።ፍቅር- ፈራን:ጠላን።🖤
"ፈራን"🖤
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን
ሌሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
https://t.me/write_event
"ፈራን"🖤
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን
ሌሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
https://t.me/write_event
Telegram
ቃላዊ
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot

የወደፊት ሲደምቅ!
“ለወደፊቱ ራእይ የሌለው ሰው ሁል ጊዜ ወደኋላው ይመለሳል” (Kevin Gates)
ካለፈውና ካከተመለት ነገር ትምህርትን አግኝቶ ወደፊት ከመገስገስ ይልቅ እሱን እንደገና እያሰቡ የመጨናነቅ፣ የመረበሽና ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ የሚያጠቃችችሁ ከሆነ ምናልባት የወደፊት ራእይ ያለመኖሩ ምልክት እንዳይሆን ጠርጥሩ፡፡
የወደፊታችሁ እየፈዘዘ ከሄደና ማየት ከተሳናችሁ የኋላችሁና ያለፋችሁት ነገር መድመቅና መጉላት ይጀምራል፡፡ በሌላ አገላለጽ የአንዱ መድመቅ የሌላኛው መደብዘዝ ነው፡፡ ምርጫው ግን በእጃችሁ ነው፡፡
ያለፈ ጉዳት … ያለፈ የተሳሳተ ውሳኔ … ያለፈ ክስረት … ያለፈ ተጀምሮ የተቋረጠ ነገር … ያለፈ ጎድቶንና ትቶን የሄደ ሰው … እየተመላለሰ ስሜታችሁን ቀውስ ውስጥ የሚጨምረው ከሆነ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀርፍላችሁ ብቸኛ ነገር የወደፊታችሁን ራእይ ማየትና እሱ ላይ ማተኮር ነው፡፡
የወደፊት ራእያችሁ ካለፈው ታሪካችሁ ሊጠነክርና ሊደምቅ ይገባዋል፡፡
ያለፈው ታሪካችሁ ከሚሰጣችሁ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይልቅ የወደፊታችሁ የሚሰጣችሁ የመጓጓት ስሜት ሊያይል ይገባዋል፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
@write_event

ለልደትህ ይድፋህ!?
(አሌክስ አብርሃም)
ወገኖቸ መልካም ልደት የሚሏችሁን ሁሉ አትመኑ! አንዳንዶች የልደት በግ አልብሰው ቀበሮ ሞት ይልካሉና😀ከፈቀዳችሁልኝ ልምዴን ላካፍል? አመሠግናለሁ! በጣም እንደምትወደኝ ዘላለም ብኖር ደስ እንደሚላት የነገረችኝ ልጅ ባለፈው አመት ልደቴን ሳከብር በፖስጣ የታሸገ ስጦታ አመጣችልኝ...ፖስታው ባዶ ስለሚመስልና ውስጡ የሆነ ወረቀት ነገር ስለነበር በቃ ዶላር ይሆናል ብየ አሰብኩ... ሰዎች ስጦታ ለመምረጥ ለመግዛት ጊዜ ካጡ ካሹን መስጠት የተለመደ ነገር ነው! (ዶላርን በስሙ ብቻ የምታውቁና ነክታችሁት ለማታውቁ እኔ አሁኑኑ.......አብራራላችኋለሁ! ዶላር /አንዳንዶች ዳላር ይሉታል / እንደምላጭ የሳሳ ግን እንደምላጭ ስለታም የገንዘብ አይነት ነው ! ከአገራችሁ ጋር የተያያዛችሁበትን ጨምሮ የማይቆርጠው እትብት የማይላጨው ፀጋ የለም😀)
እና ቆንጆ አይኖቿን እያስለመለመች "ክፈተዋ " አለችኝ ፖስታውን ! ስከፍተው ትኬት ነው ... አይኔን ማመን አልቻልኩም ....Go Skydiving on your Birthday...
Jump two miles up with Amazing Views... ይላል! አቻ ትርጉሙ " ለልደት ቀንህ ለምን ሶስት ኪሎሜትር ወደሰማይ ወጥተህ ከአውሮፕላን ዘለህ እንደዱባ አትፈጠፈጥም ለመገፍተሩ እኛ አለንልህ " ማለት ነው 😀 ያው በሉት! ትኬቱ ከፍላችሁ ከአውሮፕላን ላይ በዣንጥላ መዝለያ ነው! ለልደቴ ማለት ነው ... እኔ ማለት ነው ....በዣንጥላ ከላይ ከሰማይ ማለት ነው ...
ወ
ደ
ታ
ች
"አታካብዳ ! "
"አካብዳለሁ ! ከፍታ አልወድም አልጋ ራሱ እየራቀብኝ ፍራሽ ላይ ነው የምተኛው" አልኩ! ለነገሩ ክብደት ለመስጠት!
"ብቻህን አይደለህምኮ ...አብሮህ የሚዘል ነጭ አለ ... " ትለኛለች ጭራሽ! እንደው ቢሆን እንኳ "Where Are You From? " እየተባልኩ ከመፈጥፈጥ ...ስር መሰረቴን ከሚያውቅ ከአገሬ ልጅ ጋራ ቁልቁል እያየን "ያ ሜዳ ጎዣምን አይመስልም?" እየተባባልን አብሬ ብፈጠፈጥ አይሻልም ? ሲሆን ሲሆን እንደግብፅ ነገስታት የሆነች ቆንጆ ጋር አስተሳስረው ወደሞቴ ቢልኩኝ ሸጋ ነው!....ነፋስ ከሚያርመሰምሰው ጥቁር ፀጉሯ የሚመነጨውን የሻምፖና ኮንዲሽነር ሽታ ሳምባየን እንደሞላው ቁልቁል እንዲህ ያለም የለ እያልኩ😀 የሆነ ሆኖ በልደት ስጦታ ተጠቅልሎ ከሚመጣ ሞት ይጠብቃችሁ! እኔን አልፎኝ እዚህ ደርሻለሁ😀
#Share
#AlexAbreham
JOIN

🩸የሁለት ደቂቃ ንባብ
አትተርጉሙ!
