ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
------
.
እንባ ዘፈን መስሎ
ፊቷን አረጠባት ፣
እሳት ውሃ መስሎ
ገላዋን አጠባት ፣
.
ጠላት ወዳጅ መስሎ
ቀሚሷን ገለጠው
ዝም አለች ለዘመን
መከራ ነው መሰል ፥ ትርጉም የሚሰጠው ።
.
ማጣት ተስፋ መስሎ
መንገድ አስጀመራት ፣
ዛሬ ነገ መስሎ
ወደ ትናንት መራት ፣
.
ድንጋይ ድልድይ መስሎ
እግሯን አነቀፋት ፣
ዝም አለች እንደ ጉድ
ኖርኩ አትልም መሰል ፥ ስቃይ ካላቀፋት ።
.
.
አንጀቷን አንጥፋ
ልቧን  አንጠፍጥፋ
እንደምን ለመደች ፣ ይሁን ብሎ ማለፍ፣
እንደምን ለመደች
ለሳቅ ሲፈልጓት ፣ ለሃዘን መሰለፍ ፣

እንደምን ለመደች ፣ እንደምን ሆነችው ?
እመጣለሁ  ሲላት ፥ ለምን አመነችው ?

ምክያት

ስለወደደችው ።

_
ሶሎሞን ሽፈራው

@write_event
💚💚💚

የቅኔ ምርቃት ከሩሚ
"You are not a drop in the ocean, You are the entire ocean in a drop."
Rumi
"ጠብታ አይደለህም
ባህር ውስጥ የገባህ፥
ባህሩ አንተ ነህ
በጠብታ የሞላህ"
ሩሚ
ትርጉም - ጫንያለው በቀለች ወ/ጊዮርጊስ

@write_event
@write_event
@write_event
የዝምታ ጩኸት
.
.
ተሳዳቢ አንደበት ሰሚ አልባ ጆሮ፤
ፅልመት የወረሰው ትርጉም አልባ ኑሮ፤
ከተስፋ ጉልላት አሽቀንጥሮ ሚጥል፤
ትንፋሽ አሳጥቶ በቁም የሚገድል፤
መቅኒ የሚያፈስ አጥንትን ሰርስሮ፤
ወላፈኑ ሚፋጅ የስሜት አቀበት፤
ሌላው የማይሰማው የዝምታ ጩኸት።

  በኤደን እንደተፃፈ )
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችል ባንድ ወቅት ይህ አስቂኝና ቁም ነገር ገጥሞት ነበር .....

"አንድ ቀን ወደ ቢቢሲ ቢሮ ለቃለ መጠይቅ ለመሄድ ታክሲ ያዝኩኝ፤ቢሮዉ እንደደረስኩ ባለታክሲውን ቃለመጠይቁን ጨርሸ እስክመለስ ለ40 ደቂቃ ያህል እንዲጠብቀኝ ጠየቅኩት።ባለ ታክሲዉም ይቅርታን በማስቀደም "አልችልም ምክኒያቱም እቤቴ ሂጄ ከደቂቃዎች በኋላ ዊንስተን ቸርችል የሚያደርገዉን ቃለመጠይቅ መስማት እፈልጋለሁ።"አለኝ
የእኔን ንግግር ለመስማት ይህን ያህል በመጓጓቱ በጣም ተደነቅሁ፤ ኩራት ቢጤም ተሰማኝ።ማንነቴን ሳልገልፅለት ለታክሲ አገልግሎቱ መክፈል ከሚጠበቅብኝ በላይ መልሱ ስላስደሰተኝ 10 ፓዉንድ ሰጠሁት።ባለ ታክሲዉም የሰጠሁት ብር በደስታ አየቆጠረ"ጌታዬ እስከ ምትፈልገዉ ስዓት ድረስ እጠብቅሃለሁ ሲፈልግ ዊንስተን ቸርችል ገደል መግባት ይችላል!"ብሎኝ አረፈ

ሀሳብ ለብር ሲባል ይቀየራል፣ሀገርን ለብር ሲሉ ይሸጣሉ፣ክብርን ለብር ሲሉ ይሸጣሉ፣ቤተሰብ ለብር ሲባል ይበተናል፣ጓደኞች ለብር ሲሉ ይለያያሉ፣ሰዎች ለብር ሲሉ ክቡር የሆነውን የሰዉ ልጅ ይገድላሉ፣ሰዎች ለብር ሲሉ ባሪያ ይሆናሉ።

ብር....................
Jemal Ahmed Aragaw ገጽ የተወሰደ

https://t.me/write_event
ገንዘብን ተጠቀሙበት በራሱ መልካም ነው። ነገር ግን ፍቅርን ከገንዘብ ለማግኘት አትሞክሩ። ምክንያቱም ፍቅር የውስጣችሁ ነው። የውስጠኛው ህልውና ነው እግዚአብሔርንም ከገንዘብ ዘንድ አትፈልጉት። እርሱ ከአለማት ሁሉ በላይ የላቀና ያለፈ ነው። እያንዳንዱ ነገር በእናንተ የህልም መጠን ሳይሆን በገዛ ራሱ አቅም ተጠቀሙበት። በዚህም ጊዜ ጤናማ ሰው ናችሁ። ጤናማ መሆን ደግሞ ቅዱስ መሆን ነው።
*
ኦሾ/Osho

https://t.me/write_event
| በአንድ ወቅት አንድ ጋቭሮብ ይቸገርና ብር ለመበደር ወደ ሌላኛው ጋቭሮብ ጓደኛው ቤት በምሽት...
Book for ALL | Facebook (Facebook)

