የፍልስፍና ዓላማ ከጠርሙሱ ውጭ መብረሪያ መንገዱን ማሳየት ነው!
-- Ludwig Wittgenstein --
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
JOIN US 🙏
SHARE
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
-- Ludwig Wittgenstein --
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
JOIN US 🙏
SHARE
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
🌿#ይሉኝ-_ታ
በሰዎች ላይ ከተደረጉ አስገራሚ ጥናቶች አንዱን ልንገርህ፤
የሰው ልጅ ከሞት በላይ ምንን የሚፈራ ይመስልሃል?
በአንደኝነት የሰፈረው ፍርሃት ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ መናገር ነው። የሰው ልጅ ከሞት በላይ የሚፈራው በሰው ልጆች መሀል ንግግር ማድረግን ነው፡፡
በአጠገብህ የሚኖረው የሰው ብዛት በጨመረ ቁጥር
ዳኝነቱም እየጠነከረ ይመጣል። ከታዳሚዎች ከሚመጣልህ ጭብጨባ ይልቅ በሰው ፊት መዋረድህ ያስፈራሃል፡፡
እኔ እንዲህ ነኝ ብለን ለራሳችን ክብር መጨነቃችን (መታበያችን) እና የሰዎች ዳኝነት ተጨምሮ ሲኦል ውስጥ ገብተናል:: እናም ሳርት እንዳለው - በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ያንተ ሲኦል ናቸው:: በሌሎች እይታ ውስጥ ነህ፤ መሆን የምትፈልገውን እንዳትሆን፣ የምትወደውን እንዳታደርግ ታስረሃል...
🌿 ከሰውና_ፍልስፍናው _ስንቅ🌿

♨ግጥም እና አጫጭር ፅሁፍ
ማስተዋወቅ እና ማጋራት የምትፈልጉ ካላችሁ...
በዚህ @yimesgen1 ላይ በመላክ እኛን ማነጋገር ትችላላችሁ። ♨
JOIN
@write_event
ማስተዋወቅ እና ማጋራት የምትፈልጉ ካላችሁ...
በዚህ @yimesgen1 ላይ በመላክ እኛን ማነጋገር ትችላላችሁ። ♨
JOIN
@write_event
ንገሯት
ባልገኝ ከድግስ
ብፈለግ ብታሰስ
ቀድሞ ና ያሉኝ
ከሰርጓ የጠሩኝ
ያለፈ ትዝታ ደርሶ ለመቃረም
ከትላንት ልመለስ ጭራሽ የለኝ ጊዜም
ንገሯት አሁን ላይ
እንኳን ሰርጓን ላይ
የሰጠኝን ሰዓት ከእድሜየ ምቀንስ
መስሎ አይሰማት የለውም ከድግስ
እኔም ሰርግ አለብኝ😎
ኩኩ ግርማ✍
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
JOIN US🌼SHARE🙏
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@Write_Event
@Write_Event
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ባልገኝ ከድግስ
ብፈለግ ብታሰስ
ቀድሞ ና ያሉኝ
ከሰርጓ የጠሩኝ
ያለፈ ትዝታ ደርሶ ለመቃረም
ከትላንት ልመለስ ጭራሽ የለኝ ጊዜም
ንገሯት አሁን ላይ
እንኳን ሰርጓን ላይ
የሰጠኝን ሰዓት ከእድሜየ ምቀንስ
መስሎ አይሰማት የለውም ከድግስ
እኔም ሰርግ አለብኝ😎
ኩኩ ግርማ✍
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
JOIN US🌼SHARE🙏
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@Write_Event
@Write_Event