አንድ አባት ከልጆቹ ጋር ወደ አንድ ካፌ ይገባል።ካፌው ውስጥ እንደገቡ ብዙም ሳይቀመጡ ልጆቹ መሯሯጥና እየተጯጯሁ መጫወት ይጀምራሉ።ይሄ ሁሉ ሲሆን አባት አንገቱን ደፍቶ በሀሳብ ጭልጥ ብሏል።ይሄን ሁሉ የሚመለከት አንድ ሰው በልጆቹ እንቅስቃሴ ተረብሾ ልጆቹን ስርአት የማያስይዝ ምን አይነት ቸልተኛ ሰው ነው እያለ በአባታቸውን ይናደዳል።በዚህ ብስጭት ውስጥ ሆኖ የሚሯሯጡት ልጆች ድንገት የእሱን ጠረጴዛ ነክተውት ኖሮ ያዘዘው ሻይ ልብሱ ላይ ተደፋ።ይሄን ጊዜ ንዴቱን መቋቋም አቅቶት ውደ አባትየው ሄደ።ለግጭት እየተጋበዘ ሊያንቀውም እየዳዳው”ምን አይነት የማትረባ ሰው ነህ?ልጆችህን ስርአት አታስይዝም?”ብሎ አምባረቀበት።አባትየው በረጅሙ ተንፍሶ በተረጋጋ አንደበት”ወዳጄ የልጅነት ሚስቴ የልጆቼ እናት ታማ ከምትረዳበት ሆስፒታል አሁን ከመግባታችን ተደውሎ መሞቷን ነገሩኝ።ምን ማድረግ እንዳለብኝና ለልጆቼ ምን እንደምል ግራ ገብቶኛል”አለው።ይሄን የሰማው ሰው በትልቅ ድንጋይ እንደተመታ ሰው ራሱን አመመው።
በህይወታችን ከምንሰራቸው ስህተቶች ውስጥ አንዱ ስለ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖረን በራሳችን መተርጎምና መፈረጅ ነው።ሰዎች የሆነ ነገር ሲያደርጉ ስለማይወደኝ ነው፣ ስለማያከብረኝ ነው፣ ስልክ ሳያነሱ ወይ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ሲቀሩ ደግሞ ሆም ብለው ነው ብለን በራሳችን እንተረጉማለን።የትርጉም ዋናው መዘዝ ከእውነታው አለም ያወጣንና የራሳችንን አለም እንደንፈጥር ያደርገናል።በህይወት ያሉትን ሰዎች እንገላቸውና ክፉ ናቸው አያከብሩኝም የምንላቸውን የራሳችንን ሰዎች በአዕምሯችን እንፈጥራለን።ሀሳባችንን ፊት ለፊት የመናገር ልምድ ስለሌለን በራሳችን ትርጉም በውስጣችንን እንበሰለሰላለን እንጎዳለን።መፍትሄው ምንድን ነው?
1.ምቾት ያልሰጡን ነገሮች ሲኖሩ በራሳችን ከመተርጎም ይልቅ ፊት ለፊት መጠየቅን እንለማመድ።
2.ያሰብኩትና የተሰማኝ ሁሉ ትክክል ነው ማለትን እናቁም።
3.ሰዎች በብዙ ችግርና ውስብስብ የህይወት መንገድ ያልፋሉና ለመረዳት እንሞክር።በዚህ መልኩ ጤናማ ግንኙነታችንን ማዳበር እንችላለን።
@write_event
@write_event
@write_event
ሲሞት!
ደረት መቺ አፈር ዘጋኝ
የጨከነ ሁሉ አዛኝ
ሲሞት!
ካርታ ቁማር ገባ ወጣ
እራት ምስር እስኪመጣ
ጋቢ መልበስ ድንኳን መጣል
ወጪ ማብዛት አልፏል ሲባል
ሲኖር!!
ኑሮ ከብዶ ሲደቁሰው
ሚቀምሰው አቶ ሆድ ሲብሰው
የረገጠው ሁሉ ሲመክን
ያዝኩት ያለው በኖ ሲመን
አይዞህ ያላለው በድን ስጋ
ሞተ ሲባል ያርዳል ሰንጋ
በ ኪሩቤል አሰፋ
@write_event
ደረት መቺ አፈር ዘጋኝ
የጨከነ ሁሉ አዛኝ
ሲሞት!
ካርታ ቁማር ገባ ወጣ
እራት ምስር እስኪመጣ
ጋቢ መልበስ ድንኳን መጣል
ወጪ ማብዛት አልፏል ሲባል
ሲኖር!!
