ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
''ተው ግን ዳጊ ተው ትዕግስተን እየጨረስኩ እንደሆነ ለምን አይታይህም ግን።''
(አሁን እንባዋ መውረድ ጀመረ። እንዲህ ስትለው ይፈራል። ነፍሱ ትሸበራለች። ደንግጦ ከተቀመጠበት ተነስቶ የተቀመጠችበት ሄዶ አቅፎ ሊያባብላት ስሞክር : እንዳያቅፋት ተከላከለች። ታግሎ አቀፋት። ትወደዋለች መጨከን አትችልም ተሸነፈችለት።)

(ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ እየገነፈለ ያስቸገረውን ንዴቱን ለመቆጣጠር ብሞክርም አልቻለምና ይሄው እንደለመደው አስለቀሳት። ሳያስበው በልምምጥ የጀመረው ወሬ ቅርፁን እየቀየረ እየቀየረ ሄዶ ምልልሳቸው ወደ ጭቅጭቅ ተቀየረ። የእሱም ልምምጥ በቁጣ ተተካ። ላይ ላዩን እንደዚህ እየተቆጣ ቢያወራም ፡ ውስጡን ግን አንዳች የፍርሀት ስሜት ሰቅዞ ይዞታል። ቢትሄድብኝስ : እንደ ባለፈው : በቃ የኔና ያንተ ነገር አብቅቷል ቢትለኝስ!? የሚል ሃሳብ አእምሮው ላይ ስመጣ ፈራ። አጥብቆ አቀፋት። ልቡ ይታወክ ጀመር። ጨነቀው። ምድር ላይ የሚያስፈራህ ነገር ምንድነው? ተብሎ ቢጠየቅ ሁለት ጊዜ ሳያስብ ማርቲን ማጣት ነው ብሎ ይመልሳል። ግን ደሞ ሁልጊዜ ነገሮችን የሚያበላሸው ራሱ ነው። በዚህ ምክንያት አንድ ቀን ጥላው እንደምትሄድ ያውቃል።

የሆነ ቀን በዚሁ ጉዳይ ተጣልተው ብዙ ብዙ ተጨቃጭቀው : እቤት ተቀምጣ ምርር ብላ ስታለቅስ : እሱ ጭንቅላቱን ይዞ ሶፋው ላይ አጎንብሶ እንደ ተቀመጠ ጓደኛው ድንገት ይመጣል። ምን ሆናችሁ ነው ብለው ፡ ትንሽ ተጋጭተን ነው አለው። ታዲያ የዛን እለት ጓደኛው ሚስቱን አባብሎ ልሸመግላቸው ተቀመጠ። እናም ጓደኛው ነገር ለማለዘብ ብሎ : ለሚስቱ ለሰነዘረላት ጥያቄ እንዲህ ብላ መመለሷ አስደነገጠው። ይሄውልህ አሴ የጎደኛው ስም አሰግድ ነው። ባሏ ስጠራው በሰማችው እሷም አሴ እያለች ነው ምጠራው። ''በህይወቴ ውስጥ ከምንም በላይ ለፍቅራችን ግዴታዬን ተወጥቻለሁ . . . . . ካልሆነ መሄድ እችላለሁ።'' ነበር ያለችው።

ታዲያ ይሄን ስትል ቀዝቃዛ ውሃ የተቸለሰበት ይመስል ከተቀመጠበት ብትት ብሎ ብድግ አለ። እሱ በተራው ማልቀስ ጀመረ። የዛን እለት አሳር ፍዳውን በልቶ ጓደኛው አስታርቋቸው ሄደ። ታዲያ ሁልጊዜም ቢሆን እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ስገቡ ያንቀን የተናገረችው ነገር በጆሮው እያስተጋባ ያርደዋል። ቢሆንም ግን ክፉ አመል የሆነበት እና መቼ እንደተፀናወተው የማያውቀው አደገኛ ቅናት አለበት ለመዳን ቢታገልም መፈወስ ያልቻለበት ደዌ። ልክ እንደ {ታምራት ደስታ ሙዚቃ ወድጄ አይደለም ምቀናው ጥሎብኝ ነው የኔ ፍቅር} እንደሚለው። እሱ ራሱ ጭንቅ ስለው ከፍቶ የሚሰማው ይሄን ሙዚቃ ነው። በነገሩ ተበሳጭታ አላናግርህ ስትለውና ስታኮርፍ ይሄን ሙዚቃ በምትወድለት ድምፁ ሲያንጎራጉርላት አንጀቷ አይችልም። አቅፋ ትስመውና ማውራት ይጀምራሉ።

