ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)

የሆነ ጊዜ ላይ የተወሰኑ ጓደኞቼን የምወዳት ልጅ ወላጆች ቤት ሽምግልና ላክሁዋቸው::
የፍቅረኛየ አባት “ልጁ ምናለው?” ብለው ጠየቁ ::
ከሽማግሌዎች አንዱ ትንሽ ሲያቅማማ ከቆየ በሁዋላ፥

“ ከሁለት መቶ ሺህ ያላነሰ ተከታይ አለው፤ ፌስቡክ ላይ “ ብሎ ተከዘ::
ቁሞ የመቅረት ታሪኬም በዛች ቀን ጀመረ፤

በቀደም ለታ፥ ፌስቡክ ፥ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ተከታዮቼ መካከል፥ ዘጠኝ ሺውን ብቻ አስቀርቶል ሌላውን አፈሰብኝ፤ የገንዘቡ ሳያንስ የተከታይ ግሽበት መታገስ የምችልበት ጫንቃ አልነበረኝም::

ከተከታዮቼ መሀል ፥ ጽፌ የምለጥፈውን አንብበው መውደዳቸውን የሚያሳዩኝ አስተያየቱን የሚለግሱኝ ከአስር ሺህ አይበልጡም፤ ከተከታዮቼ መሀል” ክንዴ ቢዝል፥ ምላሴን ቢያዳልጠው፥ ግጥሜ ልቦና ባይረታ፥ ቀልዴ ጥርስ ባይመታ፥ ልክ ልኬን ሊነግሩኝ መከትከቻውን እየሳሉ እሚጠብቁኝ እንዳሉ አውቃለሁ፤ዝም ብለው ደጃፍ ላይ ተቀምጠው ሳልፍ ሳገድም እሚያዩኝም ሞልተዋል::

ቢሆንም “
“ባይነዳ ባይረዳ ባይኖረውም ሀብት “
ከደጃፍ ሲቀመጥ ደስ ይላል አባት “ ይላል እማ ሸንበቆ ጠላ ቤት ግድግዳ ላይ የተለጠፈ ጥቅስ!
እኔም እለላሁ፤
“ባይለይክ፤ ባይኮምንት ፤ አሻራው ባይታይ”
ከደጃፍ ሲቀመጥ ደስ ይላል ተከታይ”

የፌስቡክ አለቃ ፥ በሁሉን አወቅነቱ፥ ይህንን ስሜቴን ተረድቶ ፥ በነበሩት ተከታዮቼ ላይ አንድ የቀበሌ አዳራሽ የሚሞሉ ተከታዮች ከራሱ ጨምሮ መለሰልኝ::

በባለፈው ዝግጅት ላይ ለታደሙ ወዳጆቼ የምስጋና ቃል ልጽፍ ሰንዳ ሰንዳ ስል መብራት እልም አለ:: እኛ ሰፈር ያለው ትራንስፎርመር በሚፈነዳበት መጠን የልደት ፊኛ አይፈነዳም ፤ አሁን አሁንማ፥ መብራት ሲጠፋ እንደ ድሮው መናደድ አቁሚያለሁ፤ በጨለማ ውስጥም ቢሆን ስራ እንዳልፈታ ምቾት እንዳላጣ አድርጌ ራሴን አላማምደዋለሁ፤ ሆመር ፥ ሀሰን አማኑ፥ እማሆይ ገላነሽ፥ ወዘተ፤ ውበት ፥ ሀሳብ እና ለዛ ለማፍለቅ የግድ ውጫዊ ብርሀን አስፈላጊ እንዳልሆነ ምስክር ናቸው፤ እንዲህ እያልሁ ዘና ብየ ጥቂት እንደቆየሁ አምፖሉ እንደ ነሀሴ ሰማይ ብልጭ ብሎ ድርግም ይላል፤ ጉዋደኛየ ምኡዝ አንድ የሚወዳት ልጅ ነበረች፤ የሆነ ቀን ሲጽፍላት አትመልስም፤ ሲደውልላት አታነሳም፤ ጭራሽ ለተወሰኑ ወራት መገኛዋን ሁሉ ትደመስሳለች፤ እሱም ያለ እሷ ለመኖር ራሱን ለማለማመድ ይፍጨረጨራል፤ ከዛ እፎይ ብሎ እየኖረ እያለ You miss me? 😘🥰😊 '' የሚል ቴክስት ትልክለታለች፤ አምፖሌ ብልጭ ብሎ የተለማመድሁትን የጨለማ ደስታ ሲያደፈርስብኝ ትዝ የሚለኝ ይሄ ነው፤

