ቃላዊ
342 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
"""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 3
.
.
"" አማንዬ አታስብ ሰሞኑን አስተውምውቅሀለው ከንፈሮቹን እየነከሰ ቲጂ ማለት ድምፆ የሚያምር .....
ለማንኛውም አሁን እንተኛ ..

"በተደጋጋሚ መደዋውል ጀምሩ። በእሷ በኩል ሳይደውል የዋለ ቁጥር እቤት ውስጥ መነጫነጭ እና በትንሽ ነገር የመበሳጨት ነገር ...ይህን ጉዳን ለጓደኞቾ ስነግራቸው ስቀው ግን ለምን አንድ ነገር አናደርግም አሉ።
"ማክዳ ሰው እንዴት ስልክ ተሳስቶ ደውሎ ከዛ ፍቅር ምነ ምን ያዘኝ ይላይ የንቀጥ እና የጥላቻ አክት እያሳየች አብሶ የዘንድሮ ውንዶች ጋር እውነት ፍቅር አለ"

""እንደዛ አታስቢ ደሞ ሁሉም አንድ አይደሉም በዛ ላይ ከሴትም አለ። ለገንዘብ ለውለታው...ብቻ ብዙ ፍቅሮች አሉ። አንቺ ዛሬአንድ ሰው ስለጎዳሽ ያው ናቸው አትበይ ...ቲጂ ማክዳን እያየች

""በይ እሱ ድሮ ቀረ እኔ ግን fb ...በስልክ ባጋጣሚ ምነምን አይመቸኝም አብሶ ኢንተርኔት ነክ። ፍቅር ማስጀመር እንጂ ማስጨረስ....


""ሀና የነሱክ ጭቅጭቅ እና ሙግታቸውን አንድም አልሰማችም በመሀል የስልኳ ጥሪ አባነናት ስታየው እሱ ነው። እሱ ነው ስትላቸው አንሺው ለምን አንገናኝም አትይውም አሏት

"No እሱ እስኪላት ትጠብቅ ...
""ፈገግታ በተሜው ድምፅ ሀይ አሌክስ እንዴት ነክ ...ጓደኞቾ ላውድ እንዳታደርገው በመልክት ነግራዋት አድርጋ ውሬአቸውን ቀጠሉ...

""በመሀል ሀኒ የት ነሽ?ለምን አንገናኝም?

" ደንግጣ መቼ ዛሬ አሁን በመደናነር ስሜት ውስጥ ሆና ...
""ምነው አይመችሽም ጓደኞችሽ አሉ እንዴ ..
"" አዎ ሌላ ቀን እንገናኛለን
ጓደኞቾ አፋቸው ላይ የመጣውን ሳቅ በእጃቸው ይዘው .
" እሺ ነገ ምሳ ልጋብዝሽ አስቢበት እቢ ማለት አይቻልም ....
"ካመነታች በኃላ የጓደኞቾን አይኖች አይታ እሺ እንደትለው ምልክት አሳዩያት
"እሺ...
"በቃ እንደዋውላለን ብሎ ስልኩን እንደዘጋው
"ለደቂቃ የያዙትን ሳቅ ሁሉም በነፃነት መሳቅ ጀመሩ ..
"እንደዘጋችው ኡፍፍፍ ብላ ተነፈሰች
"ነገ እንዴት ሆና መሄድ እንዳለባት መነጋገር ጀመሩ።..
ለምን እቤት አንሄድም ስትላቸው እኔ ና ማክዳ የምንሄድበት ቦታ አለ። እያውቃችሁት ባይሆን ቲጂ ጋር ሂድ ..ሜሮን ነበረች።

ትግስትና ሀና ወደ ሀና ቤት አመሩ ልክ ሲደርሱ የውጪውን በር ሲያንኳኩ እንደ ድንገት ውንድሞ ሲከፍት "እንዴ ዘበኛ ሆነክ ቀረክ" ስትለው ክው ብሎ ቀረ በርግጥ የደነገጠው በአለችው ነገር ሳይሆን ቲጂን ስላያት ነው።

""እብድ ከመምጣትሽ አትልከፊኝ ሰላም ነሽ ትግስት"
ሲል እየገባች ያለችው ልጅ ዞር ብላ ምን አልክ ትግስት ነው ያልከው። ይሄውልሽ ቲጂዬ ትላንት ቲጂ እያለ እያቄመጠ ስጠራሽ አምሽቶ አንቺን ሲያይ ....የመታውቂያ ስምሽን ይጠራል ።
በሁኔታዋ ፈንጠር ብለው የቆሙት አባቷ መሳቅ ጀመሩ። ቲጂ ያለችበትን እስከምትረሳ ትስቃለች ምን ውስጡ ቢናደድም ግን ደስ ብሎታል ።..
እየተሳሳቁ ውደ ውስጥ ገብ .።

""ሀኒ ክፍል ሆነው የልብስ ቁምሳጥኑን ከፍተው ልብስ እየሞከረች ቲጂ አልጋው ላይ እግሮን አውጥታ አስተያየት እየሰጠች ለክታ የጣለችውን ልብስ እያጣጠፈች ታስቀምጠለች ።..

""ቀይ አጠር ያለች ከጀርባው ክፍት የሆነ ልብስ ስታየው wowww ምርጥ ነው ፀጉርሽን ተሰርተሽ ስለቂው ይሸፈናል ይሄ ክፍተቱ ብላ በምርጫዋ ተስማምተው ሳሎን ሄደው ፊልም ማየት ጀመሩ። ድንገት ሀኒን አባቷ ጠርተዋት ሄደች። እስራዬል ና ቲጂ ቀሩ...ሰረቅ እያለ እያያት ተጫውቺ ...እንጂ..
"በእሽታ እራሶን እየነቀነቀች ....

አንድ ሁለት እያሉ ጫውታቸውን ደራ እየፈራም ቢሆን ነገ ለምን ሻይ ብና አንልም አላት።
እንደማሰብ ብላ እሺ ብላው ስልኮን ሰጠችው ።።...

ሀና እየለፈለፈች መጣች ...

ምሽት ላይ ሀና ስልክ ሲደወልላት ወደ ክፍሏ ገብታ ማናገር ጀመረች። ኪሩቤል (አሌክስ) አናግራ እንደጨረሰች አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ተዘርግታ ታስብ ጀመር። የመኝታ ቤቶ በር ተንኳኳ....ይግብ ወንድሞ ነበር

"ዛሬ እንግዴ ስፈነጥዝ እደር ..እንደመሳቅ ብላ ...
""ማለት እንደመኮሳተር እያለ ውደ አልጋው እየተቀመጠ
"ልትዋሸኝ ባልሆነ ሁሉንም ሳዳምጥ ነበር እንድታውሩ ነው አውቄ እንዲያስጠራኝ ያረኩት..ስትለው

አንቺ ተንከሲስ ብሎ በትራስ እየመታት አቅፎ ሀኒዬ በጣም ነው የምውዳት ከምሬ ነው። የዛሬ እንዳይመስልሽ ከአመት በፊት ነው ፍቅር የያዘኝ....

""የምትፈልግክ ከሆነ ጥሩ ልጅ ናት ።ፍቅረኛ የላትም ....

መድረስ አይቀር የተቀጠረችበት ሰአት ደረሰ ...የለበሰቸውን ከለር ነገረችው ልትውጣ ስትል
ውንድሞ" ውዴት ነው"
"ኢሲዬ ስመጣ እነግርሀለው ....
""እሺ ግን እንዲ ሆነሽ....እራስሽን ጠብቂ ....
እሱም ቲጂን ስለቀጠረ ለምን አልሸኝሽም መኪና ይዛለው በሀሳብ ተስማምታ ከተቀጠረሽበት ሆቴን አድርሶት ሰዓት ስለረፈደበት በፍጥነት እየነዳ ሄደ ።.

""ልክ እንዳያት ሀኒ ብሎጠራት ልክ ስታየው...

ይቀጥላል...



share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 4
.
. "ልክ እንዳያት ሀኒ ብሎ ጠራት
የተበተነውን ፀጉራን ገለጥ አድርጋ ቀና ስትል ደነገጠች ."
"ከመቀመጫው ተነስቶ ልክ በፊት በአካል እንደሚተዋውቁ አቅፎ ሰላም አላት ግን እሷ ደንግጣ ብዙም ሰላም አላለችውም ከትንሽ ደቂቃ በኃላ
""ምን ሆነሻል እንደዚ አልጠበቅሽኝም ወይስ ....
""በመንተባተብ አይ ለዛ አይደለም ከሰው ጋር ተመሳስለክብኝ ነው"
Sorry ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ ሶፍት አውጥታ ግንባሯን እንደመጠራረግ አለች።
"ዝምታውን ለማፍረስ ብሎ "ከጠበኩሽ በላይ ቆንጆ። ነሽ ..
"አመሰግናለሁ አንተም ብላ እንደማቀርቀር አለች
"ምሳ አዘው እየበሉ ግን እሷ ውስጦ ብዙ ጥያቄዎች አደረባት ።.
"በልተው እንደጨረሱ እሱ
""በብርጭቆ ውስጥ ያለውን ውይን እየተጎነጨ ሀኒ ድፍረት አይሁንብኝ እና ቅድም ከማን ጋር ነው የተመሳሰልኩብሽ
""አይ የቆየ ታሪክ ነው እርሳው ...

