ቃላዊ
342 subscribers
39 photos
5 videos
1 file
122 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ከል ሰው መሆንን የተገነዘቡት።

በሉ ከእናንተ ጋር እያወራሁ የምሳ ሰዓትን እየረሳሁ ነው ።
አታረሳሱኝማ የምሳ ሰዓት ነው ። እትዬ ስምተው ይሁን?! እትዬ የምሳ ሰዓት ነው።]
ሰ ባ ት ( ፯ )
┈┈•✦•┈┈
ሰባት ቁጥር በርካታ ሃይማኖታዊ፣ ሳይንሳዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ ... ግጥጥሞሾች ያሉት ምስጢራዊ ቁጥር እንደሆነ ይታመንበታል። እስቲ ለዛሬ ጥቂቱን እንመልከት፦

☆ ሰባቱ ሰማያት፦
1. ኤረር 2. ራማ
3. ኢዮር 4. ሰማይ ውዱድ
5. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
6. መንበረ መንግሥት
7. ጽርሐ አርያም

☆ ሰባቱ ቀለማት፦
1. ጥቁር 2. ብጫ
3. አረንጓዴ 4. ሰማያዊ
5. ነድ 6. ወርቅ
7. ቀይ

☆ ሰባቱ የሰው ባህርያት፦
1. እሳት 2. መሬት
3. ውሃ 4. ነፋስ 5. ነባቢነት
6. ለባዊነት 7. ሕያውነት

☆ ሰባቱ ዕለታት፦
1. እሁድ 2. ሰኞ
3.ማክሰኞ 4. ረቡዕ
5. ሐሙስ 6. አርብ
7. ቅዳሜ

☆ ሰባቱ ክፍለ ዓለማት፦
1. አፍሪቃ 2. አውሮጳ
3. ሰሜን አሜሪካ
4. ደቡብ አሜሪካ
5. እስያ 6. አውስትራሊያ
7. አንታርክቲካ

☆ ሰባቱ የቀስተ ደመና ቀለማት፦
1. ቀይ 2. ብርቱካናማ
3. ብጫ 4. አረንጓዴ
5. ሰማያዊ 6. ጥቁር ሰማያዊ
7.ሐምራዊ

☆ እያንዳንዳቸው 40 ዓመት የገዙ ሰባት የዛጔ ነገሥታት፦
1.ጠጠውድም ከ925 - 965 ዓ.ም.
2.ጃንሥዩም ከ965 - 1005 ዓ.ም.
3.ግርማ ሥዩም ከ1005 - 1045 ዓ.ም.
4.ይምርሐነ ክርስቶስ ከ1077 - 1117 ዓ.ም.
5.ቅዱስ ሐርቤ ከ1117 - 1157 ዓ.ም.
6.ቅዱስ ላሊበላ ከ1157 - 1197 ዓ.ም.
7.ነኣኲቶ ለአብ ከ1197 - 1237 ዓ.ም. ናቸው።

☆ ሰባቱ ከ900 ዓመታት በላይ በምድር ላይ በሕይወት የኖሩ ሰዎች፦
1. አዳም - 930
2. ሤት - 912
3. ሄኖስ - 905
4. ቃይናን - 910
5. ያሬድ - 962
6. ማቱሳላ - 969
7. ኖኅ - 950 ናቸው።
📖 📖 📖 📖 📖
Forwarded from የብዕር ዕንባ 🀄️📝 (ቃል_ኪዳን (የአዮ ልጅ))
ለክቡር ዘበኛ ገንዘብ ቤት አንደኛ መምሪያ ሬድዮ ጣብያ አገልግሎት

ጉዳዩ:- ስለ ሰራተኛ መቀጠር

አቶ ጥላሁን ገሰሰ የተባሉ ግለሰብ ከ መጋቢት 25 ቀን 1949 ዓ.ም ጀምሮ በወር 40 ብር ደመወዝ ተቀጥረዋልና ከዚህ ቀን አንስቶ ስማቸው ከ አንደኛ መምሪያ ደመወዝ መክፈያ መዝገብ ላይ ተሞልቶ ሰቀርብልዎ በየወሩ ወጪ እየሆነ እንዲከፈላቸው ይሁን ::

ግንቦት 13 ቀን 1949 ዓ.ም
************
ጥሬ ቆሎ

ለክቡር ዘበኛ ገንዘብ ቤት አንደኛ መምሪያ ሬድዮ ጣብያ አገልግሎት

ጉዳዩ:-የደመውዝ ቅጣትን ይመለከታል

አቶ ጥላሁን ገሰሰ የተባለው የክፍሉ ሰራተኛ ጥሬ ቆሎ አምጥቶ የሙዚቃ ስራ በሚሰራበት ቀን እየጎረመደና እያስጎረመደ ለሠራተኞችም እያደለ ሥራ በማስፈታት ከአንድ ወር ደመወዙ ላይ 3 ብር እንዲቆረጥበት ይሁን።

ሐምሌ 9 ቀን 1949 ዓ.ም

* ታሪክን የኃሌት
*****


┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀🌼❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄

💜 ጦብያ መፅሔት 💜
@Keneyalew_teweld
┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀🌼❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
Forwarded from የብዕር ዕንባ 🀄️📝 (ቃል_ኪዳን (የአዮ ልጅ))
] ከአካል አርነት [
*
ቃልኪዳን የአዮ ልጅ
*
*
ከአፍ ጥሜ ያልታሰሰ
ለአቅመ ጥም ያልደረሰ

ሶስት ዘለላ ሲመዥርቅ
በተመስጦ ሲመጠቅ

እግሮቼን አቆላልፈ
እጆቼን ጭኝ በአፈ
እንዳሉት መክነፈ
አይደለም ተለክፈ

ኖረም አልነበርኩም
ጠፍቼም አልጠፋሁም
ከወሬ የለሁም
እሪታ አልዋጠኝም

ብቻ ከኔ ዓለም
ብቻዬን ተመጥቀ
ከአካል አርነት
በሀሳብ ተወሽቀ
እንደ ስንጥር ታህል
'ካካል ተሰንጥቀ
እዛው ነኝ አሁንም
ጉዞዬን ምን አውቀ....?
ትክክለኛ የፍቅር ጓደኛ ካላገኛችሁ መደበር መጨናነቅ አቁሙና ራስን በማሻሻል፣ በራእይ፣ በአመለካከት፣ በእውቀትና በገንዘብ ማደጋችሁን ቀጥሉ፡፡ ከፍቅረኛ ውጪ በመኖሩ ምክንያት የሞተ ሰው ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ ከማይሆን ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት በመጀመር የሞቱ (አንዳንዴ በቁማቸው የሞቱ) ሰዎች ግን ብዙ ናቸው፡፡
#አትሟት
© ሲራክ ወንድሙ
.
መሬት የሚጠርገው የቀሚሷ ጫፉ፣
በወንጌል ቢታሰር የሚቀድስ አፉ ፣
ምናልባት እዚህ ቤት...
ፀሀይ ፈገግታዋን የተሻማ ሁሉ ፣
ከፈገግታ ጀርባ መከልከል እንዳለ የነገራት ውሉ ፣
ባይገባው ነው እንጂ...
እስኪ አትሟት ይህቺን...
ለቆረባት ሁሉ እህትነት ይዟት ከመጣው ብትቆርብም ፣
እሷ ቀሚሷን ነው ሳቋን አትሰስትም።
................... //////....................
ሲራክ @siraaq
< የብርሃን መንገድ >
(ይስማዕከ ወርቁ)

ሰይጣን የታደለው

ሰይጣን የታደለው!
ሱሪው አያልቅበት ፤ እህል አይቸግረው ።
_አይበርደው ፤ አይሞቀው ።
ሰይጣን የታደለው!
_ቀድሞ ቁርጥ ያወቀው
_እፀድቅ - እኮነን ሲል የማይጨነቀው
ሰይጣን የታደለው !
_ልጁ አያለቅስበት ፤ ሚስቱ ልፍታ አትለው
ሰይጣን የታደለው !
_ሱሱ 'ማይደቁሰው
_ጎጆ 'ማይቀልሰው
_አፈቀርኩ ብሎ
_አንገት ማይደፋው
_ወሲብ ቅንዝርና ቂም ማያዳፋው
_የማያርስ የማይጎርሰው የማይጎለጉለው
_ሰይጣን የታደለው !
_የስልጣኔ አባት
_መፈንቅለ መንግስት
_ቀድሞ ያካሄደው
ከሰው ልጅም በላይ ፣ ፈጣሪን የሚያውቀው
የፈጣሪን ምስጢር ፣ አክስሎ የሞቀው
ባለውለታችን፤ሊቁ መልአክ ሰይጣን፣ከበለስ ጀምሮ
የተፈጥሮን ምስጢር ፤ ያምላክን ቋጠሮ
ለሰው አቀብሎ ፤ ለሰው አንቆርቁሮ
ፈትኖ ፈታትኖ ፣
ቀድሞ ተፈታትኖ ፣
ሰውን ሰው ያረገው
ግልፁ ደግ መልአክ ሰይጣን የታደለው !
ጥርቅምቅሞሽ እምነት ተደፋ!ተወጋ!ወደ ጥልቁ ውረድ !
_ሲለው የማያፍረው
_እኔ ላይ ተባሮ እሷ ላይ 'ሚሰፍረው
_ሙስሊም ክርስቲያኑ - ጴንጤ ኦርቶዶክሱ
_ካቆሊክ ---ዊትነሱ - ምዕመን መናፍቁ
___ባለዛር ጠንቋዩ --ድፍን ቅሉ ሊቁ