ግን አሁን አሁን ይሄን ፍቅር ልታድን እንደማትችል እየገባት መጥቷል። ልጅ በጣም ብትወድም በዚሁ ፍራቻዋ ምክንያት ነው የመውለድ ፍላጎቷን ያዘገየችው። እዚህ ትዳር ውስጥ ልጅ ማምጣት የልጁን ህይወት ማበላሸት ነው ብላ ነው ምታስበው። ምክንያቱም ይሄ ትዳር በፍቺ እንደሚጠናቀቅ ልቧ ያውቀዋል። እናም ከምታፈቅረው ሰው ልጅ መውለድ ፡ ብትፈታው እንኳን ለትዳሯ እና ለፍቅሯ ለከፈለችው መስዋዕትነት ሁሉ መታሰቢያ ነው ብላ ብታስብም ፡ ልጇን ያለአባት ማሳደግ ግን ልክ አይደለም ብላ ታምናለች። ባሏ ሁልጊዜ የእንውለድ ጥያቄ ያነሳል። ግን ለእሱም ቢሆን ቅናት የለብኝም እያለ ብከራከራትም መቅናትህን አቁመህ እኔን በሙሉ ልብህ አምነህ እንደሰው ማህበራዊ ህይወት ኖሮን ጤናማ ህይወት መኖር ስንጀምር ያኔ እወልዳለሁ ትለዋለች። ደሞ ሁልጊዜም ቢሆን ስላም ሆነው ስለችግሮቻቸው ሲያወሩ : ቅናት እንዳለብህ ማመን ካልቻልክ መዳንም አትችልም ትለዋለች። ካልታረምክ አልወልድልህም ማለቷ ለሱም ባህሪውን ለማስተካከል ጉልበት ይሆነዋል ብላ ታስባለች። የባሏን አስቸጋሪ አመል ለማረቅ ብዙ ነገር ታደርጋለች። ይሄን ትዳር ከተወች ምድር ላይ ብቻዋን እንደምትቀር ታውቃች። እሱ እንዳይቀና ለማድረግ ከህይወቷ ያላስወጣችው ሰው የለም ከወንድ ጓደኞቿ ጋር ብጠረጥራትና ብቀና ከሴት ጓደኞቿ ጋር ደሞ ከማን ጋር ልታገናኝሽ ነው እያለ ቁም ስቅሏን ያሳያታል። ከዚህ ሁሉ ብቀርስ ብላ ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ተወችለት። አሁን ግን ትዳርዋን ፡ ፍቅሯን ለማዳን መሞከር እና ማድረግ ያለባትን ሁሉ አድርጋ ጨርሳለች። እሱን ካጣች እንደምትጎዳ እንደምትሰበር ታውቃለች። ከሁሉ በላይ ግን እሱ እሷን ስያጣት የሚሆነውን ነገር ማሰብ ይከብዳታል። በጭራሽ ተጎድቶ ልታየው አትችልም። የሱን ጉዳት የማየት አቅም የላትም። ከራሷ በላይ የሱ ህመም ያማታል። በትዳሯ በኩል ያልተሰማ ብዙ ፀሎት : ያልሰመረ ብዙ ስዕለት አላት። አንዳንዴ አምላኳን እንዲህ ብላ ትጠይቀዋለች። የማያልቅ ፍቅር ሰጥተሄን ስታበቃ : ቅናት ይሉት ስሌት ፍቅራችንን ገዝግዞ ስቆርጠው እያየህ እንዴት ዝም ብለህ ታያለህ!? እንዴት አንድ የማርያም ምህረት ለፍቅራችን አጣህ!?)

ሰብለ ወንጌል
#share and join for more👍
SHARE🌼


=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የባህር ፈርጥ ነሽ፣ ሽሽግ ድብቅ እንቁ
የንጋት ድርሳኔ፣ ያገር በቃይ ስንቁ
ሁለመናሽ ሙሉ፣ የሴት እፁብ ድንቁ

ብርሃኔ ነሽና ለኔስ ማታ ማታ
አትጥፊ ከጎኔ ነይ የኔ ዘንካታ
የቀኑማ ቀን ነው ያልፋል በጨዋታ

የከንፈሯ ድባብ፣ ጥዑም ቃል ማስፈሪያ
አጀብ የንብ ንግስት፣ የማር መናኸሪያ
ውበት አርከፍክፎ፣ ተፈጥሮ የመጠናት
የቁም ነገር መዝገብ፣ የዕምነት ማህተብ ናት
የዕምነት ማህተብ ናት [2x]

ማርና ወተቴ ነሽ፣ ደጋፌና ክብሬ ለቤቴ
እስኪ ስሚኝ ልንገርሽ ላዚም ስላንቺ ካንጀቴ
አንቺ ነሽ ሕይወቴ፣ የፍቅር እመቤቴ

የባህር ፈርጥ ነሽ፣ ሽሽግ ድብቅ እንቁ
የንጋት ድርሳኔ፣ ያገር በቃይ ስንቁ
ሁለመናሽ ሙሉ፣ የሴት እፁብ ድንቁ

የጥርሷ ብርሃን፣ ሕይወት የሚዘራ
ተፈጥሮዋ አበባ፣ እንቡጥ ያላፈራ
እንደ ዕውነት እንደ ውኃ፣ እያደር የጠራ
ለምልክት ላይነት፣ ለይታ የተሰራ
ለይታ የተሰራ…ላይነት የተራ

ባዘንም በደስታዬ፣ ምሶሶ ዋልታዬ ለቤቴ
ውዳሴ ገዴ ክብሬ፣ ዐብይ ጉዳዬ ሕይወቴ
አንቺን ያበቀለ ቀዬው እንዴት ዋለ

ማርና ወተቴ ነሽ፣ ደጋፌና ክብሬ ለቤቴ
እስኪ ስሚኝ ልንገርሽ ላዚም ስላንቺ ካንጀቴ
አንቺ ነሽ ሕይወቴ፣ የፍቅር እመቤቴ
አንቺን ያበቀለ ቀዬው እንዴት ዋለ [2x]

#ቴዎድሮስ_ታደሰ_ሁለመናሽ_ሙሉ
🥰
👍1
ሀይማኖት በኢ–አማኙ እይታ !

ከቴዎድሮስ ተ/አረጋይ የፌስቡክ ገጽ የተገኘ

ቴዎድሮስ :– የእግዚአብሔርን መኖር ፋይዳ እናጥብበውና ሀይማኖት ሌላ ቢቀር በስነምግባር ት/ቤትነቱ እንኳ አስፈላጊ አይሆንም ?
ዜና :– አይሆንም ። ግብረገብን ሀይማኖት አይደለም የፈጠረው ፤ ከሰብዕና ላይ ነጥቆ የወሰደው ነው ። ቡድሂስቶች ጋ ሂድ ። ከእኛ የበለጡ ደጎች ናቸው ። ክርስትና ወይም እስልምና አይደለም ደግ ያደረጋቸው ። ክርስትናን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁም ። ማንኛውም ሀይማኖተኛ ጥቅሙን አስቦ ነው እግዚአብሔርን ያመነው ፤ ዘለዓለማው ሕይወትን ለማግኘት ። እኔ ደግ ስሆን ግን ምንም አስቤ አይደለም ። ደግ መሆን ስላለብኝ ፤ ሌላው ሰው ደግ ቢሆንልኝ ስለምፈልግ ነው ። አንተ ላይ ክፉ የማላደርገው እኔ ላይ ክፉ እንዲደረግ ስለማልፈልግ ነው ። ይህ ደግሞ የሀይማኖት ህግ አይደለም ። በሀይማኖት ስም አይደለም እንዴ ሞትና እልቂት የደረሰው ?

