዋችም ንሰሐ ገብ።
ክፉ ሥራ መሥራት እሳቱ ከማይጠፋበት ትሉ ከማያንቀላፋበት መጣል ግድ ነው።
እያንዳንዱ የምንሠራው ኃጢአት በመጨረሻ ምን እንደሚከፍለን ያወቀ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ፈጥነን ንስሐ ለመግባት እንፋጠን ከክፉ ሥራችንም ፈጥነን እንራቅ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን አሜን።

ከቀብር መልስ
ከቀብር መልስ እጅህን ታጥበህ ተስተናግደህ ታውቃለህ? ንፍሮስ ቀምሰህ ታውቃለህ? ንፍሮውን ስትበላ እኔ እንደማደርገው ሽንብራ ሽንብራውን ለቅመህ በልተህ ስንዴውን ለሌላ ሰው ትመርቃለህ ወይስ ሁለቱንም ትበላለህ? በሆድህ "ለምንድን ነው ግን ጨዉን የሚያሳንሱት" እያልክ ተመራምረህ ይሆን?
እኔ ደግሞ ዛሬ ከቀብር መልስ ካልጠፋ እህል ስንዴ ለምን እንደሚቀርብ ልነግርህ ነው:: ነገሩ ባሕል ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትም ነው::
ከቀብር መልስ በንፍሮ መልክ የምንበላው ስንዴ ኀዘንተኞችን የሚያጽናና ትልቅ መልእክት ይዞአል::
ቀብረን ከተመለስን በኁዋላ ስንዴ ስንበላ የንፍሮውን ጣዕም ማሰላሰል ትተን ይህንን የጌታችን ቃል እናስታውስ :-
"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች" ዮሐ 12:24
ክርስቶስ ስንዴ የሚያፈራው ሞቶ በምድር ሲቀበር ነው ብሎ ስንዴን ለእኛ ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል:: ቀብረህ ስትመለስ በእጅህ የዘገንከው ስንዴ ቀብረኸው የመጣኸው ወንድምህ ትንሣኤ እንዳለው እየነገረ ያጽናናሃል:: በምድር የወደቀ ስንዴን ያልረሳ አምላክ የሞተውን አይረሳም::
ቀብረነው መጣን ብለህ አትዘን:: ዘርተኸው እንደመጣህ አስብ:: በመዋረድ ብትዘራውም በክብር ይነሣል:: በድካም ብትዘራውም በኃይል ይነሣል:: ለመበስበስ ብትዘራውም ባለመበስበስ ይነሣል ይልሃል ሐዋርያው (1 ቆሮ 15:42-43)
ነፍሳችን ከሥጋችን በተለየች ጊዜ በምድር አስከሬናችን ይቀራል:: አስከሬን (በግሪክ ስክሪኒዉም) ኮሮጆ መያዣ ማኅደር ማለት ነው:: "ንዒ ማርያም ለእግዚአብሔር አስከሬኑ" "የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም ሆይ ነይ" እንዲል:: የነፍሳችን ማደሪያ የሆነው ሥጋ ከአዳሪዋ ነፍስ ሲለይ አስከሬን (ማደሪያ) የነፍስ ሳጥን የሚል ስም ይሠጠዋል:: ሬሳ የሚለው ቃል የበሰበሰ ነገር ምሥራቃውያኑ የቡድሃና ሂንዱ ተከታዮች ሥጋን የነፍስ እስር ቤት አድርገው ስለሚያምኑ ሥጋ ሲቃጠል ነፍስ ነፃ ይወጣል ብለው አስከሬን ያቃጥላሉ:: በዳግም ሥጋዌ (reincarnation) የሚያምኑ በመሆናቸውም አንድ ሰው ድጋሚ ሲፈጠር የተሻለ አካል ይዞ እንዲወለድ አሮጌው ሥጋው መቃጠል አለበት ብለው ያስተምራሉ::
እኛ ግን እንቀብራለን እንጂ በፍጹም አስከሬን አናቃጥልም:: የሚቀበር ነገር ዋጋ ያለውና በኁዋላ የሚፈለግ ነገር ነው:: ገንዘብ የምትቀብረው ሌላ ጊዜ ልታወጣው ካሰብክ ነው:: የምታቃጥለው ግን የማትፈልገውን ነው:: የምንቀበረው እንደምንወጣ ስለምናምን ነው:: የመለከት ድምፅ ሰምተን እንደምንነሣ ተስፋ ስላለን ምንም ብንሞትም በተስፋ እንቀበራለን:: እንደምንበቅል ተስፋ አድርገን እንዘራለን:: ሌላው ቢቀር በእሳት ተቃጥለን ብንሞት እንኳን አመዱንምና የከሰለውን አጥንትም ቢሆን በተስፋ እንቀብረዋለን::
"የሙታንን መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን!"
#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

እኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለሐምሌ ቅድስት ሥላሴ
ቅድስት_ሥላሴ
"ሥላሴን " "ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው?አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ፡ሥላሴም ይህንን
ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም
◉አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር
አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር # ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ።
◉አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት
ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ።
ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ " በማለት ያመሰጥራል።
ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና ፥
ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን ።
አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ
በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም
ቅድስት ይባላሉ ።
አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም ።
ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ።
ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን
በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ # ቅድስት እንላቸዋለን ።
◉አኔድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ
አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት
ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ #ቅድስት ይባላሉ፡፡

#ጴንጠው-- ቆይ ግን ታቦት ምንድ ነው? ጥቅስ ብቻ ስጠኝ ለእያንዳንዱ መልስህ?????