በአንድ ወቅት አንድ ጋቭሮብ ይቸገርና ብር ለመበደር ወደ ሌላኛው ጋቭሮብ ጓደኛው ቤት በምሽት ያመራል። እሳት ዳር ቁጭ ብለው እያወጉም የገጠመውን ችግር ለጓደኛው ያወያየውና ለስራ መጀመሪያ የሚሆነውን የተወሰነ ብር እንዲያበድረው ይጠይቀዋል። ጓደኛውም በሀዘኔታ የተባለውን ብር ቆጥሮ ይሰጠውና የጓደኝነት የእሳት ዳር ወጋቸውን ቀጠሉ። በመሐል ግን ፡ ብር የተበደረው ጋቭሮብ ከአንደኛው ኪሱ ውስጥ ሲጃራ ያወጣል ፣ ከሌላኛው ኪሱ ውስጥም ክብሪት ያወጣና ሲጃራውን ለኩሶ ማጨስ ይጀምራል። በዚህን ጊዜም ፡ አበዳሪው ጋቭሮብ "እስኪ ቅድም የጠሰሁክን ብር አንዴ ስጠኝ። በትክክል የቆጠርኩት አልመሰልኝምና ደግሜ ልቁጠረው!" በማለት ጓደኛውን ጠየቀው። ተበዳሪው ጋቭሮብም ምንም ሳያመነታ ብሩን አውጥቶ ድጋሚ ይቆጥረው ዘንድ ለአበዳሪው ጓደኛው ሰጠው። አበዳሪው ጋቭሮብም ብሩን በእጁ ካስገባ በኋላ ፡ ተበዳሪ ጓደኛውን "ጓደኛዬ ሆይ! ፊት ለፊትህ ይህን የመሠለ ቦግ ብሎ የነደደ እሳት እያለልህ ፡ ሲጃራህን ለመለኮስ አንዲት ክብሪትን በመጫር ያባከንክ ሰው ፡ ነገ ነግደህ ያበደርኩህን ብር ትመልሳለህ ብዬ ስለማላስብ ማበደሬን ትቼዋለሁኝ!" አለውና እሳቱ አጠገብ ቁጭ ያለውን ተበዳሪ ጓደኛውን ጥሎት ወደ ቤቱ ገባ!🙄....

ትንሽ ቀልድ መሳይ ታሪክ ናት። በውስጧ ግን ትልቅ አስተምህሮን አዝላለች። ሰዎች ከአፋችን በሚወጡ ትናንሽ ቃላቶች ጭምር ማንነታችንን ይዳኛሉ። በምንተገብራት ትንሽ ተግባርም ብትሆን ሰለ ማንነታችን ይገምታሉ። ልክ በትልቅ ድስት የተሰራን ወጥ ፡ ጠብታውን ብቻ በመቅመስ "ወጡ ጨው አለው ወይም አንሶታል ፣ ወጡ ይጣፍጣል ወይም አይጣፍጥም... ወዘተ" እያልን የትልቁን ትድስ ወጥን እንደምንዳኘው ሁሉ ማለት ነው። ሰዎችም ከውስጣችን በወጣች ትንሽ ቃልን በመስማትና ፡ ከልባችን የተገበርነው ትንሽ ተግባርን በመመልከት ማንነታችንን ይዳኛሉ! በእለት ተእለት የምንተገብራቸው ትናንሽ ተግባሮችና የምናወራቸው ትናንሽ ቃላቶች የማንነታችን መገለጫ ናቸውና እራሳችንን ለመፈተሽ ይጠቅሙናል! ይኸው ነው!🙏
https://t.me/write_event
‿︵︵‿ የታላቁ ፈላስፋ የዲዩጋን ምርጥ ምላሾች!! ‿︵︵‿︵
በቆሻሻ ቦታ ሲዘዋወር የተመለከተው የአቴና ነዋሪ ወዳጁ
ቢገስጸው፡-
‹‹አትሳሳት! ጸሀይ የማትወጣበት ቦታ የለም እስከዛሬ ግን
አልቆሸሸችም ብሎታል››፡፡
በሌላ ግዜም በገበያ ቦታ ላይ ሲበላ የተመለከቱት የአቴና
ነዋሪዎች በዙሬያው ተሰብስበው
‹‹ውሻ ውሻ ! ›› በማለት ሲጮሁበት፡-
‹‹እኔ የማውቀው ሰው ምግብ ሲበላ በዙሪያው ከቦ
የሚመለከትና የሚጮህ ብቻ ነው››በማለት
መልሳል፡፡
ሰዎች ለለማኝ እንጂ ለምን ለፈላስፋ ገንዘብ እንደማይሰጡ
ሲጠይቁት
‹‹ምክንያቱም አንድ ቀን ለማኝ እንጂ ፈላስፋ እንደማይሆኑ
ስለሚያውቁ ነው›› ብላቸዋል፡፡
ምግብ ለመመገብ የተመቸ ሰአት የቱ እንደሆነ ተጠይቆ፡-
‹‹ሀብታም ከሆንክ ስትፈልግ'ድሀ ከሆንክ ደሞ ስትችል ምግብ
ለመመገብ ጥሩ ሰአት ነው››ብላል፡፡
ለዲዩጋን ምጽዋት የሚሰጡት ሰዎች ለምን
እንደማያመሰግናቸው ሲጠይቁት
‹‹እናንተ በመስጠታችሁ ብቻ ሳይሆን እኔም የናንተን ምጽዋት
በመቀበሌ ምስጋን ይገባኛል››ብላቸዋል፡፡
ስለጸሎተኛ ሰው ሲጠይቁት
‹‹ጸሎተኛ ሰው የሚፈልገውን እንጂ መጠየቅ የሚገባው
የማይጠይቅ ሰው ነው››ብላል፡፡
ሲሞት እንዴት እንዲቀብሩት እንደሚፈልግ ሲጠየቅም
‹‹ፊቴን ወደታች ዘቅዝቃችሁ ቅበሩኝ
ምክንያቱም ዝቅ ያለ ነገር ጥቂት ቆይቶ ከፍ ማለቱ እንደማይቀር
ስለማውቅ ነው›› ብላቸዋል፡፡
እንድ የአቴና አስተማሪ ስለህይወት ክፉነት ደጋግሞ
ሲያስተምር ሰምቶ
‹‹ህይወት ክፉ ያደረጋት የሚኖራት እንጂ ህይወት በራሷ ክፉ
አይደለችም››ብሎታል፡፡
~~ በባርነት የገዛው ዜነዲየስ ‹‹እኔን ልትታዘዝ የግድ
ነው››አለው፡፡
‹‹ምንም እንኮን ባሪያህ ብሆንም አዋቂና የነቃ ሰው በባርነትም
ሆኖም ሊታዘዙት ያስፈልጋል››፡፡


