አንድ የስነ-ሰብ (Anthropology) ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።
ጨዋታውም፣ በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው:-
"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል:: "
ጨዋታው ተጀመረ።
ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።
ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ::
የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው።
ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ! " በማለት መለሱለት።
በመቀጠል አንዱ ህፃን እንዲህ አለው:-
"እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም::"
"ኡቡንቱ" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪቃው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም:-
“ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!” የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።
---------------------------
Share & join
@write_event

ንጉሥ ሲጨንቀው
የአንዲት ደሃ ሃገር ዜጎቿ በሙሉ፣
መሄጃ ቢያሳጡት “ተራብን!” እያሉ፣
ምስኪን ንጉሣቸው እንዲህ ፀለየ አሉ፦
“እባክህ አምላኬ!
የተራበ ሕዝቤን ሲያሻህ በነጠላ፤
ካሰኘህ በጅምላ፣
ከፊቴ አርቅና ባህር ክተትልኝ፤
ከሃይቅ ጣልልኝ፡፡
ከዚያማ!
ያልቻሉት ሲሰምጡ፤
የቻሉት ለማምሻ ዓሣ ይዘው ይውጡ!"
ገጣሚ -በረከት በላይነህ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የአንዲት ደሃ ሃገር ዜጎቿ በሙሉ፣
መሄጃ ቢያሳጡት “ተራብን!” እያሉ፣
ምስኪን ንጉሣቸው እንዲህ ፀለየ አሉ፦
“እባክህ አምላኬ!
የተራበ ሕዝቤን ሲያሻህ በነጠላ፤
ካሰኘህ በጅምላ፣
ከፊቴ አርቅና ባህር ክተትልኝ፤
ከሃይቅ ጣልልኝ፡፡
ከዚያማ!
ያልቻሉት ሲሰምጡ፤
የቻሉት ለማምሻ ዓሣ ይዘው ይውጡ!"
ገጣሚ -በረከት በላይነህ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የአባልነት ምዝገባ ተጀምሯል።
ለመመዝገብ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ :-
1. በ www.abrehot.org.et/register/ በመግባት የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ
2. ፎርሙን እንደጨረሱ ወደ ክፍያ ገፅ ይወስዳቹሀል ፣ አመታዊ የአባልነት ክፍያ በቴሌብር ወይም በንግድ ባንክ በኩል በቀላሉ መክፈል ይችላሉ።
3. ቅድመ ተከተሉን እንደጨረሱ አባልነቶ አፕሩቭ ይሆናል።
ቅድመ ተከተሉን ከጨረሱ ቡሀላ በ15 ቀን ውስጥ ዲጂታል የአባልነት መታወቂያ በኢሜይል ይደርሶታል።
አባል ሲሆኑ የሚከተለውን ጥቅሞች ያገኛሉ :-
1. መፃህፍትን በነፃ መዋስ።
2.ለ12 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ሙሉ ወጪ በመሸፈን።
3. የጋራ የውይይት ክፍሎችን በኦንላይን ማግኘት።.