"እንዴ ለምን ንገሪኝ ታሪክ መስማስ እወዳለው ...ስሙን ንገሪኝ ፍቅረኛሽ ነበር።

"አይ አይደለም የሰፈሬ ልጅ ነው በጣም ነበር የምንዋደደው ልጆች ነበርን ኪሩቤል ይባላል የሚገርምክ የቤት ስሙን በጣም ነው የምውድለት ((ሳንቾ))

"እሱ ክው ብሎ ቀረ እንዳይታውቅበት እና የት ሄደ sorry ግን ስሜትሽን እረበሽኩሽ ...
"በረጅሙ እንደመተንፈስ ብላ ካናዳ ሄዶል ይብቃን አናውራው አለችው ..

"ያኔ እሱ እንባው እንደመምጣት አለ ግን ሽንትቤት ብሎ ሄደ እራሱን በመስታውት እያየ ሀኒ በጥሩነትሽ እንዳትመጭብኝ
እያለ ውሀ እንደመርጨት ብሎ አደራርቆ። ወደ ቦታው ተመለሰ
እሺ ሀኒ ተጫውቺ ብሎ ግን ዳንስ አታለማምጅኝም?
" ችግር የለም ለምን ከኛጋር አትቀላቀልም...እንደመሳቅ እያለች .

ማታ ከተለያዬ በኃላ
ሀኒ ተሰምቶት የማያውቅ ስሜት ይሰማት ነበር ።በርግጥ ገና በስልክ እንዳናገራት ነበር ስለሱ ማሰብ የጀመረችው ዛሬ በአካል ስታገኛው ደሞ የበለጠ
እቤት ገብታ ሰላም ብላቸው በሆነው ባልሆነው ትስቅ ጀመር። እናቶ ሀኒዬ ምን ተገኝቶ እንዲ ፈንድሻ ያደረገሽ ዛሬ ..ምን ያው ደስታ ይከለከላይ እንዴ ብላ ውደ ሞባይሎ አቀረቀርች ..

""አይከለከልም ግን ያው አለ አይደል ...የደስታ አይነት አለው ብለን ነው አባቷ ከኮምፒውተር ላይ ገታ ብለው የሀኒን ደስታ ምክንያት ለማውቅ ።..
""እእእ ምን አልተገኛም ሰላም እደሩ ብላ ውደ ክላሷ በመግባት በደረቶ አሻንጉሊቶን አቅፋ ስሜቶን በዝምታ እንዴ በግርምት በሳቅ እያዋዛች ማዳመጥ .

"በኪሩቤል ከራሱ ጋር እንደተጣላ በሀሳብ ተውጦል ድንገት ጓደኛው ዛሬ ደሞ ብሶብካል የት እንደዋልክ ከማን ጋር እንደ ነበርክ ንገረኝ ብሎ ውጥር አድርጎታል ..

"አማን ሁሉም በጊዜው ትሰማዋለክ አሁን አትጠይቀኝ ብሎ ሌላ ውሬ ቀየረ ግን ኪሩቤል ሀናን እንዴት ውደ ፍቅር ውስጥ እንደሚከታት ነው የሚያስበው ።

"እጆቹን ወደ ስልኩ ሚሴጅ ላከ እና በረጅሙ ተንፍሶ ስልኩን ደረቱ ላይ አድርጎ ውደ ጣሪያው ተመለከት ግን ሳያስበው አይኖቹ በእንባ ተሞልተዋል

"ሀና እዛ እንቅልፍ ይዞት ስለነበር የስልኳ የቨይብሬት ጥሪ አስበረገጋት እንደማማተብ ብላ ...አይኖቾን እያሸች ስታየው የሱ ነው ያሁላ ድብርት በብርሀነ ፍጥነት ለቋት ማንበብ ጀመረች

""ሰላም ገባው አይባልም እንዴ ለማንኛውም አሪፍ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው ደና እደሪልኝ "" አብባ ስጨርስ መልስ ከመላክ ይልቅ ስልኩን ስማ አይኖቾን ጨፍና ስልኩን ደረቶ ላይ አድርጋ ስሜቶን ማዳመጥ ጀመረች ። ሳታውቀው በዛው እንቅልፍ ውስዶት ነበር ስትነሳ
ስልኳን ስትልየው
""good morning""""

ደነገጠች ባፀፋው መለሰችለት እና መልስ ስጠብቅ
ድንገት የመኝታ ቤቶን ሀኒ እያለ..
.

ይቀጥላል.....

|Share|Share|Share|


share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

t.me/Write_Event
"ላለህ ነገር ሁሉ የማመስገን ልማዱ ካለህ የበለጠ ታገኛለህ። ነገር ግን በሌለህ ነገር ላይ ብቻ የምታተኩር ከሆነ በምንም አይነት መልኩ በቂ ነገር ሊኖርህ አይችልም። "
ኦኘራ ዊንፍሬይ

"ጨለምተኛ ሰው በየትኛውም ጥሩ አጋጣሚ ውስጥ አስቸጋሪ ነገሮችን ሲመለከት ፤ የብሩህ ተስፋ ባለቤት የሆነ ሰው ግን ችግሮች ውስጥ መልካም አጋጣሚዎችን የሚመለከት ነው።"
ዊንስተን ቸርችል

Join:
t.me/Write_Event
የደስታ ዋጋው ስንት ነው?

💧ኢኮኖሚክስ ላይ 'Water & Diamond paradox' የሚባል እሳቤ አለ... ለኑረት ወሳኙ ነገር ውሃ ነው - ግን 'እርካሽ' ነው... አልማዝ ለህላዌ የሚያበረክተው ድንቡሎ የለም - ግን ውድ ነው... ለዚህም ይመስላል አንስታይን "The important things are always simple" ማለቱ...

💎ዘግይቶም ቢሆን የሚገባህ እውነት ነገሮችን በውድና ርካሽ የሚፈርጀው አስተሳሰብ እንጂ የነገሩ ወሳኝነት አለመሆኑ ነው... እርግጥ ማሕበረሰባዊ ስምምነቶች ለተፈጥሮ ህግ ከመገዛት ይልቅ መንጋነትን ያበረታሉ... ለምሳሌ:
-
ዋናው ቁምነገር አብሮነትና ፍቅሩ ቢሆንም ውዱ ግን ሰርጋችን ነው...
ትልቁ እውቀት ራስን ማወቅ ቢሆንም ውዱ ግን ከአስኳላ የምንገዛው ነው...
ጠቃሚው ውበት ጸጥታ ቢሆንም የምንከፍለው ግን ለሚበጠብጠን ጩኸት ነው...
ጤናችን ያለው ንጹህ ውሃ ውስጥ ቢሆንም ብዙ የምንከፍለው ግን ለመታመሚያችን አልኮል ነው... ወዘተ

🌊እልፍ ርቀት ሮጠህ ስታበቃ ቆም ብለህ 'ለዚህ ጉዳይ ይህን ያህል ዋጋ መክፈል ነበረብኝን?' ብለህ ብትጠይቅም መሮጥህን ግን አታቆምም...
~
💦በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ጡዘትህን እንጂ ቆምታህን አያበረቱም... ይልቁን በውድድር ውስጥ እንድትቆይ ይገፉሃል... ከጓደኛህ ትወዳደራለህ... ከጎረቤትህ ትወዳደራለህ... ከባልደረባህ ትወዳደራለህ... ከንግድ አቻዎችህ ትወዳደራለህ... እናም ማቆሚያ በሌለው ዙረት [Vicious circle] ውስጥ ትቧችራለህ...

💎ዛሬ የሆነ ነገር ለማግኘት ትሮጣለህ... ደርሰህ ስትይዘው ይቀልብሃል... ነገ ሌላ ለመጨበጥ ትዘረጋለህ... ደርሰህ ስታየው 'ለዚህ ነው በሬዬን ያረድኩት?' ያስብልሃል... እንደገና ሌላ ሩጫ... እንደገና ሌላ ፍለጋ... እንደገና ሌላ መባከን...

🌊እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም... በበርህ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም... ደስታን ከውጭ ከመፈለግ በላይ ጉድለት የሚመስለኝ ይህ ነው... እየፈለጉ መቀጠልን ማቆም ባይቻል በደረሱበት አለመብቃቃት ትልቅ ጉዳት ነው... የደረስክበት ደግሞ 'አሁን' ነው... ይህ ቅጽበት... አሁንና እዚህ...

🌊አንድ ጊዜ የምረቃ መጽሔት ላይ ከፎቶ ስር ለሚሰፍር ጽሑፍ 'የእኔ ቀን ነገ ናት' የሚል ቃል ሰጥቼ ነበር... አሁን ላይ ቆም ብዬ ሳስብ 'ምን ሆኜ ነው ግን' እላለሁ... እንዴት ሰው እርግጠኛ ከሚሆንበት ዛሬ ይልቅ በማያውቀው ነገ ላይ የደስታውን ውበት ያንጠለጥላል? ደስታ ኑረትን ግድ ይላል እኮ... 'ነገ እንትን ሳገኝ እደሰታለሁ' የምትል ከሆነ ለመደሰት ቀጠሮ እየሰጠህ ነው፣ ከዚያም በላይ ደስታህን በነገሩ መኖር አለመኖር ላይ እየመሰረትክ...

