የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
14.1K subscribers
939 photos
204 videos
77 files
1.19K links
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |
Download Telegram
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሀገራችን የመጀመሪያ በሚባል መልኩ የተለያዩ ንጽጽር ነክ ስልጠናዎችን ለማካሔድ ስርአተ ትምህርትና እቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ።

የሚሽነሪውን እንቅስቃሴ በመግታት ደረጃ የራሳቸው አሻራ ያላቸውን እነዚህን ፕርጀክቶች ለማሳለጥ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል። እርሶም የዚህ መልካም ስራ ተቋዳሽ ይኾኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።

በሚከተሉት መገኛዎች ተቀላቅለውን ስራዎቻችንን ሊደግፉ ይችላሉ፦

በቴሌግራም፦
https://t.me/+5kfHxCCm0RRkYmI0

በዋትስአፕ
https://chat.whatsapp.com/LPgG6cIEA181mtu3AO6tvW
የዛውያ ቲቪ መስራችና የምንጊዜም የማዕከሉ አበረታች የሆነው ወንድማችን ሙሳ ኑረዲን 1,200 ብር ድጋፍ አድርጓል። አሏህ ይቀበልህ..!
...
1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር ቁጥር - 8212

በሚከተሉት መገኛዎች ተቀላቅለውን ስራዎቻችንን ሊደግፉ ይችላሉ፦

በቴሌግራም፦
https://t.me/+5kfHxCCm0RRkYmI0

በዋትስአፕ
https://chat.whatsapp.com/LPgG6cIEA181mtu3AO6tvW
አንድ ሰው ታመመ ሲባል በተለይም የድጋፍ ጥሪ በተፖሰተበት ቦታ እየመጣችሁ "ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ ይቀበል፣ ይፈወሳል" እያላችሁ ኮሜንት የምታደርጉ ጴንጤዎች የአእምሯችሁን የመቀንጨር ልክ እንድናየው ባታደርጉን ምናለበት..?! ስንቱን በህመም የሞተ ጴንጤ የማናውቅ ለምን እንደሚመስላችሁ አላውቅም። የፈውስ ድራማችሁን በተመለከተ እንኳን እኛን የራሳችሁንም ሰው ማሳመን ካቆመ ቆይቷልና አደራችሁን በየኮሜንቱ አትዘባበቱብን። ይልቅ እጅ መዘርጋት የወንጌላችሁ ቃል ነውና ለታመመው እርዱ፤ እሱ ከከበዳችሁ ደግሞ ዝምበሉ። ከሞንታርቦ የተረፈ ጆሯችንን እንዳናሳርፍ እዚህም እየመጣችሁ እጅ እጅ በሚል አስቀያሚ "ሰበካችሁ አይናችንን ደግሞ አታሳምሙት..!
___
https://t.me/Yahyanuhe
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #22

https://vm.tiktok.com/ZM6gWUqT5/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጋዛ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በቃል መግለጽ አይቻልም ሲሉ የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእንባ ጋር እየታገሉ ገልጸውታል 💔

___
https://t.me/Yahyanuhe
አዲስ የኦንላይን ኮርስ

ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታልን?/A Critical Review of the authorship theories/

"ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታል" በሚል ሙስሊም ባልሆኑ ወገኖች የሚነሱ መላምቶችን የሚዳስስና የሚሞግት አዲስና በይዘትም አጭር የሆነ ኮርስ ሲሆን ፍላጎት ያለው ሰው መመዝገብና ኮርሱን መውሰድ ይችላል።

በኮርሱ የሚዳሰሱ መላምቶች፦

1/ ቁሳዊ ከበርቴነትን ለማግኘት ጽፈውታል/Material gain as motive

2/ ለስልጣንና ለክብር ሲሉ ጽፈውታል/Desire for power and glory/

3/ ከአይሁድና ከክርስትና ምንጮች ተጠቅመው ጽፈውታል/From Jews and Christian sources/

4/ ራዕይ የታያቸው መስሏቸው ሀሳባቸውን አቀናጅተው ጽፈወታል/The religious illusion theory/

5/ የቁርአንና የመጽሀፍ ቅዱስ መሠረታዊ ልዩነት/Major difference between the bible and the qur'an/

እነዚህን አስመልክቶ ማብራሪያዎችና ትንተናዎች የሚቀርቡበት ሲሆን በትምህርቱ መጨረሻ የሚሰጠውን ፈተና ተከታትለው ለሚወስዱ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቷል።

ስልጠናውን ለመከታተል፦
https://t.me/+cZu3KlAbhWYyODE8
አንዳንድ ነገሮች ሲያስደንቁኝ ዝም ከምል ማን እንደሚማርበት አላውቅምና ላካፍላችሁ፦

ከዛሬ አንድ ወር ገደማ በፊት በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትልቅ ሚሲዮናውያን/Missionary/ የማዘጋጀት ስልጠና ነበር። ይህ ስልጠና ከሌሎች ስልጠናዎች ትንሽ ለየት ያለ ነበር። ከዚህ በፊት የነበሩ ሚሽነሪዎች ሰልጥነው ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚላኩ ነበሩ። አሁን ግን ዘመኑን ያማከለ ሌላ ስልጠና ነበር ቤተ ክርስቲያኗ ለ125 ሰልጣኞች ያዘጋጀችው።

ይኸውም ሰልጣኞቹ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ተምረው ስራቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ በመስራት "ወንጌልን እንዲያገለግሉ" ነው የሰለጠኑት። ይህንን ሲሰሩም የሚያስፈልጓቸው ቴክኖሎጂዎች ተገዝተው በነጻ ተሰጥተዋቸዋል። የሚያስፈልጋቸው ስልጠናም በቸርቿ በኩል ቀርቦላቸው ሰልጥነዋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ሰልጥነውም ተመርቀዋል።

የቤተ ክርስቲያኒቷ ፕሬዝዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በማጠናቀቂያ መርሀ ግብራቸው ላይ እንዲህ ብሏቸዋል፦

"ወደ አለም ሂዱ የሚለውን ትዕዛዝ በአካል መንቀሳቀስ ሳይጠበቅ በእጃችን ባለ መሳሪያ መስራት ይቻላልና፣ ይህንን ለመስራት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላችኃለው"

الْكَلِمَةُ الْحِكْمَةُ ضَالَّةُ الْمُؤْمِنِ فَحَيْثُ وَجَدَهَا فَهُوَ أَحَقُّ بِهَا

___
https://t.me/Yahyanuhe
የሰባዎቹ ሽማግሌዎች ትንቢት

“ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመና ወርዶ ተናገረው፤ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አሳደረባቸው፤ መንፈሱ ባደረባቸውም ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን #አልደገሙትም።”
— ዘኍልቁ 11፥25 (አዲሱ መ.ት)

“እግዚአብሔር በደመናው ወረደ፥ ተናገረውም፥ በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አደረገ፤ መንፈሱም በላያቸው ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን #አልተናገሩም።”
— ዘኍልቁ 11፥25

በአማርኛው ሁለቱም እትሞች ላይ ሰባዎቹ ሽማግሌዎች መንፈሱ በላያቸው ላይ ባደረ ጊዜ ትንቢት መናገራቸውን ከዚያ በኃላ ግን አለመናገራቸውን ይገልጻል። ይህ ትርጉም ግን ከሌሎች ቋንቋ ትርጉሞች ጋር ይለያያል። ለአብነት የእንግሊዝኛውን የንጉስ ጀምስ ቅጅ ብንመለከት ሰባዎቹ ሽማግሌዎች ከዚያ በኃላ አለመናገራቸውን ሳይሆን ከዚያ በኃላ መናገር አለማቆማቸውን/መናገራቸውን/ የሚገልጽ ነው።

“And the LORD came down in a cloud, and spake unto him, and took of the spirit that was upon him, and gave it unto the seventy elders: and it came to pass, that, when the spirit rested upon them, they prophesied, and #did #not #cease.”
— Numbers 11:25 (KJV)

ለዚህም ይመስላል የአዲሱ መደበኛ ትርጉም በህዳግ ማስታወሻው ላይ "ከዚያ በኃላ ትንቢት መናገራቸውን አላቆሙም የሚሉ አሉ" ሲል የገለጸው።

___
https://t.me/Yahyanuhe
ይህ መጽሀፍ ገበያ ላይ የለም አልቋል፣ ካለቀ በርካታ አመታትን አሳልፏል። የታተመ ሰሞን የተወሰኑ ኮፒዎች አንድ ወንድም ጋ እንዲያስቀምጥልኝ አድርጌ ነበሩ። በወቅቱ እንዲተባበረኝ አስቤ የነበረ ቢሆንም በአንድ ወቅት ገጠር ለተማሪዎች የተወሰነ ኮፒ በነጻ ከሰጠሁ በኃላ ግን የተረዳሁት ነገር መጽሀፉ ከመጽሀፍት ቤቶች ከመሸጥ በላይ በላይ ለመርከዝና ለዲን ተማሪዎች መሠጠት እንዳለበት ነበር። በዚህም ምክንያት የንጽጽር መጽሀፍ ሳይታገድ ጊዜ ጀምሮ መጽሀፍቶቹ ከገበያ ላይ ማለቃቸውን ባውቅም ወደ ገበያ አልወስድኳቸውም ነበር።
...
ከሰሞኑ ሁላችንም የምናውቃቸው አንድ ትልቅ ሼይኻችን መጽሀፉን በተለያዩ መርከዞች የንጽጽር ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ለመስጠት ፈልገውት ሲጠይቁኝ መጽሀፉ እንዳለኝ ነገርኳቸው። ግን ሙሉ የግዥ ወጭው ሸይኹ ጋር መሆኑ ምቾት ነሳኝ። ከመጽሀፉ ጥቂትነት አንጻር (190 ፍሬ ብቻ ነው) ብንተባበር በቀላሉ መሸፈን እንደምንችልና ከሳቸው አልፎ ለሌሎችም ተማሪዎች መበተን እንደሚቻል አመንኩ። እናም መጽሀፍቱን በአነስተኛ ዋጋም ቢሆን የሚገዛላቸው ከተገኘ ለሸይኹም በነጻ እንዲሁም የንጽጽር ፍላጎት ላላቸው ለመርከዝ ተማሪዎች በኔ በኩል መስጠት እጀምራለሁ፣ የአንዱ መጽሀፍ ዋጋ 100 ብር ብቻ ነው። በፍላጎቱ 1ም 2ም መጽሀፍ ስፖንሰር የሚያደርግ ሰው ሲገኝ የኒያውን ያክል መጽሀፍ ለመርከዝ ተማሪዎች ይደርስለታል። ሚሴንጀር ያልሰራላችሁ በቴሌግራም ማናገር ትችላላችሁ፦

t.me/yahyanuhe1
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #24

https://vm.tiktok.com/ZM6GqfSPy/
ዛውያ ቲቪና ሀሩን ሚዲያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ዛሬ በይፋ አሳውቀዋል። ይህ የአንድነትን ጉልበት የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ነው። የሁለቱንም ሚዲያ ወንድሞች በቅርበት አውቃቸዋለሁ። ለዲን መልፋትና ቀናነትን የተሸለሙ ትጉህ ሰራተኞች ናቸው። አሏህ ﷻ ይገዛችሁ፣ የተሻለ ዲኑን በህብረት የምትኻድሙም ያድርጋችሁ።
የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች #2

ቪዲዮ መመልከት ለሚሻላችሁ፣ በቴሌግራም በጹሁፍ የማቀርበው ትምህርት እንደሚከተለው በቪዲዮም ይዘጋጃልና መርጣችሁ መመልከት ትችላላችሁ። ይህኛው በመጽሀፍ ቅዱስ የጹሁፍ ልዩነቶች/Textual variant/ ዙሪያ እየተሰራ ያለ አዲስ ተከታታይ ጹሁፍ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ነው። የመጀመሪያውን ቲክቶክ ላይ ታገኙታላችሁ፣ ፕሮግራሙም የሚቀጥል ይሆናል።
..
ለማታውቁ - የጹሁፍ ልዩነት/Textual Variant/ ማለት በመጽሀፍ ቅዱስ የመገልበጥ/Copy/፣ የመተርጎም/Translation/ ስራዎች ውስጥ የተፈጠሩ ልወጣዎችን/ብርዘቶችን/ የሚገልጽ ዘርፍ ሲሆን መጽሀፍ ቅዱስ በዚህ በኩል ያሉበት ክፍተቶች የትየለሌ ናቸው። ይህ ዘርፍ ቁርአን የነገረንን የመበረዝ ሂደት ፍንትው አድርጎ ከምንጩ የሚያሳይ በቂ አስረጅ ከመሆኑ ጋር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችን ይሆናል፣ ኢንሻላህ..!


https://vm.tiktok.com/ZM6th8sxd/
“..ቁርዓን ታሪክንም ህግንም ይዟል። በታሪኮች እየተደመሙ ህጉን የሚዘነጉ ሰዎች መርሳት የሌለባቸው ነገር ታሪኩ የሚያወራው ህጉን ስለዘነጉ ሰዎች እንደነበር ነው.."
የላሜሕ እድሜ

“ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ ሞተም።”
— ዘፍጥረት 5፥31

ይህንን የሚለው የ1954ቱ ትርጉም ሲሆን በዚህ እትም የኖረበት ዘመን 747 እንደሆነ ተገልጿል። የአዲሱ መደበኛ እትምን ስንመለከት ደግሞ የሚከተለውን እናገኛለን፦

“ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።”
— ዘፍጥረት 5፥31 (አዲሱ መ.ት)

በዚህኛው ትርጉም ደግሞ የላሜሕ እድሜ 777 እንደነበር ተገልጿል። ልዩነቱ በሁለት ብቻ አያበቃም። ከዚህ በታች አንቀጹ ላይ ያሉ ተጨማሪ ልዩነቶችን በተጨማሪ ቋንቋዎች እንመልከት፦

1/ በተለምዶ LXX ተብሎ የሚጠራው ሰብቱዋጀንት ወይንም የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም እድሜውን 753 አድርጎ የሚገልጸው ሲሆን ይህኛው ቁጥር ሌላ የተለየ ተጨማሪ ቁጥር ነው። የኢት/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ባሳተመችው የ2000 ትርጉም ላይ የሰብአ ሊቃናት ትርጉም 753 እንደሚል በህዳጉ አስቀምጣለች።

2/ በተለምዶ MT የሚባለው የማሶሬቲክ ወይንም የዕብራይስጡ ጹሁፍ ደግሞ 777 አድርጎ የሚገልጸው ሲሆን የአማርኛው አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተርጓሚዎችና አብዛኛው የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ይህንን መጠቀማቸውን መረዳት እንችላለን።

3/ የሳማሪታን አይሁዶች ተውራህ/ቶራ/ የሆነውና በምህጻረ ቃል ST ተብሎ የሚጠራው ትርጉም ደግሞ እድሜውን 653 አድርጎ ይገልጸዋል።

4/ አራተኛውና የመጨረሻው የትርጉም ገለጻ ደግሞ የ1954ቱ የአማርኛ ትርጉምን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተጠቀሙት 747 አመት የሚለው ትርጉም ሲሆን ከላይ ካሉት ትርጉሞች የተለየና አዲስ ቁጥር ነው።

◾️ ማጠቃለያ

የላሜሕ እድሜን በተመለከተ አንድ ሰው መጽሀፍ ቅዱስን ተጠቅሞ እድሜውን መናገር ቢፈልግ በትክክል መናገር አይችልም። በክርስትናው እምነት ውስጥ የትርጉም ምንጭ ተደርገው የሚታመኑ ጥንታዊ ጹሁፎች እንኳን እድሜውን በተመለከተ እርግጠኛ ቁጥር የላቸውም። አንዳንድ ሰው "ቁጥር ስለሆነ ጠቃሚ ነገር የለውምና ቢለያይም ችግር የለውም" የሚል ሀሳብ ሊያነሳ ይችላል። እንደዛ ከሆነ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥም መሠል ነገር መቀመጡ አስፈላጊ አይደለምና የመቆየቱ ነገር ላይ አብራችሁ አስቡበት። የማይጠቅም ስህተት "ቅዱስ" የሚባል መጽሀፍ ውስጥ አለ ብሎ መሟገት በፈጣሪ ክብር ላይ መዘባበት ነው።
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ለጉዳይ ስንንቀሳቀስ ከሚያስቸግሩን ነገሮች ውስጥ አንዱ መስጅድ ያለበትን ቦታ በቀላሉ አለማወቃችን ነው። ይህንን ችግር የሚፈታና በቀላሉ የትም አካባቢ ያሉ መስጅዶችን በቴሌግራም በኩል በቀላሉ የምታገኙበትን ቻናል ልጠቁማችሁ
...
ያላችሁበትን አካባቢ ስሙን ብቻ ሰርች ማድረጊያው ላይ በመጻፍ ለናንተ ቅርብ የሆነውን መስጅድ ከነጎግል ማፕ አድራሻው የምታገኙበት የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በሀገራችን ያሉ መስጅዶችን በዝርዝር እየተጨመሩበት ይቀጥላል። ለአብነት ጀሞ አካባቢ ብትሆኑና አቅራቢያችሁ ያለ መስጅድ ብትፈልጉ በቀላሉ ሰርች ማድረጊያው ላይ "ጀሞ" ብላችሁ መጻፍ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ። ከሚመጣላችሁ ዝርዝር ውስጥ ማፑን በመመልከት የሚቀርባችሁ ጋር መስገድ ትችላላችሁ። ክፍለ ሀገርም ቢሆን በተመሳሳይ ነው።

◾️ ከመስጅዶች በተጨማሪ የሙስሊም የቀብር ቦታዎችንም አካቷል።

ሼር በማድረግ በናንተ ምክንያት ሶላታቸውን ሳይቸገሩ በሰገዱ ሰዎች ልክ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ...!

https://t.me/ethiopianmosques
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #26

https://vm.tiktok.com/ZM6K5Eu6C/
የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች #4

https://vm.tiktok.com/ZM6oHsoAW/
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #27

https://vm.tiktok.com/ZMM1DKVhw/