የሕያ ኢብኑ ኑህ - የንፅፅር ትምህርት መድረክ
14K members
381 photos
118 videos
67 files
638 links
የወንድም የሕያ ኢብኑ ኑህ የኦዲዬ፣ የቪዲዬና የፁሁፍ ትምህርቶቹ የሚሰባሰቡበት ቻናል ነው..!

ወንድም የሕያ ኢብኑ ኑህ በንፅፅር ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ ሁለት መፅሀፍቶችን ያዘጋጀ ሲሆን በተጨማሪም "ሚፖስ" የተሰኘ በአምላክ ህልውና ዙሪያ መረጃ የሚሰጥ መፅሀፍም አበርክቷል። ንፅፅራዊ መፅሀፍቱን አስመልክቶ የመጀመሪያው ስራው "ስቲሮት" የሚሰኝ ሲሆን ሁለተኛው "አልተሰቀለም" በሚል ታትሟል።
Download Telegram
to view and join the conversation
የዛሬ አመት ገዳማ አንድ ቪዲዮ በቴሌግራም ደረሰኝ። በወቅቱ ቪዲዮውን ሳየው በጣም ረበሸኝ። የቪዲዮው ይዘት በባቲ ከተማ የሚገኙ ረዳት አልባ የቲም ህፃናት እርዳታ ለመቀበል የወንጌላውያን ቸርች ውስጥ ተገኝተው እርዳታውን ከመስጠታቸው በፊት አዘጋጆቹ ዝማሬ እንዲያሰሙ ሲያደርጓቸው ነው። እነዚህ የሙስሊም ልጆች ስለሚሉት ነገር በቅጡ ላያውቁ ይችላሉ፤ ቢያውቁም የራባቸው ሚስኪኖች ናቸውና በሉ የተባሉትን ከማድረግ ወደኃላ አይሉም። እነዚህ ህፃናት በችግራቸው ምክንያት ዲናቸውን ሳያጡ በራሳቸው ወንድምና እህቶች መረዳት እየቻሉ ያለምርጫቸው ችግራቸውን ተጠቅመው ሌላ ተጨማሪ ፍላጎት ከነሱ ባላቸው ሰዎች እጅ ጣላቸው።

ይህንን ቪዲዮ እንዳየሁ ለተወሰኑ ሰዎች ላኩላቸው። ከላኩላቸው ሰዎች መካከል ጋዜጠኛ አብዱረሒም አህመድ አንዱ ነው። እልህና ቁጭት በተቀላቀለበት መንፈስ የዚያው ሰሞን ኢንተርቪው አድርጎኝ ጥሩ ፕሮግራም ሰራ። ከዚያ በዋናነት ለባቲው ወዳጄ Jemal Abdu ጉዳዩን አፅንኦት ሰጥቶ እንዲከታተለው ለምኘ ላኩለት። ጀማል ቪዲዮውን ሲያየው እንቅልፍ አጣ። ያለምንም የእምነት ልዩነት እርዳታን ብቻ መሠረት አድርጎ ተቋም ካቋቋሙ በኃላ የእምነት መጠቀሚያ ማድረጋቸው አበሳጨው። ለብዙ ጊዜያት ከለፋ በኃላ በመጨረሻ እምነትና ዘር ሳይለይ እርዳታን ብቻ ትኩረት ያደረገ "አቢዘር ማሕበረሰብ አቀፍ ልማት ድርጅት" የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት /NGO/ በባቲ ከተማ አቋቋመ።