ኑሮ ከብዶ ሲደቁሰው
ሚቀምሰው አቶ ሆድ ሲብሰው
የረገጠው ሁሉ ሲመክን
ያዝኩት ያለው በኖ ሲመን
አይዞህ ያላለው በድን ስጋ
ሞተ ሲባል ያርዳል ሰንጋ
በ ኪሩቤል አሰፋ
@write_event
❤1
‹‹መኪና፡)
(አሌክስ አብርሃም)
መቸስ ለአንድ ኢትዮጲያዊ መኪና ማለት ምን እንደሆነ ታውቁታላችሁ …መኪናኮ ድፍን ሁለት ሰዓት ስለተወራለት ‹‹ኧረ አሁንስ በዛ›› የሚባልለት ንብረት አይደለም …መኪና ድፍን ሁለት ሰዓት ተሰልፈን በናፍቆት የምንጠብቀው ‹‹ምፅዓት›› ነገር ነው ለእኛ ለኢትዮጲያዊያን !
መኪናኮ መንግስት ሰልፍ በከለከለበት አገር ‹‹መሰለፍ መብታችሁ ነው በየውስጣችሁ የብሶት መፎክር ይዛችሁ ተሰለፉ ›› ያለን መቶ ፐርሰንት ሳንመርጠው ለመብታችን የቆመ የማያንቀላፋ ወኪላችን ነው ….መኪናኮ ‹‹እከሊትኮ ባል አላት›› ከመባል በላይ ‹‹እከሊትኮ መኪና ያለው ባል አላት›› እስከማስባል የሚደርስ ስሙ እንደማእረግ ከማንነታችን በፊት የሚቀድም ንብረት ነው ….መኪናኮ ከወረርሽኝ በላይ በየቀኑ ስንቱን የሚረሽን አምባገነን እቃ ነው !! መኪናኮ ቁጭ ሲሉበት ወንበሩ ከፓርላማ ወንበር በላይ የሚመች ንብረት ነው ….:)
መኪናኮ በብዙ አማርኛ ፊልሞቻችን ላይ ራሱን ችሎ አንድ ገፀ ባህሪ የመሆን አቅም ያለው ‹‹ግኡዝ ታዋቂ ›› ነው መኪናኮ …..ተው እንጅ ሆድ አታስብሱኝ ወገኖቸ ….፡)
እና ከሰሞኑ አንድ ጓደኛየ መኪና ሊገዛ እኔም ላገዛዛው ስንዞር እንደነበር ነግሪያችሁ ነበር …ኧረ እናንተም በማማከር ከጎናችን ነበራችሁ …በእርግጥ አንዳንድ እህቶች ‹‹አሌክሶ የጓደኛህን ስልክ ስጠን›› ያላችሁኝ ነገር ትንሽ አሳዝኖኛል …እኔ ይሄን ያህል አመት እያሰለቸሁ ሳስተምራችሁ(እያዝናኑ ማስተማር ከሚለው የተወሰደ) አንዲት ሴት ስልኬን ጠይቃኝ የማታውቀውን ዛሬ ነጭ ይሁን ጥቁር የማይታወቅ ጓደኛየ ስልክ መጠየቃችሁ አንገብግቦኛል፡)!!(ቀልድ ነው!! መኪና በአሁኑ ሰዓት ጫማ ማለት ነው የሚሉ እህቶች ያልተገዛውን መኪና ሲያናንቁ ታየኝ …ጫማ ራሱ በአሁኑ ሰዓት መኪና ሁኖ የለ እንዴ ተው እንጅ፡)
ወደዋናው ጉዳየ ስገባ (እስካሁን አልገባህም ወይ? በእግሬ እኮ ነው የምጓዘው ቀስ ብየ ብደርስ ምን ያስገርማል…ገና ለገና ጓደኛው መኪና ሊገዛ ነው ተብሎማ ማጣደፍ ነውር ነው፡)) እና ደላላው ምን አለን … ‹‹ይሄ መኪና አሪፍ ነው በሴት እጅ ነው የቆየው›› እንዴ ምን አገናኘው ስል …ሴቶች የሚይዟቸው መኪናዎች ከአመታት በኋላ እንኳን ገና ከፋብሪካ የወጡ ነው የሚመስሉት የሚል ምላሽ ተሰጠኝ … በቃ ሴቶች መኪና ከገዙ እንደህፃን ልጅ ነው የሚጠነቀቁለት … ወላ ከባል በላይ:) ቸግሯቸውም ይሁን የተሻለ መኪና ለመግዛት ሲሸጡት ታዲያ መኪናቸው ከዱባይ የተጫነ እንጅ አዲስ አበባ መንገዶች ላይ የተነዳ አይመስልም …አለን ደላላው !
ገረመኝ ሴቶች እንዲህ ጥንቁቅ ንብረት ተንከባካቢ ከሆኑ የከተማ አውቶብሶቻችንን ሴቶች ይያዙልን ….ባቡሩን ሴቶች ይያዙልን …እንደውም ድሪም ላይነራችንን ሴቶች ያብርሩልን ታንኮቻችንን ሳይቀር ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባሎቻችን ይያዙልን ….እያልኩ አሰብኩና በኋላ ውልና ማስረጃ ለሌላ ጉዳይ ጎራ ስል አንዳንድ የተፋቱ ባልና ሚስቶች የንብረት ጉዳይ ሲጨራርሱ እና ሲለያዩ በመመልከቴ ሃሳቤን ቆም ብየ ለመከለስ ተገደድኩ....
