ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም፤የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም፤የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።

ብዙ ውጫዊ ነገሮች አስደሳች ቢሆኑም ከጊዜ ጋር የተሳሰሩና ሃላፊ ናቸው። ዛሬ ያስደሰተን ጓደኛ ነገ ላይኖር ይችላል ዛሬ ያጌጥንበት ውበት ነገ ይረግፋል፤ ዛሬ የተመካንበት አስተሳሰብ ነገ በቆመበት አይጸናም። ከውጪ የምናገኘው ማንኛውም አይነት ደስታ በመጣበት እግሩ ጥሎን መሄዱ አይቀርም። ከዛም አልፎ ዋጋ ያስከፍለናል። ከጊዜ ጋር የማይለዋወጥ ደስታን ለማግኘት ብቸኛ መፍትሄው ደስታና ሰላምን በውስጣችን መፈለግ ነው። እንደ ኩሬ ውሃ ያነሰች፤ እንደ ኩራዝ መብራት የቀጨጨች፤ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት የደቀቀችም ብትሆንም እንኳን ውስጣዊ ደስታን በልባችን መትከል ነው። ይህ ነው ማንም ሊነካውና ሊደፍረው የማይገባው ስፍራ።

በርግጠኝነት ለሰው ብለን የምንይዘው ማንነት፤ ለኛ በልክ እንዳልተሰፋ ልብስ አያምርብንም፤ ቀላሉ መፍትሄ እራሳችንን መሆን እና፤ መክሊታችንን መኖር ነው። በዚህ ስፍራ ውስጥ ሙሉ ነን፤ እውነተኛ እኛነታችን የሚታየው በዚህ ስፍራ ነው። ወደ ውስጣችን ዘልቀን በዚህ ስፍራ ላይ ቆመን ህይወታችንን ብናየው፤ እንደምናስበው ደካማ አይደለንም፤ የሚጎድለን ብዙ አይደለም፤ ከምንም በላይ በፈጠረን ፈጣሪ አይን ውስጥ ውብና ንጹህ ነን። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ? ደስታና ሰላማችን በሰው እጅ ፤ ፍርድና ቅጣታችን በሰው ወንበር ፈጽሞ አይሁን.!!



ከ ስብዕናችን

---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
አንድ የስነ-ሰብ (Anthropology) ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።

ጨዋታውም፣ በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው:-

"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል:: "

ጨዋታው ተጀመረ።

ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።

ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ::

የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው።

ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ! " በማለት መለሱለት።

በመቀጠል አንዱ ህፃን እንዲህ አለው:-

"እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም::"

"ኡቡንቱ" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪቃው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም:-

“ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!” የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ንጉሥ ሲጨንቀው

የአንዲት ደሃ ሃገር ዜጎቿ በሙሉ፣
መሄጃ ቢያሳጡት “ተራብን!” እያሉ፣
ምስኪን ንጉሣቸው እንዲህ ፀለየ አሉ፦

“እባክህ አምላኬ!
የተራበ ሕዝቤን ሲያሻህ በነጠላ፤
ካሰኘህ በጅምላ፣
ከፊቴ አርቅና ባህር ክተትልኝ፤
ከሃይቅ ጣልልኝ፡፡

ከዚያማ!
ያልቻሉት ሲሰምጡ፤
የቻሉት ለማምሻ ዓሣ ይዘው ይውጡ!"

ገጣሚ -በረከት በላይነህ

     
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
#አዮነት (ቃልኪዳን)
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
#አዮነት (ቃልኪዳን)
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
#አዮነት (ቃልኪዳን)
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
#አዮነት (ቃልኪዳን)
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የአባልነት ምዝገባ ተጀምሯል።

ለመመዝገብ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ :-

1. በ www.abrehot.org.et/register/ በመግባት የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ

2. ፎርሙን እንደጨረሱ ወደ ክፍያ ገፅ ይወስዳቹሀል ፣ አመታዊ የአባልነት ክፍያ በቴሌብር ወይም በንግድ ባንክ በኩል በቀላሉ መክፈል ይችላሉ።

3. ቅድመ ተከተሉን እንደጨረሱ አባልነቶ አፕሩቭ ይሆናል።

ቅድመ ተከተሉን ከጨረሱ ቡሀላ በ15 ቀን ውስጥ ዲጂታል የአባልነት መታወቂያ በኢሜይል ይደርሶታል።

አባል ሲሆኑ የሚከተለውን ጥቅሞች ያገኛሉ :-

1. መፃህፍትን በነፃ መዋስ።
2.ለ12 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ሙሉ ወጪ በመሸፈን።
3. የጋራ የውይይት ክፍሎችን በኦንላይን ማግኘት።.
4. ከ 1.5 ሚልየን በላይ ጆርናሎች እና የመመረቂያ ፅሁፎች በቀላሉ በኦንላይን ማግኘት።
5.በቶሞካ ትኩስ መጠጦች ላይ 35% ቅናሽ።

ብርሀን ለኢትዮጵያ 🇪🇹
Abrihon Library Official Facebook Page


---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
#Lets #see #the #world #together
ቀናችሁን ሊያበረላችሁ የሚችል ቆንጆ App ልጠቁማችሁ።

"be my eyes" ይባላል፣ አይነ ስውራን የሆኑ ሰዎችን በ live chat የምንረዳበት app ነው።
በአለም ላይ በአሁኑ ሰዓት ከ6.2 ሚሊየን በላይ በጎ አድራጊዎች አይነስውራንን ለመርዳት ይህን አፕሊኬሽን ይጠቀማሉ። ከ452 ሺህ በላይ አይነስውራን ተጠቃሚ ሆነውበታል። አማርኛን ጨምሮ የምትችሉትን ቋንቋም ያስመርጣችኋል።

ይህን አፕሊኬሽን መኖሩን የነገረችኝ አይነስውር የሆነች ጓደኛዬ ናት። በጣም ጎበዝና ብርቱ ናት።
እንደ እድል ሆኖ አሁን ከነጋ online እያለሁ አንድ አፕሊኬሽኑን የሚጠቀም አይነስውር ሰው #ከናይጀሪያ ደወለልኝና ምንድነው ፊትለፊቴ ያለው? አለኝ ካሜራው ቪድዮ በቀጥታ እያሳየኝ የሚታየውን ነገር ነገርኩት፣ #ከኢትዮጵያ እንደሆነኩም ሲያውቅ ደስ አለው።
ይበልጥ እኔን ደስስስስስስ አለኝ።

አፕሊኬሽኑን በአካባቢያችን ላሉት አይነስውራን ብንጭንላቸው ደስታው ለኛው ነው፣ በ Androind በ ios ም አለው።

#See_the_world_together
Android Download link
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bemyeyes.bemyeyes

---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
''አንድም…
መስማትህ ምን ያህል ማየትህ ምን ድረስ
እንዳዲስ ተሰርቶ ደግሞ አድሮ ለመፍረስ፤

አንድም
የኑሮ ቡቱቶ ዝተት የሚያስጎትት
ልብ አለማለት ነዉ በልብ ዉስጥ ክትት።

አንድም
ሰዉ ራሱን ማየት ሲጀምር
ዓይነ ኅሊናዉ፤ ይከፈታል ልቡናው''


© ሙልጌታ ተስፋዬ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
''ማነው ተጠያቂ''

''ነፍሴማ ባህር ነው
እልፍ ቢረመረም
ዱካሽን አያትም!

ኮቴሽም ቆሌ ቢስ
እማያባንነኝ
በንቃት በሕልሜ
ሺህ ዘመን ብታልፊ፣
በማ ሊፈረድ ነው?
ለማን አቤት ሊባል?
ጥሪሽን ስጠብቅ
ግድቤን ጣጥሰሽ
ይዘሽ ስትጠፊ!''

©ስንቅነህ እሸቱ


---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
✦ የሳምንቱ መልዕክት ✦

''በራስ መተማመኑን ያየዘ ጥበብን ፈላጊ አዲሱን ሐሳብ ከቀደመ ማንነቱ ጋር ማስታረቅ የሚችል የብሩህ አዕምሮ ባለቤት ነው።''

ባንድ ወቅት ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ስለፍልስፍና ለቀረበለት ጥያቄ ይህን ብሎ ነበር።

''ጠያቂ፦ ፍልስፍና ያሳብዳል?

ስብሐት፦ ፍልስፍና አያሳብድም። አንድ ሰው ፍልስፍና አንብቦ ካበደ ፡ መጀመሪያውኑ ለማበድ የሚያበቃ እርሾ በውስጡ ነበረ ማለት ነው።

ጠያቂ፦ ፍልስፍና ለምን በጥርጣሬ ይታያል?

ስብሐት፦ ብዙ ሰዎች ፍልስፍናን በሩቁ ይላሉ፤ ይፈራሉ። መጀመሪያውኑም የነበራቸው እምነት ጠንካራ ስላልነበረ ትንሽ ፍልስፍና እንዳነበቡ ከሥር መሠረታቸው ይናጋሉ ፤ ልባቸው በጥርጣሬ ይሞላል። ልብ አድርግ! ያናጋቸው ፍልስፍናው አይደለም፤ ቀድሞ የነበራቸው ደካማ እምነት እንጂ!"
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
Book for ALL | (Facebook)

የትንሽ ነገር ... ከሲኣት ትንሿ እህቴ ከሩቅ እየተጣራች መጣች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ”

እናታችን ለጨረሩ መከላከያ መዳፏን ግንባሯ ላይ አጋድማ “ምነው? ምን ሆንሽ?” አለች “ዱላ ስጪኝ ዱላ ስጪኝ” “ምነው? ለምንሽ?” “አለቃ ተመረጥኩ” ዱላ አሳጥራ ሰጠቻት። . . . አመሻሽ ትንሿ እህቴ እያለቀሰች “እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ” እናታችን “ምነው? ምን ሆንሽ?” “ከአለቃነት ተሻርኩ”
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ርዕስ፡ውልብታ"
ደራሲ፡አለማየሁ ገላጋይ ገጽ፡፶
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
------- ሀገር
ስውር ድብቅ ቅኔ፤
------ ፍቅር
የፈጣሪ ጽዋ ሰው የመሆን መቅኔ።
እናም በህይወት ግንድ ላይ
እናት መውለድ ያንቃት!
ሀገር ትውልድ ያንፃት!
ፍቅርን ሞት አይግዛት!
---------------------------
ገላና ገላ የግጥም መድብል
ገጣሚ - መላኩ ደምሴ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
እኔ ምልሽ ውዴ . . .

ራብ ገብቷል አሉ...
ትልሽው ትቀምሽው
እፍኝ ቆሎ ርቆሽ ጠኔ ጣለሽ እንዴ፣
አንድ አንቺን መታደግ አቅቶት ይሆን ወይ
በዜና መስፈሪያው... የሰፈሩት ዘይት... የሰፈሩት ስንዴ?

---------------------------
አንፈርስም አንታደስም
ደራሲ - አሌክስ አብርሃም
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የ'ኔ copy right

ተሰጥኦ ኖሯቸው ፣ ዜማ የደረሱ
ዜማ ቢሰረቁ ለዳኛ ከሰሱ
እኔስ በተራዬ ፣ የት ሄጄ ልክሰሰው
ዝምታዬን ሰርቆ ዝም የምለውን ሰው።
---------------------------
ስብስብ ግጥሞች
ደራሲ - በዕውቀቱ ስዩም
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
---------ላንመለስ
እንሂድ ብላኝ ተከትያት ፣
ቃል ስትሰጠኝ ቃል አምኛት ፣
ስትጎትተኝ ስጎተታት ፣
ስመናተል ሳባብላት ።

ኼዴን ኼዴን ኼዴን...
ላንመለስ መንገድ ጠፋን ።
---------------------------
"አሁንም አይደል ወደ ማታ.."
ገፅ - 100
ደራሲ - ሔኖክ ደመቀ
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
"አላስገባም ብሎ ቢያባረኝ ወዳጄ ፣
ክፉ ቀን አወጣኝ የወለድሁት ልጄ።"

---------------------------
ከኅሩይ ፡ ወልደ ፡ሥላሴ።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
"እኔ እዘጋዋለሁ ቤቴን እንዳመሉ ፣
ቢጠይቋችሁም ከፍቶት ኼደ በሉ። "

---------------------------
ከኅሩይ ፡ ወልደ ፡ሥላሴ።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ኦ አምላክ ይቅር በል!

ባንተ ለቀለድኩት ፣
ትናንሽ ቀልድ ሁሉ፣
እማጠንሃለሁ፤
አምላክ ይቅር በለኝ ፣ ይቅርታን እሻለሁ ፤
ያኔ አንተም በኔ ላይ ፣ የቀለድክብኝን
አሳር የሚያህል ቀልድ ፣
ይቅር እልሃለሁ!!

--------------------------
ነቢይ መኮንን
--------------------------
FORGIVE O LORD

Forgive o Lord my little jokes on thee
And I will forgive Thy great big one on me

--------------------------
Robert frost
--------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event