አስወጣሁት ሲለው ምንም የማይመስለው
ሳጥናኤል ታጋሹ ሰይጣን የታደለው
ሳጥናኤል ሉሲፈር ፀሎት አያደቀው ውዳሴ አያደምቀው
ጨለማ አይዘፍቀው ገነት አትናፍቀው ።
ሳጥናኤል ሉሲፈር ፍቅር የራበውን
ከልቤ ጠሊቅ ሥር ምናለ ብወደው
ጠላቴ ከሆነ -- ሰይጣን ወዳጄ ነው ።
እስኪ በዚህች እንኳ ታላቁን ልብለጠው
ልጁ ሲያስተምረን - ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብሎ ነው ።
ምነዋ ይህች ቃል ለ'ሱም የማትሰራው?
መቂያቂያም በቂም ልክ ቂሙን ቢደብቀው
ምነው የእሱን ሥራ የማይታረቀው ?
ለሰው ልጅ ተሰቅሎ እጥፍ ለበደለው
ምነዋ ወዳጁን ይቅር ይብቃ ቢለው!?

(ለክርስቶስ ሰምራ ፣ ወለዘይገረም ፍልስፍና ዘፎገራ)

#Yisma'eke werku
@Write_Event
@Write_Event
"""ፍቅር ና በቀል:""""
ሀዊ ጌታቸው
~~~ክፍል 5
.
. ስልኳን ስታየው
"""Good morning """
በኪሩቤል ነበር ደንግጣ ስታየው የማታውንም አልመለሰለችለትም ።.ለሁለቱም በአፅፋው መለሰችላት እና መልስ ስጠብቅ
ድንገት የመኝታ ቤቶን በር ሀኒ እያለ አባቷ ውደውስጥ ዘለቀ
"እየተንጠራራች ፈለከኝ አባ ስትል መለሰችለት ...
""እንዴት እስካሁን ተኛሽ?.

ዛሬ ክላስ የለንም ለዛ ነው።
"ኦ ጥሩ እንግዳው ደብረ ዘይት እቃ ታደርሺልኛለሽ እኔ ከምሄድ እልንቺ እና ሹፊሩ ትሄዳላቹ ፈርመሽ መምጣት ነው እና አንድ ውረቀት አለ እሱን ትምስገቢያለሽ ..

እንዴ እኔ አልሄድም ምን አውቄ የምፈራረመው
""አይ እንግዴ ትሄጃለሽ ብያለው ለባብሺ ቁርስ ብዬ አትቆይም እዛ ቢያንስ 30 ደቂቃ ነው የትቆይው ትመጫለሽ ቶሎ

""ማም እያለች እየተጣራች እናቷ ቁርስ እደምማቅረብ እያሉ..
"እውነቱን አንቺ እያለሽ ሌላ ማን ይሂድ አትቆይም በይ ለባብሽ...አሏት
እየተነጫነጨች እፍሏ ገብታ
ልብስ እየመረጠች እያለ ስልክ ተደውለላት የሱ መሆኑን ስታየው በሯን ዘግታ እያውሩ እያለ በመሀል እሱ ክላስ ካሌለሽ ለም አንገናኝም ..
"ከቤት በደብረዘይት እንደተላከች ስነግረው ለምን ፍቃደኛ ከሆንሽ አንድ ላይ እንሂድ ...ብደነግጥም ግን ጥሩ ጊዜ እንደሚሆን አስባ በሀሳብ ተስማምታ .

በደስታ ልብሷን ለብሳ ቁርስ ልበላ ስትል እናትና አቧቶ ግራ ገባቸው እንደዛ እንዳልተናጫነጨች ባንዴ እንዲ መሆኖ .
ሹፊር እንደማትፈልግ እና ግን ብር ያፈልገኛል እና ሙሉ አድራሻውን እፈልጋለው ብላ ውደ ክፍሏ ገብታ ሽቶዋን ተቀባብታ ያለቸውን በሙሉ አድርገው ከውሰደች በኃላ

ሀኒ እራስሽን ጠብቂ ብለዋት ከአይናቸው እስከምትለይ ይመለከቷት ነበር ።
"የተባባሉበት ቦታ ስደርስ ከመኪና ውስጥ ውቶ ልክ እንደ ፍቅረኛ ሰላምታ ተለዋውጠው በሩን ከፍቶላት ገባች በሁኔታው ግራ ብትጋባም ግን የደስታ ስሜት ነው የሚታይባት ከ አ.አ. ወተው ዱከም እንደደረሱ ስልኳ ይጠራ ጀመር።
ጓደኞቾ ናቸው ። የት እንደሆነች እና እንገናኝ ሲሏት ደብረዘይት ከአሌክስ ጋር እየሄድኩኝ ነው ስትላቸው ቀልቃላዋ ማክዳ ቀልቃላ አንቺ እኛን በሱ ልትለውጪኝ ነው ብላ የቀልቅ ሳቃቸውን እየሳቁ ..
. እሱ ለም አታስተዋውቂኝም ወይስ ታፍሪብኛለሽ ሲላት አሰበች እና እረ ችግር የለውም ...ቲጂ አንዴ አናግሪው ...
ሁሉንም ከተዋውቀ በኃላ

ማክዳ አሌክስ አደራ ምን እንዳይከፋት ቶሎ መልስልን ናፍቃናለች ....እየሳቀ እሺ
ታዛዥ ነኝ...
። ። ስልኩ ከተዘጋ በኃላ
ሁለቱም ላይ ዝምታ ሰፈነ
"ጓደኞችሽ ደስ ይላሉ።።..
በጣም ትልቅ ቦታ ነው ያለኝ ለነሱ...
"እንደማኮሳተር ግን ሳቅ እየመጣበት
"ለእኔስ? የለሽም
""አይጠፋም አሸጋሽግሀለው..እየሳቀች
"No no እኔ ሙሉ ልብ ነው የምፈልገው ....
""እረ ቀልደኛ ነክ .

ጨውታቸው ደራ ከተባለችበት ደርሳ ሁሉንም ከጨረሰች በኃላ እዚ ደርሰን ባብጋያን ሳናይ ልንሄድ። ብሎ ውጥር ስያረጋት በሀሳብ ተሰማምታ ባቡጋያ ሄዱ ዋና በጣም እንደምትውድ ነገረችው ለምን አትዋኝም እረ ልብስ አልያዝኩም ወድያው እዛ የሚሸጥ ገዛ ደነገጠች ግን ስለምትውድ አመስግናው ወደ ገንዳው ሄደች።

እንዴ አንተስ ና አትዋኝም ስትለው እንደማይቻ ግን ታለማምጅኛለሽ አላት። እሺ ና ብላው እሱም ልብስ ቀይሮ ገባ
"በርግጥ እሱ አውቆ ነው። ይችላል ግን ፍቅር መግለፃ መንገድ እየፈለገ ነው። ውሀ ላይ ተንሳፎ ሁለት እጁን በእጆቾ ይዛ ቀስ እያለች ዙር ታዞረዋለች እሱ በምታደርግለት አይኞቾን ከማየት ውጪ ምን አልተነፈሰም ። ሌሎች ተፈነጥረው ጥንድ ጥንድ ሆነው እየተሳሳቁ ይዋኛሉ ሀሳብ ውስጥ ገባች ድንገት ስለቀው አዎ ሰመጠ እና

ደንግጣ ለሁለት ሆነው አውጥተው ምን አልተነፍስ ሲል አማራጭ ስታጣ ከናፍሮቹን በከንፈሯ ትንፋሽ ለማስውጣት ለማዳን ያደረገች እሱ ግን አውቆ ስለነበር እውነታ እንዲመስል አደረገው ከአፉ ውስጥ ውሀ ውጣው እየተርበተበተች አቅፋው በፎታው ታደረርቀው ጀመር።

ወደያዙበት ክፍል ሄዱ በመጀመርያ ገብታ ልብሶን ልትቀይር ስትል በሩላይ እጆን ይዞ ወደራሱ አስጠግቶ አይን ላይን ተያይተው።
"ሀኒ ቅድም ኩሩዬ እያልሽ ነበር በሰመመን ሰምቼሻለው
"ኦ sorry አለክስ ተሳስቼ ነው ድንጋጤዋ አለቀቃትም ዛሬ ስለኪሩቤም ሙሉን ታሪክ ንገሪኝ ምሳ እየበላን ...
""ላለመንገር ብታመነታም ግን ውጥር አድርጉ ስለያዛት ምሳ ከበሉ በኃላ አየር እየውሰድ እንዲ ብላ ቀጠለች

""ኪሩ ሰፈራችን ልጅ ነው። ከኬጂ ጀምረን እስከ ኤለመንተሪ ወይም ከዚ ሀገር እስኪውጣ አብረን ነበርን ፍቅራችን የባልና ሚስት እስኪመስል ነበር። መልካም ልጅ ነው ይሄም የቤተሰብ አስተዳደግ ይውስነዋል እኔ ምን ገንዘብ ቢኖረን ግን ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ነው እየተቆጡ መልካም ነገርን ብቻ እንድናስብ ለገንዘብ ቦታ እንዳንሰጥ ያደግነው
