ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
(ኤፍሬም ስዩም)

:- እውነት ወደ ኋላ

ገንዘብ ካለው ጋራ
ፍቅር አይኖርም ወይ ብለሽ ጠይቀሻል!?
እኔ ያንቺን እንጂ
የሌላን አላልኩም እጅግ ተሳስተሻል
አይኖርም አላልኩም...አይጠፋም ይኖራል
ይኖራል
ይኖራል
ግን?...
ከባለሐብት ጋር
ተፋቅራ 'ምናያት የቷም አይነት እንስት...
'ምን ' ትሁንም ' ምንም '
የሕይወት ታሪኳን ወደኋላ ሄደን ....ጥቂት ብንገመግም
አንድ ቡና ለሁለት ....
አብራ የጠጣችው አንድ አፍቃሪ አታጣም ።

#ኤፍሬም ስዩም
​​━━━━━✦🌺✦━━━━━

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
"ውበትን የምታገኙት የማይታየውን ስታዩ ነው፤ በግልፅ ያልሆነውን ስትረዱ ነው፤ ድምፅ የሌለውን ንግግር ስትስሙ ነው፡፡ ውበት፣ በውስጣችሁ ተጀምሮ ከሥጋዊ ፍላጐቶቻችሁ ባሻገር የሚያበቃ ድንቅ የሀዘንና ደስታ ውህድ ነው፡፡ ልቦና ውስጥ የሚገኝ ብርሃን ነው።"
ካህሊል ጂብራን

Join:

https://t.me/write_event
"ዝግመተ ለውጥ"

" እንጋባ" ብሎ ጠየቃት፥ አሳምነው።
አልተቀበለችውም አስማሩ፡፡ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው፡፡ ተስማሙ።
ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል፡፡ ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፡፡ ካላት ታቀርባለች- ይበላሉ፡፡ አውግተው ይለያያሉ፡፡ የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም፡፡
አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ጸሃይ መጣ፡፡ እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ፡፡ ስለሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ።
አስማሩ አሳምነው እረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት፡፡

ዳግም ሲመጣ ደርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም፡፡
ጃኬቱን አውልቆ ሄደ፡፡
አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው፡፡
ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!"አወለቀው።
አስማሩ አጥባ አኖረችው።ካፖርቱን ጥሎ ሄደ፥ አጥባ አኖረችው፡፡
አንድ ቀን በጠራራ ጸሃይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ፡ አስማሩ " ምነው?" አለችው። " በጠራራ ጸሃይ ብርድ ሆዴ ገባ" አላት፡፡ " ምች ይሆናል" አለቺው፡፡
የምች መድሃኒት ብታሽለት ተሻለው፡፡
ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም፡፡ ጥሎት ሄደ።
አስማሩ አጥባ አኖረችው።
ትንሽ ቆይቶ፥ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ፡፡
"ምነው?" አለችው፡፡ "ላሳድሰው መሄዴ ነው፡፡ አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው።" አላት። አመነችው፡፡

ጨዋታው ደራ፡ ፍራሹን እረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ላይ መጣ፡ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሽዋ ላይ ደርባው ደረሰ። ያኔ "ተነሽ" ከማለት "ጠጋ በይ" ማለት ቀሎት ተገኘ።
ጠጋ አለችለት፡፡


(ከዓለማየሁ ገላጋይ ኩርቢት ገጽ 11)


join

https://t.me/write_event
ለክቡር ዘበኛ ገንዘብ ቤት አንደኛ መምሪያ ሬድዮ ጣብያ አገልግሎት

ጉዳዩ:- ስለ ሰራተኛ መቀጠር

አቶ ጥላሁን ገሰሰ የተባሉ ግለሰብ ከ መጋቢት 25 ቀን 1949 ዓ.ም ጀምሮ በወር 40 ብር ደመወዝ ተቀጥረዋልና ከዚህ ቀን አንስቶ ስማቸው ከ አንደኛ መምሪያ ደመወዝ መክፈያ መዝገብ ላይ ተሞልቶ ሰቀርብልዎ በየወሩ ወጪ እየሆነ እንዲከፈላቸው ይሁን ::

