ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
"ላይለ ኩሉ"
--------------
አደይ አዳዬ እማ ደብተራ ኦሪቷ
ሀዘን ገብቷት ዛሬ ላልቶ መቀነቷ

አስኬማውን ደፍቶ መንጋውን ካልመራ
መምሬ አያስብልም ጥምጣምና ጭራ

ፍሙ ቢንቀለቀል ምን ቢያነደው ንዳድ
ምነው አልሰማ አለ ለገመ ያ ምጣድ

ጋሞ ጪማ አዋቲ ተው ባይ ቢገኝባት
ፍቅር በረታው ልብ ሳር አብርዷል እሳት

--------------
ዳን_አድማሱ
Dan_admasu

--------------
JOIN & SHARE

@Write_event
@Write_event
@Write_event
--------------
" ......ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ...በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ ?......በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ?......እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ?.....ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?.......በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም ። ...." ገፅ ( 38 / 39 )

".....ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት ....በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት ..... መሪው ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት ..... አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት ..... ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት .....

ገፅታዎች ( 153 )
የጠቢባን መንገድ


@Write_event
@Write_event
@Write_event
💡ሕይወት በ’የኔ’ እና ‘የኛ’ የምናሳንሰው ነገር የላትም… ከጽንፍ አልባው ምልዓት ላይ በተገለጸልን ልክ የገባንን ሁሉ የእኔ/ኛ አንልም… እኛ ራሳችንን ያንን ምልዓት አይደለን? “You are not a drop in the ocean; you are the entire ocean in a drop” ይላል Rumi

❤️ ይህን ሁለንተና በግላዊነት መያዝ አይቻልም… የኔ ብሎ ማሳነስ አይቻልም… እኛው ራሳችን ሁለንተናውን ነንና ፣ ብዙ የአለማችን እሳቤዎች ከሕይወት በተናጥሎ የመኖርን ቅዠት ይሰብካሉ… ውቅያኖሱን ሆነህ ሳለ የውቅያኖሱን ‘አንድ ጠብታ ወስደህ’ የኔ ማለት ከራስም ያሳንሳል…ከራስህ ተነጥለህ ‘የራስህ’ ሊኖርህ አይችልም።

💡የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን ፣ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳል ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው… ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው ምክንያቱም We are all One!

💎በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል
“የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!”

ደምስ ሰይፉ

           ውብ አሁን!!❤️


@Write_event
@Write_event
@Write_event
የሰማያት ቁጣ!
(መዘክር ግርማ)

መብረቅ ብርሃን ጅራፍህ
ሰማይ ላይ ሲጦፍ ሲኖጋ
ያጮኽከው ሥውር እጅ ሆይ!
ያረ'ከው አፍታ እንዲነጋ
የት እንደወደቀ ባላ'ቅም
ለማን እንደሆን ይህ ቁጣ
ቤቴን ደርምሶ ባይገባም
ከሁሉ እኔን ነው የቀጣ!

ዐይኖቿን ጨፍና – ውበቷን ግን ገልጣ
እንደ መልአክ አምናኝ፣ ጎኔ ተሸጉጣ
ተኝታ የነበር ተነሳች ደንግጣ፡፡



@Write_event
@Write_event
@Write_event
አንድዬና አንድ ቀን
(አሌክስ አብርሃም)


አንድ ቀን ያልፋል እያለ
አንድ ነፍስ ስንት አመት ይልፋ፣
አንድ ቀን አይመጣ መስሎት
አንድስ ክንድ ስንት ጉድ ይግፋ...
አንድዬስ ለአንድ ምፅአት
ምነዉ ገደልከን በተስፋ ?
:
''አንድ አይነድ ፍርድም ባንድ አያምር''
ሰዉኛ ብሂል ተርተዉ
ባንድ ክንድ እየደቆሱ፣
ባንድ እሳት አገር ሲያምሱ...
አንድ ሰዉ ይጠይቀዉ ዘንድ
ያንድዬ ምን ይሆን መልሱ?
:
ኮሳሶች ደስ ይበላችሁ
ካንድ ብርቱ ልትበረቱ፣
ሁለት ኮሳሳ ይሻላል
ብሎ ብያፀናን ተረቱ፣
ሁለት ኮሳሶች በርትተዉ
ስለ አንድነት ቢዘምቱ፣
አንዱ አንዱን እያደባየ
መልሶ ያዉ አንድ ብርቱ!
:
ምንድነዉ አንድ አንቆ መጮህ
አንድዬ አንድ በለና፣
አንድ ወንዝ ስንቴ እንሻገር
ጠብ ለማይል መና...
:
ሕዝብህ ሁለት ባላ ተክሎ፣
አንዱ ሲቀል በአንዱ
ተፍገምግሞ ተንጠልጥሎ...
''አንድዬ አንተ ታዉቃለህ''
እያለህ ሲኖር በዘዴ፣
ላንዳንዶች እንደምንለዉ
''ት'ግስትህ አልበዛም እንዴ''
:
አንድ ለናቱ ለመባል የእናቱን ልጆች ጨርሶ፣
አንድ አይፈርድ ተረት ቢያሰማን
የአንድ ዓይን እንባ አልቅሶ...
እኛም አንድ ጸሎት አለን
አንድዬ አንዴ ስማና...
:
አንድነት እየሰበኩን-አንድነት የሚቀፋቸዉ ፣
አንድዬ አንድ አርገንና...አንድ ቀን አንድ በላቸዉ !!
:
(አንፈርስም አንታደስም ገፅ ፩፻፸፱)


