ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ጋሽ ስብሃት አንዴ የሆነ ሞል ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ለሽያጭ ተሰቅሎ ያያሉ። ወደ ሻጩ ጠጋ ብለው

"ስንት ነው?" ብለው ጠየቁ።
ሻጭ "3 ሺህ ብር"
ፈገግ አሉ ጋሽ ስብሃት።
ሻጭ የተወደደባቸው ስለመሰለው ጋሼ ለእርሶ አስተያየት ይደረጋል። በስንት ይወስዳሉ?
ጋሽ ስብሃት "ይሁዳ ከነ ነፍሱ 30 ብር አይደል እንዴ የሸጠው? እንዴት ለስዕል 3 ሺህ?"😄
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
#ምን_ነበር?


የፍቅራችን እሣት ነዶ ግሞ ንሮ በቅቶት ሲበርድ፤
አስመስሎን እንዳረፈ አንቺን ከሰል እኔን አመድ፤
አንቺ ዳግም ስትነድጂ ፍም ስትሆኚ ገጥመሽ ከሰው፤
እኔ ስዛቅ በመጫሪያ እንደትቢያ ስታፈሰው፤
ልረሳሽ ቃል ገብቼ ተግብሬአለሁ አንድ ነገር፤
ያደረኩት ግን ምን ነበር?


አንቺን ማጣት፤
አንድ ግዜ የእግር እሣት፤
አንድ ግዜ የቋንጃ እከክ፤
እየሆነኝ ስብረከረክ፤
እኔው ለኔው ቃል ገብቼ፤
ካልረሳዋት ወንድ አይደለው ይቺን አባይ ብዬ ዝቼ፤
የተጫነኝ ዝግባ ቀንበር፤
ከልቤ ላይ እንዲሰበር፤
ትዝ ይለኛል ተግብሬአለሁ ምስ የሚሆን አንድ ነገር፤
ያደረኩት ግን ምን ነበር?


እንዳይከፋሽ እንድትስቂ፤
አንዴ ህፃን አንዴ አዋቂ፤
መሆኔን ቢያይ ውስጥሽ ውስጤን አበክሮ ስላወቀው፤
አሳቻ ሰዓት ደባ ፈትለሽ ቀበቶዬን ሳላጠብቀው፤
መልህቁን የመርከቡን ሰውረሽው ድብቅ ቦታ፤
ማበል ወጀብ እየናጠኝ እያየሺኝ ስንገላታ፤
ብቅ ጥልቅ እያስባለኝ ከወደቡ እልፍ ርቄ፤
ለብቻዬ ተጠብቤ ለብቻዬ ተጨንቄ፤
መውጫ ባጣ ማርያም መንገድ፤
ቃል ገብቼ የዛን ግዜ ፍፁም አንቺን ላለመውደድ፤
ተግብሬአለው አንድ ነገር አንቺን ከቶ እንዲያስረሳኝ፤
ምን ነበር ግን ያደረኩት? አለኝ ዛሬ አልወሳኝ።


አሁን ሳስብ በትውስታ፤
የሆነ ግዜ የሆነ ቦታ፤
ከልቤ ላይ እንዲነቅለው ያንቺን ሰንኮፍ የተጣባኝ፤
አንድ ነገር አድርጌአለሁ ግን ምን ነበር ግራ ገባኝ?


ትዝ የሚለኝ ብቻ ዛሬ፤
ያንን ነገር መተግበሬ፤
አንቺን ማጣት አንቺን መርሳት፤
ግዙፍ ቋጦኝ ዳገት መግፋት፤
እንዳልሆነ ሰብቆልኛል ይባስ እንደው በተቃርኖ፤
አንቺን መርሳት ፊቴ ቆሟል ደቂቅ ገቢር ኢምንት ሆኖ።


አይረሳኝም ስትዪ ሰማው ...
እንኳን ያንቺን ፍቅር ቀርቶ ለኩነኔ ላሳር ሰቶኝ እኔን ያኔ ያሳነሰኝ፤
የዛን ግዜ የፈፀምኩት እንድረሳሽ ያደረገኝ ፅድቁም ተግባር መች ታወሰኝ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ <<ተመስገን>> በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!

ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር
(ጋሽ ስብሀት)

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
#እንዲ_ነው_ሚከፈል



ትላንትና ሌሊት ናፍቆትሽ ቀስቅሶኝ አስሬ ስነሳ፣
እንደው የኔ ፍቅር ያየሁት አበሳ፣
አሰኝቶኝ ነበር በካልቾ በጥፊ በመታውሽ ብዬ፣
ዳሩ ምን ያደርጋል ዛሬም አብሬሽ ነኝ መከፋቴን ጥዬ።


እናም...
ቀን ቀንን ሲተካ ሲገባኝ ምስጢሩ እያደር ስረዳው፣
እንዲ ነው ሚከፈል ሰው የማፍቀር እዳው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"ቀልዴን አይደለም የምለው አዲስ ነገር የለኝም ሌሎች ያልዳሰሱት ምን አዲስ ነገር ልፈጥር እችላለሁ? በፃፍክና ባነበብክ ቁጥር ብልህ ከሆንክ የምትገነዘበዉ ነገር ቢኖር ዝም ማለት የሚመረጥ መሆኑን ነዉ። እዉነቴን ነዉ። የገደል ማሚቱ ከመሆን ዝምታ ይመረጣል።በራስህ የዝምታ ጥልቀት ዉስጥ መስመጥ እራሱ ዉበት ነዉ።"

"ኦሮማይ"
በዓሉ ግርማ

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ሰሞኑን ለምርመራ ወደ አንድ የግል ክሊኒክ ሄድኩኝ። ዶክተሩን ሳየው ድሮ አብረን የተማርነው ዮሐንስን መሰለኝ። "ዮሐንስ ደግሞ እንዲህ ሊያረጅ አይችልም" ብዬ እያሰብኩ ተራዬ ደረሰና ገባሁ።

እንደገባሁ ጠየቅሁት፣

"አንተ ዮሐንስ ነህ እንዴ?"

"አዎ ነኝ" ሲለኝ በጣም በማርጀቱ ደነገጥኩና

"ዩኒቨርስቲ አውቅሃለሁ"

"ዋው! የምን አስተማሪያችን ነበርክ?"

ባሻዬ! ጠላትህ ይደንግጥ። እኔ ከሱ በላይ አርጅቻለሁ ማለት ነው? ሰው እኮ እንደ ዝንጀሮ ነው። የራሱ ቂጥ አይታየውም።

ⓒተስፋዬ ሃ/ማርያም
ከማዕደ ጥበብ ገፅ

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
የዘመናችን የብሔረሰብ አለቆች በተወለዱበት ከተማ ውስጥ ሆስፒታል ለመስራት አምስት ሳንቲም አያወጡም ።ይሁን እንጂ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ሆስፒታል ቢያቆም በየትኛው ቋንቋ የተፃፈው ስሙ ይቅደም የትኛው ይከተል በሚለው ዙርያ ዱላ ቀረሽ ክርክር ሊያደርጉ ይችላሉ።
ምንጭ -ከአሜን ባሻገር መፅሐፍ
ደራሲ -በዕውቀቱ ሥዩም
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
Book for ALL |

የትንሽ ነገር ... ከሲኣት ትንሿ እህቴ ከሩቅ እየተጣራች መጣች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ”

እናታችን ለጨረሩ መከላከያ መዳፏን ግንባሯ ላይ አጋድማ “ምነው? ምን ሆንሽ?” አለች “ዱላ ስጪኝ ዱላ ስጪኝ” “ምነው? ለምንሽ?” “አለቃ ተመረጥኩ” ዱላ አሳጥራ ሰጠቻት። . . . አመሻሽ ትንሿ እህቴ እያለቀሰች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ” እናታችን “ምነው? ምን ሆንሽ?” “ከአለቃነት ተሻርኩ”
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ርዕስ፡ውልብታ"
ደራሲ፡አለማየሁ ገላጋይ ገጽ፡፶
---------------------------
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
---------ላንመለስ
እንሂድ ብላኝ ተከትያት ፣
ቃል ስትሰጠኝ ቃል አምኛት ፣
ስትጎትተኝ ስጎተታት ፣
ስመናተል ሳባብላት ።