https://t.me/write_event
ይቺን ቃል ንገሯት
...(አስቱ)
.
ተፈርዶብኝ እንጂ
መለ'የት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ
እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል
.
ዞር ባለች ቁጥር
አትራቂኝ እያልኹኝ የምለማመጣት
ልቻለው ብዬ እንጂ
ምሳሌ ከመሆን አፍቅሮ ከማጣት
.
"ገደል ግቢ" በሏት
.
. ይህው ደሞ ዛሬ
ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን
.
ከንፈሯን ምን ይሆን ደሞ የቀባችው!
የጇን አይበሉባ በቄንጥ አኮናትራ ሰአቷን አየችው...

.(ገና ነው መሰለኝ)
.
ጊዜን ታዘበችው
ባፏ ሸብረክ አርጋ እየገረመመች
መንቀር አለችና
እግሯን አመሳቅላ መስታወት ፊት ቆመች.
.
(ደሞ ፈገግ አለች
'
ጥርሷ ይርገፍና!

ማርያምን ታምራለች)።
.
"ገደል ግቢ" በሏት...
.
ዘከርኳት በወዳጅ መከርኳት በዘመድ
ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ .
.
ገደል ግቢ በሏት.
.
ልቧን ከጋረደው
ወዳጅ ከከለላት ስውር አይነጥላ
እንዲህ እንዳማረባት
መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰው ጥላ
.
"ልክ እንደገላዋ ይለስልስ መንገዱ ፍፁም አይጎርብጣት
አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት እንደ ጥርሷ ንጣት.".
.
አያልኩኝ መርቄ
እንደ ገጣሚ ቃል ልቤን አልጀነጅን
የታባቷንና
በፀበል ካሎጣች ትረሳለች በጅን።

"ገደል ግቢ" በሏት.
.
ልርገማት እስከጥግ
የታባቷንና ልንገራት የልኳን
እንዲህ ምታረገኝ
ጠባቂዋንና ተማምና አደል መልኳን!
.
የታባቷንና እንዲ የሚያምርባት
የት'ናቷንና እንዲ ሚደምቅባት
.
እስከመቼ ድረስ
ስቀባ እኖራለሁ ጉድፍ ልቧን ስኩል!
(ገደል ግቢ በሏት)
እኔ _ ገደል ስር ነኝ
ደንገት ከወደቀች በቆሻሻው በኩል ::
.
(ምን አደርገዋለሁ)


https://t.me/write_event
ህልም እንደ ፈቺው ነው..!