እውነቱን ለመናገር ተፋቾቹ ሚስቶች ያማረባቸው.. ውበት ከደም ግባት ጢም አድርጎ የሞላቸው.... ተፋች ሳይሆን ሙሽራ የሚመሳስሉ ፈገግታቸው ከትዳር ሳይሆን ከቅሊንጦ የተለቀቁ የሚያስመስላቸው ነበሩ ...... ወንዶቹ ግን አንጀት የራቃቸው ... ፀጉራቸው የተንጨባረረ ... ቀበቷቸውን እንኳን በስርአት ያልታጠቁ ( ጠ/ሚንስትርኮ ቀበቶ እንኳን በስርዓት ለመታጠቅ ጊዜ አልነበራቸውም አለች ያች ልጅ፡)) በቃ ጉስቁል ያሉ ናቸው … እና ብዙዎቹ ተፋቾች ደግሞ ስለቤትና መኪና ክፍፍል ጉዳይ ነው የሚያወሩት …መቸም ፍች ያሳዝናል …ሰው አንድ አካል አንድ አምሳል የተባለ አጋሩ ጋር በጥላቻ ጎራዴ ተከፍሎ ተጥሎ ስለንብረት ክፍፍል ወገቡን ገትሮ ሲከራከር ማየት …አያድርስ ነው ( ለነገሩ ውስጡን ማን አየ!)
ታዲያ ምን አሰብኩ እኒህ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ባለመኪና ተፋች ሴቶች ›› መኪናቸው አዲስና ያማረበት የሚፈቷቸው ባሎቻቸው ግን ጎስቋላና ውሃ ውስጥ ተነክራ የወጣች ድመት የሚመስሉት በምን ምክንያት ነው ብየ አሰብኩ …. ከምር አሰብኩ ….ከአድሎ ነፃ ሁኘ ስለወንዶች አሰብኩ፡) ሴቶቹ መኪናዎቻቸውን እቤት አቁመው በአዲስ አበባ ወጣ ገባ መንገዶች ላይ ባሎቻቸውን ነበር እንዴ ሲነዱ የኖሩት?:) ብየ አሰብኩ !! እኛ አንዳንድ ኢትዮጲያዊያን ባሎች ለመኪናን የሚደረገውን ያህል እንክብካቤ ከሚስቶቻችን እንዳላገኘን ተሰማኝ … ስለዚህ የሰርጋችን ለት በመኪና የታጀብን መስሎን ተሸወድን እንጅ ለካስ ባሎች ሽክ ብለንና ተሰባስበን መኪና ማጀባችን ነበር ሰርጉ፡) የሚል ሃሳብ ሽው አለብኝ ! በዚህ የመኪና ፍቅር ሚስቴን ደውየ ‹‹ሃኒየ መኪና ገጨኝ ›› ብላት ምን ልትለኝ እንደምትችል አሰብኩ ‹‹ አንተሰውየ ግን ለምን ከጥሩ ንብረቶች ጋር ትጋጫለህ ኧረ ተው ፀባይ ይኑርህ››፡)
እና እንዲህ እያልኩ ሳስብ አንድ ባልና ሚስት እየተሰዳደቡ ንብረት ክፍፍል ወረቀታቸው ላይ ይፈርማሉ ከንግግራቸው እንደተረዳሁት ባል ያለፈለት ይችን ሴትዮ ካገባ በኋላ ይመስለኛል እና ሴቲቱ እንዲህ ስትል አሽሙር ተናገረች ‹‹ከእያንዳንዱ ስኬታማ ወንድ በስተጀርባ ጠንካራ ሴት አለች›› እድሜ ለኔ በል ከኋላህ ባልኖር ደሃ መንዳካ ሁነህ ትቀራት ነበር ይመስላል ንግግሩ
ባልም እየፈረመ እንዲህ ሲል ተናገረ ‹‹ ድሮስ ከተሳካለት ወንድ ኋላ ኋላ ከመከተል ውጭ ሌላ ምን ስራ አላችሁ ቆንጆ ሚስቶች፡)››
አንድ የዋህ የሚመስል ከጎኔ የተቀመጠ ሰው ህህህህህህህ ብሎ ሳቀና እንዲህ አለ … ‹‹ይሄ ሰውየ አሁንም ሚስቱን ያፈቅራታል››
‹‹በምን አወክ አልኩት›› ተገርሜ እያየሁት
‹‹ሚስቱን እየተፋቱም ቆንጆ ይላታል ህህህህህህህ›› ከዚህ ጅል ወንድ ጀርባ ምናይነት ሴት ትኖር ይሆን ብየ እያሰብኩ ዘወር ስል ከኋላየ ቆንጅየ ልጅ ቁማለች ‹‹ ስኬታማ ሆንኩ እንዴ›› ብየ አሰብኩና ወዲያው ከጎኔ የቆመው ሰውየ ጅልነት የተጋባባኝ መስሎኝ በውስጤ ህህህህህህህ ብየ ሳኩ ! የሆነ ሁኖ አንዳንድ ሴቶች ከሚስትነት በላይ የሹፍርና ተሰጥኦ እንዳላቸው ጠረጠርኩ …ይሄ ጥሩ ሃሳብ ነው… ከሹፌር ሴት ኋላ ተሳፋሪ ወንድ ይኖራል ይሄም የተፋቹን ባል አሽሙር ውድቅ ያደርገዋል …
በነገራችን ላይ የሚፈታት ሚስቱ ቆንጆ ነች …እንደውም ለፊርማ ስክርቢቶ ሳቀብላት የሚያምር ፈገግታዋን አሻረችኝ ….ባልየው በግልምጫ አንስቶ አፈረጠኝ ‹‹እየተፋታም ይቀናል እንዴ ..ወይስ ፈገግታዋንም በውልና ማስረጃ በኩል ግማሹ ይገባኛል ብሎ ሊረካከብ አስቧል ይሄንንስ እንኳን ፈታችው›› …በየ ሳልጨርስ...