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ተይኝ አልከኝ ተውኩክ
እልፈልግም አልከኝ ብዙ
አስለመንኩክ
ቆዝሜ ቆዝሜ አልቅሼወቶልኝ
"በቃ አሳየዋለው እኔም ሕይወት አለኝ"
"ያለእርሱ እንደምኖር ማሳየት
አለብኝ”
ብዪ ተነስቼ ሕመሜን ልረሳ
ደግሞ ትመጣለህ ደግሞ ትመጣለህ
አወይ የኔ አበሳ።
By Yemariyam work
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
JOIN US🌼SHARE🙏
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@Write_Event
@Write_Event
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እልፈልግም አልከኝ ብዙ
አስለመንኩክ
ቆዝሜ ቆዝሜ አልቅሼወቶልኝ
"በቃ አሳየዋለው እኔም ሕይወት አለኝ"
"ያለእርሱ እንደምኖር ማሳየት
አለብኝ”
ብዪ ተነስቼ ሕመሜን ልረሳ
ደግሞ ትመጣለህ ደግሞ ትመጣለህ
አወይ የኔ አበሳ።
By Yemariyam work
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
JOIN US🌼SHARE🙏
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@Write_Event
@Write_Event
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ሰሞኑን እኔ እንጃ
ከጥርስሽ ንጣት ከፀጉርሽ ሐር ፤
ተልኮብኛል ህቡዕ ስውር አድማ
ከድምፅ የትንፋሽሽ ቅፅበት ፤
ባቲ ቃኝቷል የልቤ ዜማ
ሀሌታ እነኾ ለፈጣሪ ፤ ለእጆቹ አጀብ ለጥበቡ
በዳሰሳት ስለዳሰሰን ፤ ስለታነፅን በሃሳቡ
እተነፍሰው ዘንድ ፤ ምን ተስፋ አድርጌ
ልማፀነው እንጂ ፤ የልብ መሻት ፈልጌ
ቢሆንልኝ መሰረቴ ተንዶ
ቢሳካልኝ ባገኛት ከማዶ
ናፍቆት ና መናፈቅ ፤ በናፍቆት በቀሩ
ፀሐይ ና ጨረቃም ፤ ዝምድናን ባልፈሩ፤
✍ቃልኪዳን (@kaliye06)
============
JOIN US🌼SHARE🙏
============
@Write_Event
@Write_Event
============
ከጥርስሽ ንጣት ከፀጉርሽ ሐር ፤
ተልኮብኛል ህቡዕ ስውር አድማ
ከድምፅ የትንፋሽሽ ቅፅበት ፤
ባቲ ቃኝቷል የልቤ ዜማ
ሀሌታ እነኾ ለፈጣሪ ፤ ለእጆቹ አጀብ ለጥበቡ
በዳሰሳት ስለዳሰሰን ፤ ስለታነፅን በሃሳቡ
እተነፍሰው ዘንድ ፤ ምን ተስፋ አድርጌ
ልማፀነው እንጂ ፤ የልብ መሻት ፈልጌ
ቢሆንልኝ መሰረቴ ተንዶ
ቢሳካልኝ ባገኛት ከማዶ
ናፍቆት ና መናፈቅ ፤ በናፍቆት በቀሩ
ፀሐይ ና ጨረቃም ፤ ዝምድናን ባልፈሩ፤
✍ቃልኪዳን (@kaliye06)
============
JOIN US🌼SHARE🙏
============
@Write_Event
@Write_Event
============
" እሚጠይቅ ሰው እስከጠየቀበት ሰአት ብቻ ነው አላዋቂነቱ! እማይጠይቅ ሰው ግን እድሜውን ሙሉ አላዋቂነቱን ተሸክሞት ይኖራል ። "
/ ኮንፊሽየስ /
============
JOIN US🌼SHARE🙏
============
@Write_Event
@Write_Event
============
/ ኮንፊሽየስ /
============
JOIN US🌼SHARE🙏
============
@Write_Event
@Write_Event
============