ሰውዬው በህልሙ የከተማውን ከንቲባ በአለንጋ ሲገርፈው ተመለከተ። ሲነጋ ክስተቱን ለሚስቱ ነገራት። እሷም «አለሚቱ» ለተባለች ጎረቤቷ አጫወተቻት። ወሬው እየተራባ በንፋስ ፍጥነት የደህንነትና ጸጥታ አካላት ጆሮ ደረሰ። ሰውዬውን ምሽት ላይ አፍነው ከቤቱ ወሰዱት። አጓጉል አድርገው ከሰባበሩት በኋላ ማለዳ ላይ ከቤቱ ደጃፍ ፊት ለፊት ጣሉት። እንደ «ጀሶ እንጀራ» ልንኮታኮትለትና «አከመሌ» አደረጉት::

ስቃዩ ብርቱ ስለነበር ቀኑን ሙሉ ሲጮህ ዋለ። የጸጥታ አካላቱ ምሽት ላይ በድጋሜ በሩን አንኳኩ። ሲመለከታቸው «ኧረ ባካችሁ ወላሂ ተጸጽቻለሁ፤ እንዲህ አይነት ህልም ዳግም አልመለከትም» | አላቸው። «አይ አሁን እንኳ የመጣነው በህልምህ ከንቲባውን ስትገርፍ እጆቹን ጠፍሮ የያዘልህ ማን እንደሆነ እንድትነገረን ነው» አሉት። ምን ቢል ጥሩ ነው ... «ሚስቴ እና ጎረቤቴ አለሚቱ ናቸው»

ለማን ምን እንደሚነገር እና እንደማይነገር መለዬት ተስኖህ እንደሚያፈስ ስልቻ ምስጢርህን ሁሉ በየቦታው የምትዘራ ከሆነ በጀመዓ ትሞታለህ። ፌስቡክ ከግቢህ ውስጥ የተወጠረ የልብስ ገመድ ይመስል ሁሉንም የምታሰጣበት ከሆነ አላፊ አግዳሚው ነውርህን እየቆጠረ ቀን ጠብቆ ይሰብርሃል።

https://t.me/write_event
ከባለፀጎች አንደበት !

ጋዜጠኛዋ ቢሊኒየሩን ቃለመጠይቅ እያደረገችለት ነው… የስኬትህ ሚስጥር ምንድነው?
ቢሊየነሩ ባዶ ቼክ ለጋዜጠኛዋ አቀበላትና የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ ፃፊበት አላት!
ጋዜጣኛዋ በእንቢታ ቼኩን እየመለሰች «አይ እኔ እንደሱ አይነት ነገር ፈልጌ አይደለም የስኬት ሚስጥሮን መጠየቅ ፈለጌ እንጂ» አለች።
ቢሊየነሩ ድጋሚ ቼኩን መልሶ ሰጣትና «የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ ፃፊ» አላት።
ጋዜጠኛዋ እንቢ አሻፈረኝ አለች።

ቢሊየነሩ ቼኩን እያሳያት «የስኬቴ ሚስጥር አሁን አንቺ ያጋጠመሽን አይነት እድል አሳልፌ አለመስጠቴ ነው…የስኬቴ ሚስጥር ያገኘሁትን እድል ሁሉ መጠቀሜ መው።
አሁን አንቺ እንድልሽን ተጠቅመሽ ቢሆን ኖሮ የአለማችን ሃብታሟ ጋዜጠኛ ትሆኚ ነበር… እኔ ሁለቴ እድል እንደሰጠሁሽ አለም ሁለት እድል አትሰጥሽም አንዴ ያጋጠመሽን እድል መጠቀም የስኬት ሚስጥር ነው»

https://t.me/write_event
ደራሲው
(አለማየሁ ገላጋይ ከመአዛ ብሩ ጋር በሸገር ካፌ ከተጨዋወቱት)

የደራሲዎችን ምስል በተደራሲያን ዘንድ አብዮታዊ በሚባል መልኩ የቀየረው የበአሉ ግርማ ‘ደራሲው’ ነው። በመጠኑ ደግሞ የቀይ ኮከብ ጥሪ(በተለይ ደግሞ አንዱ ገፀባህሪ አእምላፍ) በአሉ ደግሞ ለዚህ መፅሀፉ እንደ ሞዴል አድርጎ የተጠቀመው ጋሽ ስብሐትን ነው። በአሉ እራሴን ሞዴል አድርጌ ብፅፍ ልክ አይመጣልኝም ብሎ ጋሽ ስብሐትን አስፈቅዶ ደራሲው ተፃፈ።

በመጽሐፉ ዋናው ገፀባህሪ ሲራክ ይባላል። ሲራክ የጋሽ ስብሐት አምሳያ ነው። ጋሽ ስብሐት ደግሞ ቃሚ፣ ጠጪ፣ ራሱን ብዙም የማይጠብቅ ደራሲ ነበር። ማህበራዊ ህይወቱ ደካማ፣ የሴት ጓደኛውን ሕይወትን ተመልከቺ እያለ ወደ ሌላ ወንድ የሚገፋ። የደራሲ ምልከታ እየተበላሸ የመጣው ከዚህ ወዲህ ነው። ደራሲ ሲባል ፀጉሩን የማያበጥር፣ ጫማው የተንሻፈፈ፣ ሰውነቱ ጥሙጋ፣ ሱሰኛ ወዘተ።

የጋሽ ስብሐት ህይወት ከበአሉ ብእር ጋራ ተቆራኝቶ ሃያል ተፅእኖ ፈጥሯል።በተደራሲ አእምሮ ውስጥ የደራሲ ምስል ሆኖ ተቀርፆ የተቀመጠው ጋሽ ስብሐት ነው።

