ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
(በረከት በላይነህ)

....
አብዬ ያልታደለ
'መልካም አስብ' ሲባል 'አንባቢ ነኝ' አለ
እምዬ ቀለለች
'የዉበቴ ምስጢር ቀለም ነዉ' ትላለች
:
የሃሳብህን ስብራት
በዉሸት ለማሸት
ስታወራ ዉለህ ስትቀባጥር ማምሸት
የመልክሽን ህመም
በቀለም ለማከም
መዳፍሽ እስኪዝል መስታወት ፊት መድከም
:
:
ምን ልልሽ መሰለሽ
'መልክ ስጠኝ እንጂ...' ብለሽ አተርቺ
በቀለም ይመጣል - በመቀባት በርቺ
:
ምን ልልህ መሰለህ
ተርት ተተርተረዉ - ማንንም አትፍራ
'ሙሉ ሰዉ' ዝም ይላል - አንተ ስታወራ. . . . .
:
:
ባንተና በሷ ንግስ - አማካሪ አያሻ
የእውነት ጅማሬ ነዉ - የዉሸት መጨረሻ፡፡
:
ሊመክርህ ያለዉን - ያኔ ታገኛለህ
ወይ እዉነት ጋር ስትደርስ - ወይ ሲዋሽ ታያለህ
፡፡


@Write_event
@Write_event
@Write_event
የእኔ ውብ ከተማ
(በዓሉ ግርማ)

ሕንጻ መች ሆነና ፣ የድንጋይ ክምር

የእኔ ውብ ከተማ

መንገድ መች ሆነና ፣ የድንጋይ አጥር
የእኔ ውብ ከተማ ፣ የእኔ ውብ አገር

የሰው ልጅ ልብ ነው

የሌለው ዳርቻ ፣ የሌለው ድንበር
ሕንጻው ምን ቢረዝም ፣ ምን ቢጸዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ፣ ቢንጣለል አስፋልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ፣ ምንድን ነው ውበቱ ?




@Write_event
@Write_event
@Write_event
ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም ፤ የመሰለች ልጅ!
(ነብይ መኮንን)

ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም
ከመሰለች ልጅ ፊት ለፊት
ተቀምጫለሁ፡፡ __ ቡና ቤት፡፡

መልኳ ጉራማይሌ ነው
በባለቀለም ጀምሮ በጥቁርና ነጭ የሚያልቅ
... የድሮ ፊልም የሚመስል።

ስትስቅ ፤ ቤት አትመታም ፤
ስታለቅስ ፤ ዜማ የላትም ፤
ስታዝ ፤ ቃላት አትመርጥም።

ማኪያቶ ስትፈልግ፦
«ጎምዘዝ ያለ መኪያቶ
ስኳሩ እንደ ጠዋት ህልም፣
... እየጣመ ‘ሚያልቅ» ትላለች፡፡

ወይም ደግሞ፤
«እስኪ አንድ ቢራ ስጠኝ እንደ ዕንባ የቀዘቀዘ»
ወይም «አንድ ጎርደን ደብል
ካልቀዘቀዘ በረዶና ከሎሚ ዝልዝል ጋር…
ምነው አኮረፍክ?
የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ?»

ዳሩ ቦዮቹም ያቋታል፡፡ ምንም አይናገሯትም፡፡

የጨዋታዋ ለዛ መብዛት፣ ለዛ-ቢስ ያ’ረጋታል
ስለራሷ ስታወራም… ነገር ታረዝም ታረዝምና
«ውይ እስቲ አንዴ አዳምጠኝ፤
... ዓመት አላወራ!!» ትልና
ከዛ ትዘበዝባለች ፣ ደሞ ሌላ ዓመት ጨምራ።

ከቶም ወደዚህ ቡና ቤት፣ መመላለስ ከጀመርኩ
እኔ ራሴ እንኳ በሷ ወግ፤ ዘልዛላ ርዝመት ሳቢያ
... ሁለት ሦስቴ አርጅቻለሁ፡፡

አንድ ቀን ግን ጨክኜ፦
«ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም!
ያን ከማንበብ ይሻላል! ፣ ገዳም ገብቶ መጋደም!»
አልኳትና ሂሳብ ከፍዬ፤ ራመድ ... ራመድ ስል

ያ! የማውቀው ፌዘኛ ቦይ፣ ወደኔ መጥቶ እንደግዳጅ
«ያቺ ያልተጨረሰች ቀሽም ግጥም፣
... የመሰለችው ሴት ልጅ፤
‘ ታኮዬ ይበላሻል እንጂ፣ እሄድብህ ነበር በልልኝ ! ’
... አለችኝ ጋሼ» አለኝ፡፡

እኔም ነገሩ ገርሞኝ
«ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም ነው ያልከው?
ኬት ሰማኸው?!» ብዬ ብለው

«ጋሼ፤ ከሷ! ከራሷ አፍ ነው፡፡
ራሷ! ራሷን የምትጠራው፣ እንዲሁ እያለችኮ ነው!»

«ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም፣»
... ላንተ ምን ስሜት ይሰጥሀል?» ብዬ ብለው

«ንገረኝ ካሉስ ጋሼ፤... የላይኛው መስመር በሷ
የታችኛው መስመር በርሶ
የተጻፈ ይመስለኛል።!?
አለ አይደለ ፤ የማያልቅ ዘልዛላ ግጥም
ላፍ የማይጥም … ለኑሮ እማይጠቅም።

... ግን ጋሼ አንድ ነገር ልንገርዎት
እሷስ ተጀምራ ያልተጨረሰች ቀሽም ግጥም ሆና ነው፤
ገና ያልተጀመረ፤ ስንት ቀሽም ግጥም አለ መሰሎት?»

አለኝና፤
ከአግራሞቴ ጋራ ጥሎኝ፣ ወደ ደንበኛው በረረ እኔም፤
ያልተጨረሰችውን ቀሽም ግጥም ልጅ!
... ልታልቅ አንድ - አሙስ የቀራት
እራፊ ጠቀሳ ጠቀስኳት፡፡

ከዚያም ያልተገረዘ ፈገግታ እያሳየኋት፤
እንዳላለቀ የገጠር መንገድ
… እየተንገዳገድኩ አስፋልቱ ጋ ስደርስ፣
ቡችላዬን አገኘኋት።

የዚያችን!
ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም ልጅ ነገር
ለሸውራራዋ ድንክ ውሻዬ ነገርኳት!

እሷም! «O my God!
ምነው መጀመሪያውኑ ሳትጻፍ ብትቀር!
እጸሐፊው አንጎል ውስጥ፣
አርፎ መቀመጥ ማንን ገደለ?!»
አለች፡፡!!

@Write_event
@Write_event

የገጣሚ፦ ነብይ መኮንን "ስውር ስፌት" ከተሰኘው የግጥም መድብል ላይ የተወሰደ
@Write_event
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ፦
- ወጣት በ97፣
- ወንድሜ ያዕቆብ፣
- ላውንድሪ ቦይ፣
- ማርትሬዛ፣
- ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣
- ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣
-  አንድ ሁለት ፣
- ብር ርርር፣
- ወደው አይሰርቁ፣
- ወፌ ቆመች፣
-  እንደ ቀልድ ፣
- ወቶ አደር ፣
- አባት ሀገር
- የሞግዚቷ ልጆች፣
- ይዋጣልን ፣
- ዋሻው፣
- ወሬ ነጋሪ እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ፤ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ፤ በታዋቂው እና ተወዳጁ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

በመግለጫው ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ወቅት የዓይን ባንኩ አምባሳደር እንደነበርና ህልፈት በሚያጋጥምበት ጊዜ የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃልገብቶ እንደነበር ጠቁሟል።

አርቲስቱ በገባው ቃል መሰረትም በቤተሰቦቹ እና በጓደኞቹ ቀና ትብብር ቃሉ ተፈፃሚ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) " ስሙንም ብርሃኑንም ከመቃብር በላይ ህያው አድርጎ ያለፈ መልካም አርቲስት " ሲል ጠርቶታል።

በሌላ በኩል ፤ የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)ን ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ ሲሆን ይኸው ኮሚቴ የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት እንደሚፈፀም ገልጻል።

ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቴአትር ሽኝት ይደረጋልም ተብሏል።
የወፍ መንገድ
(መዘክር ግርማ)

‹‹እንሂድ›› አለችኝ ፣ ተነስታ እንደ ዘበት
‹‹እንሂድ›› አለችኝ ፣ ወፍ ወደ ጮኸበት
‹‹እውነት?!
እንሂድ ምናሻኝ ፣ አሁኑ እንነሳ
ግን የምንደርበው ፣ ልብስ ብንይዝሳ?››
ይህችን ቃል ባወጣ
በቁጣ
‹‹ከመቼ ወዲህ ነው፣ ወፍ ልብስ የምታውቀው?
ይልቅ እሷን ምሰል፣ ልብስህን አውልቀው!››
ብላኝ ልብሷን ጥላ
ትታኝ ገሰገሰች ፣ ወፏን ተከትላ፡፡
‹‹እሽ ስንቅ እንያዝ?›› ልላት አሰብኩና
ተውኩት ሳልጀምረው
የትኛዋ ወፍ ነች፣ ስንቅ ይዛ ምትበረው?!
በቃ ተከተልኳት ፤
ጥብቅ አ’ረገችኝ ፣ ጥብቅ አደረኳት፡፡
አንደበቴ ሰላ ፣ ዝማሬ ጀመረው
ልቤ ክንፍ አወጣ ፣ መንሳፈፍ አማረው
ከመቼ ወዲህ ነው ፣ ወፍ የማትበረው?!