🤔 መማር ያለንን ለማውጣት ወይስ ባለን ላይ ለመጨመር..?
ሶቅራጥስ እንዲህ ብሎ ነበር...
" እኔ ማንንም ስለምንም ማስተማር አልችልም! እኔ ማድረግ የምችለው ማሰብ እንደሚችሉ ማሳየት ነው ። "
🗒 እኛ የምንማረውም ወይም መማር ያለብንስ ማሰብ እንደምንችል ለማወቅ አይመስላችሁም? እኛ የምንማረው የሆነ የምንወደውን ሰው ለመምሰል ወይም ለመተካት ከሆነ ወይም የመምራኖቻችንን አሳብ እንደወረደ የምንቀበል ከሆነ እኛ የነሱን አስተሳሰብ እንደወረደ የምንሸከም የአስተሳሰብ ወዛደሮች እንጂ ተማሪዎች መባል ይገባናል ብዬ አልልም ።
🗒 ቢላ የሚሞረደው ቅድሚያ የነበረውን ስለት ለማውጣት እንጂ አዲስ ስለት ለመስጠት አይደለም ። የትምህርት አላማውም አእምሮን ለመሳል እና ንቁ ለማድረግ እንጂ የሰውን አስተሳሰብን እና እይታ እኛ ላይ ለመጫን መሆን የለበትም ።
============
SHARE🙏
============
JOIN US🌼

ስብሀት ገ/እግዚአብሔር Vs አዳም ረታ
አዳም ረታ ስለ ድህነት ሲነግራችሁ "ጉድ ነው!!!" ብላችሁ እጃችሁን በአፍችሁ ያስጭናችኃል። ስብሀት ደሞ ድህነትን
ሲፅፈው ሚሊነር ብትሆኑም እንኳን ያላችሁን አስረስቶ በድህነት ብርድ ያስመታችኃል። አዳም ረታ ሴትን ጨረቃ ጎን ሰቅሎ ሲያስደምማችሁ፤ አቦይ
ስብሀት ደሞ ሴትን እስከ ልዩ ውበቷ አጠገባችሁ ቁጭ አርጎ እንድትነኳት ፣እንድትስሟት... ዳንስ ቤት ድረስ ወስዶ
ከከጀላችኃት እንስት ጋር እንድትደንሱ ያደርጋችኃል። አዳም ረታ ስለ ድምፅ ሲነግራችሁ ይሄም አለ እንዴ ብላችሁ
ትገረማላችሁ፤ ስብሀት ግን የሆነ ነገር አጋጭቶ ድምፁን እንድተሰሙት የሚያደርግ ምትሀታዊ ችሎታ አለው። በአቦይ ስብሀት ፅሁፍ አንባቢ ሳትሆኑ ራሳችሁ ተዋናይ ትሆናላችሁ። በአዳም ረታ ፅሁፍ ደሞ የንስር አይን ያለው አንባቢ ትሆናላችሁ። ሁለቱ በጭራሽ አይመሳሰሉም ቢሆንም ሁለቱም "ጂኒየስ" ናቸው። የአዳም ረታን ፅሁፍ ስታነቡ "እኔ በጭራሽ ደራሲ መሆን አልችልም። እንኳን መፃፍ ለአቅመ ማንበብም አልደረስኩም" ትላላችሁ። የስብሀትን መፅሀፍ ባነበባችሁ ማግስት "ፃፍ ፃፍ" የሚል አውልያ ይሰፍርባችኃል።
ስብሀት አትጨነቅ.. ፣ዘና በል.. ፣ይመችህ የሚል አራዳ ሲሆን ፤ አዳም ደሞ እያንዳንዷን ነጥብ በጥንቃቄ የሚመለከት ወግ አጥባቂ ነው (ወግ አጥባቂ በመልካም ጎኑ)። ስብሀት የቱንም ተራ ሀሳብ እንስቶ በልዩ የአፃፃፍ ፎርም
ሊያስደምማችሁ የሚችል ሲሆን፤ አዳም ረታ ደሞ ብዙ ተራ ሀሳቦችን እየጣለ ረቂቁ ላይ የሚመሰጥ ትንታግ ነው። ስብሀት የባለፈው ትውልድ እንቁ ከሆነ የኛ ዘመን አቻው አዳም ረታ ነው።....
የአቦይ ስብሐት ነፍስ በሰላም ትረፍ!!!!
የአዳም ረታ እድሜውን ያርዝምልን!!!

♥ሦስቱ ያባቴ ምክሮች (ከሞት ነጋዴው የተቀነጨበ)♦
***********************************
ልጅ እያለሁ እጅግ በጣም ራስ ወዳድና ሁሉንም ነገር ለኔ ባይ ነበርኩኝ” አሉና ጀመሩ ጨዋታ ቢጤ... እኝህ ማናቸው የቻይናው ፕሬዝዳንት? ‘ሺ ጂንግ ፒንግ’ የሚሏቸው ሰውዬ። አልፎ አልፎ እንዲህ በል ሲላቸው በንግግራቸው መሀል ስላሳለፉት የልጅነት ጊዜ ያወራሉ። አሁንም ለግማሽ ክፍለ-ዘመን ወደኋላ በትዝታ ተመልሰው ልጅ ሳሉ የሰሯቸውን ተንኮሎች በዝምታ ሲያሰቡ ቆዩና ቀጠሉ ንግግራቸውን።