ጥለት ሚድያ ባሰናዳው የሰኞ ዝግጅት ላይ የታደማችሁ ምስጋናየን ይድረሳችሁ፤ ገና ሁለተኛ ዝግጅታችን እንደመሆኑ መጠን ጉድለታችንን ለማሻሻል አጥብቀን እንሰራለን፤ ሐረር ባንድ ጀንበር አልተገነባችም፤ (በጊዜው በጉልህ የታየው የድምጽ ችግር ከመብራት መጥፋት ጋራ በተያያዘ በጄኔረተር ምክንያት የመጣ ነው፤ ለዚህ ይቅርታ እንጠይቃለን) ሌላ እንዲስተካከል እምትፈልጉትን ሳታስባንኑ ፥ በአካል አግኝታችሁ፥ ምሳ እየጋበዛችሁ፤ ትከሻየን እየቸበቸባችሁ ንገሩኝ፤ በማቱሳላ አቆጣጠር ገና ልጅ ነኝ፤ እታረማለሁ::

የዝግጅቱ ቀን ከጉዋደኛየ ጋራ ስደርስ ጥቂት አርፍጄ ነበር፤ ከብሄራዊ ትያትር ወዲህ ማዶ፥ ኢትዮጵያ ሆቴልን አለፍ ብሎ ሰው በረጅሙ ተሰልፎ ሳይ ራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ፤ ልቤ ተነካ፤” ወንድ ልጅ ብቻውን ነው እሚያለቅሰው “ ይላል ባለቅኔ ጸጋየ ገብረመድህን:: እኔ ግን ወንድ ልጅ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ባያላቅስ ደስ ይለኛል፤ የዛን ቀን ግን አልቻልኩም፤ የደስታ እምባየ “ናፕኪን” ከደረት ኪሴ እስካወጣ እንኳን አልታገሰኝም

“ አሁን እኔ ይሄን የሚያህል ሰልፍ deserve አደርጋለሁ?”
አልሁት ጓደኛየን፥

“ ተረጋጋ! እነዚህ ወደ ሜክስኮ የሚሄደውን ምኒባስ ለመሳፈር የተሰለፉ ናቸው “

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!

https://t.me/write_event
ነጠብጣብ ሐሳቦች
በ. ሥ)
ሰማይ ከሚመክን ፤ይጸንስ መከራ
ያርግፍ ! ያርግፍ! ያርግፍ ! መኣት እያፈራ
የ’ሣት ዛፍ ባለበት ፤ ሰደድ አያስፈራ
.............
ከሐምሌት ጋር ሞቷል፤ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፤ አለመሆን የለም
ሸክም ጸጋ ሆኗል፤ ጸጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ፤ ትከሻህን አስፋ!
............
አንድ ሕልም እንደ ጠጅ፤ እየደጋገሙ
ንግር ፤ትንቢት ሳይሆን፤ ታሪክ እያልለሙ
ተኝቶ መነሣት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሣት
ነፍሴን እንቆቅልሽ
(ከስብስብ ግጥሞች)
share and join
@write_event
@write_event
@write_event
ዝግ ዓለም
(በ.ሥ)
ከትራሴ ግድም ፤በተደፋው ሰማይ
ኮከብ እያበራ ፤በመከዳየ ላይ
ምንም አላነበብኩ ፤ከህዋው ግድግዳ
እውነትና ንጋት፤ እያደር እንግዳ፡፡
(ከስብስብ ግጥሞች)
share and join
@write_event
@write_event
@write_event
እረፉ!
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።.
...ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
#Eyayu Fenges