🌊ደግሞስ 'ለደስታ ምን ያህል ነው የሚበቃን?' ... ስንት ብር? ስንት መኪና? ምን ያህል ቁስ?... በዙሪያዬ ብዙ 'ያላቸው' - ተነጫናጮች እና 'የሌላቸው' ደስተኞች ሳይ... ብዙ ሃብታም የበሽታ ቋቶችና ድሃ ፍልቅልቅ ፊቶችን ሳስተውል ይሄ ጥያቄ ትዝ ይለኛል... መልሱ እኮ በአጭሩ "ደስታ ውስጣዊ እንጂ ቁሳዊ [ሰበባዊ] አይደለም" የሚለው ነው... ሆኖም በተግባባንበት መንገድ ሄጄ 'ለመደሰት ስንት ያስፈልገናል?' እላለሁ... ምንም አይበቃንም... ምናልባት ምድርን የሚያህል ሃብት ቢኖረን እንኳ ሌላ ፕላኔት ማሰሳችን አይቀርም... ደስታ ግን ከብዛትም ሆነ ከነገር ጋር አትቆራኝም...

🌊ሰውየው አንድ ቦታ ላይ እንዲህ ሲል ይጠይቃል..."A table, a chair, a bowl of fruit & a violin; what else does a man need to be happy?" ይህ አባባል ለዚህ ዘመን ኑረት ከስድብ በላይ ይመስላል... ይህን ያለው ግን አንስታይን ነው... በዘመናዊው የሳይንስ ዓለም ተስተካካይ የሌለው ተጽዕኖ ፈጣሪ... ሆኖም ከስኬት በላይ እሴት ስለሚመስጠው..."Try not to become a man of success, but rather try to become a man of value" ይላል...

💦ዲዮጋን ቀፎ መሳይ ቤት፣ ውሻና ውሃ መጠጫ ቅል ብቻ የነበረው ቢሆንም ወንዝ ሲሻገር አንድ ሰው አጎንብሶ በእጆቹ መዳፍ ውሃ ሲጠጣ ባየ ጊዜ 'ለካስ ቅልም ትርፍ ኖሯል?' ብሎ አሽቀንጥሮ ጥሏል...

🌊አንድ ቱሪስት በአንድ ዝነኛ የሱፊ መምህር ቤት ተገኝቶ ባየው ቁስ ተገርሞ ይጠይቃል... የሱፊው ንብረት አንድ ምንጣፍና ላምባዲና ብቻ ነው...
'የቤትህ ቁሳቁሶች የታሉ?'
'ያንተን ቁሳቁሶች አሳየኝ እስኪ ቀድመህ?'
'እኔማ እዚህ ጎብኚ ነኝ' መለሰ ቱሪስቱ
'እኔም እኮ ጎብኚ ነኝ'

💎ተረኮቹን ያመጣሁት በዚህ ዘመን እንዲህ መኖር አለብን ለማለት አይደለም መቼም... እንግዶች ሆነን በመጣንባት ምድር ለመኖር ቅድሚያ ያለመስጠታችን ለመሞገት እንጂ... የቁስ ጥማታችንን ለማሄስም ጭምር...

አዎን... ደስተኛ መሆን ካሻህ Be Contented እልሃለሁ!!

🌊'የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ የለውም' በሚል ከንቱ ስብከት እየተነዱ 'ያለኝ ይበቃኛል' ማለት እንደሚከብድ ግልጽ ነው... ያም ሆኖ በፍላጎታችን ላይ የምንሰለጥን እንጂ ፍላጎት የሚሰለጥንብን እንዳልሆንን ማወቅም ጠቃሚ ይመስለኛል... አግበስባሽነት በማግኘት ላይ እንድትመሰጥ እንጂ ባለህ ደስታ እንድትፈጥር ዕድል አይሰጥምና...

መልካም አሁን!!❤️

ደምስ ሰይፉ


Join:

t.me/Write_Event
📜ውብ ሐሳቦች🍂


ሰውዬው ራሱን ሊያጠፋ ነው፡፡ ደሃ ነው፣ አልተማረም፣ ሥራ የለውም - ሁሌ እየለመኑ መኖር ምርር አለው፡፡ ዘላለሜን እየለመንኩ ከምኖር ራሴን ባጠፋ ይሻላል አለ፡፡ እናም … ከትልቅ ኮረብታ ላይ ራሱን ወንዝ ውስጥ ወርውሮ፣ ሰጥሞ ለመሞት ወስኖ ኮረብታውን እየወጣ ሳለ … በአጋጣሚ … ኮረብታው ጫፍ፣ አንድ የሱፊ ተማላይ አገኘ፡፡

“እ … አጅሬ መጣህ ?” አለው ተማላዩ፣ “ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት ካልሆነ ወደዚህ ቦታ ድርሽ አይሉም፡፡ ይሄን ቦታ ለተመስጦዬ (Meditation) የመረጥኩትም ለዚሁ ነው፡፡ ማንም ስለማይመጣበት ፀጥ ያለ ቦታ ነው፡፡ እንደ አንተ አይነት ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ከስንት አንዴ ነው የሚመጡት - እንኳን ደህና መጣህ…”

“እንዴ…” አለ ሰውዬው፣ “ቃላት ሳይወጣኝ እንዴት ነው ራሴን ለማጥፋት መምጣቴን ያወቅከው ? በእርግጥ … እንዳልከውም ራሴን ለማጥፋት ነው የመጣሁት”

“መብትህ ነው፡፡ ራስህን ማጥፋት ትችላለህ፡፡ ግን አንድ መግዛት የምፈልገው ነገር አለኝ ካንተ - ሁለቱን ዓይኖችህን በስንት ብር ትሸጥልኛለህ ? ንጉሡ ሁለት የተዋቡ ዓይኖች ይፈልጋል፡፡ያንተ ዓይኖች ደግሞ እንደማየው እጅግ የሚያምሩ፣ የተዋቡ ናቸው፡፡ ንጉሡ፣ እኔ ሁሌ እዚህ የራስ ማጥፊያው ሰገነት - [አዎ የቦታው ስም ያ ነው ‘የራስ ማጥፊያ ሰገነት’ ነው የሚባለው] ላይ እንደምቀመጥ ስለሚያውቅ፣ ‘አደራ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን የሚያማምሩ የአካል ክፍሎች በጠየቁህ ገንዘብ ግዛልኝ’ ብሎኛል፡፡

ደግሞም ራስህን የምታጠፋ ከሆነ እነዚህ ውብ ዓይኖች ምን ያደርጉልሃል ! ለንጉሡ መሸጥ አይሻልም ?! ስለዚህ ዓይኖችህን የምትሸጥበትን ዋጋ ወዲህ በል፡፡ ሥንት ትላለህ ! የፈለግከውን ያህል ብር ጥራ፡፡ ችግር የለውም… ”

ሰውዬው በሐሳብ ተዋጠ - ስንት ብር ይበል ?! ማሰብ ተሳነው፡፡ 500 000 ብር ? አይይ ያንሳል፡፡ 1 ሚሊየንስ ? 5 ሚሊየን ብልስ ? .....የትኛውም ገንዘብ ለዓይኖቹ ዋጋ አልመጥልህን አለው፡፡ ቢሆንም በስተመጨረሻ እንደምንም ጨክኖ፣ “10 ሚሊየን ብር” አለ፡፡

“በጣም ጥሩ … በል ና እንሂድ” አለ ተማላዩ፤ “በመጀመሪያ ዓይኖችህን እናወጣቸውና እየመራውህ ይዤህ እዚህ እመጣለሁ - ከዛ ከዚሁ ቦታ ዘልለህ ራስህን ማጥፋት ነው”

“ግን … ሌሎች ደምበኞችም አሉኝ” አለ ተማላዩ ቀጠለና፤ “ለጭንቅላትህ ስንት ብር ትፈልጋለህ - ማለቴ ዓይኖቹ የወጡለት ጭንቅላት ?”

“በጣም የምትገርም ሰው ነህ” አለ ሰውዬው፣ “ዓይን የሌለው የእኔን ጭንቅላት ማን የሚፈልግ አለ ?”

“ስለሱ አታስብ … አንድ ደምበኛ አለኝ፡፡ ምትሐተኛ (magician) ነው፡፡ የራስ ቅል አጥቶ ተቸግሯል፡፡ ‘የራስ ቅል አምጣልኝ ያልከውን ዋጋ እከፍላለሁ…’ እያለ ውጥር አድርጎ ይዞኛል፡፡ እድለኛ ነው ይሄው አንተን ጣለለታ፡፡ ለእሱ የራስ ቅሉ ዓይን ባይኖረውም ችግር የለውም፡፡ ለነገሩ እሱ ሙልጭ ያለ የራስ ቅል ነው የሚፈልገው፡፡ ስለዚህ አታስብ”

“የፈጣሪ ያለህ” አለ ሰውዬው ጭንቅላቱን ይዞ፣ “እና ጭንቅላቴን ሸጬ እንዴት ነው ተመልሼ መጥቼ…”

“እሱን በእኔ ጣለው” አለ ሱፊው፡፡

“እንግዲህ እንዳልክ … እኔ ጭንቅላቴ ስንት እንደሚያወጣ አላውቅም … እስቲ አንተው እርዳኝ … ስንት ብር ልበል ?”

