ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ሀገር አዕምሮ ውስጥ የሚወለድ የጋራነት ሃይል ነው ። ማሰብ የማይችል ፍጡር ሀገር አይኖረውም ። እንስሶች ሀገርም ዜግነትም የላቸውም ። ጭላዳ ዝንጀሮ ፣ ቀይ ቀበሮስ እንዳንል ግን ሰው ማሰቡን ሳይኖረው ሀገር አለኝ ቢል እየዋሸ ነው ።
🔻 ሀገር የእሳቤዎች ቅኔ ናት !!

🚀 #ቡርሃን አዲስ
@write_event
👍1
1888🔥
በታርክ መዛግብት ስማቸው ሳይፃፍ ለቀሩ...ስላልተዘከረላቸው...ስላልተዘመረላቸው.. ክብርን እና ውዳሴን ሳንቸራቸው ... ጨቋኝ ባርነት ትላንት ላይ በነፃነት ስለለወጡልን..ዛሬ ቀና እንድንል ህይወታቸውን ሰውተው ላለፉት ጀግኖች ትልቅ ክብር አለን።

አድዋ🔥

እኛ እና የኛ

- @write_event
2🔥2👍1
1
ከዛሬ 46 ዓመታት በፊት የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ገብቶ የነበረውን የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት በማስወጣት ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ማወለብለቡን ታሪክ ያስታውሳል፡፡

የካራማራ ድል ከደርግ ውድቀት በኋላ በመንግስት ደረጃ የማይከበር ድል ቢሆንም የቀድሞ ሰራዊት አባላትና ግለሰቦች በተነሳሽነት እያከበሩት ነው፤ በዓሉም ብሄራዊ በዓል ሆኖ በመንግስት እንዲከበር ይፈልጋሉ፡፡

ሶማሊያ በ1952 ዓ.ም ከጣሊያንና ከእንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ነፃነቷን ባገኘች ማግሥት የሀገሪቱ መሪዎች "ታላቋ ሶማሊያን እንገነባለን" የሚል ህልም ማለም ጀመሩ፡፡ በዚህም ምክንያት በ1953 ዓ.ም የድንበር ላይ ትንኮሳ ጀምረው በ1956 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብድረሺ አሊ ሸርማርኬ እንዲሁም በ1969፣ በ1972 እና በ1973 ዓ.ም ደግሞ ፕሬዝደንት ዚያድ ባሬ (ሜጀር ጀኔራል) የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ እንዲገባና ወረራ እንዲፈፅም ሰራዊታቸውን አዘዙ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ደግሞ ሰርጎ ገቦችን አስታጥቆ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በማስገባት ፈንጅ በማፈንዳት፣ ድንገተኛና የደፈጣ ጥቃቶችን በመፈፀም እንዲሁም ባለስልጣናትንና ሰላማዊ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ ለኢትዮጵያ ሰላምና ልማት መሰናክል ሆነው መቆየታቸውንም በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪዎች ይገልጻሉ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ የሶማሊያ ወረራዎችና ጥቃቶች በኢትዮጵያ አሸናፊነት ቢመለሱም ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን አለመቻሉ ይገለጻል፡፡ በተለይ የ1969 ዓ.ም የዚያድ ባሬ ወረራ የኢትዮጵያ ድንበር በምስራቅ በኩል እስከ 700 ኪሎ ሜትር እንዲሁም በደቡብ በኩል ደግሞ እስከ 300 ኪሎ ሜትር በሶማሊያ ሰራዊት እንዲደፈር፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዲሞቱና እንዲቆስሉ፣ አካል ጉዳተኛ እንዲሆኑ በአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በርካታ የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ያደረገ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ በወቅቱ በብዙ የውስጥ ችግሮች (የመሐል አገር የሥልጣን ሽኩቻ፣ የነጻነት ጠያቂዎች በሃገር ቤት፣ የተለመደው ድህነትና ረሀብ …) ተወጥራ ስለነበር የዚያድ ባሬ ወረራ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባት ነበር ይላሉ የታሪክ ጸሐፊያን፡፡