“ራስ ወዳድ ከመሆኔ የተነሳ ሁልጊዜም ጥሩ ጥሩውን ለራሴ ነበር የምወስደው። ይኽ ባሕሪዬ ቀስ በቀስ ጓደኛ እያሳጣኝ መጣ። በመጨረሻም ጓደኞቼ ሁሉ ሸሽተውኝ ጓደኛ አልባ ሆንኩ። እኔ ግን ጥፋቴ ምን እንደሆነ አልገባኝም ነበር። ጓደኞቼ ስለሸሹኝ ኮነንኳቸው እንጂ ምን እንዳጠፋሁ ራሴን አልጠየኩም። ችግር እንዳለባቸው አሰብኩ እንጂ ችግር እንዳለብኝ አልፈተሽኩም። ቢሆንም አባቴ ሕይወትን በመልካም መንገድ እንዴት መምራት እንደምችል በተግባር አስተማረኝ።
“የአባቴ የሕይወት ትምህርት ሦስት ደረጃዎች ነበሩት።
“አንድ ቀን አባቴ ለሁለታችን የሚሆን ምግብ አዘጋጀና በሁለት ሳህን ከፍሎ የምግብ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። የተዘጋጀው ምግብ ፓስታ በእንቁላል ነበር። አባቴ ፓስታውን ሲያስቀምጠው በአንደኛው ሳህን ከፓስታው በተጨማሪ የተቀቀለ አንድ እንቁላል ከአናቱ አድርጎበታል። በሌላኛው ሳህን ግን ከፓስታው በላይ እንቁላል የሚባል ነገር የለበትም። ከዚያ አባቴ ወደ እኔ እየተመለከተ፣
“ልጄ! የትኛውን ትፈልጋለህ? አንዱን ሳህን ምረጥና አንሳ...” አለኝ።
በጊዜው፣ እንቁላል እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ ምግብ አልነበረም። ድህነቱ፣ ገንዘብ ማጣቱ በሁላችንም ቤት ጫን ያለ ስለነበረ አዲስ ዓመት ካልመጣ ወይም ዓመትባል ካልደረሰ በቀር እንቁላል መብላት ዘበት ነው። ታዲያ እኔ፣ አንዱን ሳህን መርጬ እንድወስድ አባቴ ሲጠይቀኝ ፈጥኜ እንቁላል ያለበትን ሳህን መረጥኩ። እንዴ ማን ይሞኛል? እንቁላል ተገኝቶ ነው? በሰዓቱ እንቁላል ያለበትን ሳህን ሳነሳ ቅንጣት ታህል አላመነታሁም ነበር። ደስ እያለኝ ፓስታ በእንቁላሌን መብላት ጀመርኩ።
አባቴ ሁለተኛውን ሳህን አንስቶ መመገብ ሲጀምር ግን ዐይኔን ማመን አቃተኝ። አባቴ ከሚበላበት ሳህን ውስጥ ሁለት የተቀቀሉ እንቁላሎች በፓስታው ተሸፍነው ኖሯል። አቤት አንዴት እንደተናደድኩ! ቆጨኝ በጣም! ቸኩዬ በመወሰኔ ራሴን ወቀስኩት። ምናልባትም በሕይወት ዘመኔ እንደዚያ ቀን የተበሳጨሁበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። ይኼን ጊዜ አባቴ እየሳቀ፣
“የእኔ ልጅ… ዐይኖችህ የሚያዩት ነገር ሁሉ እውነት እንዳልሆኑ መቼም እንዳትረሳ! ደግሞ በሰዎች ላይ ብልጣብልጥ ለመሆን ስትሞክር ትጎዳለህ!!” አለኝ።
በሌላ ቀን አባቴ በተመሳሳይ ምግብ አዘጋጅቶ ሲያበቃ እንደተለመደው ፓስታውን በሁለት ሳህን አቀረበው። አንደኛው ሳህን አናት ላይ አንድ የተቀቀለ እንቁላል አስቀምጦበታል። ሌላኛው ላይ ግን ካናቱ ምንም እንቁላል አላደረገበትም። ከዚያ እንደተለመደው አባቴ ወደ ምግብ ጠረጴዛው እየጠቆመ፣
“በላ ልጄ! ምረጥና የምትፈልገውን ሳህን ውሰድ..እየጠቆመ፣
ካለፈው ሥህተቴ በመማር በጥንቃቄ መምረጥ እንዳለብኝ አሰብኩና ቀልጠፍ ብዬ ካናቱ እንቁላል የተደረገበትን ትቼ ሌላኛውን መረጥኩ። ከዚያ በፍጥነት ፓስታውን ገላለጥኩና ሳህኑን ዐየሁት። በጣም ደነገጥኩ! ሳህኑ ውስጥ አንድም እንቁላል የሚባል ነገር የለውም። አባቴ በድጋሚ እየሳቀ፣