ወዲያው ይች ቆንጆ ሚስቱ እኔ ያዋስኳትን እስክርቢቱ ፈገግ ብላ ላላዋሳት ልጅ ስትመልስ አየሁ ቀልበ ቢስ!...ደግሞ እንጅ የልጁ …ያላዋሰውን ስክርቢቶ ቆንጆ ሴት ስለሰጠችው ብቻ ካለሃቁ ፈገግ ብሎ ይቀበላል እንዴ …ሆሆ !ይሄ ወረቀት አቀብላ ‹‹ፈርም›› ብትለውም ምንድነው ሳይል ነው ፊርማውን የሚገጠግጠው! ‹‹የዞረባት ይችንስ እንኳን ፈታት›› አልኩ፡) ከእያንዳንዷ ቆንጆ ሴት ጀርባ ያላዋሳትን ስክርቢቶ ለመቀበል ያሰፈሰፈ ወንድ አለ ለካ !!
ሀህሀህሀህሀህሀህሀህ አለ ይሄ ጅል !!
እውነትም ህህህህህ ወደው አይጀሉ !!
@write_event
@write_event
@write_event
😍

ጠበኛ እውነቶች
ደራሲ:- ሜሪ ፈለቀ
"እናትሽ በጠና ታማለች። እባክሽ ልታይሽ ትፈልጋለች።"
ለአራተኛ ጊዜ የተላከልኝ መልዕክት ነው።
"እስካሁን አልሞተችም እንዴ? ለምን ታጓጓኛለች? አንዳችሁ እንኳን ምናለ ‘ሞተች’ የሚል ብስራት ብታሰሙኝ?"
"በስመ አብ ወ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ!! (ገዳዳ መስቀል በሰራ እጁ እያማተበ) ምነው ልጄ? ምን የሚሉት ጭካኔ ነው? ደግም አይደል! እግዜርም አይወደው።"
መልሴ አንገሽግሾታል። ሀምሳ ዓመት የሚያልፈው ሰውዬ ነው። የወለደችኝ ሴትዮ የነፍስ አባቷ ነው።
"በናትህ ከቤቴ ውጣልኝ!!"
"ምነው ልጄ? እግዜር የሰጠኝን ሹመት ባታከብሪ በእድሜ አባትሽ አልሆንም?" የሚናገረው ቃል የለዘበ ይሁን እንጂ ቀይ ወጥ የመሰለ ግለታም ዓይኑ እንደተጠየፈኝ ያሳብቅበታል።
እድሜውን ሳይሆን የለበሰውን የቤተ ክህነት ልብስ ባከብር ደስ ባለኝ ግን ለባሹ ልብሱን እንጂ ልብሱ ለባሹን እንዴት ሊያስከብረው ይችላል? ልብሱ ይሄን ከንቱ ሰውዬ እንዴት ክቡር ሊያደርገው ይችላል? መሆን የነበረበት ልብሱ ተገፎ ለተከበረ ሰው መደረብ ነበር። ያኔ ልብሱም ለባሹም ይከበራሉ።
መጎናፀፊያ አካልን ይሸፍን ይሆናል፤ ምናልባትም የአካል እንከንን የነፍስ ሴሰኝነት ግን በልብስ አይሸፈንም። ዝቃጭ ምግባር ግን ለቅድስና ሌት ተቀን ለሚታገሉ ልበ ብርቱዎች በተዘጋጀ መደረቢያ አይከለልም። በሱ ቤት እኔ ከእናቴ ጋር የሚሰራውን ብልግና አላውቅበትም። የናቴ ውሽማዋ ነው።
ይሄኔ በየመቅደሱ ‘ሰው የዘራውን ያጭዳል’ እያለ ይቦጠለቃል። እሱ ግን ያልዘራውን ለማጨድ በሰው እርሻ ይኳትናል።
ሴሰኝነትን እየዘራ መከበርን ለማጨድ ማጭድ ይስላል። ከንቱ!!
ይሄኔ ስንቶች ስንጥር ለምታክል በደላቸው ንሰሃን ሽተው ከፊቱ ሲመጡ ዋርካ የሚያክል ስድነቱን በብብቱ ሸሽጎ ልባቸው ለንሰሃ እንዲሰበር ዘክሯል። የዘቀጠ!! የእናቴን ጣር ላይ መሆን ሊነግሩኝ እንደመጡት ሶስቱ እሱም
እየተፀየፈኝ ቤቴን ለቆ ወጣ።
(ከመፅሃፉ ገፆች የተቆረሰ)
#share -----> @write_event

"ውበትን የምታገኙት የማይታየውን ስታዩ ነው፤ በግልፅ ያልሆነውን ስትረዱ ነው፤ ድምፅ የሌለውን ንግግር ስትስሙ ነው፡፡ ውበት፣ በውስጣችሁ ተጀምሮ ከሥጋዊ ፍላጐቶቻችሁ ባሻገር የሚያበቃ ድንቅ የሀዘንና ደስታ ውህድ ነው፡፡ ልቦና ውስጥ የሚገኝ ብርሃን ነው።"
ካህሊል ጂብራን
Join: https://telegram.me/Write_Event
ካህሊል ጂብራን
Join: https://telegram.me/Write_Event
Telegram
እኛ እና የኛ
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
ጥሬ ጨዉ
=========
መስለዉኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰዉ ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸዉ
ጥሬ ጨዉ…ጥሬ ጨዉ ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት መቀየጥ
ገና እሚቀራቸዉ
“እኔ የለሁበትም!”