ኼዴን ኼዴን ኼዴን...
ላንመለስ መንገድ ጠፋን ።
---------------------------
"አሁንም አይደል ወደ ማታ.."
ገፅ - 100
ደራሲ - ሔኖክ ደመቀ
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
B O O M
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
🎉🎉💥💥ቤተሰብ 💥💥🎉🎉
👏👏👏1K💎 ገብተናል👏👏👏
🎉🎉እንኳን ደስ አለን🎉🎉
አብሮነታችሁ አይለየን ተያይዘን ወደ 2K እንዘልቃለን
Share 🤩 በማድረግ ላገዛችሁን ፈጣሪ ያክብርልን ያላደረጋችሁ ደግሞ የ2K ጉዞ ላይ አሻራችሁ ያስፈልገናል። በብዙ ክበሩ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
💥🎉🔥🎉💥🎉🏵🎉🔥💥

ኪነ - ቃል
ስልጣንሽ ያልገባኝ

ልረሳሽ አስቤ . .  .


ፎቶሽን ቀደድኩኝ
አንቺን ማስታወሻ
ሁሉን አቃጠልኩኝ
ልነግርሽ ያልኩትን
ከምላሴ ጣልኩኝ።

ሞከርኩኝ።

አንቺን ላለማሰብ
ልቤን አተጋሁኝ
ስምሽን ከከንፈሬ
ቀፍፌ አነሳሁኝ።
ግና
የማራቅ ጉዞዬ
በማጣት ሲተካ

እንደ ላጲስ ገላ
ሳጠፋሽ ስጠፋ .  .  .
አንቺ እያለሽ ያለው ፥ ወጥተሽ ከቀረው ጋር
ህይወቴ ሲናጸር ፣ መኖር ሲለካ
ታወቀኝ. . .
እኔን ስል የኖርኹት ፥ አንቺን ነበር ለካ።



ከዘንባባ መፅሐፍ
ምግባር ሲራጅ

SHARE🌼

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
The Passion Of The Christ  በአማርኛ "የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር" ማለት ሲሆን ይህ ፊልም እኤአ በ2004 በUnited States of አሜሪካ ከታላቁ መፅሐፍ ቅዱስ የሀዲስ ኪዳን ክፍል በሆኑት ማቴዎስ ወንጌል ፣ ማርቆስ ወንጌል እና ዮሐንስ ወንጌል ላይ ተመስርቶ የተሰራ የአንድ ሰዓት ከ34 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ፊልም ነው::

ፊልሙ በታዋቂው የሆሊውድ ፊልም ባለሞያ ሚል ጊብሰን ዳይሬክት እና ፕሮዲውስ የተደረገ ሲሆን  እንዲሁም በፊልሙ ጂም ካቪዜል እንደ 'ናዝሬቱ ኢየሱስ' ሚያ ሞርገንስተር እንደ 'ድንግል ማርያም' ሞኒካ ቤሉቺ እንደ 'መቅደላዊት ማርያም' በመሆን በድንቅ በቃት ተውንውበታል::

__

ታዲያ የሚገርመው ይሄን ፊልም ሰርቶ ለመጨረስ ባለው ውጣ ውረድ ውስጥ ብዙ አስደንጋጭ እና አስገራሚ እውነታዎች ገጠሟቸው እንደነበር ጂም ካቪዚል እና ዳይሬክተሩ ሚል ጊብሰን የቴሌቭዥን ሾው ላይ ቀርበው አስረድተዋል

___
የኢየሱስ ክርስቶስን ገፀ-ባህሪ ተላብሶ የተወነው ጂም 130 ፓውንድ ወይም 68 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን መስቀል ተሸክሞ በሚሄድበት ትዕይንት ወቅት  መስቀሉ ጂም ላይ ወድቆበት የግራ ተከሻው ውልቃት ደርሶበታል:: ጂም ይህንን ክስተት ለጋዜጠኛ ሲያስረዳ "መስቀሉን ተሸክሜ ስሄድ በጣም ከብዶኝ ስለነበረ ፊቴ ላይ የሚታየው ስሜት እወነተኛ የስቃይ ስሜት ነበር" ብሏል::

ሌላው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ እጅና እግሩ ታስሮ በአደባባይ ጲላጦስ ፊት የሚገረፍበትን ትዕይንት ለማሳየት እንደ ክርስቶስ ሆኖ የሚተውነው ጂም እጅና እግሩ ታስሮ ባለበት ገራፊው ድንገት በያዘው ጅራፍ ሁለቴ ሲገርፈው ጂም እጅግ በጣም የህመም ስሜት እንደተሰማው ይናገራል:: "እንደ ክርስቶስ ሆኜ እየሰራው በህመሙ ምክንያት ግን ገራፊዎቼ ላይ እንደ ሰይጣን ነበር የሆንኩባቸውም" ብሏል::