ግንቦት 13 ቀን 1949 ዓ.ም
********
ጥሬ ቆሎ

ለክቡር ዘበኛ ገንዘብ ቤት አንደኛ መምሪያ ሬድዮ ጣብያ አገልግሎት

ጉዳዩ:-የደመውዝ ቅጣትን ይመለከታል

አቶ ጥላሁን ገሰሰ የተባለው የክፍሉ ሰራተኛ ጥሬ ቆሎ አምጥቶ የሙዚቃ ስራ በሚሰራበት ቀን እየጎረመደና እያስጎረመደ ለሠራተኞችም እያደለ ሥራ በማስፈታት ከአንድ ወር ደመወዙ ላይ 3 ብር እንዲቆረጥበት ይሁን።

ሐምሌ 9 ቀን 1949 ዓ.ም

* ታሪክን የኃሌት
*


┄┄┉✽‌»‌ ‌ ❀🌼❀ ‌»‌✽‌┉┄

💜 ጦብያ መፅሔት 💜
​​━━━━━✦🌺✦━━━━━

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
┄┄┉✽‌»‌ ‌ ❀🌼❀ ‌»‌✽‌┉┄
★彡[ መድረሻህን ሳታልም ጉዞ አትጀምር ፤ መኖርህን ሳታውቅ አትሙት።

  ደ ራ ስ  ‌ና‌ሁ‌ሰ‌ና‌ይ‌ ፀ‌ዳ‌ሉ‌ አ‌በ‌ራ‌

እኛ ፣ ሰዎች እና የፈጣሪ ልጅ ፍጡሮች ነን። በዘመን መካከል የተገኘን፤ ዘር ስያራርቀን፣ ሃይማኖት ስለያየን፣ ሀብት ሲመዳድበን፣ ፖለቲካ ስከፋፍለን፣ ህይወትም ስንፈልጋት ስትጠፋ ፣ ሳንፈልጋት ስትበዛ፤ ስንከተላት ስታመልጠን፣ ስንተዋት ስትከተለን እየባከንን የምንኖር።

ሕይወት ፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሰራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች። የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የምኖር ፣ ስያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው። ሰው የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቆየት ፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ስጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የምሞት ፍጡር. . . ።

ም‌ን‌ጭ‌

ከ ╔ሜ╗╔ሎ╗╔ር╗╔ና╗
ስ ው ር  ጥ በ ብ  መፅሐፍ

ገጽ 9⃣ እና 1⃣0⃣ ]彡★

┄┄┉✽‌»‌ ‌ ❀🌼❀ ‌»‌✽‌┉┄

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
┄┄┉✽‌»‌ ‌ ❀🌼❀ ‌»‌✽‌┉┄
«ዝናብ እወዳለሁ ትላለህ፤ ሲዘንብብህ ግን ጃንጥላ ትዘረጋለህ።
ፀሐይ እወዳለሁ ትላለህ፤ ጸሐይ በወጣች ጊዜ ግን ጥላ ፍለጋ ትሮጣለህ።
ንፋስ እወዳለሁ ትላለህ፤ ዳሩ ንፋሱ ወደ ቤትህ እንዳይገባ መስኮትህን ትዘጋለህ።
…ለዚህም ነው "እወድሃለሁ" ስትለኝ የምፈራው።»

"ቦብ ማርሌይ"
┄┄┉✽‌»‌ ‌ ❀🌼❀ ‌»‌✽‌┉┄

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
┄┄┉✽‌»‌ ‌ ❀🌼❀ ‌»‌✽‌┉┄
------
.
እንባ ዘፈን መስሎ
ፊቷን አረጠባት ፣
እሳት ውሃ መስሎ
ገላዋን አጠባት ፣
.
ጠላት ወዳጅ መስሎ
ቀሚሷን ገለጠው
ዝም አለች ለዘመን
መከራ ነው መሰል ፥ ትርጉም የሚሰጠው ።
.
ማጣት ተስፋ መስሎ
መንገድ አስጀመራት ፣
ዛሬ ነገ መስሎ
ወደ ትናንት መራት ፣
.
ድንጋይ ድልድይ መስሎ
እግሯን አነቀፋት ፣
ዝም አለች እንደ ጉድ
ኖርኩ አትልም መሰል ፥ ስቃይ ካላቀፋት ።
.
.
አንጀቷን አንጥፋ
ልቧን  አንጠፍጥፋ
እንደምን ለመደች ፣ ይሁን ብሎ ማለፍ፣
እንደምን ለመደች
ለሳቅ ሲፈልጓት ፣ ለሃዘን መሰለፍ ፣

