ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
💬
❝ቀስትህን እስከመጨረሻው ካልሳብከው ዒላማው ውስጥ እስከመጨረሻው አይገባም፤ ዕውቀትን የሚሻም ተማሪ እስከመጨረሻው የሚተጋ ብቻ ነው።❞
ሜንሲየስ

💬
❝ከመጻሕፍት አንዳንዶች የሚቀመሱ፤ አንዳንዶች የሚዋጡ፤ ሌሎች ደግሞ የሚመነዠኩም ናቸው።❞
ፍራንሲስ ቤከን

💬
❝በመመገቢያ ጠረጴዛህ ላይ መጽሐፎች ይሙሉ። ከዚያም በጣም ደስተኛ ትሆናለህ። ትራስህም መጽሐፎች ይሁኑ፤ ከዚያም ፍፁም የሠላም እንቅልፍ ትተኛለህ።❞
ፊዮዶር ዶስቶዬቭስኪ

💬
❝ዛፎች መሬት ለሰማይ የጻፈቻቸው ግጥሞች ናቸው።❞
ካህሊል ጂብራን

💬
❝ንፁህ አእምሮ ማለት ሙሉ ንቃት ማለት ነው። ለዚህም ነው ንፁህ አእምሮ፣ የሚወደውን ነገር በንቃት መመልከት የሚችለው።❞
ብሌዝ ፓስካል

💬
❝አንድን ሰው ምንም ልታስተምሩት አትችሉም፤ ማድረግ የምትችሉት ነገር ቢኖር ከራሱ ውስጥ እንዲፈልገው መርዳት ነው።❞
ጋሊሊዮ

💬 💬
ጥቅሶች
@write_event
📓 ርዕስ የለውም
ኤሊያስ ሽታኹን
'
┈┈•✦•┈┈
በቀደም
አጠገቤ ሆነሽ፤ ዐይኔ አ'ይሰበር፤
ስለምሳሳልሽ፤ መች እተኛ ነበር።
ዛሬ • • •
ካጠገቤ ሄደሽ፤ ባንቺ እየተገፋኹ፤
ዘንድሮም አልተኛም፤ መቼ አንቀላፋኹኹ?
(በሁለቱም አለሁ)
ሕልምና ሐሳቤ፤ ተቀምቶ ቤቱን፤
ታዲያ ምን ሆኜ ነው?
ስትመጪም፤ ስትሄጂም፤ መንቃቴ ሌሊቱን።
ዐይኔ ተከድኖ አያውቅ፤ በደስታም በእክል፤
ንገሪኝ ዓለሜ! የቱ ነው እውነቴ? የቱ ነው ትክክል?




እየሄድሽም እንኳ
ልክ ልሁን አልሁን፤ አንቺን መጠየቄ፤ እንደዚህ ታምሜ፤
እውነቱን ንገሪኝ! ልክ ነኝ ዓለሜ?
═══════
📖 📖 📖 📖 📖

https://t.me/write_event
ለ ፈ ገ ግ ታ
😁 😁 😁

የውርርድ ሱስ የተጠናወተው ቢሊ ከሚያገኘው ሰው ጋር ሁሉ ይወራረዳል። አባቱና አጎቱ ይህን አመሉን ለማስተው የነበራቸው ምርጫ የሚያሸንፉትን ውርርድ ብቻ ከሱ ጋር በመወራረድ በመሸነፍ ብዛት ተስፋ ቆርጦ እንዲተወው ማድረግ ነበር። እናም ከቀጣዩ ቀን ጠዋት ጀምሮ ከሁለታቸው ጋር ብቻ እንዲወራረድ ቃል ያስገቡታል።

በነጋታው ጠዋት ቢሊ አጎቱ ወደ ሥራ ሲወጣ በር ላይ አስቁሞ
«አጎቴ፤ እግርህ ላይ በቆሎ እንደበቀለ በአስር ሳንቲም እንወራረድ!» አለው።
አጎቱ ውርርዱን በመቀበል አስር ሳንቲም ያስይዝና የሁለቱንም እግር ጫማና ካልሲ በማውለቅ እግሮቹ ላይ በቆሎ እንዳልበቀለ አስመስክሮ ሃያ ሳንቲሙን ይቀበለዋል።

ኋላ ላይ አባትየውን ውጭ ሲያገኘው
«ሙከራችን ሊሳካ ነው መሰል። ዛሬ ጠዋት ...» ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ አባትየው አቋርጦት
«መቼም አይሳካም ባክህ! ጠዋት ካንተ በፊት እኔ ጋ መጥቶ 'አጎቴን በአስር ደቂቃ ውስጥ ጫማውንና ካልሲውን አስወልቀዋለሁ' ብሎ ከኔ ጋር በሃምሳ ሳንቲም ተወራርዶ ነው ወዳንተ የመጣው!»