“ልጄ… ሁልጊዜ በልምድህ ላይ ብቻ የምትተማመን ከሆነ ትከስራለህ። አንዳንዴ ሕይወት ራሷ ልታሞኝህ ወይም ቁማር ልትጫወትብህ ትችላለች። ዳሩ ግን በዚህ ብዙ ልታዝን ወይም ልትቆጣ አይገባም… ትምህርት እንደሚሆንህ ቆጥረህ ብቻ እለፈው። እንዲህ ያለውን እውቀትየተቀቀለው መጽሐፍት ላታገኝ እንደምትችል አስታውስ!!” ብሎኝ፣ ያቺ ቀን አለፈች።
ለሦስተኛ ጊዜ አባቴ ምግብ አዘጋጀ። እንደተለመደው ፓስታና እንቁላሉ በሁለት ሳህኖች ቀርቧል። ባንዱ ሳህን የተቀቀለው እንቁላል ከፓስታው በላይ ተቀምጧል። በሌላኛው ሳህን ደግሞ ፓስታ ብቻ። እንግዲህ የውስጡን አላውቅም… ከላይ ግን እንቁላል የለውም። አባቴ የተለመደ ጥያቄውን አቀረበልኝ። ወደ ምግብ ጠረጴዛው በአገጩ እየጠቆመ፣
“ልጄ ምን ትጠብቃለህ? ምረጣ!! የትኛው ሳህን ይሁንልህ?” አለኝ።
አሁን እኔ ከሁለቱ ሥህተቶቼ በደንብ ትምህርት አግኝቻለሁ።
“አባቴ አንተ የቤቱ አባወራ ነህ! ለቤተሰባችን ሰርክ የምትለፋ፣ ደከመኝ ሳትል ቀን-ከሌት እኛ እንዳይርበን የምትሠራ አባት ነህ። መጀመሪያ መብላት ያለብህ አንተ ነህ… ለስኩለት። ስለዚህ ቅድሚያ አንተ አንሳ…” ስል መለስኩለት።
አባቴ በጭራሽ አላቅማማም። ከአናቱ እንቁላል የተቀመጠበትን ሳህን አንስቶ መብላት ጀመረ። እኔም ሁለተኛውን ሳህን አንስቼ ፓስታዬን ለመብላት አቀረቀርኩ። እርግጠኛ ነበርኩ፣ ሳህኑ ውስጥ እንቁላል እንደማይኖር። ከፓስታው በታች ሁለት እንቁላሎችን ሳገኝ ግን ዐይኔን ማመን አልቻልኩም። ቀና ብዬ ሳየው አባቴ ፈገግ ብሎ በፍቅር ዐይኑ እያስተዋለኝ ነበር። ከዚያም እንዲህ ሲል መከረኝ፣
“የኔ ውድ ልጅ! ለሌሎች ሰዎች መልካም መልካሙን ስታደርግ ተፈጥሮ ራሷ መልካም መልካሙን ወደ አንተ ታመጣለች! ይኼንን መቼም እንዳትዘነጋ!!” አለኝ።
ከዚያን ጊዜ በፊትም ሆነ ከዚያን ጊዜ በኋላ አባቴ ብዙ ጊዜ መክሮኛል! ገስፆኛል! ገርፎኛል! አብዛኞቹን ማስታወሴን እጠራጠራለሁ። ነገር ግን እነዚህን ሦስት ምክሮቹን በፍጹም አልረሳቸውም! እስክሞትም ድረስ የምረሳቸው አይመስለኝም። እነሆ ሕይወቴም በዚህ ምክንያት የተስተካከለ ሆኗል። ከአባቴ ምክር በኋላ ስኬት መንገዷን ወደእኔ አድርጋለች።
ከሞት ነጋዴው የተቀነጨበ።
መጽሀፉን ለማግኘት ወደ መደብሮች ጎራ ይበሉ

ቃል💠
ውዴ ትዝ ይልሀል
ያቺ ድፍን ልቤን ❤ ከፍተክ የገባህ ለት
በአይኖቼ መሀል የተተከልክ ለት
ውዴ ትዝ አይልህም?
አይኔ ካንተ ሌላ በፍጹም አያይም
ጆሮዬ ካንተ ሌላ እንደውም አይሰማም
ብዬ ያልኩህ እለት
እኔ ትዝ ይለኛል
አንቺን ያየሁ ለት
ሰማይ ምድር ጠባ ወዴትስ ልከተት
ብለህ ያልከኝ ለት
ውዴ ትዝ አይልህም?
የፍቅርን ሀሁ ያስተማርከኝ ለት
የልጅነት ክብሬን የልቤን በር ቁልፍ፣
ያስረከቡኩህ እለት
ውዴ ትዝ ይልሀል?
የህዳር ሚካኤል ቤተክስቲያን ሄደን
ቃል ኪዳን ገብተናል በአምላክ ፊት ቆመን
አባ ሲያስተምሩ
ቃል ማለት እዳ ነው
ቃል ማለት እምነት ነው
ቃል ማለት ፍቅር ነው
ቃል ማለት ህይወት ነው
ውዴ ትዝ ይልህ ይሆን?
የቃልን ምንነት የተረዳን እለት
ውዴ ትዝ ይለኛል
አንቺ ማለት ለኔ....
የምስያ ቃሎች አነሱብኝ ባይኔ
እንደውም ልንገርሽ
አንቺ ማለት ለኔ
ኩዋክብት አጅበው ዙሪያ የቆሙላት
አንቺ ጨረቃ ነሽ
ብለህ ያልከኝ እለት
አለሜ ልንገርህ
እስኪ ስማኝ አንዴ
የህዳር ሚካኤል ያቺ ቅዱስ ቀን፣
ፍርድ አዘነበለች አንዴ
አንተ ማለት ለኔ
እኔ ማለት ላንተ
ውዴ ትዝ ይልሀል?