#ኦርቶዶክሱ-- ታቦት ማለት ቤተ ሀገሬ ከምለው ከግዕዝ ቃል የወጣ ስሆን "ማደርያ" ማለት ነው። የምን ማደርያ? ካልከኝ የቃሉ ማደርያ ኦ.ዘፀ 25፥22
#ጴንጠው--እና ድሮ ለቃሉ ማደርያ ነው በአድስ ኪዳን ለምን አስፈለገ?
#ኦርቶዶክሱ--- በአዲስ ኪዳን የጌታችን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሞ ይፈተትበታክ(በዮሐ .ወ 6፥54) የምታገኘው ይህ ሥጋውና ደሙ የምከብርበት ዙፋን ነው።
#ጴንጠው - ታቦት ጣኦት ነው እግዚአብሔር ከእኔ ባቀር የተቀረፀ ምስል ለራስህ አታድርግ አላለም ወይ?
#ኦርቶዶክሱ - ታቦት ጣኦት ነው ካልክ ታቦትን ቀርፆ ለሙሴ የሰጠው እግዚአብሔር ነውኮ ኦ.ዘፀ 32፥16 እና እግዚአብሔር ከእኔ በቀር ለላ የተቀረፀ ምስል ለራስህ አታድርግ እያለ ለምን ቀርፆ ሰጠ?
#ጴንጠው -- ለሙሴ የሰጠው ታቦት ወድቆ ተሰብሯል።
#ኦርቶዶክሱ -- አው እውነት ነው ነገር ግን እግዚአብሔር እንደገና ሙሴ እንድቀርፅ አዞታል። ኦ.ዘፀ 34፥1 ።
#ጴንጠው -- እሽ ይሁንና ሙሴ የቀረፀው ሁለት ብቻ ነው ይህ ሁሉ ከየት መጣ??
#ኦርቶዶክሱ -- ከሙሴ ከጥሎ ያሉት ቅዱሳን አባቶች እንድቀርፁ ስልጣን ተሰጣቸው ኦ.ዘፀ 31፥1-6 እንዲሁም ባሰልኤም ታቦትን ቀርጿል ኤ.ዘፀ 37፥1።
#ጴንጠው -- እሽ ይሁንና ለምን በቅዱሳን ስም ይቀረፃል?
#ኦርቶዶክሱ -- የመታሰብያ ስም እስከተሰጣቸው ድረስ ት.ኢሳ 56፥4 ይቀረፅላቸዋል ነገር ግን በታቦቱ ላይ የምከብረው የጌታችን ሥጋውና ደሙ ነው።
#ጴንጠው -- እኔ አሁንም ያልገባኝ ታድያ ለምን በየሀገሩ በየአህጉሩ ታቦት በዛ ከቅዱሳኑ ቁጥርምኮ ይበዛል?
#ኦርቶዶክሱ -- መልስ ሳልሰጥህ በፊት ጥያቀ አለኝ? መጽሐፍ ቅዱስ ስታተም 1 ነበር አይደል? ታድያ አሁን በእያንዳንዳችን እጅ ላይ የምገኘው ከየት መቶ ነው?
#ጴንጠው -- ያው ተባዝተው ስለታተመ ነዋ
#ኦርቶዶክሱ -- ታቦቱም እንድሁ ለአገልግሎት እንድመች በየስፍራው አለ! ይህ ለምን ይሆናል ካልከኝ ት.ሚልክ 1፥11 ተመልከት። ደግሞም በአድስ ኪዳን እግዚአብሔር ለሰዎች ቅርብ አምላክ ነውና ነው ት.ኤር 23፥23።
#ጴንጠው -- ለምን በታቦቱ ላይ የቅዱሳን ስም ይፃፋል?
#ኦርቶዶክሱ -- በታቦቱ ላይ ብቻ አይደለም በሰማይ ቤትም ተፅፎላቸዋል ሉቃስ 10፥20።
#ጴንጠው -- ታቦት በአድስ ኪዳንኮ ተሽሯል አያስፈልግም
#ኦርቶዶክሱ -- ማነው የሻረው? ጌታ በማቴ 5፥17 ላይ ምን ነበር ያለው? ህግንና ነብያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈፅማቸው ነው እንጅ አላለም ወይ?
#ጴንጠው - እናንተ ኦርቶዶክሶች ብቻ አከረራችሁት እንጅ ታቦት የምባል ነገር መኖር የለበትም።
#ኦርቶዶክሱ - አይደለም በምድር ላይ አይደለም በኦርቶዶክሶች መቅደስ ውስጥ በሰማይምኮ አለ ታቦት። ነገ እዛ ስትሄድም ይጠብቅሃል ራእይ 11፥19 ይህንንም ስያመለክት ነው ቅዱስ ጳውሎስ ሀገራችን በሰማይ ነው እያለ 2ኛ ቆሮ 5፥1-5 የተናገረው።
#ጴንጠው -- እሽ ሁሉም እንዳለ ሆኖ ለምንድ ነው እሽ ታቦት ስሰረቅ ዝም የምለው ሃይል የለውምኮ ሌባ ሰረቀው ምናምን ስባል እሰማለው የሰረቀው ሌባም ስሸጠው ታቦቱ ታምራትን እንኳን አያደርግም።
#ኦርቶዶክሱ -- ምርጥ ጥያቄ ጠየከኝ ገና አሁን!! ለመሆኑ ታቦት ይበልጣል ወይስ ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጣል ?? ታቦት ማለት የቃሉ ማደርያ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ደሞ እራሱ የታቦቱ ባለቤት ነው። እስት ንገረኝ?
