የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
14.1K subscribers
939 photos
204 videos
77 files
1.19K links
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |
Download Telegram
አነጋጋሪው የቲቢ ጆሽዋ ዶክመንትሪና አስቀያሚ ህይወቱ
...
https://vm.tiktok.com/ZM6uwNWS2/
ማርያምን "የአብ ሙሽራ" ብሎ መጥራት ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?ጸሀፊው ምንስ መልዕክት በአአምሮው አስቦ ነው ይህንን ጹሁፍ የጻፈው?

___
https://t.me/Yahyanuhe
በስተመጨረሻም በጥራት የተሰራው ኦፍላይን አፕልኬሽን ተጠናቆ ይኸው ወደናንተ ደርሷል። አፕልኬሽኑ ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎችም ለአይፎን ተጠቃሚዎችም የተሰራ ነው። በንጽጽር ዙሪያ የተጻፉ ጹሁፎችን በዚህ ድረ ገጽ በፈለጉት ሰአት ያለ ኢንተርኔት ገብተው ማንበብ ይችላሉ። አዳዲስ ጹሁፎችም በአሏህ ﷻ ፍቃድ በተከታታይ ይጨመሩበታል። አፑን ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ፣ ለሰውም ሼር ያድርጉት፦

📌 ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.ridwan.hidaya

📌 ለአይፎን ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/hidaya-comparative/id6474642955
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በንጽጽር ትምህርት ዙሪያ የሚያገለግል አፕልኬሽን ለአንድሮይድና አይፎን ተጠቃሚዎች ማዘጋጀቱ ተገለጸ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 4/2016
...
በሚሽነሪው እንቅስቃሴ ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ የሚገኘው ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በንጽጽር ትምህርት ዙሪያ የሚያገለግል አፕልኬሽን ለአንድሮይድና አይፎን ተጠቃሚዎች ማዘጋጀቱን በትላንትናው እለት ማዕከሉ አስታውቋል።
...
አፕልኬሽኑ እስካሁን የተሰሩ የንጽጽር ስራዎችን ቀጥታ ከይፋዊ ድረ ገጻቸው በመውሰድ ተጠቃሚዎች ያለኢንተርኔት /ኦፍላይን/ እንዲያነቡ የሚያስችል ነው። አፕልኬሽኑን ማንኛውም ሰው ከፕለይስቶርና ከአፕ ስቶር ዳውንሎድ ማድረግ መጠቀም እንደሚችል የማዕከሉ መስራቾች ገልጸዋል።
...
For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.ridwan.hidaya

For Iphone: https://apps.apple.com/us/app/hidaya-comparative/id6474642955

የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን ከፈለጉ፦

https://bit.ly/4aGr93u

በቴሌግራም በኩል ሊያገኞቸው ከፈለጉ ደግሞ፦
@Hidayaislamiccenter

ተቋሙን መደገፍ ሲፈልጉም፦

1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212
...
© ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Nothing disgusts me more than hearing about justice from the West.
ዱንያ መልኳ ብዙ ነው፤ አፍጋኖች እንደሚሉት "ካገኘን ዶሮ እንበላለን፣ ካጣን ዶሮዋ የምትጥለውን እንበላለን፣ እሱንም ካጣን ዶሮዋ የምትበላውን እንበላለን" ይላሉ። በአሏህ ያላቸው መተማመን ከፍ ያለ ስለሆነ ነው መሠል ዶሮዋ የምትበላውን ጥራጥሬ ያሳጣናል ብለው ስላላሰቡ አባባሉን አልቀጠሉትም። የቀልብ ክብረት አያሳጣን..!
___
https://t.me/Yahyanuhe
ጸረ-ፍልስጤማዊ ሰባኪዎች በአረብያን ምድር..!
...
https://vm.tiktok.com/ZM6QxoVMG/
ሰዎች ያልፋሉ፣ ሲያልፉም - ይነስም ይብዛም፣ ይመርም ይክፋም አሻራቸውን ትተው ነው የሚያልፉት። አሏህ መልካም ዱካ ትተው ከሚያልፉት ያድርገን...!

