ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ልቧ እስኪጠፋ እንደምትወደኝ አውቃለው ስሜ እስኪጠፋኝ እወዳታለው....አንድ ቀን ፍቅሯ ንሽጥ አረገኝና "ታገቢኛለሽ " አልኩኝ
"ምን አለህ? " አለችኝ በማፌዝ አኳኋን::

"ማለት?" ግራ በመጋባት
"ለኔ የሚሆን ምን አለህ?" አለችኝ።
"ንፁህ ልብ ፍቅርና ጤና ....."
"ጤነኝነትህ መች ጠፋኝ በቀን ሶስት ድንች በአዋዜ ብቻ እየሰለቀጥክ እንዲህ ደልበህ እያየሁ......" አለችኝ።

'ምን?' አልኩ በውስጤ...ደሜ እንደበረንዳ ቡና ይንተከተክ ጀመር
"ቆይ ያ ሁሉ ውሸት ነበር ....አታፈቅርኝም ማለት ነው?"
"አፈቅርሃለው ነገር ግን ፍቅር ብቻ ትዳር አይሆንም?" አለችኝ።
"ፍቅር ትዳር ካልሆነ ታድያ የትዳር ዋስትናው ምንድነው?" ብሽቅ እያልኩ....
"ፍቅር የትዳር ዋስትና አይሆንሞ አላልኩም። ትዳር በፍቅር ብቻ አይቆምም። ትዳር ልብ ለልብ መግባባት፣ ፀባይ ከፀባይ መጣጣም....."

"ጀመርሽ እንግዲ....አትፈላስፊቢኝ" ስል ጮኼ አቋረጥኳት።
"አትጩህብኝ ግልፍተኛ! እንዲሁም አግብቼ እያከክኩ መኖር አልፈልግም ! አላገባህም" ስትል አንቧረቀች።

ሳላስብበት በደመነፍስ በቃሪያ ጥፊ አላስኳት።

አፍንጫዋን ይዛ ስትለቀው እየነሰረች ነበር። ምንድን ነው ያደረግኩት? የምይዝ የምለቀውን አጣሁ...

"አልጎዳሀኝም አትጨነቅ" አለችኝ። አፍንጫዋን መልስ እየያዘች፣ፈገግ ብላ እያየችኝ።

ነስሩ ጋብ ሲልላት

"አየህ ፈተናህን ወደቅክ .....እንደምታፈቅረኝ አውቃለሁ። ዳሩ ግን እንደሮሚዮ እስከመቃብር ሊከተለኝ የሚችል ፍቅር ቢኖርህም፣ ሲጥ አድርጎ ሊገድለኝ የሚችል ግልፍተኝነትህ ያሳስበኛል!" አለች ትኩር አድርጋ እየተመለከተችኝ..…

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
1
የቤት ሰራተኛዬ ነች። ልጆቼ እናታቸውን እኔ ባለቤቴን እስክረሳ ድረስ ቤቱን ቀጥ አርጋ የያዘች ታታሪ ሰራተኛ። በቀደም ለታ ስትፈራ ስትቼር አጠገቤ መጥታ፦

"ጋሼ እንደየው ቅር ካላሎት አንድ ነገር ባስቸግሮት?" አለች። አስሬ ባለቤቴ ወዳለችበት ክፍል ሰርቃ እያየች፡፡
"እሽ ምን ላግዝሽ?"
"እንድያው ጋሼ ለድፍረቴ ቅር እንዳይሎት።"
"ጌጤ ለምን በቀጥታ ወደ ጉዳይሽ አትገቢም?"
"እንድያው፤ ካላስቸገርኮት ደሞዝ ብትጨምርሉኝ? ከእትዬ ይልቅ አንተን ልጠይቅህ ብየ ነው."
"ጌጤ ጥያቄሽ ተገቢ መሆኑን አውቃለሁ። ነገር ግን ወቅቱን ያገናዘበ አይደለም። ሀገራች አሁን ባለችበት ቀውስ የደሞዝ ጭማሪ መጠየቅ ተገቢ አይደለም።" በሚል ሀተታ የጀመረ ረጅም ማብራርያ ጥያቄዋን አለመቀበሌን ገለፅኩላት።

በነጋታው አመመኝ ብላ ተኛች። ከዛሬ ነገ ይሻላታል እያልኩ ሳምንት ያህል ተኛች፡፡

ባለቤቴ ሀኪም ቤት ልትወስዳት ብትፈልግም አሻፈረኝ አለች። እናም እኔ አናገርኳት።

"መዳሃኒቴን ሀኪም መቼ አውቆት?" አለችኝ

"ዱሮስ! ካልታከምሽ፣ ካልታየሽ ሀኪም መደሃኒትሽን እንዴት ሊያውቀው ይችላል?"
"ይተው ጋሼ! ህመሜንም መድሃኒቴንም እኔ አውቀዋለሁ።" አለች በመሃል በመሀሃል እያቀሰተች፡፡

"ካወቅሽ ንገሪንና እናግዝሽ?"

"ህመሜ የቤት ጣጣ፤ መዳሃኒቴ ጥቁር በግ"

"የቤት ጣጣ? ጥቁር በግ?" አልኩ ግራ በመጋባት።

"ከአያት፣ ቅድመ አያት የወረስኩት የቤት ጣጣ፤ ዛር ነው እንዲህ የሚያረገኝ።" አለች፡፡

ዛር!? አንዳች ነገር ስውነቴን ውርር አደረገው፡፡

ማብራሪያዋን ቀጠለች።
"ሀገር ቤት እንዲህ ሲያረገኝ፤ ጥቁር በግ ታርዶ፤ ደሙን በገል ቀድተው ሲሰጡኝ ጠጥቼ...."