እንደምን ለመደች ፣ እንደምን ሆነችው ?
እመጣለሁ  ሲላት ፥ ለምን አመነችው ?

ምክያት

ስለወደደችው ።

_
ሶሎሞን ሽፈራው

@write_event
💚💚💚

የቅኔ ምርቃት ከሩሚ
"You are not a drop in the ocean, You are the entire ocean in a drop."
Rumi
"ጠብታ አይደለህም
ባህር ውስጥ የገባህ፥
ባህሩ አንተ ነህ
በጠብታ የሞላህ"
ሩሚ
ትርጉም - ጫንያለው በቀለች ወ/ጊዮርጊስ

@write_event
@write_event
@write_event
የዝምታ ጩኸት
.
.
ተሳዳቢ አንደበት ሰሚ አልባ ጆሮ፤
ፅልመት የወረሰው ትርጉም አልባ ኑሮ፤
ከተስፋ ጉልላት አሽቀንጥሮ ሚጥል፤
ትንፋሽ አሳጥቶ በቁም የሚገድል፤
መቅኒ የሚያፈስ አጥንትን ሰርስሮ፤
ወላፈኑ ሚፋጅ የስሜት አቀበት፤
ሌላው የማይሰማው የዝምታ ጩኸት።

  በኤደን እንደተፃፈ )
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችል ባንድ ወቅት ይህ አስቂኝና ቁም ነገር ገጥሞት ነበር .....

"አንድ ቀን ወደ ቢቢሲ ቢሮ ለቃለ መጠይቅ ለመሄድ ታክሲ ያዝኩኝ፤ቢሮዉ እንደደረስኩ ባለታክሲውን ቃለመጠይቁን ጨርሸ እስክመለስ ለ40 ደቂቃ ያህል እንዲጠብቀኝ ጠየቅኩት።ባለ ታክሲዉም ይቅርታን በማስቀደም "አልችልም ምክኒያቱም እቤቴ ሂጄ ከደቂቃዎች በኋላ ዊንስተን ቸርችል የሚያደርገዉን ቃለመጠይቅ መስማት እፈልጋለሁ።"አለኝ
የእኔን ንግግር ለመስማት ይህን ያህል በመጓጓቱ በጣም ተደነቅሁ፤ ኩራት ቢጤም ተሰማኝ።ማንነቴን ሳልገልፅለት ለታክሲ አገልግሎቱ መክፈል ከሚጠበቅብኝ በላይ መልሱ ስላስደሰተኝ 10 ፓዉንድ ሰጠሁት።ባለ ታክሲዉም የሰጠሁት ብር በደስታ አየቆጠረ"ጌታዬ እስከ ምትፈልገዉ ስዓት ድረስ እጠብቅሃለሁ ሲፈልግ ዊንስተን ቸርችል ገደል መግባት ይችላል!"ብሎኝ አረፈ

ሀሳብ ለብር ሲባል ይቀየራል፣ሀገርን ለብር ሲሉ ይሸጣሉ፣ክብርን ለብር ሲሉ ይሸጣሉ፣ቤተሰብ ለብር ሲባል ይበተናል፣ጓደኞች ለብር ሲሉ ይለያያሉ፣ሰዎች ለብር ሲሉ ክቡር የሆነውን የሰዉ ልጅ ይገድላሉ፣ሰዎች ለብር ሲሉ ባሪያ ይሆናሉ።