ጥለህ የሄድከኝ እለት
ፍቅሬ ትዝ ይልሀል
ቃል ኪዳን ያለባት ያች የሰንበት እለት
ለነገሩ ተወው
በቃ ተወው ፍታው
አምላክ ቃላችንን
ያቺ እለታችንን
ከቅዱስ ቃሉ ጋር፣
ባያዋህደው ነው።
ውዴ ተወው በቃ
ፍቅር ማለት ሞት ነው
ፍቅር ገሀነም ነው
ትዝታችን ትዝታ ሆኖ ዳግም መሞቱ ነው።
============
SHARE🙏
============
JOIN US🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
============
ውዴ ትዝ ይልሀል
ያቺ ድፍን ልቤን ❤ ከፍተክ የገባህ ለት
በአይኖቼ መሀል የተተከልክ ለት
ውዴ ትዝ አይልህም?
አይኔ ካንተ ሌላ በፍጹም አያይም
ጆሮዬ ካንተ ሌላ እንደውም አይሰማም
ብዬ ያልኩህ እለት
እኔ ትዝ ይለኛል
አንቺን ያየሁ ለት
ሰማይ ምድር ጠባ ወዴትስ ልከተት
ብለህ ያልከኝ ለት
ውዴ ትዝ አይልህም?
የፍቅርን ሀሁ ያስተማርከኝ ለት
የልጅነት ክብሬን የልቤን በር ቁልፍ፣
ያስረከቡኩህ እለት
ውዴ ትዝ ይልሀል?
የህዳር ሚካኤል ቤተክስቲያን ሄደን
ቃል ኪዳን ገብተናል በአምላክ ፊት ቆመን
አባ ሲያስተምሩ
ቃል ማለት እዳ ነው
ቃል ማለት እምነት ነው
ቃል ማለት ፍቅር ነው
ቃል ማለት ህይወት ነው
ውዴ ትዝ ይልህ ይሆን?
የቃልን ምንነት የተረዳን እለት
ውዴ ትዝ ይለኛል
አንቺ ማለት ለኔ....
የምስያ ቃሎች አነሱብኝ ባይኔ
እንደውም ልንገርሽ
አንቺ ማለት ለኔ
ኩዋክብት አጅበው ዙሪያ የቆሙላት
አንቺ ጨረቃ ነሽ
ብለህ ያልከኝ እለት
አለሜ ልንገርህ
እስኪ ስማኝ አንዴ
የህዳር ሚካኤል ያቺ ቅዱስ ቀን፣
ፍርድ አዘነበለች አንዴ
አንተ ማለት ለኔ
እኔ ማለት ላንተ
ውዴ ትዝ ይልሀል?
ጥለህ የሄድከኝ እለት
ፍቅሬ ትዝ ይልሀል
ቃል ኪዳን ያለባት ያች የሰንበት እለት
ለነገሩ ተወው
በቃ ተወው ፍታው
አምላክ ቃላችንን
ያቺ እለታችንን
ከቅዱስ ቃሉ ጋር፣
ባያዋህደው ነው።
ውዴ ተወው በቃ
ፍቅር ማለት ሞት ነው
ፍቅር ገሀነም ነው
ትዝታችን ትዝታ ሆኖ ዳግም መሞቱ ነው።
============
SHARE🙏
============
JOIN US🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
============
[ … ከ ት ና ን ት ፡ የ ተ ጫ ረ ‘ ሳ ት
፧
እንደሰበዓሰገል ፡ ኮከብ ፡ ምሪት
እንደመከተል – የሰጠሽኝ ፡ ምልክት
የዐይንሽ – የቃልሽ ፡ ምሥጢር
ለዛኔው ፡ እኔ ፡ ቢጠጥር ፤
ሳይገባኝ
ስቀቴ ፡ እንደመራኝ
ወርቅሽን ፡ በሰም ፡ ፈክሬ
ሲገባኝ
እሳቱ ፡ ተረፈኝ ፡ ዛሬ ።
ለካ…
ወደድኩሽ ፡ ብዬ ፡ ስመናቀር
ሞትኩልህ ፡ ብለሽኝ ፡ ነበር ።
መ ዘ ክ ር ፡ ግ ር ማ … ]
============
JOIN US🌼SHARE🙏
============
@Write_Event
@Write_Event
============
፧
እንደሰበዓሰገል ፡ ኮከብ ፡ ምሪት
እንደመከተል – የሰጠሽኝ ፡ ምልክት
የዐይንሽ – የቃልሽ ፡ ምሥጢር
ለዛኔው ፡ እኔ ፡ ቢጠጥር ፤
ሳይገባኝ
ስቀቴ ፡ እንደመራኝ
ወርቅሽን ፡ በሰም ፡ ፈክሬ
ሲገባኝ
እሳቱ ፡ ተረፈኝ ፡ ዛሬ ።
ለካ…
ወደድኩሽ ፡ ብዬ ፡ ስመናቀር
ሞትኩልህ ፡ ብለሽኝ ፡ ነበር ።
መ ዘ ክ ር ፡ ግ ር ማ … ]
============
JOIN US🌼SHARE🙏
============
@Write_Event
@Write_Event
============
ሹርባ ሰራሁት
══✦══
✍ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ)
'
እፀድቅ ብሎ ቢያዝለኝ . .
