ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ስለራሳቸው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የሚሆኑት ባለባቸው ድንቁርና ነው!
-- Franz Kafka --

============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
አስተሳስብህን ተመልከት፤ ቃላት ይሆናሉ፣ ቃላትህን ተመልከት፤ ድርጊት ይሆናሉ፣ ድርጊትህን ተመልከት፤ ልማድ ይሆናሉ፣ ልማድህን ተመልከት፤ ባህሪህ ይሆናል፣ ባህሪህን ተመልከት፤ መዳረሻህ ይሆናል !
--Lao Tez--
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
የትኛውም ሀይማኖት በሌላ ሀዘን መሳቅን አልመከረንም:: ማስትዋል የብርሀን ሁሉ ብርሀን ነው:: ከተማረ ብልጥ: ያስተዋለ መሀይም ንፁህ እውነት አለው : ምክሩም መድሀኒት የሆነ:: እንደኖርነው የሺህ ዘመናት ርቀት ከሆነ ይህ ባልተነገረን ነበር:: ነገር ግን ልብ ሲጠም ከዘመን ይርቃልና ቃሉን ከልባችን አጣነው:: ልብ እንበል:: ለራሱ ከሚያለቅስ ይልቅ ለሌላ የሚያዝን ለአምላኩ ቅርብ ነው:: ባለሀገርነትም ሩቅ ላልነው የሀገርሠው መኖር ማሰብ: ከራስ እልህ የሌላን ሠው ሀዘን ማስቀደም ነው:: የጎረቤት አባት ሚፈራበት ሚከበርበት ሰፈር ልጅ ሁሉ ጨዋ ነው:: አንዱ የሌላውን እንደራስ ስለሚያይ ስለሚጠብቅ:: የእናቶች እንባ ሚቆመው ሳይረፍድብን ያዘነ እኩያችንን ብንችል በፍቅር ባንችል ክፉ ባለመናገር ስናፅናና: ሀዘኑ እንዲሰማን ስንፈቅድ: ከአፍ በፊት ልብን ስንከፍት ብቻ ነው:: ያዘነ ልብ ለአምላክ ቅርብ ነው:: የእናት እንባ አይብዛብን ግድየለም:: ዛፍ በመሬት ምህረት እንደቆመ እኛም በፈጠረን ላይ ነን:: በምህረቱ ቆምን ብለን መልሰን ፈራጅ መሆን ለነገ ያጨልማል:: እናስተውል:: ለፍቅር ቦታ ከሌለን ከበር............::
.
.
.
#Rophnan
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"ጧፍም በጧፍ ይበራል
ሰውም ሰው አይቶ ይፀናል
የአንድ አማኝ ፀሎት ሀገር ያክማል!"

#ሮፍናን ============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
👍1
ስትቀርቢኚ ጋኔሌ ይነሳል
_-

ደግ አረግሽ ደግ አረኩ
ስቴጂ ከአይኔ፣
ከማልቀስ በፊት
ጥርሴ አልታየም እጂ
ስቄለው እኔ፣

እውነቱን ልንገርሽ ለሳቄ ምሳሌ፣
    ትቶኛል ለቆኛል...
አንቺ ከሄድሽ በኋላ የሚያስጮህ ጋኔሌ፣
     ለካ
መቅረብሽ ነበር የጋኔል አለሌ፣
መራቅሽ ግን
ሆኖ ተገኜ የመዳን ፀበሌ ፣

ሸሸሺኚ
ሸሸውሽ፣
ሸኜሺኚ
ሸኜውሽ፣

ግና
እዚህ ላይ ደግ አረኩ፣
ያላረግሺው እኔ ብቻ አረኩ፥
እኔ አንቺን አይደለው
ስትክጂኚ ግን ታመንኩ፣
__


ግዕዝ ሙላት
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
(ከወደቀ ወዲያ... )
=============+

ፍቅር የህጻን ገላ
ጠዋት አቁስለውት ቀትር ይፈ'ወሳል...
ፍቅር የህጻን አንጀት
ቀትር በድለውት ማታውን ይረሳል...
እምነት ግን አዋቂ
ትልቅ ሰው ነው መሰል
ወድቆ መች ይነሳል ??