በዚህ ፊልም የጂም ጉዳት በዚህ ብቻ አላበቃም በቀረፃ ወቅት ሁለቴ በመብረቅ ተመቷል:: አንደኛው መስቀል ላይ ተሰቅሎ በሚቀረፅበት ሰዓት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተራራ ላይ ሆኖ ደቀ መዝሙሮቹን እያስተማረ በሚቀረፅበት ሰዓት ነበር:: ጂም ሾው ላይ ቀርቦ ስለሁኔታው ሲያስረዳ "መብረቁ እንደሚመታኝ ታውቆኝ ነበር እናም ተራራ ላይ እያስተማርኩ ሳለ መታኝ ረዳት ዳይሬክተሩ መጥቶ Are you okay ሲለኝ መብረቁ ድጋሚ እሱንም መታው::

ሌላው አስገራሚው ነገር ደግሞ ይህን ፊልም ለመስራት የኢየሱስን ገፀ ባህሪ ተላብሶ የተወነው ጂም የጀርባውን ግርፋት እና አናቱ ላይ በተደረገው እሾህ አክሊል ምክንያት በፊቱ ላይ ይፈስ የነበረውን የደም ጎርፍ ለማሳየት በየቀኑ ለ10 ሰዓታት ያህል ቆሞ ሜካፕ ይሰራ ነበር :: ታዲያ ይህንን ሜካፕ ለመሰራት አስር ሰዓታትን በየቀኑ እርቃኑን ሰለሚቆም ለሳንባ ምች በሽታ ተዳርጎ ነበር::
_

ሌላኛው እውነታ ደግሞ ይህን ፊልም ለመስራት በገጠማቸው ገጠመኝ እና ባሳለፉት ሁነቶች ምክንያት አብዛኛው የፊልሙ ክሩ እምነታቸውን ወደ ክርስትና ሊቀይሩ ችለዋል:: ይሁዳን ሆኖ የተጫወተው ሉካ ሊኦኔል ፊልሙን ከመስራቱ በፊት በእግዚአብሔር መኖር የማያምን ሰው ነበር ነገር ግን ፊልሙን ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ከእነቤተሰቦቹ ጌታን ተቀብሎ ተጠመቀ:: ሌላም እንደዚሁ በፊልሙ ውስጥ ቴክኒካል ስራ የሚሰራ የነበረ ሰው እርሱም እንደዚሁ ተጠምቆ ጌታን ተቀብሏል

___

ሌላኛው ደግሞ ክርስቶስ በምድር መከራን በተቀበለበት ጊዜ ምንም አይነት የሙዚቃ መሳሪያ ባለመኖሩ ምክንያት የፊልሙ ዳይሬክተር ሜል ጊብሰን ምንም አይነት Musical Score ፊልሙ ላይ አይገባም ብሎ ነበር...ነገር ግን ምክትል ዳይሬክተሩ አንድ Musical Score ብቻ ይግባበት ብሎ ሃሳብ አስቀይሮት ገብቶ ነበር ያቺ አንድ Musical Scoreም በ2005 Oscar ላይ በቤስት Origional Sound ታጭታ አሸናፊ ሆናለች::

ሌላው አስደናቂ ነገር ይህን ሙሉ ፊልም ፕሮዲውስ ለማድርግ የትኛውም የፊልም ፕሮዳክሽን ስቱዲዮዎች ፈቃጀኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው የፊልሙ ዳይሬክተር ሚል ጊብሰን ከኪሱ 30ሚልየን ዶላር በማውጣት ነበር ፕሮዲውስ ያደረገው:: ታዲያ ፊልሙ ለዕይታ ከበቃ በኋላ ግን 18 ዕጥፍ ገቢ ማስገባት ችሏል ያ ማለት 611 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው::

____
ይህን አስደናቂ ፊልም ለህዝብ ዕይታ ሲወጣ ሲኒማ ቤቶች ደጃቸው በወረፋ ተጥለቅልቆ ነበር የሚገርመው በወረፋ ተጋፍተው ገብተው የኢየሱስን ግርፋትና ስቃይ ማየት አቅቷቸው አቋርጠው የወጡ ለመቁጠር የሚያታክቱ ቢሆኑም መከራና ስቃዩን በእንባ እየታጠቡ ያዩ ደግሞ እልፍ ነበሩ

አበቃሁ!