"በቃሽ!" ሳይታወቀኝ ጮህኩ፡፡

ወይ ጉድ! ሰው ብዬ ሳይታወቀኝ መለስተኛ-ቫንፓየር ጋር ከረምኩ? የኔስ ይሁን...እነዚህን ትናንሽ ልጆቼን ጉድ አድርጌያቸው ነበር እኮ።

ወጣች። አሰናበትኳት።
°°°°
ከወራት በኋላ የጓደኛዬ ሚስት ወልዳ ልጠይቃቸው ቤታቸው ጎራ አልኩ። ምን ቢሆን ጥሩ ነው? መለስተኛ ቫንፓየሯ ማለትም የቀደሞ ሰራተኛዬ ቤት ውስጥ ሽር ጉድ ስትል አየሁ፡፡ አጠገቤ ለተቀመጠው ኋደኛዬ፦
"ሰራተኛ አገኘህ እንዴ?" አልኩት።
"አንተ በነገርከኝ መሰረት ለደላለው ነግሬው ከአንዱ ደንባራ ቤት አስኮብልሎ አስወጣልኝ"
"ደንባራ? ማለት?" ንዴቴን ዋጥ ለማድረግ እየምከርኩ።

"አዋ! አንተ በነገርከኝ መሰረት ደላለው ከሰው ቤትም ቢሆን አስኮብልሎ እንዲያወጣልኝ መናገር....ከዚያ ልጂቱ ከደላላው ጋር ተነጋግራ "የቤት ጣጣዬ ተነሳ፤ ጥቁር በግ እረድልኝ ማለት።'...ያ ደንባራም፤ ተደናብሮ....."

"በዛ አቦ አትሳደባ" ብዬ አቋርጬው ቤቱን ጥየ ውልቅ።

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"ነጩ ዶክተር ካላከመኝ"

ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከአንድ ነጭ ተማሪያቸው ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው ህመምተኞችን እየጎበኙ ነው። አንድ በአንድ ህመምተኞቹን እያዳረሱ፣ አንድ በእድሜያቸው ገፋ ያሉ አዛውንት ጋር ደረሱ።

አዛውንቱ ነጭ–አምላኩ ነበሩና " ነጩ ዶክተር ካላከመኝ" ብለው ድርቅ አሉ። እንግዲህ ወጣቱ ነጭ ፕሮፌሰር አስራትን ፣ በትምህርት ደረጃ ፣ በስራ ልምድ ፣ በግል ተሰጥኦ ይወዳደራል ተብሎ አይታሰብም ። ከእርሳቸው ሰፊ ልምድ፣ ስር ሆኖ ሊማር በፈቃደኝነት የመጣ ነው።

አዛውንቱ ግን በሀሳባቸው ፀኑ። ስለዚህ ፕሮፌሰር አሥራት መላ ዘየዱ። እርሳቸው ለነጩ ተማሪ እንደ ረዳት ሆነው አዛውንቱን ሊመረምሩ ( ትህትና የአዋቂዎች ንብረት ናት)

በዚህ መሰረት ነጩ ተማሪ የፕሮፌሰር አሥራትን መመሪያ እየተከተለ አዛውንቱን መረመረ። በሽታቸውም ታወቀ። ፕሮፌሰር አሥራት የፈውስ መድሃኒቱን ማዘዣው ላይ ፅፈው ለነጩ ተማሪ አስረከቡ። ተማሪው ደግሞ ለአዛውንቱ። አዛውንቱ ፣ መልአክ የመሰለ ነጭ ሰው ስላከማቸው በጣም እየተደሰቱ፣ ገና መድሃኒቱን ሳይወስዱ የመሻል ስሜት እየተሰማቸው ፣ ሆስፒታሉን ለቀው ወጡ።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፣ ፕሮፌሰር አሥራት ያንን አዛውንት ከመንገድ ያገኟቸዋል። የተለመደ ጥያቄያቸውንም ይሰነዝራሉ ፦ " እንዴት ኖት አሁን? ጨርሶ ተሻሎት?"

አዛውንቱ ሲመልሱ ፦ "አሁን ፍፁም ጤነኛ ነኝ። ጭራሽ አሞኝ አያውቅም። ያ የተባረከ ፈረንጅ በሙሉ ነው የፈወሰኝ"

ፕሮፌሰር አሥራት በአዛውንቱ የጤንነት ሁኔታ ተደስተው፣ አሁን እውነቱን ብነግራቸው ችግር የለውም ብለው አሰቡና፦

"ይኸውሎት አባቴ፣ ፈረንጁ የኔ ተማሪ ነበር፣ ከኔ ሊማር ነው የመጣው። ያከምዎት፣ ህመምዎን ያገኘሎት ፣ መድሐኒት ያዘዘሎት እሱ አይደለም፣ እኔ ነኝ" ቢሉ፣

አዛውንቱ መልሰው፦ "ለዚያ ነዋ ህመሙ እየደጋገመ የሚነሳብኝ!"

/HakimEthio
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ጋዜጠኛና ጸሐፊ ተውኔት ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ፍልስምና ፩ ፣ ፪ እና ፫ን ደምሮ ባወጣው መፅሐፉ ጋሽ ስብሃትን እየጠየቀው ነው።

#ቴዎድሮስ :- እንደው ጋሽ ስብሃት በስጨት ብለህ "በዚህ ዓለም ባልተፈጠርኩ" ያልክበት ጊዜ ኖሮ ያውቃል?