“አይዞህ … አትፍራ … ራስሁ የፈለግከውን ብር ጥራ … የራስሁ ጭንቅላት አይደለ እንዴ ! እንዴ … ምን ይላል ይሄ” አለ ሱፊው… እናም ሰውዬው የራስ ቅሉን በ10 ሚሊየን ብር ሸጠ… ጥቂት እንደተጓዙ፣ “የተቀረውን አካልህንስ መሸጥ አትፈልግም ?!” ሲል ጠየቀ ሱፊው፤ “ምክንያቱም ምን ዋጋ አለው ? አንተ እንደሆነ አንዴ ሞተሃል፡፡

ዓይኖችህ፣ ጭንቅላትህ የለ… ምን ቀረህ ? ከዚህ በኋላ አካልህ ኖረ አልኖረ ምን ያደርግልሃል … እኔ ደምበኛ አለኝ፡፡ ሳይንቲስት ነው፡፡ ሬሳ እየቀደደ ምርምር ያካሄዳል፡፡ ሁሌ ባገኘኝ ቁጥር … ‘አስክሬን አምጣልኝ ነው !’ ፡፡ በተለይ አሁኑኑ የሞተ ሰው አስክሬን ባሉት ዋጋ ለመግዛት ዓይኑን አያሽም፡፡ ምክንያቱም ትኩስ አስክሬን አይገኝማ፡፡

በዕርግጥ ዓይኖችህ ወጥተዋል፡፡ ጭንቅላትህ የለም፡፡ ቢሆንም … ወዲያው እንደሞትክ፣ አስክሬንህ ሳይቀዘቅዝ ስለምሰጠው ደስታውን አይችለውም፡፡ አይገኝማ … ትኩስ ሬሳ፡፡ ልክ እኮ አሁኑኑ የተቆረጠ አበባ እንደማለት ነው፡፡ እስኪጠወልግ ሁለት ሶስት ቀን ይፈጅበት የለ - እንደዛ ነው፡፡

“አይይ በቃ ተውኩት - ራሴን አላጠፋም - ይቅርብኝ” አለ ሰውዬው ድንገት እርምጃውን ገትቶ…

“የግድ ራስህን ማጥፋት እኮ አይጠበቅብህም” አለ ሱፊው፣ “ዋናው ነገር ዓይኖችህን እና ጭንቅላትህን ሸጠህልኛል - እንዳትረሳ !”

“ቆይ ለመሆኑ … ብሩን ማነው የሚወስደው ?” ጠየቀ ሰውዬው…

“ብሩንማ እኔ ነኝ የምወስደው … ምክንያቱም አንተ የት አለህና ?” አለ ሱፊው፣ “እና ስታስበው - ብሩን ማን ይውሰደው ? ብሩ የእኔ የኮምሽን ክፍያ እንደሆነ ቁጠረው፡፡ ይዤው ልሙት ካልክም ብሩን ይዘኸው ሙት - ግን ምን ያደርግልሃል - አንተ እኮ የለህም - ሞተሃል”

ቤተመንግሥቱ አቅራቢያ ሲደርሱ ሰውዬው ሐሳብ ገባው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ … ዓይኖቹ ይሄን ያህል እንደሚያወጡ አያውቅም ነበር - 10 ሚሊየን ብር ! ይገርማል፡፡

‘ከራስ ቅሌ ጋር በአጠቃላይ ይሄ ተራ መሳዩ ጭንቅላቴ ብቻ 20 ሚሊየን ብር ያወጣል !! የተቀረው አካሌም እንዲሁ ! እና ይሄ ሰውዬ በእኔ አካል ሚሊየነር ሆኖ ሊከብር ነው ማለት ነው...’

“አልፈልግም … ትቼዋለሁ … እንደዚህ አይነት ቢዝነስ ይቅርብኝ”

“እሺ ራስ ማጥፋቱንስ ?” ጠየቀ ሱፊው…

“ራሴን ማጥፋትም አልፈልግም” አለ ሰውዬው ቁፍጥን ብሎ፣ “አሁን … በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐብታም መሆኔን ተረድቻለሁ፡፡ እስከዛሬ ራሴን እንደለማኝ ነበር እቆጥር የነበረው፡፡ ራሴን ላጠፋ የተነሳሁትም ምንም የለኝም ብዬ በማሰቤ ነበር - አሁን ግን ምን ያህል ትልቅ ሐብት እንዳለኝ ተረድቻለሁ”

“ያ ያንተ ውሳኔ ነው” አለ ተማላዩ፣ “እኔ እዛችው ኮረብታ ላይ ተቀምጬ ሌላ ሰው ልጠብቅ - አንተ ግን ብታስብበት ይሻላል - እንዲህ አይነት ደምበኞች መቼም አታገኝም…”

“አላግኝ !!! ተወኝ አልኩህ ሰውዬ - ልኑርበት” ተቆጣ ሰውዬው፣ “አንተ በጣም አደገኛ ሰው ነህ፡፡ ኮረብታው ላይ ሁሌ ተመስጠህ ሳይህ ኃይማኖተኛ ሰው ትመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ነው ምን አይነት ሰው እንደሆንክ የተረዳሁት - በጣም አደገኛ ሰው !!! ጨካኝ !!! አንድ በአንድ የአካል ክፍሌን ሸጠህ ብር ልትወስድ ! ብልጥ ! ሞኝህን ፈልግ፡፡
እስከዛሬ ስንቱን ሸጠክ ኪስህን እንዳደለብክ እግዜር ይወቀው፡፡ አሁን ግን ገብቶኛል… ለምን እዚያ ኮረብታ ላይ እንደምትቀመጥ ገብቶኛል፡፡ ቢዝነስህ ያለው እዛ ነዋ፡፡ ለከተማው ሰው ሁሉ ነው እየዞርኩ የምናገረው፡፡ ወደዚያ ኮረብታ እንዳትሄዱ፡፡ ኮረብታው ላይ አንድ አደገኛ ሰውዬ አለ ብዬ ሁሉንም አስጠነቅቃለሁ…”
“እኔ አንተኑ ለመርዳት ብዬ ነው” አለ ተማላዩ፣ “ይሄን ትልቅ ዋጋ ያለውን አካልህን በከንቱ ወንዝ ውስጥ ጨምሬ ካልገደልኩ ስትል ምን ላድርግ ?! ከገባህበት ክፉ ቅዠት ላነቃህ ነው የሞከርኩት፡፡ ተፈጥሮ ውድ ስጦታ ሰጥታሃለች፡፡ አንተ ግን እንደማመስገን በአስቀያሚ መንገድ መሄድን መረጥክ ! ደምበኛ አለኝ ያልኩህ ሁሉ ውሸት ነው፡፡ ንጉሡ ያንተ ዓይን ምን ያደርግለታል ? የሞቱ ዓይኖች ! ምትሐተኛውም የሚፈልገውን ያህል የራስ ቅል ከቀብር ቦታ ማግኘት ይችላል፡፡

በየቀኑ የማን እንደሆነ የማይታወቅ የባይተዋር ሰው አስክሬን
ወደ ሆስፒታል ይጎርፋል፣ ሆስፒታሎች ውስጥ በርካቶች ይሞታሉ፡፡ እና ለሳይንቲስቱ ምርምር ማካሄጃ የሚሆን ትኩስ አስክሬን መች ጠፍቶ ! ስለዚህ … ደምበኛ የሚባል ነገር የለም፡፡ ተፈጥሮ ምን ያህል ዋጋቸው በገንዘብ ሊተመን የማይችል ውድ ስጦታዎችን ሰጥታህ ሳለ አንተ ግን ምን ያህልvምስጋና ቢስ እንደሆንክ እንድታውቀው ብዬ ነው ! ተፈጥሮ ለሰጠችህ ውድ ስጦታዎች የምታቀርበው አንዳችም ምስጋና የለህም ? ራስን ማጥፋት ነው ያንተ ምስጋና ?!”


📚[Osho, The New Dawn, Ch 3, Q 3 (excerpt)]
ትርጉም:- ግሩም ተበጀ


||ይ🀄️🀄️ሉ||
http://t.me/Write_Event
ቃለ መጠይቅ ድሮና ዘንድሮ

(በእውቀቱ ስዩም)

📌ድሮ

ጋዜጠኛ:- ቁርስህን ምንድነው የበላህ?
ወጋየሁ:- "ዱለት"

ጋዜጠኛ:- የልብስ ምርጫህ?
ወጋየሁ:- "ቢትልስ ሹራብ"

ጋዜጠኛ:- በትርፍ ጊዜህ ምን ያዝናናሃል ?
ወጋየሁ:- "ካርታ ጨዋታ "
The end!


📌ቃለ -መጠይቅ ዘንድሮ

ጋዜጠኛ: - ዛሬ ቁርስህን ምን በላህ?

አርቲስት: -" ያው ሰው ሆነን ስንፈጠር ፤ ሰውነታችን እንደ ሰውነት ምግብ መጠየቁ አይቀርም ፤ አርቲስት ደሞ እንደማንኛውም ሰው ምግብ ያስፈልገዋል ፤ ምን ልልህ ፈልጌ ነው፤ ለኔ ትልቁ ነገር ለምግብ ሳይኖር ለህዝብ መኖር ነው ፤ ህዝብ እሚጠብቅብህን ነገር ካበረከትክ ቀኑን ሙሉ ባትበላ እንኩዋ የርሃብ ስሜት አይሰማህም ፤ ወደ ጥያቄህ ስመጣ ቁርሴን የበላሁት በቅርቡ የሚዳሰስና የሚቀመስ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበውን ጨጨብሳ ነው።"

ጋዜጠኛ:- የልብስ ምርጫህ ?