በአሉ ራሱን ሞዴል አድርጎ ቢሆን ነገሮች ሌላ መልክ ይይዙ ነበር። በአሉ በጣም ንፁህ፣ ሽቅርቅር ደራሲ ነበር። በመንገድ እየሄደ ጫማውን ትንሽ አቧራ ከነካው እንኳን ቆም ብሎ በመሀረብ ሳይወለውል መንገዱን አይቀጥልም። በአሉ ሁሌ ዘናጭ፣ አንደበቱ ቆጠብ ያለ፣ ከአንገቱ ከረባት የማይለይ፣ ሽቶው ከሩቅ የሚጣራ፣ ሸሚዝ ግማሽ ቀን ላዩ ላይ ከቆየ የሚቀፈው ፣ ጢሙን ቀን በቀን የሚላጭ ነበር።

ሌሎች ቀደምት ደራስያንን ብንመለከትም ታሪኩ ከደራሲው ገፀባህሪ ሲራክ እጅግ የተለየ ነበር። አብዛኛዎቹ ሚኒስትር የነበሩ፣ የመንግስት ወኪል የነበሩ፣ ራሳቸውንም የሚጠብቁ፣ ክብራቸውንም፣ ልብሳቸውንም ከሱስም የተጠበቁ ነበሩ። ከበደ ሚካኤል በጣም ሽቅርቅር ነበሩ። መኮንን እንዳልካቸው ራሳቸው ሚኒስትር ደረጃ የደረሱ ነበሩ። ልጃቸው እንዳልካቸው መኮንን እንደ ራሳቸው ደራሲ የነበረና በመንግሥት ሥልጣንም ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ የደረሰ ነበር። አፈወርቅ ገብረየሱስ ራሱ እንደ ሚኒስትር ሊቆጠሩ የሚችሉ፣ በሁለት ሃገሮች ጉዳይ ላይ በማማከር እጃቸውን ያስገቡ ሰው ነበሩ። ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደሥላሴ ባህላዊ አለባበሳቸው በራሱ ግዝፈትና በሚመለከታቸው ሰው ላይ ጫና የሚያሳድር፣ ከላይ ካባ ከውስጥ ቀጭን ኩታ የማይለያቸው ነበሩ። ሀዲስ አለማየሁ በባለቤታቸው ክበበ―ፀሐይ ለተሰየመው ወላጅ ለሌላቸው ልጆች ማሳደጊያ እንዲሆን 3000 ካሬ ሜትር ቤታቸውን የሰጡ ነበሩ።

ስብሐት ድንቅ ስብእና ነበረው። አይካድም! ነገር ግን የግል ህይወቱ የሚያስቀና አልነበረም። በአሉ ከነዚህ ሁሉ ደራሲዎች ስብሐትን ሞዴል አድርጎ በመምረጡ የደራሲነት ምስል ተሰባብሮ፣ እግራችን ስር ድቅቅ ብሎ ተዘረረ።

አንድ ግዜ ‘60 ሻማዎች’ የተሰኙ የወጣቶች የስነጽሑፍ ማህበር አባላት አለማየሁ ገላጋይን ለአንድ ጉዳይ ይቀጥሩታል። ወጣቶቹ ከዚህ ቀደም አለማየሁን በአካል አያውቁትም ነበር። አለማየሁ ወጣቶቹ ከቀጠሩት ቦታ ደርሶ አጠገባቸው ሆኖ ወጣቶቹ እርስ በእርስ ከተላላፊ መንገደኞች መሐል ጥሙግ ያለ፣ መሄድ ያቃተው፣ ፀጉሩ የተንጨባረረ፣ ሲጋራ የያዘ፣ በሱስ የናወዘ ሲያዩ

"ያ ነው! ያ ነው!" ይባባላሉ።

አለማየሁ አጠገባቸው ተቀምጦ የሚባባሉትን ትንሽ ከሰማ በኋላ፦

"አለማየሁ ገላጋይ ማለት እኔ ነኝ!" አላቸው። ወጣቶቹ አመዳቸው ቡን ብሎ፦

"ውይ! አትመስልም!"

😂

https://t.me/write_event
​​~~~~እኔ ወድሻለሁ~~~~

እኔ ወድሻለሁ፤ ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት፤ እንደ ዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ ፤ደርቦ እንደመምታት
እኔ ወድሻለሁ፤
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት፤ ግማሽ እንደመውረስ
እኔ ወድሻለሁ፤ እንደ መቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ፤ ያንች ልዝብ ሰይጣን።.

✰ገጣሚ ፦በእውቀቱ ስዩም

https://t.me/write_event
የዛሬ መቶ ዓመት ማንኛችንም አልነበርንም።ከመቶ ዓመት በኋላም አንዳችንም አንኖርም። ይህንን ከልባችን ማሰብና አስረግጠን መረዳት ብንችል ትንሽ መተዛዘን የተሻለ_መተሳሰብ ያለንን ተከፋፍለንና ተረዳድተን አብረን በሰላም መኖር ብንችል ምን እንሆናለን ??? ሀገር የጭንቅላታችንን እንጂ የቆዳ ስፋቷን ያህል አይደለችምና።

ዶክተር_ምህረት_ደበበ


@write_event
"የተዘጋ ሀሳብ"

( በኤፍሬም ሥዩም)