😂 😂 😂
━━━━━━━━━━
📓 የሳቅ ምንጭ
📖 📖 📖 📖 📖

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
የተስፋዬ ዛፉ
┈┈•✦•┈┈
ደበበ ሰይፉ
'
የተስፋዬ ዛፉ
ሲከረከም ቅርንጫፉ፤
ሥሩ ሲነቃቀል
ሲበጠስ ሲፈነገል፤
ጭላንጭል ስትዳፈን
ብርሃን ዐይኑ ሲከፈን፤
አንጥፌ ደርቤ ማቄን
ዘንግቻት እንቁጣጣሽን
ፀደይ አበባ ዐደዬን፤
በድቅድቁ ተቀመጥሁኝ
ላለማሰብ እያሰብሁኝ፤
የልቤን ልበ-ባሻነት ገሠፅኩኝ
ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አረኩኝ።
════════
📓 የብርሃን ፍቅር
📖 📖 📖 📖 📖

https://t.me/write_event
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኤልያስ ሽታሁን ድንቅ ግጥም በሳቅሽልኝ ቁጥር ከ ርዕሰ የለውም የግጥም መድብል የተወሰደ
እኔ ባፈቅርሽም .......

ቀለሜ እስኪጠቁር ስጋየ እስኪከሳ
እጅግ ባፈቅርሽም ሰው እስከምረሳ
የወገቤን ስፋት የልቤን ብርታቱን
እኔ አውቃለሁና የውስጤን ምኞቱን
ሀቁን ላሳውቅሽ ልንገርሽ እውነቱን

ከራሴ አብልጬ ምን ብሳሳልሽም
ከሰዎች አብልጬ ምንም ብወድሽም
ግና
አግብቼሽ ሊቆጨኝ ኃላ ሊፀፅተኝ
የኔ የሬሴን ክፍተት አንቺ ላትሞይልኝ
እኔ አላገባሽም ከቶ እንዳጠብቂኝ::

ከሴት ሁሉ በላይ እጅግ ብቀርብሽም
እስከመቼም ድረስ ከቶ ባረሳሽም
እኔ ባፈቅርሽም ግን አላገባሽም!!

@write_event
እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ።

በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ።

አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ።

በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ  መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ።

በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ  ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል።  ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው።

በኖረበት  ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ።

አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር።

ይህ ታሪክ ለአብዛኞቻችን አስተማሪ ይመስለናል ።
በውስጣችን አዳፍነነው ያስቀመጥነው ተሰጥኦ እንዳለ እናምናለን ።

ይህን ተሰጥኦ ከውስጣችን ጎትቶ የሚያወጣልን ውጫዊ አካል አንጠብቅ ።

የተሰጠን ቀን ዛሬ ነውና ለማናውቀው ነገ ቀጠሮ አንስጥ ።

ስለ ነገ ማንም አያውቅም። የተሰጠን ዛሬ እንደሆነ አውቀን የተዳፈነውን ችሎታችንን አውጥተን ለሌሎች የብርሃን ችቦን እንለኩስ።

JOIN

@write_event
@write_event
@write_event
አዕምሮ ተምሮ ልብ ካልተማረ በጥቅሉ ትምህርት አይደለም!
               -- Aristotle --
@write_event
ቅምሻ 😍

በዚህ ምድር ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ (ያለምንም Qualification) ጥሩ የሆነው ነገር ምንድ ነው ?" ሲል ይጠይቃል ኢማኑኤል ካንት የሞራል ፍልስፍናውን ሲጀምር ። ለዚህ ጥያቄ ካንት እራሱ መልሱን እንዲ ሲል ይሰጠናል ።

#ገንዘብ!? አይደለም ፤ ገንዘብ ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ነገር ስናውለው እንጂ ገንዘብ በራሱ በተፈጥሮ ባህሪው ጥሩነት የለውም ።
# ዕውቀት!? ዕውቀት አይደለም ፤ እውቀት ጥሩ የሚሆነው መልካም ሰው ሲያገኝ ነው ።