Yoakin bekele


SHARE🌼

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
👍1
ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት. . .
"ሄሎ"
"ሄሎ ሰላም ነው?"
"አለሁ።"
"ምን እየሰራሽ ነው?"
"እኔ?.... እዚህ ተኝቼ አንተን አስባለሁ።"
"እኔም አንቺን እያሰብኩ ነበር።"
"ለምን አልደወልክም?"
"ፈርቼሽ።"
ለምን ፈራኸኝ?
"እውነት ስላሌሽ።"
"እውነቴ ከአንተ አይበልጥም።"
"ስልክህን ስጠብቅ ዛሬን አንድ ቀን አመታት ኖርኩኝ። ያረክብኝን ሳይሆን አለመደወልህን ሳንሰላስል ብዙ ብዙ አሰብኩ።"
"ምን አሰብሽ?"
"አንተን ማጣት፣
አንተን መተው፣
አንተን መርሳት፣
አንተን ነበረ ማለት፣
አንተን ድሮ ማለት፣
አንተን የበፊቱ ማለት፣
ከዛ ፈራሁ፣
አለቀስኩ፣
አልተፅናናሁም፣
ከራሴ ተጣላሁ፣
ከኔ በለጥክብኝ። ከኔ ገዘፍክብኝ።"
( እሱ ይሰማኛል እኔ አወራለሁ )
"አ ፈ ቅ ር ሃ ለ ው እኮ. . . . ስቅስቅታዬ ቃለን ቆረጠው።"
( በደረቀ ቆፈናም ድምፀት)
"በድዬሻለሁ እኮ አለኝ።"
"ቶሎ ብዬ ይቅር ብየሃለው አልኩት. . . ."
"ፀጥ አለ። እረጭ። እረጅም ዝምታ. . . . .ዝም አለ።"
( እንባዬ ይወርዳል ቃሉን ጠብቃለሁ. . . .)
( በተሰበረ ድምፅ )
"አይገባኝም። አለኝ"
"እሱን የመወሰን መብት የለህም። አልኩት ቆጣ ብዬ"
(የመተው ዋዜማ ላይ እንዳለሁ ሲሰማኝ ነው የዋለው። እሱ በልቡ ያሰበውን በልቤ ሰምቼው ኖሯል። የማፍቀር ትልቁ ጥበብ ያፈቀሩትን ሰው ልብ ማድመጥ ነው መሰለኝ። ለካንስ እውነት ነበር።)
"ማሬ አልችልም። አለኝ"
ስፈራ ስተባ. . . ም ኑ ን? አልኩት
"ይሄን ተሸክሜ አብረሽ መሆን አልችልም። ይቅርታ ስልኩን ልዘጋው ነው።"
"ቆይ ቆይ ላስረዳህ. . . እንደዚህ አይደለም እኮ ፣ የኔ ፍቅር እንዳዘጋው በፈጠረህ"
"ማሬ አሁን ላወራሽ አልችልም።"
( ተ ዘ ጋ )
የጆሮዬ ታንቡር ላይ ኃይለኛ ፍንዳታ የጮኸብኝ አይነት ፣ ተሰማኝ ጭውውው.... አለብኝ ነገር አለሙ ዞረብኝ ፣ መላ ሰውነቴ ሲቀዘቅዝ ተሰማኝ። በረደኝ። ልቤ ስብርባሪው እስከማይገኝ ድረስ ተሰባበረ። መጮህ አማረኝ። በርግጥ መጮህ ያንስብኛል። በኃይል ማንባረቅ ፈለኩ። ትንፋሽ አጠረኝ። ልቤ ላይ አጥወለወለኝ። አንድ ሰው እንዴት በዳይም ጎጂም መሆን ይፈልጋል!? ብዬ ራሴን ጠየኩኝ። ግን እሱ ነው አይደል!? ያፈቅረኛል ብየ የማስበው ሰው ፣ ሁሉ ነገሬን አሳልፌ የሰጠሁት ሰው። አላውቀውም ነበር ማለት ነው!?. . . . ከበደለኝ በደል በላይ የጎዳኝ ይሄኛው ድርጊቱ ነበር። ልቤን ሀዘን ሲውጠው ይሰማኛል። በርግጥ ሀዘንና መጎዳት ራሱ ፣ አሁን እየተሰማኝ ያለውን ስሜት አይገልፀውም። ሌላ ቃል ያስፈልገዋል ፣ የሆነ ባዶነት ውስጥ እንዳለሁ እየተሰማኝ ነው።

ሰብለ ወንጌል(fb)

SHARE🌼

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
👍1
#ኤያስ_መልካ ………አበደ……!!!

ወደ 90 ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ላይ ኤሊያስ ከሚዲያውም ከምሽት ቤቶችም አካባቢ እራቀ እራሱንም ለመንፈሳዊነት አስገዝቶ ስራ እና ስራው ላይ ብቻ አተኮረ ታዲያ በኤሊያስ መጥፋት ላይ ወሬ እና አሉባልታው በረከተ ሙዚቃ አቁሞ ነው፣ታሞ ነው፣እና ከሁሉ የሚገርመው ደሞ አብዶ ነው የሚልም አሉባልታ ነበር  ወሬ እና አሉባልታው በተወራበት ቦታ ብቻ አልቀረም ኤሊያስ ወዳጆች ጆሮ ገባ እና ስጋት የገባቸው ወዳጆቹ እየተወራ ስላለው ነገር መጥተው እንዲህ እየተወራ ነው አሉት …ትኩረቱን በስራው ላይ ያደረገው ኤሊያስ ጉዳዩን ሲነግሩት  ወትሮም ግጥም ያለምክንያት ለማይፅፈው ኤሊያስ መልካ ትልቅ ግብአት ነበርና የተወረወረበትን ጠጠር ለቅሞ ለፍቅረኛ የተዜመ አስመስሎ እንደሚከተለው አርጎ ሙዚቃውን አስውቦ  ገነባው…
              
                 ""    ይዘባርቃሉ
                       ሳይገባቸው  ነገሩ ሁሉ
                       ከቶ ለምን ፈራሽ
                       ማንነቴን በደንብ እያወቅሽ …………""

ከስጋታቸው መላቀቅ ያልቻሉ ወዳጆቹ ግን አሁንም ወሬው በእነሱ ይመጣ ጀመር ይሄኔ ኤሊያስ ወዳጆቹንም ገሰፅ ማድረግን አሰበና የሚከተለውን ጨመረበት ……
                  ""  ፍቅርሽ ላይ ያንቺን ጉዳይ
                      ማን ያውቃል ካንቺ በላይ
                       አልፈርድም በማያውቁ
                       ላንቺ ነው ግልፅ የሆንኩ ""
ሳያዩ ለሚያወሩ እድል አትስጡ እናንተ በቅርብ ስለ እኔ ሁሉን እያያችሁ ሳለ በ እሩቅ ስለሚያወሩ አትጨነቁ ………
                   ""  ውሎ ሲያድር ይረዱታል ""
እያለ ሞገተ አስከትሎም………
                     "" አታውሪ ደግመሽ ለእኔ
                         እያየሽ ሆነሽ ጎኔ
                         ሆድ ባሰኝ እያወቅሽኝ
                         መሰለኝ አንቺም ያልሽኝ ""
እነሱ የሚያወሩትን አትድገሙልኝ የእነሱን ባወራችሁ ቁጥር እናንተም ያላችሁኝ ነው የሚመስለኝ አለ …እሺ ቢያንስ በየሚዲያው እየወጣን እናስተባብል አይነት ምክር ተሰነዘረለት ………የኤሊያስም መልስ የሚከተለው ሆነ
                    """ ግድ የለብንም ማሳመር
                          ሌሎቹን ለማሳመን
                          ውሎ ሲያድር ይረዱታል
                          ኋላ ያፍሩበታል ""……

ይሄውላችሁ ኤሊያስ እንዲህ ያለ ጥበበኛ ሰው ነበር የ ኢዮብ መኮንን " ይዘባርቃሉ " track መነሻ ታሪኩ ይሄ ነው …!!!
ዘመን በይሻራቸው አድረው እንደወይን ጠጅ በሚጣፍጡ ስራዎቹ ሁሌም በልባችን ይኖራል 💖

#ኤሊያስ_መልካ_ኢዮብ_መኮንን የሁለቱንም ነፍስ ይማርልን 💔

ቤዛ አዲሱ !!!
SHARE🌼

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ስለ ተፈጠረው ክፍተት (መጥፋት) ይቅርታ...🙏
ጠቃሚ ትምህርት!