☞ እዚህ……
ሙዚቃ ከሌለው ስሜት ከማይሰጥ ቤት
ሀዘን ያልተለየው የከሰለን ህይወት
አዳፋ ለባሾች የቀን ሰራተኞች
ንቃቃታም ሴቶች ጉሊት ቸርቻሪዎች
አግዳሚ ወንበሩን ሚስኪኖች ከበውት
ማገር የሌለውን ጠባቡን ያፈር ቤት
በጠላ ባረቂ በጠጅ አጅበውት።
.
ከኑሯቸው በላይ ጫጫታቸው በዝቶ
ካዘናቸው ይልቅ ሳቃቸው ተሰምቶ
አንዱ ድሀ ዘፋኝ አንዱ አጨብጫቢ
አንድኛው ፎካሪ የጋባዥ አጃቢ
ባንድነት ተፋፍገው እየተማማሉ
ምግብ አልበላንም እየተባባሉ
ለድሃ እሚራራ ነፍስን ያደማሉ።
.
☞ እዚያ....
ጥቂት ሹማምንቶች የመተያያን ገንዘብ 'ሚጥሉበት
አጥተው
የግፍ ነጋዴዎች ንጋት ሳይቀድማቸው
ያልፈኩ አበቦች ከሚቆረጡበት
ለአይን የሚያሳሱ እንስቶች ካሉበት
ልክ በሌለው አፍ ዘፈኑ ተከፍቶ
የሚረግጠው ስፍራ እግራቸው ቦታ አጥቶ
በሬጌና በቫልስ፣ በቡጊ በቻቻ በሳንባና በራፕ፤
እንዲሁም በስክስታ ጭፈራቸው ደርቷል
የቀን ግፋቸውን ግድ የለሽ አይምሮን በውስኪ ያጥቡታል።
.
ከደጅ ከሀብታሞች ቡና ቤት፣ ድሆችም ባሉበት ካረቂ ቤቱ
በር
ከገንዳ ላይ ለቅሞ ሆዱን የሚሞላ አንድ ሚስኪን ነበር።
.
☞ እኔ .....
ሀብትን ከማይጠሉት ለድሆች ከሚያዝኑት መካከል ላይ
ቆሜ እሰቃይ ነበረ...
እውነት በሚሰፍር ቀን በሚታይ ህልሜ።
.
☞ ገንዳ ለቃሚው....
ኑሯቸው ነው ብለህ ስለነዚህ ድሆች ስለምን ታዝናለህ
እኒህ ትንሽ ድሆች ሀብት ቢሞላቻው ብር ቢተርፋቸው
ከባንኮኒ ቆመው ከመጠጣት ሌላ ምንድን ነው ትርፋቸው?
ምንድን ነው ተስፋቸው ገንዳው ላይ ለቆመው?
.
እኒህስ ሀብታሞች ከውስኪ ቤት አልፈው
ከመግባት ውስኪ ቤት
አንዷን ቆንጆ ትተው ከማቀፍ ሌላ ሴት
አይምሮአቸው ሂዶ ደርሶ የሚያርፍበት
አዲስ ኬላ የለም ሰርተው የሚፈጥሩት።
.
ስለዚህ ግጥምህን እንዲህ ብለህ ዝጋው
እንደዚህ አትማው
ሰካራም ድሃና መጠን አልባ ሀብታም
ፍፃሜው አንድ ነው
ከባንኮኒ ቆመው ከአግዳሚ ተነስተው ውስኪ ለማድረግ
ነው
አረቄውን ደፍተው።



(ከሶልያና የግጥም ሲዲ የተጻፈ)


@write_event
" # እጅ_ከፍንጅ "?
-
አንዲት ባለትዳር ፥ በጓዳዋ ሳለች ፥ ጉንዳን ቆነጠጣት
ከእግር እስከ ራሷ ፥ ተርመስምሶ ገብቶ ፥ ነክሶ ፋታ አሳጣት
-
ይሄን ጊዜ ጮኸች፤
ልብሶቿን አራግፋ ፥ ራቁቷን ቀረች!
-
ጩኸቷን የሰማ ፥ ላጤ ጎረቤቷ ፥ ገባ ተንደርድሮ
ያቺን ቆንጆ እንስት ፥ እርቃኗን ሲያያት ፥ ቀረ ተገትሮ!
-
በዚህ ሁነት መሃል ፥ ሰይጣን አይኑን ሲጥል ፥ ባል ድንገት
ይደርሳል
ሰበብ የጠፋ 'ለት ፥ የጉንዳን ወረራ ፥ ትዳርን ያፈርሳል ።
---------//----------
( በርናባስ ከበደ )

https://t.me/write_event
( በወዳጃችን ጥያቄ የተደገመ....)

አንቺነት ሰይጣኑ ከኔነት ጋንኤል



አየሽ....
የሄደው ሲመጣ
የመጣም ይሄዳል

ከመንፈስሽ አስኳል
ካንቺነትሽ ጫፍ ላይ
የሚቀርሽ እውነት ብቻነት ይባላል፡፡

ትዝ ይልሻል ያኔ -!?

ከትዝታሽ ማኅደር
ስለተሰደረ ታጅሎ ኩነኔ
ማስታወስሽ አለ እልህ ቋጥሮ ካይኔ፡፡

እናም...
ትዝ ይልሻል- -፤

ሀይማኖት ልንማር
እምነት ልንሰበክ
ከቤተ - እምነታችን
በም’መናን ፅናት ካ’ውደ - ም’ረት ውለን
በሊቀ - ቀንዳችን እግዜር ሲነገረን - !?