وَاجْعَل لِّي لِسَانَ صِدْقٍ فِي الْآخِرِينَ

(ሱረቱ አልሹዐራ - 84)
በኋለኞቹም ሕዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ፡፡
አንዱ ወንጌላዊ ሰባኪ "እስራኤልን መደገፍ እንዳለብኝ ጌታ ተናግሮኛል" ሲል ሰማሁት። በወንጌላውያን ዘንድ "ጌታ ተናገረኝ" እንደሚለው ቃል መጫወቻ የሆነ ብሂል ያለ አይመስለኝም። ይህንን ፖስት ለመፖሰት እራሱ የነሱ ወገን ብሆን "ጌታ እንድፖስት ተናግሮኝ ነው" ማለት እችላለሁ። የወደቀብህን እስክርቢቶ ማንሳት እንዳለብህ ውስጥህ ቢነግርህም ጌታ እንደተናገረህ ማሳበብ ግን ትችላለህ።የውስጥህን መሻት ሁሉ በጌታ እያሳበብክ መፈጸምም፣ ማስፈጸምም ትችላለህ። ምሳ እንኳን ሲርብህ "ጌታ ብላ ብሎ ተናግሮኛል" ልትል ትችላለህ፣ በእውነታው ግን የተናገረህ ሆድህ እንጅ ጌታ አይደለም። እና አንድ ወንጌላዊ ጌታ ተናግሮኛል ሲል በቀላሉ "እንዲህ ማድረግ ፈልጌያለሁ" ብሎ እንደተናገረ ተረዱት...!
___
https://t.me/Yahyanuhe
በሚያስቅ ሁኔታ የትላንቱንም ፖስቴ ፌስቡክ ሰርዞታል 😄 ከቴሌግራም በተጨማሪ ቲክቶክ ቴክስት መጀመሩ ጠቀመን እንጅ በብስጭት ያስረጀን ነበር። በነዚህ በኩል ተወዳጁኝ፤ ለሌላውም ሰው ሼር አድርጉልኝ፣ በተለይም በፌስቡክ

ቲክቶክ፦
https://www.tiktok.com/@yahyaibnunuhe?_t=8j9pFCIutT4&_r=1

ቴሌግራም፦
https://t.me/Yahyanuhe
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሀገራችን የመጀመሪያ በሚባል መልኩ የተለያዩ ንጽጽር ነክ ስልጠናዎችን ለማካሔድ ስርአተ ትምህርትና እቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ።

የሚሽነሪውን እንቅስቃሴ በመግታት ደረጃ የራሳቸው አሻራ ያላቸውን እነዚህን ፕርጀክቶች ለማሳለጥ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል። እርሶም የዚህ መልካም ስራ ተቋዳሽ ይኾኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።

በሚከተሉት መገኛዎች ተቀላቅለውን ስራዎቻችንን ሊደግፉ ይችላሉ፦

በቴሌግራም፦
https://t.me/+5kfHxCCm0RRkYmI0

በዋትስአፕ
https://chat.whatsapp.com/LPgG6cIEA181mtu3AO6tvW
የዛውያ ቲቪ መስራችና የምንጊዜም የማዕከሉ አበረታች የሆነው ወንድማችን ሙሳ ኑረዲን 1,200 ብር ድጋፍ አድርጓል። አሏህ ይቀበልህ..!
...
1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር ቁጥር - 8212

በሚከተሉት መገኛዎች ተቀላቅለውን ስራዎቻችንን ሊደግፉ ይችላሉ፦

በቴሌግራም፦
https://t.me/+5kfHxCCm0RRkYmI0

በዋትስአፕ
https://chat.whatsapp.com/LPgG6cIEA181mtu3AO6tvW
አንድ ሰው ታመመ ሲባል በተለይም የድጋፍ ጥሪ በተፖሰተበት ቦታ እየመጣችሁ "ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ ይቀበል፣ ይፈወሳል" እያላችሁ ኮሜንት የምታደርጉ ጴንጤዎች የአእምሯችሁን የመቀንጨር ልክ እንድናየው ባታደርጉን ምናለበት..?! ስንቱን በህመም የሞተ ጴንጤ የማናውቅ ለምን እንደሚመስላችሁ አላውቅም። የፈውስ ድራማችሁን በተመለከተ እንኳን እኛን የራሳችሁንም ሰው ማሳመን ካቆመ ቆይቷልና አደራችሁን በየኮሜንቱ አትዘባበቱብን። ይልቅ እጅ መዘርጋት የወንጌላችሁ ቃል ነውና ለታመመው እርዱ፤ እሱ ከከበዳችሁ ደግሞ ዝምበሉ። ከሞንታርቦ የተረፈ ጆሯችንን እንዳናሳርፍ እዚህም እየመጣችሁ እጅ እጅ በሚል አስቀያሚ "ሰበካችሁ አይናችንን ደግሞ አታሳምሙት..!
___
https://t.me/Yahyanuhe
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #22

https://vm.tiktok.com/ZM6gWUqT5/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጋዛ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በቃል መግለጽ አይቻልም ሲሉ የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእንባ ጋር እየታገሉ ገልጸውታል 💔