እና የኪሩ እህት ና የእኔ ውንድም ፍቅር ይጀምራሉ ማለቴ ታላቄ የመጀመርያ ውንድሜ ከዛ
...

ይቀጥላል


share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 6
.
. እና የኪሩ እህት ና የእኔ ውንድም ፍቅር ይጀምራሉ ማለቴ ታላቄ የመጀመርያ ውንድሜ ከዛ ይበልጥ ዝምድነችን ይጠነክራል እያለን ደስታ ውስጥ ነበርን ዘመድ አስማድ አውቀ የሁለቱን ፍቅር ከዛም አልፎ ለመጋባት ሽማግሌ ተላከ የሰርግ ቀን ተቆረጠ ብላ እንባዋ ከአይኖ ድብ እያለ ይውርዳል"

""በርግጥ የሱም ስሜት ተረብሿል ግን እንዳያስታውቅበት ከዛስ ሀኒ

"" ወንድሜ ግን አፍቅሯት ውዶት ሳይሆን የመጀመሪያው ፍቅረኛው ጥላው ስለሄደች ነበር እና ሰርጉ 5ቀን ሲቀረው ጠፋብን ብናፈላልግ አየን የሚል ጠፋ ከኛ በላ የምታፈቅረው የኪሩ እህት ትጨነቅ ታነባ ነበር ግን እሱ አውቆ እንደጠፋ ሰላም እንደሆነ ይቅርታ የሚል ደብዳቤ ደረሰን

የመጀመርያው ፍቅረኛ መጣች አብረው እንደጠፉ ..
"""አሌልክ ከዛ በኃላ ምኑን ልንገርክ ቤተሰቤ ከሰው እንዳይገጥም ለብቻችን ከማህበራዊ ኑሮ ተገለልን ...

ግራ እንደገባው ሆኖ ለምን?
""ውድያው እንደሰማች ነበር ከዱባይ የመጣላትን ቬሎ ለብሳ እሯሷን ያጠፋችው። የእሷን ሞት ያልቻሉ እናትም ሲሰሙ ደንብዛት ስለነበራቸው ውድያው ለሆስፓታል ተዳረጉ ግን ፈጣሪ ሊረዳቸው አልቻለም። ልጃቸውን ተከትለው የማይመለሱበት ሄዱ።
አስበው ያን የደስታ ቤተሰብ በእኛ ቤተስብ ሀዘን ስገርፋቸው
እንባዋን መቆጣጠር አቃታት ...እንኳን እነሱ እኔ በዛ በለጋ እድሜ ሁሉን ነገር እያየው አቃተኝ ኪሩቤል እንደዛ የሚውዳትን እህቱን እናቱን የእኔ ውንደም ምክንያት አሳጣሁበት እንዴት ልየው ።
ምንስ ድፍረት አለኝ ።
ሁሉም ነገር እፊቶ ተደቀነ ..

ቤተሰቦቼም እንዴት ይሁኑ ከቤት መውጣት ከሰው ጋር መግባባት አቆምን እኔ ትምህርቴን አቆምኩኝ ግን አባቴ ህሊናው እረፍት ነሳው ፓሊስ ጣቢያ ሄዶ አመለከተ።
የኪሩ ቤተሰብ ግን ክስ አልሄድም .

"በርግጥ ጅብ ከሄደ ውሻ ይጮሀል ሆነብን ነገሩ"
""በጣም ያሳዝናል እያለ ውደራሱ ደረት አስጠግቶ.እያባበላት እና እንዴት ከሀገር ሊውጡ ቻሉ"
"ታላቅ ውንድሞቹ እዛ ነበር እና
በትምህርት ከዛ ጥሩ ነገር ስላላቸው አባቱን እና ኪሩንም ውሰዷቸው።

""የሚገርመው አማን የሚባል ጓደኛ አለው የማክዳ ፍሬድ ነበር። በጣም ነው የሚውዳት እረፍት ሰዓት ላይ እኔ ኪሩን እሷ ደሞ አማንን ነበር። አቤት ፍቅራችን
በመካከላችን ሁለቱ ናቸው ውንዶች
አማንም ከዛ ሰፈር ኪሩ ስሄድ እናቱ ውደ ድባይ ስትሄድ ውደ ሌላ ሰፈር አስገብታው ሄድች።

ከአንኖቼ የትዝታ እንባ እየውረደ ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ታያት ዘገነናት

"ሀኒ እና አማንን የሚባለውን ለማፈላለግ ለማግኘት አልሞከርሽም?

""እረ ያልፈለግንበት የለም ግን ደብዛው ጠፋ ማክዳም ከዛ በኃላ ለውንድ ጥሩ ስሜት የላትም የሚገርምክ አሁንም ስትውድቅ የሆነ ነገር ስትሆን ስትምል በሱ ስም ነው የምትምለው አማንዬ ከዛ ለምን አስተውሰዋለው እያለች በሯሶ ትመሰጫለች ወይ ፍቅር

ምን ፍቅር ቢኖርም ግን በልጅነትክ ምን በማታውቅብት ውስጥ የገባውን ማውጣት ይከብዳል
"
""እና ግን ታፈቅሪው ነበር ቢመጣስ? ብታገኝው?
""በጣም ነው የምፈራው ማለት ውንድ በፍቅር የማልቀርበው የውንድሜ ግፍ እኔ ላይ እንዳይመጣ አባቴም በጣም የሚፈራው የሱ ግፍ በአንድ ልጄ እንዳይመጣ ተጠንቀቂ ይለኛል"

"እውነት ነው የሰው ደም መቼ ይለቃል ግን የሆድን ፈጣሪ አይደል የሚያቀው ሚባለው ኪሩቤል አይመጣም ቢመጣም የማየት አቅም የለኝም። እንዴት ብዬ

ይህኔ ከእግሩ እስከራሱ ነዘረው እና
""አይዞሽ አታልቅሺ እያለ ፀጉሯን እያሻሸ ግን ከናፍሮቹን በቁጣ እየነከሰ ...
ያባብላታል ሰዓቱ ስለሄደ ተነሱ ጉዞ ጀመሩ።
ግን ከዛ በኃላ ዝምታ ሰፈነ
""ሀኒ ምን ይሆን የኪሩቤል ነገር ያገበግባታል የልጅነት ማንነቶን በውንድሞ ጥፋት ያጣችው ስለሆነ
መድረስ አይቀር ደረሱ ስለሁሉም ነገር ይቅርታ የማፈልጊው ስሜት አነሳው መሰለኝ አለት
""ችግር የለም አስቼ ቻው ብላ ወደ ቤቶ ገባች።
እሱም በንዴት መጠጥ ገዝቶ እቤቱ ገባ

""ጓደኛው የት እንደዋለ ለምን እንደሚጠጣ ቢጠይቀውን መልስ የለም .

ቀናት ወራትም ተተክተው ከሀኒጋር በጣም መገናኘት መደዋወል ተያይዘውታል
አንድ ቀን .
'"ፊልም ገብተው እንደውጡ ሰፈሯ ልደርሱ ሲል

መኪናውን አቁሞ ከኃላ ውንበር ገብቶ ቁጭ አለ ስትዞር ሀኒ ነይ እዚ አላት።
"እሺ ብላ ምነው ምን ሆንክ ...ካቀረቀረበት ቀና እያደረገችው

ይቀጥላል..

|Share|Share|Share|

share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

ለማንኛውም አስተያየት
@kaliye06
""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 7



መኪናውን አቁሞ ከኃላ ውንበር ገብቶ ቁጭ አለ ስትዞር ሀኒ ነይ እዚ አላት።
"እሺ ብላ ምነው ምን ሆንክ ...ካቀረቀረበት ቀና እያደረገችው
"""እጆቾን ይዞ ልብ ላይ አስጠግቶ ታምሜልሻለው ሀኒዬ ለውራታት ያልክ በሽታዬን ሳልናገር ቆየው አሁን ግን አልቻልኩም #አፈቅርሻለው

አይን አይኖን ከአፋ የሚውጣውን ቃላት ይጠብቅ ጀመር ግን.

""እሷ ግን አይኖቾን እየጨፈነች ከአይኖ የእንባ ዘለላ ዱብ ዱብ ይል ጀመር።
"ሀኒ ለውንድ እንዲ ተሸንፋ ስለማታውቅ ለሱ ግን ገና ድምፁን የሰማች ግዜ ነው የተሸነፈችለት
የያዛትን እጆች ከመዳፉ አውጥታ አቅፋው #አፈቅርሀለው ግን ብላ ከላዩላይ ነጠል ብላ አለክስ #እንዳትጎዳኝ ስለኔ ሁሉንም ታቃለክ እሽ

#አልጎደሽም አላት ድምፁ እየተቆራረጠ።