@Write_event
@Write_event
@Write_event
አራት ዓይነት እብደት...
ኤፍሬም ሥዩም ( ኑ ግድግዳ እናፍርስ!)



ብቸኝነት ብርዱ ገላህን ቀዝቅዞ
ከሰው መሀል አንተን ለብቻህ ሰቅዞ
መጠየቅ ስትጀምር ...
ለምን!...እንዴት?...ስትል?
ጥያቄህ በራሱ እብደት ነው የሚባል
ኡፍፍፍ...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!


መጠየቅ ሰልችቶህ ከሕዝቦች ስትርቅ
በራስህ ዓለም ላይ ህሊናህ ሲራቀቅ
አፍህ ዝም ባለ
እብድ መባል አለ።
ኤጭ!...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!


የሕዝብ ሁሉ ሀሳብ የእብደት ሲመስልህ
ያንተ አሳብ የእውነት....
እውነት እንደሆነ ውስጥህን ሲሰማህ
እብዱ ትባላለህ።
ኤዲያ!...
አውቆ የሚተኛ ሕዝብ መሀል ነቅተን፣
አቦ ተሰቃየን!


ዓለሙም እብድ ነው!
ግና ያለም እብደት ካንተ የሚለየው
አንተ የምታብደው ለዓለም ስትል ነው
ዓለሙ ያበደው አንተን ሊያሳብድ ነው።
ወገን ተሰቃየን!
አውቆ በተኛ አቋመ ቢስ መሐል...
ለብቻችን ነቅተን
አወይ ተሰቃየን!!
.....



@Write_event
@Write_event
@Write_event
(በረከት በላይነህ)

....
አብዬ ያልታደለ
'መልካም አስብ' ሲባል 'አንባቢ ነኝ' አለ
እምዬ ቀለለች
'የዉበቴ ምስጢር ቀለም ነዉ' ትላለች
:
የሃሳብህን ስብራት
በዉሸት ለማሸት
ስታወራ ዉለህ ስትቀባጥር ማምሸት
የመልክሽን ህመም
በቀለም ለማከም
መዳፍሽ እስኪዝል መስታወት ፊት መድከም
:
:
ምን ልልሽ መሰለሽ
'መልክ ስጠኝ እንጂ...' ብለሽ አተርቺ
በቀለም ይመጣል - በመቀባት በርቺ
:
ምን ልልህ መሰለህ
ተርት ተተርተረዉ - ማንንም አትፍራ
'ሙሉ ሰዉ' ዝም ይላል - አንተ ስታወራ. . . . .
:
:
ባንተና በሷ ንግስ - አማካሪ አያሻ
የእውነት ጅማሬ ነዉ - የዉሸት መጨረሻ፡፡
:
ሊመክርህ ያለዉን - ያኔ ታገኛለህ
ወይ እዉነት ጋር ስትደርስ - ወይ ሲዋሽ ታያለህ
፡፡


@Write_event
@Write_event
@Write_event
የእኔ ውብ ከተማ
(በዓሉ ግርማ)

ሕንጻ መች ሆነና ፣ የድንጋይ ክምር

የእኔ ውብ ከተማ

መንገድ መች ሆነና ፣ የድንጋይ አጥር
የእኔ ውብ ከተማ ፣ የእኔ ውብ አገር

የሰው ልጅ ልብ ነው

የሌለው ዳርቻ ፣ የሌለው ድንበር
ሕንጻው ምን ቢረዝም ፣ ምን ቢጸዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ፣ ቢንጣለል አስፋልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ፣ ምንድን ነው ውበቱ ?