#ስብሃት :- የለም። በፍፁም ኖሮ አያውቅም። የመረረ ችግር ገጥሞኝም አያውቅም። እኔ ችግር የምለው በጣም ርቦህ የምትበላው ካጣህ ፣ በጣም በርዶህ የምትለብሰው ከሌለህ ነው። ይህ እኔን ገጥሞኝ አያውቅም። የገጠመኝ ከእናቴ ተለይቼ ወደ እዚህ ስመጣ ናፍቆት ነው። ምናልባት ለዓመት ያህል ማታ ማታ አለቅስ ነበር። ይህ ችግር ነው።

#ቴዎድሮስ :- ደስተኛ ነህ?

#ስብሃት :- በጣም!

#ቴዎድሮስ :- ምንድንነው ደስታ ማለት?

#ስብሃት :- እግዜር ካልበደለህ ወንድ ከሆንክ ሴት አቅፈህ ለብቻህ ስትሆን ነው - ደስታ። ከእሱ ቀጥሎ ርቦህ ስትበላ ነው - ደስታ። ከእሱ ቀጥሎ ሽንትህ ወጥሮህ ስትሸና ነው - ደስታ። ደስታ መዓት ነው መቁጠር ከፈለክ። ግን ለምን ትቆጥራለህ? ዝም ብለህ መኖር ነው።

#ቴዎድሮስ :- ችግር ወደን የማንገባበት ት/ቤታችን ነው። ለመሆኑ ባንተ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ትምህርት ሰጥቶህ ያለፈና እንደ ባለውለታዬ እቆጥረዋለሁ የምትለው የችግር ጊዜ ነበር?

#ስብሃት :- አዎን። ሕይወቴን መለወጥ ሳይሆን ቀርፆታል የምለው የችግር ጊዜ ነበር። ልጅ ሆኜ እስከ አስር ዓመቴ (ከወላጆቼ ጋር ሆኜ) ማለት ነው እስኪተርፈን የምንበላው በዓመት ሶስትና አራት ጊዜ ይሆናል። ጠገብኩ እንላለን እንጂ አንጠግብም። ይርበናል። ከዚያ በኋላ አዲስአበባ መጥቼ ርቦኝ አያውቅም። ግን የራበውን ሰው ገና ሳየው መራቡን አውቃለሁ። የሚርባቸው ደግሞ ብዙ ጊዜ የማይናገሩ ናቸው። ይታየኛል። በቃ ኪሴ ገንዘብ ይኖራል አውጥቼ እሰጠዋለሁ። እሱም ደስ ይለዋል ፤ እኔም ደስ ይለኛል። ይህን ሁሉ ለማሰብ " እንኳንም እየራበኝ አደግሁ" እላለሁ።
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ልሂድ ባልሽኝ ቁጥር
ስንቴ አንቺን ልሸኝሽ
በር ድረስ ወጣሁ
ሸኝቼሽ ስመለስ
አንቺን ነው ማገኘው
እራሴን እያጣሁ
እንዴት አትይኝም...
እንደዘበት መርሳት
ላይችል አቅፎ ሰንበር
እንዴት ሄድሽ ልበል
ትዝታሽ ጠብቆ እየከፈተልኝ በር
ግን ግን ....
የሚለኝ አይጠፍም
ስትሄድ ሸኝቷት አያዝናል እንዴ ደግሞ
መኖር ይባላል ወይ
ካቀፉት ገላ ስር ልብ ሲሸሽ ቀድሞ
አየሽ የኔን ህይወት
ከዕለት ለት እያደር
ቢጠጥርም ከአለት
ከመሄድሽ በላይ
ትዝታን መርሳት ነው
አንቺ የለሽም ማለት
አትጠራጠሪ
የሚሆነው ሁሉ
ስለሆነ አይደለም
በአንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም
የኔ ያልሆነን ነው
አግኝቼ የማጣው
ያለፍኩትን ታሪክ
ባሻገረኝ ድልድይ
ዘወር ብዬ ሳየው
በእርሱ ፍቃድ እንጂ
በምኞቴ አይደለም
ዛሬ የሚለየው
አዎን እመኛለሁ
የተመኘሁትን አንቺን አግኝቻለሁ
ያገኘሁትንም አንቺን አጥቻለሁ
ባጣሁት ነገር ላይ
ፈፅሞ አልከፋም
ለምን እከፋለሁ
እንኳን የኔ ያልኩሽ
አግኝቼ ላጣሁሽ
እኔ እንኳን እራሴ
የራሴው አይደለሁ
ያ ደግሞ ምንድን ነው
የሚሆነው ሁሉ ስለ ሆነ አይደለም
በአንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም
የኔ ያልሆነን ነው
አግኝቼ የማጣው

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

By #Abel
.............አታምነኝም...............