#kiyorna


============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ጦቢያው ለይቅርታ ቅደም
ቀድመህ እንዳትተው ድገም
ደግሞ ቢያስቀይምህ ሰልስ
ያአባትህን አደራ መልስ
ያኔ በላይ ይዘልቃል
ያንጊዜም ቴዎድሮስ ይነግሳል
ያንጊዜም አሉላ ራስ ነው
ሚኒሊክ _ዛሬም_ንጉስ_ነው!!
#Rophnan
🥰💚💛❤️
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ኢጆሌ ቢያኮ ጀጀባዳ መሌ
ጀዴቶ ከኤ ያገሬ ኮበሌ
ዱበት ኢንዴምኑ አልከን ተኤ ጉያ
ዲናፍ ኢላኑ ኢትዮጵያ
ጀዴ አጆሌ ቢያኮ
ሆሆ ሆሆ ሆሆ

#Teddy afro
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ዘነበ እና ጋሼ ማስታወሻ ላይ ሲጨዋወቱ!

#ዘነበ_ወላ :-ጋሽ ስብሐት ሥለ ንጉስ ምኒልክ ምን ትላለህ?
.
#ጋሽ_ስብሀት:- ኧረ ..ስማኝ...እምዬ ሚኒሊክእኔን ከትግሬ አምጥቶ አንተን ከአርባምንጭ ጎትቶ አንድ የሚያደርገንን አማርኛ አስተምሮ ተግባብተን ባንድነት ምርጥ ጓደኛሞች እንድንሆን አደረገን፡፡
አየህ ሚኒሊክ የኔንም ትግሬነት ያንተንም ጋሞነት አላጠፋብንም አንድ የምንሆንበትን የፍቅር ገመድ አስታጠቀን እንጂ......"

============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ስልኩን ጥሎ ወደ ውጪ እንደወጣ ይጠራ ጀመር። የደዋዩዋ ስም ደግሞ "እህተ-ማርያም" ይላል።

ሲመለስ "እህተ-ማርያም ደውላ ነበር!" አልኩት።

"ሴት አይደለችም። ዘሪሁን እኮ ነው?!"

"ዘሪሁን ጓደኛችን?!"

"አዎን!"

"ለምንድነው እህተ-ማርያም ብለህ ስልኩን Save ያደረግከው?!" - ጥያቄዬን ወረወርኩ።

"ትላንት የፍስክ ሲበላ እጅ ከፍንጅ ይዤው ነው!"
*
የገባንበትን ሀገራዊ ድባቴ በፈገግታ እንለፈው በሚል የተለጠፈ።
#tilahun girma
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ይድረስ ላገሬ ሰው

በሆነ ባልሆነው
በጩኽት በሆታ ሲበዛ መፈክር
ባላየህው ዶሴ ባላወከዉ ነገር
መሃላቸዉ ገብተህ አብረህ አትጨፍር
ያገሬ ሰው ጠርጥር...
ጥልቅ ጉድጓድ ምሰው
ልክ እንደ መቃብር
ይደፉህ ይሆናል ከመፈክሩ ስር!!!

(ሰለሞን ሳህለ
የልብ ማኅተም
2010 ዓም)


============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
(በረከት በላይነህ)

....
አብዬ ያልታደለ
'መልካም አስብ' ሲባል 'አንባቢ ነኝ' አለ
እምዬ ቀለለች
'የዉበቴ ምስጢር ቀለም ነዉ' ትላለች
:
የሃሳብህን ስብራት
በዉሸት ለማሸት
ስታወራ ዉለህ ስትቀባጥር ማምሸት
የመልክሽን ህመም
በቀለም ለማከም
መዳፍሽ እስኪዝል መስታወት ፊት መድከም
:
:
ምን ልልሽ መሰለሽ
'መልክ ስጠኝ እንጂ...' ብለሽ አተርቺ
በቀለም ይመጣል - በመቀባት በርቺ
:
ምን ልልህ መሰለህ
ተርት ተተርተረዉ - ማንንም አትፍራ
'ሙሉ ሰዉ' ዝም ይላል - አንተ ስታወራ. . . . .
:
:
ባንተና በሷ ንግስ - አማካሪ አያሻ
የእዉት ጅማሬ ነዉ - የዉሸት መጨረሻ፡፡
:
ሊመክርህ ያለዉን - ያኔ ታገኛለህ
ወይ እዉነት ጋር ስትደርስ - ወይ ሲዋሽ ታያለህ፡፡

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"ይድረስ ለዚያ ሰው ወራሪውን ለመለሰው
የነፃነት ተምሳሌት አርጎ ስሜን ክብር ላለበሰው
ያረክልኝ ብዙ ነው ከፍዬም የማልጨርሰው
ያረክልኝ ሁሌ አዲስ በሄድኩበት የምለብሰው"