@Write_event
@Write_event
@Write_event
ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም ፤ የመሰለች ልጅ!
(ነብይ መኮንን)

ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም
ከመሰለች ልጅ ፊት ለፊት
ተቀምጫለሁ፡፡ __ ቡና ቤት፡፡

መልኳ ጉራማይሌ ነው
በባለቀለም ጀምሮ በጥቁርና ነጭ የሚያልቅ
... የድሮ ፊልም የሚመስል።

ስትስቅ ፤ ቤት አትመታም ፤
ስታለቅስ ፤ ዜማ የላትም ፤
ስታዝ ፤ ቃላት አትመርጥም።

ማኪያቶ ስትፈልግ፦
«ጎምዘዝ ያለ መኪያቶ
ስኳሩ እንደ ጠዋት ህልም፣
... እየጣመ ‘ሚያልቅ» ትላለች፡፡

ወይም ደግሞ፤
«እስኪ አንድ ቢራ ስጠኝ እንደ ዕንባ የቀዘቀዘ»
ወይም «አንድ ጎርደን ደብል
ካልቀዘቀዘ በረዶና ከሎሚ ዝልዝል ጋር…
ምነው አኮረፍክ?
የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ?»

ዳሩ ቦዮቹም ያቋታል፡፡ ምንም አይናገሯትም፡፡

የጨዋታዋ ለዛ መብዛት፣ ለዛ-ቢስ ያ’ረጋታል
ስለራሷ ስታወራም… ነገር ታረዝም ታረዝምና
«ውይ እስቲ አንዴ አዳምጠኝ፤
... ዓመት አላወራ!!» ትልና
ከዛ ትዘበዝባለች ፣ ደሞ ሌላ ዓመት ጨምራ።

ከቶም ወደዚህ ቡና ቤት፣ መመላለስ ከጀመርኩ
እኔ ራሴ እንኳ በሷ ወግ፤ ዘልዛላ ርዝመት ሳቢያ
... ሁለት ሦስቴ አርጅቻለሁ፡፡

አንድ ቀን ግን ጨክኜ፦
«ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም!
ያን ከማንበብ ይሻላል! ፣ ገዳም ገብቶ መጋደም!»
አልኳትና ሂሳብ ከፍዬ፤ ራመድ ... ራመድ ስል

ያ! የማውቀው ፌዘኛ ቦይ፣ ወደኔ መጥቶ እንደግዳጅ
«ያቺ ያልተጨረሰች ቀሽም ግጥም፣
... የመሰለችው ሴት ልጅ፤
‘ ታኮዬ ይበላሻል እንጂ፣ እሄድብህ ነበር በልልኝ ! ’
... አለችኝ ጋሼ» አለኝ፡፡

እኔም ነገሩ ገርሞኝ
«ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም ነው ያልከው?
ኬት ሰማኸው?!» ብዬ ብለው

«ጋሼ፤ ከሷ! ከራሷ አፍ ነው፡፡
ራሷ! ራሷን የምትጠራው፣ እንዲሁ እያለችኮ ነው!»

«ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም፣»
... ላንተ ምን ስሜት ይሰጥሀል?» ብዬ ብለው

«ንገረኝ ካሉስ ጋሼ፤... የላይኛው መስመር በሷ
የታችኛው መስመር በርሶ
የተጻፈ ይመስለኛል።!?
አለ አይደለ ፤ የማያልቅ ዘልዛላ ግጥም
ላፍ የማይጥም … ለኑሮ እማይጠቅም።

... ግን ጋሼ አንድ ነገር ልንገርዎት
እሷስ ተጀምራ ያልተጨረሰች ቀሽም ግጥም ሆና ነው፤
ገና ያልተጀመረ፤ ስንት ቀሽም ግጥም አለ መሰሎት?»

አለኝና፤
ከአግራሞቴ ጋራ ጥሎኝ፣ ወደ ደንበኛው በረረ እኔም፤
ያልተጨረሰችውን ቀሽም ግጥም ልጅ!
... ልታልቅ አንድ - አሙስ የቀራት
እራፊ ጠቀሳ ጠቀስኳት፡፡

ከዚያም ያልተገረዘ ፈገግታ እያሳየኋት፤
እንዳላለቀ የገጠር መንገድ
… እየተንገዳገድኩ አስፋልቱ ጋ ስደርስ፣
ቡችላዬን አገኘኋት።

የዚያችን!
ያልተጨረሰ ቀሽም ግጥም ልጅ ነገር
ለሸውራራዋ ድንክ ውሻዬ ነገርኳት!