አታምነኝም እንጅ
አድርጌህ ነበረ የልቤ ወዳጅ
አታምነኝም አይደል
ፍቅርህ አለቅ ብሎኝ እንደሄድኩኝ ፀበል
አታምነኝም ለካ
በፍቅርህ አብጄ ብቻዬን በለቅሶ ሳሽካካ
አታምነኝም በቃ
ያን ሁሉ ሳፈቅርህ ሳለቅስ በሲቃ
አታምነኝም አየህ
ደስ ይለኝ እንደነበር እየተደበኩኝ አይን አይንህን ሳይህ
አታምንም አውቃለው
ባንተ ቤት ውሸት ነው ስልህ እወድሀለው
ያ ሁሉ አለፈ ፀበሉ ሰራና
ጠላሁህኝ ላይኔ ሳይህ እንደገና
1 አመት ስሰቃይ ዝም ብዬ እንደ ዲዳ
ጊዜ ተቀይሮ ተሳስቼ ሳይህ ሊያስመልሰኝ ዳዳ

By meswatttt


SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ሰው
( አጭር ልቦለድ)
(በእውቀቱ ስዩም)
ጢም ማቀምቀም በጀመርኩበት ዘመን በከተማችን አንድ ተአምረኛ ባህታዊ ብቅ አለ፤ 'ጥቁር ኢየሱስ ብለው ሊጠሩት የደፈሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ ፤ ባህታዊው እውር ያበራል፤ ጎባጣ ያቀናል፤ ባንድ ጊዜ የከተማው ሆስፒታሎች ሁሉ ባዶ ሆኑ፤ የሆነ ጊዜ ላይ እንዲያውም ሙት ማስነሳት ሁሉ ጀምሮ ነበር፤ የከተማችን አስተዳዳሪ ግን “ ለተነሺዎች ማቋቋሚያ የሚሆን በጀት የለንም ብሎ ከለከለው፤

ባህታዊው ባንድ ወቅት ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ወልደ ሰንበት ከተባለ የከተማው ነዋሪ ጋራ ተገናኘ፤ ወልደ ሰንበት በራዛ ዘመቻ ጊዜ ፈንጅ ብልቱን ቆርጦበታል፤ በጥሮታ ከተገለለ በሁዋላ ‘መራባት የተሳናቸው ወንዶች ማህበር’ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያገልግላል፤

ወልደሰንበት ባህታዊውን ሲያየው “ አባት ሆይ፥ አገሬን አገሬን ብየ ስዋትት ዘሬን ሳልተካ ላልፍ ነው፤ ፈውሰኝ “ ሲል እግሩ ላይ ወድቆ ተማጠነው።

ባህታዊው ወደ ሰማይ አንጋጦ ትንሽ ከጸልዩ ሲያበቃ ወልሰንበትን አስወልቆ ጉያውን ዳበስ አደረገው ፥ መቸም አታምኑኝም ፤ ግን ሀቅ ከከመመስከር አልታገድም፤ የሰውየው ጉምድ ብልት ወዲያውኑ አቆጠቆጠ። ተአምረኛውን ሰውየ ያጀቡ ወንዶች አፋቸውን በጋቢያቸውና በኮሌታቸው ጫኑ !የሴቶች እልልታማ ፤እስከመተማ ፤ ተሰማ፥

ባህታዊው ይህንን ተአምራዊ የብልት- ተከላ ፈጽሞ ትንሽ አለፍ እንዳለ ወልደ ሰንበት እያለከለከ ደረሰበትና እግሩ ስር ተደፋ፤

“ አሁን ደግሞ ምን ፈለግህ?” አለው ባህታዊ፥ በታከተ ሰው ድምጽ ፥
ወልዴ እንዲህ ሲል መለሰ፥

“አባት ሆይ ! በነካ እጅህ ትንሽ ተለቅ ልታረግልኝ ትችላለህ?”

SHARE🌼

=ኪ==ነ==ቃ==ል=

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ማህሌተ ገንቦ

(በውቀቱ ስዩም)

ባጭር ቀረን ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን

ቺርስ!!

ፊታችንን ዐይተው -እንደተቸገርነ- ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው-ቆመው ላልጠበቁ

ቺርስ!!!

ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ😉

ቺርስ!!!!

ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን-ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ-
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን

ቺርስ!!!!!

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ሙላ ነስሩዲን ሊሞት ተቃርቧል።

"ልጄ ..."አሉት። አጠገቡ የተቀመጡት የንሰሃ አባቱ እጁን እያሻሹ "እንግዲህ ወደ እውነቱ ቦታ መሄድህም አይደለ...በል አሁን ሰይጣንን ረግመህ፣ አውግዘህ ከጌታህ ጋር ትገናኛለህ። አዎ እርገመው ሰይጣንን፤ ምን ያህል እንደምትንቀውና እንደምትፀየፈው ይወቅ ይሄ ከይሲ..."

ሙላ ዝም!

"እርገመው አልኩህ እኮ" አሉ የንሰሃ አባቱ... አሁንም ጭጭ!!
"ሰይጣንን ትፈራዋለህ እንዴ ይሄ ከይሲ-እርገመው!!"
ተቆጡ የንሰሃ አባቱ...
"አዬ አባቴ...እኔ በበኩሌ" አለ ሙላ ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ፣ "መግብያዬ የት እንደሆነ ሳላውቅ ማንንም
ማስቀየም አልፈልግም።"

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ህፃን ልጅ አለችው። 'ሚጣ' እያለ ነው የሚጠራት። እናቷ ጥላት ሂዳ ብቻውን ነው የሚያሳድጋት። ሸክም እንደሆነችበት ያስባል፤ በዚህ የተነሳ ይነጫነጭባታል። ከሰው ላለመቀራረቡ እሷን ይኮንናል፤ እሷ ባትኖር ጊዜ ይኖረኝ ነበር ብሎ ያስባል። 'ከጓደኞቼ አራቀችኝ' ይላል።

ሚጣ ግን አባቷን ትወዳለች። ለምን እንደሚናደድባት ባይገባትም በዚያች ትንሽ አቅሟ ልታስደስተው ትጥራለች።

አንድ ቀን ብር ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ወጥቶ ሲመለስ ከቦታው ያጣዋል።
"ሚጣ፣ ሚጣ" ብሎ በጩኸት ጠራት።
"አቤት አባዬ" አለችው። በፍርሃት ውስጥ ሁና።
"ብር አንስተሻል?"
"አዎ አባዬ"