___
https://t.me/Yahyanuhe
አዲስ የኦንላይን ኮርስ

ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታልን?/A Critical Review of the authorship theories/

"ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታል" በሚል ሙስሊም ባልሆኑ ወገኖች የሚነሱ መላምቶችን የሚዳስስና የሚሞግት አዲስና በይዘትም አጭር የሆነ ኮርስ ሲሆን ፍላጎት ያለው ሰው መመዝገብና ኮርሱን መውሰድ ይችላል።

በኮርሱ የሚዳሰሱ መላምቶች፦

1/ ቁሳዊ ከበርቴነትን ለማግኘት ጽፈውታል/Material gain as motive

2/ ለስልጣንና ለክብር ሲሉ ጽፈውታል/Desire for power and glory/

3/ ከአይሁድና ከክርስትና ምንጮች ተጠቅመው ጽፈውታል/From Jews and Christian sources/

4/ ራዕይ የታያቸው መስሏቸው ሀሳባቸውን አቀናጅተው ጽፈወታል/The religious illusion theory/

5/ የቁርአንና የመጽሀፍ ቅዱስ መሠረታዊ ልዩነት/Major difference between the bible and the qur'an/

እነዚህን አስመልክቶ ማብራሪያዎችና ትንተናዎች የሚቀርቡበት ሲሆን በትምህርቱ መጨረሻ የሚሰጠውን ፈተና ተከታትለው ለሚወስዱ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቷል።

ስልጠናውን ለመከታተል፦
https://t.me/+cZu3KlAbhWYyODE8
አንዳንድ ነገሮች ሲያስደንቁኝ ዝም ከምል ማን እንደሚማርበት አላውቅምና ላካፍላችሁ፦

ከዛሬ አንድ ወር ገደማ በፊት በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትልቅ ሚሲዮናውያን/Missionary/ የማዘጋጀት ስልጠና ነበር። ይህ ስልጠና ከሌሎች ስልጠናዎች ትንሽ ለየት ያለ ነበር። ከዚህ በፊት የነበሩ ሚሽነሪዎች ሰልጥነው ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚላኩ ነበሩ። አሁን ግን ዘመኑን ያማከለ ሌላ ስልጠና ነበር ቤተ ክርስቲያኗ ለ125 ሰልጣኞች ያዘጋጀችው።

ይኸውም ሰልጣኞቹ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ተምረው ስራቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ በመስራት "ወንጌልን እንዲያገለግሉ" ነው የሰለጠኑት። ይህንን ሲሰሩም የሚያስፈልጓቸው ቴክኖሎጂዎች ተገዝተው በነጻ ተሰጥተዋቸዋል። የሚያስፈልጋቸው ስልጠናም በቸርቿ በኩል ቀርቦላቸው ሰልጥነዋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ሰልጥነውም ተመርቀዋል።

የቤተ ክርስቲያኒቷ ፕሬዝዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በማጠናቀቂያ መርሀ ግብራቸው ላይ እንዲህ ብሏቸዋል፦

"ወደ አለም ሂዱ የሚለውን ትዕዛዝ በአካል መንቀሳቀስ ሳይጠበቅ በእጃችን ባለ መሳሪያ መስራት ይቻላልና፣ ይህንን ለመስራት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላችኃለው"

الْكَلِمَةُ الْحِكْمَةُ ضَالَّةُ الْمُؤْمِنِ فَحَيْثُ وَجَدَهَا فَهُوَ أَحَقُّ بِهَا

___
https://t.me/Yahyanuhe
የሰባዎቹ ሽማግሌዎች ትንቢት

“ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመና ወርዶ ተናገረው፤ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አሳደረባቸው፤ መንፈሱ ባደረባቸውም ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን #አልደገሙትም።”
— ዘኍልቁ 11፥25 (አዲሱ መ.ት)

“እግዚአብሔር በደመናው ወረደ፥ ተናገረውም፥ በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አደረገ፤ መንፈሱም በላያቸው ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን #አልተናገሩም።”
— ዘኍልቁ 11፥25