አርቲስት:-" እንግዲህ ሁላችንም ወዲዚህ ምድር ራቁታችንን ነው የመጣነው ፤ ራቁታችንን ሆነን ይሄንን ምድር እንቃለን ፤ ምን ልልህ ፈልጌ ነው፤ ርቃኔን ይሸፍንልኝ እንጂ የጣልያን ሱፍም ቢሆን ለመልበስ ዝግጁ ነኝ’

ጋዜጠኛ:- በትርፍ ጊዜህ ምን ያዝናናሃል?

አርቲስት:- "በዚህ አለም ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፤ ትርፍ ጊዜ ያላቸውና ከጊዚያቸው የሚያተርፉ፤ እኔ ከሁለተኛው ነኝ :: ያለችኝን ትንሽ የረፍት ጊዜ የማሳልፈው ከጉዋደኞቼ ጋር መስቀል አደባባይ ጉግስ በመጫወት ነው::"

ጋዜጠኛ:- ካነሳኸው ላይ የጉግስ ጨዋታን የፈጠረው ኢትዮጵያዊ ማን ይባላል?

አርቲስት:- "እንጃ!! የጥላሁን ጉግሳ አባት መሰለኝ"😂


||ይ🀄️🀄️ሉ||
https://telegram.me/Write_Event
📜ውብ ሐሳቦች🍂


በእየለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን።ያለፀፀት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁምነገር አሳልፍ።ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ልክ እንደገና በህይወት የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና የመወለድ ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውን ና ለማከናወን የምትመርጠውን አይነት ህይወት ለመኖር ሞክር።


📚ዝጎራ
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ

https://telegram.me/Write_Event
📜ውብ ሐሳቦች🍂



"ትልቅ ነገር አብዝተህ አትመኝ"

" ለምን?"

" ትንሽ ከትልቅ ስለሚበልጥ!"

"እንዴት"ልለው ስዘጋጅ "ወራጅ "ብሎ ወረደ::ከአንድ ዓመት በኃላ ታክሲ ላይ ተገናኘን:: ሰውየው በመስኮት አሾልኮ አተር ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ላከ:: የድመት ፊት የምታክለውን ፊቱን እንደስፖኪዮ ወደኔ ቀለበሰው::

" ከሰማይና ከፀሐይ በስፋት የሚልቀው ማነው?" አለኝ ከመቅፅበት::

"ሰማይ ነዋ!"

" ብርሀንን የምታጎናፅፈን ግን ትንሿ ፀሐይ ናት::" ገረመመኝ::

" ከዋክብት ኢምንቶች ናቸው አይደል?" ማታ ማታግዙፉን ሰማይ የሚያስውቡት ግን እነሱ ናቸው::

" ከበጋ እና ክረምት የሚረዝመው የቱ ነው ? ቡጋ ነው:: ዘር እየተዘራበት እህል እየታጨደበት የፍጥረትእስትንፋስ እንዳይቆም ሕይወት እንድትቀጥል እንድትቀጥል የሚያደርገው ግን ከበጋ የሚያንሰው ክረምት ነው:: ከጋንና ከጠጠር ጋን እንደሚተልቅ ሁሉም ያውቃል:: ትልቁን ጋን እንዲቀመጥ የሚያስችለው ትንሹ ጠጠር መሆኑን ግን አብዛኛው ሰው አያገናዝብም::


ከምጣድና ከጉልቻ ምጣድ ይሰፋል ግና ያለ ጉልቻ ምጣድ ማለት ጥቅም የለሽ ተራ ሸክላ ይሆናል:: እየሰማኸኝ ነው አይደል? ደሞ ስማኝ ብትፈልግም አትስማኝ ግን ስማ! ልለኔ አይደለም ለራስህ ስትል ስማ ! ልብ " ሰው" ሰው በሚባል ሀገር ውስጥ የወደቀች ብይ ናት :: ይቺ ትንሽ ብይ አምፃ ቀጥ ባለች ቅፅበት ግን ትልቁ ሰው ከሰውነት ወደ አድከሬንነት
ዜግነቱን ይቀይራል::


ከቅፅበትና ከዘልዓለም የሚረዝም የቱ እንደሆኑ ብጠይቅህ ዘለዓለም እንደሆነ እፍታ ሳትቆይ ትነግረኛለህ:: ዘልዓለም የተፈጠረው ትንሽ እንኳበማይገልፀው ትንሹ ቅፅበት ውስጥ መሆኑን አትነግረኝም:: ልንገርህ? ዘለዓለም ዝርጥርጥ ነው::የቅፅበት ጥበት ውስጥ ነው ውልደት ያለው: የቅፅበት ውልደት ውስጥ ሞት ያለው::


ዘመናት ከቀናት ቢረዝሙም ዘመናትና ፍጥረታት በሞላ የተፈጠሩት በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ ነው::
አሁንም ልንገርህትሪሊዮን ከአንድ ይበልጣል:: ከትሪሊዮን የሚበዙትን ፍጥረታት እና ዓለማት ጨምሮ ሰውን ከነኮተቶቹ የፈጠረው ግን አንድ ነው:: አንድ ፈጣሪ!!::


ወደ መፅሐፉ ተጎነበሰ እንደተጎነበሰ - " በብዙ ውስጥ ትንሽ ከመኖር በትንሽ ውስጥ ብዙ መኖት ይበልጣል::" ብሎ መፅሐፍ ውስጥ ተቀረቀር....🙇


📚[ጥቁር ሽታ]
ደራሲ:- መሐመድ ነስሩ( ሶፎንያስ አቢስ)

||ይ🀄️🀄️ሉ||
https://telegram.me/Write_Event
⭐️🌟⭐️ አብሪ ኮከቦች 💫💥💥

🇪🇹🇪🇹ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ🇪🇹🇪🇹

ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በደብረ ኤልያስ ቀበሌ፣ ጎጃም ተወልደው ሰኔ ፴ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. አረፉ) ስመ ጥር ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ለሕትመት አልበቁም። የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል።


ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ፲፱፻፴፭ ዓ/ም እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመታባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን እንዲሁም የደራስያን፤- ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ እና አቶ [[ተመስገን ገብሬን ምስል የተቀረጸባቸው ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል። (ዊክፕድያ)


ዮፍታሔ ንጉሴ፣ ብሔረ ነገዱ፣ ሀገረ ሙላዱ፣ ጎጃም፤ ቅኔ የተቀኘበት፣ ድጓ የተማረበት፣ ምስጢር ያገመረበት ደብረ
ኤልያስ ነበር። ጠይም ረዥም፤ ጠጉረ ሉጫ፤መልከ መልካም የቆንጆ ጠር፤ ቀጭን ዠርጋዳ ጣተ መልካም ፤ሽቅርቅር ጥዩፍ፤ ኮከቡ ሚዛን ነፋስ ነበር። ምዕ.1 ዮፍታሔ የቀለም ትምህርቱን ከመጀመሩ አስቀድሞ ምግበ አእምሮው የሆነውን የኤልያስን አየር እየተመገበ፣ ዝንጀሮ ያልቸውን ሁሉ ዘፈኑን፣ ስለምኑን፣ቁም ነገሩን፣ ወዘበሬታውን፣ ተረቱን፣ድርሳነ ባልቴቱን፣ ቀረርቶውን፣ልቅሶውን፣እማ በራዩን፣ ሙሻሙሾውን፣አይኮሉን፣ አረቦኑን፣ ወዘተ... እየሰማ ነበር ያደገው። ይኽ ሁሉ ኋላ ለተቀኘው ቅኔና ለደረሰው መዝሙር፣ ቲያትርና ስለምን ዐይነተኛ ዳራ ሁኖታል። ምዕ.1 የቅኔ ትምህርተ ተራውና ደረጃው ከፀዋትወ ዜማ ቀጥሎ ከትርጓሜ መጻሕፍት አስቀድሞ በጉልምስና ወራት ነው። ... ቅኔ የንባብና የጸዋትወ ዜማ ደጀን የትርጓሜ መጻሕፍት ፊታውራሪ ነው።


... ቅኔን ከጸዋትዋ ዜማ በፊት ከትርጓሜ መጻሕፍት በኋላ ለመማር በፍጹም አይቻልም። ይኽውም ከዘር በፊት ቡቃያ ከባል በፊት ልጅ ይሆናል። የቅኔ ትምህርት...የትውልድ አገርን ትቶ ጋራ ዙሮ፣ ወንዝ ተሻግሮ ወጥቶ ወርዶ፣ከውሻ ተከላክሎ ፣ቁራሽ እንጀራ ለምኖ ፣ ደበሎና ማቅ ለብሶ፣ ተዋርዶ ተንከራትቶ፣ ብዙ ፈተና ተቀብሎ፣ አይመስሉ መስሎ፣ ቀይ የነበረው ጠቁሮ፣ ረዥም የነበረው አጥሮ፣ተርቦ ተጠምቶ ፣ ፀዋትወ መከራውን ሁሉ ታግሶ የሚማሩት የተባሕት ትምህርት ነው። "ምዕ.1፤ አለቃ ዕንባቆም ቃለ ወልድን ጠቅሶ" ስለደራሲው በጥቂቱ " ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ ክብሩ" የሚል የኖረ የግእዝ አባባል አለ:: አንዱ ኮከብ በብርሀኑ፤ በግዘፉ፤ መጠቅላላ ተፈጥሮው ከሌላው ኮከብ ይበልጣል::