ከቤተ - ዓምልኳችን
ቅፅር አለፍ ብሎ ድሪቶውን ለብሶ

እሱም ተደራርቶ
እንዳልባሌ ቁስ ነፍሱ ላይ ተኝቶ
ለሌላው አይን ሻግቶ

ያለፍነው ያ ነዳይ...!!
ብጤያችን ያልሆነ የኛ ብጤ ተባይ
የኛ ብጤ መሳይ...!!!

ምንድን ነበር ያልነው - !?

“....የለማኝ ሀገር ልጅ
የመለመን እጣው ደምቆ የተፃፈ

የማሳፈር ገድሉ
የማሰደብ ሀይሉ
እንደመልካም ታሪክ ጠሎ ያሰፈፈ፡፡

መለመን
መለመን …!!!
ሀገሪቱ ለማኝ

ዜጎቿ በሙላ
የለማኝ ልጅ ሁላ
ነዳይ በጠቅላላ፡፡

ከልመና ከርስ ውስጥ ነፍሳቸው ተጥላ

በቧጋች ማንነት
መፅዋች በመፈለግ ያለች ተንጠልጥላ
አሳሯን አጥልላ....፡፡”

አልነበረ ያልነው - !?

ሀገርን....ዜጎቿን
በማን አለብኝ ልጥ አስረን የዘለፍነው - !?

አየሽ …
ሐረግና ማማ
ሆኖ መተቃቀፍ ለሁሌው ይመስላል

እጣ ክፍልሽ ሲሆን
የያዙትን መልቀቅ ያነሱትን መጣል

“እኔነት” የሚባል
የሚያውቁት ዲያቢሎስ
ከማያውቁት መላ’ክ ላይሻል ይበቅላል፡፡

አየሽ …
ካድማሱ ገመገም ከተራራው አናት
ሰማዩን ልቀርበው ልደመም በውበት
የያዘኝን ፍቅር ልይዘው በግዞት

- - ቆሳስዬ ወጣሁ - -

ሰማይ ከተራራ ካድማስ እንደሚርቅ
የተራራው ጉጠት የሜዳው ሌላ መልክ

- - መሆኑን ተረዳሁ - -

አየሸ …
የቀን ሲቀርቡት ሌላ ርቀት አለ፡፡
ጥልቁንም ሲደርሱት ሌላ ጥልቀት አለ፡፡

የያዘኝ ፍቅርሽ ውስጥ ምስልሽ ተንፈላ’ሷል
የደለው ምስልሽ ውስጥ
ሊነኩት
ሊደርሱት ሊየውቁት የማይቻል
አንቺነት ተኝቷል፡፡

እኔነት አጋንንት እኔነት ጋንኤል
ካንቺነት ሰይጣኑ
ካንቺነት ደያቢሎስ
ፍቅር ይሉት አዘቅት ውስጥ ወድቆ ይዳክራል፡፡

ትዝ ይልሻል ያኔ - !?

ሃይማኖት ሲሰብኩን
ማመን ሲያስተምሩን.....

ገኖ የከበረ
የገዢዎች ሁሉ ገዢያቸው የሆነ
“ፍቅር እግዜሩ ነው” ብለውን ነበረ፡፡

ልሳን ብናወራ
ጥበብን መርምረን ጉባኤ ብንመራ

አውቀን ብንመነጥቅ
ከልባችን ሙዳይ ፍቅር ካልሆነን ስንቅ

ከንቱ ነው ብለዋል ከምኩራብ ላይ ቆመው
በኩራት ተጠምቀው፡፡

የሉት ይመስልሻል - !?
’ውነት ነው ብለሻል - !?

የተኛን መቀስቀስ
ፀላየ ሰናይን
ማገጠም ከሆነ ከፍተኛ ግብሩ

አንድነት መዘመር
በሚል ቃል ጠፍሮ
መለየት ከሆነ ዕፀ - መሰውሩ

“ፍቅር” ለሚለው ቃል
ሃይማኖት አብሏል
ማር የተለወሰ እሬት ሆኖ ቀርቧል፡፡

’ውነት ግን - !?
’ውነት ግን - !?

- - እንዲያ ነው እግዜሩ - - !?

እኔነት ካንቺነት ለህመም ሲጣመሩ
ለሞት ሲቃጠሩ -፤

መለየትነ ቋጥረው
ከጊዜው ሸሽገው አብሮነት ሲያወሩ

ኖረው የሚያልፉበት
ገድለው ’ሚኖሩበት

- - እንዲያ እኮ ነው ፍቅሩ - -!!!

እኔነት ካንቺነት
ስጋት ረግረግ ውስጥ ተውጠው እያሉ

ፀሀይን ለተስፋ
ጨረቃን ለማጌጥ ይዘናል እያሉ

የሚታበዩበት
የታይታ ህይወትን የሚያራምዱበት

- - እንዲያ እኮ ነው ፍቅሩ - -!!