share and join
@write_event
@write_event
@write_event
"""""""" ናፍቆት """""""""
እንደምነሽ እቴ ?
እኔ እንዳለሁ አለሁ ሳላሰማ ኮቴ
ይኸው ነጥቀውኛል ስሜን ከነ እርስቴ
እንደምነሽ አንች ?
እኔማ ዴግ ነኝ ተስፋ አይሞትም ስባል
ተስፋ እየጠበኩኝ በጨለማ መሃል
አዎ እኔ ደህና ነኝ ¡
ያው እንደምታይኝ ቁመቴ ጨምሯል
በእድሜየ ግማሽ ላይ ዘመን ይታከላል
ይኸውልሽ ዘንድሮ _
ያ የምንጠጣበት ኩሬያችን ደፍርሶ
የምናወጋበት ግራራችን ታርሶ

በእንተማርያም የሚል የዋህ ዲያቆን ጠፍቶ
ሸሚዜን ሰረቀኝ ቀየረው ጠረኔን በማይሆን ቡትቶ
ጦሴን ይዞት ይሂድ

ግን አንች እንደምነሽ ? ሞት እንዲህ ያኮራል?
ገነት እንደምናት? የጻድቃን መኖሪያ ሰምቻለሁ ሲባል
እዚህ እንደሚወራው ሲኦል ከምር አለ?
እዚህማ ሞልቷል ምን የቀረን አለ
ኪራይ ቤት ሲኦል ነው
ሽንትቤት ሲኦል ነው
ስራውም ሲኦል ነው
ምድርም እኮ እራሷ ሲኦል መሆኗ ነው

አንች እንደምን አለሽ ?
ከሰማያት በላይ ከደመና እርቀሽ
በመላእክት መዝሙር ነው አሉ ሚያስተኙሽ
እዛስ ሙዚቃ አለ ?
እዚህ ዘፈን በዝቷል ሁሉም ሙዚቀኛ
ተሸላሚ ሞልቷል ከነክብሩ አንደኛ
በዝቶልሻል ቅኔ
ይናገረው ይዟል ሰው ሁሉ በወኔ
____አየ ቅኔ
_አወይ እኔ
መንግስትም አለ እኮ ምንግዜም የማይወርድ
ለ ግብጽ ወታደር የማይርበደበድ
ድርቅ የማይነካካው ረሃብ የማያውቅ
እድገት አስመዝግቧል ታይቶ ማይታወቅ
እረ ምን ነክቶሻል ምን የሌለን አለ
ኔት ወርክ በሽ ነው ሁሉ እየታደለ
አለሜ
እኔ ግን መሮኛል ምጻት አልጠብቅም
___ምጻት ይምጣ አልልም
እኔ እቀድመዋለሁ በናፍቆትሽ በትር ቁሜ አልገረፍም
ያሬድ ከበደ
( ያሬዳዊ ግጥም)
*
እምነት ሲበረታ


እንደው ለተአምር
የመርፌ ቀዳዳ ግመል ካሻገረ
"""""" """""""
ድር ያበረ ለታ
ከሠንሠለት ከሮ አምበሳን ካሰረ
""""""" """"""""
ከሚባለው እጥፍ
እጥፍ ከሚባለው ሆድ ካገር ከሰፋ
““"""" “““"""
በልቡ ያመነ
ከጥፋቱ ድኖ ተራራን ከገፋ
““““ “"""""
ቀስትና ፍላፃው
ክንዱ ሲበረታ የእምነታችን ደጋን
"""""" """""""
ድጋፉ ሳይዋልል
በጠጠር መዳፍ ላይ ከተቀመጠ ጋን
"""""" """""""""
በባለፀጋ ህልም
በመርፌ ቀዳዳ ከመሻገር ጥማት
""""""" """"""""
በፅድቅ መነፅር
ከግመል ቁመና ይወፍራል ጅማት