አሜሪካ ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቄስ አንድን ውርጃ የሚሰራ ዶክተር ቤቱ በር ላይ ገደለው ። ከዚያ ሄዶ እጁን ለፖሊስ ሲሰጥ " የእግዚአብሔርን ስራ ሰራሁ " ነው ያለው ። ይህን የሰማ ስቲቨን ዊልበርግ የተባለ የፊዚክስ ሊቅ ምን አለ መሰለህ ? ቃል በቃል እንጥቀሰውና " With out religion you will find good people doing good things , bad people doing bad things . But good people to do bad things you need religion " ( " ያለ ሀይማኖት ጥሩ ሰዎች ጥሩ ፣ መጥፎ ሰዎች መጥፎ ሲሰሩ ታገኛለህ ። ነገር ግን ጥሩ ሰዎች እርኩስ ነገር እንዲሰሩ ከፈለግህ ሀይማኖት ያስፈልግሀል " ማለት ነው ።)
( ከ" ፍልስምና " 3 መጽሐፍ የተወሰደ)

አንድ አባት ገዳም ውስጥ በጽድቅ እየኖሩ ሳለ አንድ ሐሳብ ወደ አዕምሯቸው ይመጣል። "ይህን ሁሉ ዓመት በጽድቅ ኖሬ ሳበቃ ከሞት በኋላ ሕይወት ባይኖርስ? ፈጣሪ ባይኖርስ? መና መቅረቴም አይደል?" ብለው አሰቡ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሞቱና ሰማይ ቤት ሄዱ። መልኣክት በሥራ ተወጥረው ሳለ ነው የደረሱት። መልኣክቱ ይራወጣሉ። ምን እየሠሩ እንደሆነ አልገባቸውም። አንድ መልኣክ ይመጣና "እዚህ ምን እየሠራህ ነው? ምን ታደርጋለህ?" ብሎ ጠየቃቸው። "በቅርቡ ሞቼ ለፍርድ መጥቼ ነው!" ብለው መለሱለት። መልኣኩ በአንክሮ ካስተዋላቸው በኋላ "ማን ነው የምትባለው? ከየትስ ነው የመጣኸው" ሲላቸው፥ "ሰው ነኝ! መሬት ከምትባል ፕላኔት ነው የመጣሁት" ብለው መለሱለት። መልኣኩ እጅግ ተገርሞ "መሬት የሚባል ፕላኔት እና ሰው የሚባል ፍጡር አላውቅም!" አላቸው። መልኣኩ ትንሽ አሰበና ከሱ ከፍ ላለው መልኣክ ነገሩን አሳወቀ። መልኣክቱ ግራ ሲገባቸው የባሕር መዝገቡን አገላብጠው ቢመለከቱት መሬትና ሰው የሚባል ነገር ጨርሶውኑ አጡ። ግራ ሲገባቸው ሽማግሌውን ይዘው እግዚአብሔር ጋር ወሰዱት። እግዚአብሔርን እጅግ በሥራ ተወጥሮ ያገኙታል። እግዜሩም እጅግ ተቆጥቶ "ምንድነው በተዋረድ ወስኑ አላልኳችሁም?! ለምን ሥራ ታስፈቱኛላችሁ?" አላቸው። መልአኩም "መሬት ከሚባል ፕላኔት ሰው የሚባል ፍጡር እግዚአብሔር ፈጥሮኛል ብሎ መጥቶ ነው" አለው። እግዜሩ ቢያስብ ቢያስብ ሰውን ስለመፍጠሩ ሊያስታውስ አልቻለም። "ለመሆኑ ባሕር መዝገቡ ላይ ሰፍሮ ይሆን?" ብሎ ጠየቃቸው። "የባሕር መዝገቡ ላይ መሬት የሚባል ፕላኔትም ሆነ ሰው የሚባል ፍጡር ጨርሶውኑ የለም" አሉት። እግዜሩም "በቃ ምናልባት ከመጀመሪያዎቹ ሥራዎቼ አንዱ ሊሆኑ ስለሚችሉ Others የሚባል Folder ክፈቱና እዚያ ላይ መዝግቧቸው" አለ።

#ዓለማየሁ ገላጋይ ከፈረንሳይ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ያገኘውን ተረክ በሸገር ኤፍኤም ከመዓዛ ብሩ ጋር ባደረገው ቆይታ ከተናገረው የተወሰደ፨
ምክር ከሃኪሞች ሠፈር!