አይን አይኖን እያየ ሀኒ አንቺ ከዚ በኃላ ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነሽ የእናቴ ምትክ አፈቅርሻለው ትልቅ ባታ አለሽ። እያለ ግንባሯን እየሳመ እቅፍ አድርጎ ልብ ላይ አስጠግቶ አቀፋት ሁለቱም የደስታ ስሜት ውስጥ ገብ።

""እቤቶ ስገባ የሌለ ደስ ብሎት ትቀብጥ ጀመር። ሚስጥረኛዋ ውንድሞ ስነግረው ተደሰተ በጣም ነው የሚዋደድት እሱም ቲጂን በፍቅር አንድ ላይ እንደሆኑ ሲነግራት
""ልዬ ቀን ነው ዛሬ የሚለውን ከፍተው እሷ አልጋዋ ላይ እሱ በጀርባው ተኝቶ ያያት ጀመር እናትና አባት ከታች ከሳሎን ምን ሆነዋል ብለው እየተሯሯቱ ስሚጡ ሁለቱ ግን ማን ይምጣ የሚያዩ ጊዜ አልነበራቸውም ሀኒ ፃጉሮቾን እያመነቀረች
""እናትም አባትም የልጆቻቸው ደስታን አይተው ተሳስቀው ተቃቅፈው ተመለሱ።

""ኪሩቤል የሀኒ የፍቅር ጥያቄውን በመቀበሏ ደስ ብሎታል እቤት ገብቶ እራሱን በመስታወት እያየ ሀኒ ምን ጥሩነትሽ ቢኖርም.....እኔ ግን ....እያለ ጥርሶቹን እየነከሰ አንድ እስቴፕ ብቻ ነው የቀረኝ ያበቃልሻል....እያለ አጠገብ ያለው አልጋ ላይ በጀርባው ተኝቶ ግን ስለኪሩቤል እያለች ያውራችለትን እያሰበ እንባ ይፈሰዋል ።
"""እውነተኛ ስሙን ሳይነግራት ለብዙ ግዜ በፍቅር ቆዩ ሀኒ በጣም ስለምታፈቅረው ምን በሱ ቢመጣም አትደረደርም አንድ ቀን .
""ከጓደኞቾ ጋር እራት ይጋብዛቸዋል
ደስ አላት ...


ለግብዣው አምረው ተውበው ወደ ተባለበት ሆቴል አመሩ።
ደስ የሚል ግዚ እያሳለፍ ነው።
ድንገት ከስራቸው ተነስቶ የሚካኤል በላይነህ የሚዘፍነውን ልጅ ማይኩን ተቀብሉ
""ይቅርታ አንዴ ....ሲል ቀና ሲሉ
ኪሩቤል ለነሱ አሌክስ ደነገጠች ጓደኞቾ በደስታ አስተያየት አይተዋት ማክዳ ተነስታ አቀፈቻት
""እሱ ከመድረክ ሆኖ በጣም የምውዳት የማፈቅራት የውደፊት የልጆቼ እናት የሆነችውን ሀኒዬ አንዴ ውደዚ እድ
መጣ በሞራል ተቀበሉልኝ

ጓደኞቾ ጩኸታቸው ማመን አቃታት
""Omg ብላ አፏን በእጆቾ ያዘችው
አስነስተዋት እንደትሄድ አደረጉ ...
""እዛ ሆቴል ውስጥ ወንድሞ ከጓደኞቹ ጋር እየተዝናና ነበር ...ለጓደኛው ማን ትሆን ፍቅራቸው የሚያስቀና ነው እያለ አይኖቹ መድረክ እስከምትደርስ አጣድፎታል ....
"ከመድረክ ደርሳ የውረዱ ፀጉሮቾን ባንድ ጎን አድርጋ ቀና ስትል ....

"የራሱ ጉድ ደርቆ ቀረ በእጁ የያዘውን የቢራ ጠርሙስ ለቀቀው ጓደኞቹ እንዴ ሀኒ ናት ብለው ያባብሱበት ጀመር።
አስሬ አይኑን እያሸ ይመለከታል።
""ግን ምን ሳይል መጨረሻውን መከታተል ጀመረ።
"ኪሩቤልም ከቆመበት ተበርክኮ ቀለበት ይዞ #ታገቢኛለሽ
ይህኔ ሁሉም በጩኸት እና በፉጨት ሆቴሉን አናውጡት
"እሷ አይኖቾን ጓደኞቾ ጋር ጣል። አድርጋ እነሱም ተቀበይ የሚል ምልክይ ሰጦት
"ቀና ስትል ውንድሞን አየችው ደነገጠች ግን እሱም በአይኑ ተቀበይው የሚል ምልክት ነው ።

"አዎ አገባሀለው ብላ አለንጋ የመሰሉ ጣቶቾን ዘረጋችለት እዚ ያሉትን ሂሳብ እኔ እከፍላለው ጠጡ ብሎ ደስታውን። ተካፋይ አደረጋቸው ።
ከመድረክ እንደውረድ ውንድሞ ጋር ሄዳ ተቃቀፉ እና ልታስተውዋውቃቸው ይዛው ሄደች ግን ኪሩቤል ሳየው ቢደነግ ግን ምን ሳያስነቃ ተዋውቀው
"የሀኒ ውንድም ግን ተጠራጥሯል
"በውሬ መሀል ይቅርታ ሀኒ ግን ኪሩን አይመስልም አስደነገጠኝ እኮ ብሎ ሲያውራላት ሰማ ..
"

"እንደማያቅ ሆኖ ኪሩቤል ማነው ?
አይ የሰፈራችን ልጅ ነበር። ይሆነ ነገርክ መስሎኝ ነው። በቃ ደስታቹን አላበላሽ ጓደኖቼ ጋር ልቀላቀል ነው አይለያቹ ብሎ ጥሎቸው ሄደ።
ያምሽት በደስታ አምሽታ ወደ ቤቶ ስገባ የቤቱን በር ስከፍተው መብራት ጠፍቶ ግን ብልጭ ድርግም የሚል አለ እናትና አባቷ ከሶፋው ተቀምጠዋል እንደቤተሰብ የሚመለከቷት የቤት ስራተኛቸውም ቡና እያፈላች ነው።
በመደንገጥ እንዴ ምድነው ያለመብራት መቀመጥ ብላ ልታበራ ስትሄድ ""አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ እሆሆ
ሀኒ እህቴ ብሎ የሰርግ ዘፈን ከፈቶ ተጠጋት
አንተ እብድ ብላ በያዘችው የእጅ ቦርሳ መምታት ጀመረች ግን እናትና አባት ምን የሰሙት ነገር የለም ።መብራቱን አብርቶ አንቺ ታውሪ እኔ አላት ...
"ምኑን ነው የማውራው ብላ ስታፈጥበት ...

""እናት ምድነው የሆናችሁት እሱ ከመጣጀምሮ ይሄን የሰርግ ዘፈን ይለዋል...
""አባትም ሳቅ ብለው አንቺም ከሆንሽ አንተም የምታገብት እስቲ እንስማቹ
""ከተቀመጠበት ተነስቶ
"'በጣም የምውዳት የማፈቅራት የውደፊት የልጆቼ እናት የሆነችውን ሀኒን ወደ መድረክ በጭብጨባ ተቀበሉልኝ....
"""ያኔ አባቶ ጋር ሄዳ ተሸጎጠች ...
ቤቱ በልልታ በደስታ ደመቀች ...
እናት ....

ይቀጥላል

|Share|Share|Share|

share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

ለማንኛውም አስተያየት
@kaliye06
""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 8

"'በጣም የምውዳት የማፈቅራት የውደፊት የልጆቼ እናት የሆነችውን ሀኒ ወደ መድረክ በጭብጨባ ተቀበሉልኝ....
ከመድረክ ደርሳ ቀና አለች
ተበርክኮ ""ታገቢኛለሽ .የጣት ቀለበት ይዞ.......ከዛ እሷ እንዳለ
ውንድሞ ሆቴል ውስጥ የተደረገውን በወሬ ብቻ ሳይሆን ተግባሩንም እያሳያቸው ነበር
እናቷ ጣቶን አዩ

"""አንተ ግን ለወሬ ችኮላክ ብላ ያኔ አባቶ ጋር ሄዳ ተሸጎጠች ...
ቤቱ በልልታ በደስታ ደመቀች ...
እናት በይ ይሄን የልጃችንን ልብ ያሸፈተውን አስተዋውቂኝ
"" አባትም ፀጉሯን እያሻሸት እየሳማት እና ነገ እቤት ምሳ ግልብዠው ...
"
ቡናቸውን ጠጥተው ወደ መኝታ ቤቶ ስገባ ልደውልለት ስትል ደወለ አልጋዋ ላይ በደርቶ ተኝታ ታዋራው ጀመር እቤት እንዴት እንደጠበቋት እና ነገ ምሳ ተጋብዘሀል ስትለው ደነገጠ ግን
"ውስጡ ደስ ብሎታል ...
ስልኩን እንደዘጉት