ሶማሊያ ኢትዮጵያን ለመውረር ሰፊ የሰው ኃይል፣ የትጥቅ፣ የስንቅ፣ የሥነ ልቦና ዝግጅት ስታደርግ ቆይታለች፤ኢትዮጵያ ግን በውስጣዊ ችግሮች ከመወጠሯም ባሻገር በወቅቱ የነበራት የሰራዊት ቁጥርና ጥራትእንዲሁም የትጥቅ አቅርቦት እጅግ የተመናመነ እንደነበርም ነው የሚገለጸው፡፡

300ሺ የሚሆን ሕዝባዊ ሰራዊት በአጭር ጊዜ ሰልጥኖ ለውጊያ የተሰለፈ ሲሆን ፤ የኩባና የደቡብ የመን መንግሥታት ጦራቸውን ይዘው ከኢትዮጵያ ጎን መሰለፋቸውም ይታወሳል፡፡ ሶቭየት ኅብረት በጀኔራል ፔትሮቭ የሚመሩ ወታደራዊ አማካሪዎቿን ለኢትዮጵያ ረዳት አድርጋ ወደ ኢትዮጵያ መላኳንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከኢትዮጵያ በኩል ተሰልፈው ህይወታቸውን ላጡ ኩባውያን ወታደሮች በአዲስ አባበ መታሰቢያ ተሰርቶላቸዋል፡፡

የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት የማባረሩ ዘመቻ በሐምሌ ወር 1969 ዓ.ም ተጀመረ፡፡ ኢትዮጵያውያን በምድርና በአየር አስደናቂ ገድል ስለመፈጸማቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡ ዘመቻው እስከ የካቲት ወር 1970 ዓ.ም ቆይቶ የሶማሊያ ጦር በኢትዮጵያ ሰራዊት ተከቦ መፈናፈኛ ሲያጣ ለአሜሪካና ለሶቭየት ኅብረት የድረሱልኝ ጩኸቱን አሰማ፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሶማሊያን ጦር እያባረረ የሶማሊያን ድንበር ጥሶ ወደ ሃርጌሳ ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት ስለነበር ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈው የነበሩት የውጭ አገራት የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ግዛት እንዳይገባ ልመናና ተማፅኖ ጭምር ማቅረብ ጀመሩ፡፡

አሜሪካና ሶቭየት ኅብረትም ኢትዮጵያና ሶማሊያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ፤የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ሶማሊያ ድንበር ጥሶ እንዳይገባና የሶማሊያ ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር በ24 ሰዓታት ውስጥ ጠቅልሎ እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የአሜሪካና የሶቭየት ኅብረት ጥሪ ተፈፃሚ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ሰራዊትም የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውለበለበ፡፡

በአሁኑ ወቅት ይህ የድል ዕለት ታዲያ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው አይደለም የሚሉ ወቀሳዎች አሉ፡፡በተለይ ዕለቱን ሳይቀር ብዙዎች የማያስታውሱት እንደሆነና መንግስትም ሰፊ ትኩረት እየሰጠው እንዳልሆነ ይነገራል፡፡

በወቅቱ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪዎች ሳይቀሩ እየተዘከሩና እየታወሱ አለመሆኑም ይገለጻል፡፡
____

ኢትዮጵያ ትቅደም !!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!!
Share💚💛
----------
join
@write_event
💚💛
@write_event
👍21
የአንድ አይኑን ብርሃን ያጣዉ ሚኖንጎ በክለቦች የአለም ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ ነዉ።

እ.ኤ.አ. በ 2002 የተወለደው ጆርጂ ሚኖንጎ የእግር ኳስ ህይወቱን ለመከታተል ሲል በአይቮሪ ኮስት የሚገኘውን መንደሩን ለቆ ተሰዷል። በሜጀር ሊግ ሶከር አሜሪካ በሲያትል ሳውንደርስ በአሁኑ ወቅት እየተጫወተ ነዉ።