#ጴንጠው -- መብለጡንማ ኢየሱስ ነው የምበልጠው
#ኦርቶዶክሱ -- ታድያ ይሁዳ በ30 ብር አሳልፎ ስሸጠው ለምን ኢየሱስ ዝም አለ?? ሀይል ስለለለው? አቅም ስለለለው? ወይስ ይሁዳንም አይሁዶችንም በአንዴ ማጥፋት ስለማይችል ነውን??
#ጴንጠው -- ዝምምምምምም
#ኦርቶዶክሱ -- አየህ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁዳ አሳልፎ ስሸጠው ዝም ያለው በኃላ እነርሱንና ጠላት ዲያብሎስንም ድል ልነሳው ስለፈለገና አዳምንም ነፃ ልያወጣው ስለወደደ ነው እራሱን አሳልፎ የሰጠው። ዛሬ ታቦታትም ስሰረቁ ዝም የምሉት በኃላ ላይ የእግዚአብሔርን ኃይልና የታቦትን ክብር ለማሳየት ብቻ ነው ለዚህ ደሞ 1ኛ ሳሙ 4,, 5,, 6 እነዚህን 3ምዕራፎችን ካየህ ይበቃሃል።
#ጴንጠው---በኦርት ጊዜኮ ኦዛ ታቦቱን ስነካ ተቀስፏል?
#ኦርቶዶክሱ---አው ተቀስፏል። በኦርት ጊዜ ሰው ሁሉ በመርገም ነውና ያለው እግዚአብሔር ለቁጣው አይዘገይም። በአድስ ኪዳን ግን ዘመኑም "አመተ ምህረት" ይባላልና የምህረት ዘመን ነው አምላክ ቶሎ አይፈርድም ምሳሌ እንድሆንልህ ማቴ 13፥24-30 .....ማቴ 5፥45...አንብብ....
#ጴንጠው---ስግደት ለምን አስፈለገ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ አትስገድ አላለም ወይ?
#ኦርቶዶክሱ---እሽ መልካም ኢያሱ ማለት በመ.ኢያሱ 24፥15 ላይ "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ" ያለ ቅዱስ ነብይ ነው አይደል? ታድያ ለምን በመ.ኢያሱ 7፥6 ላይ ለታቦቱ ሰገደ???????? ስለዚህ እኛ ደሞ ዕብ 13፥7 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለን ሁሉ ይህንኑ እንፈፅማለን።
#ጴንጠው----እኛ የምሸከመንን እንጅ የምንሸከመውን አናመልክም እናንተኮ ታቦትን ትሸከሙታላችሁ?
#ኦርቶዶክሱ---አሁንም መልሼ ልጠይቅህ ከታቦት ኢየሱስ ይበልጣል ተባብለናል አይደል? ታቦት ዙፋኑ ነው እርሱ ደሞ የዙፋኑ ባለቤት ነው።
ጴንጠው----አዎ
ኦርቶዶክሱ---እሽ የሰው ልጅ ይበልጣል ወይስ አህያ?
#ጴንጠው---የሰው ልጅ ነዋ
#ኦርቶዶክሱ---ታድያ የሰው ልጅ ታቦትን ከተሸከመ ምን ይገርምሃል? አህያ የታቦቱን ባሌበት ሰማይና ምድርን በቃሉ ያፀናቸውን አምላክ ጌታችንን በጀርባዋ አልተሸከመችውምን?????
#ጴንጠው----- ለካ እሱም አለ!!!.........
#ኦርቶዶክሱ----ገና ብዙ አለ!!!! እርሱን የተሸከመችው አህያ በብቃቷ በጉልበቷ ሳይሆን በእርሱ ፈቃድና ሃይል ነው። ካህናትም ታቦቱን የምሸከሙት በራሳቸው ጥበብና በስልጣናቸው አይደለም፤ የሾማቸው አምላክ ፈቅዶላቸው በቸርነቱ እንደፈቃዱ ነው እንጅ።
ሃይማኖቴ ተዋህዶ ማለት ይህችው ናት። ኦርቶዶክስ መልስ አላት!!
@yeberehanljoche

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ስለ ፍርድና የእግዚአብሔር ምሕረት ! ]
ማንም ሊያመልጥበት በማይችለው በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል !
አባ መቃርዮስ እንዲህ አለ ፦ "ራስህን ለማየት ወደ መስተዋት ብትመለከት ውበትህን ወይም ጎዶሎህን ያሳይሃል፡፡ ከመልክህ ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም ፣ መስታወቱም አንተን ሊዋሽህ አይችልም ፤ አንተ የሆንኸውን ትክክለኛውን መልክህን መልሶ ለአንተው ያሳይሃል እንጂ፡፡ ፈገግ ብትል ምን ዓይነት ፈገግታ ፈገግ እንዳልህ ያሳይሃል ፣ ፀጉርህ ጥቁር ከሆነ ጥቁረቱን ፣ ግራጫ ከሆነም ያንኑ ያሳይሃል ፤ አንተ የሆንከውን ለአንተው መልሶ ምን ዓይነት ሰው እንደ ሆንክ ያሳይሃል፡፡
" ማንም ሊያመልጥበት በማይችለው በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡ በዚያ ያለው በሰዎች እጅ የተሠራ መስተዋት አይደለም ፣ ማንነትህን ፍንተው አድርጎ የሚያሳየው ሥራህ እንደ ተሰጣ ጨርቅ በፊትህ ይዘረጋል ፣ በአንገት ዙሪያ እንደ ተጠመጠመ ኮርቻ ወይም ገመድ እንቅ አድርጎ ኃጢአትህንም ይገልጣል፡፡
ከእነርሱ መሸሽና ማምለጥ አትችልም ፣ ያለ ምንም ምስክር አስፈላጊነት እነርሱ በፊትህ ቆመው ይወቅሱሃል፡፡ የኃጢአቶችህ መስተዋት ሁሉንም ያስተምርሃል ፣ ያደረግኸውን ነገር ሁሉ በምን ጊዜ እንዳደረግሃቸው ፣ በምን ምክንያት እንደ ፈጸምካቸው አንድ በአንድ እያሳሰቡህና እያስታወቁህ እንዲሁም እየወቀሱህ በልብህ ውስጥ እንደ ብር አንጥረኛ ማኅተም የተቀረጹ ይሆናሉ፡፡ በአጭሩ ሲጠቃለል ለአንተ አሳፋሪዎች ይሆኑብሃል ፣ በአስፈሪው በታላቁ የፍርድ ቦታም እንድታፍርና እንድትዋረድ ያደርጉሃል፡፡ ሁሉም ቅዱሳንና ሰማያውያን ኃይላትም በሠራሃቸው መጥፎ ሥራዎች ምክንያት በአንተ ላይ ታላቅ ውድቀት ደርሶ ሲያዩ ስለ አንተ ያዝናሉ ፣ ያለቅሳሉ፡፡
ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሐሪና ምሕረትን የተመላ ነው ፣ መሐሪ የሆነው እርሱ በቅዱስ ፈቃዱ ካልሰማን በስተቀር ንስሐም ሆነ ምሕረት ወይም ሌላ ምንም ነገር የለምና ፤ እርሱ መዝገቡ በምሕረትና በኃዘኔታ የተመላ ነውና ፣ መግደልና ማዳን የሚችል ፣ ወደ ሲዖል ሊያወርድና ከዚያም ሊያወጣ የሚችል ፣ እርሱም የኃጥኡን መመለሱንና መዳኑን እንጂ ጥፋቱን የማይወድ [ ሕዝ.፴፫፥፲፩ ] የሰውነታችንና የነፍሳችን መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
ወንድሞቻችን ሆይ ! ይህን ነገር ልብ ብለን እንረዳ ፣ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር ተገንዝበን ከአሁን ጀምሮ ከእንግዲህ ወዲያ ጠቢባን እንሁን፡፡ አስቀድሞ ለአልዓዛር እንዳዘነለትና እንዳለቀሰለት ፣ ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀን በኋላም እንዳስነሣው [ ዮሐ.፲፩፥፩-፵፬ ]፡፡ ስለሆነም በምሕረቱ ሕያዋን ሆነኝ እንኖር ዘንድና ያዝንልን ዘንድ በጸሎቱና በተቀደሰ ዕንባ ወደ እሱ እንቅረብ፡፡ "
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና በረከቱ አይለየን፡፡

✥ የተቆለፈ ሳጥን
#ልዩ_ልዩ
አንድ በተቆለፈ ሳጥን ላይ ተቀምጦ የሚለምን ለማኝ ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀንም በዚያ መንገድ የሚያልፍ ሰው ወደሱ ጠጋ ብሎ ለመሆኑ የተቀመጥክበትን ሳጥን ከፍተህ ውስጡን አይተህ ታውቃለህን ? ብሎ ጠየቀው። ለማኙም አረ አላቅም አለና ከፍቶ ቢያየው ሳጥኑ በወርቅ በብር የተሞላ ነበር። እኛም እንደዛ ነን እኔ ዋጋ የለኝም አልረባም ብኖር ባልኖር። አልጠቅምም እንላለን። ግን አንድም ቀን ውስጣችንን አይተን አናውቅም። ውስጣችን ግን ወርቅ በመሰሉ አላማዎች እንቁ በመሰሉ በጎ ሀሳቦች የተሞላ ነው። ማይልስ እንዳለው የአለም ውድ ሀብት ያለው በአረብ ሀገራት የነዳጅ ቦታ ውስጥ አይደለም የአለም ውድ ሀብት ያለው በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ቦታዎች ውስጥም አይደለም ።የአለም ውድ ሀብት ያለው የመቃብር ቦታዎች ውስጥ ነው።
ምክኒያቱም ብዙዎች ወደዚህ አለም ይዘው የመጡትን አላማና ራዕይ አውጥተው ሳይኖሩትና ለአለም ሳያበረክቱት ስለሚሞቱ ነው። ማግኘት ማጣት የጊዜ ጉዳይ ነው። ማንም ባዶ የለም ምንአልባት አሁን ባዶ እጃችንን እንሆን ይሆናል ነገር ግን ባዶ ልባችንን አልተፈጠርንም። ለዝች አለም የምናበረክተው አንዳች ነገር በውስጣችን አለ። እኛ ምን አልባት ለቤተሰቦቻችን በስህተት የተወለድን ይመስላቸው ይሆናል። ነገር ግን በስላሴ ዘንድ መለኮታዊ አጀንዳ ተይዞልን ለአለማ ተወልደናል። አለም ላይ ላሉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ የያዝን አለን: ለተዘበራረቀው ፖለቲካችን የተስተካከለ የአመራር ብቃት ያለን አለን ፡ እየጠፉ ላለው ስነፅሁፋችን የተባ ትንቱግ ብዕር የጨበጥን አለን ፡ ብቻ ሁላችንም ውስጥ ውድ ሀብት አለ። እኛ ግን ቆልፈንበት ተቀምጠናል እናውጣው እንጠቀምበት

#የጸሎት_ጠባይ
ከምንም ነገር በላይ የጸሎት ጠባይ ማለት ምንድን ነው? ለጸሎት ድካም፥ ትኩረትና ጥረት ማውጣት ተገቢ ነገር ነው?