ጆሮዋን ለቁንጥጫ ያዘ። በዚህ መሃል፦
"አባዬ አባዬ ለአንተ ብዬ እኮ ነው" አለች።
"እንዴት" አላት።
"ለአዲስ ዓመት ስጦታ ልሰጥህ ብዬ"

አባዬ ለቀቃት። እሷም ሄደች።

በሳምንቱ ዓዲስ ዓመት ደረሰ። ሚጣም ለ'አባዬ'ዋ ስጦታ አሽጋ ሰጠችው። በፈገግታ ስጦታውን ተቀበላት። ከተቀበለ በኋላም ከፈተ። ውስጡ ባዶ ነበር። የጠበቀው ባለመሆኑ...ተበሳጨ።

"አንቺ! ምን ዓይነት ልጅ ነሽ? ባዶ በስጦታ መሸጊያ አሽገሽ ተሰጭኛለሽ? ምን የሚሉት ጨዋታ ነው?" ብሎ በጩኸት ተንጣጣባት።

ሚጣም ድመት እንዳየ አይጥ እየፈራች..

"አባዬ ባዶ እኮ አይደለም።" አለችው። የሰማውን ማመን እየከበደው
"ጭራሽ ዐይን የለህም ነው?"
"በሳጥኑ ወስጥ ብዙ መሳሞች አሉ፤ ከጠዋት ጀምሬ አንተን የምሰመውን ያክል እየሳምኩት ነበር። እንዳይወጣ ነው ያሸገኩት። ስለምወደህ እኮ ነው። "

ሰውዬው በግልፍተኝነቱ አፈረ።

ይኸ በሆኘ በወር ሚጣ በአደጋ ህይወቷ አለፈ። አባቷም ሀዘኑ ከበደው። የሰጠችውን የስጦታ ሳጥን ከተራሱ አስቀምጦ ሁሌም ይስመዋል..

ሚጣ ሳያውቅ ያመለጠችው በረከቱ ነበረች...ሚጣ ከሰው ያላገኘውን ፍቅር ያለበሰችው ሸማው ነበረች። ከእጁ ካመለጠች በኋላ፤ ከረፈደ በኋላ ነበር ይኸ የገባው። እሷ የብቸኝነቱ ማስታገሻ እንደነበረች ከረፈደ ነበር የተገለጠለት...

እንዳንዶቻችን እንዲህ ነን እስክናጣው ድረስ ምን እንዳለን መረዳት ይከብደናል....እስኪረፍድ እንጠብቃለን...
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"እወድሃለሁ እኮ!"
"የጠየቀሽ የለም"
"ግን እንደማታገባኝ እኔም አንተም እናውቃለን።"
"የጠየቀሽ የለም!"
"ልጅነታችን ገና አለቀቀንም ነበር። ቤተሰብ መመስረት እንደማንችል..."
"በፈጠረሽ አምላክ ተይኝ ኤደን!!! እኔ ማብራሪያ ጠይቄሻለሁ? 'ምክኒያትሽን የማወቅ ፍላጎት አለኝ' ብያለሁ?"
"እሽ እኔስ እንዴት ብዬ ልተኛ? ራሴን በምን ላፅናና?"

(ገርሞት እጁን በአፉ እየጫነ..)
"ምን አ'ርግ ነው የምትይኝ አሁን እሽ?"

"ይቅርታ ብጠይቅህ ትቀበለኛለህ?"
"ሲጀመር ይቅርታ የሚያስጠይቅ ጥፋት አላጠፋሽም'ኮ!"
"በናትህ ተው.."
"የምሬን ነው። ከኔ የተሻለ ወንድ አገኘሽ። ጥለሽኝ ሔድሽ። ይሔ ደሞ በጣም ጤናማ ነገር ነው። መብራት ሲመጣለት ሻማውን 'እፍፍ' ብሎ የማያጠፋ አለ? የለም። እንደዛ ተመልከችው ይሔንንም። እርግጥ ነው አምፖል ውስጥ የሻማን ያህል ሮማንስ ላይኖር ይችላል። ግን ከሻማው ሰላሳ እጥፍ ብርሀን ለቤትሽ ይዞልሽ ይመጣል። ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰንሽው እኔን ከጠየቅሽኝ።"

"የምትወደውን ሰው አሳዝነህ መኖር አይቻልማ ስዩሜ። እኔ አቃተኝ!"

"ማን የሚያሳዝን ነገር ሁሉ ልክ ነው እንዳለሽ አላውቅም። የሆነን ሰው እንዲያዝን ስላደረግሽው በድለሽዋል ወይም ስህተት ሰርተሻል ማለት አይደለም። ይሔ ሕይወት ነው። ይሔ ጥሎ ማለፍ ነው። ራስሽን መምረጥሽ ልክ ነበረ። Move on በቃ!"

"እሽ በናትህ...እንደው በናትህ...አንድ ነገር ብቻ ልለምንህ"
"ምን?"
"በጥፊ ምታኝ"
"አብደሽ ልታሳብጅኝ ነው እንዴ የተነሳሽው?! ጭራሽ ነፍሰ ጡር ሴት ላይ እጄን ላንሳ?"
"እሺ ሰድበኸኝ እንኳን ሒድ!"