እ.ኤ.አ. በ 2023 ግን ተስፋ አስቆራጭ ነገር በህይወቱ ላይ ተፈጠረ። ነገር ግን እርሱ ተስፋ አልቆረጠም ነበር። በአንድ አይኑ ላይ ባጋጠመዉ ኢንፌክሽን የአይን ብርሃኑን አጣ።

የአካል ጉዳተኛ ሆኖ ህይወቱን ለመምራትም ተገደደ። ኋላ ላይ ግን በአካል ጉዳቱ ከእግርኳስ አለም ሳይገለል መጫወቱን ቀጠለ። በአሜካዉ ክለብም የአራት አመት ኮንትራት ፈርሞ በአለም ክለቦች ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዉን አድርጓል።

"ይህ አካል ጉዳተኝነት አይገድበኝም" ይላል ሚኖንጎ።"


ሁለት አይኖች ካላቸው በተሻለ ሁኔታ መስራት እንደምችል አምናለሁ"

ሲል ይናገራል።

ከአይቮሪኮስት እስከ የአለም ክለቦች ዋንጫ ድረስ ህልሙን መፈለግ አላቆመም ነበር።

©ሸገር sport
JOIN

@write_event
@write_event
@write_event
1👍1🔥1
Channel photo updated
🔥 ተመልሰናል! 🔥
ከተወሰነ ጊዜ ዝምታ በኋላ እንደገና ወደ እናንተ ተመልሰናል።
ከዛሬ ጀምሮ በየቀኑ ጥራት ያላቸው ፖስቶች፣ አዳዲስ ሀሳቦች እና አስደሳች ይዘቶችን እናቀርባለን።
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከእኛ ጋር ለነበራችሁ እናመሰግናለን። ❤️
ዝግጁ ናችሁ? 🚀
4
"ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም። ህይወት እንደ ቡና በወተት ነው። ወተቱ እውነት ቡናው ውሸት ይሁን። ግን ይሄ ልዩነት በአንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ በአንድ በኩል ቡና በሌላው ወተት የለም። ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው። ህይወትም ውስጥ በቀኝ በኩል እውነት በግራ በኩል ውሸት የለም። ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነትና የውሸት ቅልቅል ነው።"

ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር
🍃🤝
🥰4
ለፈገግታ 😂

አንድ ጓድኛዬ የሁለት አመት ፍቅረኛው ታማበት ፀበል ነገር ይዟት ይሄዳል ወደ ገዳም!

እንደወሰዳትም "አንተ የseyጣን ነገር ነው  መለፍለፍ  ጀመረች ሳምንት እንቆያለን" ብሎ ደወሎ አሳወቀኝ!

በመጨረሻም በሳምንቱ ከፀበል መመለሱን ነገሮኝ  እንገናኝ ብሎኝ ተገናኝን...

ያው እኔም እንዳገኘውት እንዴት ሆነች ተሻላት ወይ ምናምን ብየ ጠየኩት!

"አዎ!...ግን  የሷን ነገር አታውራብኝ " ምናምን አለኝ

ነገሩ ግራ ሲገባኝ ምን ተፈጥረ? ምናምን ስለው ...መለያየታቸውን ነገረኝ!

ግራ ገብቶኝ የታመመች ልጅ ወስደህ ፀበል  አስጠምቀሃት (seytan ኬዙ ሲሻላት ) ለምን ተለያያችሁ?... ስለው

እሱም ቀጠለና "ባክህ ከፀበል ስንወጣ 'ይቅርታ መለያየት አለብን አለችኝ! ራሷ...'  እኔም ደንግጨ ለምን ? ስላት ...'አንተን የሚያፍቅርህ እኔ አልነበርኩም ሰይጣኑ ነበረ " አትለኝም መሰለህ"....ብሎ ነገረኝ ....