በጃፓን ይማር የነበረ አንድ አፍሪካዊ ወጣት በአንድ ወቅት በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል።

በጃፓን ባለ ፣ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንግዳ ነበርኩ ፣ እና እኔ በምኖርበት ሆቴል መዋኛ ገንዳ ውስጥ እያለሁ ፣ ገንዳው ውስጥ ከእኔ በቀር ማንም አልነበረም ፣ ውሃው ስር ሽንቴ አመለጠኝ ፣ እናም ድንገት... ውሃው ወደ ሮዝ ተለወጠ።

አላርም (ማንቂያው) ጮኸ ወዲያው ሰራተኞቹ መጥተው ከገንዳው ውስጥ አወጡኝ። ከዚያም ውሃውን ባዶ እንደሚያደርጉት እና ገንዳውን እንደሚያጸዱ ነገሩኝ። የሆቴሉን አስፈላጊ ህግና ደንብ እንደጣስኩም ነገሩኝ።

ከዚያ በኋላ ጠሩኝና እንግዳ ተቀባይዋ ፓስፖርቴን ሰጠችኝና ከሆቴሉ እንድወጣ ጠየቀችኝ። 

ከሆቴሉ ወጥቼ ሌላ አማራጭ ፈለግሁ ፣ እና ሆቴል በገባሁ ቁጥር እንግዳ ተቀባዩ ፓስፖርቴን እያየ “ይቅርታ ፣ አንተ ነህ…!?… እኛ ስላልተቀበልንህ ይቅርታ…! ሌሎች ሆቴሎችም ስሄድ ተመሳሳይ ነው… በየትኛውም ሆቴል እንዳላርፍ ስለተከለከልኩ ወደ ኤምባሲው ሄድኩ።

ኤምባሲዬ የመዋኛ ገንዳ የሌለው ሆቴል እንድይዝ መከሩኝ...።

ከጃፓን ስወጣ የፓስፖርት ሹሟ ፓስፖርቴን ስታረጋግጥ ‹ ትምህርቱን እንደተማርክ ተስፋ አደርጋለሁ› አለችኝ።

ማጠቃለያ፡- ሁሉም ጃፓናዊ ሽንቴን በመዋኛ ገንዳ ውስጥ እንደሸናሁ ያውቅ ነበር ፤ እኔ የመጣሁባት አፍሪካዊት ሀገሬ ላይ ግን እስካሁን ድረስ መንግስታችን ከመንግስት ግምጃ ቤት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሰረቀ ማን እንደሆነ አያውቅም።

#ምንጭ:Tales Of Africa
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
#ውሉድ ወወላድ*


የወለደች ኹሉ . . .
እናት አትባልም ! ግብሯ ካልተለየ ፤
የተወለደ ልጅ . . .
አይባልም ጧሪ ! ምግባሩ ካለየ ።

ዘር ስላካፈለ . . .
የአባት መሆን ክብር በከንቱ አይሰጥም !
ከልጅ ስም ቀጥሎ ስሙ አይቀመጥም !

እፍኝትን እይዋት . . .
እናት ትሞታለች ፣ ትውልድ ለማስቀጠል
አባትም ይሠዋል  ፣ በፍትወት መቃጠል ።
አንበሳም ደቦሉን . . .
በጊዜው ካልቀጣ ንግስናው ይቀማል ፤
የልጅነት ሥሥት ፣
የአባትነት ድርሻ ለክብር ይወድማል ።

አዎ !
እናት ክብሯን ይዛ ፣
ልጅ ግብሩን ተላብሶ ፣
አባት በስም ነግሦ ፣
ካልተነፃፀረ ፤
የመዳን ምሳሌው ትንቢቱ ተሻረ ።

#የሞት ጥቁር ወተት
#ተስፋሁን ከበደ

SHARE🌼

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ጋዜጦችን የማታነቡ ከሆነ ምንም መረጃ አይኖራችሁም
የምታነቡ ከሆነ ደግሞ የሚኖራችሁ መረጃ የተሳሳተ ነው።

#ማርክ _ትዌይን