ሹርባ ሰራሁት . .
ሱሪው ባተ ሁለት .. ያውም ተፈሪ ቅድ
መቸም ትጥቅ አይፈታም .. በልቡ ሳያቅድ
ሁሉ እንዳገሩ ወፍ .. ሲጮህ እንደመልካው
ጎራ ያስረግዳል .. ጃሎውን ሲያስነካው
ወድቆ እንዳይሰበር .. ተናግሮ እንዳያፍር
ያንጀት በሆድ ያድራል .. ጥርስ በከናፍር
ለጋስ እንዳይባል .. መስጠት ሲያመነታ
ይሰበራል ልቡ .. ለተቀባይ ፋንታ
እኔይቱ ልጅት . .
መደቆሻ መጂት . .
እንዲያም እንዲያም ብዬ . .
አደረግኩት ድርጅት
ፊት እንደመቅለስለስ
እንደማለሳለስ
ኋላ እንደማሽኮርመም . .
አቅፎ እንደማስታመም
ደሞ ዳበስ ዳበስ
ደሞ ራሱን ስርት . .
በፍቅር አሸንፌ . .
ወንዱን ጥዬ ኩርት . .
════════
📓 የነቢያት ጉባኤ
🗓 የካቲት 2011 ዓ.ም.
አሰናጅ፦ ፋሲካ ከበደ
📖 📖 📖 📖 📖
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
══✦══
✍ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ)
'
እፀድቅ ብሎ ቢያዝለኝ . .
ሹርባ ሰራሁት . .
ሱሪው ባተ ሁለት .. ያውም ተፈሪ ቅድ
መቸም ትጥቅ አይፈታም .. በልቡ ሳያቅድ
ሁሉ እንዳገሩ ወፍ .. ሲጮህ እንደመልካው
ጎራ ያስረግዳል .. ጃሎውን ሲያስነካው
ወድቆ እንዳይሰበር .. ተናግሮ እንዳያፍር
ያንጀት በሆድ ያድራል .. ጥርስ በከናፍር
ለጋስ እንዳይባል .. መስጠት ሲያመነታ
ይሰበራል ልቡ .. ለተቀባይ ፋንታ
እኔይቱ ልጅት . .
መደቆሻ መጂት . .
እንዲያም እንዲያም ብዬ . .
አደረግኩት ድርጅት
ፊት እንደመቅለስለስ
እንደማለሳለስ
ኋላ እንደማሽኮርመም . .
አቅፎ እንደማስታመም
ደሞ ዳበስ ዳበስ
ደሞ ራሱን ስርት . .
በፍቅር አሸንፌ . .
ወንዱን ጥዬ ኩርት . .
════════
📓 የነቢያት ጉባኤ
🗓 የካቲት 2011 ዓ.ም.
አሰናጅ፦ ፋሲካ ከበደ
📖 📖 📖 📖 📖
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
" . . . ሲጋደም ሀበሻ የሚያስበው ትላንትናን እና ነገን ነው። ብዙ ግዜ ያለፈ አመቱን ነው። ሲወለድ እናቱ ያላሰችውን ቅቤ ነው።
ሀበሻ ከማንም ዜጋ የበለጠ ታሪካዊ እንስሳ ነው።
ታዲያ "ዛሬ" የተባለች የጊዜ መለያ በአጠገቡ እያፉዋጨች ስታልፍ አያያትም። እንደገናም፡ ነገን ላገኝ ብሎ፡ ለሆነ ቆራጣ ራእይ ዛሬ ሸር ሲሰራባት፡ ሲጠልፍባት፡ በፖለቲካ ሲናከስባት፡ ሲብጠለጠልባት የሚመኛት ነገን በዛሬ ሲያፈርስ ጊዜ ያልፋል"
#ይወስዳል_መንገድ_ያመጣል_መንገድ
ደራሲ አዳም ረታ

የታርክ ድግግሞሽ በቅብብሎሽ አልፎ
በወንበዴው ስሌት ሚስኪን ተሰልፎ ይሄው ...