አየሽ …
የሄደው ሲመጣ
የመጣም ይሄዳል

ከመንፈስሽ አስኳል
ካንቺነትሽ ጫፍ ላይ
የሚቀርሽ እውነት ብቻነት ይባላል፡፡

- - ጥለሽኝ ስለሄድሽ - -

ነፍሴን ጎርፍ ሞላት
የልቤ ክረምቱ
ፀደዬን ገደለ ደመና አረገዘ

በነዝናዛ ካፊያ
ዘላለም በሚመስል
አሰቃቂ ውድቀት መንፈሴ ተያዘ፡፡

- - ጥለሽኝ ስለሄድሽ - -

ስለኔ መኖሬ
ስለኔ ማደሬ
ስለኔ ማዝመሬ መሰለኝ ተረቴ
እንዲህ የምቀምሰው የእጦት ዳረጎቴ፡፡

“… እኔነት የሚባል ካንቺነት የዋለ
ካንቺነት ያደረ
ጋንኤል ነበረ … (!?)

ግና ካልነበረ...
ዳቦውን ሳትቆርሱ
አፍም ሳታብሱ
ተረት አትመልሱ …”

አየሽ …
ጥለሽኝ ስለሄድሽ ‘ነበር’ እንኳን ጣለኝ
እኔነቴ ብቻ ችንካሩ አሳዘነኝ።

የጭንቅ ስቅላቱ
ዳር...ወሰን አልባነት ለራሴው ሰቀቀኝ፡፡

አየሽ …
የማይታወቅን
ለማወቅ መታከት ህመም ያስታቅፋል፡፡

የማይደርሱበትን
ለመድረስ መታገል ስቀይን ይወልዳል፡፡

የታቀፉት ህመም
የወለዱት ስቃይ
የማይለቁት ሆኖ ከሰይጣን ይከፋል፡፡

የሰው ጫካ መሀል
እንደተላጠ ግንድ
የተለበለበ እርቃንን ያስኬዳል፡፡

የሚገርመው ደግሞ...
ለኔነት ጋንኤል
ላንቺነት ዲያቢሎስ የሚያከብረው ምሱ

ከምንም መሻቱ
አጥብቆ እሚመኘው ይኼ እኮ ነው ሱሱ፡፡

አየሽ …
ሀረግና ማማ
ሆኖ መተቃቀፍ ለሁሌው ይመስላል

እጣ ክፍልሽ ሲሆን
የያዙትን መልቀቅ ያነሱትን መጣል

“እኔነት” የሚባል
የሚያውቁት ዲያቢሎስ
ከማያውቁት መልአክ ላይሻል ይበቅላል፡፡



( ዮሐንስ ሀብተማሪያም (ጆ) )

@write_event
#እሷና ወንዝነት
(ትርጉም ፦ Khalil Gibran)
አለ ፍርሀት በወንዝ እውነት
በባህር ውስጥ መቅረት
እሷም እንደዚህ ናት
ስትወርድ ከላይ ከተራራው ቁልቁል
ከተማ 'ሚያካልል ...
አለ ውቅያኖስ ከመንደሩ ማዶ
የብስ አይሆን ነገር ወደኋላው ሄዶ
አትችልም መሻገር
ከማመን በስተቀር
ማመን ትልቅነት
አቅምን መገመት
ያድናል ከመስመጥ !
ሆኖም ለወንዝነት
በዚያ ፍሳሽ ዥረት
ፍርሀት ደንብ አይደለም
በዛው ሰምጦ መቅረት
ውረድ.. ፍሰስ.. .ክነፍ
ግባ ከሰፊው አምድ አትሰጋ ተንደርደር
ፍርሀት ሲሞት ነው ...
ባህር ነህ ተብሎ ላንተ የሚነገር!

(ሚካኤል.አ)

@write_event
@write_event
@write_event
የሰው ልጅ የልምምድ ውጤት ነው። በልምምድ እንጅ በመወለድ ብቻ ሰው መሆን አይችልም። ከማፍቀር እስከ መቆርቆር ይለማመዳል። ማፍቀርን ያህል ያህል ነገር እንኳ አውቆ አይወለድም። እርሱን ብቻ አይደለም፤ መጥላትን ሳይቀር ይለማመዳል። ከማወቅ እስከ መናቅ፣ ከመወለድ እስከ መታነቅ፤ ከመድቀቅ እስከማድቀቅ፤ ከመጋባት እስከ መፍታት፤ ከስንፈት እስከ ጥረት ... ከመርመጥመጥ እስከ መፈርጠጥ፣ ከቆመጥ እስከ ነፍጥ...ተለማምዶት እንጅ ተሰጥቶት አይደለም። ከክህደት እስከ እምነት ካልተለማመደ አይችልም።

ከራሱ ያገኘው ማንነት የለውም። ሁሉም በሂደት እና በልምምድ የመጣ ነው። መልኩን ቆላ ሲወርድና ደጋ ሲወጣ ይቀያየራል። ልቡን በየግድሙ ይጥላል። ቀልቡን መቋጠሪያ የለውም። በመለማመድ አሁን የደረሰበትን እንጅ ወደፊት የሚሄድበትን ማንም ሊያውቅ አይችልም።

ክቡር ድንጋይ
ይስማዕክ ወርቁ

@write_event
@write_event
@write_event