""ከራሱ ጋር ንግግር ጀመረ አሁን ያሰብኩት እየተሳካልኝ ነው ፍፃሜ አሳምርልኝ....

"ኪሩ ግን ይሄን ሰሞን ምድነው የተለየ ነገር አይብካለው ብቻክን ማውራት ስልክ እረጅም ሰዓት መጠቀም ?
""ንገረኝ የምደብቀኝ ነገር አለ ብዬ አላስብም .
እሱን ተውውና ማክዳን የምትመስል ዛሬ አይቼ ትዝ አለኝ የድሮ በረጅሙ እየተነፈሰ
"አማንም ማኪ ብሎ ዝምታ
ሰፈነ
ግን አማን ከዛ ከውጣክ ጀምሮ አግኝተካቸው አታቅም?
""እረ እነሱ ባያዩኝም እኔ ግን ብዙ ጊዜ አይቻቸዋለው የሚገርምክ ኪራ አሁንም ያው ናቸው ፍቅራቸው ደስ ይላል። አማን እንባው በአይኖቹ ሞልተው ደንስ ትሬዲንግ የሚሰሩበት የጓደኛዬ ውንድም ነው።
""ግን ትውዳታለክ አሁንም? አይደል አማን እንዳትዋሸኝ ""
"እንዴ ምን ያስዋሸኛል ከመውደድም አፈቅራትም ነበር።
"አስታውስከው ሀኒ በጣም ነው የምትውድክ ከሴት ጋር ስታውራ እንዴት እንደምትናደድ አንተ ከሄድክ በኃላ ትምህርት ቤት እኔ ስታይ ማልቀስ ማንባት ነበር እኔ እንደዛው እሷን ሳይ አንተን ማሰቤ ማስታውሴ አይቀርልኝም በሞት ያጣሁክ ነበር የሚሰማኝ
"ይህኔ ኪሩቤል ያለቅስ ጀመር።

ከለቀኩኝ በኃላ ሀኒም ትምህርት እንዳቆረጠች ማክዳም ኢንኮንፕሌት እንደተባለች ሰማው። ያኔ አሳዘኑኝ ባይገርምክ ሳላያት አላድርም አልውልም።
"
ሁፍ ያለፈ ታሪክ አታንሳ ብሎት ውደ ክፍሉ ገባ።

መንጋት አይቀር ነጋ በተባለበት ሰዓት
እና ሀና ቤት ሄደ ግን የሀና አባት ሲያዩት ደነግጠው ነበር። ሀሳባቸውን ሰብሰብ አድርገው ምሳ በልተው ጫውታ ጀመሩ።
ኪሩቤል እንባው እየመጣ ቢሆን ግን የደስታ ስሜት ያሳያል ያ እየቦረቀበት ያደገበት ቤት ከሀኒጋር እቃቃ የተጫወቱበትን ቤት ዛሬ እንደማይታውቅ ሲጋበዝ ..አቃተው ....
በመሀል ስልክ ተደውሎለት መሄድ አለብኝ አለ። ብሎ ሄደ

እቤት እንደገባ እያደረገ ያለው እራሱን በቢራው ውስጥ መሸሸግን ተያይዞታል

ከውራት በኃላ ከሀኒ ጋር ፍቅራቸውን በማሳለፍ ላይ አንድ መዝናኛ ሆነው ከነሱ ፈንጠር ብለው የተቀመጡትን ተመልክቶ። ""
"ሀኒዬ እንዲ መሆን አማረኝ ወደሰዎቹ እያየ ...
"""በእነሱ እኩያ ያሉ ውንድ ልጃቸውን መሀል አድርገው ሲጫውቱ እየተመለከተ
""ሀኒ በረጅሙ እየተነፈሰች የሚቀድመውን ማስቀደም ነዋ ካማረክ
አይኖቹን ሀኒ ላይ አድጎ መቼ ሽማግሌ ልላክ እንጋባ ... እጆቾን እየሳመ
""ደንግጣ ታየው ጀመር ..
አትቀልድ!
""አልቀለድኩም እውነቴን ነው። የሚያስተዳድር ብር አለኝ ምን አይጎልብኝም .ዛሬ እንደውም እሁድ አይደለ ለሳምንት እሁድ ይሁን ሰርጋችን ""
""" እየሳቀች ወይ አንተ ኮሜዲም ሆንክልኝ ..
""ሀኒ እኔ አልቀለድኩም ምነው ትዳር ከኔ ጋር አትፈልጊም?

እውነት ከሆነ ደስ ይለኛል ።.
ምርጥ ጊዜ አሳልፈው እቤት እንደገባች ቤተሰቦን ቁጭ አድርጋ
"እንጋባ ብሎኛል ምን ታስባላቹ ...
"አባት ከተቀመጡበት ተነስተው


ይቀጥላል 😂

|Share|Share|Share|

share and Join
t.me/Write_Event
"" ፍቅር ና በቀል""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 9
.
. "አባት ከተቀመጡበት ተነስተው "
ልጄ የቸኮላቹ አይመስልም በጭራሽ አይሆንም አንቺም ትምህርትሽን ጨርሺ እስከዛ ተጠናኑ ትዳር ቀልድ አይደለም ።

እናት ደስ ብሏቸዋል

ሀኒ እየተነጫነጨች አባ ደሞ ከውደደኝ ከውደድኩት ከዚ በላይ ምን አለ። ለውጪው ከሆነ ሰርግ አልፈልግም.
ይህኔ እናት አይ ልጄ ለሱ አይደለም አንድ ልጃችን አይደለሽ ድል አድርገን ነው የምንድርሽ ያው ለሁሉም ቸኮላቹ ነው እንጂ ለዛ አይደለም።

እንዴ እኔ ልጃቹ አይደለሁም አንድ ልጄ የምትያት ...
ልጄ ነክ ያው ሌላ ሴት ይለኝም ለማለት ነው።
ሀኒ አባቷን እእእእ ምን ውሰንክ
እሺ ግን እሱን ላናግረው እፈልጋለው ስልኩን።
በደስታ አባቶን ስማው ስልኩን ሰጠችው።

""ሰራተኛዋ ቡናውን እየቀዳች አይ ጊዜ ስቱን ያሳያል .

ሀኒ እንዴት ውርቄ ማለት ምን ለማለት ነው።
"አይ ያው አለ አይደል የድሮ ሰርግ እና የዘንድሮ ምኑን ተምኑ ተገናኝቶ""

አግብተሽ ነበር እንዴ አላት እስራዬል

አዎ ያውም 13 አመቴ ነዋ ብላ ቡናውን ልትሰጥ ስትል
ሀኒ እስሯ ደርሳ እኔ እሳጥልሻለው ንገሪኝ እንዴት እንደነበር ብላ የተቀዳውን ቡና ለሁሉም ሰታ። አባቷ ጋር ሽጉጥ ብላ ተቀመጠች።

በሀገራችን ልጄን ለልጄ ነው የሚባለው እና እኔ 13 እድሜ ስደርስ ነው ።
ሰርግ የተደገሰልኝ ማግባቴን ያውኩት የሰርጉ ቀን ነበር ።
ባለከበርቴ ነው። በእኛ ሀገር ክብር ነው ለሀብታም መዳር እድሜው 29 ነው

እስራዬል what?

ኢሱ ዋጥ አድርግና አዳምጥ
ቀጥይ ወርቄ
ያው ሆ ብለው ዳሩኝ ግን 15 እስኪሞላኝ ግንኙነት እንዳያደርገኝ በሽምግልና ተነገረው ተስማምቶ ፈረመ ግን ከተጋባን በ3ቀን ነበር ይፈታተነኝ የነበረው። እኔም ከዛ ብን ብዬ ጠፋው
ግን ሂውት በስቃይ ተቀበለችኝ
ጎዳና ነበር። እዛም ተደፈርኩኝ
ከስት ስቃይ በኃላ ነው እዚ ቤት የገባሁት ፈጣሪ እናተን ልክ እንደቤተሰብ የምዬኝ ጋር ጣለኝ እንዲ ስትላቸው እንባዋ ድብ እያለ ነበር። በርግጥ ሁሉንም አስለቀሳቸው።

ሀኒ እስሯ ሄዳ። ታላቅ እህታችን ነሽ ምን አይክፋሽ ደሞ ድል ባለ ሰርግ እንድርሻለን።

"በርግጥ ልክ ነሽ እኔም ፍቅርተን በፍቅር አብደን ለጋብቻ ቤተሰቦ ስጠይቅ አሻፈረኝ ብለው ግን ሁለታችንም ውስጥ ፍቅር ስላለ ከደሴ ጠፍተን እዚ ገባን ጠንክረን ሰርተን ነው እዚ ደረጃ የደረስ ነው።

ለፍቅር እንጂ ለገንዘብ ቦታ እንዲኖራቹ አድርጌ ያላሳደኳቹ ፍቅር ከምን በላይ ነው ፍቅር ይቅር ይላል።

ያምሽት በደስታ ና በምክር ሲያውሩ
ቆይተው ሀኒ ወደ ክፍሏ አምርታ አባቶ እሺ እንዳላት ደውላ ነገረችው።

ኪሩቤልም ሁሉም ነገር ሊያበቃለት ነው እያለ ከናፍሮቹን ይነክሳል።

ጠዋት ላይ አባቶ ስልክ ደውለው ምሳ ሰዓት እንደሚፈልጉት ሲነግሩት