እኔን የሚያስገርመኝ ይኽ አይደለም:: እንዳንድ ከዋክብት አሉ--በተለየ አጠራር ተወርዋሪ የምንላቸው:: በሌሊቱ ኅዋ ውስት ከአንዱ መአዘን ሰማይ ወደ ሌላው ተወርውረው ብልጭ ብለው ይጠፋሉ:: ይህ ሁሉ የሚሆነው በቀፅበት ነው::ያንን በጨለማው ግርማ የተዋጠውን ኅዋ በብርሃን ጎርፍ ሰንትቀው አጥለቅልቀውት ይጠፋሉ:: ተመልካችም ከመገረም በሚመነጭ ዝምታ ይዋጣል:: በኢትዮዽያም የሥነ ጽሑፍ ኅዋ ውስጥ ዮፍታሔ ንጉሤ አንድ ተወርዋሪ ኮከብ ነበር።


ብሩህ ነጸብራቁ፤
ውበቱና ድምጹ አንድነት ተሰማ
ተው አንድነት ቢበርቁ፤
የመያው ቅለት ጠፍቶ፤
ምስጢሩን አካቶ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በምናየው ሰማይ ነበረ በይፋ።


አዎን፤ ነበረ። በዚያን ቅጽበት በሆነው የጽሁፍ ዘመን ዮፍታሔ፤ የኢትዮዽያን የስነጽሁፍ ኅዋ በቅኔ ፤ በግጥም ፤በመዝሙርና በተውኔት የብርሃን ጎርፍ ሰንጥቆ አጥለቅልቆት ጠፍቷል። ዛሬ የሚያሳዝነው የዚህ ተወርዋሪ ኮከብ ተጽእኖ በዘመናችን
መጥፋቱ ነው። ስለ ዮፍታሔ ንጉሴ በሕፃንነቴ እናት አባቴ ሲያወጉ፤ ሲወያዩ፤ አንዳንዴም ሲከራከሩ እሰማ ነበርበተለይ አባቴ ከዮፍታሔ ንጉሴ ተውኔቶችና መዝሙሮች በቃሉ የሚያስታውሳቸውን ስንኞች ሲያንጎራጉር እየሰማሁ የዮፍታሔ ፍቅር በሕፃን ልቦናዬና ስሜቴ ተሳለብኝ ። ያኔ ከሰማኋቸው ትዝ የሚሉኝ "አንተ ባ...ጎራዴ ግዛ" እና "ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቻ ብላ እጅግ ሳይትሩባት ሳይዘሯት አብቅላ" የተባሉት መዝሙሮች ናቸው። ሁለተኛው በጣም ጠሊቅ መዝሙር ነው። ጠሊቅነቱ የተገነዘብሁት ካደግሁ በኋላ ነው። ያኔ መዝሙሩ ይመስጠኝ የነበረው በቃላቱ ጣእመ ዝማሬ ነበረ። የፊተኛውን መዝሙር ግጥሙን በሙሉ ላገኘው አልቻልሁም። የኋለኛው ግን "ብርሃንና ሰላም" ይባል በነበረው ጋዜታ በሙሉ ተጽፎ ስላገኘሁት ከዚህ ቀጥሎ ጽፌዋለሁ፤

ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቿብላ፤
እጅግ ሳይጥሩባት ሳይዘሯት አብቅላ፤
ስንዴውን ጠብቃ እንክርዳዱን ነቅላ፤
ስትመግበን አየን በፀሐይ አብስላ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናብ መንግሥታችን።
በመልካሙ ዘርእ ላይ እንክርዳቸ ሲዘራ፤
ታሳድገውና ከእንክርዳዱ ጋራ፤
ገለባ ሲቃጠል ገበሬ ሲያመራ፤
ታቃጥለዋልች እንክርዳዱን አብራ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
አይዞህ የኛ ጌታ ነገርህን አትርሳ፤
አለስልሰህ ዝራ የስንዴውን ማሳ፤
የተዘራችው ዘርእ ፈርሳና በስብሳ ፤
ታፈራልቸ ፍሬ ሙታ ስትነሣ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
በጊዜው የዘራ መልካም ዘር አትርፎ፤
ከበሮቹ ጋራ ማታ ከትላ አርፎ፤
ብርነት ታትቆ በቅን ተሰልፎ፤
በቸርነት ታጥቆ በቅን ተሰልፎ፤
ደግሞ ዘሩን ዘራ መክር አሳልፎ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።

………………
ማንም በዕድሜው ብዛት አያስጠራም ስሙን
በጥቂቱም ዕድሜው ይሠራል ሐውልቱን።
ታሪክ ሲያበላሸው ረጅሙም ያጥራል፣
ታሪክ ሲያሳምረው አጭሩም ይረዘማል፤
ብዙ ዘመን ቢኖር ዕድሜውም ቢበዛ፤
በሳቅ በጨዋታ ዋዛን በፈዛዛ፣
ሲለዋውጥ ኖሮ ሃሳቡን ሳይገዛ፣
እንዲሁ ይቀራል እንዲያው እንደዋዛ።

📖ከ "ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" መፅሀፍ የተወሰደ ፤ ደራሲ ዮሐንስ አድማሱ

🙏🙏ክብር ለታላቁ ደራሲና ገጣሚ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ
📜 ውብ ሐሳቦች🍂


« .....በአዕምሮህ ውስጥ ያለው ድብቅ ኋይል በዙሪያ ያለውን ዓለም የመቀየር ተአምራዊ ብቃት አለው! ካሰሩ ነገሮች በላይም የአዕምሮህ አቅም ይልቃል! ሕይወትህን ያለ ምንም ተስፋ መቁረጥ በብልሀት ኑራት! አሸናፊ ሆነህ ተፈጥርሀልና አሸናፊ ሆነህ ኑር። አሸናፊ ሆነህ እለፍ! ከውስጥህ የተሸናፊነት የአልችልም ባይነት የደካማነትንና የስንፍናን ስሜት አስወግድና ሕይወትህን በአሸናፊነት ኑራት!



አንተ ምንም አይነት ሰው ብትሆን እራስህን አክበር፤ እራስህንም ውደድ። ምክንያቱም ጨዋታውን እንድትጫወት የመረጠህና ብቃት አለው ብሎ ያመነብህ እንዲሁም ወደ ሜዳው እንድትገባ የፈቀደልህ አካልም እንዳንተ አይነት ስጋ የለበሰ ሰው ሳይሆን ሰማይና ምድርን በውስጧም ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ሀያል አምላክ ነው። አንተ በብቃትህና በችሎታህ የታመነብህና የተመሰከረልህ ድንቅ ተጫዋች ነህ እኔ ተራና ምስኪን ሰው ነኝ ብለህ በደምህ ውስጥ የሚሯሯጠውን በአዕምሮህ ውስጥ የሚንበለበለውን ሀያሉን እሳት ቀዝቃዛ ውኋ እየረጨህ አታጥፋው።



ያለህን እውቀትና ችሎታ ሸፍነህ ይዘህ አታዳፍነው። አይገርምም! ዛሬ በሀገር ውስጥና በአለም ላይ በሕይወት ካሉ ሀብታም ስኬታማ ታዋቂ ሰዎች እኩል 24 ሰዐት ተሰቶሃል። እሱንም ይህንን እድል ያገኙት እድለኛ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን በጊዜያቸው በንቃት በትጋትና በፍቅር ስለተጠቀሙበት ነው። ለካ ምድር ላይ ለውጥ ለመፍጠር ወሳኙ የቸሰጠን ጊዜ ብዛት
ሳይሆን የተሰጠንን ጊዜ ምን ያህል ተጠቅመንበታል የሚለው ነው።..."


📚[ የ'ኔ ስጦታ]
ደራሲ ብሩክ የሽጥላ


||ይ🀄️🀄️ሉ||
https://telegram.me/Write_Event
ወንጀለኛው
(ካህሊል ጂብራን)

፨፨፨

አንድ በርሀብ የተጎዳ፣ ፈርጣማ ሰውነት ያለው ወጣት በእግረኛ መንገድ ላይ ተቀምጦ እጆቹን በመዘርጋት ረሃብና ሃፍረት እየሸነቆጡት በሚያሳዝን ዜማ ይለምናል። ምሽት ላይ ከናፍሮቹ እና ጉሮሮው ደረቁበት። እጁ ግን እንደሆዱ ባዶ ነበር። ከተቀመጠበት ተነስቶ ከከተማ ወጣና በአንድ የዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ በምሬት ያነባ ጀመር። ከዚያም ረሃብ ውስጡን እየሞረሞረው ግራ የተጋቡ አይኖቹን ወደ ሰማይ ላካቸውና እንዲህ አለ፤ <<ጌታዬ ሆይ፣ ወደ አንድ ሃብታም ሄጄ ስራ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት። እሱ ግን ቡትቶዬን አይቶ ፊቱን አዞረብኝ። የአንድ ትምህርት ቤት በር አንኳኳሁ፣ ግን ባዶ እጄን ነበርና ችላ ተባልኩ። ቁራሽ ዳቦ የሚያስገኝልን የትኛውንም አይነት ስረ ሞከርኩ፣ ይሄ ሁሉ ግን ከንቱ ነበር። ተስፋ በመቁረጥ እንዲመፀውቱኝ ለመንኩ፣ መፅዋቾቹ ግን ተመለከቱኝና <ጠንካራና ሰነፍ ነው፤ መለመን አልነበረበትም> አሉኝ... <<ጌታዬ ሆይ፣ እናቴ የወለደችኝ በአንተ ፍቃድ ነው። አሁን መጨረሻው ከመድረሱ በፊት ምድር ወደ አንተ እንድመለስ ፈቅዳልኛለች።>>