4. ከ 1.5 ሚልየን በላይ ጆርናሎች እና የመመረቂያ ፅሁፎች በቀላሉ በኦንላይን ማግኘት።
5.በቶሞካ ትኩስ መጠጦች ላይ 35% ቅናሽ።
ብርሀን ለኢትዮጵያ 🇪🇹
Abrihon Library Official Facebook Page

#Lets #see #the #world #together
ቀናችሁን ሊያበረላችሁ የሚችል ቆንጆ App ልጠቁማችሁ።
"be my eyes" ይባላል፣ አይነ ስውራን የሆኑ ሰዎችን በ live chat የምንረዳበት app ነው።
በአለም ላይ በአሁኑ ሰዓት ከ6.2 ሚሊየን በላይ በጎ አድራጊዎች አይነስውራንን ለመርዳት ይህን አፕሊኬሽን ይጠቀማሉ። ከ452 ሺህ በላይ አይነስውራን ተጠቃሚ ሆነውበታል። አማርኛን ጨምሮ የምትችሉትን ቋንቋም ያስመርጣችኋል።
ይህን አፕሊኬሽን መኖሩን የነገረችኝ አይነስውር የሆነች ጓደኛዬ ናት። በጣም ጎበዝና ብርቱ ናት።
እንደ እድል ሆኖ አሁን ከነጋ online እያለሁ አንድ አፕሊኬሽኑን የሚጠቀም አይነስውር ሰው #ከናይጀሪያ ደወለልኝና ምንድነው ፊትለፊቴ ያለው? አለኝ ካሜራው ቪድዮ በቀጥታ እያሳየኝ የሚታየውን ነገር ነገርኩት፣ #ከኢትዮጵያ እንደሆነኩም ሲያውቅ ደስ አለው።
ይበልጥ እኔን ደስስስስስስ አለኝ።
አፕሊኬሽኑን በአካባቢያችን ላሉት አይነስውራን ብንጭንላቸው ደስታው ለኛው ነው፣ በ Androind በ ios ም አለው።
#See_the_world_together
Android Download link
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bemyeyes.bemyeyes

Google Play
Be My Eyes - Apps on Google Play
Enables blind to receive live assistance from sighted volunteers.
''አንድም…
መስማትህ ምን ያህል ማየትህ ምን ድረስ
እንዳዲስ ተሰርቶ ደግሞ አድሮ ለመፍረስ፤
አንድም
የኑሮ ቡቱቶ ዝተት የሚያስጎትት
ልብ አለማለት ነዉ በልብ ዉስጥ ክትት።
አንድም
ሰዉ ራሱን ማየት ሲጀምር
ዓይነ ኅሊናዉ፤ ይከፈታል ልቡናው''
© ሙልጌታ ተስፋዬ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
መስማትህ ምን ያህል ማየትህ ምን ድረስ
እንዳዲስ ተሰርቶ ደግሞ አድሮ ለመፍረስ፤
አንድም
የኑሮ ቡቱቶ ዝተት የሚያስጎትት
ልብ አለማለት ነዉ በልብ ዉስጥ ክትት።
አንድም
ሰዉ ራሱን ማየት ሲጀምር
ዓይነ ኅሊናዉ፤ ይከፈታል ልቡናው''
© ሙልጌታ ተስፋዬ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
''ማነው ተጠያቂ''
''ነፍሴማ ባህር ነው
እልፍ ቢረመረም
ዱካሽን አያትም!
ኮቴሽም ቆሌ ቢስ
እማያባንነኝ
በንቃት በሕልሜ
ሺህ ዘመን ብታልፊ፣
በማ ሊፈረድ ነው?
ለማን አቤት ሊባል?
ጥሪሽን ስጠብቅ
ግድቤን ጣጥሰሽ
ይዘሽ ስትጠፊ!''
©ስንቅነህ እሸቱ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
''ነፍሴማ ባህር ነው
እልፍ ቢረመረም
ዱካሽን አያትም!
ኮቴሽም ቆሌ ቢስ
እማያባንነኝ
በንቃት በሕልሜ
ሺህ ዘመን ብታልፊ፣
በማ ሊፈረድ ነው?
ለማን አቤት ሊባል?
ጥሪሽን ስጠብቅ
ግድቤን ጣጥሰሽ
ይዘሽ ስትጠፊ!''
©ስንቅነህ እሸቱ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
✦ የሳምንቱ መልዕክት ✦
''በራስ መተማመኑን ያየዘ ጥበብን ፈላጊ አዲሱን ሐሳብ ከቀደመ ማንነቱ ጋር ማስታረቅ የሚችል የብሩህ አዕምሮ ባለቤት ነው።''
ባንድ ወቅት ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ስለፍልስፍና ለቀረበለት ጥያቄ ይህን ብሎ ነበር።
''ጠያቂ፦ ፍልስፍና ያሳብዳል?
ስብሐት፦ ፍልስፍና አያሳብድም። አንድ ሰው ፍልስፍና አንብቦ ካበደ ፡ መጀመሪያውኑ ለማበድ የሚያበቃ እርሾ በውስጡ ነበረ ማለት ነው።
ጠያቂ፦ ፍልስፍና ለምን በጥርጣሬ ይታያል?