እሷም! «O my God!
ምነው መጀመሪያውኑ ሳትጻፍ ብትቀር!
እጸሐፊው አንጎል ውስጥ፣
አርፎ መቀመጥ ማንን ገደለ?!»
አለች፡፡!!

@Write_event
@Write_event

የገጣሚ፦ ነብይ መኮንን "ስውር ስፌት" ከተሰኘው የግጥም መድብል ላይ የተወሰደ
@Write_event
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ፦
- ወጣት በ97፣
- ወንድሜ ያዕቆብ፣
- ላውንድሪ ቦይ፣
- ማርትሬዛ፣
- ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣
- ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣
-  አንድ ሁለት ፣
- ብር ርርር፣
- ወደው አይሰርቁ፣
- ወፌ ቆመች፣
-  እንደ ቀልድ ፣
- ወቶ አደር ፣
- አባት ሀገር
- የሞግዚቷ ልጆች፣
- ይዋጣልን ፣
- ዋሻው፣
- ወሬ ነጋሪ እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ፤ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ፤ በታዋቂው እና ተወዳጁ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

በመግለጫው ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ወቅት የዓይን ባንኩ አምባሳደር እንደነበርና ህልፈት በሚያጋጥምበት ጊዜ የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃልገብቶ እንደነበር ጠቁሟል።

አርቲስቱ በገባው ቃል መሰረትም በቤተሰቦቹ እና በጓደኞቹ ቀና ትብብር ቃሉ ተፈፃሚ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) " ስሙንም ብርሃኑንም ከመቃብር በላይ ህያው አድርጎ ያለፈ መልካም አርቲስት " ሲል ጠርቶታል።

በሌላ በኩል ፤ የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)ን ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ ሲሆን ይኸው ኮሚቴ የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት እንደሚፈፀም ገልጻል።

ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቴአትር ሽኝት ይደረጋልም ተብሏል።
የወፍ መንገድ
(መዘክር ግርማ)

‹‹እንሂድ›› አለችኝ ፣ ተነስታ እንደ ዘበት
‹‹እንሂድ›› አለችኝ ፣ ወፍ ወደ ጮኸበት
‹‹እውነት?!
እንሂድ ምናሻኝ ፣ አሁኑ እንነሳ
ግን የምንደርበው ፣ ልብስ ብንይዝሳ?››
ይህችን ቃል ባወጣ
በቁጣ
‹‹ከመቼ ወዲህ ነው፣ ወፍ ልብስ የምታውቀው?
ይልቅ እሷን ምሰል፣ ልብስህን አውልቀው!››
ብላኝ ልብሷን ጥላ
ትታኝ ገሰገሰች ፣ ወፏን ተከትላ፡፡
‹‹እሽ ስንቅ እንያዝ?›› ልላት አሰብኩና
ተውኩት ሳልጀምረው
የትኛዋ ወፍ ነች፣ ስንቅ ይዛ ምትበረው?!
በቃ ተከተልኳት ፤
ጥብቅ አ’ረገችኝ ፣ ጥብቅ አደረኳት፡፡
አንደበቴ ሰላ ፣ ዝማሬ ጀመረው
ልቤ ክንፍ አወጣ ፣ መንሳፈፍ አማረው
ከመቼ ወዲህ ነው ፣ ወፍ የማትበረው?!

@write_event
@write_event
@write_event
ያፍ ዘመድ

ዝም ያለው ዘመዴ እኔ ሳጣጥር፣
ዝም ያለው ወንድሜ እኔ ሳጣጥር፣
ሞተ ቢሉት መጣ አልቅሶ ሊቀብር።
የልቤን እንዳደርስ የእግዚአብሄር ፈቃዱ፣
ሆኖ ተነስቼ እነሱ ሲያረግዱ፤
እንዲህ አልኩት ዘመድ የተባለውን፣
እንዲህ አልኩት ወንድም የተባለውን፣
"ታምሜ ነበረ ሳጣጥር ማዘን፤
አሁን ክንዴ ክንዴ ቀኝ እጄ ቢሉኝ፣
አሁን የናቴ ልጅ ወንድሜ ቢሉኝ፣
ከሞትኩኝ በኋላ ምንም አይገባኝ፣
ይልቅ ልተኛበት አታደንቁረኝ።"
ይህን ተናግሬ የልቤን አድርሼ፣
ወደመጣሁበት ሄድኩኝ ተመልሼ።

