ግጥም ከብሶት አንደበት(@wubie m)
183 subscribers
13 photos
4 videos
59 links
Death die with me
Download Telegram
የሳቅሽን አቦል ድምቀት
ለዘመናት ሞቄ ሞቄ
እንድታለቅሽ አልፈልግም
ስለ እምባሽ መች አውቄ
የምትስቂው ሙሉ ብርሃን
የተስፋ ቃል ፍንጣቂ
እምባሽ ግና ጽልመት ወሳጅ
ሞት እና ህይወት አስታራቂ
ብደምቅበት በዓለም ሁሉ
ሳቅሽን በገፍ እየቀዳው
ስታለቅሺ ባይ ለአንዴ
እምባሽ ሊሆን
አይኔን ዳዳው

ለዘመናት ያልተሻረ
ህመም ስቃይ ነበረብኝ
ጠብ አድርጎ ቁስሌን ሻረው
ከሳቅ እምባሽ በለጠብኝ

ለዘላለም ብጸልይም
ከሀዘን ችግር እንዳትገቢ
ግና ለቅሶሽ ይናፍቃል
ያምርብሻል ስታነቢ.

# ሚኪ.
ግጥም መግጠም ተውኩኝ!
ለምን?
..... ስላላተረፍኩኝ!
ላንች ልብ መግዣ፣
ቃላትን ብበደር ፣
ከመጻፍት መደብር፤
ሆሄያትን ብቃርም፣
ፊደል ብለቃቅም፣
ላንች ምን ሊጠቅም።
ግጥም መግጠም ተውኩኝ!
ለምን ?
......... ስላላተረፍኩኝ!
የስንኘን ዋጋ ስላላስገመትኩኝ፤
በአንጓወቼ ልክ ስለተበደልኩኝ፤
ባሰብኩሽ ብዛት ልክ ስለተገፋሁኝ።
የመዉደዴ ስፋት፣
የመድከሜ ልፋት፣
የብዕሬ መከፋት፣
የእንባየ መገንፋት፣
ቢፈስ ወደ እግዜር ቤት ፣
እድፍ ነው ባንች ፊት።
ግጥም መግጠም ተውኩኝ!
ለምን ?ብለሽ ካልሽኝ
.... ... ስላላተረፍኩኝ!
ቤት ሊመታ ሳስብ እየፈራረሠብኝ።
አዎ! ግጥም መግጠም ይብቃ ይብቃ ፤
የቃላት ሰቆቃ ፤
የሆሄያት ሰረቃ፤
ፍቅር ካላመጣ አንችን ካላነቃ።
ዘፋኝም አልሆንም!
የለውም ጥቅም፣
ስሰሜ ኖረሽየል የመውደድን ትርጉም፣
ከነጥሌ አልበም።
አይተሻል ትዝታም ሲወጋ፣
ከማሙድ መንጋጋ፣
ሰምተሻል ከሁሎቹ ዜማ፣
ግን ልብ ስለሌለሸ ልብ አትይማ።
ለዚህ ነው መግጠምን ያቆምኩኝ ፣
በእውን የመሰለኝ ያላተራረፍኩኝ፣
የተፈቀደልኝን አሜን ስላላልኩኝ።
✍️✍️wubie maralem
https://t.me/wubiemlove
.......መልስ ያጣችው ምላስ ...🌿
ውሸት ባካለላት ፣በውዥምብር አለም ፤
እውነት ባነሰባት ፣የፌዘኞቾ ሸክም፤
ሰሚ የሌለበት ፣ጀሮ ያጣች ምላስ ፤
በሀቀኛ ትናጋ ላይ ፣የበቀለች በለስ ።
ስንቶች ነጋባቸው በተድፈነፈነ ህልም፤
ከራስ ጋር ሲጣሉ ተረጅ ባጣ ህመም ፤
ጥል ባከሰላት ፍቅር ባጣች ምድር ፤
ለቧልተኞች ጣፋጭ ለብሩሆች መሪር ።
ታናሽ በበዙባት በዝች ትንሽ ሳህን፤
እያደሩ ማንስ ነው የለም ትልቅ መሆን ፤
ስንቶች ተረገጡ ሀቅን ባገዘፉ፤
ሠርተው ባበቀሉ ጽድቅን እየተፉ ።
ጉድፉን ከውሀው ለይተው ባጠለሉ ፤
አንሰው ተገመቱ መዳፍ ላይ ተጣሉ ፤
ከተኩላ ፅንስ ላይ በግ አይታለምም
የውሽት ክስ እንጂ የእውነት ፍትህ የለም።
.........እናማ ልምከርህ .........
አንተው ላንተው ቆመህ ጠበቃ ካልሆንከው፤
መልስ ያጣችው ምላስ ተርፏ
_ኡ _
_ ኡ_
_ ኡ_
ነው።😩😩
✍️✍️✍️wubie maralem
https://t.me/+HVr8q26fWq41ZTFk
እኔ አንችን ስወድሽ!
እኔ አንችን ስወድሽ ቀናቶች ያውቃሉ፤
ሳላውቀው የሄድኩባቸው ጎዳናወች አሉ ፤
ብዙ እጾች ነበሩ ስላንች ለመስማት የተጎናተሉ፤
የፎነጨርኳቸው እልፍ ግንዶች አሉ፤
ውሸት እንዳይመስልሽ ፤
ብትጠይቂያቸው ይመሰክራሉ።
አኔ አንችን ስወድሽ!
ድንጋዮች ነበሩ ፣
የደነቋቆሩ፣
እንባየን ያቆሩ፣
ስጮህ የጠቆሩ ።
እኔ አንችን ስወድሽ !
ፖሎች እኮ አቀዋል ፤
ስንደፋደፍልሽ ደግፈው አዝነዋል ፣
እንደተገተርኩኝ ማታወች አልፈዋል፤
እኔ አንችን ስጠብቅ አብረውኝ ነግተዋል።
እኔ አንችን ስወድሽ!
የተሸሸኩበት ጣሳወች ያቃሉ፤
አንሳት ይሉኛል ጌሾ እያቀበሉ፤
ደጋግሜ እንድልሽ ስላንች እያስማሉ፤
መለኪያወች ናቸው የተሸምኩሽን አንችን
ያቀለሉ።
እናማ ስወድሽ !
ቀን ከሌት አልመርጥም፤
ነጋ ፣መሸ አልልም፤
አመት አልደምርም ፤
ዘመን አልቀንስም ፤
በቃ ማሰብ ብቻ ፤
አንችን በመጠበቅ እንዳይኖረኝ አቻ፤
እስከመኖሬ ጫፍ እስከ ሞት መባቻ።
እኔ አንችን ስወድሽ !
ጨርቄ ፣ማቄ አልልም፣
ጫማም አላጠልቅም ፣
መኪና አልጠይቅም፣
መዳንች ስመጣ ወዳንች ሳዘግም።
አወ! አልፈልግም!
አለኝ ምርኩዝ ነፋስ፣
አፍጥኖ የሚያደርስ፣
አለኝ!
የሌት ህልም ፈረስ!!!!

✍️✍️✍️wubie maralem
https://t.me/wubiemlove
🙏____
የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል
ምንም መረጋጋት አልቻልኩም የማይታወቅ ድብቅ
ስሜት በደምስሬ ሲርመሰመስ ሲሯሯጥ ሲፈራገጥ ይታወቀኛል ምናለ እንደ ወጥ ገንፍሎ ቢወጣልኝ ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር በቃ ውስብስብ ያለ ህይወት
____😴
''እየገነፈለ ድንገት ሆድ የሚያስብስ
ሒማ የሚያሳንስ አቅልን የሚበጥስ''
ስሜት አለ ውስጤ
__

ውስጤ ይጨሳል
ሆዴ ተቀጣጥሎ እንደ ሰው ፊት ደርሶ ይገርፈኛል
በማይመከት ወላፈን ድኩም ሰውነቴን ያነደኛል
በቃ እንደ ሰደድ እሳት እየተንቀለቀለ ትኩስ ትንፋሼን እያበዛ በጭሱ ሳምባዬን ይገርፈኛል
ወላፈኑም ያለ ከልካይ ልፍስፍስ ጅስሜን ያቃጥለኛል
''
😴በቃ ያኮረፈ ስሜት
ደስታን የሚሠውር ሣቅን የሚቀማ
ልብን የሚያቆስል ሆድን የሚያደማ

ስቃይን የሚያሳይ ፍዳን የሚያበላ
ልብን የሚያቆሽሽ ዕምነት የሚያላላ
ውስጤ ስሜት አለ
__
ሁሉም ነገር ተዘበራርቋል
ውል አልባ ማንነቴን ለመፈለግ ሳስብ ይደክመኛል
ምክንያቱም :- መንገዴ ከመንገዱ ጋር ተለያይቷል
ሀሳቤም ከሀሳቡ ጋር ተራርቋል ለዛ ነው የተረበሽኩት በቃ ውስብስብ ያለ ህይወት
🙏
የዘመን ድካም ልፋቱ በቀን ጎደሎ ሲበላሽ
የሚኖርለት ሕይወቱ በሰው ባለጌ ሲኮላሽ
ስታይ ምን ትላለህ ??

ተስፋ
ታጣለህ
በኑሮህ ለህይወት ምንም አትጓጓም

የቱንም
ያህል ብትጥር አቲዝም የደስታ ልጓም

__😴
ለዛም ነው
ብዙ ጊዜ ስሜቴን በፅሁፍ እንጂ በንግግር
ለመግለፅ የሚከብደኝ ማንም የሚረዳኝ ያለ አይመስለኝም አለ አደል ውስጤ እንዲነው የሚሰማኝ
😭
የውስጣችን ስንኝ
የልባችን ጩኸት የሆዳችን ዜማ
የታፈነ ህመም ስቃይ ነው ሲሰማ
_
ሁሉም ነገር ተዘበራርቋል
ውል አልባ ማንነቴን ለመፈለግ ሳስብ ይደክመኛል
ምክንያቱም :- መንገዴ ከመንገዱ ጋር ተለያይቷል
ሀሳቤም ከሀሳቡ ጋር ተራርቋል ለዛ ነው የተረበሽኩት በቃ ውስብስብ ያለ ህይወት
🙏

ስለዚህ ! በቃ በዚች ስንኝ
ሀሳቤን ልቋጭላችሁ መሰለኝ
👇
ህይወት እንዲሰምር ተስፋህ እንዲታደስ
የሰይጣንን ዕምነት በጌታህ ስም ገርስስ
በልብህ ዙፋን ላይ አምላክን ብቻ አንግስ ።
🙏
ፍርጃ

@ጋሻው የኋላሸት (ዘቢደር)

በልቦናየ ተዳፍኖ  -
የተቀየጥሽኝ በሀዘን -
የተዋሃድሽኝ በፌሽታ፣
ትላንቴ ዛሬን ከቀማኝ -
ትዝታ ይምከን ይገነዝ -
የቁም ፍታቱ ይፈታ!
አሁኔን ብቻ ልበርታ!

በሰማይ በምድር -
አክንፎ አገስግሶ -
ከߴቅፍሽ ካልጣለኝ፣
በማበርታት ፈንታ -
ተብትቦ ለጉሞ - ደካማ ካረገኝ፣
ታንቆ ይሙት ናፍቆት -
እያጠወለገ አንቺን ካስናፈቀኝ!

ይጨክን አንጀቴ!

እንደ ሞት ልዘንጋሽ -
የጎደለብኝን ስማስን ልሞላ፣
ታዛቢ ይውቀሰኝ - ልባል ልብ የበላ፣
መኖር ላይደገም!
ለምን ከቁም ሞት ጋር - በቁሜ ልታደም?

ከመላ ህዋሴ -
ከደም ስሬ ሰርፆ -
ከሕይወት ወለላ - አፍላ ፍቅር ቀስሞ፣
መርሳት ህያው ይሁን - ይለምልም ከራርሞ!