ስብሐት፦ ብዙ ሰዎች ፍልስፍናን በሩቁ ይላሉ፤ ይፈራሉ። መጀመሪያውኑም የነበራቸው እምነት ጠንካራ ስላልነበረ ትንሽ ፍልስፍና እንዳነበቡ ከሥር መሠረታቸው ይናጋሉ ፤ ልባቸው በጥርጣሬ ይሞላል። ልብ አድርግ! ያናጋቸው ፍልስፍናው አይደለም፤ ቀድሞ የነበራቸው ደካማ እምነት እንጂ!"

Book for ALL | (Facebook)
የትንሽ ነገር ... ከሲኣት ትንሿ እህቴ ከሩቅ እየተጣራች መጣች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ”
እናታችን ለጨረሩ መከላከያ መዳፏን ግንባሯ ላይ አጋድማ “ምነው? ምን ሆንሽ?” አለች “ዱላ ስጪኝ ዱላ ስጪኝ” “ምነው? ለምንሽ?” “አለቃ ተመረጥኩ” ዱላ አሳጥራ ሰጠቻት። . . . አመሻሽ ትንሿ እህቴ እያለቀሰች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ” እናታችን “ምነው? ምን ሆንሽ?” “ከአለቃነት ተሻርኩ”
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ርዕስ፡ውልብታ"
ደራሲ፡አለማየሁ ገላጋይ ገጽ፡፶

------- ሀገር
ስውር ድብቅ ቅኔ፤
------ ፍቅር
የፈጣሪ ጽዋ ሰው የመሆን መቅኔ።
እናም በህይወት ግንድ ላይ
እናት መውለድ ያንቃት!
ሀገር ትውልድ ያንፃት!
ፍቅርን ሞት አይግዛት!
---------------------------
ገላና ገላ የግጥም መድብል
ገጣሚ - መላኩ ደምሴ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ስውር ድብቅ ቅኔ፤
------ ፍቅር
የፈጣሪ ጽዋ ሰው የመሆን መቅኔ።
እናም በህይወት ግንድ ላይ
እናት መውለድ ያንቃት!
ሀገር ትውልድ ያንፃት!
ፍቅርን ሞት አይግዛት!
---------------------------
ገላና ገላ የግጥም መድብል
ገጣሚ - መላኩ ደምሴ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
እኔ ምልሽ ውዴ . . .
ራብ ገብቷል አሉ...
ትልሽው ትቀምሽው
እፍኝ ቆሎ ርቆሽ ጠኔ ጣለሽ እንዴ፣
---------------------------
አንፈርስም አንታደስም
ደራሲ - አሌክስ አብርሃም
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ራብ ገብቷል አሉ...
ትልሽው ትቀምሽው
እፍኝ ቆሎ ርቆሽ ጠኔ ጣለሽ እንዴ፣
አንድ አንቺን መታደግ አቅቶት ይሆን ወይ
በዜና መስፈሪያው... የሰፈሩት ዘይት... የሰፈሩት ስንዴ?---------------------------
አንፈርስም አንታደስም
ደራሲ - አሌክስ አብርሃም
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የ'ኔ copy right
ተሰጥኦ ኖሯቸው ፣ ዜማ የደረሱ
ዜማ ቢሰረቁ ለዳኛ ከሰሱ
እኔስ በተራዬ ፣ የት ሄጄ ልክሰሰው
ዝምታዬን ሰርቆ ዝም የምለውን ሰው።
---------------------------
ስብስብ ግጥሞች
ደራሲ - በዕውቀቱ ስዩም
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ተሰጥኦ ኖሯቸው ፣ ዜማ የደረሱ
ዜማ ቢሰረቁ ለዳኛ ከሰሱ
እኔስ በተራዬ ፣ የት ሄጄ ልክሰሰው
ዝምታዬን ሰርቆ ዝም የምለውን ሰው።
---------------------------
ስብስብ ግጥሞች
ደራሲ - በዕውቀቱ ስዩም
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
---------ላንመለስ
እንሂድ ብላኝ ተከትያት ፣
ቃል ስትሰጠኝ ቃል አምኛት ፣
ስትጎትተኝ ስጎተታት ፣
ስመናተል ሳባብላት ።
ኼዴን ኼዴን ኼዴን...
ላንመለስ መንገድ ጠፋን ።
---------------------------
"አሁንም አይደል ወደ ማታ.."
ገፅ - 100
ደራሲ - ሔኖክ ደመቀ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
እንሂድ ብላኝ ተከትያት ፣
ቃል ስትሰጠኝ ቃል አምኛት ፣
ስትጎትተኝ ስጎተታት ፣
ስመናተል ሳባብላት ።
ኼዴን ኼዴን ኼዴን...
ላንመለስ መንገድ ጠፋን ።
---------------------------
"አሁንም አይደል ወደ ማታ.."
ገፅ - 100
ደራሲ - ሔኖክ ደመቀ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
"አላስገባም ብሎ ቢያባረኝ ወዳጄ ፣
ክፉ ቀን አወጣኝ የወለድሁት ልጄ።"---------------------------
ከኅሩይ ፡ ወልደ ፡ሥላሴ።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
"እኔ እዘጋዋለሁ ቤቴን እንዳመሉ ፣
ቢጠይቋችሁም ከፍቶት ኼደ በሉ። "---------------------------
ከኅሩይ ፡ ወልደ ፡ሥላሴ።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ኦ አምላክ ይቅር በል!
--------------------------
ነቢይ መኮንን
--------------------------
FORGIVE O LORD
Forgive o Lord my little jokes on thee
And I will forgive Thy great big one on me
--------------------------
Robert frost
--------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ባንተ ለቀለድኩት ፣
ትናንሽ ቀልድ ሁሉ፣
እማጠንሃለሁ፤
አምላክ ይቅር በለኝ ፣ ይቅርታን እሻለሁ ፤
ያኔ አንተም በኔ ላይ ፣ የቀለድክብኝን
አሳር የሚያህል ቀልድ ፣
ይቅር እልሃለሁ!!--------------------------
ነቢይ መኮንን
--------------------------
FORGIVE O LORD
Forgive o Lord my little jokes on thee
And I will forgive Thy great big one on me
--------------------------
Robert frost
--------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ነው የተወለደው። በትምህርት ዓለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው ልብወለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት።
ከተደራሲው ጋር የተዋወቀበት እና በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ተከታታዮችና አንባቢዎች ልብ ውስጥ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበት “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት የታተመው በ1977 ዓ.ም. ነው። (በዚህ መድብል ውስጥ አራት ሥራዎችን አዋጥቷል “ድብድብ”፣ “ዕብዱ ሺበሺ”፣ “ሲሮኮ” እና “ሲፊንክስ”)
ሜጋ አሳታሚ ድርጅት በ1990 ዓ.ም. ባሳተመው “ጭጋግና ጠል” የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ “ዘላን” የተባለው ልብወለዱ ታትሟል።
በ1981 ዓ.ም. በኩራዝ አሳታሚ የታተመው “ማህሌት” የደራሲው የመጀመሪያ ወጥ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሐፍ ነው።
በሻማ ቡክስ በ1997 ዓ.ም. የታተመው “ግራጫ ቃጭሎች” እንደ ብሉይ (classic) ሥራ ሊታይ የሚችልና የደራሲው ልዩ ብቃት የታየበት ወጥ ረጅም ልብወለድ ነው።