መንግሥቱ ለማ (ደማሙ ብዕረኛ)
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
ተወኝ
(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

ላታስታምም አትመመኝ
ላትወስደኝ አታንጠልጥለኝ
ይቅር፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ጋሽዬ፥ አልወድሽም በለኝ።
እጅ እጅ አልበል አታባክነኝ
ባክህ፥ ወንድ ነው ቆራጡ፥ እንትፍ-እርገህ ተወኝ።
አየህ፥ እንዳንተ አባት አለኝ
ሴት በወለድኩ ተዋረድኩ፥ ረከስኩ ቀለልኩ እሚለኝ፥
እኔም እንዳንተ እህት አለኝ
ሥጋሽን ሳይሆን ልብሽን፥ ከፍተሽ ጥለሽ ነው እምትለኝ
እና ተወኝ፥ ባክህ ተወኝ፤
እንዳንተ እኔም አለኝ እናት
የሴት ቁንጮ እምመስላት
ጐረቤት ፊት እምታፍር፥ እንዲህ ሆነችልሽ ሲሏት!
እና፥ አልሆንሽም በለኝ
ባክህ አንጀቴን ቁረጠኝ
ፍቅር እንደሁ የኔ ይበቃል፥ ላንተም ለኔም እኔው ልውደድ
ከዘመድ ግንባር ደብቄ፥ እኔ ለብቻዬ ልንደድ፥
ብቻ፥ ከወጥመድህ ለየኝ
አልችልህም፥ ንቀህ ማረኝ
ካንተም ከስሜም ከቤቴም፥ ያጣሁ ብኩን አታድርገኝ፥
ባክህ፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ተወኝ፥ ተወኝ፥ ተወኝ።
---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የመጀመሪያ ቀን

አየችው ተያዩ
አየና ወደዳት
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ
ሁለት እራት መጣ
ብርጭቆው ተጋጨ
አየችው ተያዩ
አያት ተሳሳቁ
በጠረጴዛው ስር
ጭኗ ጭኑን ነካው
አየችው ፈገገ
እጇን በእጁ ያዘው
ጠበቅ አደረጋት
ጠበቅ አረገችው
ከፈሉና ወጡ
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ነደዱ
ታፋቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ፡፡

(ገብረክርስቶስ ደስታ)

---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event
የ ገ ዢ ኪ ሳ ራ


ይህ ሰፊ ገበያ!
በመንፈስ ተሞልቶ በፍቅር ሲጣራ!
ሸማች የሚጋፋው ቅራቅንቦ ተራ።

“ያ ስንት ነው?” ይላል፣
“ይሄኛውስ?” ይላል፤
የብልጭልጭ አይነት ያነሳል ይጥላል።

ከመንፈስ ገበያ
የውበት ጥሬ እቃ ሞልቶ ተትረፍርፏል፤
ሸማች ግን ልብ የለው
ለኮልኮሌ ፍቅር ማልዶ ተስልፏል።

“ወዴት ነህ?" አይባል -
“ወዴትም! ነው መልሱ!
“ምን በላህ?" ይሉታል -
“ምንም! ልትል ነፍሱ።

እንዲያውም ካሰኘው!
ምን እንደሚፈልግ ፈፅሞ ይዘነጋና፤
“ፀሐይ ስጡኝ!” ብሎ ብቅ ይበል ማምሻውን!
ሰልፈኛ ነውና 'ከጨረቃ ቆርሶ' ይወስዳል ድርሻውን።

የሸማች ሕሊናን መምስል ከሸፈነው፤
ገበያ መታየት ከመግዛት እኩል ነው።

የጠየቀም ገዝቶ፣ የከፈለም ገዝቶ፣
የተላከም ገዝቶ፣ የላክም ሽምቶ፤
እዚያው ይሞታታል!
ያልሞላ ቅርጫቱን ለአምሳዮቹ ትቶ።

ይኸው መጨረሻው !
ሽማቹ ለገላው እየተጨነቀ፣
ገዢው ለብልጭልጭ እየተደነቀ፤
የመንፈስ ከፍታ ተሽርሽሮ አለቀ።



(በረከት በላይነህ - የመንፈስ ከፍታ)


---------------------------
Share & join
@write_event
@write_event
@write_event