#ጉብዝና(Courage)!? እሱም አይደለም ፤ ጉብዝና ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ዓላማ ሲሆን ነው ። ለምሳሌ ሂትለር ጎበዝ (Couragous) ነው ። ሆኖም ግን ፣ የእሱ ጉብዝና መጥፎ #ጉብዝና ነው ።
# እና ታዲያ ምንድ ነው? ለካንት መልሱ አንድ ነው~በዚህ ዓለም ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በራሱ መልካም የሆነው ነገር አንድ ብቻ ነው ፤ እሱም "በጎነት ወይም ቅንነት /Good Will" ነው። (Kant 1987 ፡ 7)
ዕውቀት ፣ በጎነትና ጉብዝና ቅንነት ላይ ካላረፉ አደገኛ ይሆናል ። የፍልስፍና ትምህርት ።

#ቅን እንሁን-

@write_event
ለፈገግታ 😂

" ነገራችንን "አትንሳን
(አሌክስ አብርሃም)

ወታደራዊ ሰላምታ ሰጥቻለሁ! ! እኔ
ጓድ ኮሮኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም ብሆንእና በአሁኑ ሰአት
ኢትዮጲያን የማስተዳድረው እኔ ብሆን ኖሮ የሚከተሉት አብዮታዊ እርምጃዎች እወስድ
ነበር,,,,,,የእናተንም ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል!!

☹️1ኛ, መሰለ መንግስቱ የሚባለውን ሰውየ በክብር አባርሬ ያንን
ቢራ የወለደው የሬዲዮ ጣቢያ ፍቅር ይልቃልና ገነነ መኩሪያ
(ሊብሮ) በጋራ እንዲያስተዳድሩት እሰጥ ነበር! !
2ኛ, " አቤ ከቤ ከአሰላ " የሚባለውን ሰውየ የአምስት አመት
ስልክ ያለመደወል መአቀብ እጥልበት ነበር! !

3ኛ,....

4ኛ, ለቀጣይ ሁለት አመታት የአማርኛ ፊልሞች እንዳይሰሩ እገዳ እጥል ነበር!የመድረክ
ቲያትሮችም በእጥፍ እንዲጨምሩ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፍ ነበር
5ኛ, ማንኛውም የሬዲዮ ጣቢያ የስፖርት ዜናም ይሁን ትንታኔ
በቀን ከ5 ደይቃ ለማይበልጥ ጊዜ ብቻ እንዲያቀርብ እንዲሁም በቀን ከ3 ዘፈኖች በላይ
እንዳያቀርብ አስገድድ ነበር!
6ኛ, በኢትዮጲያ ጥራታቸውን የጠበቁ ግዙፍ ( በመቀበል
አቅማቸውም በትምመህርት ጥራታቸውም) 10 ዮኒቨርስቲዎች ብቻ በማስቀረት ሌሎቹን
የሱሰኞች ማገገሚያ እንዲሆኑ አዝ ነበር!
7ኛ, ሁሉም (( ሴቶች )) ከአምስተኛ ክፍል ጀምሮ በግድ
ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስደዱ እና ( ሴቶች ከሄዱ ወንዱም
እየተጋፋ ይገባል:)) ሁሉም ዜጋ ቢያንስ በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤቶች ቆይታው
ክላሲክ የሚባሉ የአገር ውስጥም ይሁኑ የውጭ መፅሃፍትን እንዲያነብ አስገድድ ነበር,,,
ግዙፍ የመፃህፍት ማከፋፈያዎችንም እከፍት ነበር
8ኛ, አዲሱን የባቡር ሃዲድ ድልድይ ምናምን አስፈርሸ አዲስ
አበባን እጅግ በሰፋፊ መንገዶች እሞላት ነበር
9ኛ ከዚህ በኋላ አዲስ አበባ ላይ ከአራት ፎቅ በላይ ህንፃ
እንዳይሰራ አዝ ነበር,,,, ባለመስተዋት ህንፃዎችማ ድርሽ
አይሏትም!
10ኛ ቢራና የአልኮል መጠጦች ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል ቢራ መጠጣትንም
መጥመቅንም በአገራችን እጅግ በጣም ውዱ ነገር አደርገው ነበር እንዲሁም
11ኛ, ማታ ማታ በቲቪ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ከሌለ በስተቀር
ዜና እንዳይነበብ አደርግ ነበር !!
ከወራደራዊ ሰላምታ ጋር ገጭ!!