ዛሬም በኛ ዘመን በርባኖች ሲተርፉ
እንደ ቅዱሱ ክርስቶስ ሚስኪኖች አለፉ።
✍#ቃልኪዳን (@kaliye06)
============
JOIN
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
የእውነት ደስተኛ መሆን ከፈለግክ ሰዎችን ሳይሆን ፈጣሪን ብቻ ለማስደሰት ሞክር!
-- ሊኦ ቶልስቶይ --
============
SHARE
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
-- ሊኦ ቶልስቶይ --
============
SHARE
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"የሰው ልጅ ራሱን መካድ ሲጀምር ባህልና ስልጣኔን አመጣ... እንዲሁ መቀጠል ቢፈቀድለት ደግሞ ዓለማችን ላይ ከፍ ያለ ዋጋ የምንሰጠውን ነገር ሁሉ እንዲያበቃለት ማድረግ ይቻለዋል ። ስለሆነም በዚህ የባርነት ሞራላዊ አስተሳሰብ ልንቀጥል አይገባንም ።"
#ኒቼ-
============
SHARE
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
#ኒቼ-
============
SHARE
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🌗``ክፉ ቀን ጥሩ ነው´´
============
SHARE
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
✍ፕሮፌሰር መስፍን "አገቱኒ ተምረን ወጣን" በሚለው መጽሀፋቸው ስለ ክፉ ቀን እንዲህ ይላሉ፡፡.....
🌗 ክፉ ቀን ጥሩ ነው መማር የፈለገውንም ያስተምራል ፈጣሪ ሀያላን ነን የሚሉትንም ያስተምራል፡፡
ክፉ ቀን ጥሩ ነው ደጋግ ሰወችን ይቀሰቅስና የግፍን መራራነት እንዲቀንሱት ያደርጋል፡
ክፉ ቀን ጥሩ ነው በተለያየ የኑሮ ደረጃ የተከፋፈሉትን በአላማ ያያይዛቸዋል፡፡
ክፉ ቀን ጥሩ ነው የግፍን ጥርስ ሁሉም እንዲያየውና እንዲንቀው ያደርጋል፡፡
🌗 ክፉ ቀን ጥሩ ነው ብዙ ጉድ ያሳያል።የተማረውና የተመራመረው አምሮውን በኦሞ ሙልጭ አድርጎ አጥቦ ህሊናውን በጨጓራው አፍኖ የሆነውን አልሆነም እያለ ለልጆቹ ሀፍረን ሲሆን ያሳየናል።
-
ክፉ ቀን ጥሩ ነው ያለፈውን ካለው ጋር በእውነት እንድናወዳድረው ያስገድደናል።
ክፉ ቀን ጥሩ ነው ክብርን ወደ ውርደት ውርደትን ወደ ክብር ይለውጣል።
ክፉ ቀን ጥሩ ነው የጉልበተኛውን ልብ ያደነድናል አእምሮውንም ደርግሞ ይዘጋዋል የጭካኔውንም ወሰን የለሽነት ያሰየናል።
🌓 ክፉ ቀን ጥሩ ነው ጥሩ ቀንን እየጮኸ ይጣራል።
ክፉ ቀን ጥሩ ነው የወደቀውን ለድል የጣለውን ለውድቀት ያዘጋጃል
ክፉ ቀን ጥሩ ነው ክፋት በጎነትን አሸንፎ እንደማይዘልቅ ያሳያል ህግ ቀልቡ ሲገፈፍ ዳኝነት ሚዛን ሲያጣም ያሳያል
ክፉ ቀን የጠራ መስትዋት ነው መልካችንን ብቻ ሳይሆን ባህሪያችንንም ጤናችንን ብቻ ሳይሆን ህመማችንንም ውበታችንን ብቻ ሳይሆን አስከፊነታችንንም ቁልጭ አርጎ ያሳየናል
ክፉ ቀን ጥሩ ነው ባጠቃላይ የመጪው ጥሩ ቀን ምልክት ነው።============
SHARE
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
አዋቂ ዝም ሲል ሞኝ ይበዛል!
-- Nelson Mandala --
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
-- Nelson Mandala --
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ስለራሳቸው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የሚሆኑት ባለባቸው ድንቁርና ነው!
-- Franz Kafka --
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
-- Franz Kafka --
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
አስተሳስብህን ተመልከት፤ ቃላት ይሆናሉ፣ ቃላትህን ተመልከት፤ ድርጊት ይሆናሉ፣ ድርጊትህን ተመልከት፤ ልማድ ይሆናሉ፣ ልማድህን ተመልከት፤ ባህሪህ ይሆናል፣ ባህሪህን ተመልከት፤ መዳረሻህ ይሆናል !
--Lao Tez--
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
--Lao Tez--
============
SHARE🌼
============
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event