ይህ ተቋም የፋይናንስ ችግር ያለበት ቢሆንም ጀማል የራሱን የኪራይ የሚያከራየውን ሱቅ በነፃ ቢሮ አድርጎ እሱ እየቀለጠ ከ100 በላይ ለሆኑ ህፃናት ሻማ መሆን ቻለ። ከሰሞኑ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ስራውን አስጎብኝቷል። ወንድሜ ጀማል በጥቂት ጊዜ ከቁጭት ባለፈ እንዴት ትልቅ ተቋም መሠራት እንዳለበት በትጋትና በልፋት አሳይቶናል። የጀማል መንገድ ቀላል አልነበረም፤ እኔ በቅርበት አቀዋለሁ። ግን ከምንም በላይ የየቲሞች ስቃይ ከኔ አይበልጥም ብሎ እዚህ አድርሶታል። ዛሬ ይህንን በህይወት ኑሬ በማየቴ አሏህን አመሰግነዋለሁ።
“ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።”
— ማቴዎስ 26፥39

ኢየሱስ እንዴት ፀለየ የሚለውን ጥያቄ ወደ ጎን እናድርገውና አንድ ሰው አምላክን "ቢቻል" ብሎ እንዴት ይጠይቃል? ያውም ስለ አምላክ ሀያልነት ጠንቅቆ ያውቃል ከሚባል ሰው በዚህ መልኩ "ፀሎት" ይጠበቃል? አምላክን "እባክህ አድርግልኝ" እንጅ "ከቻልክ አድርግልኝ" ይባላል?

T.me/yahya5
ሳኡድ አረቢያ ያላችሁ የኡስታዝ ኢሊያሕ ማሕሙድን መጽሐፍ መግዛት የምትፈልጉ

ሱመያ እና ኢክራም ኢስላማዊ መፅሀፍት እና አልባሳት ሱቅ በሳኡድ አረቢያ በሁሉም ከተማ እና ወደ ሀገርም እንልካለን።
ያናግሩ
👇👇👇👇👇
0509230683
0596497006
ኤልሳዕና ህፃናቱ
የሕያ ኢብኑ ኑህ
🔖 አንቀፁን በተመለከተ የተወሰነ የምልከታ ሀሳቦች

🎙 የሕያ አብኑ ኑህ

T.me/yahya5
ከሰሞኑ አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ አንዲት ጋዜጠኛ ማርያምን በተመለከተ የተናገረችው ንግግር ከሰሞኑ መነጋገሪያ ሁኖ ቆይቷል። ከዚያ ጋር በተያያዘ አንዲት ሌላ አማኝ ጋዜጠኛዋን አስመልክቶ የተናገረችው እርግማን እየተዘዋወረ ሲወገዝ ሳይ በአንድ ወቅት አይቸው የነበረ የቤተ ክርስቲያኗ የገድል መጽሀፍ ትዝ አለኝ። መጽሀፉ በአንዳንዶች ዘንድ ጠዋት ጠዋት የሚደገም መጽሀፍ ሲሆን በጠላት ላይ ላለ ጉዳይ ፍቱን እርግማን ተደርጎ ይወሰዳል።

ስለዚህ በአጭሩ ምን ልላችሁ ነው? የልጅቱ (የተራጋሚዋ) ጥፋት ሊታየኝ አልቻለም። ልጅቱ የተማረችውንና ሲደገም የሰማችውን ተናገረች፤ ሌላ ምን አደረገች?

T.me/yahya5
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወ በረከቱ
ውድ የመልሶቻችን ቻናል ተከታታዮች ሙስሊም እህት ወንድሞች እንዲሁም ከኢስላም ውጭ ያላችሁ ወገኖቻችን ሁላችሁንም ሰላም ብለናል

በመቀጠል ኢንሻአላህ
=============
በዚህ ቻናል የተለያዩ በከሃድያን ለሚነሱ ጥያቄዎች (ሹባሀዎች) መልስ እንሰጣለን
ቻናላችንን ሸር በማድረግ ለሁሉም አድርሱ


وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا

በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን (መልስ) መልካምን ፍችም የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ፡፡

https://t.me/Islamhasanswer
3ኛ ዙር የነሕው ደርስ

"አን-ነሕው" اَلنَّحْو ማለት "ሰዋስው"grammar" ማለት ሲሆን የቁርኣንን እና የጥንቱን የአነጋገር ዘይቤ በዐማርኛ እና በእንግሊዝኛ በተደገፈ መልኩ መማር የምትፈልጉ ሁሉ ቦታው ክፍት ነው። የነሕው ደርስ የቦርድ አባላት አራት ናቸው፥ እነርሱ፦
1. ወንድም ወሒድ የደርሱ ጦማሪ፣
2. እኅት ሐደል የደርሱ አቅራቢ፣
3. እኅት ሐናን የደርሱ ፈተና አርቃቂ
4. ወንድም መህዲ የደርሱ ፈታኝና ውጤት ክፍል ናቸው።

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!

ለመመዝገብ፦
እኅት ሐድልን፦ https://t.me/Ohanw9
እኅት ረምላን፦https://t.me/REMLANEG
አኅት ዘሃራን፦ https://t.me/zharamustefa
እኅት ሐቢባን፦ https://t.me/Mahbub_Abi
ወንድም መህዲን፦ https://t.me/Qelb_Seleem

በውስጥ ያናግሩ!
ምቹ እድል ለጀማሪ ፀሃፊዎች

ይወዳደሩ እስከ 50 ሺህ ብር ያሸንፉ

ተቋማችን የኢትዩጵያ ሙስሊሞች ዳዕዋ እና ትምህርት ተቋም (ኢሙዳት) ከተመሠረተባቸው አላማዎች መካከል የሀገራችን ህዝበ ሙስሊም ሀይማኖታዊ ትምህርቶችን እንዲያገኙ ማመቻቸት ፣ ማጠናከርና ማስተማር ይገኝበታል። በመሆኑም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ህብረተሰብ ተደራሸ የሚሆን መፅሃፍ ለማሳተም በሂደት ላይ ይገኛል። በዚህ ተግባር ላይ ፍላጎት ያላቹህ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኃል።

የመወዳደሪያ ርዕስ

◾️ የነብያት መልዕክት
◾️ የእስልምና ውበት
◾️ ሳይንስ እና እስልምና
◾️ የፈጣሪና የፍጥረቱ ቁርኝት

ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚኖርባቸው መስፈርት

◉ ከዚህ በፊት መፅሃፍ ያላሳተሙ መሆን አለባቸው

◉ የመወዳደሪያ እድሜ ከ18 ዐመት በላይ

◉ ጾታ - ወንድ እና ሴት (ሴቶች ይበረታታሉ)

◉ የመወዳደሪያ ቋንቋ ፦ አማርኛ

◉ በርዕሱ ለውድድር የሚሆን ከ25 ገፅ ያላነሰ ፁሁፍ አቅርቦ አሸናፊ ከሆነ ወደ 100 ገፅ ለማሳደግ ፍቃደኛ የሆነ

◉ አንድ ጸሃፊ ከአንድ በላይ ርዕስ መሳተፍ የተከለከለ ነው፡፡

◉ የተኮረጀ መሆን የለበትም፤ የሚጠቀማቸውን ፁሁፎች ምንጭ መግለፅ ይኖርበታል።

◉ ፁሁፍ የማስገቢያ ቀን የካቲት 15/2013 ጀምሮ እስከ የካቲት 30 2013 ባሉት የስራ ቀናት (መጋቢት 1 በኃላ የሚመጡ ፅሁፎች ተቀባይነት አይኖራቸውም)

ለበለጠ ማብራሪያ፦

ቤቶ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 101
ስልክ 0925 599999
የሰለምቴዎች ልዩ እና አተማሪ የሒዳያ ሰበብ የሆነው ታሪካቸውን ለማንበብ ለማድመጥ ከፈለጉ፦

ቴሌግራም ቻናል፦ በጹሑፍ ይቀርባል http://t.me/AshaBuleyamine

የፕሮግራሙ መገኛ ዩቱብ፦ ከአንደበታቸው ለማድመጥ
https://m.youtube.com/watch?v=ssov6TY3yzc&feature=youtu.be

እርሶዎም ሰለምቴ ከሆኑ ወደ የሰለምቴዎች ግሩፕ
ይቀላቀሉ
http://t.me/Selmeta
በገፅም በይዘትም ደጎስ ያለው የኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ የትርጉም መጽሀፍ በጥቂት ቀናት ውስጥ በአሏህ ﷻ ፍቃድ እጃችሁ ይገባል። የመውላና ዋሒዱዲን ኻን ስራ የሆነው ዘመን አይሽሬው "God Arises" መጽሀፍ በወንድማችን ኢልያህ ልቅም ተደርጎ ተተርጉሞል። መጽሀፉን በአረብኛና በእንግሊዝኛው ለምታቁት ሰዎች የስራውን ክብደት ለመረዳት አይቸግራችሁም። ለማንኛውም መጽሀፉ እነሆ በቅርቡ ህትመቱን አጠናቆ ወደናንተ ሊደርስ መንገዱን ጀምሯል።

https://t.me/Yahya5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህች ህፃን ልጅ አባቷ ቁርአን ሲቀራ አንዲት ኸርፍ እንኳን ሲስት እንዴት እንደምታስተካክለው ተመልከቱ..! ቁርዓን ለዘመናት ልቦና ውስጥ የተመዘገበው በዚህ መንገድ ነው። አይደለም በአዋቂዎች ልቦና ይቅርና በህፃናት ልብ ውስጥ እንኳን ፋናው ጥልቅ ነው..!

T.me/yahya5
በክርስትናው ዓለም በአፖሎጂቲክስ ዘርፍ ስማቸው ከገነኑ ሰዎች መካከል ራቪ ዘካሪያስ ተቀዳሚው ነው። በቅርቡ በካንሰር ከሞተ በኃላ እሱን አስመልክቶ ይወጡ የነበሩ የወሲብ ቅሌት ክሶች ለመስማትም የሚዘገንኑ ናቸው። ከአካዳሚክስ ፍራውዱ በተጨማሪ ሲንከባበለሉ የነበሩት የወሲብ ክሶቹ አሁን ላይ ወደመረጋገጥ በመድረሳቸው ታላላቅ ሰባኪ ወዳጆቹ ሳይቀር በግልፅ እያወገዙት ይገኛሉ። በስተመጨረሻም የካናዳ ቅርንጫፉ ሊዘጋ እንደሆነ ተሰምቷል። እንዲያ በክርስትናው ዓለም የገዘፈ ስብዕና የነበረው ሰው ሞቶ እንኳን ነውሩ መነጋገሪያ ሲሆን ማየት ያሳዝናል። አሁን ላይ ክርስቲያን ነን የሚሉ እስልምናን የሚተቹ አንዳንድ ሰዎችን ስነ ምግባር ስመለከት ራቪን በሌላ ስጋ አየዋለሁ። ምግባርህ ሳይስተካከል ምግባር ለማቃናት መድከም ነውርህ ከመግዘፉ በተጨማሪ ሌጋሲ እንኳን ሳይኖርህ ተራ ሰው አድርጎ ይገድልሀል። አሏህ ﷻ ከዚህ አይነት ውርደት ይሰውረን..!

t.me/yahya5
በአጭር ቋንቋ "መካንነቱ እንዲሻርልህ ገንዘብ ከፍለኸኝ ልፀልይልህ" እያሉ ነው 🤦‍♂️

T.me/yahya5
የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ቁጥር 21 የዲያቆን ዩሐንስ ታሪክ ክፍል አንድ እንሆ

ዲያቆን ዩሐንስ እንዴት ሰለመ ..!?

https://m.youtube.com/watch?v=zNrMrq6iP-A&feature=youtu.be

በቴሌግራም
http://t.me/AshaBuleyamine
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዛሬው ዕለት በአሶሳ ከተማ ሶስት ወገኖቻችን እስልምናን ተቀብለዋል። አልሐምዱሊላህ..!
_____

T.me/yahya5