በ2001 ዓ.ም. ሁለት ልዩ ሥራዎች ይዞ የቀረበው አዳም፤ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው “አለንጋና ምስር” እና እርስ በርሳቸው በቀጭን የታሪክ ክር የሚገናኙ ልቦለዶች (ኖቬላዎች) ያካተተው “እቴሜቴ ሎሚ ሽታ”ን ለአንባቢያን አበርክቷል። ይህ የአጻጻፍ ስልቱ ሕጽናዊነት የሚባል ሲሆን ደራሲው በሌሎቹ መጽሐፍቱም ውስጥ በስፋት ተጠቅሞበታል፡፡
በቀጠሉት ሦስት ዓመታት በየዓመቱ አንዳንድ መጽሐፍ ለአንባቢያን ያደረሰ ሲሆን በ2002 ዓ.ም. “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር”፣ በ2003 ዓ.ም. “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” እና በ2004 ዓ.ም. “ሕማማትና በገና” ታትመው ለንባብ በቅተዋል።
“ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” የተሰኘው መጽሐፉ በድንቅ የፋንታሲ (ፈንጠዝያ) ሥራዎች የተካተተ ነው፤ በ”ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” ለመጀመሪያ ጊዜ መቼቱን ከሀገር ውጭ በማድረግ የውጭውን ሕይወት በስሱ የዳሰሰ ሲሆን ከሌሎቹ ሥራዎቹ በተለየ መልኩ ስለሀገራችን ፖለቲካ ወጣ-ገባ መንገድ በታዛቢ ዓይን ምልከታውንና ትውስታውን አስፍሯል።
”ሕማማትና በገና” የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ ሲሆን ለየት ያለ ቅርፅ ያላቸው አንዳንድ ልብወለዶች ተካተውበታል። ፍልስፍናውና ስልቱ ሕፅናዊነት በሚል ስያሜው ይፋ ሆኗል። አዳም ረታ በተለየ የአጻጻፍ ስልቱ እና በሥራዎቹ ጥልቀት በሃያስያን ዘንድ አዎንታዊ ሂስ እና ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።
ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል፦
«አዳም ረታ ታዋቂ ደራሲያን ከሆኑት ከሀዲስ ዓለማየሁ፣ በዓሉ ግርማ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ ጸጋዬ ገብረመድኅን ጋራ መመደብ የሚችል ነው ሊባል ይችላል…»
Aklilu Dessalegn Adam Reta as a Literary Existentialist፡ Textual and Descriptive Criticism (2010)
«…ዳኛቸው ወርቁ በ“አደፍርስ” የኢፒሶዲክ ሕግጋትን አጋምሶ ለማስተዋወቅ ከሞከረ ወዲህ በአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ በኢፒሶዲክ ተሟልቶ የተገኘ ድርሰት “ግራጫ ቃጭሎች” ነው። “ግራጫ ቃጭሎች” ከገፀ-ባህሪው አካልና ሥነ-ልቡና አሳሳል አልፈን ድንቅ ዓላማውን፣ ቋንቋውንና የሕይወት አተረጓጎሙን ስንመለከት የአዳም ረታ እውቀትና ልምድ ጠንከር፣ ጠጠር ብሎ በ'መዝገቡ' በኩል ሲያስተጋባ ነው የምንመለከተው።…»
ዓለማየሁ ገላጋይ - ደራሲና ጋዜጠኛ
ኢሜጅ መጽሔት፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 02፣ ግንቦት 1998
ለሕትመት የበቁ የአዳም ረታ ሥራዎች፦
1. አባ ደፋር እና ሌሎች ታሪኮች - 1977 ዓ.ም. (ድብድብ፣ ዕብዱ ሺበሺ፣ ሲሮኮ እና ሲፊንክስ)
2. ማሕሌት - 1981 ዓ.ም.
3. ጭጋግና ጠል እና ሌሎች - 1990 ዓ.ም. (ዘላን)
4. ግራጫ ቃጭሎች - 1997 ዓ.ም.
5. አለንጋና ምስር - 2001 ዓ.ም.
6. እቴሜቴ ሎሚሽታ - 2001 ዓ.ም.
7. ከሰማይ የወረደ ፍርፍር - 2002 ዓ.ም.
8. ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ - 2003 ዓ.ም.
9. ሕማማትና በገና - 2004 ዓ.ም.
10. መረቅ - 2007 ዓ.ም.
11. የስንብት ቀለማት 2008 ዓ.ም.
12. አፍ 2010 ዓ.ም. ናቸው።
═══════
ምንጮች፦
➢ ጭጋግና ጠል ገፅ 108 አ.አ. ሜጋ አሳታሚ ድርጅት 1990 ዓ.ም.
➢ አዲስ አድማስ ጋዜጣ
━━━━━━━
👉 ዊኪፒዲያ