ይሄን ጊዜ ፊቱ ተለዋወጠ። ብድግ አለና አይኖቹን በቁርጠኝነት አጉረጠረጣቸው። ከአንዱ የዛፍ ቅርንጫፍ ወፍራም አርጩሜ ቆርጦ ወደ ከተማዋ በመቀሰር ጮኾ ተናገረ። <<ያለኝን ድምፅ ሁሉ አጠራቅሜ ዳቦ ስጡኝ ብያችሁ ነበር። እናንተ ግን ችላ አላችሁኝ። አሁን በጉልበቴ አገኘዋለሁ! በፍቅር እና በርህራሄ ስም ለምኜያችኋለሁ፤ ስብዕና ግን ዋጋ አልነበረውም። አሁን በርኩስ መንፈስ ስም አገኘዋለሁ!>>
ዓመታት ሲያልፉ ወጣቱ ዘራፊ፣ ነፍሰ-ገዳይ እና የነፍስ አጥፊ ሆነ፣ የተቃወሙትን ሁሉ ያጠፋል፤ ጉልበቱን በመጠቀም ብዙ ሃብት ሰበሰበ። ከግብረ-አበሮቹ አድናቆትን አገኘ፣ በሌሎች ሌቦች ተከበረ፣ በህዝቡ ዘንድ ደግሞ ተፈሪ ሆነ።



ሃብቱና በጉልበቱ ያገኘው ተፈሪነቱ፣ አሚሩ የከተማዋ ባለስልጣን አድርጎ እንዲሾመው አበቃው- ብልህነት የጎደላቸው አገረ-ገዢዎች አሳዛኝ ሥራ። ከዚያ በኋላ ስርቆት ህጋዊ ስራ ሆነ፤ ጭቆና በስልጣን ይደገፍ ጀመር፤ ደካሞችን ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሆነ እናም ዙፋኖች ይፈሩና ይከበሩ ጀመር።
#ስለዚህ ስግብግብነት ነካ ያደረገው ስብዕና አይናፋሮችን ወንጀለኛ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ደግሞ ነፍሰ-ገዳይ ያደርጋል፤ ስግብግብነት የጎበኘው ስብዕና ያድግና መልሶ ስብዕናን አንድ ሺ እጥፍ ጊዜ ያጠፋዋል!


ምንጭ ፦ እንባ እና ሳቅ(Tears and Laughter)

@Write_Event
@Write_Event
ራዛ መጽሔት [ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታህሳስ 30
2013 ]
.
[" ይህ ቀን ባይኖር ምንም ቀን የለም "]ቃልኪዳን የአዮ ልጅ
.
.

...የሰመረ እንቅልፍ ተኝቼ ነበር ግን መንጋቱ አይቀር ነጋ፤አዕምሮዬ ንጋትን ከጠላ ሰነባብቷል። በቃ እንድሁም ሲነጋ ይጨንቀኛል ፤ ደግሞ የትላንቱ ቀን ተመልሶ "ዛሬም አንድላይ ነን " የምለኝ ይመስለኛል ።
የዚህ ዓለም ውጥንቅጡ ትዝ የምለኝ ሲነጋጋ ብቻ ነው። ሲነጋጋ ሁሉም ብልጭ ይልብኛል የፓለቲካ ርዕዮተ ዓለም ፣ የኑሮ ጋጋታው ፣ሃይማኖት የምሉት እስር ፣ ትምህርት የምሉት የነጩ ድስኩር ድርሳናት ...ኤጭ ሁሉም ያንገሸግሸኛል።
ምን አለ እንደ ጨለማው እርጋታ አርምመን በቀረን ?
ህልቆ ዓመታት ለማንኖርባት ዓለም ባይነጋ ?
ምን አለ "(ወዳጄ እንደምለው )ከሞት ታናሽ ወንድም(እንቅልፍ ) ጋር ተፋቅረን ብናመሻሽ ? ፍፁም ሰላማዊ ሌሊቶችን ብንኖር ?
ይሄው ገና ሳይነጋ ናላዬ ይናጋብኝ ጀመር ።

ለማስታወሻዬ ስለዚህ ቀን መንጋት ተናግረ እንደ'ኔ ሰላሟን ላናጋ አስቤ ሲገልጥ አሀዱ ብሎ ቁጥሮች ታዩኝ 11-06-1992 ዓ.ም መብረቅ የመታኝ ያህል በድንጋጤ ስንጥቅ ብዬ ሁለት ቦታ ወጣሁ ፤ ጭንቅላቴ ወድያ በጭንቀት ተወጥሮ ሰውነቴ ወድህ በፍፁም እርጋታ ዘፍ ብሏል ።
ዛሬ የእርግቤ ልደት መሆኑን ዘንግቼው ኖሯል ፤ማታ እንድህ የተመናቀረችው ለዚህም ነው ለካ?!

አፈን ከፍቼ ጥርሶቸን አብለጨለጭኩ ሳቅ መሆኑ ነው፤ በቀን ስቀ አላቅም በቀን መሳቀን ከታርከ እና ከዘመኔ መዝገብ ስፈትሸው ሳልስቅ አያሌ አመታትን እንደ ኖርኩኝ ለመታዘብ ቻልኩ።
በችኮላ ማስታወሻዬን ሳምኳት እና ቀኑ ስለ መንጋቱ ሳላወጋት ከመፃፎቹ ተርታ አቀላቅያት ስልኬን አውጥቼ ወደ እርግቤ ደወልኩ።
ስልኳ ሶስተ እንዳቃጨለ
"እሺ የቀኑ የመጀመሪያው ደዋይ" የምል የእርግቤ መረዋ ድምፅ ተሰማኝ ...
የቀኑ ማለትዋን ግን አልወደድኩትም። ቀን ምን አገባው በኛ መሀከል....
"ሄሎ ሄሎ" ብላ ከሀሳበ ነጠቀችኝ..
ወዬ እርግቤ..
"እንቅልፍህን ሳትጨርስ አትደውልልኝ አላልኩም"
ምንም ሳልል ቀጥታ ሀሳበን እንደወረደ እርግቤ ዛሬ ወደዚህች ከንቱ ዓለም የመጣሽበት... አልጨረስኩም ቀን ማለት አስጠላኝ ምሽት ልበላት እንደ...? እንደ አካሄድ ቆይ ቀንም በቀን ምሽትም በምሽት ለምን አይቆምም ?
ለምን ተጨምቀው ቀን ብቻ ይባላሉ ?
" እ..እ..ተለጎምክሳ" የምል የእርግቤ ድምፅ ስሰማኝ
ያቋረጥኳትን ሃሳብ እርግቤ ዛሬ ወደዚህች ከንቱ ዓለም የመጣሽበት....
( ከራሴ ጋር ተሟግቼ ) ቀን ነው... ብዬ እንኳን ወደ ጥልቁ ምድረ መጣሽ አልኳት
እሷም "ሰልኩን አየር ማረፊያ አስመሰልከው አሁን ምኔ ዲያስፖራ ይመስላል " ብላ በመረዋ ድምጾ ሳቀችና አሰከትላ "ቀኑን የረሳሄው መስሎኝ ነበር" አለች
...ልጅቷ ምን ነካት ቀን የምለውን ቃል ዛሬ ለሁለተኛ ግዜ ጠራችው... እኔም አጸፋውን ቀን. ..ቀን ..አስረ አትበይ እርግቤ ማታ ጨለማ ካባዋን ስትከናነብ ሶስት ሰዓት ላይ የተወለድሽበትን..ትን ..ቀ...ቀ...ቀ..
ካላበድኩ በስተቀር ቀን አልልም!
በፍጹም !
...ከትኩስ ንትርክ መሀከል አዕምሮዬ ዕለትን ወለደ ...
የተወለድሽበትን ዕለት ከጨረቃ ስር ተቀምጠን ስለምንረግም ከ... ከ... ከማንም ጋር ሳይሆን ብቻሽን እንድትመጭ እናሳስባለን ብዬ ሳልጨርስ ሳቋ ቀደመኝ...
የማይቋረጥ ሳቅ ይሄኔ እንባዋ ኩልል ኩልል እያለ በጉንጯ ላይ እየተንከባለለ እየተንኮለከለ ከንፈሯ ላይ የምያርፍ ይመስለኛል ምን አለ እሱን ባደረገኝ...
[የቀጠለ ]

ከረጅም ሳቅ በኃላ "ስምንት ሰዓት ላይ ቀኑን እናከብራለን " አለች...
ለሶስተኛ ዙር ቀን አለች በገንኩ ለጉድ! ጭራሽኑ ቀኑን እናከብራለን ወቸው ጉድ አለ የሀገረ ሰው ታድያ ይበላ ምን ያገባኛል ደሞ ለተረት...
ግደታ ካልሆኔ በ... ቀ... ቀ... ቀን(እያበድኩ ነው ወይስ አበድኩ) ከቤት እንደማልወጣ እያወቅሽው...
የንዝንዝ ድምፅ ተከተለ "እኔ የተወለድኩበት ቀን ላንተ ምንም ናት በቃ የኔ ቀን ግደታ ላንተ መሆን አትችልም እያልከኝ ነው..?"