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ብሏል፦ "ጸሎት በሕይወት ማዕበል ውስጥ መጠጊያ ወደብ ማዕበል ለሚያንገላታቸው መልሕቅ የድሀው ሀብት የባለጸጋው ደህንነት የታማሚው መዳኛ ወይም ጤና ማግኛ ነው። ጸሎት መጥፎ ነገሮች ያስወግዳል መልካሙን ግን ይጠብቃል።"
ይኸው እግዚአብሔርን የያዘ መንፈሳዊ አባት በዚያው አስከትሎ ሲናገርም እንዲህ ብሏል፦ "ጸሎት የነፍስን ተራ ስሜቶች ጸጥ ያደርጋል የቁጣን ዓመጽ ያበርዳል ቅናትን ያጠፋል ክፉ ፍላጎቶችን ይበትናል የዓለማዊ ነገሮችን ፍቅር ያመነምናል ለነፍስም ታላቅ ሰላምና እርጋታን ያመጣል።"
የጸሎት ጠባይ ከሚሰጠው ነገር ግልጽ እየሆነ ይመጣል። ባለ መሰላሉ ቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ መንገድ ነው ብሏል። ለእያንዳንዱ ሰው የጸሎት ጥቅም ለማስተማር ሲል ዓለሙን ኣቋርጦ ለመሄድ ይፈልግ የነበረውና በጥብቅ ምናኔ ሕይወቱ የሚታወቀው የሲናው ቅዱስ ጎርጎርዮስም እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፦ "ጸሎት ለጀማሪ ሰዎች መልካም እስት ሲሆን ቀድሞ ለጀመሩት ደግሞ በተቀጣጠለ ጊዜ መልካም መዓዛ የሚያወጣ እሳት ነው። ጸሎት ለልብ እንዲህ እያለ ይነግረዋል፦ ጸሎት የድህንነት፥ ተስፋ፥ የመንጻት ምልክት፥ የቅድስና ምሳሌ፥ የእግዚአብሔር እውቀት፥ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ደስታ፥ የነፍስ ተድላ፥ የእግዚአብሔር ምሕረት፥ የእርቅ ምልክት፥ የክርስቶስ ማሕተም፥ ጎልቶ የሚታይ የጸሐይ ጨረር፥ የክርስትና እምነት ማረጋገጫ የመላእክት ሕይወት ማስረጃ ነው።"
ለጸሎት ጥብቅ እንቅፋቶች፦
#እጅግ_የበዛ_እንቅልፍ፥
#እጅግ_የበዛ_ምግብ፥
#እጅግ_የበዛ_ወሬ እና
#እጅግ_የበዛ_ምቾት ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅፋቶች እግዚአብሔርን ለማስረሳትና ሰውነት ልፍስፍስ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፥ ነፍስ ንቁ በመሆን መምፈሳዊ ሐሴት እንዳያደርግም ነግሮች አስቸጋሪ ያደርጋሉ። ራስን ለማጥራት አይረዱም በጸሎት ጊዜ የተረጋጉ ሰላማዊና ጸጥ ማለት ለሚገባቸው ሕሊናን ልብንና ፍትሕን ግራ ያጋባሉ።
#አቡነ_ሺኖዳ

ፆመ ፍልሰታ የእመቤታችን እረፍት ትንሳኤና እርገት ሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ እመቤታችን በተለያዩ ጊዜያት ሞትና ትንሣኤዋን ለሐዋርያት የገለጸችበትን ምስጢር ከነሐሴ 1-16 ድረስ ምእመናን በጾም በጸሎት ተወስነው የልጇን ቸርነት የእርሷን አማላጅነት በሱባኤ ይማጸናሉ፡፡ የሱባኤው ወቅት ሲፈጸም “እመቤታችን በእውነት ተነሥታለች” ብለው በደስታ የጾሙን ወቅት ይፈጽማሉ፡፡ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን ቅዱስ ያሬድ “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው፡፡ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል” በማለት ገልጾታል፡፡
በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ 64 ዓመታት ያህል ቆይታ አርፋ ተነሥታ በክብር አርጋለች፡፡ ይህንን የትንሣኤና ዕርገት ዐቢይ ምሥጢር ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “ተንሥአ እግዚኦ” ውስተ ዕረፍትከ፡፡ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፡፡ አንተና የመቅደስህ ታቦት” /መዝ.131፡8/፤ እንዲሁም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” /መዝ.44፡9/ ሲል የተናገረው ቃለ ትንቢት በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና የጸናች የቅድስት ድንግል እመቤታችንን ዕረፍት፣ ትንሣኤ፣ ፍለሰት /ዕርገት/ ያስገነዝባል፡፡ /ራእ.11፡19/
እመቤታችን ታቦተ እግዚአብሔር መሆኗን አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ሲገልጽ “ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ” ሲል አመስግኗታል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በትርጓሜያቸው ይህንን ቃለ ትንቢት ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ከገለጣት “ንግሥተ ሰማይ፤ የሰማይ ንግሥት” /ራእ.12፡1/ ጋር በማገናዘብ የእመቤታችንን ሁለንተናዊ ክብርና ልዕልና አምልተውና አስፍተው ገልጸውታል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ “… በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው፡፡….. ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል” /ራእ.14፡13/ ብሎ እንደመሰከረው እመቤታችን ከዕረፍቷና ዕርገቷ በኋላ የመጨረሻ ወደ ሆነው ክብር መሸጋገሯ ያስረዳል፡፡
ይህንን ክብርዋን በመረዳት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር “ወበእንተዝ ናዐብየኪ ኩልነ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ንጽሕት ኩሎ ጊዜ፡፡ ንስአል ወናንቀዐዱ ኀቤኪ ከመ ንርከብ ሣህለ በኀበ መፍቀሬ ሰብእ፤ ሁልጊዜ ንጽሕት የምትሆኚ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ስለዚህ ነገር እናከብርሻለን፣ እናገንሻለን፡፡ ሰውን ከሚወድ ልጅሽ ዘንድ የቅርታንና ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ሁል ጊዜ ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን፡፡ በማለት ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ሁል ጊዜ ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን፡፡ በማለት ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣትን ልዩ የቃል ኪዳን ጸጋና አምላካዊ ክብር እያመሰጠሩ ያመሰግኗታል፡፡ ሊቁ “ቀስተ ደመና ማርያም ትእምርተ ኪዳኑ ለኖኅ፣ ዘእግዚአብሔር ሤመኪ ለተዝካረ ምሕረት ወፍትሕ፣ ህየንተ ቀስፋ ለምድር ወአማሰና በአይኅ፡፡ ብሎ እንዳመሰገናት፡፡
እመቤታችን በአጸደ ሥጋ ሳለች ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ በመዋዕለ ሥጋዌ ላደረገው የድኅነት ዓለም ጉዞ ምክንያት ነበረች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ባርነትና ስደት ለማጥፋት ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ የሰው ልጆችን ያሳደደ ሠይጣን በሄሮድስ አድሮ ሲያሳድደው ልጇን ይዛ በመሰደድ ለድኅነታችን ምክንያት ነበረች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ባርነትና ስደት ለማጥፋት ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ የሰው ልጆችን ያሳደደ ሠይጣን በሄሮድስ አድሮ ሲያሳድደው ልጇን ይዛ በመሰደድ ለድኅነታችን ምክንያት ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራእዩ እንዳየው፤ “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ እርስዋም ፀንሳ ነበር፡፡ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች፡፡ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ፡፡ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ፡፡ ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስልሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች ”/ራእ.12፡1-6/

1🔷የእብደት የመጀመሪያ ምልክት እራስን
አዋቂ አድርጎ ማሰብ ነው!"
2🔷መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ
3🔷የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን፤ ቢሆንም
ደግነትህ አትናገር!!"
4🔸ራሱን ያጎበጠ ሰው መቼም ሌሎችን አቅንቶ አያውቅም
5🔸ችግርን በጥቅም ላይ እንደማዋል ጣፋጭ ነገር የለም
6🔸መጥፎ ቀን የምንለው
መጥፎ ሃሳብ ያሰብንበት ቀን ነው
📮ድህነትን አትፈርበት! የሚያሳፍርህ ነገር ቢኖር የአዕምሮ ድህነት
መሆኑን እወቅ
7…" ቃል ለመግባት የዘገየህ፤ ከገባህ ደግሞ የፈጠንክ ሁኑ!!"
8…"የአንተን ውድቀት ለሚመኙ ስትል ራስህን አሻሽል!!"
9……" መጀመሪያ ራስህን እወቅ! ጠንካራ ጎኖችህን ይበልጥ አጠንክርህ
በድክመትህ ላይ ፈጥነህ ዝመትባቸው!!"
10……" የተፃፈውን ሁሉ አንብበህ በህሊና መዝገብህ ከመፃፍህ በፊት
በህሊናህ ሚዛንህ አብጠርጥር!!"
11……" ምላስህን ካልጠበካት እስዋ አትጠብቅህም!!"
12……"መከራን እና የተወረወረ ድንጋይን ዝቅ ብሎ ማለፍ ብልህነት
ነው!!"
13……" መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ!!"✔
14……" ራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ በኑሮው ደስተኛ ነው!!"
15…" ጠንካራ ሞራል የህይወት ተስፋ ነው!!"
16.…" ጨዋ አንደበት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል!!"
17.." ዛሬን ስለነገ በመጨነቅ ካሳለፍከው ዛሬን በቅጡ መኖር
ተስኖሃል!!"

ጳጉሜ/ጳጉሜን
ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት
ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ
ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን
ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine /
በመባል ትታወቃች ፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ
ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ
ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ
በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት
በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/
በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ
ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን
ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት
ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ
ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ
ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር
አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡-2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው
በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ
ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን
እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም
ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን
ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ
ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን
ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ
ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፡-2 ፡፡ ከዚህ
በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ
እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር
አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን
ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን
ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ
የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው
የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ
ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና
ነው፡፡
ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት
ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን
የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው
ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ
ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን
ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ
ያደርግልናል፡፡ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንላችሁ፡፡

ከቤት ያሳደግነው ሴይጣን🙊
.......አንድአንድ ሰዎች በጭራሽ የማያዉቁትን ሰው አይተዉ ዝም ብለዉ ከመሬት ተነስተዉ "ይህንን ሰዉዬ ቆሌዬ አልወደደዉም"ይላሉ።አንድ አንዴ ደግሞ ከሱቅ የሆነ ዕቃ ሲገዙ እንደዚሁ "ይህን እቃ ቆሌዬ አርፎበታል በጣም ወድጀዋለሁ" የሚሉ ሰዎች ገጥመዋችሁ ያዉቁ ይሆናል።ይህ ቆሌ እንግዲህ የዕለት ከዕለት ኑሮአቸዉ ዉስጥ እየገባ ለዛም፣ለዚህም ፣እየጠቀሱ እንደ ድመት እና ዶሮ በቤታቸው ያሳደጉት ይመስል እንደግላቸው ንብረት የሚያዩት ጥቂት አይደሉም።በአንድ አንዶቻቸው ህይዎት ዉስጥ ሳያዉቁት እንደ ቀልድ ቆሌ የበላይ አዛዣቸው ሆኖ የሚበሉት ቆሌአቸው የወደደውን ነው።የሚተዋወቁት ሰው ከቆሌቸው የተስማማውን ብቻ ነው።አንድ አንዴ ደግሞ ስሜታዊ ሲሆኑ ከቆሌም ከፍ ብለዉ "እንግዲህ ሴጣኔን አታምጣው" የሚሉበት አጋጣሚ አለ። አስባችሁታል "ሴጣኔን" 😊😊።የራሳቸው፣የግላቸው ሴጣን ማለት ነው።ይህ ማለት "ቆሌ" የሴጣን የዳቦ ስሙ መሆኑ ነው ማለት ነው እንግዲህ።ሲሻቸው ቆሌአችን፣ሲሻቸው ደግሞ ሴጣናችን ስለሚሉ ማለት ነው።በተለይ ደግሞ በድንጋጤ ወቅት ብዙ ጊዜ"ወይ ቆሌዬ ተገፈፈ"የሚል ንግግር እንሰማለን።ሌላው የ"ቆሌ"ቅፅል ስም ደግሞ "ሙድ" ነው።"ኡፍፍፍፍ ሙዴን ከነትከው" ይባላል ብዙ ጊዜ።ግን ይህ ቆሌ የሚባለው የግል ጣኦት ምንድነው?ከየት አመጣነው?ማንስ አስተማረን?ሙድስ ምንድነው?ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት እስኪ ከራሳችን ባህሪ ተነስተን ስለ ቆሌ አንድ አንድ ባህርያትን እንመልከት።በራሳችን የህዎት ጉዞ ባየነውና በተረዳነው ልምድ ቆሌአችን በባህሪው ለነፍስ የሚበጁ ነገር ግን ለስጋ የማይመቹ ነገሮችን በፍፁም የማይወድ ለስጋችን ያደላ ቅምጥል አለቃችን(ጣኦታችን) ነው ማለት ይቻላል።ቆሌ የአምላክ ምስጋን ከሆነው መዝሙር ይልቅ የሰይጣን መስዋይዕት የሆነውን ዘፈን ይመርጣል። ብዙ ጊዜ አንድ አንዶቻችን "መዝሙር መስማት ይጨንቀኛል" እንላለን። የሚጨንቀው ግን እኛን ሳይሆን ቆሌአችንን ነው።ያው እርሱን ጨነቀው ማለት እኛን ጨነቀን ማለትም አይደል?ያው የሚያዘን እርሱ ነዋ!!! እርሱ መዝሙር ቢሰማም ወደ ዘፈን ያደሉ የዘመኑን መዝሙሮች እየመረጠ ነው የሚሰማው(ዕድሜ ለተሃድሶዎች ይሁንና) በተለይ ደግሞ የእነ ጋሽ "ሉተራዉያን" መዝሙር ይሉት የዳንኪራ ዘፈን በጣም ይመቸዋል።ልብን በተመስጥኦ ወደ እግዚአብሔር የሚያመጥቀው የንሰሃ መዝሙር ባለበት ግን "ጨነቀኝ" ይመጣል።ቤተክርስቲያንም የመሄድ ፍላጎት በፍፁም አይኖረዉም።ከዛ ይልቅ እንቅልፍና በሰበባሰበቡ ከቤተክርስቲያን መራቅ ይፈልጋል።ተኝተን ሰዎች እንኳን ቤተክርስቲያን እንሂድ ቢሉን "ትንሽ ዉስጤ ጥሩ አይደለም ደብሮኛል ተኝቼ ራሴን ማሳረፍ እፈልጋለሁ"እንላለን።የእግዚአብሔር መንፈስ የረበበት ሰው ግን"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስስስ አለኝ" ይላል።ቆሌ ግን ፅሎት እንድንጀምር ፈፅሞ አይሻም።እንደምንም ብለን እንኳን ብንጀምርም ቶሎ እንዲያልቅ ያለው ፍላጎት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው።አንድ አንዴ "ሙድ" ብለን የምንጠራው ራሱ የቆሌ ሌለኛው ስሙ መሆኑን ደግሞ ልብ በሉ።ምክንያቱም ለነፍሳችን ለሚጠቅም ነገር ማለትም መፀሐፍ ቅዱስ ለማንበብ፣ለመፅለይ፣መዝሙር ለመስማት፣ስብከት ለማዳመጥ፣ፅበል ለመጠመቅ ሁሌ ሙዳችን ዝግ ነው።ነገር ግን ለሌሎች ዓለማዊ ነገሮች ደግሞ 24 ሰዓት ሙዳችን ኦን ላይን ነው ማለት ይቻላል።እንግዲህ ሙድ፣ቆሌ፣ስይጣኔ ብለን የግላችን ከምናደርገው፣ከምናቆለባብሰው፣ይህንን ስሙን ቀይሮ ዉስብስብ የጦር ስልት ቀይሶ የሚዋጋንን አዳኝ ጠላታችን ሴይጣንን ቤተክርስቲያን በመሄድ"እክህደከ ሴይጣን በቅድመ ዛቲ እምየ ቅድስት ቤተክርስቲያን"ልንለው ይገባል እንጂ ሙድ ምናምን እያልን እስከ መቼ ሲያሻን "ሙድ" ስንለው፣ሲያሻን "ቆሌአችን" ስንለው፣ባስ ሲል ደግሞ "ሴይጣኔን" እያልነው የሚሻዉን እያደረግንለት፣በባርነት እየተገዛንለት ከዲያብሎስ ጋር ተስማምተን እንኖራለን? ስጋዉያን እስከሆንን ድረስ ብዙ ሠርተን መድከማችን እረፍት መሻታችን ግድ ነው።ነገር ግን ዲያቢሎስ የትክክለኛውን እንቅልፍ እና ድካም በሃይ ኮፒ አመሳስሎ ድብርት እና ሙድ በሚል ስም 4 ደቂቃ እንኳን ሳንሰራ 24 ሰዓት እንቅልፍ ድካም ይለቅብናል።የሰው ልጅ ሳይሰራ የሚደክመው ከሆነ፣ጥሮ ግሮ ሳይለፋ እንዲሁ ቀኑን ሙሉ አካሉ የሚዝል ከሆነ፣ሁሌ ሙዴ ጥሩ አይደለምን የሚያበዛ ከሆነ፣ያኔ አቶ ቆሌ ስራውን ሰርቷልና የጤነኝነትም መልክት አይደለምና በፍጥነት ወደ ተዋህዶ ሆስፒታል በመሄድ ቢያንስ በቀን ጠዋት እና ማታ ሁለት "እክህደከ ሰይጣን(ፅሎት) እና ስግደት ቴራፒ ያስፈልገዋል።ፅበል፣ቅዳሴ፣ንሰሃ ና ስጋ ወደሙ ሲጨመሩ ደግሞ ሙሉ ፈውስ አግኝቶ ከሙድ እና ከቆሌ ባርነት ሥጋም ነፍሱም ነፃ ይሆናሉ።በነገራችን ላይ ይህ ሙድ ይሉት ሴይጣን ብዙዎችን ወደ ሲጋራ መርቶአቸዋል።ቀላል የማይባሉትን ወደ መጠጥ ገሚሶቹን ወደ ጭፈራ እና ዝሙት ኃጢአት ከቷቸዋል።ባስ ሲልም በራሳቸው ላይ ጨክነው የሥላሴን መቅደስ ያለ ስልጣናቸው እስኪያፈርሱ፣ራሳቸውን እስኪያጠፋ ድረስ ወስዷቸዋል።ከሰው አጋጭቶ ትዳር አፋቷል፣ ከጎረቤት አለያይቷል፣ከዘመድ አራርቋል።እንግዲህ ቆሌ ብለን እንደቀልድ ያየነው ሙድ እያልን እንደዋዛ የምንናገርው የዲያብሎስ ወጥመድ እያሳሳቀ በ1000km/s እጅግ ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት ወደ ሞት ከተማ እየወሰደን መሆኑን ልብ እንበል።ሁላችንም ራሳችንን እንመርምር እናስመርምርም።እሲኪ ወደ ኃላ መለስ ብለን ያጠፍናቸውን ጥፋቶች ፈጣሪን ያስከፋንባቸውን ቀናቶች እናስታዉስ።ለእኒዚያ ክፋ ክስተቶች መፈጠር ምክንያቱ ምን ነበር? ብለን እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ።እመኑኝ ምክንያቱ ከዚህ ቆሌ ወይ ደግሞ ሙዴ ወይ ደግሞ ሴይጣኔ ብለን ከምንጠራው የራሳችን ካደረግነው የሴጣን ወጥመድ ዉጪ የሆነ አይደለም።ሙዴ ተከነተ(ደብሮኛል) ብለን ከመጠን በላይ ጠጥተን አይደለም አጭሰን ይሆናል፤ጨፍረን ሌላም ሌላም ነገር አድርገን ይሆናል።ከመጠን በላይ በመጠጣት ደግሞ ዝሙት ጥል እና ሱስ ተከታትለው ይመጣሉ።ደብሮኛል በሚል ሰበብ ብዙ ወጣቶች እንቅልፋቸው ሳይመጣ ወደ አልጋ ስለሚወጡ "ግብረ አዉንያ" (ሴጋ) ለሚባል አደገኛ የዲያቢሎስ ወጥመድ ዉስጥ ተዘፍቀዋል።ሙዳቸውን ለማስተካከል ሲሉ በሚያዩት ዓለማዊ ፊልም እና ለዝሙት የሚቀሰቅሱ የእርቃን ዘፈኖችበሚበማየት ጥቂት የማይባሉ ወጣቶች በፍትወት እሳት ተቃጥለዋል።ይህ ደግሞ ለዲያቢሎስ ስኬት ለእኛ ለአዳም ልጆች ደግሞ የሞት ሞት ነው። ልንነቃ ይገባል ዲያቢሎስ እጅግ ዉስብስብ ወጥመዶችን እያዘጋጀ እያጠመደን ይገኛል።በማናስበው እና ባልገመትነው መንገድ በቀላሉይመጣብናል።ምክንያቱም እርሱ 5700 ዓመት በላይ በክፋት የሥራ ልምድ አለው።እኛ ግን ትላንት ነው የመጣነው።እንዲህ አንችለዉም እጅግ በጣም ረቂቅ እስትራቴጂ ነው ያለው።የምናሸንፈው በፀሎት እና በፀሎት ብቻ ነው።አይደለም 24 ሰዓት ተኝተን 24 ሰዓት ፀልየንም ፈተናው ከባድ ነው።ልንተጋ ይገባል፣ልንዋጋው ይገባል፣የምንዋጋው ግን ከስጋዊ አካል ሳይሆን 24 ሰዓት ከማይተኛ መንፈስ ጋር ነው።ስለዚህ 24 ሰዓት ከማይተኛ ጠብቂያችን ጋር መሆን ይኖርብናል።ከእግዚአብሔር ጋር።ከእርሱ ጋር እንድንሆን የሚያገናኘን ድልድይ ደግሞ ፀሎት ነው።ሚሳየላችን የጦር መሳሪያችን ፀሎት ነው።ስለዚህ በርትተን እንፀልይ እግዚአብሔር አምላክም በምህረቱ ይጠብቀን
ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን!ይቆየን፣ያቆየን።

ወዳጄ ሆይ፦
ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛቆሮ.10፥31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