By Jah mac
😂

https://t.me/write_event
😁5
‎ሰራተኛ እያፈላለኩ በደላላ አንዲት  ልጅ አገኘው

‎አንገቷን እንደደፋች "ጋሽዬ እኔ የስራ ሆነ የሙያ ችግር የለብኝም ብቻ ‎ስራ እንዳልቆይ ተደግሞብኛል ፤ ሰርቼ እንዳልለወጥ አሰርተውብኛል" ምናምን ብላ ዘበዘበች


‎"ብሎ ነገር የለም እኔ ተረት ተረት አልወድም ድግምት ምናምን የለም " ብዬ ካለችው አምስት መቶ ብር ጨምሬ ቀጠርኳት

‎21 ቀን እንደሰራች
‎አንዴ

‎ጠረጴዛዬ ላይ አንገቴን ደፍቼ እየፃፍኩ አንድ ሶስቴ ስጠራኝ አልሰማ ብያታለሁ መሰለኝ
‎"ምን አባህ ይዘጋሃል ብላ"
‎ይዛው በነበረው ፔርሙዝ  አናቴን አለቺኝ

‎ተጮኸ። I think እኔ ነኝ የጮህኩት
‎ጎረቤት ተሰበሰበ ‎መቼ ፣ ማን እንደመታኝ በደንብ ያወቅኩት ከሁለት ቀን በኋላ ነው

‎መንፈስ ፣ ድግምት ፣ ተተብትቦብኛል የሚለኝ ሰው ሲገጥመኝ የጀመረውን አረፍተነገር ሳይጨረሰው ነው የማመልጠው

‎የሻሼን ፍንክት የቀመሰ ሰው በዚህ ነገር አይፈላሰፍም 😁

By Adhanom Mitiku

https://t.me/write_event
😁3
የጠቋር  ሚስት 😂

ጓደኛዬ አዲስ ሙሽራ ነው። ገና ስድስት ወሩ ነው ካገባ። የሆነ እሁድ ጠዋት ልጠይቃቸው ቤታቸው ስሄድ ይሄን ገንገበት ጓደኛዬን ባለቤቱ “ዳዲ” እያለች ስትጠራው ሰማሁ። ተወልዳ እስክታድግ በአንድ የአምበሳ ቆዳ ጫማ እየዳከረ ያሳደጋትን የአባቷን ስም እንደቀልድ ለስድስት ወር ባሏ መስጠቷ ግርም አለኝ። አጎቴ "ሴትና የቀበሌ ቤት የኔ ነው አይባልም" የሚለው እውነት ሳይሆን አይቀርም።

ቤታቸው የሄድኩት እሁድ ጠኋት ስለነበር “ቸርች ልንሄድ ስንል መጣህ” ብለው አብረን ካልሄድን አሉኝ። ላለመሄድ ብሞክርም ባለቤቱ ቆጣ ብላ “ኖህ! ወደድራፍት ቤት እንሂድ ቢሉህ መች እምቢ ትላለህ? በል ተነስ” አለችኝ።
ይሄ ግምብ ራስ ባሏ ድራፍት እንደምወድ ነግሯታል ማለት ነው። ሰነድ መሻሻጥ ተጀመረ? ብዬ እያመነታሁ አብሬያቸው ሄድኩ።

የወሰዱኝ ቸርች አንድ ነብይ የሚያገለግልበት አዲስ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ነው። ጓደኛዬ ባለቤቱ በቅርቡ ጌታን እንደተቀበለች ነግሮኛል። ገና ውስጥ ገብተን አረፍ እንዳልን በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸች ትፀልይ ጀመር።
“ጌታ ሆይ ለዚህ አብሮን ለመጣው፣ ነፍሱ በሃጢአት ለታሰረችው ጎስቋላ ወንድሜ ዛሬ ድረስለት” ስትል ደነገጥኩ። ጭራሽ ስለኔ ነው ፀሎቱ?
“ጌታ ሆይ” አለች ጭራሽ ተንጠራርታ እጇን ትከሻዬ ላይ ጭና። ድምጿ እየጨመረ ነው
“ጌታ ሆይ፥ ዛሬ ስለዚች ነፍስ እፀልያለሁ ...” አለች። {እቺ ነፍስ የተባልኩት እኔው ነኝ}
“ዛሬ እቺ ነፍስ ከስካርና ከሃጢአት ቀምበር እንድትላቀቅ እፀልያለሁ፥ እቺ ነፍስ ዛሬ ከዝሙትና ጌታ ከማይከብርበት የሃጢአት ልምምድ እንድትፈታ እፀልያለሁ” ስትል ቀና ብዬ ምእመኑን አየሁ። እኛ አጠገብ ያሉ ምእመናን ሁሉም ወደኔ እጃቸውን ዘርግተው ይፀልዩልኛል። የት ልግባ? ጭራሽ በሰው ሁሉ ፊት ሰካራም ነው። ያመነዝራል። ትበለኝ? ለምን አንደኛዋን የቲክቶክ ቪዲዮ አትሰራብኝም?
ዞር ብዬ ጓደኛዬን ሳየው ሳቁን አፍኖ በቆረጣ ያየኛል። በስጋ ብገለጥበት ደስ ባለኝ። እሱ ነው አብረን በነበርን ግዜ ምንሰራውን ነገር ሁሉ ዘክዝኮ ነግሯት የሰው መሳቂያ ያረገኝ።