ለአምስተኛ ዙር ቀን አለች እኮ ኡ.............ኡ............ኡ..........ብሎ መጮኽ አማረኝ ለስድስተኛ ዙር ሳትለው እሽ ስምንት ሰዓት ላይ ተባብለን ተስማማን ና ስልኩን ዘጋን።

ቀን ቀን ስሆን የኤሊን እግር እና ማታ ማታ ስሆን የጥንቸልን እግር ሰዓት እንደምትዋስ ካወኩኝ አመታት አልፈዋል ።

ከመፅሐፍዎች መሀከል መዝገበ ቃላት የምለውን መፅሐፍ አወጣሁ ...ሿ..ሿ...ሿ.. እያደረኩ 'ቀ' ላይ ደረስኩ በጥሞና እያገላበጥኩ ቀን ለተሰኘ ቃል ትርጉሙን ማንበብ ጀመርኩኝ ።

"ቀን"
1ኛ" ሃያ አራት ሰዓታት የምሆን የብርሃን ና የጨለማ ግዜ" እኔ በዚህኛው አላምንም የትኛው ነው የብርሃን ግዜ ? የትኛው ነው የጨለማ ግዜ ?

2ኛ"ከጠዋት እስከ ማታ ያለው የብርሃን ግዜ" ጨለማስ? ይሄው ከራሳቸው ሳይሆኑ ልያሳምሙኝ ነው።
መታመም ምንድነው ? እኔ እንጃ! መፃፏን አሽቀንጥረ ጣልኳት።
ወደ ራሰ ትርጓሜ ስመጣ ቀን ማለት የፀሐይ አንባገነናዊ ግዛት ነው።
ምሽት ማለት ደሞ የጨረቃ ደሞክራሲያዊ ግዛት ነው ።
የጨረቃ ህገመንግስታዊ ራዕይ ለጨለመበት ማፍካት እና አብሮ መጓዝ ነው።
የጨረቃ ህገመንግስት አንቀጽ 39 የእጅ ባትር የያዘ ካለ መገንጠል ይችላል ይለናል ።
ሁሌ ስገዱልኝ ብላ እንደ ፀሐይ ስለማትወጣ ሰላማዊነትን እንጂ አንባገነናዊ ስርዓት አታራምድም።

ይዋል ይፈጅ እንጅ መድረሱ አይቀርምና ሰዓቱ ደረሰ።
ከክፍለ ቀጥሎ ካለው መምህሩ ቤት ክፍት አፉ ቲቢ የሰባት ሰዓት ዜና ይዜን ቀርበናል ስል..
የት ? ብዬ ከቤተ ውሄ ይዥ ወጣሁና ተጣጠብኩ ፤ ልብሴን ስቀያይር 7:30 ሆነ ሮጨ ከቤት ወጣሁ የቀጠሮ ቦታ ስደርስ አስር ደቂቃ ይቀራል ዞር ዞር ብዬ ስቃኝ እርግቤ ገና አልመጣችም ።
ጥግ ተቀምጨ በእጅ ምልክት አስተናጋጁን ና ብየው እርግቤ እስክትመጣ ማኪያቶ አዘዘኩኝ።

እርግቤ ከቀጠሮው ሰዓቱ ሁለት ደቂቃ አረፍዳ መጣች። በስሱ ጉንጯን ስመ ወንበር ስበ አስቀመጥኳት።
እ..ር..ግ..ቤ ..ብዬ ጠርቼ ሳልጨርስ ምን ልታዘዝ የምለው የአስተናጋጁ ድምፅ ረበሸኝ ፤ ፈጥኘ ምንም አልኩ
እርግቤ ሳቋን አስቀደመችና " ሞቆኛል በመጀመሪያ የቀዘቀዘ ውሃ አምጣ ቀጣዩን ላስብበት" አለች ከዛን " የኔ ውድ ቃልዬ ቤት እንቀይራለን ከዛን የመጀመሪያውን እቅድ እናሟላለን " ስትለኝ
የመጀመሪያውን እቅድ ምንነት ጠየኳት ተቅለስልሳ"ቃልዬ በመጀመሪያ ወይንን ለፍቅራችን እናነሳለን ከዛን እጅ አቆላልፈን እንጠጣለን " ብላ መለሰችልኝ

እኔም ኤድያ ስንቱ ተርቦ ፣ተጠምቶ፣ እየማቀቁ እያየን ውስኪ የመርጨት ጥቅሙ ነው እኔ የማይገባኝ ነገር...
እውነት ለፍቅር ካልን ምንም ባናደርግም የኔ ብጤን በማቀፍ ፍቅራችንን እናሳይ ካልሆነ ብዬ እንቢተኝነተን ስገልፅ

ፍቷን ሰረዝ በሰረዝ ፅፋው የምፈጀውን ንዴቷን አስከትላ "baby you don't understand how I waiting this day ይሄ ቀን ማለት ለኔ ትርጉም አለው።
የዛሬውን ቀን ከምን በላይ እወዳለሁ ።
የዛሬ ቀን ማለት ይህ ቀን የመፈጠር ምክንያት ነው።
በህይወቴ ይህ ቀን ሁሉም ቀን ናት ።
`ይህ ቀን ባይኖር ምንም ቀን የለም ። '' አንተም ብትሆን ።

ገና ሳለገኛት አምስተ ቀን... ቀን.. ቀን..ስትለኝ ጭንቅላተን ይዥ ብድግ ብዬ ከአጠገቧ ተነስቼ ከካፈ ወጣሁ

ተከትላኝ ወታ " ቃል
Channel name was changed to «የቃልኪዳን ገጾች»
[``ዝግመተ ምዥራጥ'']
.
ቃልኪዳን
.
የነፍሴ መዋለል
የሃሳቤ ብክለት ፥
ዝግመተ ምዥራጥ

ሰማዩም ምድሩም
እነሆ የዞረበት
ልፍታው በቃላት


ኑሮ ተማገረ
ከትላንት ዛሬ ስል
አካሌ ማሰነ

መብከንከኔ ቀርቶ
ቢናፍቀኝ መስከነ
ህይወትን ዘገነ

ግን የለም የራቀው
መንሰፊሰፍ ነው
ተግ ሸሽቶ ከቀኔ

ከህልውና ኑረት
ተቅበዝብዞ መሸሽ
ደራ በዘመኔ
* * *
ይሄው እላለሁኝ
አለህም የለህም
ከራሴ ተጣልቼ

መኖርህን በገሀድ
እጠራጠራለሁ
እውነታውን ስቼ

ተስፋ ያደረኩት
ህልሜ እየተነነ
ካልተሞሉ ግቦቼ

የለህም እንዳልኩኝ
አለህ እላለሁኝ
ከራሴ ተሟግቼ
* * *
ወዴት ነህን ?
የትስ ነህን ?

መገኛውን ቀርቦ
መዳሰስ መጠየቅ
ሰርክ ያምረኛል

በኔ ህይወት ምናኔ
የሱ ህያው መሆን
አልታወቅ ይለኛል

ደሞ ምንተዳዬ
በኔ መኖር ዳና
እሱ ይኖር ይሆናል

ኤልሻዳይ ነው ስሉኝ
እኔም አሜን ብያለሁ
መኖሬን ማን ያውቃል ?
* * *
በህልውና ህያውነት
ስገለጥ ሃያልነቱ
ካለው በህይወት

ህያው ነው ማለቴ
እውነታውን ኖሯል
ይገዝፋል ከኑረት

ደሞ ምን በወጣኝ
ከመኖረ በላይ
ስደንቀኝ እስትንፋሴ

ያለውን የለም ስል
ምናምኒት ሳልጨብጥ
ልኳትን ከነፍሴ


join

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
መቼ ያቆማሉ...

ቃልኪዳን አዮ




በምድረ በዳው ልቤ
የፍቅርሽ ዝናብ ሲፈስ
የመውደድ ረሃበ
በዳናው ሲረሰርስ
ታውቆኛል እርግቤ
ቡቃያ ሲጠነሰስ
ወፍ የማይጠረጥረው
ፍረው እንደምቀነጠስ

እናማ እርግቤ ሆይ
የተባልኩት ሁሉ
ጨርሶ ካልገለፀኝ
ያሉትን ስለ'ኔ ይበሉ
ስለ'ኔ እንዳወሩት
ስ'ላንች ይቀባጥራሉ
መቀበልን ወድያ
ወድህ ከውነት ቃሉ
ሀ ብለን ከሰማን
መቼ ያቆማሉ

'ባሉባልታ ዝግመት
አይቋጥርም ልቤ ቁርሾ
'ባሉባልታ ዝግመት
አይቋጥር ልብሽ ቁርሾ

የምለውን ብቻ ስሚ
ያንችን ብቻ ልስማ
የጋረደን ግርዶሽ
በፅኑ እንዳይለማ


ያኔ እስከ ምንለው
ይህም በዛሬ አልፎ
ዝግ ይሁን እስከዛ
ልባችን ተቆልፎ
ማንም አይግባበት
ለሁካታ ተሰልፎ
ለፍቺ እንዳይገፋን
ተዕምነት ተላልፎ

share n join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
የምሳ ሰዓት
.
.
.
ሰሞኑን ስራ መግባት መውጣት ስልችት ብሎኛል ። ቆይ ሰራተኞች ይሄንን ሁሉ አመታት ድግግሞሽ የሆነ ህይወት እንደት ይችላሉ ? ይብላኝ ለነሱ እኔስ ተማር ነኝ ማለት ያምረኛል ግን ዘንድሮ ተመራቂ መሆነን እና አሁን ልምድ ልውውጥ ላይ መሆነ ትