ቃላዊ
344 subscribers
39 photos
5 videos
1 file
122 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ጥሬ ጨዉ
=========
መስለዉኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰዉ ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸዉ
ጥሬ ጨዉ…ጥሬ ጨዉ ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት መቀየጥ
ገና እሚቀራቸዉ
“እኔ የለሁበትም!”
የዘወትር ቋንቋቸዉ።
___
ደበበ ሰይፉ


@Write_Event
@Write_Event
ፍቅር የሚሰጠውንም የሚቀበለውንም ይፈውሳል።

ሁለቱ ወንድማማቾች በቤተሰቦቻቸው እርሻ ላይ አብረው ይሰራሉ። አንደኛው ያገባና ብዙ ቤተሰብ ያለው ሲሆን ሌላኛው ገና ያላገባ ነበር። ሁልጊዜ በቀኑ መጨረሻ ላይ ወንድማማቾቹ ምርቱን እና ትርፉን ሁሉንም ነገር እኩል ይካፈሉ ነበር።

አንድ ቀን ብቻውን የሚኖረው ወንድም ለራሱ "ምርቱን እና ትርፋን እኩል መካፈላችን ትክክል አይደለም። እኔ የምኖረው ብቻዬን ነው ፤ የሚያስፈልገኝ ጥቂት ነው።" ብሎ አሰበ። ከዚያ በእያንዳንዱ ምሽት ከራሱ ጎተራ አንዳንድ ጆንያ እህል ይወስድና በእርሱና በወንድሙ ቤት መካከል ያለውን ሜዳ አቋርጦ በወንድምየው ጎተራ ውስጥ ያስቀምጣል።

ያገባው ወንድምም ለራሱ "ምርቱን ና ትርፋን እኩል መካፈላችን ፍትሀዊ አይደለም። እኔ ለሚመጡት አመታት የሚንከባከቡኝ ሚስት ና ልጆች አሉኝ። ወንድሜ ግን ማንም የለውም ፤ወደፊት የሚንከባከበው የለም። "ብሎ አሰበ። ስለዚህ በየምሽቱ ከራሱ ጎተራ አንዳንድ ጆንያ እህል እየወሰደ ሳያየው ወንድምየው ጎተራ ወስጥ ያስቀምጥ ነበር።

ሁለቱም ሰዎች ጎተራቸው ውስጥ ያለው እህል መጠኑ ባለመቀነሱ ለአመታት ይገረሙ ነበር። ከዚያ በአንድ ጨለማ ምሽት ሁለቱ ወንድማማቾች በድንገት ተጋጩ። ቀስ በቀስ ምን እየተከሰተ እንደነበር ተረዱ ከዚያ ሁለቱም የተሸከሟቸውን ጆንያዎቻቸውን ጥለው ተቃቀፉ።

አስተማሪ ታሪክ ነውና ለወዳጅዎ ያጋሩት

👉 @Write_Event
@Write_Event
ጠላቴ

ጠላቴን ስፈልግ፣ ከጎሮቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከሩቅ፣ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው።

ሰለሞን ሞገስ

👉 @Write_Event
@Write_Event
ፍቅር

"ፍቅር ራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም ፤ ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም ምንም አይቀበልም፤ ፍቅር ለፍቅር በቂ ነውና!! ፍቅር ምንም ንብረት የለውም፣ የማንም ንብረት ሊሆንም አይችልም።"

ካህሊል ጂብራን
👉 @Write_Event
👉 @Write_Event
"""ፍቅር ና በቀል""
ሀዊ ጌታቸው
።።።።።።።
።።ክፍል 12
.

አማን እየሮጠ ተከተለው
ሀኒ ቤተሰቧቾ ይዘዋት ወደቤት
የመኝታ ቤቶን ቆልፋ ማልቀስ ጀመረች ማንም ቢለምናት ምን ቢሎት አልከፍት አለቻቸው ።

አማንም እቤት እንደደረሱ ኪሩቤል ሲል
አማን plzzz ምን እንዳትለኝ ብሎት ክፍሉ ገብቶ በሰራው ነገር ያለቅሳል

ሰዓታት ቀናትም ተቆጠሩ
ኪሩም የምር የበፊቱ ፍቅር አገርሾበታል ግን እንዴት አይኖን አያለው ብሎ ተቀመጠ እሷም ከበፊቱ ይልቅ አሁን ያሳለፉትን እያሰበች በትዝታ ውስጥ እንዳሉ አንድ ወር ሆናቸው

እለተ ህሮብ ኪሩቤል ሳሎን ሶፋው ላይ እኛደተኛ ይግብ ጋሼ እያለ ሻንጣ እንሰመጎተት ሲል ከተኛበት ቀና ሲል አባቱ ናቸው። አባ ብሎ ተጠመጠመባቸው ቢደነግጥም ግን እንዴት መጣክ ከማለት ይቅርታ አባዬ እያለ ያለቅስ ጀመር። አባትም አታልቅስ ልጅ ይሄ አንተ ውደክ ሳይሆን በልጅነትክ ውስጥክ የነበረው ነው። ያም ደሞ በደላቸው የከፋ ስለሆነ ነው። ግን በቀልን በፍቅር የሚለውጥ ልብ ነበረክ። ልጅ ለማንኛውም ሁሉም አልፋል።

ትንሽ እንዳረፉ ምግብ ከተበላ በኃላ የኪሩቤል አባት ልጅ አማን እስቲ አዲሱን ቤቴን ልየው ሲሉ
""ኪሩቤል የምን ቤት ግራ ተጋብቶ አማንና አባቱን እያየ""