አርበኛው አያቴ ሆስፒታል ሄዶ ሲመለስ ብስጭትጭት አለ።
"ምነው ምን ነካህ?"
"ጠቅል የድሃ ልጅ አስተምሮ ተጫወተብን"
"እንዴት?"
"ሃኪም አትብሉ ይላል?የታመመ ጥሩ ጥሩውን ካልበላ ይሆናል?የደሃ ልጅ ስለሆነ እሱ ያላገኘውን ሰው ሲበላ አይኑ ደም ይለብሳል።ታድያስ?ጮማ እትብሉ፣ቅቤ አትብሉ፣ጠጅ አትጠጡ እናስ?እለዋለሁ አትክልት ብሉ ባዶ ሽሮ ምናምኒት የሌለው "
"ምን አልከው?"
"ሽሮውን አንተው እንዳደክበት እዛው ሙትበት፤እኔ የሰጠኝን በረከት ትቼ ያልሰጠኝን ስበላ አልገኝም።ድሃ የድሃ ልጅ አልኩታ"

አለማየሁ ገላጋይ -ውልብታ

****

ሰውየው በእድሜ የገፉ ባለጠጋ ናቸው።
ሃኪም ጋር ሄደው
"አባት በሽታዎችዎ እነ ደምግፊት፣ስኳር እና ዩሪክ አሲድ የመሳሰሉት እርስዎ የሚያዘወትሯቸውን ምግቦች ይከለክላሉ።
ጥሬ ስጋ፣ቅባት የበዛባቸው..."
"ጮማስ?"
"እሱንም"
"ጠጅስ"
"አይፈቀድም ወይ ይቀንሱት"
"እና ሞትን ሞተህ ጠብቀው ነው የምትለኝ"

በሃይሉ ገ/መድህን ከሸገር ኢንተርቪው

***

እኚህኛው ደግሞ ኑሮ የደቆሳቸው እናት ናቸው።
"እማማ በሽታ ሳይሆን ያለብዎ ችግር እራስዎን ያለመጠበቅ ነው።በምግብ ይጠገኑ ለምሳሌ ጥዋት ሲነሱ እንቁላል፣በምሳ ሰዓትም እማይከብድ መረቅ ነገር ከተገኘም ጭማቂ ወይም..."
"ጨረስክ?"
"አዎ ጨርሻለሁ ብቻ ለስለስ ያለ ነገር..."
"ጨረስክ ወይ?
"ጨርሻለሁ"
"አንት ቅንዳሻም!እራስህ የማትበላውን ለኔ ታዛለህ!"

ተስፋዬ ካሳ

#share and join for more👍
SHARE🌼


=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
😁2
"ደራሲ ደራሲ ከመሆኑ በፊት አንባቢ ነው ። ደራሲ ደራሲ ከሆነም በኋላ አንባቢ ነው ።የህይወት ቅጠሎችንም ያነባል ፤ እድሜ ልኩንም ያነባል ።"
ደበበ ሰይፋ።


#share and join for more👍
SHARE🌼


=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
(''ዛሬ በልግ ነው
ዘወትር አለቅሳለሁ
ዛሬ በልግ ነው
ፀደዩ ምንኛ ይርቃል።'')
📖ትኩሳት📖
በጋሽ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር
🔥1
ሀገር አዕምሮ ውስጥ የሚወለድ የጋራነት ሃይል ነው ። ማሰብ የማይችል ፍጡር ሀገር አይኖረውም ። እንስሶች ሀገርም ዜግነትም የላቸውም ። ጭላዳ ዝንጀሮ ፣ ቀይ ቀበሮስ እንዳንል ግን ሰው ማሰቡን ሳይኖረው ሀገር አለኝ ቢል እየዋሸ ነው ።
🔻 ሀገር የእሳቤዎች ቅኔ ናት !!

🚀 #ቡርሃን አዲስ
@write_event
👍1
1888🔥
በታርክ መዛግብት ስማቸው ሳይፃፍ ለቀሩ...ስላልተዘከረላቸው...ስላልተዘመረላቸው.. ክብርን እና ውዳሴን ሳንቸራቸው ... ጨቋኝ ባርነት ትላንት ላይ በነፃነት ስለለወጡልን..ዛሬ ቀና እንድንል ህይወታቸውን ሰውተው ላለፉት ጀግኖች ትልቅ ክብር አለን።

አድዋ🔥

እኛ እና የኛ

- @write_event
2🔥2👍1
1
ከዛሬ 46 ዓመታት በፊት የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ገብቶ የነበረውን የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት በማስወጣት ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ማወለብለቡን ታሪክ ያስታውሳል፡፡

የካራማራ ድል ከደርግ ውድቀት በኋላ በመንግስት ደረጃ የማይከበር ድል ቢሆንም የቀድሞ ሰራዊት አባላትና ግለሰቦች በተነሳሽነት እያከበሩት ነው፤ በዓሉም ብሄራዊ በዓል ሆኖ በመንግስት እንዲከበር ይፈልጋሉ፡፡

ሶማሊያ በ1952 ዓ.ም ከጣሊያንና ከእንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ነፃነቷን ባገኘች ማግሥት የሀገሪቱ መሪዎች "ታላቋ ሶማሊያን እንገነባለን" የሚል ህልም ማለም ጀመሩ፡፡ በዚህም ምክንያት በ1953 ዓ.ም የድንበር ላይ ትንኮሳ ጀምረው በ1956 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብድረሺ አሊ ሸርማርኬ እንዲሁም በ1969፣ በ1972 እና በ1973 ዓ.ም ደግሞ ፕሬዝደንት ዚያድ ባሬ (ሜጀር ጀኔራል) የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ እንዲገባና ወረራ እንዲፈፅም ሰራዊታቸውን አዘዙ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ደግሞ ሰርጎ ገቦችን አስታጥቆ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በማስገባት ፈንጅ በማፈንዳት፣ ድንገተኛና የደፈጣ ጥቃቶችን በመፈፀም እንዲሁም ባለስልጣናትንና ሰላማዊ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ ለኢትዮጵያ ሰላምና ልማት መሰናክል ሆነው መቆየታቸውንም በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪዎች ይገልጻሉ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ የሶማሊያ ወረራዎችና ጥቃቶች በኢትዮጵያ አሸናፊነት ቢመለሱም ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን አለመቻሉ ይገለጻል፡፡ በተለይ የ1969 ዓ.ም የዚያድ ባሬ ወረራ የኢትዮጵያ ድንበር በምስራቅ በኩል እስከ 700 ኪሎ ሜትር እንዲሁም በደቡብ በኩል ደግሞ እስከ 300 ኪሎ ሜትር በሶማሊያ ሰራዊት እንዲደፈር፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዲሞቱና እንዲቆስሉ፣ አካል ጉዳተኛ እንዲሆኑ በአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በርካታ የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ያደረገ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ በወቅቱ በብዙ የውስጥ ችግሮች (የመሐል አገር የሥልጣን ሽኩቻ፣ የነጻነት ጠያቂዎች በሃገር ቤት፣ የተለመደው ድህነትና ረሀብ …) ተወጥራ ስለነበር የዚያድ ባሬ ወረራ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባት ነበር ይላሉ የታሪክ ጸሐፊያን፡፡