@write_event
@write_event
@write_event
"እጅህ የሚያገኘውን ስራ ሁሉ በሙሉ ሀይልህ ስራው ፣ልትሄድበት ባለው መቃብር ውስጥ መስራትም ሆነ ማቀድም የለምና"።

⚜️ ጠቢቡ ሰለሞን⚜️

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
😂😂ለፈገግታ😂😂

‹‹ቲማቲም ወርውሮ ትላንትና አንድ ሰው
አንዱን ጓደኛውን ግንባሩን ገመሰው››
(አሌክስ አብርሃም)
🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅
የሆነ ጊዜ ሃላፊየ ወክለውኝ ሃላፊ ሁኘ ስሰራ . . . ሁለት ወጣቶች ቢሮየ መጡ . . .💃🕺
ሴትና ወንድ ናቸው ! ሁለቱም መስሪያ ቤቴ አካባቢ ካለ
የሃብታም ልጆች ትምህርት🏢 ቤት ነበር አመጣጣቸው . . .
የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪወች ሲሆኑ የሴቷ አለባበስ ያለማጋነን የኦስካር እጩ
አስመስሏታል . . .በዛ ላይ ኑሮ ምችት ያላት ቆንጆ . . .በእንግሊዝኛ አፏን ስለፈታች ነው መሰል አማረኛ ገደል ሁኖባት ቃላትን እየፈለገች ነው
የምትናገረው …ወንዱም እንደልጅቱ ባይሆንም ሽክ ብሏል ….

👱‍♀‹‹ የመጣነው ላሰብነው ፕሮግራም ስፖ….ንሰር እንድትሆኑን ነው ››
አለች
ልጅቱ ብዙ ጊዜ ወደቢሮ ብቅ እያሉ ስፖንሰርየሚጠይቁን የቀበሌ
የወጣቶች ..የሴቶች …የምንትስ ሰወች ወይም የተቸገሩ ሚስኪኖች ስለነበሩ ‹‹ስፖንሰር ›› የሚለው ፅንሰሃሳቡ ወይ የድሆች ወይ
የፖለቲከኞች እየመሰለኝ ከመጣ ቆይቷል . . . እነዚህ ምቾት ያሰቃያቸው ልጆች እንዴት ‹‹ስፖንሰር ሁኑን ›› እንዳሉ ገርሞኝ ጉደዩን ጠየኩ

👱‍♀‹‹ ዩ ኖ . . . በትምህርት ቤታችን ‹የቲማቲም ቀን🍅› ልናከብር አስበናል . . . ዛት ማች ብዙ ብር ምናምን የሚፈልግ አይደለም …››

👨‍💼‹‹የቲማቲም ቀን 🍅? ›› ስል ጠየኩ

👱‍♀‹‹ያ …በቃ ተማወች የሆነ ሰአት ይወስኑና ግቢ ውስጥ ቲማቲም መወራወር ምናምን በጣም ያዝናናል ...ውጭ ምናምን የተለመደ ነው
..እናም በጎ ነገሮችን ወደሃገራችን ብናስገባ ቀስ እያለ ከትምህርት ቤት ወደሁሉም ትምህርት ቤቶች ከዛ በአገር ደረጃ በቃ የቲማቲም ቀን
ተብሎ በአመት አንዴ ይከበራል . . . ››
ሁለቱም ገርመውኝ ተራ በተራ እያየኋቸው

👨‍💼‹‹እና ቲማቲም🍅 እየተወራወራችሁ ቀኑን ልታከብሩ ነው . . ?>>

👱‍♀<<YAp>>

👨‍💼<<.አላማው ግን ምንድነው ?››

👱‹‹ ጀስት ፈን! …እና ደግሞ አለ አይደል ሌላው <ወርል ድ> በፋሚን ድሮውውት ምናምን ነው ኢትዮጲያን የሚያውቃት ..የቲማቲም ቀን
በማክበር ግን አገራችን ጀስት ከእርሃብ እንደወጣች ለማሳየት … በዛ ላይ ቦንብ ምናምን ድንጋይ የሚወረወርበት ጊዜ እንዳለፈና ፒስ
መሆናችንን ለማሳየት ››
አለ ወንዱ ልጅ

👱‍♀‹‹በተጨማሪም ›› አለች ሴቷ ‹‹በተጨማሪም አሁን ያለንን የአበላል ሃቢት አለ አይደል ፒፕሉ ስጋ ቁርጥ ምናምን ያበዛል .. ይሄ ለብዙ በሽታ
ስለሚያጋልጥ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲመገብ ፕሮሞት ማድረግም ይቻላል
›› ስትል አብራራችልኝ !

👨‍💼ጎበዝ ተበላን ! እነዚህ የሃብታም ትምህርት ቤቶች ባለራእይ ትውልድ እያመረቱ ነው . . . ትክዝ ብየ አየኋቸው . . . ደመወዝ ጨምሩልኝ እያለ
ሁለት ወር ቢሮየ የተመላለሰው የአራት ልጆች አባት ጋሽ ወጋየሁ ቢሮየ በር ላይ ቁሞ ይታየኛል ልጆቹ እስኪወጡ እየጠበቀ . . . ሁለት መቶ
ብር ጨምሩልኝ ብሎ ሁለት ገፅ ማመልከቻ ፅፏል …ሚስኪን የቲማቲም ቀን ሲከበር ይሄ ሰውየ ‹‹የአበላል ሃቢቱን ያስተካክል ይሆን ? ››
እላለሁ . . .

👱‍♀‹‹ አስር ሽ ብር ምናምን ስፖንሰር ብትሆኑን . . . ›› ልጅቱ ቀጥላለች . . .


እኔም በዓሉ ላይ ብገኝ እና ቲማቲም እነዚህ ልጆች ላይ እንዲሁም መምህራኖቻቸው ላይ ብወረውር ብየ ተመኘሁ ...እና በተለይ
ወላጆቻቸው ላይ ....ግን እኔ የምወረውረው ቲማቲም በጣሳ የታሸገ መሆን አለበት . . . ግንባር ግንባራቸውን !
ቲማቲም ወርውሮ ትላንትና አንድ ሰው
አንዱን ጓደኛውን ግንባሩን ገመሰው
ደነገጥኩ አይቸ ሲንዠቀዠቅ ደሙ
በጣሳ ውስጥ ነበር ለካስ ቲማቲሙ …..እንዲል ገጣሚው !
*
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
*
ማንም ሰው በዛ ቦታ ቢሆን ተመሣሣዩን ላለማድረጉ በፍፁም ታማኝነት ራሱን እስካልጠየቀ ድረስ መፍረድ የለበትም!
            -- Viktor Frankl --

JOIN US 🙏
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
እምነት - ክህደት - እውነት
┈┈┈•✦•┈┈┈
ኤፍሬም ስዩም
'
የምናምን ዕለት
ፀሐይ ትዞራለች
ባስራ-ሁለቱ መስኮት ገብታ ትወጣለች

የምንጠይቅ ወራት
መሬት ትዞራለች
ያማኝን ልቦና.. ሽፍታ ታደርጋለች

በገጣሚ ምናብ
ከንቱ የ'ምነት ዓይን ከንቱ ፍልስፍና
ሰማይ ነው የሚዞረው። ...
ምክንያቱም..
የትላንቱን ኮከብ ከትላንቱ ቦታው
ዛሬ ላይ መች አየው? ...
════════
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
════════
ኤፍሬም ስዩም

ጊ ዜ
┈✦┈
እግዜር
በምድራችን የተከላት
ጊዜ የሚሏት - ጽጌረዳ
ገና እንኳን ሳታብብ ገና ሳትፈነዳ
ጨለማዋ እሾህ
ጨክኖ ቢወጋት
ወግቶ ቢያሸንፋት
የልቧን አወራች
እውነት ተናገረች ...
ነገ በማለዳ ... ዛሬ ሟች ነኝ አለች።
════════
📓 ኑ ግድግዳ እናፍርስ
join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ውዴ!
ሂድ ባልሽኝ መንገድ
ቃልሽን አክብሬ ከፊትሽ ሄጃለሁ፤
ግን
የመውደዴን ቅኔ ለልብሽ ትቻለሁ ፤
እናም አንቺ
ለቅኔው ፍቺ ፈልገሽ፣
ሂድ ባልሽኝ መንገድ ና ያልሽኝ ለታ፣
ከመንገድ ቆሜያለሁ
ሌላ ቅኔ አግኝቼ ቅኔሽን ሳልፈታ።

==========
መላኩ ደምሴ
ከ"ገላ ና ገላ' የግጥም መድብል መፅሐፍ
2013
==========
https://t.me/write_event
ዝሜን እጮኻለሁ
============
ቃል እስከሚያልቅብኝ
ቃልን እስክኾነው...
የምጮኸው ኹሉ ፣ ታላቅ ጥሞና ነው።



=======
ዲበኩሉ ጌታ
ከ"ነፍስ ቦታ"
========

JOIN & SHARE

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ቅኝት
____
አንድ ነው ክራሩ...
የጅማት ነው ክሩ...
የሚወጣው ዜማ ለየቅል የሆነው
ቅኝቱን ስንቃኝ...
ያንተ አንቺ ሆዬ የኔ ትዝታ ነው።

========
በረከት አበበ
ከ"ሰው ከሆሳዕና እስከ ስቅለት " የግጥም መድብል።
___

JOIN & SHARE
___
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event