share and join
@write_event
@write_event
@write_event
፨፨፨፨የይቅርታ መሐልይ፨፨፨
ማነዉ የፈለገኝ?
በማይነጋ ሌሊት
በማይመሽ ቀን መሀል
ተዘርሬ ስገኝ።
ከተዉሽኝ በኀላ 'ርቃን ቀርታ ነፍሴ
እንኳን ከሰው ዐዉድ ተነጠልኩ ከራሴ፡፡
፨ ፨ ፨
ተመልሼ ልምጣ ተመልሰሽ ነዪ
ልጣል ምሰሶዬን ማገርሽን ጣዪ
አዲስ ቤት መገንባት ዛሬ መች ይደላል
ለምደዉ ወደተዉት መመለስ ይቀላል፡፡
፨ ፨ ፨
ካሳ ባልክልሽ ቁና ጤፍ ሰፍሬ
ባዶ እጄን አልቆምም ከደጅሽ ደፍሬ
ጵንፍ የለሽ ይቅርታን ውሰጅ ከከንፈሬ፡፡
★★★በእውቀቱ ስዩም★★★
https://t.me/write_event
---ድምጽ አልባ ፊደላት---
ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት
ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ነገር
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጧት
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት
ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል
እናትነት ሲጎድል
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ፊደል።
👉👉ኤፍሬም ስዩም👈👈

https://t.me/write_event
ቀደም ነበር...
ባላወቅሁሽ ባላወቅሽኝ
በሰናይ ግብር በጥዑም ቃል ባልገዛሽኝ

አሁንማ...
እስትንፋስሽ ከእስትንፋሴ ተቆራኝቶ
ሴትነትሽ ከህላዌ መልቶ ሰልቶ
ከነፍሴ ጋር ተዋህደሽ
ቀልቤ ከድቶ ጥሎኝ ሲሸሽ

  ከሔዋን ዘር እያማርሽኝ እየጣምሽኝ
እስከ ጥጉ ስከተልሽ እያወቅሽኝ
"ወደድሁሽ" ስል፣
"ተው አድትከም" የምትይኝ
አንቺን ችሎ የሚነጠል ልብ የት አለኝ!?

ታደሰ ደምሴ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
share and join
@write_event
@write_event
@write_event
Forgot password is my password!
(አሌክስ አብርሃም)