ሶማሊያ ኢትዮጵያን ለመውረር ሰፊ የሰው ኃይል፣ የትጥቅ፣ የስንቅ፣ የሥነ ልቦና ዝግጅት ስታደርግ ቆይታለች፤ኢትዮጵያ ግን በውስጣዊ ችግሮች ከመወጠሯም ባሻገር በወቅቱ የነበራት የሰራዊት ቁጥርና ጥራትእንዲሁም የትጥቅ አቅርቦት እጅግ የተመናመነ እንደነበርም ነው የሚገለጸው፡፡

300ሺ የሚሆን ሕዝባዊ ሰራዊት በአጭር ጊዜ ሰልጥኖ ለውጊያ የተሰለፈ ሲሆን ፤ የኩባና የደቡብ የመን መንግሥታት ጦራቸውን ይዘው ከኢትዮጵያ ጎን መሰለፋቸውም ይታወሳል፡፡ ሶቭየት ኅብረት በጀኔራል ፔትሮቭ የሚመሩ ወታደራዊ አማካሪዎቿን ለኢትዮጵያ ረዳት አድርጋ ወደ ኢትዮጵያ መላኳንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከኢትዮጵያ በኩል ተሰልፈው ህይወታቸውን ላጡ ኩባውያን ወታደሮች በአዲስ አባበ መታሰቢያ ተሰርቶላቸዋል፡፡

የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት የማባረሩ ዘመቻ በሐምሌ ወር 1969 ዓ.ም ተጀመረ፡፡ ኢትዮጵያውያን በምድርና በአየር አስደናቂ ገድል ስለመፈጸማቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡ ዘመቻው እስከ የካቲት ወር 1970 ዓ.ም ቆይቶ የሶማሊያ ጦር በኢትዮጵያ ሰራዊት ተከቦ መፈናፈኛ ሲያጣ ለአሜሪካና ለሶቭየት ኅብረት የድረሱልኝ ጩኸቱን አሰማ፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሶማሊያን ጦር እያባረረ የሶማሊያን ድንበር ጥሶ ወደ ሃርጌሳ ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት ስለነበር ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈው የነበሩት የውጭ አገራት የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ግዛት እንዳይገባ ልመናና ተማፅኖ ጭምር ማቅረብ ጀመሩ፡፡

አሜሪካና ሶቭየት ኅብረትም ኢትዮጵያና ሶማሊያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ፤የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ሶማሊያ ድንበር ጥሶ እንዳይገባና የሶማሊያ ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር በ24 ሰዓታት ውስጥ ጠቅልሎ እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የአሜሪካና የሶቭየት ኅብረት ጥሪ ተፈፃሚ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ሰራዊትም የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውለበለበ፡፡

በአሁኑ ወቅት ይህ የድል ዕለት ታዲያ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው አይደለም የሚሉ ወቀሳዎች አሉ፡፡በተለይ ዕለቱን ሳይቀር ብዙዎች የማያስታውሱት እንደሆነና መንግስትም ሰፊ ትኩረት እየሰጠው እንዳልሆነ ይነገራል፡፡

በወቅቱ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪዎች ሳይቀሩ እየተዘከሩና እየታወሱ አለመሆኑም ይገለጻል፡፡
____

ኢትዮጵያ ትቅደም !!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!!
Share💚💛
----------
join
@write_event
💚💛
@write_event
👍21
የአንድ አይኑን ብርሃን ያጣዉ ሚኖንጎ በክለቦች የአለም ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ ነዉ።

እ.ኤ.አ. በ 2002 የተወለደው ጆርጂ ሚኖንጎ የእግር ኳስ ህይወቱን ለመከታተል ሲል በአይቮሪ ኮስት የሚገኘውን መንደሩን ለቆ ተሰዷል። በሜጀር ሊግ ሶከር አሜሪካ በሲያትል ሳውንደርስ በአሁኑ ወቅት እየተጫወተ ነዉ።

እ.ኤ.አ. በ 2023 ግን ተስፋ አስቆራጭ ነገር በህይወቱ ላይ ተፈጠረ። ነገር ግን እርሱ ተስፋ አልቆረጠም ነበር። በአንድ አይኑ ላይ ባጋጠመዉ ኢንፌክሽን የአይን ብርሃኑን አጣ።

የአካል ጉዳተኛ ሆኖ ህይወቱን ለመምራትም ተገደደ። ኋላ ላይ ግን በአካል ጉዳቱ ከእግርኳስ አለም ሳይገለል መጫወቱን ቀጠለ። በአሜካዉ ክለብም የአራት አመት ኮንትራት ፈርሞ በአለም ክለቦች ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዉን አድርጓል።

"ይህ አካል ጉዳተኝነት አይገድበኝም" ይላል ሚኖንጎ።"


ሁለት አይኖች ካላቸው በተሻለ ሁኔታ መስራት እንደምችል አምናለሁ"