የተወሰነ ቆይቶ ነብዩ ወደመድረክ ወጥቶ ፀሎት ማድረግ ጀመረ። ቤቱ ፀጥ አለ። አንዳንድ ሰዎች ብቻ በየመሃሉ አሜን ይላሉ። እሱም ትንሽ ከፀለየ በኋላ ...
“የጌታ መንፈስ ጅብ ጋላቢ መንፈስ ያሳየኛል” አለ። የዚህ ግዜ የጓደኛዬ ሚስት ዞር ብላ አታየኝም መሰላችሁ? ምናባሽ ላርግሽ? ብላት ደስ ባለኝ። አንተ ነህ  ለማለት ፈልጋ ነው? ይሄ የተረገመ ልጅ ጅብም ይጋልባል ብሏት ይሆን እንዴ?

ነብዩ ቀጠለ። “በጉባኤ ውስጥ አንድ ሰው ይታየኛል። ቤተሰቦቹ ቃልቻ ነው ሚያመልኩት። እሱንም በልጅነቱ በአጋዘን ደም ያጥቡት ነበር። ዋናው የአጋንንቶች አለቃ ይጠቀምበታል” ሲል በሃዘኔታ እንደገና ዞራ አየችኝ። አረ እቺ ሴትዮ ለምን አትፋታኝም? እያልኩ ፀሎቱን መከታተል ጀመርኩ።

ነብዩ ወደኔ አካባቢ ፍጥጥ ብሎ ካየ በኋላ ከመድረክ ወርዶ ቀጥ ብሎ መጣ ..... አሁንስ እኔም ፈራሁ። ስለኔ ነው እንዴ ሚያወራው? የሚል ሃሳብ ውልብ አለብኝ። ምናልባት ነፍስ ሳላውቅ ቤተሰቦቼ እንዳለው በአጋዘን ደም አጥበውኝ ይሆን እንዴ? መቸስ ሰው ማመን ከባድ ነው በዚህ ዘመን ምናምን እያልኩ ሳስብ ነብዩ አይኑን አፍጥጦ ቀጥ ብሎ እኛ ወዳለንበት መጣና እጁን አንስቶ....... የጓደኛዬ ሚስት ላይ ሲጭን ከተቀመጠችበት ወምበር ሁለት ሜትር ወደላይ ነጥራ መሬት ላይ ተነጠፈች። እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ። ምን ጉድ ነው?

በኔ ሲስቅ የነበረው ጓደኛዬ ሚስቱ እንደዚያ ስትሆን ሲያያት ክፉኛ ደነገጠ። እኔም ምን መጣ ብዬ አንዴ ነብዩን አንዴ እሷን ማየት ጀመርኩ
ነብዩ “ዋናው መንፈስ ተያዘ!” ሲል ጉባኤው በጩኸትና በጭብጨባ ተሞላ። ከዚያማ ያቺ ድምፀ ለስላሳዋ የጓደኛዬ ሚስት በሙላቱ አስታጥቄ ድምፅ ትለፈልፍ ጀመር