በእሽታ መልሶ የሚገናኙበትን ቦታ ተነጋግረው ተዘጋ ።

ኪሩቤል ላይ ግን ፍራት ይትምይበት ነበር።

""የተቀጣጠሩበት ቦታ ኪሩቤል ቀድሞ ተገኛ እየተጫውቱ ምሳ በልተው ሲጨርሱ
""ዛሬ የፈለኩክ ትዳር እንዳሰባቹ ነግራን ነው። ጥሩ ሀሳብ ሆኖ ግን ትንሽ ፈጠነ እሷም ትምህርቶን ብትጨርስ አሪፍ ነበር። ሀኒ ነጭናጫ እና በቶሎ የሚከፋት ልጅ ነት ተፈጥሮዋ አይደለም በርግጥ ከጊዜ በኃላ የመጣ ነው።
መቻቻልን ይስጣቹ አደራ ልጅ ብዙ ነገር አሳልፈን ነው ዛሬ ሰው የሆነው ሀኒም ከዛ ውዲ ነው። መነጫነጭ ያመጣችው ።

ግን አይ ካላቹ አሁን ላይ እንደቀለበት እናድርገው እና ሰርጉን የምርቃቶ ቀን ይሁን።
ኪሩቤልም ስሜቱ ተደበላለቀ እንደውም ደስ ይለኛል ቀለበት ይሁንና ሰርግ በዛ ቀን እናደርገውለን በተቆራረጠ ድምፅ ....
"ያው አንተ ምን ሰው የለኝም ስላልክ ውከባ ላሁኑ አያስፈልግም ሆቴል ደግሰን እናከብረዋለን።...
እሺ....ኪሩቤል ልብ ትመታ ጀመር። እስከሚለያዩ አጣድፎታል
""እንደተለያዩ እቤት ሀኒ ደውለችለት አያነሳም ግራ ገባት ለማክዳ ደውላ ነይ አለቻት ።
ኪሩቤል እቤት እንደገባ ጓደኛው እሳት ጎርሶ ጠበቀው ።
"""ምን ሆነሀል አማን እያለ ጠረጵዛው ላይ ያለውን ውሀ ሊጠጣ እየቀዳ .

አማንም በመቆጣት ስሜት ግን ምድነው? እያረክ ያለከው
""ምን አደረኩ ምን ሳደርግ አየከኝ ..
""የፊዝ ሳቅ እየሳቀ እረ እኮ ይሄ ምድነው ?

ይቀጥላል ...




share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
:""ፍቅር ና በቀል""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 10
.
.
አማን በመቆጣህ ስሜት ግን ምድነው? እያደረክ ያለከው
""ምን አደረኩ ምን ሳደርግ አየከኝ .
""አማን የፊዝ ሳቅ እየሳቀ እረ ምን አላደረክም.... ከየቱ ልጀምርልክ አንደኛ አባትክን ከዚ15 ቀን ውስጥ ፍሪ ቪዛ እንዲሰራልክ ሁለተኛው ደሞ ካንተ ይሄን አልጠብቅም ነበር ..
ያኜ ኪሩቤን ደንግጦ ሶፋው ላይ ቁጥ ብሎ እራሱን ያዘ....

ንገረኛ ከመቼ ጀምሮ ነው አንተ እንዲ ለበቀል የተነሳከው ከስንት አመት በኃላ እንዲ ማሰብ ምን ይሉታል ሀኒ የልጅነትክ ባልና ሚስት ...የእቃቃ እረስቱን ላንሳልክ እንዴት እንደዛ እውዳታለው የምትለው ላይ በእህትክ የተደረገውም ትደግማለክ እኮ እንዴት ኪራ መልስልኝ እድሜ ላባትክ ተከታተለው አላማረኝም ግዴታ ቅዳሜ ላይ ነው ምፈልገው ብሎኛል አሉኝ። እኔ እዚ አጠገብክ ሆኜ ምን የማላውቀው እሳቸው ግን ለምን ይሄን ያክል ድብቅ ሆነካል ...አማን ያለቅስ ጀመር ።

አዎ እኔው እራሴ ነኝ በዛ በልጅነቴ ሁለት የምውዳቸውን ነው ያሳጡኝ ቢያስ ከመሀከላቸው ማንም ባይሞት ግን ሰርጉላይ አልገኝም ከዛ ምን ያክል ከባድ እንደሆነ ይመልከቱ።
አንተ እንዴት ይሰማካል እኔ ግን እኔግን ዛሬም ነገም አይውጣልኝም አባቴ በስተርጅና ሰው በዓድ ሀገር የሚኖረው ቤታችን ስለፈረሰ አይደል። አንተ እኮ ናፈኩሽ ስትላይ የምትመጣ የምትዳብስክ እናት አለክ እኔ ማን አለኝ።
እያለ እየተንሰቀሰቀ ያለቅሳል ።
አማን አቃተው ቤቱ በጩኸትና በለቅሶ ባንድ እግሯ ቆማለች
ሀኒ ስደውልለት አያነሳም ግራ ገባት ማክዳ ጋር ደውላ ጠራቻት እንደመጣችም በእሷ ስልክ ስደውልም አይነሳም። አባቴ አስቀይሞት ነው እንዴ? እያለች ታስብ ነበር። ማክዳ ለምን እንዲ አናደርግም አለቻት።

አማን አንባዎቹን እየጠራረገ እኔ ለምን ትምህርት አቆምኩኝ ሀኒ እኔ ባየች ቁጥር አንተን እያሰበት ምን ያክል እንደተጎዳች አውቃለው እኔ ፍቅሬን ጥዬ ለሷ ስሜት እንደገናም ለኔም ጥሩ አይደለሁም ማኪን ምን ሳልላት ነው የተለየዋት። አየክ ውንድሞ ባጠፋው አንተን አታ የተቀጣችው ይበቃታል። አታሳዝንህም አትውዳትም ....ንገረኛ
ሀኒ አሁንም ድረስ እንደማረሳቅ አውቃለው 100% እያደረክ ያለከውን አቁም ይብቃክ .

አውቃለው በጣም እንደምትውደኝ ኪሩቤል ብላ ሙሉ ታሪካን ነግራኝ ነበር ።

" እና እንዲ እያለችክ እሷ ላይ እ ኪራ እኔ የማቀው ኪሩቤል ቂም አያቅም። አትውዳትም ፦"""

"^ እውዳታለው ግን...

አትውዳትም ብትውዳትማ
#ፍቅር ስጋዊ ፍላጎት አይደለም፡፡ ለአንዳንዶች #ፍቅር ማለት ድንገት መጥቶ የሚይዛቸው የማይቆጣጠሩት ስሜት ነው፡፡ #ፍቅር ለሌሎች ይጠቅመኛል ለኔ ጥሩ ነው ብለው ወደሚመኙት
መሳብ ነው፡፡ አንተ ግን በቀልን ነው ሀኒ ላይ ብትውዳት

#ፍቅር ለራስ ወዳድነት ስሜታችን
የሚስማማን ነገር ማድረግ አይደለም፡፡ #ፍቅር
ምኞታችንን መከተል አይደለም፡፡ #ፍቅር በህይወታችን ያለውን ጉድለት እጦት የምናሟላበት አቋራጭ መንገድ አይደለም፡፡ #ፍቅር ከሌላው የምንወስድበትና ሌላውን ለራሳችን ጥቅም የምንጠቀምበት መንገድ አይደለም፡፡አንተ ግን ሀኒን እየተጠቀምክባት ነው

አማን ይብቃክ ...እራሱን ይዞ ቀረ

ልገርክ
#ፍቅር ሲጀመር ሰውን መረዳት ነው፡፡ #የፍቅር አላማ ስለምንወደው ሰው እንጂ ስለእኛ አይደለም፡፡ #ፍቅር የሚያማክለው የምንወደውን ሰው እንጂ የራሳችንን ጥቅም አይደለም፡፡ #ፍቅር የእኛ ፍላጎት ሳይሆን የምንወደው ሰው ፍጎትን
በማሟላት ላይ ያተኩራል፡፡ እንዴት የልጅነትክን የምትውዳትን

#ፍቅር_ለምንወደው ሰው ስኬት መስራትና፤ #ለምንወደው ሰው መነሳት መትጋት ነው፡፡
#የምንወደውን ሰው በመረዳት ለምንወደው #መልካም_ማሰብ#መልካም_መናገርና መልካም
ማድረግ #ፍቅር ነው፡፡ #ፍቅር ከምንወደው ሰው ጋር ራሳችንን ማስተባበር ነው፡፡ በአጠቃላይ እውነተኛው የፍቅር ትርጉም
(((ከምንወደው ሰው ጋር በመረዳት ራሳችንን ማስተባበር ነው))) ፡፡ Love is identifying ourselves with the person we kira understand

..