ብር....................
Jemal Ahmed Aragaw ገጽ የተወሰደ

https://t.me/write_event
ገንዘብን ተጠቀሙበት በራሱ መልካም ነው። ነገር ግን ፍቅርን ከገንዘብ ለማግኘት አትሞክሩ። ምክንያቱም ፍቅር የውስጣችሁ ነው። የውስጠኛው ህልውና ነው እግዚአብሔርንም ከገንዘብ ዘንድ አትፈልጉት። እርሱ ከአለማት ሁሉ በላይ የላቀና ያለፈ ነው። እያንዳንዱ ነገር በእናንተ የህልም መጠን ሳይሆን በገዛ ራሱ አቅም ተጠቀሙበት። በዚህም ጊዜ ጤናማ ሰው ናችሁ። ጤናማ መሆን ደግሞ ቅዱስ መሆን ነው።
*
ኦሾ/Osho

https://t.me/write_event
| በአንድ ወቅት አንድ ጋቭሮብ ይቸገርና ብር ለመበደር ወደ ሌላኛው ጋቭሮብ ጓደኛው ቤት በምሽት...
Book for ALL | Facebook (Facebook)

በአንድ ወቅት አንድ ጋቭሮብ ይቸገርና ብር ለመበደር ወደ ሌላኛው ጋቭሮብ ጓደኛው ቤት በምሽት ያመራል። እሳት ዳር ቁጭ ብለው እያወጉም የገጠመውን ችግር ለጓደኛው ያወያየውና ለስራ መጀመሪያ የሚሆነውን የተወሰነ ብር እንዲያበድረው ይጠይቀዋል። ጓደኛውም በሀዘኔታ የተባለውን ብር ቆጥሮ ይሰጠውና የጓደኝነት የእሳት ዳር ወጋቸውን ቀጠሉ። በመሐል ግን ፡ ብር የተበደረው ጋቭሮብ ከአንደኛው ኪሱ ውስጥ ሲጃራ ያወጣል ፣ ከሌላኛው ኪሱ ውስጥም ክብሪት ያወጣና ሲጃራውን ለኩሶ ማጨስ ይጀምራል። በዚህን ጊዜም ፡ አበዳሪው ጋቭሮብ "እስኪ ቅድም የጠሰሁክን ብር አንዴ ስጠኝ። በትክክል የቆጠርኩት አልመሰልኝምና ደግሜ ልቁጠረው!" በማለት ጓደኛውን ጠየቀው። ተበዳሪው ጋቭሮብም ምንም ሳያመነታ ብሩን አውጥቶ ድጋሚ ይቆጥረው ዘንድ ለአበዳሪው ጓደኛው ሰጠው። አበዳሪው ጋቭሮብም ብሩን በእጁ ካስገባ በኋላ ፡ ተበዳሪ ጓደኛውን "ጓደኛዬ ሆይ! ፊት ለፊትህ ይህን የመሠለ ቦግ ብሎ የነደደ እሳት እያለልህ ፡ ሲጃራህን ለመለኮስ አንዲት ክብሪትን በመጫር ያባከንክ ሰው ፡ ነገ ነግደህ ያበደርኩህን ብር ትመልሳለህ ብዬ ስለማላስብ ማበደሬን ትቼዋለሁኝ!" አለውና እሳቱ አጠገብ ቁጭ ያለውን ተበዳሪ ጓደኛውን ጥሎት ወደ ቤቱ ገባ!🙄....