"ከአሁን ቡኃላ አንቺ ጋ ጠብም ሰላምም አልፈልግም። ዛሬም ባልሽ ማነው አለቃዬ ብቀር ያኮረፍኩ ይመስለዋል ብዬ ስለሰጋሁ ነው'ጂ ላንቺ ልደት ግድ ሰጥቶኝ አይደለም እዚህ ድረስ የመጣሁት።"

(ጥሏት ሊሔድ ሲል እጁን ይዛ እያስቀረችው...)
"ሲጀመር ለምን የዛን ቀን 'እህቴ ናት' ብለህ አስተዋወቅከን ቆይ?"

"ኦኬ! ጭራሽ ልትወቅሽኝም ያምርሻል? ኧረ ውቀሽኝ። እንደፈለግሽ እንዳውም።"

"የምሬን ነው። ለምንድን ነው እንደዛ ታፍርብኝ የነበረው? እኔ አደንዛዥ እፅ ነኝ እንዴ ቅያስ ውስጥ ስንገባ ብቻ እየጠበቅክ የምትስመኝ? መልስልኝ እስኪ? እውነት በጓዳ ያፈፈቀርከኝን ያህል በአደባባይ ልታፈቅረኝ ሞክረሀል?"

"ያምሻል እንዴ? አብሮ አደጎች እኮ ነን። ለሰው ካሳወቅን ሁሉንም ነገር ጨራርሰን ነው መሆን የነበረበት። ሲቀጥል እኔ ለሱ ነው'ጂ 'እህቴ ናት' ያልኩት ወዳንቺ ዙሬ 'እህቴ ነሽ' አላልኩሽም። ለዛም ነው መቼም እሱን የማልቀዬመው። ለዛም ነው ዛሬም ድረስ አብሬው የምሰራው።"

"እንዲህ እያልክ ራስህን አታስደስት! የዋሸኸው ገና እንዳዬኝ እንደወደደኝ ስለገባህ ነው። 'ፍቅረኛዬ ናት' ብለህ ልታስቀይመው ስላልፈለግክ ነው 'እህቴ ናት' ያልከው። አሽቃባጭ እና ቦቅቧቃ መሆንህን እመን መጀመሪያ!!"

(ባልዬው ተጠግቷቸው እየቆመ..)
"እንግዶቻችሁን ትታችሁ የሞቀ ወሬ ይዛችኋላ እናንተ! ቆይ ስለምን እያወራችሁ ነው?"

(ኤደን ፈጠን እያለች)
"ኧረ ዝምብለን ነው። ስለመፀሀፍ ቅዱስ እያወራን ነበር።"

"አይይይ ድካሙ ነው የሚተርፍሽ! ብዬው ብዬው ያልሰማኝን!!"
"ሰሚ ልብ ካለ ለምህረት አይረፍድም ብዬ ነበር እኔማ..!"
"እውነት ነው እሱስ! ለመሆኑ በየትኛው ወንጌል ላይ ነው እንዲህ ልባችሁ እስኪጠፋ የምትሟገቱት?"
(ስዩም ሀሳብ ውሰጥ እንደገባ) "የሆነ ያለፈ ታሪክ ላይ ነው!" (እግሩን ስትረግጠው ነቃ እያለ...) "ማለቴ የሀዲስ ኪዳን ታሪክ አይደለም። ዘመነ ፍዳ ላይ የተፈጠረ ነው።"
"የትኛው ታሪክ?"
"እእእእ.." (አገጩን ይዞ ፂሙን ሲያሻሽ ከቆዬ ቡኃላ የሆነ ነገር እንደመጣለት ሰው አይኖቹን እያፈጠጠ...) "ይገርምሀል...ይገርምሀል...አንድ ባዬሁት ቁጥር የሚያስገርመኝ ታሪክ ነበረ። ድንገት እሱን አንስተን ሳናስበው ቀውጢ ሙግት ውስጥ ገባን።"
"እኮ የትኛውን ታሪክ?"
"እንትን...አብርሀም ስደት ሂዶ የገጠመውን ታውቀዋለሀ?"
"እኔ እንጃ...?"
"ንጉሱን ፈርቶ ሚስቱ ሳራን 'እህቴ ናት' ብሎ ያስተዋወቀበትን እንኳን?..."

"ኦኬ! ኦኬ! እሱንማ በደንብ አውቀዋለሁ! ፈርኦኑ ሳራን ሊያገባት ሲል እግዚያብሔር ቁጣና መዓት ያወርድበታል...ከዛ ፈርኦኑ አብርሀም እንደዋሸው ሲያውቅ አስጠርቶ 'ውሰድልኝ ሚስትህን!' ብሎ ይቆጣዋል ምናምን ምናምን..ኣ?"

"አዎዎዎዎዎ! እና እሱ ታሪክ ላይ ጥፋተኛው ማነው ትላለህ? አብርሀም? ሳራ? ወይስ ንጉሱ?"

(ኤደን ጣልቃ እየገባች)
"እንዴ ምን ጥርጥር አለው አብርሀም ነዋ! አይደል የኔ ቆንጆ?"
"ሳራስ ንጉሱ ሲወስዳት ፀጥ ብላ መውሰዷ አልገረመህም? እግዜር እስኪናገርላት መጠበቋ ልክ ነው ትላለህ? እውነተኛ ፍቅር እንደዛ ነው?"