ኑረትን በከንቱ -
ዕድሜን ካለፋይዳ ከተቀራመቱ፣
ትዝታߴና ናፍቆት -
ለወሬ አይትረፉ - ተረስተው ይሙቱ!
(ለምጻትሽ ብቻ ለߴቅፍሽ ይበርቱ!)
    -//-
እንኳን   ለ፳፻፩፮ኛው ለአምላካችን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

በዓሉን የሰላም የፍቅር ያድርግልን
ሎሚየን ልወርውር!
ነገ ገብያ ልውረድ ማለዳ ማልጄ፣
ሎሚዬን ልሸምት ቶሎ ልቅደም ሄጄ፣
መጣጭ ሳይበዛበት ሳይወደድብኝ፣
ፈጥኘ ልወርውር ቆንጂት ሳቴድብኝ።
መቼም ማርፈድ ነው ልምዴ ፥
መበለጥ፣ መቀደም ነው ገዴ፥
ስለዚህ ልወርውር!
ደረቷን እንዳልስት አስቤ መሳትን፣
ውብ የሆነችውን አይኔ ያረፈባትን፣
ቀርቤ ላማትር መልሷን ልጠባበቅ ፤
በመራቄ ምክንያት መንገድላይ እንዳይደርቅ፤
ለኔ የቀሰርሽው ቀልብሽ ሳይሰረቅ።
ሎሚየን ልወርውር!
ልላከው ገምቸ ፣
ዋጋው ላልበለጣት በውድ ገዝቸ፣
ከእጅ እየነጠቀች መምጠጥ ላለመደች ፤
ዘንድሮን የዋለች አምናን ላልነበረች፤
ሎሚዬን ልወርውር !
ጥምቀቱን ሂደሻል መጣሁ ተሻምቸ ፣
እየተንደረደርኩኝ መሄድሽን ሰምቸ፣
ከታቦቱ ስደርስ አንችን እረሳሁኝ፣
ለካ ስጋዬን ነኝ አንችን ያ'ሳደድኩኝ።
✍️✍️wubie maralem
https://t.me/wubiemlove
ከራስ መፈራራት.........!
በብቻ መንገድ ላይ ራሴን ፈርቸው ፤
መገኝትን ፈራሁ አቋራጭ እያበዛው፤
አይኑን ማየት ፈራው!
በጠየቀኝ መጠን ምላሼን ነፍጌው።
እራሴን ፈራሁት!
ጧት አላገኘውት ፣
ማታም አላየሁት፣
ሳቅ አመሳስየ ስለሸነገልኩት፤
እራሴን ፈራሁት!
ብቻየን ቢቀጥረኝ በጀማ አሳደድኩት፤
መካክሮ ማሳመን !
ሞት አስኪመስለኝ ድረስ እራሴን ገመትኩት ፤
መሸሽን መርጬ ፣
እንባዬን አምጬ፣
.....................መባ እየገበርኩት፤
እግዜሩም ታዘበኝ ነጋ እያስቸገርኩት።
እራሴን ፈራሁት ፣
እራሴን አየሁት ፣
በድብቅብቆሽ ማህል፣
ባኮኩሎ ሲውል።
አየሁት ራሴን :
በራስ ጥላቻ ስር ፣
አባሮሽ በቀትር፣
በድሮ ጨዋታ ዘመኑን የሚኖር!!!!!!
✍️✍️wubie maralem
https://t.me/wubiemlove
.............አድዋ !
የደም ማተም ቀንዲል፤
የጥቁሩ አለም ቃል፤
የነፃነት ፅዋ ዝክር፤
የሀገር ፍቅር ምስክር።
.............አድዋ!
የልም አጥምት ብቃይ ፤
የማይጠወልግ ለዘመናት ቢታይ ፤
የማንነት ቋት ገንቦ ፤
ያልጠለፋት የዘር ሀረግ ስቦ፤
ያልጠመዳት የጎጥ ቀንበር፤
ያልታረሰች በነጭ ሞፈር፤
ያልተገዛች በነጭ ሳንቲም፤
ያረከሰች የአለም ቀደም፤
...............አድዋ!
የጀግንነት ጥልቅ ምስል፤
የሞት ሽረት ፊደል፤
ለመሞት እሽቅድምድም፤
ታሪክ ለመቀለም ፤
በደም ሸራ ቀለም።
..............አድዋ !
የሉአላዊነት መድረክ፤
የኢትዩጵያዊነት ስፋት ልክ፣
የጥቁር ወዝ እንጥፍጣፊ፤
ደማቅ አርማ የሰማይ ላይ ተንሳፋፊ።

...............አድዋ!
የህብር ቃል ትርጉም ፤
የእግዜር ኪዳን ማህረም፤
የሚኒሊክ አዋጅ ጥንካሬ፤
የታቦቱ መባ ፍሬ።
አድዋ!
አድዋ! ........አረንጓዴ፤
የለም አፈር ስንዴ።
አድዋ!............. ቀይ ፤
የደም ግብር ብቃይ።
አድዋ! ..............ቢጫ!
የአንገት ላንገት መስዋት የጀግኖች ነፍስ ቅርጫ።
አድዋ!............ነፋስ፤
አድዋ !.............እስትንፋስ፤
አድዋ!............. ወንዝ ነው ወደ አለም የሚፈስ።
✍️✍️✍️✍️wubie maralem
ለምን አንዴ ሴት አንዴ ደግሞ ወንድ አልካት አድዋን ለምትሉ ምክንያቱም አድዋ አንድም ሚኒልክ አንድም ጣይቱነች ።
https://t.me/wubiemlove
***
ባለዙፋን ባለመሪ
       በደም ቀላጅ፣
ምን ነበረ ከሰይጣን
       ጋር ባትወዳጅ፣
አንተ ዘመን አንተ እለት
        ነገ አላፊ፣
ማንን መረጥክ አፈር ለባሽ
        ዛሬ ጠፊ፣
ምድርስ ብትሆን
         ባለገደል ባለመስኳ፣
ስንት እሬሳ ስንት ደም ነው
         አቅም ልኳ?

የኔስ ትውልድ የለመደ
         ጭንቅ አመፃን፣
እስከመቼ ያበጃጃል
           ያስክሬን ግንብ ያፅም ህንፃን፣
መራጩስ ህዝብ
          ሰላም ብሎ ሰልፍ የወጣ፣
እስከመች ነው
          ባነገሰው የሚቀጣ?

ኤዶምገነት  ፃፈችው

https://t.me/wubiemlove
ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን
በዓብይ ሐይል ወሥልጣን
ዓሰሮ ለሰይጣን
አጋዕዞ ለአዳም
ሰላም
ዕምይዕዜሠ
ኮነ
ፍሰሃ ወሰላም
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰዎ!
ሠላም፣ ፍቅር እና ደስታ የሞላበት በዓል እንዲሆንልዎ ከልብ እመኛለሁ!
ህ'ያው አባት የኛ ጌታ
........በሞቱ ሞትን የረታ፤
.........የፈታልን የሀጺያት ቀንበር፣
.........ዝቅ ብሎ ወደምድር፤
.........ከፍ ሊያደርግ የኛን ክብር፣
..........ተጎነጨ ሀሞት መሪር፣
......... የቁም ሞትን ውርደት ሊሽር።
.ህ'ያው አባት የኛ ጌታ!
  ........ እየገፉት ፈቅዶ ሚረታ፣
  .........እየተፉበት ጥቁር ምራቅ፤
  ........ጌታ ሆኖ ማይሳቀቅ፤
   .......እየገረፉት ከልብ እሚወድ፤
  .... ...እያረከሱት ፍቅሩ እሚከብድ፤
   .......ቸንክረውት ቃሉን  አንጋሽ፤
   .......እየረገጡት ፍፁም ታጋሽ፤
   .......እንዲህ ብሎ የሚጸልይ ፤
  .......እያቁም እና ይቀር በላቸው፤
  .......ስለደላን እያወቅን በበደልነው፤
.........ጥጋብ ልቆ በክፋት ሀይል በጎተትነው።
       ህ'ያው አባት የኛ ጌታ!
.........ተሰቀለ ጎለጎታ፤
..........ደሙን ረጬ ለአለም ደስታ፤
..........በመቃብሩ ሞትን ገታ፤
..........ክዋክት ሁሉ ረገፈ፤
.........ጨራቃ አይኗ ደም ጎረፈ፣
.........ቀን እና ሌት ተኳረፈ ፣
........ፀሀይ ብርሀኗ ተገፈፈ፤
.........አለቶች ተሰነጣጠቁ፤
.........ያሸለቡት ከሞት ነቁ፤
.........መፈፀሙን ስላወቁ፤
.....ህያው አባት የኛ ጌታ ፤
... ያደምን ሞት በሞት ፈታ።
✍️✍️✍️by wubie maralem
ምረት ካንተ እሻለሁ እንዳላየህ እለፈኝ፡
በስንኩል አምሮዬ ቃልክን ካጎደፍኩኝ።
      https://t.me/wubiemlove