ትንሽ ቀልድ መሳይ ታሪክ ናት። በውስጧ ግን ትልቅ አስተምህሮን አዝላለች። ሰዎች ከአፋችን በሚወጡ ትናንሽ ቃላቶች ጭምር ማንነታችንን ይዳኛሉ። በምንተገብራት ትንሽ ተግባርም ብትሆን ሰለ ማንነታችን ይገምታሉ። ልክ በትልቅ ድስት የተሰራን ወጥ ፡ ጠብታውን ብቻ በመቅመስ "ወጡ ጨው አለው ወይም አንሶታል ፣ ወጡ ይጣፍጣል ወይም አይጣፍጥም... ወዘተ" እያልን የትልቁን ትድስ ወጥን እንደምንዳኘው ሁሉ ማለት ነው። ሰዎችም ከውስጣችን በወጣች ትንሽ ቃልን በመስማትና ፡ ከልባችን የተገበርነው ትንሽ ተግባርን በመመልከት ማንነታችንን ይዳኛሉ! በእለት ተእለት የምንተገብራቸው ትናንሽ ተግባሮችና የምናወራቸው ትናንሽ ቃላቶች የማንነታችን መገለጫ ናቸውና እራሳችንን ለመፈተሽ ይጠቅሙናል! ይኸው ነው!🙏
https://t.me/write_event
‿︵︵‿ የታላቁ ፈላስፋ የዲዩጋን ምርጥ ምላሾች!! ‿︵︵‿︵
በቆሻሻ ቦታ ሲዘዋወር የተመለከተው የአቴና ነዋሪ ወዳጁ
ቢገስጸው፡-
‹‹አትሳሳት! ጸሀይ የማትወጣበት ቦታ የለም እስከዛሬ ግን
አልቆሸሸችም ብሎታል››፡፡
በሌላ ግዜም በገበያ ቦታ ላይ ሲበላ የተመለከቱት የአቴና
ነዋሪዎች በዙሬያው ተሰብስበው
‹‹ውሻ ውሻ ! ›› በማለት ሲጮሁበት፡-
‹‹እኔ የማውቀው ሰው ምግብ ሲበላ በዙሪያው ከቦ
የሚመለከትና የሚጮህ ብቻ ነው››በማለት
መልሳል፡፡
ሰዎች ለለማኝ እንጂ ለምን ለፈላስፋ ገንዘብ እንደማይሰጡ
ሲጠይቁት
‹‹ምክንያቱም አንድ ቀን ለማኝ እንጂ ፈላስፋ እንደማይሆኑ
ስለሚያውቁ ነው›› ብላቸዋል፡፡
ምግብ ለመመገብ የተመቸ ሰአት የቱ እንደሆነ ተጠይቆ፡-
‹‹ሀብታም ከሆንክ ስትፈልግ'ድሀ ከሆንክ ደሞ ስትችል ምግብ
ለመመገብ ጥሩ ሰአት ነው››ብላል፡፡
ለዲዩጋን ምጽዋት የሚሰጡት ሰዎች ለምን
እንደማያመሰግናቸው ሲጠይቁት
‹‹እናንተ በመስጠታችሁ ብቻ ሳይሆን እኔም የናንተን ምጽዋት
በመቀበሌ ምስጋን ይገባኛል››ብላቸዋል፡፡
ስለጸሎተኛ ሰው ሲጠይቁት
‹‹ጸሎተኛ ሰው የሚፈልገውን እንጂ መጠየቅ የሚገባው
የማይጠይቅ ሰው ነው››ብላል፡፡
ሲሞት እንዴት እንዲቀብሩት እንደሚፈልግ ሲጠየቅም
‹‹ፊቴን ወደታች ዘቅዝቃችሁ ቅበሩኝ
ምክንያቱም ዝቅ ያለ ነገር ጥቂት ቆይቶ ከፍ ማለቱ እንደማይቀር
ስለማውቅ ነው›› ብላቸዋል፡፡
እንድ የአቴና አስተማሪ ስለህይወት ክፉነት ደጋግሞ
ሲያስተምር ሰምቶ
‹‹ህይወት ክፉ ያደረጋት የሚኖራት እንጂ ህይወት በራሷ ክፉ
አይደለችም››ብሎታል፡፡
~~ በባርነት የገዛው ዜነዲየስ ‹‹እኔን ልትታዘዝ የግድ
ነው››አለው፡፡
‹‹ምንም እንኮን ባሪያህ ብሆንም አዋቂና የነቃ ሰው በባርነትም
ሆኖም ሊታዘዙት ያስፈልጋል››፡፡


https://t.me/write_event
ይቺን ቃል ንገሯት
...(አስቱ)
.
ተፈርዶብኝ እንጂ
መለ'የት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ
እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል
.
ዞር ባለች ቁጥር
አትራቂኝ እያልኹኝ የምለማመጣት
ልቻለው ብዬ እንጂ
ምሳሌ ከመሆን አፍቅሮ ከማጣት
.
"ገደል ግቢ" በሏት
.
. ይህው ደሞ ዛሬ
ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን
.
ከንፈሯን ምን ይሆን ደሞ የቀባችው!
የጇን አይበሉባ በቄንጥ አኮናትራ ሰአቷን አየችው...

.(ገና ነው መሰለኝ)
.
ጊዜን ታዘበችው
ባፏ ሸብረክ አርጋ እየገረመመች
መንቀር አለችና
እግሯን አመሳቅላ መስታወት ፊት ቆመች.
.
(ደሞ ፈገግ አለች
'
ጥርሷ ይርገፍና!

ማርያምን ታምራለች)።
.
"ገደል ግቢ" በሏት...
.
ዘከርኳት በወዳጅ መከርኳት በዘመድ
ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ .
.
ገደል ግቢ በሏት.
.
ልቧን ከጋረደው
ወዳጅ ከከለላት ስውር አይነጥላ
እንዲህ እንዳማረባት
መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰው ጥላ
.
"ልክ እንደገላዋ ይለስልስ መንገዱ ፍፁም አይጎርብጣት
አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት እንደ ጥርሷ ንጣት.".
.
አያልኩኝ መርቄ
እንደ ገጣሚ ቃል ልቤን አልጀነጅን
የታባቷንና
በፀበል ካሎጣች ትረሳለች በጅን።

"ገደል ግቢ" በሏት.
.
ልርገማት እስከጥግ
የታባቷንና ልንገራት የልኳን
እንዲህ ምታረገኝ
ጠባቂዋንና ተማምና አደል መልኳን!
.
የታባቷንና እንዲ የሚያምርባት
የት'ናቷንና እንዲ ሚደምቅባት
.
እስከመቼ ድረስ
ስቀባ እኖራለሁ ጉድፍ ልቧን ስኩል!
(ገደል ግቢ በሏት)
እኔ _ ገደል ስር ነኝ
ደንገት ከወደቀች በቆሻሻው በኩል ::
.
(ምን አደርገዋለሁ)


https://t.me/write_event
ህልም እንደ ፈቺው ነው..!

ሰውዬው በህልሙ የከተማውን ከንቲባ በአለንጋ ሲገርፈው ተመለከተ። ሲነጋ ክስተቱን ለሚስቱ ነገራት። እሷም «አለሚቱ» ለተባለች ጎረቤቷ አጫወተቻት። ወሬው እየተራባ በንፋስ ፍጥነት የደህንነትና ጸጥታ አካላት ጆሮ ደረሰ። ሰውዬውን ምሽት ላይ አፍነው ከቤቱ ወሰዱት። አጓጉል አድርገው ከሰባበሩት በኋላ ማለዳ ላይ ከቤቱ ደጃፍ ፊት ለፊት ጣሉት። እንደ «ጀሶ እንጀራ» ልንኮታኮትለትና «አከመሌ» አደረጉት::

ስቃዩ ብርቱ ስለነበር ቀኑን ሙሉ ሲጮህ ዋለ። የጸጥታ አካላቱ ምሽት ላይ በድጋሜ በሩን አንኳኩ። ሲመለከታቸው «ኧረ ባካችሁ ወላሂ ተጸጽቻለሁ፤ እንዲህ አይነት ህልም ዳግም አልመለከትም» | አላቸው። «አይ አሁን እንኳ የመጣነው በህልምህ ከንቲባውን ስትገርፍ እጆቹን ጠፍሮ የያዘልህ ማን እንደሆነ እንድትነገረን ነው» አሉት። ምን ቢል ጥሩ ነው ... «ሚስቴ እና ጎረቤቴ አለሚቱ ናቸው»

ለማን ምን እንደሚነገር እና እንደማይነገር መለዬት ተስኖህ እንደሚያፈስ ስልቻ ምስጢርህን ሁሉ በየቦታው የምትዘራ ከሆነ በጀመዓ ትሞታለህ። ፌስቡክ ከግቢህ ውስጥ የተወጠረ የልብስ ገመድ ይመስል ሁሉንም የምታሰጣበት ከሆነ አላፊ አግዳሚው ነውርህን እየቆጠረ ቀን ጠብቆ ይሰብርሃል።

https://t.me/write_event
ከባለፀጎች አንደበት !