በአማርኛው ሁለቱም እትሞች ላይ ሰባዎቹ ሽማግሌዎች መንፈሱ በላያቸው ላይ ባደረ ጊዜ ትንቢት መናገራቸውን ከዚያ በኃላ ግን አለመናገራቸውን ይገልጻል። ይህ ትርጉም ግን ከሌሎች ቋንቋ ትርጉሞች ጋር ይለያያል። ለአብነት የእንግሊዝኛውን የንጉስ ጀምስ ቅጅ ብንመለከት ሰባዎቹ ሽማግሌዎች ከዚያ በኃላ አለመናገራቸውን ሳይሆን ከዚያ በኃላ መናገር አለማቆማቸውን/መናገራቸውን/ የሚገልጽ ነው።

“And the LORD came down in a cloud, and spake unto him, and took of the spirit that was upon him, and gave it unto the seventy elders: and it came to pass, that, when the spirit rested upon them, they prophesied, and #did #not #cease.”
— Numbers 11:25 (KJV)

ለዚህም ይመስላል የአዲሱ መደበኛ ትርጉም በህዳግ ማስታወሻው ላይ "ከዚያ በኃላ ትንቢት መናገራቸውን አላቆሙም የሚሉ አሉ" ሲል የገለጸው።

___
https://t.me/Yahyanuhe
ይህ መጽሀፍ ገበያ ላይ የለም አልቋል፣ ካለቀ በርካታ አመታትን አሳልፏል። የታተመ ሰሞን የተወሰኑ ኮፒዎች አንድ ወንድም ጋ እንዲያስቀምጥልኝ አድርጌ ነበሩ። በወቅቱ እንዲተባበረኝ አስቤ የነበረ ቢሆንም በአንድ ወቅት ገጠር ለተማሪዎች የተወሰነ ኮፒ በነጻ ከሰጠሁ በኃላ ግን የተረዳሁት ነገር መጽሀፉ ከመጽሀፍት ቤቶች ከመሸጥ በላይ በላይ ለመርከዝና ለዲን ተማሪዎች መሠጠት እንዳለበት ነበር። በዚህም ምክንያት የንጽጽር መጽሀፍ ሳይታገድ ጊዜ ጀምሮ መጽሀፍቶቹ ከገበያ ላይ ማለቃቸውን ባውቅም ወደ ገበያ አልወስድኳቸውም ነበር።
...
ከሰሞኑ ሁላችንም የምናውቃቸው አንድ ትልቅ ሼይኻችን መጽሀፉን በተለያዩ መርከዞች የንጽጽር ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ለመስጠት ፈልገውት ሲጠይቁኝ መጽሀፉ እንዳለኝ ነገርኳቸው። ግን ሙሉ የግዥ ወጭው ሸይኹ ጋር መሆኑ ምቾት ነሳኝ። ከመጽሀፉ ጥቂትነት አንጻር (190 ፍሬ ብቻ ነው) ብንተባበር በቀላሉ መሸፈን እንደምንችልና ከሳቸው አልፎ ለሌሎችም ተማሪዎች መበተን እንደሚቻል አመንኩ። እናም መጽሀፍቱን በአነስተኛ ዋጋም ቢሆን የሚገዛላቸው ከተገኘ ለሸይኹም በነጻ እንዲሁም የንጽጽር ፍላጎት ላላቸው ለመርከዝ ተማሪዎች በኔ በኩል መስጠት እጀምራለሁ፣ የአንዱ መጽሀፍ ዋጋ 100 ብር ብቻ ነው። በፍላጎቱ 1ም 2ም መጽሀፍ ስፖንሰር የሚያደርግ ሰው ሲገኝ የኒያውን ያክል መጽሀፍ ለመርከዝ ተማሪዎች ይደርስለታል። ሚሴንጀር ያልሰራላችሁ በቴሌግራም ማናገር ትችላላችሁ፦

t.me/yahyanuhe1
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #24

https://vm.tiktok.com/ZM6GqfSPy/
ዛውያ ቲቪና ሀሩን ሚዲያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ዛሬ በይፋ አሳውቀዋል። ይህ የአንድነትን ጉልበት የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ነው። የሁለቱንም ሚዲያ ወንድሞች በቅርበት አውቃቸዋለሁ። ለዲን መልፋትና ቀናነትን የተሸለሙ ትጉህ ሰራተኞች ናቸው። አሏህ ﷻ ይገዛችሁ፣ የተሻለ ዲኑን በህብረት የምትኻድሙም ያድርጋችሁ።