አሜሪካ ኑሮው ከባድ ነው፣ብቸኝነቱ ከባድ ነው፣ አየሩ ከባድ ነው ፣ ይሄ ከባድ ነው …ያ ከባድ ነው ይላሉ እንጅ እኔ እስከአሁን የከበደኝ ሁለት ነገር ብቻ ነው! አንዱ ፓስወርድ ማስታወስ ! ፓስወርድ የሌለውን ነገር ጠይቁኝ …. ፓስወርድ በጣም ከመብዛቱ የተነሳ ዝም ብሎ በተራ ቁልፍ የሚከፈት ነገር ላይ ሁሉ ጣቴን አሾላለሁ! ዋሌቴን የሞላውን ካርድ አውጥቸ ብበውዘው …. በየመንገዱ እየዞርኩ በመጫዎቻ ካርድ ማጅክ ምናምን የምሰራ ሰው ያስመስለኛል !እዚች አገር ትንሽ ከቆየሁ እንደጋሽ ስብሃት ካርዴን በፌስታል መያዜ የማይቀር ነው! እንግዲህ ይሄ ሁሉ ካርድ ፓስወርድ አለው! እንዴት እንደሚሰለች የደረሰበት ያውቀዋል! እና አንድ ወዳጀ forgot password is your password ይለኛል !
ሁለተኛው ችግሬ … በጣም የሚበዙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ስቀላቀል ልክ እንደቻይና ኮሪያ ምናምን አንድ አይነት ይሆኑብኛል ! መለየት በጣም ነው የሚከብደኝ ! በምሳሌ ላስረዳ! አሁን በቅርቡ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ምሳ ጠሩኝ …ምክንያት? ከኢትዮጵያ እህታቸው ስለመጣች! ....ስደርስ ያለምንም ግነት ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ አንድ አይነት ሴቶች ቤቱ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይላሉ …የሌላውን እንግዳ ብዛት ደግሞ ተውት …ሁሉም አንድ አይነት የባህል ልብስ ለብሰዋል …ሁሉም ሹሩባ ተሰርተዋል …ሁሉም በሜካፕ አብደዋል …ሁሉም አይፎን ስልክ ይዘዋል … እና ሁሉም ጥርሳቸው ብሬስ …በእርግጥ ሁሉም ቆንጆዎች ነበሩ ! እና ምሳ የጠራችኝ አክስታቸው እያስተዋወቀችኝ ነው …
እሷ ቲጅ ናት ባለፈው ዳኒን አግብታ የመጣችው …ያው ዳኒ ግን የአጎቷ ልጅ ነው …ለፕሮሰስ ነው እንጅ እሷ አላገባችም ሲንግል ነች ሂሂሂ(ምን ሂሂሂ ያስብላል) !ትክ ብየ አየኋት በስማም ቁንጅና ….ሌሎቹ ጋር አንድ አይነት !ይሄ የተረገመ ሹርባ እንዴት ነው ሰው የሚያመሳስለው! …ይችኛዋ ኪያ ነች ….የዛሬ አመት አሴን አግብታ የመጣችው …አሴን ታውቀው የለ የኔ ትልቁ ልጅ የሩታ ባል …ለፕሮሰስ ነው እንጅ ትክክለኛ ባሏ ዳጊ ነው ! ያች (ነይ አንች ሰላም በይው ) ፍልቅልቅ እያለች መጣች ! ይች ሩሃማ ነች … ለቫኬሽን መጥታ በአሳይለም የቀረችው …
ፖለቲከኛ ነች ጋዜጠኛ?…አልኩ …..
ማን እሷ? አሁን ያለው ጠቅላይ ሚንስትር ማነው ብትላት አታውቀውም …ለፕሮሰስ ነው ! ያችኛዋ ናኒ ነች የፍሬው ሚስት …እና ደግሞ ይች ፊኖ የሽሜ ሚስት …ያች ….ኪራ ለፕሮሰስ ፍፄን አግብታ የመጣችው ናት …ፍፄን ታውቀው የለ የሲቲና ባል ….
ዘወርወር ስላለብኝ …ከምግብ ቡፌው ላይ ሁለት ናብኪን አንስቸ ሰሃኑ ላይ ካነጠፍኩ በኋላ ቀይ ወጥ ጨመርኩበት …አልጫ ልጨምርበት ስል ነው እንጀራውን እንደረሳሁ ትዝ ያለኝ😐! ወደውስጥ ገብተው በተመለሱ ቁጥር አንዷ ከሌላኛዋ ይምታቱብኛል …ዋናው ነጥብ ሲንግል የተባለችውን ላለመርሳት መሞከር ነው እላለሁ ለራሴ…ለምልክት ቀሚሷን ቀይ ወጥ ላስነካው ይሆን ….! ግን ነገሩ ቀይዋን ያየ የሚሉት አይነት የካርታ ጨዋታ ነበር …ተበወዙብኝ …ውር ውር ውር ያገባች ያላገባች ፕሮሰስ አሳይለም! የቷ ናት ሲንግል ይለኛል አእምሮየ …ይች ነቻ እላለሁ …ተሳሳትክ ይች የፍሬው ሚስት ናት!
ሲንግሏ ናት ብየ ያሰብኳትን ፈገግ አልኩላት ፈገግ አለች …ብሬስ ! እንዴት ነው ታዲያ አገሩን ለመድሽው … ኦ እኔ አይደለሁምኮ የመጣሁት …የት ሄደች ቲጅ ናት … ተሳሳቅን! ቆይቸ ቲጅን አገኘኋት ብየ ወሬ ስጀምር ቶማስ መጥቶ አብርሽ ተጫዎት ተዋወቃችሁ?…ናኒ ባለቤቴ ነች ! እንዲቹ እንደተምታታብኝ ‹‹የታለች ሲንግሏ ቲጅ ? መልሳችሁ.... ወደአገር ቤት ላካችኋት እንዴ ? ….›› ብየ ልጮህ ምንም አልቀረኝም በሰው አገር ሰንደል ፀጉሬ ላይ ሰክቸ ከመዞሬ በፊት ማሰቡትን ትቸ ሰሀኔ ላይ አቀረቀርኩ! ምናይነት ፊዚክስ የሆነ ቤተሰብ ነው?! ተሰናብቸ ስወጣ አክስታቸው …ከተል ብላኝ በቁም ነገር …
‹‹እኔ የምልህ አብርሽ …. ትንሽ አትጫዎትም ነበር? ….
‹‹ሌላ ቀን እመጣለሁ ››
‹‹ መምጣትማ አለብህ ! አንግዳዋን እናተ ካላላመዳችኋት ማን ያላምዳታል?! …ካለች በኋላ ወደዋናው ነጥቧ ገባች! እየውልህ …ሰው በቁሙ ካልተጠቃቀመ መቸም በኋላ እየየ ምን ያደርጋል …አንድ ነገር አስቤኮ …አንድ እህታቸው ብቻ አገር ቤት ቀርታለች … ለፕሮሰስ ለማን ልዳራት ብየ ሳስብ አንተ ትዝ አልከኝ … ባይሆን ያንተን እህት ደግሞ አንዱ የኔ ልጅ አግብቶ ያመጣታል !
ሲንግል ናት …? አልኩ (እስቲምናገባኝ)
ኧረ አግብታ ሁለት ወልዳለች …ባሏ በካቦ ቢጎትቱት ከዛ አገር የሚንቀሳቀስ አይነት አይደለም እንጅ ! እንዴት ያለች ቆንጆ መሰለችህ …መዓዚየ! ይች ሴትዮማ በአሳይሎም ቀርታ እንጅ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ሳትሆን አትቀርም ! …ወደቤት ስመለስ መንገድ ላይ የትኛው መስመር የኔ የትኛው በተቃራኒ መስመር የሚመጣው መኪና እንደሆነ ብዥዥዥዥዥዥዥዥ …ጭራሽ የተሳሳተ ሰፈር ገብቸ አረፍኩ! ጂፒኤስ ለመጠቀም ስልኬን አወጣሁ…. ስልኬ በፓስወርድ ጥርቅም ተደርጎ ተዘግቷል ….ፓስወርዱን ምን ነበር ? ….አዎ forgot password is my password!


#AlexAbreham
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!


share and join
@write_event
@write_event
@write_event
የደራሲ በአሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ አበራ አረፉ

የታላቁ ደራሲና ጋዜጠኛ የበአሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ ዛሬ ጥቅምት 30/2015 ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው አርድተውኛል ሲል ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ አስታውቋል።

አልማዝ ባለቤታቸውን የበአሉ ግርማን ሞትና መሰወር አልቀበል ብለው የቆዩ ሲሆን፤ ሁልግዜ ጠዋት ላይ ቤታቸውን አፀዳድተው በር ከፍተው በአሉ ግርማን ይመጣል እያሉ ሲጠብቁት ኖረው በዛሬው ዕለት ህይወታቸው አልፏል።

አልማዝ አበራ ከደራሲ በአሉ ግርማ ያፈሯቸው የሦስት ልጆች እናት ነበሩ።

ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማርል።

@write_event
@write_event
@write_event
😥ልብ የሚነካ #የእናትና ልጅ አጭር ታሪክ፠
👇👇👇👇👇👇👇👇
አንድ የ16 አመት ወጣት ‹‹እማ፤ 18ኛ አመት ሲሞላኝ ምን ስጦታ ትሰጭኛለሽ ?›› ሲል እናቱን ይጠይቃል፡፡ እናትም ‹‹ልጄ፤ ለ18 አመት እኮ ገና ብዙ ይቀርሃል›› ስትል ትመልሳለች፡፡ ልጁ 17 አመት ከሞላዉ በኋላ አንድ ቀን ራሱን ስቶ ይወድቅና እናቱ ወደ ሆስፒታል ትወስደዋለች፡፡ ያዩት ዶክተሮቹም... ‹‹ልጅሽ ልቡ ጥሩ አይደለም›› ሲሉ ያረዷታል፡፡ ስትሬቸር ላይ የተቀመጠዉ ልጇ… ‹‹ እማ፤ ዶክተሩ እንደምሞት ነገረሽ ወይ?›› ብሎ ሲጠይቃት እናት ማልቀስ ትጀምራለች፡፡ በመጨረሻም ልጁ በ18ኛ አመት የልደት ቀኑ ላይ ወደ መልካም ጤንነቱ ተመልሶ፤ ወደ ቤቱ
ሲመጣ፤ አልጋዉ ላይ እናቱ የተወችለት ደብዳቤ ያገኛል፡፡ ደብዳቤዉም እንዲህ የሚል ነበር፡-
‹‹ልጄ፤ ይሄን ደብዳቤ እያነበብክ ከሆን፤
ይህ የሆነዉ ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ በመሄዱ ነዉ፡፡ ለ18ኛ አመትህ ምን እንደምሰጥህ የጠየከኝንና የምመልሰዉ (መልስ) ያጣሁበትን ያን ቀን አስታዉስ፡፡ የምወድህ ልጄ፤ ልቤን ሰጥቸሃለሁ፡፡ በጥንቃቄ ያዘዉ፡፡ መልካም የደስታ ዘመንም ይሁንልህ፡፡››


እናት ልቧን ለልጇ መስጠት ስለነበረባት (እናትነት አስገድዷት) ህይወቷ አልፏል፡፡

ከእናት ፍቅር በላይ የሆነ ምንም ነገር የለም።
ስንቶቻችን በወላጆቻችን እናፍር ይሆን? ስንት አይነት መስዋዕት ከፍለው አሳድገውን ይሆን? ዛሬስ ምላሻችን ምንድነው? ጊዜው ያልመሸባችሁ በቻላችሁት አቅም ሁሉ ‘አለሁልህ አባቴ ፣ አለሁልሽ እናቴ’ በሏቸው። እኛን ሰው ለማድረግ ከሰውነት ተራ ወጥተው ያሉ ወላጆችን ቤቱ ይቁጠራቸው። እናስተውል! እንዳይቆጨን! ብዙ ወላጆች እኛን ራሳችንን እንጅ የእኛን ነገር አይፈልጉም ፣ በተቃራኒው ደግሞ እኛ የእንሱን ነገር እንጅ እነሱን አንፈልግም። እነሱን በመፈለግ ፍቅራችንን እናሳያቸው!

ይህ ታሪክ ከደረሳችሁ እናንተ ጋር እንዲቀር አትፍቀዱ ፣አስተማሪ ስለሆነ
እስከቻላችሁ ድረስ ለጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ እንጋብዛቸው።



Join and Share
@write_event
@write_event
@write_event
Forwarded from °•ᴍᴏᴏɴ•° (ᴍᴏᴏɴ)
እውነተኛው ጓደኛህ ማነው?
፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨
እውነተኛው ጓደኛህ ማነው? በቀላሉ የሚረዳህ፣ መንገድህን የሚጠርግልህ፣ ሃሳብህን፣ ህልምህን፣ ራዕይህን የሚደግፍልህ፣

አዎ! ብዙ ሰው ብዙ ጓደኞች አሉት፤ ከብዛታቸው ያተረፈው ነገር ግን የለም።

አዎ! ጓደኝነት ሁሉም ነገር ነው። እየሳቀ ከሚጥልህ እየተቆጣ፣ እየገሰፀ የሚያስተካክልህ ሰው ላንተ ትልቅ ስፍራ አለው። ቢኖርም ከማይጠቅምህ፣ ቢሄድም ከማይጎዳህ ሰው መለየት ይኖርብሃል
-
ᎢᎬᏞᎬ :- @M00N_i 🖤
ራሴን ወግቼ ላንቺ የምወግን
(በእውቀቱ ስዩም)

አይደለሁም ጀግና
ልቤን እና ክንዴን ፥እጠራጠራለሁ
ግን ተኩሼ ባልጥል፥ አነጣጥራለሁ
ቀማኛ ቢከብሽ፥ ፖሊስ እጠራለሁ::

ቅዱስ አይደለሁም፥
የጻድቃን ቤት ካለ፥ በውስጡ የለሁም::
መናኛው ራሴ፥ ቢበጠር፥ ቢላጭም
ለሳር ባርኔጣ እንጂ፥ ላክሊል አይታጭም::

ምንድን ሆኘ ነው ግን?
ራሴን ወግቼ ላንቺ የምወግን
ምኔን አሞኝ ነው ግን ?
እንችን የማሞግስ፥ ራሴን ወቅሼ
ሳቄን የማካፍል፤ ለብቻየ አልቅሼ፤

እንደ ጋሻ ጃግሬሽ ፤ ከሁዋላሽ ስባክን
ከፊትሽ ቀድሜ፥ እንቅፋት ሳመከን
አይተሽ እንዳላየ
ጀግኖች ምናረጉ
ሰማታት ምን ሰሩ፤ ከዚህ የተለየ፥


https://t.me/write_event
።ፍቅር- ፈራን:ጠላን።🖤

"ፈራን"🖤
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን

ሌሬት ፀጋዬ ገ/መድህን


https://t.me/write_event
የወደፊት ሲደምቅ!

“ለወደፊቱ ራእይ የሌለው ሰው ሁል ጊዜ ወደኋላው ይመለሳል” (Kevin Gates)

ካለፈውና ካከተመለት ነገር ትምህርትን አግኝቶ ወደፊት ከመገስገስ ይልቅ እሱን እንደገና እያሰቡ የመጨናነቅ፣ የመረበሽና ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ የሚያጠቃችችሁ ከሆነ ምናልባት የወደፊት ራእይ ያለመኖሩ ምልክት እንዳይሆን ጠርጥሩ፡፡

የወደፊታችሁ እየፈዘዘ ከሄደና ማየት ከተሳናችሁ የኋላችሁና ያለፋችሁት ነገር መድመቅና መጉላት ይጀምራል፡፡ በሌላ አገላለጽ የአንዱ መድመቅ የሌላኛው መደብዘዝ ነው፡፡ ምርጫው ግን በእጃችሁ ነው፡፡

ያለፈ ጉዳት … ያለፈ የተሳሳተ ውሳኔ … ያለፈ ክስረት … ያለፈ ተጀምሮ የተቋረጠ ነገር … ያለፈ ጎድቶንና ትቶን የሄደ ሰው … እየተመላለሰ ስሜታችሁን ቀውስ ውስጥ የሚጨምረው ከሆነ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀርፍላችሁ ብቸኛ ነገር የወደፊታችሁን ራእይ ማየትና እሱ ላይ ማተኮር ነው፡፡

የወደፊት ራእያችሁ ካለፈው ታሪካችሁ ሊጠነክርና ሊደምቅ ይገባዋል፡፡

ያለፈው ታሪካችሁ ከሚሰጣችሁ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይልቅ የወደፊታችሁ የሚሰጣችሁ የመጓጓት ስሜት ሊያይል ይገባዋል፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@write_event
@write_event
@write_event
"ዓለም ከንቱ ዓለም ብላሽ
ላንዱ ንፉግ ላንዱ አጉራሽ"

#ጌትሽ ማሞ
#KE_HASAB_ALEM

@write_event
@write_event
@write_event