ጋዜጠኛዋ ቢሊኒየሩን ቃለመጠይቅ እያደረገችለት ነው… የስኬትህ ሚስጥር ምንድነው?
ቢሊየነሩ ባዶ ቼክ ለጋዜጠኛዋ አቀበላትና የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ ፃፊበት አላት!
ጋዜጣኛዋ በእንቢታ ቼኩን እየመለሰች «አይ እኔ እንደሱ አይነት ነገር ፈልጌ አይደለም የስኬት ሚስጥሮን መጠየቅ ፈለጌ እንጂ» አለች።
ቢሊየነሩ ድጋሚ ቼኩን መልሶ ሰጣትና «የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ ፃፊ» አላት።
ጋዜጠኛዋ እንቢ አሻፈረኝ አለች።

ቢሊየነሩ ቼኩን እያሳያት «የስኬቴ ሚስጥር አሁን አንቺ ያጋጠመሽን አይነት እድል አሳልፌ አለመስጠቴ ነው…የስኬቴ ሚስጥር ያገኘሁትን እድል ሁሉ መጠቀሜ መው።
አሁን አንቺ እንድልሽን ተጠቅመሽ ቢሆን ኖሮ የአለማችን ሃብታሟ ጋዜጠኛ ትሆኚ ነበር… እኔ ሁለቴ እድል እንደሰጠሁሽ አለም ሁለት እድል አትሰጥሽም አንዴ ያጋጠመሽን እድል መጠቀም የስኬት ሚስጥር ነው»

https://t.me/write_event
ደራሲው
(አለማየሁ ገላጋይ ከመአዛ ብሩ ጋር በሸገር ካፌ ከተጨዋወቱት)

የደራሲዎችን ምስል በተደራሲያን ዘንድ አብዮታዊ በሚባል መልኩ የቀየረው የበአሉ ግርማ ‘ደራሲው’ ነው። በመጠኑ ደግሞ የቀይ ኮከብ ጥሪ(በተለይ ደግሞ አንዱ ገፀባህሪ አእምላፍ) በአሉ ደግሞ ለዚህ መፅሀፉ እንደ ሞዴል አድርጎ የተጠቀመው ጋሽ ስብሐትን ነው። በአሉ እራሴን ሞዴል አድርጌ ብፅፍ ልክ አይመጣልኝም ብሎ ጋሽ ስብሐትን አስፈቅዶ ደራሲው ተፃፈ።

በመጽሐፉ ዋናው ገፀባህሪ ሲራክ ይባላል። ሲራክ የጋሽ ስብሐት አምሳያ ነው። ጋሽ ስብሐት ደግሞ ቃሚ፣ ጠጪ፣ ራሱን ብዙም የማይጠብቅ ደራሲ ነበር። ማህበራዊ ህይወቱ ደካማ፣ የሴት ጓደኛውን ሕይወትን ተመልከቺ እያለ ወደ ሌላ ወንድ የሚገፋ። የደራሲ ምልከታ እየተበላሸ የመጣው ከዚህ ወዲህ ነው። ደራሲ ሲባል ፀጉሩን የማያበጥር፣ ጫማው የተንሻፈፈ፣ ሰውነቱ ጥሙጋ፣ ሱሰኛ ወዘተ።

የጋሽ ስብሐት ህይወት ከበአሉ ብእር ጋራ ተቆራኝቶ ሃያል ተፅእኖ ፈጥሯል።በተደራሲ አእምሮ ውስጥ የደራሲ ምስል ሆኖ ተቀርፆ የተቀመጠው ጋሽ ስብሐት ነው።

በአሉ ራሱን ሞዴል አድርጎ ቢሆን ነገሮች ሌላ መልክ ይይዙ ነበር። በአሉ በጣም ንፁህ፣ ሽቅርቅር ደራሲ ነበር። በመንገድ እየሄደ ጫማውን ትንሽ አቧራ ከነካው እንኳን ቆም ብሎ በመሀረብ ሳይወለውል መንገዱን አይቀጥልም። በአሉ ሁሌ ዘናጭ፣ አንደበቱ ቆጠብ ያለ፣ ከአንገቱ ከረባት የማይለይ፣ ሽቶው ከሩቅ የሚጣራ፣ ሸሚዝ ግማሽ ቀን ላዩ ላይ ከቆየ የሚቀፈው ፣ ጢሙን ቀን በቀን የሚላጭ ነበር።