አማን እናቴ እህቴ አያሳዝንህም ከመንገዴ ዞር በልልኝ ሀኒም እንድትጎዳ ሳይሆን ትንሽ የኔን ስሜት ምን ያክል እንደተጎዳ ትየው .....አማን plzz ተወኝ

""ፍቅር ወይስ በቀልን ንገረኛ እያደረክ ያለውን" አማን ኪሩቤል ላይ አፍጥጦ
ድንገት የቤቱ በር ብርግድ ብሎ ቀና ሲሉ....

share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
""ፍቅር ና በቀል""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 11
.
.
""ፍቅር ወይስ በቀልን ንገረኛ እያደረክ ያለከውን። አማን ኪሩቤል ላይ አፍጥጦ

ድንገት የቤቱ በር ብርግድ ብሎ ቀና ሲሉ
"ኪሩቤል በድንጋጤ ሀኒ ሲላት እራሷን ስታ ወደቀች አብራት ያለችው ጓደኛዋ ዋይ ሀኒ ሀኒ እያለች እያለቀሰች ሀኒን እንደማንሳት ስታ ሀኒ ብለው አማንም ኪሩም ሲጠጓት እንዳትነኮት ደስ አላቹ አስመሳዮች እያለች ትሰድባቸው ጀመር ግን የሀኒ ነገር አሳሳቢ ሆነ እንደምን ማክዳን አሳምነዋት ውደ ሀኪም ውሰዶት

ውስጥ ዶክተሮች እንዳስገቦት አንድ ሰው ሲባል ኪሩቤል እኔ ብሎ ሊገባ ሲል ማክዳ ጭራሽ እንድገላት ነው እኔ የምትለው አታፍርም ትንሽ የዚ መንስኤ ማን ሆነና
ነርሷ ከምትከራከሩ አንዳቹ ግብ ያኔ አማን ማክዳን እንዳገባ ያዛት ኪሩቤል እንባውን እየረጨ ውደ ውስጥ ተፈናጥሩ ገባ ።
ማክዳ ልቀቀኝ እያለች አመነጫጨቀችው
"አማን ማኪ ምን መሰለሽ እያለ ሊያናግራት ሲጠጋ
""ማኪ ነው ያልከው የት የምታቃትን ነው። ከሀዲ አስመሳይ የዛ አልበቃ ብሏቹ ዛሬም ከእኛ ምድነው ምፈልጉት ንገሩን። እንደዚ አይነት ሰው አትመስሉኝም ነበር። አዝናለው ብላ ከስሩ ተልይታ ለሀኒ ውንድም ደውላ ቤተሰቦ እየተሯሯጡ መጡ ልክ ማክዳን እንዳዬ ማኪ ሀኒስ የት ነች ምን ሆነ ነው። እናት ልጄ ምን አገኛብኝ ላዳፍታ ውታቹ ከእናት ከአባት የሀኒ ወንድም ባሰ ቲጂና ሜሮንም መጡ ሀኒ ድንጋጤ ስትውድቅ በሩ ስለመታት ግንባሯ አካባቢም ደምታ ነበር።

ከክርሉ ኪሩቤል ዶክተሮቹ አስወጡት ልክ እንዳዩት አሌክስ ምድነው የሆነችው ከውንድሞን አይን የሚውርደው እንባ ኪሩቤል እንዳየ መቆጣጠር አቃተው ማክዳ አሌክስ ነው ያልከው ኢሱ ስህል አማን የማክዳን እጅ ይዞ ከቦታው ገለል አደረጋት።

ሁሉም ግራ ተጋብ ኪሩቤል ከልብ አዝኖ የሰራው ስራ. የሀኒን ሁኔታ ሲያይ እንባውን ያነባ ጀመር።
እና ምነው ልጅ ከባድ ነገር ነው እንዴ ንገረን ቁርጣችንን እንውቀው።
እየተከራከሩ እያለ የዶክተሩ ከክፍሉ ሲውጣ እናት ልጄ ሀኒ እንዴት ነት ብለው ሲጠይቁ

ተረጋጉ ደና ነት እራሷን ስታ ስለውደቀች ነው። አሁን ትነቃለች ብሎቸው እንደሄደ እና መሬት ስመው ኪሩቤል አታልቅስ ይሄው ደና ናት ብለውናል እያሉ እየደባበሱት ያባብሉት ነበር እሱ ግን ተቀምጦ እራሱን አዘቅዝቆ ያለቅሳል.።
ትግስት አለክስ በቃክ ሁሉም የሱን ሁኔታ አይተው አዘኑለት ከግማሽ ሰዓት በኃላ ሀኒ ነቅታ ክፍሉ ውስጥ ከኪሩቤል ና አማን ና ማክዳ በስተቀር ሁሉም አሉ።
አይታቸው ከተኛችበት ተነስታ ማክዳ እና አማን ፈንጠር ብለው ይጨቃጨቃሉ።

"ኪሩቤል እራሱ ይዞ አዘቅዝቆ ቁጭ እንዳለ
ሀኒ እንዳየችው ግን ለምን እያለች እግሩ ስር ተበርክካ ባለፈ ታሪክ እኔ ያ የልጅነቴ እንዲያ ከማንም በላይ የሚውደኝ ሰው እንኳን ስገላምጠኝ የማይውድ ልጅ ዛሬ በውንድሜ ከስንት አመት በኃላ እኔ ላይ እንዲ መልስልኝ እያለች ታነባው ጀመር አሁን ሁሉም ተሰበስብ

ግራ በመጋባት ስሜት ስያዩ ማክዳ መቋቋም አቃታት ጥላቸው እየሯጠች ከሆስፓታሉ ውጣች

ሀኒ ከልቤ ነው ያፈቀርኩሽ ባደባባይ የማፈቅራት ነገ የልጆቼ እናት የሆነችው ብለክ እንዲያ የጨፈርነው። ካንቺ ልጅ እፈልጋለው እንጋባ ያልከኝስ አታቀርቅር እየኝ ተሸንፉልሻለው ያልከኝሽ ግን አላሳዝንህም አንተን አጥቼ ምን ውስጥ እንደነበርኩ አታቅም አንተ እኮ ማንነቴ ነክ። የምውደው የልጅነቴ እያልኩ ስምህን አስሬ ስጠራ እንኳን....ኪራዬ ንገረኛ የት ልግባ ለምን ለምን ሀኒ እኮ ነኝ እየኝ ያቺ የምትሳሳላት እያለች ስትነግረው ሁሉም ደነገጡ

አባት ደንግጠው ምን እኮ አንተ ኪሩቤል ነክ። ምነው ልጄ አባትክ እንኳን ይቅር ለእግዜር ተባብለን ነው የተለያየነው ። ሀኒ እኮ ነች እረሳካት በልጅነታቹ ምን በማታውቁበት ያለሷ የማትበላ እሷም እንደዛ በርግጥ ልክ ነክ ግን ሀኒ ምን በደለች ።

ቲጂ ንገሪው ሀኒ በሱ ናፍቶት እንደተቀጣች ማም ንገሩት ምን እንደሆንኩ

አቃተው ተነስቶ ሲሄድ
ሀኒ እዛው የተበረከከችበት እንባዋን እያዘራች ኪራዬ ስትለው እንደመቆም አለ።
"እባክህን በቀልን ተውና አብረን እንሁን ስለሁሉም ፈጣሪ ያውቃል አንተ እኮ ታስታውሳለክ ከሰው ስጣላ አይደለም በድዬ በድለውኝ እንኳን #ይቅርታ ጠይቂ ስትለኝ አልነበር። ያኛው ኪሩ የት ሄዶ ነው ለበቀል እንዲ የተነሳሳከው መልስልኝ ...

ግን ምን ሳይመልስላት ጥሎት ሄደ።
አማን እየሮጠ ተከተለው
ሀኒ ቤተሰቦቾ ይዘዋት ወደቤት
የመኝታ ቤቶን ቆልፋ ማልቀስ ጀመረች ማንም ቢለምናት ምን ቢሎት አልከፍት አለቻቸው ።
ያቀን ....


ይቀጥላል ...

share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
የሆድ ነገር...
ቋንቋና ስነ ልቦና የበዓሉ ግርማ እይታ
=======================
"...እዚህ ሀገር የህልውናችን ማእከል ሆድ ነው። ሰው ሲናደድ አንጀቱ ደበነ ወይም ሆዱ አረረ፤ሲደሰት አንጀቱ ራሰ፤ ሲያዝን ወይም ሲጨነቅ፥አንጀቱን በላው፥ አንጀቱ ተላወሰ፥ ሆዱን ባር ባር አለው፥ ከውሳኔ ሲደርስ፥ አንጀቱ ቆረጠ፤ ትእግስት ሲያሳይ - ሆደ ሰፊ ነው፤ሆድ ከሀገር ይሰፋል ብልጥ ሲሆን ሆዱ አይገኝም፤ ሲወድ ካንጀቱ ይወዳል፤ ሲጠላም እንደዚሁ፤ አንዱ ሌላውን ማሞኘት ሳይችል፥ ሆድ ለ ሆድ ይተዋወቃሉ፤ ብቻ ምናለፋችሁ ስናስብም፥ ስንወድም፥ ስንጠላም፥ ስናዝንም፥ ቂም ስንይዝም፥ ብልጥ ስንሆንም፥ ሁሉም በሆዳችን ነው!...