ግን መልስ ሳይሰጡት አስነስተው ሄዱ። ቤቱን ስያዩት አባት ደስ አላቸው ከመጠን በላይ።
አየክ ባልውልደውም ግን ከልጅነት ጀምሮ የደኛክ ውንድምክ ነው። ለኔም ልጄ ነው። ማነው እስቲ እንዲ የሚያደርገው ያሁን ጊዜ እኮ እሺ ብሎ የሚበላ ነው። አማንዬ ተባረክ ጥሩ ትዳር ይስጥክ። ብለው ሳሙት

የኪሩቤል አባት ኢት መኖር እንደሚፈልጉ ሲነግሩት በደስታ ነው።
የኪሩቤል ውንድሞች ብር ልከውልት ሁሉን ያመቻቸው ያው ብር ካለ ሁሉንም በአንዴ ማድረግ ይቻላል። የሚገርመው የቤት ሰረተኛ አድርጎ ነው የጠበቃቸው ቤቱ ሲገብ አማን ሁሉንም ነገር ስላዘጋጀ የሞቀ ቤት መስሏል ኪሩቤል እያለቀሰ አማን ውለታክን እንዴት እንደምከፍል አላቅም ብሎት ተጠመጠመበት

አማን ግን የኔን ደስታ የምፈልግ ከሆነ ይህን ፂምህን ስታነሳ ነው ውለታዬን የምከፍለው።እየሳቁ ምን አታስብ ያልከውም ብሎ አቀፈው ።
ትንሽ ከተጫውቱ በኃላ አማን መጣው ብሏቸው ወጣ አባትና ልጅም ማውራት ጀመሩ።

አማን ማክዳ ጋር ደውሎላት እንደሚፈልጋት ሲነግራት እቢ ብላ ስትሳደብ የት ታቀኛልክ ስትለው እሺ አንዴ ላግኝሽ..
ከብዙ ጭቅጭቅ በኃላ እሺ ብላው የተቀጠሩበት ባታ እንደደረሰች ሰላም ሳትለው
""ለምን ነበር የፈለከኝ ...
እየሳቀ አሁንም ያው ነሽ መጀመርያ ሰላምታ ይቀድማል ...

"ይመለከተካል የምሄድበት ቦታ አለብኝ ንገረኝና ልሂድ ግን ውስጦ ደስ ብሎታል ስላየችው ከምን በላይ ስለምታፈቅረው

""ማኪ ስለሁሉም ነገር በጣም ይቅርታ ...!!

ማኪ ነው ያልከው የት የምታቃትን ለዚ ነው የፈለከኝ እኔ አንተ አንተዋውቅም ህፃን ብላ ተነስታ ልትሄድ ስትል

እውነት ማኪ ሀኒ ጉዳቶ አያሳዝንሽም እንርዳት plzzz ተረጋግተሽ አናግሪኝ

ምን የጉዳቶ መንስዔ ማን ሆነ እና ምነው አልሞት አለቻቹ እንዴ ስትለው"

ከተቀመጠበት ተነስቶ ማኪ ይብቃሽ። የምትውጃት ከሆነ እናውራ ቁጭ በይ
እንደምን ቁጭ አለች።

""ማኪ እውነት እኔም የዛን ቀን ስንጨቃጨቅ የሰማቹክ ቀን ነው ያውኩት ምን የነገረኝ ነገር የለም።

እንደማሾፍ ብላ እረ ኪሩቤል ላንተ ሳይነገር የሄን ሁሉ ያስባል ማለት የማይታመን ነው።ግን እንዴት በቆየ ነገር ላይ ያውም የተማረ አይደል ለበቀል ......omg ያውም በሀኒ

ማኪዬ ሙች ምን አላቅም። በርግጥ አሁን ግን በጣም ታሞል ወደ መፍትሄው ብለው ብዙ አወርተው አንድ ነገር ላይ እንደሚደርሱ ተነጋግረው ተለያዩ

በማግስቱ የቲጂ ልደት ስለሆነ ፓርቲ ካልውጣን ብለዋት ደስ ባይላትም አንዶ ልብስ አንዶ ደሞ ፃጉሯን ሜካፖች በትብብር አስውበው ይዘዋት ውጡ ሀኒ የለበሰችው ከራት ልብስ አልፎ ለቀለበት የሚደረግ ልብስ ነው።

ሆቴሉ እንደደረሱ ሀኒ ግቢ እኛ ኬክ እናምጣ ብለዋት ሂድ ሀኒም ወደተባለው ለመግባት ስትል ....

ይቀጥላል...


share



share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ሕገ-ደንብ
ከጥቁሩ ሰሌዳ...
ከጨቅሎች ፊትለፊት፤
እንደ'ዚኽ ተጻፈ...
ከጨዋታው በፊት።
"በተሰጣችኹ መብት...
እውነትን መስክሩ
ሐቃችኹን አውሩ! "
ብሎ እንዳ'ሠመረ፤
"ሕጉ ለእኔ አይሠራም!"
ብሎ ተናገረ።

#የሞት_ጥቁር_ወተት
@Write_Event
@Write_Event
#Tesfahun kebede
.... 🌹🌹🌹🌹
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል ይሁንላችሁ🌺🌺🌺🌺🌺
Forwarded from የብዕር ዕንባ 🀄️📝 (ቃል ለ ቃል)
እንኳን ለ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች

ቀን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን!

join---->
@poem06
@poem06
@poem06


Share---->@poem06
@poem06
@poem06
""""ፍቅር ና በቀል"".
የመጨረሻው ክፍል
.
ሆቴሉ እንደደረሱ ሀኒ ግቢ እኛ ኬክ እናምጣ ብለዋት ሂዱ ሀኒም ወደ ሆቴሉ ስገባ ጨለማ ነው። ውስጦ ብፈራም ግን ከመግባት አልገደባትም ሞባይሏን አውጥታ ላይት ልታበራ ስትል ሞባይሏ የለም ኡፍፍፍፍ እያለች ትንሽ ከተራመደች በኃላ ጨለማው አስፈራት ወደ ኃላ ልትመለስ ስትል ያደረገችው ቀሚስ ጠልፏት ልትውድቅ ስትል የሰው እጅ መዳፍ ላይ ውደቀች ለመለየት ብትጥርም ግን ለተውሰነ ሰኮንዶች ከእጅ ላይ ሳትነሳ ቆይታ thanks ብላ እንደመላቀቅ ስትል ሁለቱ ባሉበት። ላይት በራ ሌላውን ጨላማ እንደሆነ ቀና ስትል ኪሩቤል ነው። አይኖቾን ጨፍን ገለጥ አድርጋ አመሰግናለሁ በድጋሚ ብላ ልትሄድ ስትል ..
እሱ በለሰለሰ አንደበት ሀኒዬ እያለ አይኖቹን ማንከራተት ጀመረ።
የኔ ያንተ ነገር አብቅቷል ለምን ትከተለኛለክ ልቤን ላክምበት ኪሩ በፈጠረክ ልለምንክ ተወኝ ይብቃኝ። ስቃዬን አታብዛው። እያለች አይኖ ላይ የታዘሉ እንባዎቾ መውረድ ጀመረ።

ሀኒዬ አንድ እድል ብቻ አውቃለው ግን አሁን ለምን እንዳረኩት ግራ ነው የገናኝ ከልጅነቴ አሁን ያለኝ ስሜት ላንቺ ይበልጣን plzz ባሳለፍናቸው የፍቅራት ጊዜ ልለምንሽ ሀኒ ብሎ ውደስሯ ተጠጋት።

ኪሩ ስታ አፏን አፍኖ አውቃለው ዛሬም ልብሽ ውስጥ አለው። አንቺ ጋር ያለው ስሜት እኔም ጋር አለ። እመኝኝ በደስታ እንኖራለን ከልቤ ነው የማፈቅርሽ ያለፈውን እርሽው ይጎዳኛል ብለሽ እንዳታስቢ ...
ዝም ብላ እያየችው አይኖቾ ያነብ ነበር እንባዋን እየጠረገ
ካንቺ የእንባ ዘለላ ማየት አልፈልግም በፍቅርሽ አሸነፍሽኝ ማሪኝ አንቺ ማለት ለኔ የእናቴ የእህቴ ምትክ ነሽ ሚስቴ የልጆቼ እናት ብቻ ሳትሆኝ

ይህኔ ሁለቱም ተላቅሰው ተቃቅፈው ተላቀሱ ከላዬ ላይ አንስቶ ተበርክኮ #ታገቢኛለሽ ..
የደስታ እያነባች ያለጥርጥር ብላ እጆን ዘረጋችለት ይህኔ መብራቱ በራ ያኔ አይኖቾን ጨፍና ገለጥ ስታደርግ ቤቱ በሰው ተሞልቶል ጥግ ጥግ ከያዙበት በጭብጨባ ና በፉጨት ቤቱ ቀውጠ ዞር ስትል አባት እናቷ ጓደኞቾ አማን የኪሩቤል አባት ሁሉም ነበሩ።

በርግጥ የትግስት ልደት ነው።
እሷን ሰርፕራይዝ ለማድረግ የተደረገ ነው። ቀለበቱን ካደርገላት በኃላ ቤተሰብ እንዴት እንደመጡ ግራ ስለገባት ጓደኞቾን እንዴት እንደሆነ ስጠይቃቸው።

ኪሩቤል እና አባቱ ይቅርታ አባትሽን ጠየቁ አባትሽም ይቅርታ ጠይቁ አየሽ በቀልን በፍቅር ሲለውጥ ምንኛ ደስታ እንደመጣ
የሚገርመው አለች ትግስት አባትሽ የተነገሩት አባባል እውነት ነው #ጣት_ገማ_ተብሎ_አይቆረጥም_ምን ላድርግ አንድ መጥፎ ልጅ ነው ለዚ ያበቃን ይቅር በሉኝ ብሎ ኪሩቤል ላይም አባቱላይም እግር ስር ውደቁ አየሽ ይቅርታ ትልቅ ነገር ነው። መቼም እኛ ሰው ስንባል ጠላቴ ነው። መቼ ልበቀለው ማለት እንውዳለን እንጂ በፍቅር ብንለውጠው ምንኛ ደስታ ነበር።

ግን እንዴት ሊሳካ ቻለ ብላ በግርምት ስታያቸው። አይናቸውን አማን ነው ለዚ ሁላ ነገር።
ሀኒ እየሳቀች ማኪ ብላ አየቻት።


ማኪ ባክሽ ላንቺ ስል ነው እንጂ በፍቅር አንድ ላይ ልንሆን እንዳይመስልሽ ስትል
አታፍጡብኝ ብላ ውደ ከትምህርት ቤት የትግስትን ልደት ሊታደሙ የመጡ ነበር። እነሱጋር ሄደች።

ሀኒ አማን ጠርታ በጣም አመሰግናለው ከልቤ ብላ ተጠመጠመችበት
""ግዴታዬ ደሞ ጓደኖችሽው ናቸው።
ትግስት ሜሮን ሀኒ አማን አብረው እንዳለ ።
ኪሩ አጠገቦቸው ደርሶ ማኪስ ሲላቸው .
ሀኒ እየሳቀች አማንን አይታው እሱን ጠይቀው
...
አማን ወይ ሀኒዬ የታረቅን መሰለሽ እንዴ ላንቺ ስትል ነው። እየሳቀ ሜሮን ድምፃን ከፍ አድርጋ። """ማኪ ነይማ አማን ይፈልግሻል አለች ሰው እየሰማ .

ማክድ ተናዳ ብመታት ምንኛ ደስ ባላት ።
ቲጂ ማጣው ብላ እስራዬል ጋር ሄደች የኪሩቤል አባት የሀኒ እናት እና አባቷ ተቀምጠው ይጫውታሉ።

እንደምን ማክዳን አስመጥታ ማኪ ትውጂዋለሽ ፍቅረኛ የለሽም ይቅር ተባባሉ ፍቅራቹ ይታደስ ማክዳን ና አማንን መሀል አስቀምጠው ኪሩቤል ና ሀኒ ለሁለት ከግራ ከቀኝ ይነግሯቸዋል ማኪ ግን አይሆንም የእህትነት ፍቅር ሊኖረኝ ይችላል ስትል
""ሀኒ ተናዳ ማኪ በጣም እንደምትውጂው አሁንም ድረስ እንደምታስቢው አውቃለው ልብሽ የሚያስበውን ተናገሪ
ፍቅር ይቅር ባይ ነው ስትይኝ አልነበር እስቲ እይኝ እኛን ብዙ ነገር ነበር። ደሞ በኛ ምክንያት ነው የተለያያቹት ለምን ህሊናዬን እረፍት እንዲነሳኝ ታደርጊያለሽ


ማኪ አማንን እያየች ከናፍሮቾን እየነከሰች አማን ስትል
እየሳቀ አውቃለው የልብሽን ብሎ በደስታ ተቃቅፈው ይስቁ ጀመር።

እስራኤል መድረኩ ላይ ወቶ መልክት ነበረኝ። ሲል ሁሉም ጫውታቸውን ወሬውን ገታ አድርገው ያዩት ጀመር።
ምን ሊል ነው ብለው በጉጉት ሲጠብቁት

""ቲጂዬ እንኳን ተመለድሽ hBD ለማት ነው። ሲል ሁሉም ሳቁበት ሀኒ የቀድሞ ጫውታዋ ተመልሷል ፈጠን ብላ ውንድሞ ጋር ደርሳ
ማይኩን ተቀብላው
"ይቅርታ ማለት የፈለገውን እኔ ልተንፍሰው ስትል

ሁሉም አዎ ይነገረን ብለው ባንድ ድንፅ ሀኒ ሀኒ የክፍሏ ልጆች 1.2.3 ማለት የፈለገው ....ሲሉ
""ቲጂዬ አንዴ ውደዚ ትመጪ
ቲጂም እየሳቀች ሄደች።

#ታገቢኛለሽ ሊላት ነው ሁሉም
እስራዬል እያሉ ሲያፋጩ ካላመናችሁኝ ስትል .....ኪሱን እንፈትሽ

በሀኒ ሁኔታ ሁሉም ተገርመዋል

ተቀበላትና አንዴ ዝም በሉ ብሎ ከdj ጋር ተጠቃቅሰው መብራቱን አጥርተው ትግስት ላይ ብቻ ብርሀን እንዲታይ አድርገው የውንዲን.ማክ ታገቢኛለሽ ወይ የሚለውን አስከፍቶ ተበርክኮ ጠየቃት ያኔ ሁሉም ሁሉም በጭኸት በጭብጨባ ቤቱን አቀለጡት። እሽታዋን አሰምታ አጠለቀላት። ሻፓዮን ተከፍቶ በደስታ ባህር ይዋኛሉ። ቤተሰብ ልጆቹን መርቀው ውደ ቤት ሊሄዱ ሲሉ። የሀኒ አባት አንዴ ንግግር ላድርግ ብለው መድረክ ላይ ውጡ
ዛሬ በእውነቱ ዳግም የተውለድኩ ነው የመልለኝ ከጥላቻ ከበቀል #ፍቅር የተማርኩበት ነው። እኔም የማውቀውን ልምከራቹ ልጆቼ
ፍቅር ልክ እንደውሃ ምንጭ ነው፤ ከራስ ፈልቆ ሌላውን የሚያጥለቀልቅ።
""""ፍቅር ልክ እንደጸሃይ
ብርሃን ነው፤ ከልብ ፈንጥቆ ለሌላው ብርሃን የሚሆን፤
እናም እናንተ ለምታፈቅሩት ብርሀን ናቹ
ማፍቀር ከባድ የሚሆንብ ለራሳችን ፍቅር ስለሌለን ነው፤ ልባችን ፍቅርን ስላልተለማመደ።

""""ለአለም ብርሃንን መስጠት፤ ለጸሃይ ስራዋ አይደለም፤ አያለፋትም፤ ምክንያቱም ተፈጥሮዋ ነውና።

እኛም በውስጣችንን ፍቅርን
ከኮተኮትነው፤ አለምን ሁሉ መውደድ ልፋት አይሆንብም፤ ሳናውቀው ፍቅር ከኛ ወደሌላው
እንደጨረር ይፈነጥቃል እንጂ…. ልክ እንደ ጸሃይ ብርሃን ይበራል

""የፍቅርም ምንጩ እኛው እራሳችን ሆነን ሳለን... ፍቅርን የማያፈልቅ ሌላ ጉድጓድ ስንቆፍር፤ ጅንበራችን እንዳትጠልቅ።
""ፍቅርን ከፍቶ ፍቅር መፈለግ ሞኝነት ነው።
""ለሁላችሁም ከማስመሰል ከውሸት የነፃ ንፁ ፍቅር ይስጣቹ"""
እናንተ ተጫውቱ እኛ ሽማግሌዎች እናዝግም ብለው ተሰናበቱ
እናሱም ደስታቸውን ቀጠሉ.

____{ተፈፀመ}_______
ከማውቀው.ላካፍላቹ

♡♡አንዳንድ ሰዎች #ፍቅር ልክ እንደ እቅፍ አበባ ለሌላው የሚሰጥ ነገር እንደ ሆነ ሲያስቡ ሌሎች ደግሞ በላይህ ላይ የተጣለ የማይረባ ግን
@Write_Event
​​#ወንድሜ!"
➊.ፍቅር የለም ከማለትህ በፊት፣ እኔ ውስጥ ፍቅር አለ ወይ? ብለህ ፈትሽ!
:
➋.ሚስት የምትሆን ሴት የለችም ፣ ከማለትህ በፊት እኔ ባል መሆን እችላለሁ ወይ? ብለህ ራስህን መርምር!
:
♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡

#እህቴ!"
:
➊.ወንድ እንጂ ባል የለም ከማለትሽ በፊት፣ እኔ ጥሩ ሚስት መሆን ችላለሁ ወይ? ብለሽ ራስሽን ጠይቂ!
:
➋.ጥሩጉዋደኛ የለም ከማለትሽ በፊት እኔ ጥሩ ጉዋደኛ መሆን እችላለሁ ወይ? ብለሽ አስቢ!
:
♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡

#አዎን_ወዳጆቼ
:
ማንም ሰው ጥሩ ከሆነ ጥሩ ነገሮች ሁሉ ከሱ መራቅ አይችሉም።

💔 መልካም ቀን ይሁንላችሁ! 💔
​​#ወንዶች_ተሰልፈው_እግዜር_ጋር_ቀረቡና_ቅሬታቸውን_አቀረቡ....


✍️በአሌክስ አብርሃም

☞ወንዶች ተሰልፈው እግዜር ጋር ቀረቡና ቅሬታቸውን አቀረቡ....‹‹ እኛ ለፍተን ጥረን ግረን ላባችንን ደማችንን ጠብ አድርገን ባመጣነው ገንዘብ ሴቶቻችን እቤት ተጎልተው፦

ይበላሉ ይጠጣሉ ፤
ይለብሳሉ ይዋባሉ
ሶፋ ላይ እየተንፈላሰሱ ፊልም ያያሉ !!
እኛ በስፒል እንደ ተወጋ ፊኛ እየሞሸሽን እነሱ ዝናብ እንደጠገበ ዱባ ይደነድናሉ ..
በቃን እነሱን መሸከም .....›› አሉ፡፡
እግዜር ታዲያ ምንይደረግላችሁ ሲል ጠየቀ ....
☞ወንዶቹ ቀጠሉ‹‹ጌታ ሆይ ድፍረት አይሁኑብና ከአሁን ጀምሮ ቦታ እንቀያየር እነሱ የእኛን ቦታይውሰዱ እኛ የእነርሱን ቦታ እንውሰድ››

☞እግዜር ‹‹ከመጭው ሰኞ ጀምሮ ቦታ እንድትቀያየሩ ወስኛለሁ››... አለ ፡፡

☞ወንዶች በደስታ ፈነደቁ!

☞ሰኞ.... ሚስቱ የባሏን ጎን ደቃችውና
‹‹የስራ ሰአት እየደረሰ ተጋድማሃል ተነስቁርስ ስራ ››
☞ወንዱ ደንግጦ ተነሳና ወደ መፀዳጃ ቤት ሂዶ ሽንቱን ሊሸና ሲልነገሩ ሁሉ ተቀያይሯል ፡፡ቀስ ብሎተቀመጠና ሸና፡፡

☞ኩሽና ገብቶ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረ ‹‹ እንዲህ ነበር የምቀሰቅሳት ለካ› እያለ፡፡

☞እንደምንም ቁርስ ሰርቶ አቀራረበ ሚስት ተነስታ ሸሚዜን ተኩስ ጫማየንም ወልውል ቁርስ እስከምበላ›› አለችና ቁርሱን መብላት ጀመረች ...

☞‹‹ኤጭ ምንድነው ይሄ ሁሉ ጨው ምላስ የለህም አትቀምስም ›› ብላ በብስጭት ሳህኑን ወርውራው ልብሰዋን ለባብሳ ቦርሳዋን አንስታ ወጣች ፡፡

☞ቁርስ የተበላበትን ሰሃን ለማጠብ አልጋ ለማንጠፍና ቤት ለመጥረግ ሲንደፋደፍ የመሳ ሰአት ደርሶ ሚስት ከተፍ አለች ምሳ የለም!ብስጭት ብላ
‹‹ እዚህ ተጎልተህ ቴሌቪዥን ላይ ስጣፈጥ በየጎረቤቱ እየዞክ
ወሬ ስታወራ ምሳ ሳተሰራ ሰአቱ ሄደ ምናይነት ድድብናነው ››
አበደች

☞ባል ተሸማቀቀ

☞ራት ሰአት ላይ ሚስት ስትመለስ
አንድ ሁለት ብላ ሞቅ ብለዋት ነበር የመጣችው ....

☞ባል ድክም ብሎት ወገቡ ተንቀጥቅጦ መተኛት አምሮት ‹‹ እስቲ ቆንጆ ቡና
አፍላ›› አለችው ...

☞እንደምንም አፈላ ›› ቡና ተጠጥቶ እንደተኙ ምንድነው ሽንኩርት ሽንኩርት የምትሸተው ተነስና ታጠብ ›› አዘዘች
ሚስት....

☞ባል ማልቀስ እየፈለገ ተነስቶ ታጠበ....ልክ ጋደም ከማለቱ ሚስት ትነካካው ጀመረ! ምንም ነገር አላማረውም
ድካሙ ...እንቅልፍ ብቻ ነበር የፈለገው ..በየት አስተኝታው!

☞ጭራሽ ሲነጫነጭ ‹‹ ምነው ሌላ ትዳር አማረህ ዙር እባክህ እግርህን ክፈት....›› ሂሳቡን!!፡
☞ሌሊት 3 ጊዜ ....ጠዋት እንደገና
ተነስቶ ቁርስ ስራ.....እየተማረረ ....

☞ማክሰኞ ጠዋትሰውየው እግዜር ጋር ሲሄድ ሌሎች ብዙ ወንዶች ቀድመውት ደርሰው ነበር

☞....እግዜር ጠየቀ ‹‹ደግሞ ዛሬ ምን ሆናችሁ‹‹ አይባለፈው የተየቅነው ነገር በስህተት ነው ወደ ቦታችን እንመለስ
ሚስቶቻችንም ባል መሆናቸው ይቅርና
ወደ ሚስትነታቸውይመለሱ››

☞እግዜር ‹‹ጥሩ ሌሊት ሚስቶቻችሁ
ጋር ግንኙነት ፈፅማችኋል››ሲል ጠየቀ ...

☞ወንዶች- ‹‹አዎ በጣም ያስመርራል ለካ......›› ሲሉ መለሱ፡፡

☞እግዜር ‹‹ እንግዲያውስ ሁላችሁም በፈፀማችሁት ግንኙነት ስለ ፀነሳችሁ ወደ ወንድነታችሁ ለመመለስ ዘጠኝ ወር ጠብቁ›› ጨርሻለሁ!! በማለት አሰናበታቸው፡፡

#ረጅም_ እድሜና ጤና ለእናቶቻችን ይሁን!"

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
በመንገድህ ሁሉ ለለመነህ የምትሰጠው ነገር አታጣም ፤ ቸር ለመሆን ሃብት እስክታገኝ አትጠብቅ።
😊አንዳንዶች ካንተ የሚፈልጉት ፈገግታህን ነው
🤚አንዳንዶች ሰላምታህን፤
አንዳንዶች ጊዜህን፤
🤔አንዳንዶች ሃሳብህን፤
💪አንዳንዶች ድጋፍህን፤
👫አንዳንዶች ጓደኝነትህን ነው ።
ሁላችንም ለሌላው የምናካፍለው ብዙ ነገሮች አሉን (ከምንም በላይ ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች) ፤ ያለተጠቀምንባቸው ሰስተን ሳይሆን አለን ብለን ስላላመንን ይሆናል ።
ሌላው ይቅርና ፈገግታ እና ደስታህ ፤ እንኳን የምታውቀውን ሰው ይቅርና
የመንገደኛውን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ ብርቱ ሃይል አለው።
🤔የሚለኩሳቸው ያጡ ብዙ ሻማዎች አሉ፤ ለኳሾቹም ሻማዎችም ግን እኛ ነን፤ ክብሪቱ ደግሞ ፍቅር ነው።
🌞ስለዚህ ጀግናዬ የራስህን ሻማ ለኩስ ለሌላውም 🌟ብርሃን ሁንለት።
የስጦታ ቀን ይሁንልን!!!🌅🌆
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ !!!

src: ምክረ-አዕምሮ

መልካም ቀን ተመኘሁ!!!


@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🌿እርቃን ማንነት!

💫ሰው ሌሎች ሰዎች ስለሱ መጥፎ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ይፈራል። እሱን በተመለከተ ሰዎች ጥሩ ሲናገሩ ይደሰታል፤ ምክንያቱም ስለ ራሱ ያለው እውቀት ሌሎች ስለሱ በሚሰጡት አስተያየት ላይ የተመሰረተ ነው። ስለራሱ ቅጽበታዊ የሆነ እውቀት የለውም፤ ራሱን የሚያውቅበት ቀጥተኛ ተሞክሮ የለውም። ራስን በቀጥታ የማወቅ ተሞክሮ ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ከራሳችን_ለማምለጥ ስለምንሞክር ግን አይከሰትም።

💫አይምሮን ለመጋፈጥ የመጀመርያው ዘዴ ሌሎች ስለሚሉት ወይም ለሌሎች እንዴት ሆነን መታየት እንደሚኖርብን አለመጨነቅ ነው። አንድ ሰው መሰረታዊ እሱነቱን በቀጥታ መጋፈጥ አለበት። ለብቻው ሆኖ አይምሮውን በመክፈት ውስጡ ያለውን ነገር መመልከት አለበት። ይህ የድፍረት ተግባር ነው። ከውስጥ ወዳለው ሲዖል ለመግባት የሚያስችል የድፍረት ተግባር....። እርቃን ማንነትን ለመመልከት የሚወሰድ የድፍረት እርምጃ ነው። ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል።

📖 ፦ የነፍስ መንገድ
••●◉Join

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"ትንንሽ ሀሳቦች ሁሌም ትንንሽ ናቸው ግን የትልቁን ቦታ ይይዛሉ" ይለናል አዘርግ የተባለ ደራሲ። ሰዎች ስለኔ ምን ያስባሉ ብሎ ከማሰብ በላይ ምን ትንሽ ሀሳብ አለ?

በዚህ አለም አንድ ነገር አትርሳ ዋናው አንተን ደስ የሚልህ ወንጀል ወይ መጥፎ ተግባር አይሁን እንጂ.....የምትሰራው የምትማረው አንተን ደስተኛ የሚያደርግህ ነገር ከሆነ እኮ ትልቅ ሀሳብ ነው! በትንሽ ሀሳብ አትጠመድ፤ አለዛ የትም አትደርስም!

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
#የፀሐዬ ዮሐንስ

ተበድየስ ይቅርታ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ
ተበድየስ ማርኝ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ

እንኳን ልልክ አማላጅ
እግረ አይረግጥም ያንችን ደጅ

ተበድየስ ይቅርታ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ
ተበድየስ ማርኝ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ

እንኳን ልልክ አማላጅ
እግረ አይረግጥም ያንችን ደጅ 2*

አፍቅረ ኖራለሁ-ስትይኝ ከርመሻል
ታምኘ ዘልቃለሁ-ስትይኝ ከርመሻል
ያኔ ባንደበትሽ ፅኑ ሰው መስለሻል
ቃልሽ የታጠፈው ዛሬ ምን ነክቶሻል

ከአካሌ መለየት መራቁን ስትመርጭ
ሸርተት እያልሽብኝ ከእቅፈ ስትወጭ
ልቤን እየከፈው ላሰናብትሽ እንጅ
ተከትየ አልመጣም ጥለሽኝ ስትሄጅ

በደል ያሸከረው ሆዴን ላታባቢ
የጨከነ አንጀቴን ችለሽ ላታባብይ
የማይሽር ጥላቻ በኔ ልብ አፍርተሽ
በእንባ መማፀኑን አታስብ ደፍረሽ

የት ነበርሽየት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ

ተበድየስ ይቅርታ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ
ተበድየስ ማርኝ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ

እንኳን ልልክ አማላጅ
እግረ አይረግጥም ያንችን ደጅ

ተበድየስ ይቅርታ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ
ተበድየስ ማርኝ አልልም
የቀረው ይቅር እንጅ

እንኳን ልልክ አማላጅ
እግረ አይረግጥም ያንችን ደጅ 2*

ስታጠፊ ኖረሽ
ስታገስሽ ኖሬ
ስንቱን ግዜ አለፍኩት
ቀን በቀን መክሬ
ያንች ነገር ባይሆን
እየፈጁ ጥሬ
ደክመልሽ ነበር
እኔስ እስከ ዛሬ

ዕድሜ ሳይገደብ
ከልጅ እስከ አዋቅ
የበደለ ሰው ነው
ይቅርታ ጠያቅ
መቻሌ ሳያንሰኝ
የጥፋትሽን ሽመል
እንደው ምን አድርጌ
ይቅር በይኝ ልበል

ዛሬ ህልናሽ ወቅሶሽ ምንም ብትቆጭ
በደልሽ አጥሮሻል መቼም
ከኔ አትመጭ
የፀፀት መንገዱ ጎዳናው ከታየ
ምህረት ባልነፍግሽም አንች ግን ዘገየሽ

የት ነበርሽየት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
የት ነበርሽየት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ...

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
comment
@kaliye06
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
#እዮብ_መኮንን
#ደብዝዘሽ
መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ፣ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንች በላይ እዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን
ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ፣ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንች በላይ እዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ለኔው ጥቅም በኔው ሰው ተመክሬ
አላውቅም አብልጬ፣ ከልብ አምርሬ
አሁን ለምን ገባኝ፣ ባንቺ ሲመከር
ያሉግንን ብለሺኝ፣ የምፍጨረጨር ከኔ ነው፣ ወይ ካንቺ ነው
ልቤን ለጅሽ፣ የሰጠነዉ
ማኩረፍ የኔ ነበር አልሸፋፈንኩም
ካንቺ ጀምሬ ግን አልተቀየምኩም
ምንድነው ብርቅ ሆኖ የሚያስወድደኝ
ሁሉሺን እንዳደንቅ የሚያስገድደኝ የት ብለው፣ የት ቢሄዱ
መስፈርት የለም፣ ከወደዱ መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን
ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ፣ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንቺ በላይ አውቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ተቀይሩዋል አይኔ፣ ወዷል መልክሺን
ስመዝኑሽ ያደንቁዋል፣ ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ አይነት ብቻ
ባይም ልቤ አያምንም፣ እንዳለሽ አቻ የት ብለው፣ የት ቢሄዱ
መስፈርት የለም፣ ከወደዱ ተቀይሯል አይኔ፣ ወዷል መልክሺን
ሲመዝኑሽ ያደንቋል፣ ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ አይነት ብቻ
ባይም ልቤ አያምንም፣ እንዳለሽ አቻ ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆወቹን አስናቅሻቸው