የዘወትር ቋንቋቸዉ።
___
ደበበ ሰይፉ
@Write_Event
@Write_Event
=========
መስለዉኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰዉ ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸዉ
ጥሬ ጨዉ…ጥሬ ጨዉ ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት መቀየጥ
ገና እሚቀራቸዉ
“እኔ የለሁበትም!”
የዘወትር ቋንቋቸዉ።
___
ደበበ ሰይፉ
@Write_Event
@Write_Event
" # እጅ_ከፍንጅ "?
-
አንዲት ባለትዳር ፥ በጓዳዋ ሳለች ፥ ጉንዳን ቆነጠጣት
ከእግር እስከ ራሷ ፥ ተርመስምሶ ገብቶ ፥ ነክሶ ፋታ አሳጣት
-
ይሄን ጊዜ ጮኸች፤
ልብሶቿን አራግፋ ፥ ራቁቷን ቀረች!
-
ጩኸቷን የሰማ ፥ ላጤ ጎረቤቷ ፥ ገባ ተንደርድሮ
ያቺን ቆንጆ እንስት ፥ እርቃኗን ሲያያት ፥ ቀረ ተገትሮ!
-
በዚህ ሁነት መሃል ፥ ሰይጣን አይኑን ሲጥል ፥ ባል ድንገት
ይደርሳል
ሰበብ የጠፋ 'ለት ፥ የጉንዳን ወረራ ፥ ትዳርን ያፈርሳል ።
---------//----------
(✍ በርናባስ ከበደ )
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
-
አንዲት ባለትዳር ፥ በጓዳዋ ሳለች ፥ ጉንዳን ቆነጠጣት
ከእግር እስከ ራሷ ፥ ተርመስምሶ ገብቶ ፥ ነክሶ ፋታ አሳጣት
-
ይሄን ጊዜ ጮኸች፤
ልብሶቿን አራግፋ ፥ ራቁቷን ቀረች!
-
ጩኸቷን የሰማ ፥ ላጤ ጎረቤቷ ፥ ገባ ተንደርድሮ
ያቺን ቆንጆ እንስት ፥ እርቃኗን ሲያያት ፥ ቀረ ተገትሮ!
-
በዚህ ሁነት መሃል ፥ ሰይጣን አይኑን ሲጥል ፥ ባል ድንገት
ይደርሳል
ሰበብ የጠፋ 'ለት ፥ የጉንዳን ወረራ ፥ ትዳርን ያፈርሳል ።
---------//----------
(✍ በርናባስ ከበደ )
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🙏1
።።።ምን አገባኝ ።።።
እኔ ምን አገባኝ
የምትሉት ሀረግ
እሱ ነዉ አገሬን
ያረዳት እንደ በግ
ብዬ ግጥም ልፅፍ
ብድግ አልኩኝና
ምን አገባኝ ብዬ
ቁጭ አልኩ እንደገና
(በእውቀቱ ስዩም)
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
እኔ ምን አገባኝ
የምትሉት ሀረግ
እሱ ነዉ አገሬን
ያረዳት እንደ በግ
ብዬ ግጥም ልፅፍ
ብድግ አልኩኝና
ምን አገባኝ ብዬ
ቁጭ አልኩ እንደገና
(በእውቀቱ ስዩም)
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
ጎ ጆ ቤ ት
┈•✦•┈
✍ እንዳለጌታ ከበደ
'
ሀገርስ ጎጆ ናት!!!
መሪዋም ምሰሶ
ሹማምንቷም ማገር
አንዳንዶቹም ቋሚ
ሌሎቹም ወጋግራ
ሠራዊቷም አጥር!
ሀገርስ ጎጆ ናት!!!
ሕዝቡም ክዳን ሆኖ
ጎጆውን አልብሶ
እንደሳር ቢቀጥን፤
ቢኖር ተራ መስሎ
ከዝናብ ያድናል፤
ውርጩን አሰናብቶ
ፀሐይን ይከላል፤
በጥላው ከልሎ ...
ሀገርስ ጎጆ ናት!!!
እውነትም ጎጆ ናት
ሊቃውንቷም እሳት
ላንዱ ጭስ ሲደርሰው
ለሌላው ትኩሳት።
ምሰሶው ቢተልቅ -
መሪው ገዝፎ ቢታይ
ጎጆው ከቶ አይሞቅም -
ካልጫሩበት እሳት
ጎጆው ቤት አይሆንም -
ሳር ከሌለው በአናት...
... ሀገርስ ጎጆ ናት!!! ...
═══════
📓 ልብ ሲበርደው
🗓 መጋቢት 2007 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Write_Event
┈•✦•┈
✍ እንዳለጌታ ከበደ
'
ሀገርስ ጎጆ ናት!!!
መሪዋም ምሰሶ
ሹማምንቷም ማገር
አንዳንዶቹም ቋሚ
ሌሎቹም ወጋግራ
ሠራዊቷም አጥር!
ሀገርስ ጎጆ ናት!!!
ሕዝቡም ክዳን ሆኖ
ጎጆውን አልብሶ
እንደሳር ቢቀጥን፤
ቢኖር ተራ መስሎ
ከዝናብ ያድናል፤
ውርጩን አሰናብቶ
ፀሐይን ይከላል፤
በጥላው ከልሎ ...
ሀገርስ ጎጆ ናት!!!
እውነትም ጎጆ ናት
ሊቃውንቷም እሳት
ላንዱ ጭስ ሲደርሰው
ለሌላው ትኩሳት።
ምሰሶው ቢተልቅ -
መሪው ገዝፎ ቢታይ
ጎጆው ከቶ አይሞቅም -
ካልጫሩበት እሳት
ጎጆው ቤት አይሆንም -
ሳር ከሌለው በአናት...
... ሀገርስ ጎጆ ናት!!! ...
═══════
📓 ልብ ሲበርደው
🗓 መጋቢት 2007 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Write_Event
Telegram
እኛ እና የኛ
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
💬
❝ቀስትህን እስከመጨረሻው ካልሳብከው ዒላማው ውስጥ እስከመጨረሻው አይገባም፤ ዕውቀትን የሚሻም ተማሪ እስከመጨረሻው የሚተጋ ብቻ ነው።❞
ሜንሲየስ
💬
❝ከመጻሕፍት አንዳንዶች የሚቀመሱ፤ አንዳንዶች የሚዋጡ፤ ሌሎች ደግሞ የሚመነዠኩም ናቸው።❞
ፍራንሲስ ቤከን
💬
❝በመመገቢያ ጠረጴዛህ ላይ መጽሐፎች ይሙሉ። ከዚያም በጣም ደስተኛ ትሆናለህ። ትራስህም መጽሐፎች ይሁኑ፤ ከዚያም ፍፁም የሠላም እንቅልፍ ትተኛለህ።❞
ፊዮዶር ዶስቶዬቭስኪ
💬
❝ዛፎች መሬት ለሰማይ የጻፈቻቸው ግጥሞች ናቸው።❞
ካህሊል ጂብራን
💬
❝ንፁህ አእምሮ ማለት ሙሉ ንቃት ማለት ነው። ለዚህም ነው ንፁህ አእምሮ፣ የሚወደውን ነገር በንቃት መመልከት የሚችለው።❞
ብሌዝ ፓስካል
💬
❝አንድን ሰው ምንም ልታስተምሩት አትችሉም፤ ማድረግ የምትችሉት ነገር ቢኖር ከራሱ ውስጥ እንዲፈልገው መርዳት ነው።❞
ጋሊሊዮ
💬 💬
ጥቅሶች

📓 ርዕስ የለውም
✍ ኤሊያስ ሽታኹን
'
┈┈•✦•┈┈
በቀደም
አጠገቤ ሆነሽ፤ ዐይኔ አ'ይሰበር፤
ስለምሳሳልሽ፤ መች እተኛ ነበር።
ዛሬ • • •
ካጠገቤ ሄደሽ፤ ባንቺ እየተገፋኹ፤
ዘንድሮም አልተኛም፤ መቼ አንቀላፋኹኹ?
(በሁለቱም አለሁ)
ሕልምና ሐሳቤ፤ ተቀምቶ ቤቱን፤
ታዲያ ምን ሆኜ ነው?
ስትመጪም፤ ስትሄጂም፤ መንቃቴ ሌሊቱን።
ዐይኔ ተከድኖ አያውቅ፤ በደስታም በእክል፤
ንገሪኝ ዓለሜ! የቱ ነው እውነቴ? የቱ ነው ትክክል?
•
•
•
•
እየሄድሽም እንኳ
ልክ ልሁን አልሁን፤ አንቺን መጠየቄ፤ እንደዚህ ታምሜ፤
እውነቱን ንገሪኝ! ልክ ነኝ ዓለሜ?
═══════
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/write_event
✍ ኤሊያስ ሽታኹን
'
┈┈•✦•┈┈
በቀደም
አጠገቤ ሆነሽ፤ ዐይኔ አ'ይሰበር፤
ስለምሳሳልሽ፤ መች እተኛ ነበር።
ዛሬ • • •
ካጠገቤ ሄደሽ፤ ባንቺ እየተገፋኹ፤
ዘንድሮም አልተኛም፤ መቼ አንቀላፋኹኹ?
(በሁለቱም አለሁ)
ሕልምና ሐሳቤ፤ ተቀምቶ ቤቱን፤
ታዲያ ምን ሆኜ ነው?
ስትመጪም፤ ስትሄጂም፤ መንቃቴ ሌሊቱን።
ዐይኔ ተከድኖ አያውቅ፤ በደስታም በእክል፤
ንገሪኝ ዓለሜ! የቱ ነው እውነቴ? የቱ ነው ትክክል?
•
•
•
•
እየሄድሽም እንኳ
ልክ ልሁን አልሁን፤ አንቺን መጠየቄ፤ እንደዚህ ታምሜ፤
እውነቱን ንገሪኝ! ልክ ነኝ ዓለሜ?
═══════
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/write_event
Telegram
ቃላዊ
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
ለ ፈ ገ ግ ታ
😁 😁 😁
የውርርድ ሱስ የተጠናወተው ቢሊ ከሚያገኘው ሰው ጋር ሁሉ ይወራረዳል። አባቱና አጎቱ ይህን አመሉን ለማስተው የነበራቸው ምርጫ የሚያሸንፉትን ውርርድ ብቻ ከሱ ጋር በመወራረድ በመሸነፍ ብዛት ተስፋ ቆርጦ እንዲተወው ማድረግ ነበር። እናም ከቀጣዩ ቀን ጠዋት ጀምሮ ከሁለታቸው ጋር ብቻ እንዲወራረድ ቃል ያስገቡታል።
በነጋታው ጠዋት ቢሊ አጎቱ ወደ ሥራ ሲወጣ በር ላይ አስቁሞ
«አጎቴ፤ እግርህ ላይ በቆሎ እንደበቀለ በአስር ሳንቲም እንወራረድ!» አለው።
አጎቱ ውርርዱን በመቀበል አስር ሳንቲም ያስይዝና የሁለቱንም እግር ጫማና ካልሲ በማውለቅ እግሮቹ ላይ በቆሎ እንዳልበቀለ አስመስክሮ ሃያ ሳንቲሙን ይቀበለዋል።
ኋላ ላይ አባትየውን ውጭ ሲያገኘው
«ሙከራችን ሊሳካ ነው መሰል። ዛሬ ጠዋት ...» ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ አባትየው አቋርጦት
«መቼም አይሳካም ባክህ! ጠዋት ካንተ በፊት እኔ ጋ መጥቶ 'አጎቴን በአስር ደቂቃ ውስጥ ጫማውንና ካልሲውን አስወልቀዋለሁ' ብሎ ከኔ ጋር በሃምሳ ሳንቲም ተወራርዶ ነው ወዳንተ የመጣው!»
😂 😂 😂
━━━━━━━━━━
📓 የሳቅ ምንጭ

የተስፋዬ ዛፉ
┈┈•✦•┈┈
✍ ደበበ ሰይፉ
'
የተስፋዬ ዛፉ
ሲከረከም ቅርንጫፉ፤
ሥሩ ሲነቃቀል
ሲበጠስ ሲፈነገል፤
ጭላንጭል ስትዳፈን
ብርሃን ዐይኑ ሲከፈን፤
አንጥፌ ደርቤ ማቄን
ዘንግቻት እንቁጣጣሽን
ፀደይ አበባ ዐደዬን፤
በድቅድቁ ተቀመጥሁኝ
ላለማሰብ እያሰብሁኝ፤
የልቤን ልበ-ባሻነት ገሠፅኩኝ
ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አረኩኝ።
════════
📓 የብርሃን ፍቅር
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/write_event
┈┈•✦•┈┈
✍ ደበበ ሰይፉ
'
የተስፋዬ ዛፉ
ሲከረከም ቅርንጫፉ፤
ሥሩ ሲነቃቀል
ሲበጠስ ሲፈነገል፤
ጭላንጭል ስትዳፈን
ብርሃን ዐይኑ ሲከፈን፤
አንጥፌ ደርቤ ማቄን
ዘንግቻት እንቁጣጣሽን
ፀደይ አበባ ዐደዬን፤
በድቅድቁ ተቀመጥሁኝ
ላለማሰብ እያሰብሁኝ፤
የልቤን ልበ-ባሻነት ገሠፅኩኝ
ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አረኩኝ።
════════
📓 የብርሃን ፍቅር
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/write_event
Telegram
ቃላዊ
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።
ግጥም ለመላክ
➫ @Melikitegna_bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኤልያስ ሽታሁን ድንቅ ግጥም በሳቅሽልኝ ቁጥር ከ ርዕሰ የለውም የግጥም መድብል የተወሰደ
እኔ ባፈቅርሽም .......
ቀለሜ እስኪጠቁር ስጋየ እስኪከሳ
እጅግ ባፈቅርሽም ሰው እስከምረሳ
የወገቤን ስፋት የልቤን ብርታቱን
እኔ አውቃለሁና የውስጤን ምኞቱን
ሀቁን ላሳውቅሽ ልንገርሽ እውነቱን
ከራሴ አብልጬ ምን ብሳሳልሽም
ከሰዎች አብልጬ ምንም ብወድሽም
ግና
አግብቼሽ ሊቆጨኝ ኃላ ሊፀፅተኝ
የኔ የሬሴን ክፍተት አንቺ ላትሞይልኝ
እኔ አላገባሽም ከቶ እንዳጠብቂኝ::
ከሴት ሁሉ በላይ እጅግ ብቀርብሽም
እስከመቼም ድረስ ከቶ ባረሳሽም
እኔ ባፈቅርሽም ግን አላገባሽም!!
@write_event
ቀለሜ እስኪጠቁር ስጋየ እስኪከሳ
እጅግ ባፈቅርሽም ሰው እስከምረሳ
የወገቤን ስፋት የልቤን ብርታቱን
እኔ አውቃለሁና የውስጤን ምኞቱን
ሀቁን ላሳውቅሽ ልንገርሽ እውነቱን
ከራሴ አብልጬ ምን ብሳሳልሽም
ከሰዎች አብልጬ ምንም ብወድሽም
ግና
አግብቼሽ ሊቆጨኝ ኃላ ሊፀፅተኝ
የኔ የሬሴን ክፍተት አንቺ ላትሞይልኝ
እኔ አላገባሽም ከቶ እንዳጠብቂኝ::
ከሴት ሁሉ በላይ እጅግ ብቀርብሽም
እስከመቼም ድረስ ከቶ ባረሳሽም
እኔ ባፈቅርሽም ግን አላገባሽም!!
@write_event
እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ።
በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ።
አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ።
በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ።
በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል። ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው።
በኖረበት ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ።
አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር።
ይህ ታሪክ ለአብዛኞቻችን አስተማሪ ይመስለናል ።
በውስጣችን አዳፍነነው ያስቀመጥነው ተሰጥኦ እንዳለ እናምናለን ።
ይህን ተሰጥኦ ከውስጣችን ጎትቶ የሚያወጣልን ውጫዊ አካል አንጠብቅ ።
የተሰጠን ቀን ዛሬ ነውና ለማናውቀው ነገ ቀጠሮ አንስጥ ።
ስለ ነገ ማንም አያውቅም። የተሰጠን ዛሬ እንደሆነ አውቀን የተዳፈነውን ችሎታችንን አውጥተን ለሌሎች የብርሃን ችቦን እንለኩስ።