ሲል ይናገራል።

ከአይቮሪኮስት እስከ የአለም ክለቦች ዋንጫ ድረስ ህልሙን መፈለግ አላቆመም ነበር።

©ሸገር sport
JOIN

@write_event
@write_event
@write_event
1👍1🔥1
Channel photo updated
🔥 ተመልሰናል! 🔥
ከተወሰነ ጊዜ ዝምታ በኋላ እንደገና ወደ እናንተ ተመልሰናል።
ከዛሬ ጀምሮ በየቀኑ ጥራት ያላቸው ፖስቶች፣ አዳዲስ ሀሳቦች እና አስደሳች ይዘቶችን እናቀርባለን።
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከእኛ ጋር ለነበራችሁ እናመሰግናለን። ❤️
ዝግጁ ናችሁ? 🚀
4
"ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም። ህይወት እንደ ቡና በወተት ነው። ወተቱ እውነት ቡናው ውሸት ይሁን። ግን ይሄ ልዩነት በአንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ በአንድ በኩል ቡና በሌላው ወተት የለም። ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው። ህይወትም ውስጥ በቀኝ በኩል እውነት በግራ በኩል ውሸት የለም። ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነትና የውሸት ቅልቅል ነው።"

ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር
🍃🤝
🥰4
ለፈገግታ 😂

አንድ ጓድኛዬ የሁለት አመት ፍቅረኛው ታማበት ፀበል ነገር ይዟት ይሄዳል ወደ ገዳም!

እንደወሰዳትም "አንተ የseyጣን ነገር ነው  መለፍለፍ  ጀመረች ሳምንት እንቆያለን" ብሎ ደወሎ አሳወቀኝ!

በመጨረሻም በሳምንቱ ከፀበል መመለሱን ነገሮኝ  እንገናኝ ብሎኝ ተገናኝን...

ያው እኔም እንዳገኘውት እንዴት ሆነች ተሻላት ወይ ምናምን ብየ ጠየኩት!

"አዎ!...ግን  የሷን ነገር አታውራብኝ " ምናምን አለኝ

ነገሩ ግራ ሲገባኝ ምን ተፈጥረ? ምናምን ስለው ...መለያየታቸውን ነገረኝ!

ግራ ገብቶኝ የታመመች ልጅ ወስደህ ፀበል  አስጠምቀሃት (seytan ኬዙ ሲሻላት ) ለምን ተለያያችሁ?... ስለው

እሱም ቀጠለና "ባክህ ከፀበል ስንወጣ 'ይቅርታ መለያየት አለብን አለችኝ! ራሷ...'  እኔም ደንግጨ ለምን ? ስላት ...'አንተን የሚያፍቅርህ እኔ አልነበርኩም ሰይጣኑ ነበረ " አትለኝም መሰለህ"....ብሎ ነገረኝ ....

By Jah mac
😂

https://t.me/write_event
😁5
‎ሰራተኛ እያፈላለኩ በደላላ አንዲት  ልጅ አገኘው

‎አንገቷን እንደደፋች "ጋሽዬ እኔ የስራ ሆነ የሙያ ችግር የለብኝም ብቻ ‎ስራ እንዳልቆይ ተደግሞብኛል ፤ ሰርቼ እንዳልለወጥ አሰርተውብኛል" ምናምን ብላ ዘበዘበች


‎"ብሎ ነገር የለም እኔ ተረት ተረት አልወድም ድግምት ምናምን የለም " ብዬ ካለችው አምስት መቶ ብር ጨምሬ ቀጠርኳት

‎21 ቀን እንደሰራች
‎አንዴ

‎ጠረጴዛዬ ላይ አንገቴን ደፍቼ እየፃፍኩ አንድ ሶስቴ ስጠራኝ አልሰማ ብያታለሁ መሰለኝ
‎"ምን አባህ ይዘጋሃል ብላ"
‎ይዛው በነበረው ፔርሙዝ  አናቴን አለቺኝ

‎ተጮኸ። I think እኔ ነኝ የጮህኩት
‎ጎረቤት ተሰበሰበ ‎መቼ ፣ ማን እንደመታኝ በደንብ ያወቅኩት ከሁለት ቀን በኋላ ነው

‎መንፈስ ፣ ድግምት ፣ ተተብትቦብኛል የሚለኝ ሰው ሲገጥመኝ የጀመረውን አረፍተነገር ሳይጨረሰው ነው የማመልጠው

‎የሻሼን ፍንክት የቀመሰ ሰው በዚህ ነገር አይፈላሰፍም 😁

By Adhanom Mitiku

https://t.me/write_event
😁3
የጠቋር  ሚስት 😂

ጓደኛዬ አዲስ ሙሽራ ነው። ገና ስድስት ወሩ ነው ካገባ። የሆነ እሁድ ጠዋት ልጠይቃቸው ቤታቸው ስሄድ ይሄን ገንገበት ጓደኛዬን ባለቤቱ “ዳዲ” እያለች ስትጠራው ሰማሁ። ተወልዳ እስክታድግ በአንድ የአምበሳ ቆዳ ጫማ እየዳከረ ያሳደጋትን የአባቷን ስም እንደቀልድ ለስድስት ወር ባሏ መስጠቷ ግርም አለኝ። አጎቴ "ሴትና የቀበሌ ቤት የኔ ነው አይባልም" የሚለው እውነት ሳይሆን አይቀርም።

ቤታቸው የሄድኩት እሁድ ጠኋት ስለነበር “ቸርች ልንሄድ ስንል መጣህ” ብለው አብረን ካልሄድን አሉኝ። ላለመሄድ ብሞክርም ባለቤቱ ቆጣ ብላ “ኖህ! ወደድራፍት ቤት እንሂድ ቢሉህ መች እምቢ ትላለህ? በል ተነስ” አለችኝ።
ይሄ ግምብ ራስ ባሏ ድራፍት እንደምወድ ነግሯታል ማለት ነው። ሰነድ መሻሻጥ ተጀመረ? ብዬ እያመነታሁ አብሬያቸው ሄድኩ።

የወሰዱኝ ቸርች አንድ ነብይ የሚያገለግልበት አዲስ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ነው። ጓደኛዬ ባለቤቱ በቅርቡ ጌታን እንደተቀበለች ነግሮኛል። ገና ውስጥ ገብተን አረፍ እንዳልን በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸች ትፀልይ ጀመር።
“ጌታ ሆይ ለዚህ አብሮን ለመጣው፣ ነፍሱ በሃጢአት ለታሰረችው ጎስቋላ ወንድሜ ዛሬ ድረስለት” ስትል ደነገጥኩ። ጭራሽ ስለኔ ነው ፀሎቱ?
“ጌታ ሆይ” አለች ጭራሽ ተንጠራርታ እጇን ትከሻዬ ላይ ጭና። ድምጿ እየጨመረ ነው
“ጌታ ሆይ፥ ዛሬ ስለዚች ነፍስ እፀልያለሁ ...” አለች። {እቺ ነፍስ የተባልኩት እኔው ነኝ}
“ዛሬ እቺ ነፍስ ከስካርና ከሃጢአት ቀምበር እንድትላቀቅ እፀልያለሁ፥ እቺ ነፍስ ዛሬ ከዝሙትና ጌታ ከማይከብርበት የሃጢአት ልምምድ እንድትፈታ እፀልያለሁ” ስትል ቀና ብዬ ምእመኑን አየሁ። እኛ አጠገብ ያሉ ምእመናን ሁሉም ወደኔ እጃቸውን ዘርግተው ይፀልዩልኛል። የት ልግባ? ጭራሽ በሰው ሁሉ ፊት ሰካራም ነው። ያመነዝራል። ትበለኝ? ለምን አንደኛዋን የቲክቶክ ቪዲዮ አትሰራብኝም?
ዞር ብዬ ጓደኛዬን ሳየው ሳቁን አፍኖ በቆረጣ ያየኛል። በስጋ ብገለጥበት ደስ ባለኝ። እሱ ነው አብረን በነበርን ግዜ ምንሰራውን ነገር ሁሉ ዘክዝኮ ነግሯት የሰው መሳቂያ ያረገኝ።

የተወሰነ ቆይቶ ነብዩ ወደመድረክ ወጥቶ ፀሎት ማድረግ ጀመረ። ቤቱ ፀጥ አለ። አንዳንድ ሰዎች ብቻ በየመሃሉ አሜን ይላሉ። እሱም ትንሽ ከፀለየ በኋላ ...
“የጌታ መንፈስ ጅብ ጋላቢ መንፈስ ያሳየኛል” አለ። የዚህ ግዜ የጓደኛዬ ሚስት ዞር ብላ አታየኝም መሰላችሁ? ምናባሽ ላርግሽ? ብላት ደስ ባለኝ። አንተ ነህ  ለማለት ፈልጋ ነው? ይሄ የተረገመ ልጅ ጅብም ይጋልባል ብሏት ይሆን እንዴ?

ነብዩ ቀጠለ። “በጉባኤ ውስጥ አንድ ሰው ይታየኛል። ቤተሰቦቹ ቃልቻ ነው ሚያመልኩት። እሱንም በልጅነቱ በአጋዘን ደም ያጥቡት ነበር። ዋናው የአጋንንቶች አለቃ ይጠቀምበታል” ሲል በሃዘኔታ እንደገና ዞራ አየችኝ። አረ እቺ ሴትዮ ለምን አትፋታኝም? እያልኩ ፀሎቱን መከታተል ጀመርኩ።

ነብዩ ወደኔ አካባቢ ፍጥጥ ብሎ ካየ በኋላ ከመድረክ ወርዶ ቀጥ ብሎ መጣ ..... አሁንስ እኔም ፈራሁ። ስለኔ ነው እንዴ ሚያወራው? የሚል ሃሳብ ውልብ አለብኝ። ምናልባት ነፍስ ሳላውቅ ቤተሰቦቼ እንዳለው በአጋዘን ደም አጥበውኝ ይሆን እንዴ? መቸስ ሰው ማመን ከባድ ነው በዚህ ዘመን ምናምን እያልኩ ሳስብ ነብዩ አይኑን አፍጥጦ ቀጥ ብሎ እኛ ወዳለንበት መጣና እጁን አንስቶ....... የጓደኛዬ ሚስት ላይ ሲጭን ከተቀመጠችበት ወምበር ሁለት ሜትር ወደላይ ነጥራ መሬት ላይ ተነጠፈች። እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ። ምን ጉድ ነው?

በኔ ሲስቅ የነበረው ጓደኛዬ ሚስቱ እንደዚያ ስትሆን ሲያያት ክፉኛ ደነገጠ። እኔም ምን መጣ ብዬ አንዴ ነብዩን አንዴ እሷን ማየት ጀመርኩ
ነብዩ “ዋናው መንፈስ ተያዘ!” ሲል ጉባኤው በጩኸትና በጭብጨባ ተሞላ። ከዚያማ ያቺ ድምፀ ለስላሳዋ የጓደኛዬ ሚስት በሙላቱ አስታጥቄ ድምፅ ትለፈልፍ ጀመር

“ተቃጠልኩ! አረርኩ!”
“ማነህ?” አለ ነብዩ
“ጠቋር ነኝ”
“ተናገር የት ነው የያዝካት?”
“ባሏ ነኝ። ከልጅነቷ አሳድጌ ነው ያገባኋት” አለ ሴጣኑ። ጓደኛዬን አየሁት ሚገባበት ጠፍቶታል። “ጭራሽ የሌላ አካልን ሚስት ነው ያገባሁት?” የሚል ይመስላል።
አጋንንቱ ጭራሽ ወደሱ አፍጥጦ “አጠፋሃለሁ አንተ እርጉም ሚስቴን ነጠቅከኝ” እያለ መጮህ ጀመረ። ቺት አድርጋበት መሆኑ ነው።
ጓደኛዬ እንዲሁም ፈሪ ነው ጭራሽ አሁን ከሰይጣን ጋር የግል ፀብ ውስጥ በመግባቱ ያልበው ጀመር።