ካራማራ💚💛
የካቲት 26 - 1970 ዓ.ም
መንጌ💪💪💪

ኢትዮጵያ ትቅደም 💚💛
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
‘Don't gain the world and lose your soul, wisdom is better than silver or gold’ - Bob Marley. =ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ምናልባት ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት እንደማያስፈልገው የሚታሰበው ብቸኛው የሙያ ዘርፍ ፓለቲካ ይመስለኛል!
    -- Robert Louis Stevenson --

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
⁰◊
የወደድኩሽ ይመስለኛል..፤

ቁጥር በሌላቸው ቅርጾች..
ጥንፍ አልባ ጊዜያቶች...

ከህይወት በኋላ ፣ በህይወት ክስተትም
ከዕድሜ በኋላ ፣ እስከ ዘላለም።

ንሸጣ
Rabindranath Tagore

#አዮነት ( ቃልኪዳን)
@kaliye06

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
አደን ከመሄዱ በፊት ቃለ መጠይቅ እየተደረገለት ነው

"በጣም ፈጣን የሆነውን ነብር ነው የምታድነው እና ስትተኩስበት ብትስተውስ?"

"መሳት እንኳን አልስተውም ግን ከሳትኩት ፍጥነቱን ተጠቅሞ ወደኔ ሳይመጣ ቶሎ አቀባብልና ተኩሼ እጥለዋለሁ"

"አሁንም ብትስተውስ?"

"ለሁለተኛ ጊዜ?"

"አዎ"

"ለሁለተኛ ጊዜ እንኳን አልስተውም ግን አይበለውና ከሳትኩት ወደኔ ከመጠጋቱ በፊት በፍጥነት አቀባብልና ተኩሼ እጥለዋለሁ"

"አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ብትስተውስ"

ይሄኔ አዳኙ በስጨት ይልና

"አንተ ሰውዬ ከኔ ጋር ጠብ አለህ እንዴ"

ከሰሎሞን ሳ..

፦አስተማሪ ነው ብላችሁ ያሰባችሁት ታርክ ለጓደኞቻችሁ Share በማድረግ አስተምሩ እኛም ይበልጥ እንተጋለን።


=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ጥቂት ግንዛቤ ...

ትልቅ የንግድ መርከብ ተበላሽቶ ቆሞ ብዙ መካኒኮች ቢሞክሩትም መጠገን አቃታቸው ፣ በኋላም አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ ኢንጅነር አግኝተው እንዲሰራው ቀጠሩት።

ኢንጅነሩም ሞተሩን ከታች እስከላይ ከገመገመ በኋላ አነስ ያለች የእቃ ቦርሳውን ከፍቶ ትንሽዬ መዶሻ አወጣ፣ ከዛም በጥንቃቄ በመዶሻው አንዷን ስፍራ መታ መታ አረገና ሞተሩ መስራት ጀመረ።

ከሳምንት በኋላ የሰራበትን ዋጋ አንድ ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ ሪሲቱን ሰጠው።

"ምን" አለ ባለቤቱ ጭንቅላቱን ይዞ ምን ሰርተህ ነው ይሄን ያህል ብር የምትጠይቀኝ በል ምን እንደሰራህ ዝርዝሩን ጽፈህ ስጠኝ አለው ተናዶ።

በቀላሉ እንዲህ ጽፎ ሰጠው
በመዶሻ የመታሁበት 200 ብር
የተበላሸበትን ቦታ ላወኩበት ደግሞ 999800 አለው።

ይሄን ስራ በ30 ደቂቃ ውስጥ ነው የሰራውት ላለፉት 20 አመታት እንዴት በ30 ደቂቃ መስራት እንዳለብኝ ተምሬ ነው፣ የማስከፍልህ ለተማርኩበት አመታት እንጂ ለሰራውበት ደቂቃ አይደለም አለው ይባላል።

#Cosmos_Michael

፦አስተማሪ ነው ብላችሁ ያሰባችሁት ታርክ ለጓደኞቻችሁ Share በማድረግ አስተምሩ እኛም ይበልጥ እንተጋለን።

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
እናት....