“ተቃጠልኩ! አረርኩ!”
“ማነህ?” አለ ነብዩ
“ጠቋር ነኝ”
“ተናገር የት ነው የያዝካት?”
“ባሏ ነኝ። ከልጅነቷ አሳድጌ ነው ያገባኋት” አለ ሴጣኑ። ጓደኛዬን አየሁት ሚገባበት ጠፍቶታል። “ጭራሽ የሌላ አካልን ሚስት ነው ያገባሁት?” የሚል ይመስላል።
አጋንንቱ ጭራሽ ወደሱ አፍጥጦ “አጠፋሃለሁ አንተ እርጉም ሚስቴን ነጠቅከኝ” እያለ መጮህ ጀመረ። ቺት አድርጋበት መሆኑ ነው።
ጓደኛዬ እንዲሁም ፈሪ ነው ጭራሽ አሁን ከሰይጣን ጋር የግል ፀብ ውስጥ በመግባቱ ያልበው ጀመር።

ያቺ መላአክ የመሰለች ሚስቱ ጭራሽ አይኗን አፍጣ በወፍራም ድምፅ ዛቻዋን ቀጠለች።
“ወንድወሰን ደበበ ጊሚራው” አለችው ሌባ ጣቷን ወደሱ ጠቁማ። {ዳዲ ቀረ በቃ}
ነብዩ ዝም ብሎ ያያል።
“አንተን ካላጠፋሁ እኔ ጠቋር አይደለሁም” አለ መንፈሱ። ጓደኛዬ እንባ ተናነቀው። በሆዱ "Who TF did i marry?" እያለ ነው
“ብዙ ግዜ በተኛህበት በገጀራ እንድትሰነጥቅህ አቅጄ ነበር። ዛሬ ይሄ ነብይ ቀደመኝ” እያለ ማጓራት ጀመረ። ጓደኛዬ እንባውን በአራት መንታ አወረደው። ምን ውስጥ ነው የገባሁት? የሚል ይመስላል።

ብቻ አጋንንቱ ከነብዩ ጋር ውጣ አትውጣ እያለ ሲታገል እኔ እንደምንም ሾልኬ ወጥቼ ወደቀበሌ ጃምቦ ቤት ሮጥኩ። ከአዳራሹ ወጥቼ ጥቂት እንደሮጥኩ ሩጫዬን አቀዘቀዝኩና ወደኋላዬ ስዞር ጓደኛዬ ኮቱን ጥሎ በሩጫ ወደኔ ይመጣል። አጠገቤ ሲደርስ እያለከለከ ቆመና
“ወዴት ነው ጥለኸኝ ምትሮጠው” አለኝ
“እንዴ አንተስ ሚስትህን ጥለህ ወዴት ነው?” ስለው
“አፍህን ዝጋ” ብሎኝ አብሮኝ ወደግሮሰሪ አመራ።

አሁን ሰባተኛ ጃምቧችን ላይ ደርሰናል። “እኔ ግደሉኝ እንጂ ያቺን ሴት አምኜ እዛች ቤት አላድርም” ስላለ ተሰብስበን ወደቤቱ እንዲሄድ እየለመንነው እንገኛለን።

By  Noah Daniel

😂
😂
😂
😂
😂
😂
JOIN
====
https://t.me/write_event
😁5
ንጉሱ  ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት  ቆንጅዬዋ ሚስቱን  በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈት እና ሚስቴን አግባት…" ብሎት ፈረሱ ላይ ወጥቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ።  ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው አቧራማ ንፋስ እንዳለ አየ።  ቆም ብሎ ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየሮጠ ሲመጣ አየ።
...
"ምነዉ ምን ሆንክ ?" ብሎ ንጉሱ ጠየቀ። በጣም ከመሮጡ የተነሳ ትንፋሹ እየተቆራረጠ ጓደኛው ሙሳ "የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ" ሲል መለሰ።
....
"ምን?"  ብሎ ንጉሱ አይቶት በድንጋጤ እና በመገረም አየዉ  ቁልፎቹን ከመሞከሩ በፊት ለአራት  ቀናት ይቅርና ለ አንድ ሰአት እንኳን አልጠበቀም።
...
እንደ “ጓደኞችህ” ከምትቆጥራቸው ሰዎች ጋር ተጠንቀቅ እና በትጋት ለምታገኘው ሃብት አደራ ልትሰጣቸው ትችላለህ፤ እነሱ በቅርቡ እንድትሞት እየተመኙልህ ሊሆን ይችላል እና እራስህን  መጠበቅህን መዘንጋት የለብንም።

(ዶክተር እዮብ ማሞ-ንጉሱ የኦቶማን ንጉስ አህመድ  ነው ብሎ ነው ታሪኩን የፃፈው። )

😂
JOIN
====
@write_event
@write_event
@write_event
😁3
የደራሲ ቅጣት ...