ያቺ መላአክ የመሰለች ሚስቱ ጭራሽ አይኗን አፍጣ በወፍራም ድምፅ ዛቻዋን ቀጠለች።
“ወንድወሰን ደበበ ጊሚራው” አለችው ሌባ ጣቷን ወደሱ ጠቁማ። {ዳዲ ቀረ በቃ}
ነብዩ ዝም ብሎ ያያል።
“አንተን ካላጠፋሁ እኔ ጠቋር አይደለሁም” አለ መንፈሱ። ጓደኛዬ እንባ ተናነቀው። በሆዱ "Who TF did i marry?" እያለ ነው
“ብዙ ግዜ በተኛህበት በገጀራ እንድትሰነጥቅህ አቅጄ ነበር። ዛሬ ይሄ ነብይ ቀደመኝ” እያለ ማጓራት ጀመረ። ጓደኛዬ እንባውን በአራት መንታ አወረደው። ምን ውስጥ ነው የገባሁት? የሚል ይመስላል።

ብቻ አጋንንቱ ከነብዩ ጋር ውጣ አትውጣ እያለ ሲታገል እኔ እንደምንም ሾልኬ ወጥቼ ወደቀበሌ ጃምቦ ቤት ሮጥኩ። ከአዳራሹ ወጥቼ ጥቂት እንደሮጥኩ ሩጫዬን አቀዘቀዝኩና ወደኋላዬ ስዞር ጓደኛዬ ኮቱን ጥሎ በሩጫ ወደኔ ይመጣል። አጠገቤ ሲደርስ እያለከለከ ቆመና
“ወዴት ነው ጥለኸኝ ምትሮጠው” አለኝ
“እንዴ አንተስ ሚስትህን ጥለህ ወዴት ነው?” ስለው
“አፍህን ዝጋ” ብሎኝ አብሮኝ ወደግሮሰሪ አመራ።

አሁን ሰባተኛ ጃምቧችን ላይ ደርሰናል። “እኔ ግደሉኝ እንጂ ያቺን ሴት አምኜ እዛች ቤት አላድርም” ስላለ ተሰብስበን ወደቤቱ እንዲሄድ እየለመንነው እንገኛለን።

By  Noah Daniel

😂
😂
😂
😂
😂
😂
JOIN
====
https://t.me/write_event
😁5
ንጉሱ  ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት  ቆንጅዬዋ ሚስቱን  በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈት እና ሚስቴን አግባት…" ብሎት ፈረሱ ላይ ወጥቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ።  ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው አቧራማ ንፋስ እንዳለ አየ።  ቆም ብሎ ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየሮጠ ሲመጣ አየ።
...
"ምነዉ ምን ሆንክ ?" ብሎ ንጉሱ ጠየቀ። በጣም ከመሮጡ የተነሳ ትንፋሹ እየተቆራረጠ ጓደኛው ሙሳ "የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ" ሲል መለሰ።
....
"ምን?"  ብሎ ንጉሱ አይቶት በድንጋጤ እና በመገረም አየዉ  ቁልፎቹን ከመሞከሩ በፊት ለአራት  ቀናት ይቅርና ለ አንድ ሰአት እንኳን አልጠበቀም።
...
እንደ “ጓደኞችህ” ከምትቆጥራቸው ሰዎች ጋር ተጠንቀቅ እና በትጋት ለምታገኘው ሃብት አደራ ልትሰጣቸው ትችላለህ፤ እነሱ በቅርቡ እንድትሞት እየተመኙልህ ሊሆን ይችላል እና እራስህን  መጠበቅህን መዘንጋት የለብንም።

(ዶክተር እዮብ ማሞ-ንጉሱ የኦቶማን ንጉስ አህመድ  ነው ብሎ ነው ታሪኩን የፃፈው። )

😂
JOIN
====
@write_event
@write_event
@write_event
😁3
የደራሲ ቅጣት ...

የሆነ ሰውዬ ይሞትና ገነትንም፣ ሲዖልንም ይጎበኛል፡፡ ገነት ሲደርስ በጎ ምግባሮች እንደቀጠሉ ናቸው። መልካም ሰርተው የፀደቁትንም አስተዋለ፡፡ ይልቅ የገረመው አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ የሚፅፍ ሰው ተመለከተ። ገረመውና ምን እንደሆነ ቢጠይቅ "ደራሲ ነው" አሉት። እየተደነቀ “አይ ደራሲ ፀድቆም አያርፍ፣ አሁኑም ይፅፋል” ሲል ተደመመ።

ከሚንቀለቀል የእሳት እቶትን ውስጥ የሲዖልም ሕይወት ቀጥላለች። አመፅ፣ ግርግሩ፣ ጦርነቱ…ኃጥያቱ አናት ባናቱ ይደራረባል። አሁንም አንድ ሰውዬ ከእሳት ዛፍ ስር አረፍ ብሎ በእሳት ብዕር፣ በእሳት ወረቀት ይቸከችካል። ተመልካቹ ሰውዬ ግራ ተጋባም ምን ሊሆን ይችላል ሲል እያሰበ ጠየቀ "ደራሲ ነው፣ ይከትባል" አሉት።

እየተገረመ፣ እየተደነቀ መልዓኩን "ቆይ ደራሲ እዚህም ሲፅፍ አይቼዋለሁ… እዛም ሲቸከችክ ተመልክቼዋለሁ ካዲያ ገነትም ገባ፣ ሲዖልም ወረደ ምን ቀረበት? ምንድነው ቅጣቱ? ምን ተጎዳ?" ሲል ጠየቀው።

መልዓኩም መለሰለት “ገነት ያሉት ይታተምላቸዋል"😂

By Alemayew Gelagay

Join
https://t.me/write_event
1😁1