ተረቶቻችን ከሆድ አይርቁም። ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል። እስቲ ጨምሩበት።....የእናት ሆድ ጅንጉርጉር ነው።...ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው።......ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ
....

...በሆዳችን ስለምናስብ ይሆን ነው ጭንቅላታችን የማይሰራው?"

ከበዓሉ ግርማ
የቀይ ኮከብ ጥሪ ገፅ 251-252 የተወሰደ

የምናስበው በቋንቋችን ነው። ቋንቋችን ምን አይነት ስነ ልቦናዊ ተጽእኖ አሳድሮብን ይሆን????


@Write_Event
🌿" የምትናገሩት ከሀሳቦቻችሁ ጋር ሰላም መፍጠር ሲያቅታችሁ ነው ። በልባችሁ ውስጥ ባለው ጭር ያለ ስፍራ መኖር ሳትችሉ ስትቀሩ፣ በከናፍሮቻችሁ ውስጥ ትኖራላችሁ
ንግግርም አቅጣጫን የሚያዛንፍ ጊዜ ማሳለፊያ እና መደሰቻ ነው ...እናም በአብዛኛው ንግግራችሁ(ወሬያችሁ) ውስጥ የማሰብ ችሎታችሁ በከፊል ይሞታል ። ሃሳብስ በህዋ ላይ እንደምትበር ወፍ አይደለምን ?
በፍርግርግ ብረት በተሰራ የቃላት መረብ ውስጥ ከተዘጋባትስ ክንፎቿን ትዘረጋ እንደሆን እንጂ ልትበር ትችላለችን...?
በእናንተ መካከል ለብቻቸው መሆንን በመፍራት ወሬኞችን የሚፈልጉ አሉ ። ምክንያቱም የብቸኝነት ፀጥታ ለአይኖቻቸው እርቃኑን የቀረውን ራሳቸውን አጋልጦ ያሳያቸዋልና ሁሌ ከእሱ ለመሸሽ ይፈልጋሉ...ደግሞም ሳያውቁት ወይም ቀደም ብለው ሳያስቡበት የሚያወሩ እና በዚህ ንግግራቸው ራሳቸው እንኳን የማያውቁትን እውነት ገልጠው የሚያሳዩም አሉ...
በውስጣቸው እውነትን የያዙ ፣ ነገር ግን በቃላት የማይናገሩትም አሉ ። እንደዚህ ባሉት ሰዎች ልብ ውስጥ የእውነት መንፈስ ዜማ በሚደረድር ትርታዊ ፀጥታ ውስጥ ይኖራል...
ጓደኞቻችሁን በመንገድ ዳር ወይም በገበያ ቦታ ስታገኙዋቸው በውስጣችሁ ያለው መንፈስ ፣ ከናፍራችሁን ያንቀሳቅስ ፤ ምላሳችሁንም ይምራ ። የጽምፆቻችሁ ድምፅም ለጆሮዋቸው ጆሮ ይናገር..የወይንን ጣዕም ሁሌ እንደሚያስታውስ ሁሉ ፣ የጓደኞቻችሁ ነፍስ የልባችሁን እውነት ጠብቆ ያቆያል አይደለምን? ቀለሙ(ጣዕሙ) በተረሳ ጊዜ ግን ዕቃውም አይታወስም ። "

ካህሊል ጂብራን -
••●◉Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
@Write_Event
@Write_Event
በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው።ሕይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብና ተስፋን የተሞላች ናት! በዚህ ዓለም ሁሉ ነገር አበቃ፤አከተመ ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል፤ የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር፤ዙሪያችን ጭው ያለ በረሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሬያለሁ።ዕድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳ ቢሆን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና !

#ከሰበዝ
••●◉Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════

@Write_Event
@Write_Event
ጥሬ ጨዉ
=========
መስለዉኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰዉ ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸዉ
ጥሬ ጨዉ…ጥሬ ጨዉ ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት መቀየጥ
ገና እሚቀራቸዉ
“እኔ የለሁበትም!”
የዘወትር ቋንቋቸዉ።
___
ደበበ ሰይፉ


@Write_Event
@Write_Event
ፍቅር የሚሰጠውንም የሚቀበለውንም ይፈውሳል።

ሁለቱ ወንድማማቾች በቤተሰቦቻቸው እርሻ ላይ አብረው ይሰራሉ። አንደኛው ያገባና ብዙ ቤተሰብ ያለው ሲሆን ሌላኛው ገና ያላገባ ነበር። ሁልጊዜ በቀኑ መጨረሻ ላይ ወንድማማቾቹ ምርቱን እና ትርፉን ሁሉንም ነገር እኩል ይካፈሉ ነበር።

አንድ ቀን ብቻውን የሚኖረው ወንድም ለራሱ "ምርቱን እና ትርፋን እኩል መካፈላችን ትክክል አይደለም። እኔ የምኖረው ብቻዬን ነው ፤ የሚያስፈልገኝ ጥቂት ነው።" ብሎ አሰበ። ከዚያ በእያንዳንዱ ምሽት ከራሱ ጎተራ አንዳንድ ጆንያ እህል ይወስድና በእርሱና በወንድሙ ቤት መካከል ያለውን ሜዳ አቋርጦ በወንድምየው ጎተራ ውስጥ ያስቀምጣል።

ያገባው ወንድምም ለራሱ "ምርቱን ና ትርፋን እኩል መካፈላችን ፍትሀዊ አይደለም። እኔ ለሚመጡት አመታት የሚንከባከቡኝ ሚስት ና ልጆች አሉኝ። ወንድሜ ግን ማንም የለውም ፤ወደፊት የሚንከባከበው የለም። "ብሎ አሰበ። ስለዚህ በየምሽቱ ከራሱ ጎተራ አንዳንድ ጆንያ እህል እየወሰደ ሳያየው ወንድምየው ጎተራ ወስጥ ያስቀምጥ ነበር።

ሁለቱም ሰዎች ጎተራቸው ውስጥ ያለው እህል መጠኑ ባለመቀነሱ ለአመታት ይገረሙ ነበር። ከዚያ በአንድ ጨለማ ምሽት ሁለቱ ወንድማማቾች በድንገት ተጋጩ። ቀስ በቀስ ምን እየተከሰተ እንደነበር ተረዱ ከዚያ ሁለቱም የተሸከሟቸውን ጆንያዎቻቸውን ጥለው ተቃቀፉ።

አስተማሪ ታሪክ ነውና ለወዳጅዎ ያጋሩት

👉 @Write_Event
@Write_Event
ጠላቴ

ጠላቴን ስፈልግ፣ ከጎሮቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከሩቅ፣ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው።

ሰለሞን ሞገስ

👉 @Write_Event
@Write_Event