ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
1.41K subscribers
85 photos
4 files
99 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
የሰርግ ልብስ
፨፨፨፨፨፨፨፨

አንድ ሰው መጥቶ እናንተ የምትለብሱትን አንዲት ቁራጭ ልብስ እንኳ ሳይሰጣችሁና ሰውነታችሁ በብርድና በዋዕየ ፀሐይ እየተቆራመደ ሳለ ቤታችሁን በወርቅና በተንቆጠቆጠ የመጋራጃ ዓይነት ቢያስጌጥላችሁ ምን ጥቅም አለው? እኛስ ነፍሳችን ዕራቁቷ ሳለች ሥጋችንን ወርቅ ብናለብሰው በወርቅ ብናስተኛው ምን ትርጉም አለው? ነፍሳችን በመሬት እየተንፏቀቀች ደሳለኝ ሥጋችን በከበሩ ሠረገሎችና የተለያዩ ማጓጓዣዎች ብትንፈላሰስ ምን ጥቅም አለው?ልጆቼ! እውነተኛውን ልብስ ልበሱ። የሰርጉን ልብስ ልበሱ። እስኪ ወደየገዳማቱ ሒዱና ይህን ከቅዱሳን አበው ወእማት ተማሩ።
እነዚህ ቅዱሳን በእልፍ ወትእልፊት ዕንቁ የተሽቆጠቆጡ ልብስ ብትሰጥዋቸው አይቀበልዋችሁም። ለምን?እነእረሱ ጋር ያለው ልብስ እናንተ ይዛችሁት ከሔዳችሁ ይልቅ በእጅጉ እንደሚበልጥ ስለሚያውቁ። ይኸውም የነፍሳቸው ልብስ ማለቴ ነው። ለነእርሱ ይዛችሁት የሔዳችሁት ልብስ ለአንድ ምድራዊ ንጉሥ ብትሰጡት እጅግ ያመሰግናችኋል። እነእርሱ ግን ከዚህ ንጉሥ በላይ በከበረ ልብስ ያጌጡ ናቸውና አይቀበልዋችሁም። ወርቃቸውን ወደሚያስቀምጡበት መዝገብ
/ልቡናቸው/ ገብታችሁ ስታዩማ ራሳችሁን ሰታችሁ ትወድቃላችሁ።የሀብታቸውን/ምግባር ትሩፋታቸውን/ ብዛት የወርቃቸውን ንጻት እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። እናንተም ከእነእርሱ ተማሩና እውነተኛውን ልብስ ለመልበስ ተሽቀዳደሙ።
https://t.me/yeberhanljoche
🌼✞              🕯🕯🕯              ✞🌼                 

በቸርነትኽ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።
የምድረ በዳ ተራራዎች ይረካሉ፥ኰረብታዎችም በደስታ ይታጠቃሉ።

🌼 ✢     መዝ 64÷11-12      ✢ 🌼

ውድ የውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ ብዙ ሰዎች በህይወታቸው አንዲት የንስሐ ቀን በተሰጣቸው በተመኙ ነበር ግን አልቻሉም እኛ ግን ሳይገባን እንዲሁ ከወደደን ከእግዚአብሔር ሌላ 365 የንስሐ ቀናት በታላቅ ስጦታ መልክ ተሰቶናል እና እንጠቀምበት ይህ ዘመን ሀገራችን ሳላም ሆና የምናይበት ይሁንልን ለኛም መልካሙን የተመኘ ነውን ከኀጢአት በስተቀር አምላክ ይፈፅምልን መልካም አመት እንዲሆን መልካም ምኞቴ ነው።

      ከ ው/ሰ/ት/ቤት መልካሙን ሁሉ እመኝላቹሀለው መልካም አዲስ አመት።
ይቅርታ ምንድን ነው ?

የይቅርታ ጥጉስ እስከምን ነው ?

“ትርጉም የሌለው ይቅርታ ፈርዶ ከመግደል አይለይም” ዛሬ በህይወት ባይኖሩም ትምህርታቸው ግን ህያው ሆነው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ፡- ብጹዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ፡፡

ሰው የግጭት አካል ነው፡፡ ፍጹም ተሆኖ አይኖርም፣ አይቻልምም፡፡ የሰው ሰውነቱ የሚለካው በስሁትነቱ ነው፡፡ ጻድቅ ጻድቅነቱ ሰባት ጊዜ ወድቆ ሰባት ጊዜ መነሳቱ የጽድቁ ልኬቱ እንደሆነ ሁሉ ማለቴ ነው፡፡ ይቅርታን መጠየቅ መጸጸት ሲሆን ይቅርታን ማድረግ ግን ታላቅነት ነው፡፡ ማመን ቀላል ሲሆን መታመን ደግሞ እጅግ ከባድ ሸክም ነው፡፡ ማመን ኃላፊነት መወጣት ነው፣ መታመን ግን ኃላፊነትን መሸከም ነው፡፡ ይቅርታ በማድረግ ውስጥ “ፍጹምነት” ሊኖር ግድ ነው፡፡ ይቅርታን የምታደርጉ ሁሉ ሸክምን ይቅርታችሁን ጠይቋችሁ ለሰጣችሁት ሰው እንዳሸከማችሁት እመኑ፡፡ ቅርታን ስታደርጉ “እዳው በአንተ ላይ ይሁን” ማለታችሁ ነው፡፡ ስለሆነም ወደ ኋላ ከመመለስ ይልቅ እንደ ጳውሎስ በፊታችሁ ያለውን ለመያዝ ሩጡ እንጂ ያስተፋችሁትን ቆሻሻ መልሳችሁ ለመቁጠር ወደ ኋላ ለመመለስ ቁጥር አትጀምሩ፡፡