@write_event
@write_event
@write_event
ያፍ ዘመድ

ዝም ያለው ዘመዴ እኔ ሳጣጥር፣
ዝም ያለው ወንድሜ እኔ ሳጣጥር፣
ሞተ ቢሉት መጣ አልቅሶ ሊቀብር።
የልቤን እንዳደርስ የእግዚአብሄር ፈቃዱ፣
ሆኖ ተነስቼ እነሱ ሲያረግዱ፤
እንዲህ አልኩት ዘመድ የተባለውን፣
እንዲህ አልኩት ወንድም የተባለውን፣
"ታምሜ ነበረ ሳጣጥር ማዘን፤
አሁን ክንዴ ክንዴ ቀኝ እጄ ቢሉኝ፣
አሁን የናቴ ልጅ ወንድሜ ቢሉኝ፣
ከሞትኩኝ በኋላ ምንም አይገባኝ፣
ይልቅ ልተኛበት አታደንቁረኝ።"
ይህን ተናግሬ የልቤን አድርሼ፣
ወደመጣሁበት ሄድኩኝ ተመልሼ።

መንግሥቱ ለማ (ደማሙ ብዕረኛ)
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ተወኝ
(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

ላታስታምም አትመመኝ
ላትወስደኝ አታንጠልጥለኝ
ይቅር፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ጋሽዬ፥ አልወድሽም በለኝ።
እጅ እጅ አልበል አታባክነኝ
ባክህ፥ ወንድ ነው ቆራጡ፥ እንትፍ-እርገህ ተወኝ።
አየህ፥ እንዳንተ አባት አለኝ
ሴት በወለድኩ ተዋረድኩ፥ ረከስኩ ቀለልኩ እሚለኝ፥
እኔም እንዳንተ እህት አለኝ
ሥጋሽን ሳይሆን ልብሽን፥ ከፍተሽ ጥለሽ ነው እምትለኝ
እና ተወኝ፥ ባክህ ተወኝ፤
እንዳንተ እኔም አለኝ እናት
የሴት ቁንጮ እምመስላት
ጐረቤት ፊት እምታፍር፥ እንዲህ ሆነችልሽ ሲሏት!
እና፥ አልሆንሽም በለኝ
ባክህ አንጀቴን ቁረጠኝ
ፍቅር እንደሁ የኔ ይበቃል፥ ላንተም ለኔም እኔው ልውደድ
ከዘመድ ግንባር ደብቄ፥ እኔ ለብቻዬ ልንደድ፥
ብቻ፥ ከወጥመድህ ለየኝ
አልችልህም፥ ንቀህ ማረኝ
ካንተም ከስሜም ከቤቴም፥ ያጣሁ ብኩን አታድርገኝ፥
ባክህ፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ተወኝ፥ ተወኝ፥ ተወኝ።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የመጀመሪያ ቀን

አየችው ተያዩ
አየና ወደዳት
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ
ሁለት እራት መጣ
ብርጭቆው ተጋጨ
አየችው ተያዩ
አያት ተሳሳቁ
በጠረጴዛው ስር
ጭኗ ጭኑን ነካው
አየችው ፈገገ
እጇን በእጁ ያዘው
ጠበቅ አደረጋት
ጠበቅ አረገችው
ከፈሉና ወጡ
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ነደዱ
ታፋቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ፡፡

(ገብረክርስቶስ ደስታ)

---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የ ገ ዢ ኪ ሳ ራ


ይህ ሰፊ ገበያ!
በመንፈስ ተሞልቶ በፍቅር ሲጣራ!
ሸማች የሚጋፋው ቅራቅንቦ ተራ።

“ያ ስንት ነው?” ይላል፣
“ይሄኛውስ?” ይላል፤
የብልጭልጭ አይነት ያነሳል ይጥላል።

ከመንፈስ ገበያ
የውበት ጥሬ እቃ ሞልቶ ተትረፍርፏል፤
ሸማች ግን ልብ የለው
ለኮልኮሌ ፍቅር ማልዶ ተስልፏል።

“ወዴት ነህ?" አይባል -
“ወዴትም! ነው መልሱ!
“ምን በላህ?" ይሉታል -
“ምንም! ልትል ነፍሱ።

እንዲያውም ካሰኘው!
ምን እንደሚፈልግ ፈፅሞ ይዘነጋና፤
“ፀሐይ ስጡኝ!” ብሎ ብቅ ይበል ማምሻውን!
ሰልፈኛ ነውና 'ከጨረቃ ቆርሶ' ይወስዳል ድርሻውን።

የሸማች ሕሊናን መምስል ከሸፈነው፤
ገበያ መታየት ከመግዛት እኩል ነው።

የጠየቀም ገዝቶ፣ የከፈለም ገዝቶ፣
የተላከም ገዝቶ፣ የላክም ሽምቶ፤
እዚያው ይሞታታል!
ያልሞላ ቅርጫቱን ለአምሳዮቹ ትቶ።

ይኸው መጨረሻው !
ሽማቹ ለገላው እየተጨነቀ፣
ገዢው ለብልጭልጭ እየተደነቀ፤
የመንፈስ ከፍታ ተሽርሽሮ አለቀ።



(በረከት በላይነህ - የመንፈስ ከፍታ)


---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
አንድ ሰው

እሁድ ማለዳ ላይ...
ገላዋን ታጠበች
ልብሶቿን ለበሰች
ሽቶ ተርከፍክፋ ከጎዳና ወጣች

በመንገድ ስትጓዝ...

የፀጉሯን መዘናፈል የጡቷን መኮፈስ
የረጨችው ሽቶ ካደባባይ ሲነፍስ
እሷን ያየ ሁሉ ወንዱ ተጨነቀ
በደም በውበቷ እየተደነቀ
ያስተዋላት ሁሉ ዓይኑ መንገድ ሳተ
ከዳሌ ከጡቷ ሔደ ተከተተ።

ከቦታው ስትደርስ...

ወዳጇ አልመጣም
ሰአት አልጠበቀም
ለውበቷ አልሳሳም።
ሠዓት ገላመጠች
ፊት ኋላዋን ቃኘች
ማኪያቶ ደገመች
ዙርያዋ ባለው ሰው እጅግ ተናደደች
እልህ ልቧን ሞላ
ፊቷ ከደም ቀላ
የሚመኛት ሁሉም
ወንዶቹ በሞላ
የርሷ ልቧ ሌላ።

ሠዓቱ ረፈደ...

የጠዋት ደስታዋ ከሷ ተሰደደ
አይኖቿ ረጠቡ
አንድ ሰው አሰቡ
አንድ ሰው ተራቡ።

አንድ ሰው ነበረ እርሷን የናፈቀው
ያን ያልመጣውን ሰው
ዓይኗ የተራበው

(ኤፍሬም ስዩም)


---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
በስብሐት ገብረእግዚያብሄር

ምንም ብታደርጉ ሰዎች ከማውራት ስለማይመለሱ ዝም
:
☞ ደሀ ብትሆን የመናጢ ልጅ ፤ ሀብታም ብትሆን ዶላር ያሳበጠው ይሉሀል።
☞ ከሴት ጋር ብትሄድ ሴሰኛ ፤ ብቻህን ብትሆን ወፈፌ ይሉሀል ።
☞ ብትፈጥን ቀዥቃዣ ፥ ብትዘገይ ዘገምተኛ ።
☞ ብታወራ ለፍላፊ ፥ ዝምብትል ዝጋታም ።
☞ ብትራመድ አርፎ አይቀመጥም ፥ አርፈህ ብትቀመጥ ዝፍዝፍ
☞ ብትማር አወቅሁ ባይ ፥ ባትማር የአቡጊዳ ሽፍታ ።
☞ ብትወፍር ጠብደል ፥ ብትከሳ በልቶ ማይጠረቃ ።
☞ ብትይዝ ቋጣሪ ፥ ብትለቅ መንዛሪ ። ...
እንደውም አንድ የሀገራችን ተረት አለ"ባልና ሚስት አህያ እየነዱ ሲሄዱ ተቺዎች አገኙዋቸውና ፦"እንከፎች አህያዋ ሳለች እንዴት አይሳፈሩባትም" ሲሉ ባል ሰማና ሚስቱን " በይ ፍጠኚና አህያዋ ላይ ተሳፈሪ" - አላት።
ትንሽ እንደሄዱ ሌሎች ተቺዎች ፦ "ይች ባለጌ ፥ ባል በእግር እየሄደ ሚስት በጋማ ከብት" ብለው ወረፏቸው።ባል ሚስቱን አስወርዶ አህያዋ ወገብ ላይ ቂብ አለ ፤ትንሽ እንደተጋዙ ሌሎች ተቺዎች አገኝዋቸው ፦ "የተረገመ ሚስቱን በእግር እያስኬደ እሱ በአህያዋ ብለው ወረዱባቸው ።
ባልና ሚስት ድንገት ቢተዉን ብለው አህያዋ ላይ ሲፈናጠጡ ሌሎች ተቺዎች ደም አገኙዋቸውና "ምን እንስሳ ብትሆን ለሁለት ይከመሩባታል ግፈኞች ..." የስድብ ናዳ ለቀቁባቸው ።
እንግዲህ ወዳጆቼ ፦ አህያዋን ቢሸከሙ ኖሮ ከዚህ አይብስምን ?
ስለዚህ ሰዎች ያሉትን ይበሉ አንተ አንተነትህን ሁንና ህሊናህ አውጥቶና አውርዶ ከተቀበለው ሀሳብ ጋር ተስማማ።
:
ለጮኸ ውሻ ሁላ ድንጋይ መወርወር ጊዜን ማባከን ነው፡፡
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም፤የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም፤የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።

ብዙ ውጫዊ ነገሮች አስደሳች ቢሆኑም ከጊዜ ጋር የተሳሰሩና ሃላፊ ናቸው። ዛሬ ያስደሰተን ጓደኛ ነገ ላይኖር ይችላል ዛሬ ያጌጥንበት ውበት ነገ ይረግፋል፤ ዛሬ የተመካንበት አስተሳሰብ ነገ በቆመበት አይጸናም። ከውጪ የምናገኘው ማንኛውም አይነት ደስታ በመጣበት እግሩ ጥሎን መሄዱ አይቀርም። ከዛም አልፎ ዋጋ ያስከፍለናል። ከጊዜ ጋር የማይለዋወጥ ደስታን ለማግኘት ብቸኛ መፍትሄው ደስታና ሰላምን በውስጣችን መፈለግ ነው። እንደ ኩሬ ውሃ ያነሰች፤ እንደ ኩራዝ መብራት የቀጨጨች፤ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት የደቀቀችም ብትሆንም እንኳን ውስጣዊ ደስታን በልባችን መትከል ነው። ይህ ነው ማንም ሊነካውና ሊደፍረው የማይገባው ስፍራ።

በርግጠኝነት ለሰው ብለን የምንይዘው ማንነት፤ ለኛ በልክ እንዳልተሰፋ ልብስ አያምርብንም፤ ቀላሉ መፍትሄ እራሳችንን መሆን እና፤ መክሊታችንን መኖር ነው። በዚህ ስፍራ ውስጥ ሙሉ ነን፤ እውነተኛ እኛነታችን የሚታየው በዚህ ስፍራ ነው። ወደ ውስጣችን ዘልቀን በዚህ ስፍራ ላይ ቆመን ህይወታችንን ብናየው፤ እንደምናስበው ደካማ አይደለንም፤ የሚጎድለን ብዙ አይደለም፤ ከምንም በላይ በፈጠረን ፈጣሪ አይን ውስጥ ውብና ንጹህ ነን። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ? ደስታና ሰላማችን በሰው እጅ ፤ ፍርድና ቅጣታችን በሰው ወንበር ፈጽሞ አይሁን.!!



ከ ስብዕናችን

---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
አንድ የስነ-ሰብ (Anthropology) ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።

ጨዋታውም፣ በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው:-

"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል:: "

ጨዋታው ተጀመረ።

ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።

ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ::

የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው።

ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ! " በማለት መለሱለት።

በመቀጠል አንዱ ህፃን እንዲህ አለው:-

"እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም::"

"ኡቡንቱ" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪቃው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም:-

“ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!” የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ንጉሥ ሲጨንቀው

የአንዲት ደሃ ሃገር ዜጎቿ በሙሉ፣
መሄጃ ቢያሳጡት “ተራብን!” እያሉ፣
ምስኪን ንጉሣቸው እንዲህ ፀለየ አሉ፦

“እባክህ አምላኬ!
የተራበ ሕዝቤን ሲያሻህ በነጠላ፤
ካሰኘህ በጅምላ፣
ከፊቴ አርቅና ባህር ክተትልኝ፤
ከሃይቅ ጣልልኝ፡፡

ከዚያማ!
ያልቻሉት ሲሰምጡ፤
የቻሉት ለማምሻ ዓሣ ይዘው ይውጡ!"

ገጣሚ -በረከት በላይነህ

     
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
#አዮነት (ቃልኪዳን)
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event