የሆነ ሰውዬ ይሞትና ገነትንም፣ ሲዖልንም ይጎበኛል፡፡ ገነት ሲደርስ በጎ ምግባሮች እንደቀጠሉ ናቸው። መልካም ሰርተው የፀደቁትንም አስተዋለ፡፡ ይልቅ የገረመው አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ የሚፅፍ ሰው ተመለከተ። ገረመውና ምን እንደሆነ ቢጠይቅ "ደራሲ ነው" አሉት። እየተደነቀ “አይ ደራሲ ፀድቆም አያርፍ፣ አሁኑም ይፅፋል” ሲል ተደመመ።

ከሚንቀለቀል የእሳት እቶትን ውስጥ የሲዖልም ሕይወት ቀጥላለች። አመፅ፣ ግርግሩ፣ ጦርነቱ…ኃጥያቱ አናት ባናቱ ይደራረባል። አሁንም አንድ ሰውዬ ከእሳት ዛፍ ስር አረፍ ብሎ በእሳት ብዕር፣ በእሳት ወረቀት ይቸከችካል። ተመልካቹ ሰውዬ ግራ ተጋባም ምን ሊሆን ይችላል ሲል እያሰበ ጠየቀ "ደራሲ ነው፣ ይከትባል" አሉት።

እየተገረመ፣ እየተደነቀ መልዓኩን "ቆይ ደራሲ እዚህም ሲፅፍ አይቼዋለሁ… እዛም ሲቸከችክ ተመልክቼዋለሁ ካዲያ ገነትም ገባ፣ ሲዖልም ወረደ ምን ቀረበት? ምንድነው ቅጣቱ? ምን ተጎዳ?" ሲል ጠየቀው።

መልዓኩም መለሰለት “ገነት ያሉት ይታተምላቸዋል"😂

By Alemayew Gelagay

Join
https://t.me/write_event
1😁1
ከባላጌ ጓደኛ ጋር ስማግጥ.....😭

ሲነጋ እራሴ ላይ ትልቅ ፎቅ የተሸከምኩ ያህል እየተሰማኝ መነሳት ከጀመርኩ ቆይቻለሁ አላማ የሌለው ዝም ብሎ ህይወት እየኖርኩ ከትልቅ ግንብ ጋ እየተጋፋሁ የማይነጋ ሌት ላይ ላይ እያፈጠጥኩ የምኖር ይመስለኛል።

የሳሎኑ በር ገርበብ እንዳለ መስኮቱ እንደተከፈተ ቀን የለበስኩትን ልብስ ሳልቀይር ሻሽ ሳላስር ነው የተኛሁት።ማንም በህይወቴ ቢመጣ ከዚህ የከፋ ነገር እንደሌለ ውስጤ አምኗል ኑሮ ጅብ ሆኖ እየጎተተኝ የትኛውን የምድር አውሬ ፈራለሁ??ሀሞቴ በየቀኑ ሲፈስ ልቤ ሲልፈሰፈስ አቅም ሲከዳኝ ይታወቀኛል ፅልመት የወረሰው ጠዋቴን በቦዘ አይኔ እያየሁት አብ ከመኝታ ቤት ተጣራ...

መክሊቴ...መክሊቴ መ...

መጣሁ አብ መጣሁ ተነሳህ እንዴ??

ስሮጥ ጨለማ የወረሰውን መኝታቤት ከፍቼ መብራቱን ሳበራው አብ ማታ እንዳስተኛሁት በጀርባው ተንጋሎ ተኝቷል።መቼስ የህይወትን እውነትነት ትቼ መተወኔን ከተያያዝኩ ዘመን የለኝም።እያነቡ መፈገግ እየታመሙ ጤነኛ መምሰል እያዘኑ መደሰትን የመሠለ ከባድ ነገር ምን አለ??