እናት ለልጇ ሁለመናው አይደለች? የህይወት መንገዱ፣ ተስፋው፣ ጽናቱና የፍቅር ምንጩ ናት። የመቀነትን ሚስጥር እናስታውስ። ርሃብ ተሰምቷት ልትጎርስ የያዘችውን ቁራሽ ወደ አፏ ከማስጠጋቷ ልጇ አንዳች ቅዘት ውስጥ ሆኖ ብታየው የያዘችውን ጉራሽ በቀጥታ ለልጇ አጉርሳ መቀነቷን ታጠብቃለች። የኃይሏ ምንጭ ለልጇ የምትሰጠው ፍቅር-ነፍስ እንጂ ምግብ አይደለም። ከሚበላው ምግብ በላይ ወገቧ ላይ ሸብ የምታደርገው መቀነት ያጠግባታል።

እናት ለልጇ የምታደርገውን ሁሉ ቆጥራ አታውቅም። ማድረግ አለማድረጓን ብቻ ነው የምትከታተለው።
ፍቅር መጀመሪያ እንጂ መደምደሚያ የለውም። እናት አፍቃሪ ናት... ሁሌም ፍቅር መጀመሯን ታስባለች እንጂ “በቃኝ ከእንግዲህ የራሱ ጉዳይ” ስትል ልጇ ላይ አታምፅም። እኛ ደግሞ በተቃራኒው ያደረግንላትን እንቆጥራለን። ለሰው ስለእናት ፍቅር ስናወራ እንጂ በድርጊት ስናፈቅራት እምብዛም ነን።

መሀመድ አሊ(ቡርሐን አዲስ)
📖 የዘር ካርድ



=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
👍1
ልቧ እስኪጠፋ እንደምትወደኝ አውቃለው ስሜ እስኪጠፋኝ እወዳታለው....አንድ ቀን ፍቅሯ ንሽጥ አረገኝና "ታገቢኛለሽ " አልኩኝ
"ምን አለህ? " አለችኝ በማፌዝ አኳኋን::

"ማለት?" ግራ በመጋባት
"ለኔ የሚሆን ምን አለህ?" አለችኝ።
"ንፁህ ልብ ፍቅርና ጤና ....."
"ጤነኝነትህ መች ጠፋኝ በቀን ሶስት ድንች በአዋዜ ብቻ እየሰለቀጥክ እንዲህ ደልበህ እያየሁ......" አለችኝ።

'ምን?' አልኩ በውስጤ...ደሜ እንደበረንዳ ቡና ይንተከተክ ጀመር
"ቆይ ያ ሁሉ ውሸት ነበር ....አታፈቅርኝም ማለት ነው?"
"አፈቅርሃለው ነገር ግን ፍቅር ብቻ ትዳር አይሆንም?" አለችኝ።
"ፍቅር ትዳር ካልሆነ ታድያ የትዳር ዋስትናው ምንድነው?" ብሽቅ እያልኩ....
"ፍቅር የትዳር ዋስትና አይሆንሞ አላልኩም። ትዳር በፍቅር ብቻ አይቆምም። ትዳር ልብ ለልብ መግባባት፣ ፀባይ ከፀባይ መጣጣም....."

"ጀመርሽ እንግዲ....አትፈላስፊቢኝ" ስል ጮኼ አቋረጥኳት።
"አትጩህብኝ ግልፍተኛ! እንዲሁም አግብቼ እያከክኩ መኖር አልፈልግም ! አላገባህም" ስትል አንቧረቀች።

ሳላስብበት በደመነፍስ በቃሪያ ጥፊ አላስኳት።

አፍንጫዋን ይዛ ስትለቀው እየነሰረች ነበር። ምንድን ነው ያደረግኩት? የምይዝ የምለቀውን አጣሁ...

"አልጎዳሀኝም አትጨነቅ" አለችኝ። አፍንጫዋን መልስ እየያዘች፣ፈገግ ብላ እያየችኝ።

ነስሩ ጋብ ሲልላት

"አየህ ፈተናህን ወደቅክ .....እንደምታፈቅረኝ አውቃለሁ። ዳሩ ግን እንደሮሚዮ እስከመቃብር ሊከተለኝ የሚችል ፍቅር ቢኖርህም፣ ሲጥ አድርጎ ሊገድለኝ የሚችል ግልፍተኝነትህ ያሳስበኛል!" አለች ትኩር አድርጋ እየተመለከተችኝ..…

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
1
የቤት ሰራተኛዬ ነች። ልጆቼ እናታቸውን እኔ ባለቤቴን እስክረሳ ድረስ ቤቱን ቀጥ አርጋ የያዘች ታታሪ ሰራተኛ። በቀደም ለታ ስትፈራ ስትቼር አጠገቤ መጥታ፦