"ሃሃሃሃ ጋይስ! Look! ሁለታችሁም እዚህ ጋ መረዳት ያለባችሁ አንድ ቁምነገር ያለ ይመስለኛል።"
(ሁለቱም አንድ ላይ)
"ምን?"
"በወቅቱ ሁለቱም ምንም አማራጭ የሌላቸው ችጋራም እና ረሀብተኞች ነበሩ።"
(ስዩም እና ኤደን ተያይተው በሀፍረት ስሜት አንገታቸውን ደፉ።)
"ምንም አድርገው...ምንም ብለው ንጉሱን ማስቀዬም አይፈልጉም። ከዛ ቡኃላ የተፈጠረው ነገር ሁሉ የተፈጠረው ከዚህ ጋ በተያያዘ ምክኒያት ነው። በኔ በኩል ለመኖር ጉጉት ማሳያተቸውን እንደ ጥፋት አላይባቸውም።"
(ሁለቱም በተዳከመ ድምፅ አንድ ላይ..)
"ልክ ነህ!"

(አቀርቅረው ሀሳብ ውስጥ እንደመግባት ሲሉ ጩኸቱ አስደነገጣቸው። ቀጥ ብለው አዩት። በመስታውቱ በኩል ኳስ የሚጫወቱ ህፃናትን አይቶ ነው የጮኸው። ልጆቹን ሊያገላግል ወደ ውጭ ሲወጣ በቆሙበት ሁነው በድጋሜ ቁዘማ ውስጥ ገቡ። ዝም ተባብለው ቆዩ። ማውራት የጀመረው ስዩም ነው።)

"እኔ እና አንቺ ግን ለምን ይመስልሻል እንደ ልጅ ውጭ ላይ ኳስ ምናምን ተጫውተን ያላደግነው?"
"እ?"
"ለምን ይመስልሻል ሁል ጊዜ የቤት ውስጥ ጨዋታዎችን ብቻ ስንጫወት የነበረው?"
"እኔ'ጃ! ክረምት ላይ ስለተዋወቅን መሰለኝ..?"
"እና ዝናቡ አያባራም ነበር ነው?"
"ማባራትማ ያባራል። ግን ብዙ ጊዜ ዝናቡ እስኪያባራ ስንጠብቅ ይመሽብንና ሳንጫወት እንለያያለን።"

(በጨረፍታ አንዴ እሷን አንዴ ባለቤቷን እያዬ)
"ዛ..ዛሬ...ዛሬም ያው ነው መሰለኝ ኤዱ!..ዝናቡ እኮ መጣል አቁሟል...ጀንበር ግን ጠልቃብናለች....ያ..ያው.."
(ድምፁን ሳግ ሲያንቀው ዝም አለ። በቀስታ ከተጠጋችው ቡኃላ "ገብቶኛል" በሚል አስተያዬት እያዬችው እጆቹን ጨበጠቻቸው። ተቃቀፉ...የስንብት። ተላቀቁ...የእውነት።)

Mickel Azmeraw

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ጋሽ ስብሃት አንዴ የሆነ ሞል ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ለሽያጭ ተሰቅሎ ያያሉ። ወደ ሻጩ ጠጋ ብለው

"ስንት ነው?" ብለው ጠየቁ።
ሻጭ "3 ሺህ ብር"
ፈገግ አሉ ጋሽ ስብሃት።
ሻጭ የተወደደባቸው ስለመሰለው ጋሼ ለእርሶ አስተያየት ይደረጋል። በስንት ይወስዳሉ?
ጋሽ ስብሃት "ይሁዳ ከነ ነፍሱ 30 ብር አይደል እንዴ የሸጠው? እንዴት ለስዕል 3 ሺህ?"😄
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
#ምን_ነበር?


የፍቅራችን እሣት ነዶ ግሞ ንሮ በቅቶት ሲበርድ፤
አስመስሎን እንዳረፈ አንቺን ከሰል እኔን አመድ፤
አንቺ ዳግም ስትነድጂ ፍም ስትሆኚ ገጥመሽ ከሰው፤
እኔ ስዛቅ በመጫሪያ እንደትቢያ ስታፈሰው፤
ልረሳሽ ቃል ገብቼ ተግብሬአለሁ አንድ ነገር፤
ያደረኩት ግን ምን ነበር?


አንቺን ማጣት፤
አንድ ግዜ የእግር እሣት፤
አንድ ግዜ የቋንጃ እከክ፤
እየሆነኝ ስብረከረክ፤
እኔው ለኔው ቃል ገብቼ፤
ካልረሳዋት ወንድ አይደለው ይቺን አባይ ብዬ ዝቼ፤
የተጫነኝ ዝግባ ቀንበር፤
ከልቤ ላይ እንዲሰበር፤
ትዝ ይለኛል ተግብሬአለሁ ምስ የሚሆን አንድ ነገር፤
ያደረኩት ግን ምን ነበር?


እንዳይከፋሽ እንድትስቂ፤
አንዴ ህፃን አንዴ አዋቂ፤
መሆኔን ቢያይ ውስጥሽ ውስጤን አበክሮ ስላወቀው፤
አሳቻ ሰዓት ደባ ፈትለሽ ቀበቶዬን ሳላጠብቀው፤
መልህቁን የመርከቡን ሰውረሽው ድብቅ ቦታ፤
ማበል ወጀብ እየናጠኝ እያየሺኝ ስንገላታ፤
ብቅ ጥልቅ እያስባለኝ ከወደቡ እልፍ ርቄ፤
ለብቻዬ ተጠብቤ ለብቻዬ ተጨንቄ፤
መውጫ ባጣ ማርያም መንገድ፤
ቃል ገብቼ የዛን ግዜ ፍፁም አንቺን ላለመውደድ፤
ተግብሬአለው አንድ ነገር አንቺን ከቶ እንዲያስረሳኝ፤
ምን ነበር ግን ያደረኩት? አለኝ ዛሬ አልወሳኝ።


አሁን ሳስብ በትውስታ፤
የሆነ ግዜ የሆነ ቦታ፤
ከልቤ ላይ እንዲነቅለው ያንቺን ሰንኮፍ የተጣባኝ፤
አንድ ነገር አድርጌአለሁ ግን ምን ነበር ግራ ገባኝ?