መክሊቴ ሽንቴን ወጠረኝ ፖፖውን ወዲ በይው እስቲ ፍቅር

እሺ ባሌ አይዞህ ቆይ ቀና ላድርግህ...

አብ ባሌ ነው!! በልቡ ቀለበትነት ሴትነቴን ሸብቦ ያሰረ በቃልና በተግባሩ የታመነ በህይወቱ ስለ ፍቅር የታገለ ለኔ ሲል ሙሉ እድሜውን ጤንነቱን የከፈለ ፍቅሬ ነው።እሱ ባይኖር ስሜ መቃብር ላይ ብቻ የሚቀር በድን ሬሳ ነበርኩ።የኔን መቃጠል ተቃጥሏል፤የኔን ህመም ታሟል፤የኔን ሞት ሞቷል።ከአመታት በፊት ከሚነድ ቤት ውስጥ ተሸክሞ በነብሱ ተወራርዶ ያወጣኝ እሱ ነው...

ፍቅር አስቸገርኩሽ አደል ምናለ አሁንስ በወሰደኝ!!(ብልቱን ከቱታ ውስጥ ሳወጣው በሀፍረት እያቀረቀረ

አብ እንዲ አትበል እባክህ እጅ እግርህ አልሰራም ማለ...

ተይ መክሊቴ ተይ እባክሽ!!ሴትነትሽን በላሁት!! እድሜሽን አሳለፍኩት ለኔ ስትዪ እዛ ሶፋ ላይ...

አብ እረፍ እባክህ ይሄን ሁሉ ያደረከው ለኔ ነው ይህንን ባታደርግ ዛሬ እኔ ባንተ ቦታ አልነበርኩ??እኔ እንደዚ ብሆን ትተወኛለህ ማለት ነው??(አፌ ይቅጠፍ እንጂ የልቤ እንደ አብ ብልት ተልፈስፍሶ ትኝት ብሏል

መክሊቴ አልተውሽም ፍቅርኮ በጉድለት ውስጥ ያለ ዘላለማዊ ሙላት እንጂ በሙላት ውስጥ ያለ ጊዜያዊ መፈላለግ አደለም ይልቅ ለሚኪ ደውዪለት...

እ እሺ...ግ.. ግን ..ምነው ፈልገከው ነው??

አይ የሚያስፈልግሽ ነገር ካለ ገዝቶልሽ ይምጣ እኔም ፈልገዋለሁ ተነሺ ደውዪለት...

ሚኪ!!ሚኪ!!ሚኪ!! ልቤ ገደቡን አልፎ እየመታ ወደ ሳሎን አመራሁ።የተከፈተችው መስኮት ንፋስ እያወዛወዛት ፂጥ ፂጥ ፂጥ ስትል ሀጥያቴን ለማስታወስ የእግዚአብሔር መላክ ጫፏን ይዞ ሲያወዛውዛት ታይቶኝ እሮጩ ዘጋኋትና ሚኪ ጋ ለመደወል እጄ እየተንቀጠቀጠ ሰውነቴ እየራደ ደረቱ አይኔ ላይ እየዋለለ ጭኖቼ መሀል እሳት እየነደደ ስልኩ ጠራ ...

ወዬ...(ሚኪ ስልኩን አነሳው ስጠራው ሩጦ መጣ

ሚኪ እረፍ አብ ይሰማል... ሚካዬ በናትህ ቀስበል..አ..(ኮሊደሩ ስር አንገቱ ላይ ተጠምጥሜ በስሜት እየቃተትኩ

አንቺ ዝም ካልሽ እሱ አይሰማም የኔ ውድ...

ቱታዬን ለማውለቅ እየታገለ እኔ ደሞ ቲሸርቱን ሰብስቤ አንቄ እየሳምኩት በድንገት የሳሎኑ በር ሲከፈት

✍️ Ermi ye hawi

ይቀጥል የምትሉ በlike አሳውቁን