ሌሎች ቀደምት ደራስያንን ብንመለከትም ታሪኩ ከደራሲው ገፀባህሪ ሲራክ እጅግ የተለየ ነበር። አብዛኛዎቹ ሚኒስትር የነበሩ፣ የመንግስት ወኪል የነበሩ፣ ራሳቸውንም የሚጠብቁ፣ ክብራቸውንም፣ ልብሳቸውንም ከሱስም የተጠበቁ ነበሩ። ከበደ ሚካኤል በጣም ሽቅርቅር ነበሩ። መኮንን እንዳልካቸው ራሳቸው ሚኒስትር ደረጃ የደረሱ ነበሩ። ልጃቸው እንዳልካቸው መኮንን እንደ ራሳቸው ደራሲ የነበረና በመንግሥት ሥልጣንም ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ የደረሰ ነበር። አፈወርቅ ገብረየሱስ ራሱ እንደ ሚኒስትር ሊቆጠሩ የሚችሉ፣ በሁለት ሃገሮች ጉዳይ ላይ በማማከር እጃቸውን ያስገቡ ሰው ነበሩ። ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደሥላሴ ባህላዊ አለባበሳቸው በራሱ ግዝፈትና በሚመለከታቸው ሰው ላይ ጫና የሚያሳድር፣ ከላይ ካባ ከውስጥ ቀጭን ኩታ የማይለያቸው ነበሩ። ሀዲስ አለማየሁ በባለቤታቸው ክበበ―ፀሐይ ለተሰየመው ወላጅ ለሌላቸው ልጆች ማሳደጊያ እንዲሆን 3000 ካሬ ሜትር ቤታቸውን የሰጡ ነበሩ።

ስብሐት ድንቅ ስብእና ነበረው። አይካድም! ነገር ግን የግል ህይወቱ የሚያስቀና አልነበረም። በአሉ ከነዚህ ሁሉ ደራሲዎች ስብሐትን ሞዴል አድርጎ በመምረጡ የደራሲነት ምስል ተሰባብሮ፣ እግራችን ስር ድቅቅ ብሎ ተዘረረ።

አንድ ግዜ ‘60 ሻማዎች’ የተሰኙ የወጣቶች የስነጽሑፍ ማህበር አባላት አለማየሁ ገላጋይን ለአንድ ጉዳይ ይቀጥሩታል። ወጣቶቹ ከዚህ ቀደም አለማየሁን በአካል አያውቁትም ነበር። አለማየሁ ወጣቶቹ ከቀጠሩት ቦታ ደርሶ አጠገባቸው ሆኖ ወጣቶቹ እርስ በእርስ ከተላላፊ መንገደኞች መሐል ጥሙግ ያለ፣ መሄድ ያቃተው፣ ፀጉሩ የተንጨባረረ፣ ሲጋራ የያዘ፣ በሱስ የናወዘ ሲያዩ

"ያ ነው! ያ ነው!" ይባባላሉ።

አለማየሁ አጠገባቸው ተቀምጦ የሚባባሉትን ትንሽ ከሰማ በኋላ፦

"አለማየሁ ገላጋይ ማለት እኔ ነኝ!" አላቸው። ወጣቶቹ አመዳቸው ቡን ብሎ፦

"ውይ! አትመስልም!"

😂

https://t.me/write_event
​​~~~~እኔ ወድሻለሁ~~~~

እኔ ወድሻለሁ፤ ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት፤ እንደ ዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ ፤ደርቦ እንደመምታት
እኔ ወድሻለሁ፤
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት፤ ግማሽ እንደመውረስ
እኔ ወድሻለሁ፤ እንደ መቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ፤ ያንች ልዝብ ሰይጣን።.

✰ገጣሚ ፦በእውቀቱ ስዩም

https://t.me/write_event