ትዝ የሚለኝ ብቻ ዛሬ፤
ያንን ነገር መተግበሬ፤
አንቺን ማጣት አንቺን መርሳት፤
ግዙፍ ቋጦኝ ዳገት መግፋት፤
እንዳልሆነ ሰብቆልኛል ይባስ እንደው በተቃርኖ፤
አንቺን መርሳት ፊቴ ቆሟል ደቂቅ ገቢር ኢምንት ሆኖ።


አይረሳኝም ስትዪ ሰማው ...
እንኳን ያንቺን ፍቅር ቀርቶ ለኩነኔ ላሳር ሰቶኝ እኔን ያኔ ያሳነሰኝ፤
የዛን ግዜ የፈፀምኩት እንድረሳሽ ያደረገኝ ፅድቁም ተግባር መች ታወሰኝ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ <<ተመስገን>> በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!

ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር
(ጋሽ ስብሀት)

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
#እንዲ_ነው_ሚከፈል



ትላንትና ሌሊት ናፍቆትሽ ቀስቅሶኝ አስሬ ስነሳ፣
እንደው የኔ ፍቅር ያየሁት አበሳ፣
አሰኝቶኝ ነበር በካልቾ በጥፊ በመታውሽ ብዬ፣
ዳሩ ምን ያደርጋል ዛሬም አብሬሽ ነኝ መከፋቴን ጥዬ።


እናም...
ቀን ቀንን ሲተካ ሲገባኝ ምስጢሩ እያደር ስረዳው፣
እንዲ ነው ሚከፈል ሰው የማፍቀር እዳው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"ቀልዴን አይደለም የምለው አዲስ ነገር የለኝም ሌሎች ያልዳሰሱት ምን አዲስ ነገር ልፈጥር እችላለሁ? በፃፍክና ባነበብክ ቁጥር ብልህ ከሆንክ የምትገነዘበዉ ነገር ቢኖር ዝም ማለት የሚመረጥ መሆኑን ነዉ። እዉነቴን ነዉ። የገደል ማሚቱ ከመሆን ዝምታ ይመረጣል።በራስህ የዝምታ ጥልቀት ዉስጥ መስመጥ እራሱ ዉበት ነዉ።"

"ኦሮማይ"
በዓሉ ግርማ

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ሰሞኑን ለምርመራ ወደ አንድ የግል ክሊኒክ ሄድኩኝ። ዶክተሩን ሳየው ድሮ አብረን የተማርነው ዮሐንስን መሰለኝ። "ዮሐንስ ደግሞ እንዲህ ሊያረጅ አይችልም" ብዬ እያሰብኩ ተራዬ ደረሰና ገባሁ።

እንደገባሁ ጠየቅሁት፣

"አንተ ዮሐንስ ነህ እንዴ?"

"አዎ ነኝ" ሲለኝ በጣም በማርጀቱ ደነገጥኩና

"ዩኒቨርስቲ አውቅሃለሁ"

"ዋው! የምን አስተማሪያችን ነበርክ?"

ባሻዬ! ጠላትህ ይደንግጥ። እኔ ከሱ በላይ አርጅቻለሁ ማለት ነው? ሰው እኮ እንደ ዝንጀሮ ነው። የራሱ ቂጥ አይታየውም።

ⓒተስፋዬ ሃ/ማርያም
ከማዕደ ጥበብ ገፅ

SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
የዘመናችን የብሔረሰብ አለቆች በተወለዱበት ከተማ ውስጥ ሆስፒታል ለመስራት አምስት ሳንቲም አያወጡም ።ይሁን እንጂ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ሆስፒታል ቢያቆም በየትኛው ቋንቋ የተፃፈው ስሙ ይቅደም የትኛው ይከተል በሚለው ዙርያ ዱላ ቀረሽ ክርክር ሊያደርጉ ይችላሉ።
ምንጭ -ከአሜን ባሻገር መፅሐፍ
ደራሲ -በዕውቀቱ ሥዩም
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
Book for ALL |

የትንሽ ነገር ... ከሲኣት ትንሿ እህቴ ከሩቅ እየተጣራች መጣች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ”

እናታችን ለጨረሩ መከላከያ መዳፏን ግንባሯ ላይ አጋድማ “ምነው? ምን ሆንሽ?” አለች “ዱላ ስጪኝ ዱላ ስጪኝ” “ምነው? ለምንሽ?” “አለቃ ተመረጥኩ” ዱላ አሳጥራ ሰጠቻት። . . . አመሻሽ ትንሿ እህቴ እያለቀሰች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ” እናታችን “ምነው? ምን ሆንሽ?” “ከአለቃነት ተሻርኩ”
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ርዕስ፡ውልብታ"
ደራሲ፡አለማየሁ ገላጋይ ገጽ፡፶
---------------------------
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
---------ላንመለስ
እንሂድ ብላኝ ተከትያት ፣
ቃል ስትሰጠኝ ቃል አምኛት ፣
ስትጎትተኝ ስጎተታት ፣
ስመናተል ሳባብላት ።

ኼዴን ኼዴን ኼዴን...
ላንመለስ መንገድ ጠፋን ።
---------------------------
"አሁንም አይደል ወደ ማታ.."
ገፅ - 100
ደራሲ - ሔኖክ ደመቀ
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM