Forwarded from Temari-Ethiopia
የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለፃል ?
#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ባገኘው መረጃ መሰረት የ12ኛ ክፍል የሁለተኛ ዙር ፈተና እርማት እየተጠናቀቀ ይገኛል።
እስከ የካቲት 15 ድረስ ዘገየ ቢባል እስከ የካቲት 20 ድረስ የውጤት ስራው ተጠናቆ ሊገለፅ እንደሚችል ሰምተናል።
ውጤት ከተገለፀ በኃላ በፍጥነት ወደ ምደባው እንደሚገባ የተገለፀልን ሲሆን በጣም ዘገየ ቢባል እስከ የካቲት 30 ድረስ ተማሪዎች ምደባቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ተብለናል።
ከምደባው በፊት ግን ቅሬታዎችን ቀድሞ ለመፍታት ይረዳ ዘንድ አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በፍጥነት እንዲያስገቡ ተጠይቋል።
#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርስዎ የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete

Forwarded from Crypto news
ለምዶበት ነው እንጂ-
ለምዶበት ነው እንጂ ጥርሴ የሚስቀው፡
የልቤን መከፋት እኔው ነኝ የማውቀው፡
የራሴን በሽታ ላስታም ብዬ ራሴ፡
ለሰው ሳላወጋው ሸሽጌው በጥርሴ፡
፡
፡
በሳቄ መለያ ስቃይ እያጫወትኩ፡
የውስጤን ጫጫታ ራሴው እያዳመጥኩ፡
አለሁኝ እስካሁን ለይምሰል እየሳኩ፡
፡
፡
የደበነው ውስጤ በበደል ያረረው፡
ጠባሳ የሞላው ጊዜ የማይሽረው፡
ያለኔ ማን አውቆት የልቤን ስብራት፡
ፈገግታዬ እንጂ ስሜቴ ማ ገብቶት፡
መደሰቴን እንጂ ማንባቴን ማን አይቶት፡
፡
፡
በይምሰል ፈገግታ ውስጤን እየደበኩ፡
አለሁኝ እስካሁን ለይምሰል እየሳኩ፡
በመሰለች ምድር ለምሳሌ እየኖርኩ፡
ስቄ ላልስቅበት ጥርሴንም እያስዋብኩ
፡
፡
ህህ ልበልና ፈገግታዬን ላሳይ፡
ደብቄው ነው እንጂ በዝቷል የኔ ስቃይ፡
ለምዶበት ነው እንጂ ጥርሴ አመል ሆኖት፡
ፈገግ ያስብለኛል ስቄ ላልስቅበት፡
@getemntarik
ለምዶበት ነው እንጂ ጥርሴ የሚስቀው፡
የልቤን መከፋት እኔው ነኝ የማውቀው፡
የራሴን በሽታ ላስታም ብዬ ራሴ፡
ለሰው ሳላወጋው ሸሽጌው በጥርሴ፡
፡
፡
በሳቄ መለያ ስቃይ እያጫወትኩ፡
የውስጤን ጫጫታ ራሴው እያዳመጥኩ፡
አለሁኝ እስካሁን ለይምሰል እየሳኩ፡
፡
፡
የደበነው ውስጤ በበደል ያረረው፡
ጠባሳ የሞላው ጊዜ የማይሽረው፡
ያለኔ ማን አውቆት የልቤን ስብራት፡
ፈገግታዬ እንጂ ስሜቴ ማ ገብቶት፡
መደሰቴን እንጂ ማንባቴን ማን አይቶት፡
፡
፡
በይምሰል ፈገግታ ውስጤን እየደበኩ፡
አለሁኝ እስካሁን ለይምሰል እየሳኩ፡
በመሰለች ምድር ለምሳሌ እየኖርኩ፡
ስቄ ላልስቅበት ጥርሴንም እያስዋብኩ
፡
፡
ህህ ልበልና ፈገግታዬን ላሳይ፡
ደብቄው ነው እንጂ በዝቷል የኔ ስቃይ፡
ለምዶበት ነው እንጂ ጥርሴ አመል ሆኖት፡
ፈገግ ያስብለኛል ስቄ ላልስቅበት፡
@getemntarik
Forwarded from Crypto news
-ማነው?-
ማነው
ማነው ፂሙን አንዠርግጎ የቆመው ከፊቴ፤
ሳየው የወረረኝ ዘልቆ ከጅማቴ፤
አካሌም የራደ ጥኑው ሰውነቴ፤
.