#share #share #share
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
comment
@kaliye06
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
አነቃቅ እና አስተማሪ የሆኑ ታርኮችን ወደ እናንተ ስናደርስ ነበር። ከበፊቱ በተሻለ መልኩ አዳድስ ታርኮችን ይዘን መተናል አብሮነታችሁ አይለየን።
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
comment
@kaliye06
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
​​━━━━━✦🌺✦━━━━━
❤️ የቃልኪዳን ገጾች❤️
🌹@Write_Event🌹┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄

😭የማይሽር ጠባሳ💔

ክፍል አንድ

እውነተኛ ታሪክ

ታሪኬ የሚጀምረው ገና የሁለት ወር ህፃን እያለው እናቴ ለእንጀራ እናቴና ለ አባቴ እኔና ታላቅ ወንድሜን ጥላን የጠፋች እለት ነበር
አዎ ገና የሁለት ወር ጨቅላ እያለው በእንጀራ እናቴ እጅ እድገቴን ጀመርኩ
በርግጥ አባቴ ልጆቹን ወዳጅ ስለነበር እንጀራ እናታችን እኛን ለመጉዳት መንገድ አልነበራትም
ውልደቴም እድገቴም በ ወለጋ ነቀምቴ ነበር አባታችን የራሱ ገቢ ነበረው እናታችን ጥላን ብጠፋም ታላቅ ወንድሜ እጅግ ይወደኝ ስለነበር አንድም ቀን እንድከፋ አይፈልግም ይበልጥ ከአባቴና እንጀራ እናቴ ወንድሜ ይጠብቀኝ ነበር
ከዛ ባሻገር የእርሻ ቦታም ነበረን
አባቴ ከመደበኛ ስራው ባሻገር የእርሻ ቦታውን ዘወትር የመጎብኘት ልምድ ነበረው
ግን ከለታት በአንዱ ቀን ከስራ መልስ ወደ እርሻ ቦታ የመሄድ ልምድ ስላለው እንደ ልማዱ ወደ እርሻ ቦታ አመራ
ነገር ግን የዛሬው የእርሻ ቦታ ጉብኝቱ የህይወቴን ሁለተኛ ምእራፍ ገና በለጋነቴ በጨቅላነቴ እንድጀምር አረጋት
አባቴ በእባብ ተነድፎ በሰዎች እርዳታ እቤት በገባ በ3 ቀን በህይወት አጣነው
ነገር ግን አባቴ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ለእንጀራ እናቴ ቃል አስገባት
"ልጆቼን በምድር ሰጥቼሻለው በሰማይ እቀበልሻለው "
ይህ ቃል በልጅነት አእምሮዬ ተፅፎ ቀረ
በወቅቱ ወንድሜ እንጀራ እናቴ ስታለቅስ እሱም አብሮ እያለቀሰ ነበር እኔ ግን ልጅነቴ ምኑም እንዲገባኝ አላደረገም ነበር
እንጀራ እናቴ ከሌላ የወለደቻቸውና በትዳር ላይ የሚገኙ ሁለት ሴት ልጆች ነበርዋት
አባቴ ከሞተ በኃላ ግን እንጀራ እናቴም ጤንነት ስለማይሰማት ልጆችዋ ወሰድዋት ።ይህ 3ኛው ምእራፍ የኔና የወንድሜ ነበር እኔና እኔን በ6 አመት ልዩነት ያለን ወንድሜ ብቻችንን ኦና ቤት ታቅፈን ቀረን
የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት ቤት ውስጥ ኑሮአችንን መግፋት ጀመርን
ወንድሜ ከኔ የተሻለ ስለነበር ቀን ቀን ምግብ ፍለጋ ሄዶ ማታ ለሱ ሳይበላ ለኔ ይዞ ይመጣ ነበር
በዚህ ሁኔታ ግን ስላልቻልን ጎረቤት ተጠጋን እሱ በእረኝነት እኔ ደግሞ እንደ ልጅነት ልንኖርበት
አዎ የተጠጋናቸው ሰዎች ያላቸው ስለነበሩ ወንድሜ ለኔ መስዋት በመሆን ደሞዙ የኔ በሳላም በደስታ እዛ ቤት መኖር ብቻ ነበር
እንዲ እንዲ እያልን ለአንድ አመት ኖርን
በመሀል የምንኖርባቸው ሰዎች አዲስ አበባ በትዳር የምትኖር ትልቅ ልጅ ነበራቸው
በተሰብዋን ለመጠየቅ በምትመጣበት ሰአት እኔ አይንዋ ውስጥ ገባው
ስለ እኔ ጠየቀች ሁሉንም ተረዳች አዘነችም ወስዳም እንደምታስተምረኝ ቃል ገባች
ወንድሜም በገጠመኝ እድል ደስተኛ ስለነበር ሳያቅማማ ፈቀደ
እኔም ልጅነቴ እንዳለ ያገኘውት እድል አስደስቶኝ ስለ እኔ መሰዋት የሚሆነውን ወንድሜን ትቼ ወደ አዲስ አበባ ገሰገስኩ......

ታሪኩ እንዲቀጥል ♥️

ይቀጥላል......


❤️ ❤️
❤️ ❤️
🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
comment
@kaliye06
◌◉◎◦◈◦◎◉◌