"ጋሼ እንደየው ቅር ካላሎት አንድ ነገር ባስቸግሮት?" አለች። አስሬ ባለቤቴ ወዳለችበት ክፍል ሰርቃ እያየች፡፡
"እሽ ምን ላግዝሽ?"
"እንድያው ጋሼ ለድፍረቴ ቅር እንዳይሎት።"
"ጌጤ ለምን በቀጥታ ወደ ጉዳይሽ አትገቢም?"
"እንድያው፤ ካላስቸገርኮት ደሞዝ ብትጨምርሉኝ? ከእትዬ ይልቅ አንተን ልጠይቅህ ብየ ነው."
"ጌጤ ጥያቄሽ ተገቢ መሆኑን አውቃለሁ። ነገር ግን ወቅቱን ያገናዘበ አይደለም። ሀገራች አሁን ባለችበት ቀውስ የደሞዝ ጭማሪ መጠየቅ ተገቢ አይደለም።" በሚል ሀተታ የጀመረ ረጅም ማብራርያ ጥያቄዋን አለመቀበሌን ገለፅኩላት።

በነጋታው አመመኝ ብላ ተኛች። ከዛሬ ነገ ይሻላታል እያልኩ ሳምንት ያህል ተኛች፡፡

ባለቤቴ ሀኪም ቤት ልትወስዳት ብትፈልግም አሻፈረኝ አለች። እናም እኔ አናገርኳት።

"መዳሃኒቴን ሀኪም መቼ አውቆት?" አለችኝ

"ዱሮስ! ካልታከምሽ፣ ካልታየሽ ሀኪም መደሃኒትሽን እንዴት ሊያውቀው ይችላል?"
"ይተው ጋሼ! ህመሜንም መድሃኒቴንም እኔ አውቀዋለሁ።" አለች በመሃል በመሀሃል እያቀሰተች፡፡

"ካወቅሽ ንገሪንና እናግዝሽ?"

"ህመሜ የቤት ጣጣ፤ መዳሃኒቴ ጥቁር በግ"

"የቤት ጣጣ? ጥቁር በግ?" አልኩ ግራ በመጋባት።

"ከአያት፣ ቅድመ አያት የወረስኩት የቤት ጣጣ፤ ዛር ነው እንዲህ የሚያረገኝ።" አለች፡፡

ዛር!? አንዳች ነገር ስውነቴን ውርር አደረገው፡፡

ማብራሪያዋን ቀጠለች።
"ሀገር ቤት እንዲህ ሲያረገኝ፤ ጥቁር በግ ታርዶ፤ ደሙን በገል ቀድተው ሲሰጡኝ ጠጥቼ...."

"በቃሽ!" ሳይታወቀኝ ጮህኩ፡፡

ወይ ጉድ! ሰው ብዬ ሳይታወቀኝ መለስተኛ-ቫንፓየር ጋር ከረምኩ? የኔስ ይሁን...እነዚህን ትናንሽ ልጆቼን ጉድ አድርጌያቸው ነበር እኮ።

ወጣች። አሰናበትኳት።
°°°°
ከወራት በኋላ የጓደኛዬ ሚስት ወልዳ ልጠይቃቸው ቤታቸው ጎራ አልኩ። ምን ቢሆን ጥሩ ነው? መለስተኛ ቫንፓየሯ ማለትም የቀደሞ ሰራተኛዬ ቤት ውስጥ ሽር ጉድ ስትል አየሁ፡፡ አጠገቤ ለተቀመጠው ኋደኛዬ፦
"ሰራተኛ አገኘህ እንዴ?" አልኩት።
"አንተ በነገርከኝ መሰረት ለደላለው ነግሬው ከአንዱ ደንባራ ቤት አስኮብልሎ አስወጣልኝ"
"ደንባራ? ማለት?" ንዴቴን ዋጥ ለማድረግ እየምከርኩ።

"አዋ! አንተ በነገርከኝ መሰረት ደላለው ከሰው ቤትም ቢሆን አስኮብልሎ እንዲያወጣልኝ መናገር....ከዚያ ልጂቱ ከደላላው ጋር ተነጋግራ "የቤት ጣጣዬ ተነሳ፤ ጥቁር በግ እረድልኝ ማለት።'...ያ ደንባራም፤ ተደናብሮ....."

"በዛ አቦ አትሳደባ" ብዬ አቋርጬው ቤቱን ጥየ ውልቅ።

=ኪ==ነ==ቃ==ል=
SHARE🌼
=ኪ==ነ==ቃ==ል=
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event