እግዚአብሔር መሐሪ ነው፡፡ ምን ድረስ ? ልጁን ኢየሱስን እስከመስጠት ድረስ፡፡ ይቅር የምንል ሁሉ ይቅርታ የተደረገልን ነን፡፡ በወንጌል ላይ እዳው ተሰርዞለት በደስታ ዘልሎ ሳይጨርስ እሱ ደግሞ እዳ ያለበትን ባለእዳውን ሲመለከት የተሰረዘለት እዳው ተረስቶት ባለእዳውን ያነቀውን ሰው አስቡት፡፡ የእሱ እዳ እንደተሰረዘለት እሱም የሌላውን እዳ መሰረዝ ሲኖርበት እሱ ግን ባለ እዳዬ ያለውን በማነቁ ወደ ወኅኒ መጣሉን አስታውሱ፡፡ ከክፋት ሁሉ የከፋ ክፋት የሰጠነውን ይቅርታ መልሰን ለመንጠቅ የምናደርገው ነው፡፡ ይቅርታ ያልነውንና . በደል እያነሳን ማቁሰል እግዚአብሔርን አለማወቅ ክፉ ቂመኝነትም ነው፡፡ የእኛ ድርሻ በይቅርታ ውስጥ የይቅርታን ጌታ አስታውሶ በንጹህ ኅሊና መኖር ነው፡፡ “ትቼልሃለው” ብሎ ትቶ መኖር እንዴት ያለ ክርስትና መሰላችሁ ! እዳን ለባለ እዳ ተዉለት እንጂ የእዳ ተሸካሚ አትሁኑ፡፡ ክርስቶስ እዳን ሰረዘ እንጂ አልቆጠረም፡፡ ታዲያ የሰረዝነውን እዳ መልሰን የምንቆጥር እኛ ከማን ተምረን ነው ? በማመን ወደፊት ሂዱ እንጂ በመጠራጠር ወደ ኋላ አትመለሱ፡፡ እግዚአብሔር ተቆጣጥሮልን እንጂ እኛ ተከታትለን የምናሸንፈው ነገር የለም፡፡

ይቅርታ ዋጋ አውጥቷል፡፡ ይቅርታ ዋጋ ያeወጣልም ፡፡ የምንወደውን ሰው ይቅር ለማለት ዋጋ እንከፍላለን፡፡ ዋጋው የቀደመውን ፍቅርና ለይቅርታ ራቁቱን የተሰቀለውን ማሰብ፡፡ በአንድ ወቅት ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ጌታ ቀርቦ “ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት?” አለው፡፡ ጴጥሮስ ግን ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ከመጠበቅ ይልቅ የውስጥ ደንዳናነቱ እንዲጸድቅለት በማሰብ ይመስላል በትንሽዋ አእምሮው ያለውን የራሱን አስተያየት ሰጠ፡፡ “እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” በዚያ የመስቀል ስቃይ ላይ ሆኖ የሰቀሉትን ይቅር ያለና ለሰቃዮቹ እንኳን የመዳንን ሀብት የሰጠ ጌታችን ግን እንዲህ አለ “እስከ 70 ጊዜ 7 እንጂ እስከ 7 ጊዜ አልልህም” ማቴ 18 ÷ 21-22 በሂሳብ ስሌት መሰረት በቀን 7 x 70 = 490 ጊዜ ይቅር ማለት ይጠበቅብናል፡፡ እውነተኛ ፍቅር ይህ ነው፡፡ እውነተኛ ፍቅር ይሰርዛል እንጂ አያከማችም፣ ኃጢአትን ያፈሳል እንጂ አይቋጥርም፣ ያቅፋል እንጂ አይወጋም፣ ያክማል እንጂ አያደማም፡፡ ይቅርታ ማድረግ ትክክለኛ ትርጉሙ “መተው” ወይንም “መርሳት” መሆኑን ክርስቶስ ተማሩ፡፡ ጠቢቡ እንዲህ ይላል “ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፣ በደለኛውንም ይቅር የሚል ክብር ይሆንለታል” ምሳ 19÷11

የይቅርታ ሰዎች የሆናችሁ የመንግስቱ ውራሾች ያድርገን አሜን መልካም ቀን
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
" ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ . . ." (2ኛ ጢሞ 1፥9)

መለኮታዊ የሆነውን ተልእኮ ለመፈጸም ከቶ የሰውን ፈቃድ መጠበቅ የለብንም። እግዚአብሔር ወደራሱ ሲጠራን ማንንም አላማከረም፤የእኛን የልብ ፈቃድ ከመመልከት ውጪ። ማንም ደግሞ እግዚአብሔር ወደራሱ እንዴት እንደሳበንና ልባችንን እንደነካው ፍጹም የሆነውን ሚስጥር አያውቅም፤ ከድንጋይ ይልቅ ጠጣራ፣ እንኳን የሰውን የአምላክን ማንነት ክዳ በምድረበዳ ልኖረችው ልባችን፡ እንዴት አድርጎ ክርስቶስ በፍቅሩ መዶሻ እንዳፈረከሳት የሚረዳም ሆነ የሚያውቅ ፈጽሞ የለም። እናም ሰውን ደስ ከማስኘት ይልቅ አምላክን መታዘዘ ብርቱ ከሆነ ኪሳራ አውጥቶ ዘላለማዊ ትርፍ የሚስገኝ ነገር መሆኑን ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ነው።

በልብህም ይሁን በአእምሮ ጽላት ላይ የተጻፈውን መልኮታዊ አጀንድ፣ ለእግዚአብሔር ይህን በሕዝቤ መካከል አደርጋለው ብሎ ሲያመልክትክ ለልብህም ሲናገራት ማንን አማክሮ ነው? ባጠገብህስ ማንን ምስክር አስቀምጦ ነው? አምልካዊ እይታውን መንፈሳዊ አይኖችህን አብርቶ በመንግስቱ ውስጥ የድርሻህን እንድትወጣ ያየውን እንድታይ እና እንድትከውን ራዕይን ሲሰጥህ ማንን ተማምኖ ነው? ከዚያ ከውዳቂ ሰፈር እውጥቶ ወደ አላማ እና ግቡ ወደ ሚያደርሰው የከበረ ሰረገላ ላይ ሲያሳፍርክ እርሱን ለመታዘዝና ለመሄድ " አማላክ ሆይ ይህው እኔ ላከኝ" በሚል ልብ በፊት ከመሆን ይልቅ ስለምን በዙሪያ ያልውን ነገር ማይት አስፈለገ? ስለምንስ ካምላክ ይልቅ የሰውን ፍቃድ እንጠብቃልን?? አብርሃም አምላኩን እሺ ባይልና ባይታዘዝ ለዓለሙ መዳን ተስፋ የሆነው የክርስቶስ የኪዳን ዘር ምን ይመስል እንደነበረ ማሰብ ከባድ ነው። ዳዊት ስንቅን ሊያደርስ ሲሄደ ከአምላኩ ይልቅ፡ የሰማውንና የታዘዘው ውንድሞቹን ቢሆን ፍልስጤም በእስራኤል ላይ ምን ያደርግ ይሆን? ከደም መፍሰስ ነጻ ወጥታ የክርስቶስን እግር በሽቱ የጠበችው ማሪያም መቅደላዊት ያንን ለማደረግ ለቧ ከውሰነው ውሳኔ ይልቅ ለደቀመዛሙርቱና በቤቱ ለነበረው ማጉረምረም ታዛ ወደ ኋላ ብትል " ይህ ወንጌል በተነገረበት ስፍራ ሁሉ" የተባለው ስለ እርሷ የተነገረው ምስክርነት ይነገር ይሆን?።

እርግጥ ነው እንዳንድ ጊዜ ተመክሮዎችንም ይሁን ምክሮችን በመልካምነቱ ከሰዎች መቀበል ይሁን፣ መስማትና መተግበር አስፈላጊ ነው፤ ፍጹም በሆነ መንገድ ግን ሰምቶ መልኮታዊውን የአምላክ ትዕዛዝ ለመታዘዝ የሰውን ፍቃድ መጠበቅ ፈጽሞ ስህተት ነው። " ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።" ሐዋ 5፥29
ልንታዘዘው የተገባውን የመልኮትን እጀንዳ ጊዜና ውቅት ልንቀጥርለት አይገባም በፍጹም፤ ዘግይቶ መታዘዝ ካለመታዘዝ አይለይም። እርሱ ነውና ለአላማው የጠራችሁ እርሱን ታዘዙት።

" የሚጠራችሁ የታመነ ነው፥ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።" 1ተሰ 5፥24

ኃጢአት የኀሊናና የመንፈስ ሞት ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ‹‹የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው›› (ሮሜ.፮፥፲፫) ሰው በዚህች በዓለም ውስጥ ሲኖር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ኃጢአት ይሠራል፤ በመታገስ ኃጢአትን ማሸንፍ አቅቶት ክፉት ሲሠራ ለኃጢአት ይሸነፋል፡፡  ይህም ከልጅነቱ ያርቀዋል፡፡ አዳም ከልጅነቱ ተዋርዶ ከገነት የወጣው ለኃጢአት በመሸነፉ ነበር፡፡ ‹‹ክፉን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አታሸንፉ›› (ሮሜ.፲፪፥፳፩) ከአባቱ ቤት የወጣ ልጅ፣ ከእረኛው የተለየ በግ፣ ባለቤት የሌለው ገንዘብ ነውና ኃጢአተኖች የጠፉ ናቸው፤ ዓለማዊ ሕይወት የሚያሸንፋቸው ይጠፋሉና፤ ‹‹ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም››፡፡ (፩ ዮሐ. ፪፥፲፮)
ኃጢአት የሚሠራ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር የለውምና ከፈጣሪው ይርቃል፤ ለዚህም ነው ኃጢአትም ከእግዚብሔር መለየት ነው የተባለው፤ ‹‹ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?፤ ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?›› ( ፪ ቆሮ.  ፮፥፲፬-፲፭)
ኃጢአት እግዚብሔርን ማጣትም ነው፤ በኃጢአት የሚኖር ሰው ራሱንና ልቡናውን ከእግዚአብሔር በመለየቱ እግዚአብሔርን ያጣል፤ ‹‹የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል››፤ (ዮሐ.፲፬፥፳፫)  ፈጣሪን የማያምን ግን ኃጢአትን አብዝቶ ይሠራል፤ መጥፎ ሥራዎችን የሚሠራ ሰው መንፈስ ቅዱስ ይርቀዋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም ሥራ ይቃወማል፡፡ ‹‹ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ›› (ኤፌ.፬፥፴) መንፈስ ቅዱስ በሰው ልቡና ውስጥ ሥራውን ካልሠራ ሰው ንስሓ ሊገባ አይችልም፤ ሰው በኃጢአቱ እንደተጸጸተና ንስሓ እንዲገባ የሚያበረታው መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ ኃጢአተኛ ሰው የሕይወትን ትርጉም አያውቅም፤ ስለንስሓ ቢነገረው ‹በሕይወቴ እንድደሰት ተውኝ› ይላል፤ ምድራዊና ዓለማዊ ደስታ ሕይወት እንደሆነ ያስባልና፡፡
በኃጢአት ውስጥ የኖረ ሰው ውስጣዊ ሰላም የለውም፤ ‹‹ለክፎዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር›› (ኢሳ. ፵፰፥፳፪) ልቡናውም በጭንቀት ስለሚሞላ ፈሪ ይሆናል፡፡ መጥፎ ባሕርይን ይወርሳል፡፡ አዳም ኃጢአትን በሠራ ጊዜ ከዚያ በፊት ያልነበሩ ሦስት ነገሮችን ገንዘብ አደረገ፤ ፍርሀት፣ ድንጋጤና ሰላም ማጣት፤ ፍርሀት የሥነ ልቡና ሕመምተኛ ያደርጋል፤ ኃጢአት ሕሊናን ያደክማል፡፡ ጻድቃን ግን በሰላም፣ በፍቅርና በድስታ ይኖራሉ፡፡ የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነውና፤(ገላ. ፭፥፳፪-፳፫)
በዚህ ምድር ስንኖር ሕገ እግዚአብሔርን በመተላለፍ የተነሳ መርገሞች የሚያስከትሉአቸው ቅጣቶች ብዙ ናቸው፡፡ ‹‹የዚህን ሕግ ቃሎች ያደርግ ዘንድ የማያጸና ርጉም ይሁን…››(ዘዳ. ፳፰፥፳፮) ሰው ንስሓ ሳይገባ ለድንገተኛ ሞት ሊዳረግ ይችላል፤ በበሽታ ይቀጣል፤ ረኃብ፣ ቸነፈርና ድኅነት ይበዛበታል፤ በደልም ይደርስበታል፡፡
ሰው ንስሓ ከገባ ከዘለዓለማዊ ቅጣት ይድናል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር የተወሰነበትን ምድራዊ ቅጣት መቀበል ይኖርበታል፡፡ ያም የሚወሰነው ከሚሠራው የኃጢአት ዓይነት ነው፡፡ በእርግጥ የኃጢአት ትንሽና ትልቅ የለውም፤ ሆኖም ሰው ዐሥርቱ ትእዛዛትን በተላለፈበት መጠን ይቀጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሳ የሚመጣ ቅጣትና በፍትሐ ብሔር ወይም በቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ቅጣት ሊቀበል ይቻላል፡፡ ይህም ለተወሰነ ጊዜ ከቅዱስ ቁርባን መከልከና ቤተክርስቲያን እንዳይገባ መከልከል ሊሆን ይችላል፡፡
 ኃጢአትን አብዝቶ መሥራት በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ መሆንን ያስቀራል፤ የኅሊና ነጻነትንና የልቡና ንጽሕናንም ያሳጣል፡፡ ‹‹እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› (ዘሌ.፲፩፥፵፬) ኃጢአትን የማይተው፣ እስከዕለተ ሞቱም ንስሓ የማይገባ ሰው ግን የዘላለም ቅጣት ይፈረድበታል፡፡ እግዚአብሔር መሓሪና ምሕረቱም የበዛ እንደሆነ ሁሉ ፍርዱም እውነትና ፍጹም መሆኑን፣ በደልን ይቅር የሚል፣ ኃጢአትንም የማይወድ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር ቸርነትና ምሕረት አንጻር ፍርዱንና ቅጣቱንም አስቦና ተረድቶ ወደ ንስሓ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ቸርነቱን በመተማመን ጭከናውን መርሳት፣ ምሕረቱንም ተስፋ በማድረግ ፍርዱንም ደግሞ መዘንጋት አይገባም፡፡ ‹‹እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ጭከናውም በውድቀቱ ላይ ነው፤ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ›› (ሮሜ. ፲፩፥፳፪)
እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ ፍርዱም በትክክል ነው፤ ንስሓ ገብተን ከፊቱ ብንቆም የእግዚአብሔርን ቸርነት እናያለን፡፡ በግድ የለሽነት የምንኖር ንስሓ የማንገባ ሆነን በፊቱ ብንቆም ደግሞ በጭካኔውና በፈራጅነቱ እግዚአብሔርን እናየዋለን፡፡
የዓለም ፍጻሜ የፍርድ ቀን አስደንጋጭና አስፈሪ ነው፤ ‹‹እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞቿንም ከእርሷ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቁጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል›› (ኢሳ. ፲፫፥፱) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ ጣኦቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ፡፡ እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ  ዋሻና ወደ ምድር ንቃት ውስጥ ይገባሉ፡፡ (ኢሳ.፪፥፲፯-፳) ፭ኛው የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳም እንዳሉትም ‹‹ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ››፡፡ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ሲወርሱ ኃጥኣን ግን ዘለዓለማዊ ቅጣት ወዳለበት ገሀነመ እሳት ውስጥ ይጣላሉ፡፡ ‹‹እነዚያም ወደ ዘለዓለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ›› (ማቴ.፳፭፥፵፮)
በዚያች በፍርድ ቀን ለቅሶ፤ ዋይታና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤ ሆኖም ሁሉም የማይጠቅም ጩኸት ነው፡፡ ጨለማውና የማይጠፋው እሳት እጅግ ከባድና አስፈሪ ነው፡፡ ከባድነቱንም ለመረዳት የሚቻለው ግን የጻድቃንን ሕይወት በማየት፣ በመረዳትና በማወቅ ነው፡፡
ምንጭ፤ የንስሓ ሕይወት መጽሐፍ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ  የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፤ ውርስ ትርጉም ቀሲስ እሸቱ  ታደሰ ወንድምአገኘሁ በ፳፻፱ ዓ.ም.

https://t.me/yeberhanljoche
* ሀልወተ እግዚአብሔር *
ሀልወተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው ። እግዚአብሔር የሚባል ነገር የለም የሚሉ አሉና ከሱ እንጀምር ። ታዲያ የእግዚአብሔር መኖር በምን ይታወቃል ? ቢሉ ። 1ኛ.በስነ ፍጥረት ይታወቃል ። ም/ቱም ፍጡር ካለ ፈጣሪ አለና ። ስዕል ካለ ሰዓሊው አለ ፣ ቤት ካለ አናፂ አለ ፣ ሙዚቃ ካለ ሙዚቀኛው አለ ማለት ነው ። ስለዚህ በዚ መሰረት ስናየው ይሄ ሁሉ ስነ ፍጥረት አስገኚ አካል ወይም ፈጣሪ አለው ማለት ነው ። 2ኛ. የሰው ልጆች ዝንባሌ ነው ።ይህም ማለት ግማሹ ሙስሊም ፣ ግማሹ ቡዲስት ፣ ግማሹ ክርስቲያን ፣ ግማሹ ባዕድ አምልኮ አምላኪ የሆነው ነብሱ ከውስጥ የፈጠራት አካል እንዳለ ስለምትጮህ ነው ። ስለዚ ይህም አንዱ የፈጣሪ መኖር ማስረጃ ነው ። 3ኛ.የቀናትና የወቅቶች መፈራረቅ ነው ። ይህም ለምሳሌ መብራት ሲጠፉና ሲመጣ መብራት ሀይል የሚባል አካል እንዳለ እንደምንረዳው ሁሉ ፡ የቀንና የማታ የበጋና የክረምት መፈራረቅም አምላክ እንዳለ ማስረጃ ናቸው ። ፀሀይን በቀን ጨረቃን በማታ ያሰለጠነ ቀኑን ለሰራዊት ሌሊቱን ለአራዊት ያደረገ አምላክ መሆኑን እናውቅበታለን ።የስነ ፍጥረት አይነቱ ብዛቱ ድንቅ ነው ። 1ፀሀይ ሆና ለአለም ሁሉ እንድታበራ ማን አደረጋት ? የዛፎቹ አይነት አንዳንዱ ቅጠሉ ሰፊ አንዳንዱ ቅጠሉ ቀጭን ፣ የአእዋፏቱ አይነት ፣ የአሶችና የሌሎች ባህር ውስጥ ያሉ ነብሳት መኖር ፣ ስናይ ፈጣሪ እንዳለ እንረዳበታለን ። ለውቅያኖሶች ዳርቻዎቻቸውን የወሰነላቸው ሰማይን በከዋክብት ምድርን በአበቦች ያስጌጠ ስራው ድንቅ የሆነ አምላክ የመኖሩ ማስረጃ ናቸው ። ሸክላና ተሽከርካሪ ፣ መርከብና አየር በራሪ ፣ ድልድይና አስፓልት ፣ መኪናና ሌሎችም ሞተር ነክ ነገሮች ፣ ታሪካውያን ህንፆዎች ፣ የሚያስገርሙ ነገሮች ሁሉ ያለ ሰሪ ፣ አትክልትና አዝርዕት ያለ መሬትና ያለ ዘሪ ፣ ልጅ ያለ እናትና አባት እንደማይገኝ ሁሉ ግዑዛንና ግዙፉን ጥቃቅንና ረቂቃን ፍጥረት ሁሉ ያለ ፈጣሪ እንዳልተገኙ እናምናለን ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚታየው ከማይታየው እንደሆነ እናምናለን" እንጂ ዳዊት በመዝሙር 13:1 "ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል" እንዳለው አምላክ የለም አንልም
https://t.me/yeberhanljoche
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ገዳማዊ "ቅዱስ አባ ባውላ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ አባ ባውላ መስተጋድል +"+

=>ቅዱሱን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::

+ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ2 አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን (ኃጣውዕን) ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::

+በተለይ 2ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: ታላቁ አባ ባውላ ገዳማዊ ጻድቅ እንደ መሆኑ ትግሉ የነበረው ከአጋንንት ጋር ነው:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::

+ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ (ቀዝቃዛ) በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::

+ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::

+ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታ "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" (ማቴ. 16:24) እንዳለው: ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::

+ታላቁ አባ ባውላ የተወለደው በላይኛው ግብጽ አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከክርስቲያን ወላጆቹ መንፈሳዊ ነገሮችን ተምሮ በወጣትነቱ መንኗል:: ያ ዘመን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን የነበሩበት ነውና ወደ ጠመው አካባቢ ሔዶ ምናኔን ተምሯል::

+ሥርዓተ ገዳምን ማለትም:- አገልግሎትን: ፍቅርን: ተጋድሎንና የመሳሰሉትን ከተማረ በሁዋላም ደቀ መዝሙሩን አባ ሕዝቅኤልን አስከትሎ ለዋናው የተጋድሎ ሕይወት ወደ በርሃ ወጣ:: አባ ባውላ ዘወትር በፍቅረ ክርስቶስ ይመሰጥ ነበርና የተጋድሎ ምርጫው ልዩ ሆነ::

+አንድ ቀንም እንዲህ ሲል አሰበ:- "ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ለኃጥአን ኃፍረተ መስቀልን ታግሠህ: ሞትን ከሞትክልን እኛ ደግሞ ስለ ንጹሑ አምላክ ስንል እልፍ ሞትን መታገስ አለብን::"

+ይህንን ብሎ ከወትሮው በተለየ መንገድ ሊጋደል ጀመረ:: በዚህ እጅግ የጸና ተጋድሎው ምክንያትም 7 ጊዜ ሙቶ 7 ጊዜ ተነሳ::

1.እግሩን ከረዥም ዛፍ ላይ አስሮ: ወደ ታች ተዘቅዝቆ ይጸልይ ጀመረ:: እህልም: እንቅልፍም: ዕረፍትም አልነበረውምና ደሙ በአፍ: በአፍንጫው ፈሶ አለቀ:: እንዲህ በሆነ በ40ኛው ቀንም ሞተ:: መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ ከሞት አስነሳው::

2.ጥልቅ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ እንዳስለመደ ይጸልይ ጀመረ:: ከባሕሩ ሳይወጣ: ከቆመ ሳያርፍ: ከዘረጋም ሳያጥፍ ለ40 ቀናት ጸለየ:: በዚያው ሳለም ለ2ኛ ጊዜ ሞተ:: ቅዱስ መልአክ መጥቶ ከሞት አስነሳው::

3.እርሱ በሚኖርበት ጠመው አካባቢ ረዥም ተራራ ነበርና ወደዚያ ወጣ:: ከተራራው ጫፍ ሆኖ ወደ ታች ተመለከተ:: የተጠራረቡ ድንጋዮች በየመንገዱ ተሰልፈው ነበር:: በዚያች ቅጽበት የጌታ ኅማማት ከፊቱ ቢደቀንበት ከላይ ወደ ታች ተወርውሮ ሔደ::
በየመንገዱ ያሉት ጥርብ ድንጋዮች ቢቀበሉት አካሉ እየተነተፈና እየተቆራረጠ በየመንገዱ ቀረ:: በዚህም ሞተ:: አሁንም ፈጣሪው ከሞት አስነሳው::

4.አንድ ቀን ደግሞ (ዕለቱ ዓርብ ነበር) የጌታን ኅማማት እያሰበ የሚያደርገው ጠፋው:: ከቆመበት አካባቢ ትልቅ ዛፍ ነበርና ወደዚያ ወጥቶ ሲመለከት ከመሬት ላይ የተነጠፈ ትልቅ ድንጋይ አየ:: ከላይ ወደ ታች ሲወድቅና ድንጋዩ ላይ ሲያርፍ ለሁለት ተከፍሎ ሞተ:: አሁንም በፈጣሪ ትዕዛዝ ተነሳ::

5.በሌላ ቀን ደግሞ በዕለተ ዓርብ ጭንቅላቱን ከእግሩ ጋር አሥሮ ይጸልይ ገባ:: ያለ ምንም እህል: ውሃና እንቅልፍ ለ40 ቀናት ቆይቶ ሞተ:: እንደገናም ተነሳ::

6.እጅግ ሊመለከቱት እንኩዋ በሚከብድ የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ገብቶ ለ40 ቀናት እጆቹን ዘርግቶ ቢጸልይ ከጭንቁ ብዛት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች::

7.አንድ ቀንም እንደዚሁ የጌታን ሕማማት እያሰበ ወደ ጽኑ ቆላ ወረደ:: በአካባቢው ከአሸዋ በቀር ምንም አልነበረምና ቆሞ ሲጸልይ አሸዋው ውጦ ደፈነውና ለ7ኛ ጊዜ ሞተ:: በዚህ ጊዜ ግን ሊያስነሳው የመጣው እንደ ወትሮው ቅዱስ መልአክ ሳይሆን ራሱ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ ነበር::

+ጌታችን አባ ባውላን ከሞተበት አስነስቶ:- "ወዳጄ ባውላ! ስለ እኔ ፍቅር እጅግ ተሰቃየህ" አለው:: ቅዱሱ ግን "ጌታየ ሆይ! የእኔ መከራ በአንተ መከራ ሲታሰብ ኢምንት ነውና እባክህ ስለ ስምህ ሌሎች መከራዎችን እንድቀበል ፍቀድልኝ? ገና ሕማምህን አስቤ አልረካሁምና" አለው::

+ጌታ ግን "የለም! መከራው ይበቃሃል:: መጥቼ እስክወስድህ ድረስ ከአባ ብሶይ ጋር ቆይ" ብሎት: ባርኮት ዐረገ:: አባ ባውላም እንደ ታዘዘው በአባ ብሶይ ገዳም ከቅዱስ ብሶይ ጋር ቆይቶ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+ይህቺውም ዕረፍቱ ለ8ኛ ጊዜ ሆና ተቆጥራለች:: የቅዱሱን ዜና የጻፈው ደቀ መዝሙሩ አባ ሕዝቅኤል ሲሆን ያሰፈረው እንባው እንደ ዥረት እየወረደ ነው:: አባቶቻችን ሊቃውንትስ ታላቁን ጻድቅ ሲያመሰግኑት እንዲህ አይደለምን!
"ውስተ ገድል ጽኑዕ ዘአልቦ ምምዐ:
ወደቀ ስብአ: ወተንሳእከ ስብአ::"

=>አምላከ አባ ባውላ በጻድቁ ላይ ያሳደረውን ፍቅሩን ያሳድርብን:: ከበረከቱም ያድለን::

=>ጥቅምት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ባውላ መስተጋድል
2.አባ ሕዝቅኤል ጻድቅ
3.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ሐናሲ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ: ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? +"+ (ማቴ. 16:24)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/yeberhanljoche
.💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

#ኪዳነ ምህረት

ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡

ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡

እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡

ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ስም ቀል እገባልሻለው ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል።

በዚህም የተነሳ እመቤታችን እኛን በምልጃዋ የምታስምርበተ ፣ ጥያቄያችንን የምታስመልስበት ፣ እንቆቅልሻችንን የምታስፈታበት የምህረት ኪዳን የካቲት 16 ተቀብላለች እና ኪዳነ ምህረት እንላታለን ።


💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛https://t.me/yeberhanljoche
💠 #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። 💠

✧ በወንጌልም ሆነ በተለያዩ የሀዲስ ኪዳን የመልእክት ክፍሎች ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ተጠቅሶ ይገኛል። እንደውም ማንኛውም ክርስቲያን፥ ኢየሱስ እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ማመን መቀበል እንዳለበት አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

✧ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቂሳርያ ሀዋርያቱን ሰብስቦ ሰዎች ማን እንደሚሉት በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች ኤልያስ ከነብያት አንዱ እንደሆነ እንደሚናገሩ ሲነግሩት እናንተ ማን እንደሆንኩ ትላላችሁ ብሎ ቢጠይቃቸው ክርስቶስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ ተናግሯል ጌታችንም ቅዱስ ጴጥሮስን አመስግኖ ስጋና ደም እንዳልገለጠለት የሰማዩ አባቱ እንደገለጠለት በመናገር በዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር ቤተክርስቲያኑን እንደሚመሰርት ጌታ ተናግሯል ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለው የቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር የቤተክርስቲያን መሰረት ነው። የጌታን ማንነት የሚገልጽ እምነታችን መሰረት ነው፡፡

✧ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የማያምን እንዲሁም ብሎ የማይመሰክር ሰው ክርስቲያን ተብሎ ሊጠራ አይችልም ምክንያቱም የክርስትና መሰረት ይህ ስለሆነ ‹‹ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። እርሱም፦ አንዳንዱ #መጥምቁ_ዮሐንስ ፥ ሌሎችም #ኤልያስ ፥ ሌሎችም #ኤርምያስ ወይም #ከነቢያት_አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
እርሱም፦ #እናንተስ #እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ #አንተ #ክርስቶስ_የሕያው_እግዚአብሔር_ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ #በሰማያት ያለው #አባቴ እንጂ #ሥጋና #ደም ይህን #አልገለጠልህምና #ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።››ማቴ 16፡13-19

ቅዱስ ገብርኤልም እመቤታችንን ለማብሰር በተላከ ጊዜ ከእርሷ የሚወለደው <<ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ>> እንደሚባል ነግሯታል እሷም ይህንን በእምነት ተቀብላ ስግው ቃል/ሰው የሆነ አምላክ/ እግዚአብሄርን በስጋ ወልዳዋለች ስለዚህም ወላዲተ አምላክ ብለን እንጠራታለን፡፡ የሉቃስ ወንጌል 1፡35 ‹‹መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።››

✧ በተለያየም ቦታ አጋንንት እኳን ሳይቀሩ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መስክረዋል፡፡ ማቴ 8፡29 አይሁድም የእምነታችን መሰረት የሆነውን የእግዚአብሔር ልጅነቱን አልተቀበሉም ነበር፡፡ማቴ 26፡63 ይዘብቱበትም ነበር ማቴ 27፡43 ፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ወንጌሉን ሲጀምር እግዚአብሔር ልጅነቱን መስክሮ ነው ማር1፡1፡፡ በተለያየ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ክፍል ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ተጠቅሷል ይህንንም እናመን ዘንድ ወንጌል እንደተፃፈ ይነግረናል ዮሐ 1፡34 ፤1፡50 ፤6፡69 ፤ 10፡36 ፤11፡4 ፤11፡27 ፤ 19፡7 ፤ 20፡31፡፡

✧ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ይህንን አምኖ እንደተጠመቀ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ሐዋ 8፡37፡፡ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱም ኢሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ተናግሯል ‹‹ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።››1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡15፡፡

እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው መጽሀፍቅዱስ አፅንኦት ሰጥቶ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በእግዚአብሔር ልጅነቱም ማመን እንዳለብን ይናገራል...

??? ለመሆኑ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ሲባል ምን ማለት ነው ???

✧ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ሲባል መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። እኛ የሰው ልጆች ሰዎች እንደምንባል ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስም እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ሲባል አብን በመልክ የሚመስለው በባህሪ የሚስተካከለው ማለታችን ነው ዮሐ 1፡1-3 ፤ ዮሐ 10 ፡30 ፤ዮሐ 14፡8-10 ‹‹እኔና አብ አንድ ነን እኔን ያየ አብን አይቷል››፡፡ ልጅነቱም የባህሪ ልጅነት ነው ማለትም ከማንም ያልተቀበለው ማንም የማይወስድበት ዘላለማዊ ልጅነት ነው፡፡

✧ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ልጅ እንደሆነ ከአብ ጋር አንድ እንደሆነ እና አብ የሚያደርገውን ሁሉ እንደሚያደርግ ለአይሁድ ሲነግራቸው ድንጋይ አንስተው ሊወግሩት በማሰባቸው ጌታችን ስለምን ትወግሩኛላቻሁ ባላቸው ጊዜ ስለመልካም ስራህ አንወግርህም ስለስድብህ ነው ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለማድረግህ ነው ማለታቸው በወንጌል ተመዝግቧል እንግዲህ አይሁድ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ አምላክ ነኝ ማለቱ እንደሆነ ገብቷቸዋል ማለት ነው ዮሐ 10፡25-38

✧ ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው ጌታችን ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ መጥራቱ አምላክ ነኝ ማለቱ እንደሆነ ነው/ ሙሉውን የአይሁድ እና የጌታን ንግግር አንብቡት/፡፡በሌላም ቦታ አይሁድ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሎ ራሱን መጥራቱን ተቃውመው ሊገሉት እንደነበር የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ ማለቱ ደግሞ እግዚአብሔር ነኝ ማለቱ እንደሆነ ተረድተውት ሊገሉት እንደሚፈልጉ ተገልጧል ‹‹እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ <<
እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።››ዮሐ 5፡18

✧ ስናጠቃልለው ኢየሱስ እግዚአብሔር ልጅ ተብሎ መጠራቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተመለከትነው አምላክ/እግዚአብሔር መሆኑን የሚገልጥልን ልጅነቱም ከማንም ያልተቀበለው ባህሪ ልጅነት እንደሆነ እግዚአብሄርንም የሚስተካከልበት ልጅነት በመልክ ሚመስልበት ልጅነት እንደሆነ ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሰላም የተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ🙏

ከዛሬ ጀምሮ በአዲሱ ቻናላችን ስለ ሰ/ት/ቤቱ መረጃዎች እንዲሁም ስለተዋህዶ ሀይማኖት እየፃፍን እናቀርባለን።
ጎደኛዎትን ለመጋበዝ ከፈለጉ ከታች የለዉን ሰማያዊ ሊንክ ሼር በማድረግ አባልነቶን ያሳዩን።

@yeberhanljoche @yeberhanljoche
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
ስማኝ ልጄ!!!!!!!

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!

@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
እንኩዋን ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት

=>ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

+ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

+በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

+ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

+"+ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ +"+

=>ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን እንደ ረዳው ታስተምራለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 5 ላይ እንደ ተጻፈው ቅዱሱ መልአክ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: እሥራኤልን በምድረ በዳ የመራ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሲያርፍ ታላቅ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር::

+እግዚአብሔር ግን ኢያሱን አስነስቶ አረጋግቷቸዋል:: ቅዱስ ሚካኤል 40ውን ዘመን እሥራኤልን ደመና ጋርዶ: መና አውርዶ: ክንፉን ዘርግቶ: ጠላትን መክቶ ከሙሴ ጋ እንደ መራቸው ከኢያሱ ጋርም ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወረደ::

+በኢያሪኮ አካባቢም የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በግርማ ለኢያሱ ታየው:: ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ "አንተ ከእኛ ወገን ነህን? ወይስ ከጠላቶቻችን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ ሚካኤልም መልሶ "እረዳህ ዘንድ እነሆ የሠራዊት አለቃ ሆኜ ተሹሜ መጥተቻለሁ" አለው::

+ያን ጊዜ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰገደለት:: ቅዱሱ መልአክም አክሎ "ፍታሕ ቶታነ አሳዕኒከ እም እገሪከ: እስመ ምድር እንተ ትከይዳ ቅድስት ይዕቲ - የረገጥካት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ" አለው::

+ኢያሱም የተባለውን አደረገ:: ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን "ለመላእክት የጸጋ (የአክብሮ) ስግደት ይገባል: በቅዱሳኑ ፊትም ጫማ ተለብሶ አይቆምም" የምትለው:: ያ መሬት ሊቀ መላእክት ቢቆምበት ተቀድሷል:: ዛሬም ቤቱ በታነጸበት: ታቦቱ በተቀረጸበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱ መልአክ አለና ጫማን አውልቆ: ባጭሩ ታጥቆ መግባት ይገባል::

+ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከኢያሱ ጋር ሆኖ አማሌቅን ጨምሮ የእሥራኤልን ጠላት አጥፍቷል:: ጥቅመ ኢያሪኮን (ቅጥሩን) አፍርሷል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: በገባኦን ፀሐይን: በቆላተ ኤሎምም ጨረቃን ሲያቆም ከእርሱ ጋር ሆኖ ረድቶታል::

+"+ ዱራታኦስና ቴዎብስታ +"+

=>ቅዱሳኑ ዱራታኦስ (ዶርታኦስ) እና ቴዎብስታ (ቴዎብስትያ) የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ:: በድርሳነ ሚካኤልና በመጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ እንደምናገኘው 2ቱ ቅዱሳን በተቀደሰ ትዳር ተወስነው: ሕጉን ትዕዛዙን ፈጽመው: ለነዳያን ራርተው: ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ ነበሩ::

+ይልቁኑ ግን የጌታችን: የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያለማስታጐል ያደርጉ ነበር:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ሐብት ንብረታቸው አልቆ ተቸገሩ:: ግን የጨነቃቸው መቸገራቸው ሳይሆን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ሊያቆሙ መሆናቸው ነው::

+አማራጭ ሲያጡ ተቀምጠው ተመካከሩ:: የቅዱሱ መልአክ ዝክር ከሚቀር ልብሳቸውን (ያውም የክብር ልብሳቸውን) ሊሸጡ ተስማሙ:: በዚህ መሰረት ቅዱስ ዱራታኦስ ወደ ገበያ ሲሔድ ወዳጁ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወረደለት::

+መንገድ ላይም የጦር መኮንን ሃገረ ገዢ መስሎ ተገናኝቶ አጫወተው:: ችግሩን ጠይቆም መፍትሔውን ነገረው:: "እኔ እዋስሃለሁና ለበዓል የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሁሉ ገዝተህ አሰናዳ" አለው::

+"እኔ ወደ ቤትህ መጥቼ ስለምስተናገድ አንድ አሣ አምጥተህ አቆየኝ:: እኔ ሳልመጣ ግን አትረደው" አለው:: ቅዱስ ዱራታኦስ የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ ወደ ቤቱ ሲሔድ ድንቅ ነገርን ተመለከተ:: ሚስቱ ቅድስት ቴዎብስታ በቤቱ መካከል ሁና ቤቱ በበረከት ሞልቷል::

+ማሩ: ቅቤው: እሕሉ ሁሉ በየሥፍራው ሞልቷል:: ባልና ሚስቱ ደስ ብሏቸው:: ነዳያንን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ዋሉ:: በሁዋላ ያ መኮንን (ቅዱስ ሚካኤል) በቤታቸው መጥቶ ተስተናገደ::

+በእርሱ ትዕዛዝ የአሣው ራስ (ሆድ) ሲከፈት በውስጡ 300 ዲናር ወርቅ (እንቁ) ተገኘ:: ቅዱሳኑ ይህን ተመልክተው ሲደነግጡ ቅዱስ ሚካኤል ክንፉን ዘርግቶ ራሱን ገለጸላቸው:: ደንግጠው በግንባራቸው ተደፉ::

+እርሱ ግን "በተገኘው ሃብት እዳችሁን ክፈሉ:: ከዚህ በሁዋላ ግን በምድር አትቸገሩም:: በሰማይም ክፍላችሁ ከእኔ ጋር ነው" ብሎ ባርኩዋቸው ወደ ሰማይ ዐረገ:: እነርሱም በሐሴትና በበጐ ምግባር ኖረው ዐርፈዋል:: ለርስቱም በቅተዋል::

+"+ ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ +"+

=>የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::
*በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
*በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
*በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
*ምጽዋትን ያዘወተረ::
*አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

+"+ አፄ በእደ ማርያም +"+

=>"በዕደ ማርያም" ማለት "በማርያም እጅ" እንደ ማለት ነው:: እኒህ ሰው የኢትዮዽያ ንጉሥ ሲሆኑ የነገሡትም በ1460 ዓ/ም ነው:: ደጉ አባታቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሲያርፉ በመንግስቱ ተተክተው ሃገራችንን አስተዳድረዋል:: ድርሰት ደርሰዋል:: አብያተ መቃድስ አንጸዋል::

+በተለይ ለቅኔ ትምሕርት ማበብ ልዩ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይነገራል:: ልክ በነገሡ በ10 ዓመታቸው ግን መንግስተ ምድር በቃኝ ብለው በምናኔ በርሃ ገብተዋል:: በዙፋናቸውም አፄ እስክንድር ተተክተዋል:: ጻድቁ ንጉሥ ግን ቅዱስ ሚካኤልን ይወዱት ነበርና በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም አይለየን::

=>ኅዳር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ
3.ቅዱሳን ዱራታኦስና ቴዎብስታ
4.አፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
6.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
7.አባ ፊላታዎስ ሊቀ ዻዻሳት
@yeberhanljoche
ንነኳን ለሊቀ መላኩ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በአል አደረሳችሁ አደረሰን🙏🙏🙏