.
የት ይሆን እትብትህ ብዬ እንዳልጠይቀው፤
ይለያል ወዘኑ ደመ ሃበሻዊ ነው፤
ንካው በል በል አለኝ ሰውነቱን ዳብሰው፤
.
.
ማነው
ስስቅ ፈገግ በሎ ስኮሳተር ግንባሩን ሸብሽቦ፤
ስቃኘው ስጨነቅ 'ሱም ባሳብ ተስቦ፤
በል ልበልህ እንዳለ ማደርገውን ደግሞ፤
.
ማነው የበለስ አገኝ የጀግኖች ዘር መሠል እንደኔ የኮራ፤
ኋላው ከበድ ያለ የፊት ልበ ትልቅ የፊት ባላደራ፤
.
ያቺ ልም አይኑን እያየሁ ቀርቤ፤
የኔን ትመስላለች እያልኩኝ በልቤ፤
ማነህ? ከየትስ ነህ ብለው ደግሞ እየጠየቀኝ፤
ከኋላው ሰው መ'ቶ ጀርባየን ቢነካኝ፤
ያኔ ነው የነቃሁ ሰውነቴባሰኝ፤
.
.
ለካስ 'ኔኑ ኖሯል ማነህ ስል የቆየሁ፤
መስታውት ፊት ቁሜ እራሴን እያየሁ።
@wollovine
ማነው
ማነው ፂሙን አንዠርግጎ የቆመው ከፊቴ፤
ሳየው የወረረኝ ዘልቆ ከጅማቴ፤
አካሌም የራደ ጥኑው ሰውነቴ፤
.
.
የት ይሆን እትብትህ ብዬ እንዳልጠይቀው፤
ይለያል ወዘኑ ደመ ሃበሻዊ ነው፤
ንካው በል በል አለኝ ሰውነቱን ዳብሰው፤
.
.
ማነው
ስስቅ ፈገግ በሎ ስኮሳተር ግንባሩን ሸብሽቦ፤
ስቃኘው ስጨነቅ 'ሱም ባሳብ ተስቦ፤
በል ልበልህ እንዳለ ማደርገውን ደግሞ፤
.
ማነው የበለስ አገኝ የጀግኖች ዘር መሠል እንደኔ የኮራ፤
ኋላው ከበድ ያለ የፊት ልበ ትልቅ የፊት ባላደራ፤
.
ያቺ ልም አይኑን እያየሁ ቀርቤ፤
የኔን ትመስላለች እያልኩኝ በልቤ፤
ማነህ? ከየትስ ነህ ብለው ደግሞ እየጠየቀኝ፤
ከኋላው ሰው መ'ቶ ጀርባየን ቢነካኝ፤
ያኔ ነው የነቃሁ ሰውነቴባሰኝ፤
.
.
ለካስ 'ኔኑ ኖሯል ማነህ ስል የቆየሁ፤
መስታውት ፊት ቁሜ እራሴን እያየሁ።
@wollovine
Forwarded from Crypto news
" ድሀ ነህ አትበይኝ "
---------
ልክ ነሽ ድሀ ነኝ ይህንን አውቃለሁ ፤
ሌላ ሰው ሳይነግረኝ እኔው እፈርዳለሁ ፤
ፍቅር አሸንፎት ልቤ አንችን ቢመኝም ፤
አቻየን የሚመርጥ ነጋሪ አያሻኝም ፤
ግን ስሚኝ ፍቅሬ፦
ማጣት ቢያሳንሰኝ ባልኮራ በሃብቴ ፤
ምንም ባይኖርበት ወና ቢሆን ቤቴ ፤
እጀ ባዶ ቢሆን ኪሴ ቢራቆትም ፤
ልቤ ግን ሀብታም ነው ፍቅሩን አይሰስትም ፤
ስለዚህ ኣለሜ ፦
ምንም ከፍ ብትይ ዘቅዝቀሽ ብታይኝ ፤
በጅሽ ብመፀወት ተርፎሽ ብታበይኝ ፤
በፈጠረሽ ውዴ ፦
ፍቅሬን ናቅ አድርገሽ ድሃ ነህ አትበይኝ ።
@getemntarik
---------
ልክ ነሽ ድሀ ነኝ ይህንን አውቃለሁ ፤
ሌላ ሰው ሳይነግረኝ እኔው እፈርዳለሁ ፤
ፍቅር አሸንፎት ልቤ አንችን ቢመኝም ፤
አቻየን የሚመርጥ ነጋሪ አያሻኝም ፤
ግን ስሚኝ ፍቅሬ፦
ማጣት ቢያሳንሰኝ ባልኮራ በሃብቴ ፤
ምንም ባይኖርበት ወና ቢሆን ቤቴ ፤
እጀ ባዶ ቢሆን ኪሴ ቢራቆትም ፤
ልቤ ግን ሀብታም ነው ፍቅሩን አይሰስትም ፤
ስለዚህ ኣለሜ ፦
ምንም ከፍ ብትይ ዘቅዝቀሽ ብታይኝ ፤
በጅሽ ብመፀወት ተርፎሽ ብታበይኝ ፤
በፈጠረሽ ውዴ ፦
ፍቅሬን ናቅ አድርገሽ ድሃ ነህ አትበይኝ ።
@getemntarik
Forwarded from Crypto news
😘ላፍቅርሽ😘
ከማንኩሳ እስከ እመጓ
በቅኔ ድርሳን ድጓ
ደብተራዉ ዜማ ቢያወርድ
ማህሌት ቢቆም ቢንገዳገድ
ካህን ቢጠበብ በብራና
ቢዘንብ የቅኔ መና
፡
ከቆላዉ እስከ ደጋ
ሚስጥርሽን ፍለጋ
በበገና በከበሮ
አይፈታ ቅኔሽ ተመስጥሮ
እንቁነትሽ እያበራ
ሆነሽ አግማስ ጮራ
ወዲህ በሳይንሱ
አምሳያ አጥተዉ ቢያስሱ
፡
ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ
ስትበሪ በቅኔ አክናፍ
ከደቂቅ እስከ ሊቁ
ቅኔነትሽን ሳይደብቁ
ምንም ባልመሰጥርሽ
ቅኔ ሆነሽ ተፈጥረሽ
ልፈወስ በድርሳንሽ
ዝም ብዬ ላፍቅርሽ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Getemntarik
ከማንኩሳ እስከ እመጓ
በቅኔ ድርሳን ድጓ
ደብተራዉ ዜማ ቢያወርድ
ማህሌት ቢቆም ቢንገዳገድ
ካህን ቢጠበብ በብራና
ቢዘንብ የቅኔ መና
፡
ከቆላዉ እስከ ደጋ
ሚስጥርሽን ፍለጋ
በበገና በከበሮ
አይፈታ ቅኔሽ ተመስጥሮ
እንቁነትሽ እያበራ
ሆነሽ አግማስ ጮራ
ወዲህ በሳይንሱ
አምሳያ አጥተዉ ቢያስሱ
፡
ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ
ስትበሪ በቅኔ አክናፍ
ከደቂቅ እስከ ሊቁ
ቅኔነትሽን ሳይደብቁ
ምንም ባልመሰጥርሽ
ቅኔ ሆነሽ ተፈጥረሽ
ልፈወስ በድርሳንሽ
ዝም ብዬ ላፍቅርሽ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Getemntarik
Forwarded from Temari-Ethiopia
የ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እንደተባለው ከሆነ ከ መክሰኞ እስከ አርብ ድረስ ይለቀቃል።
ስለዚህ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄ ጀምሯል። መልሶችን በተቻለው መጠን ከታች👇
1⃣ 1ኛ- ከ Natural ወደ Social መቀየር ይቻላል። ነገር ግን ከ Social ወደ Natural አይቻልም።
መቼ ነው ለምለው ደግሞ ውጤታችሁ ከመጣ ቡሃለ ምደባ ሳይደረግ በፊት ነው። መቀየር የምትፈልጉ ጊዜው ስደርስ ኢትዮ ዩኒቨርስቲ ቻናል ያሳውቃቹሃል።
2⃣ 2ኛ ውጤታችሁ ከመጣ ቡሃላ ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከል ትችላላችሁ። ነገር ግን ዘንድሮ ጊዜ የለንም ብለው ልከለክሉ ይችላሉ።
3⃣ 3ኛ- የተሰረቁ ፈተናዎች አሉ ተብለው ነበር። እነሱን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ብቻ ነው የሚያውቀው።
4⃣ 4ኛ - ASTU ,AASTU እና Phaulos መወዳደር የሚትፈልጉ ተማሪዎች ከዚህ በፊት የነበረውን ፈተና እያያችሁ ተዘጋጁ።
ፈተናው ውጤት መጥቶ ማለፊያው ከታወቀ ቡሃላ ግቢዎች ማስታወቂያ ያወጣሉ።
5⃣ 5ኛ - እኛ ትምህርት ቤት የሞላነው ዩኒቨርስቲ ምርጫ እስካሁን Portal ላይ አልገባም ምን እናርግ?
➖በትምህርት ቤታችሁ የሞላችሁት የዩኒቨርስቲ ምርጫ እስካሁን Portal ላይ ካልገባ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራችሁ ጋር በመቅርረብ አቤቱታ ማቅረብ ይኖርባችኋል።ርዕሰ መምህሩ የ ዩኒቨርስቲ ምርጫ ቅፃችሁን ወድ Portal እንዳስገባላችሁ እርግጠኛ ስትሆኑ የNEAEA ገፅ ላይ እስኪታይ ድረስ በ ትዕግስት ጠብቁ።
🌟ለ AASTU/ASTU/st.paul መግቢያ የሚያዘጋጇቹ ማቴሪያሎች አንለቅላችኃለን::
#source - et_university

ማሳሰቢያ ❗️
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁ የተበላሸባችሁ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ሄዳችሁ አስተካክሉ።
በ ወረቀት ላይ የሞላችሁት እና በ Portal ላይ የገባው ተመሳሳይ ካልሆነ ትምህርት ቤት በመሄድ ማስተካኪያ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ምደባ ከመለቀቁ በፊት ምርጫችሁን ለማስተካከል ሙሉ መብት አላችሁ። ትምህርት ቤቶችም በእናንተ ምርጫ ለማስተካከል ግዴታ አለባቸው።
ሁሉም ተማሪዎች ይሄን ጉዳይ ከውጤት በፊት ሰምተው እንዲያስተካክሉ ሼር አድርጉላቸው።

Forwarded from Ethio Students [SCAM]
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Temari-Ethiopia
ሰበር ዜና ‼️
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።
የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።
በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።
ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።
ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።
ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በ9444 SMS)፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሳብድ ግን ዝም በይኝ
ብዬሽ ነበር የኔ
አንቺ እየሳቅሽ እያለቀስኩ እኔ
ሳብድ ዝም በይኝ
በበርሽ ስገባ በመስኮት ወተሻል
አንቺን ስጠብቅሽ አንቺ ግን ቀርተሻል
እኔማ
ፍቅር ሳይኖረኝ ስለ ፍቅር ዘፍኛለው
ተስፋ ሳይኖረኝ ስለ ተስፋ ገጥሜለው
ሳላገኝ ስለ ማግኘት ፃፌለው
አንቺ ሳታስቢኝ ስለ አንቺ አስቤለው
እናማ
ድንገት ካገኘሺኝ መንገድ ላይ አብጄ፡
ባላየ እለፊኝ ግድ የለም ወዳጄ፡
ምንም ቅር እንዳይልሽ በሰራሺው ስራ፡
ብቻ ዝም በይኝ ሳብድልሽ አደራ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሳብድ ግን ዝም በይኝ
ብዬሽ ነበር የኔ
አንቺ እየሳቅሽ እያለቀስኩ እኔ
ሳብድ ዝም በይኝ
በበርሽ ስገባ በመስኮት ወተሻል
አንቺን ስጠብቅሽ አንቺ ግን ቀርተሻል
እኔማ
ፍቅር ሳይኖረኝ ስለ ፍቅር ዘፍኛለው
ተስፋ ሳይኖረኝ ስለ ተስፋ ገጥሜለው
ሳላገኝ ስለ ማግኘት ፃፌለው
አንቺ ሳታስቢኝ ስለ አንቺ አስቤለው
እናማ
ድንገት ካገኘሺኝ መንገድ ላይ አብጄ፡
ባላየ እለፊኝ ግድ የለም ወዳጄ፡
ምንም ቅር እንዳይልሽ በሰራሺው ስራ፡
ብቻ ዝም በይኝ ሳብድልሽ አደራ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
Forwarded from Temari-Ethiopia
የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡት እነማን ናቸው?
° ተማሪ አላዛር ተካ (ወ)
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ሚኒሊክ I ሳይንስ ሼር ካምፓስ (አዲስ አበባ)
አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 659
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 563
(🎯 ሒሳብ 100/100 ፤ 🎯 ፊዚክስ 100/100)
-------------------------------
° ተማሪ ተመስገን ገብረወልድ (ወ)
ሊቃ ትምህርት ቤት (ዎላይታ)
አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 651
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 555
(🎯 ሒሳብ 100/100 )
-------------------------------
° ናታኒም በላይ (ሴ)
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ሚኒሊክ I ሳይንስ ሼር ካምፓስ (አዲስ አበባ)
አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 651
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 554
-------------------------------
° ተማሪ ሙሴ ፊሊጶስ (ወ)
ሊቃ ትምህርት ቤት (ዎላይታ)
አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 647
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 551
-------------------------------
° ተማሪ ኮኬት ተስፋዬ (ወ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)
አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 643
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 548
(🎯 ፊዚክስ 100/100 )
-------------------------------
° ተማሪ አብዱላዚዝ ዜኑ (ወ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)
አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 644
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 547
-------------------------------
° ተማሪ ሲፈን ፊጣ (ሴ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)
አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 639
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 542
(🎯 ሒሳብ 100/100 )
NB፦
- በ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሲቪክ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ እንደማያገለግል መገለፁ ይታወቃል።
- መረጃው ከተላኩልን መልዕክቶች የተሰበሰበ መሆኑና የጸና መረጃ አለመሆኑ ከግምት ውስጥ ይቀመጥ።
Via -tikvahethmagazine
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርስዎ የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebet

☞ ፍቅር ያጣመደኝ
ገና በማለዳ
.............ልቤን አስነድፌ
በሀሳብ ንውዘት
...............ትካዜን ታቅፌ!!
ያ ፀዳል ውበቷ
.....በንብርክክ አስኪዶኝ
የውስጥ ማንነቷ
ሀሴት ውስጥ አስምጦኝ
የፍቅሬ ጥግ ጥግ
....ጫፍ ደርሶ ሲያጦዘኝ!!
አጡዞ አጡዞ
አናውዞ አናውዞ
........እግሯ ስር ቢጥለኝ
ለካስ ከእባብ ነው
..........ፍቅር ያጣመደኝ!!
፡፡ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
ገና በማለዳ
.............ልቤን አስነድፌ
በሀሳብ ንውዘት
...............ትካዜን ታቅፌ!!
ያ ፀዳል ውበቷ
.....በንብርክክ አስኪዶኝ
የውስጥ ማንነቷ
ሀሴት ውስጥ አስምጦኝ
የፍቅሬ ጥግ ጥግ
....ጫፍ ደርሶ ሲያጦዘኝ!!
አጡዞ አጡዞ
አናውዞ አናውዞ
........እግሯ ስር ቢጥለኝ
ለካስ ከእባብ ነው
..........ፍቅር ያጣመደኝ!!
፡፡ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
☞ ሰላም ይስጡንና
እኮ እነዛ ከርሶችሽ
...............ለንዋይ የመነኑ
ሞላላቸው መሰል
..........አንችው ላይ ዘመኑ!!
እናልሽ አለሜ
አደብ ግዙ ብለሽ
............ከቻልሽ ንገሪያቸው
በርግጥ የነርሱ ነዋይ
..........ምግብ አይሆናቸው
ከቻሉ ግን ጦቢያ
ሰላም ይስጡንና
............አርሰን እናብላቸው!!!!
@የፍሬ ልጅ አዶ
እኮ እነዛ ከርሶችሽ
...............ለንዋይ የመነኑ
ሞላላቸው መሰል
..........አንችው ላይ ዘመኑ!!
እናልሽ አለሜ
አደብ ግዙ ብለሽ
............ከቻልሽ ንገሪያቸው
በርግጥ የነርሱ ነዋይ
..........ምግብ አይሆናቸው
ከቻሉ ግን ጦቢያ
ሰላም ይስጡንና
............አርሰን እናብላቸው!!!!
@የፍሬ ልጅ አዶ
☞ እንዳይቆጭህ ኀላ
ስማ ስማ ስማ
..........ላልሰማው አሰማ
ቁመህ አትመልከት
ሀገር ስትጨነቅ
ሀገር ስትቆስል
............ጦብያ ስትደማ
ስማ ስማ ስማ
.........ሰምተህም አሰማ
ቆመህ አትታዘብ
ሀገርህ ስትፈርስ
.........በማንም ጠማማ
ተመልካች አትሁን
ታሪክህም ሲናድ
በማንም እንክርዳድ
...........ዳውላ ቀውላላ!!
አንተ የሀገር ሰው
በእሳት አትጫወት
.......እንዳይቆጭህ ኀላ!!
፡፡ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
ስማ ስማ ስማ
..........ላልሰማው አሰማ
ቁመህ አትመልከት
ሀገር ስትጨነቅ
ሀገር ስትቆስል
............ጦብያ ስትደማ
ስማ ስማ ስማ
.........ሰምተህም አሰማ
ቆመህ አትታዘብ
ሀገርህ ስትፈርስ
.........በማንም ጠማማ
ተመልካች አትሁን
ታሪክህም ሲናድ
በማንም እንክርዳድ
...........ዳውላ ቀውላላ!!
አንተ የሀገር ሰው
በእሳት አትጫወት
.......እንዳይቆጭህ ኀላ!!
፡፡ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
ሳማይቱ ኑሮ
----------------
ይሄ ነወይ ኑሮ?
ይሄ ነወይ እድሜ?
ጆሮና አይኔን ይዤ
አልመጣም ደግሜ
አልቃሻ ልቤማ
ጭራሽ ጉጉ አ'ደለም
በጠማማ ማገር
በተሰራች ዓለም
ፍትህና እውነትን
አለቅጥ ብጠማ
ቅፅል ስሜ ሆኗል
መንፈሰ ደካማ
አልመጣም! አልመጣም!
አልመጣም! ደግሜ!
እናንተው ኑሩበት
በአሸሼ ገዳሜ
በነፍሴ፣ በልቤ፣
በደሜ ውስጥ ያለው
የእኔ ሕይወትና
የእኔ ዓለም ሌላ ነው።
----------------------
✍ ሰለሞን ሞገስ (ፋሲል)
📖 📖 📖 📖 📖
----------------
ይሄ ነወይ ኑሮ?
ይሄ ነወይ እድሜ?
ጆሮና አይኔን ይዤ
አልመጣም ደግሜ
አልቃሻ ልቤማ
ጭራሽ ጉጉ አ'ደለም
በጠማማ ማገር
በተሰራች ዓለም
ፍትህና እውነትን
አለቅጥ ብጠማ
ቅፅል ስሜ ሆኗል
መንፈሰ ደካማ
አልመጣም! አልመጣም!
አልመጣም! ደግሜ!
እናንተው ኑሩበት
በአሸሼ ገዳሜ
በነፍሴ፣ በልቤ፣
በደሜ ውስጥ ያለው
የእኔ ሕይወትና
የእኔ ዓለም ሌላ ነው።
----------------------
✍ ሰለሞን ሞገስ (ፋሲል)
📖 📖 📖 📖 📖
በእድሜ ሰንሰለት
.....በታሰረች ህይወት
እኔው ተጠምጄ
.....እንዲሁ ከምቃትት
ይሻለኝ ይሆናል
.........እኔ ካንቺ ብርቅ!!
እንጂማ
አንቺ አንችን ስትሰሪ
.......ማን ቆሞ ይቀራል
አላውቃትም ብዬ
.........ብረሳሽ ይቀላል
እንኳንስ መውደዴ
የናት ሞት እንኳን
.........ከረሱት ይረሳል!!
አፈቀርኩ እያለ
.....ማን ማቆ ይሞታል
ከቀረሽ ቅሪ እንጂ
ልቤስ ላይቀመስ
.....ልቡን ከርችሞታል!!
.....በታሰረች ህይወት
እኔው ተጠምጄ
.....እንዲሁ ከምቃትት
ይሻለኝ ይሆናል
.........እኔ ካንቺ ብርቅ!!
እንጂማ
አንቺ አንችን ስትሰሪ
.......ማን ቆሞ ይቀራል
አላውቃትም ብዬ
.........ብረሳሽ ይቀላል
እንኳንስ መውደዴ
የናት ሞት እንኳን
.........ከረሱት ይረሳል!!
አፈቀርኩ እያለ
.....ማን ማቆ ይሞታል
ከቀረሽ ቅሪ እንጂ
ልቤስ ላይቀመስ
.....ልቡን ከርችሞታል!!
የመንታ እናት
-----------------
ሐኪም አዋላጅዋ
ቶሎ ሳይደርስላት፣
ተንጋላ ልትሞት ነው
ይቺ የመንቶች እናት፤
ለዚህች ጓዘ ብዙ
ረዳት ለሌላት፣
ብትገላገለው
ጸሎት አድርሱላት።
===========
ሥልጣኔ ማለት
--------------------
ሥልጣኔ ማለት
የልማት 'ርምጃ፣
በአንድ እጅ ዲሞክራሲ
በሌላው ጠብመንጃ።
============
✍ ታደለ ገድሌ ጸጋዬ
📖 የዘመን ቀለማት
📖📖📖📖📖📖
-----------------
ሐኪም አዋላጅዋ
ቶሎ ሳይደርስላት፣
ተንጋላ ልትሞት ነው
ይቺ የመንቶች እናት፤
ለዚህች ጓዘ ብዙ
ረዳት ለሌላት፣
ብትገላገለው
ጸሎት አድርሱላት።
===========
ሥልጣኔ ማለት
--------------------
ሥልጣኔ ማለት
የልማት 'ርምጃ፣
በአንድ እጅ ዲሞክራሲ
በሌላው ጠብመንጃ።
============
✍ ታደለ ገድሌ ጸጋዬ
📖 የዘመን ቀለማት
📖📖📖📖📖📖
☞ ፈልፍለው ጨረሷት
የስልጣኔ ቅብብሎሽ
.....ህልም ሆኖ ቀርቶባት
እንደ ክፉ ዕጣ
...ወጭ ወራጅ በዝቶባት
ሁሉም በየፊናው
ቦጭቀው...
ቦጫጭቀው...
...........በደዌ ለክፈዋት
ሀገሬን.....
ጦብያዬን......
ሀይ ባይ በሌለበት
.......ፈልፍለው ጨረሷት!!
ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
የስልጣኔ ቅብብሎሽ
.....ህልም ሆኖ ቀርቶባት
እንደ ክፉ ዕጣ
...ወጭ ወራጅ በዝቶባት
ሁሉም በየፊናው
ቦጭቀው...
ቦጫጭቀው...
...........በደዌ ለክፈዋት
ሀገሬን.....
ጦብያዬን......
ሀይ ባይ በሌለበት
.......ፈልፍለው ጨረሷት!!
ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
ይበልጥ አሳመመኝ
የውስጥ ቁስሌን ያላየ
............የስሜት ገለባ
ምንም ያልተረዳው
..........የስቃዬን እምባ
ላያቀልልኝ ነገር
.........የጫንቃዬን ካባ¡¡
ሸለምኩልህ ይላል
ላይረባኝ ላይጠቅመኝ
ቁስሌን ላያሽረው
እምባዬን ላይገድብ
ፈውስ እንኳን ላይሆነኝ¡¡
እናም......
በተጨነቀች ሀገር
....በጭንቅ እየኖርኩኝ!!
ሸለምኩልህ ሲለኝ
....ይበልጥ አሳመመኝ¡¡
ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
የውስጥ ቁስሌን ያላየ
............የስሜት ገለባ
ምንም ያልተረዳው
..........የስቃዬን እምባ
ላያቀልልኝ ነገር
.........የጫንቃዬን ካባ¡¡
ሸለምኩልህ ይላል
ላይረባኝ ላይጠቅመኝ
ቁስሌን ላያሽረው
እምባዬን ላይገድብ
ፈውስ እንኳን ላይሆነኝ¡¡
እናም......
በተጨነቀች ሀገር
....በጭንቅ እየኖርኩኝ!!
ሸለምኩልህ ሲለኝ
....ይበልጥ አሳመመኝ¡¡
ጨ፡፡ረ፡፡ስ፡፡ኩ፡፡
@የፍሬ ልጅ አዶ
እኔ ምልሽ ውዴ
አንቺን በመውደዴ
ባውቶብስ ፌርማታ
ባቡር ተጠበቀ
ሌባው እየኮራ
ፖሊስ ተደበቀ
ጥርስ ያለው አይስቅም
ድዳሙ እየሳቀ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ሌላው ቀርቶ
አንቺም የኔዋ ጉድ
የኔን ልብ ሠርቀሻል።
@robi_RK 😻😻
አንቺን በመውደዴ
ባውቶብስ ፌርማታ
ባቡር ተጠበቀ
ሌባው እየኮራ
ፖሊስ ተደበቀ
ጥርስ ያለው አይስቅም
ድዳሙ እየሳቀ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ሌላው ቀርቶ
አንቺም የኔዋ ጉድ
የኔን ልብ ሠርቀሻል።
@robi_RK 😻😻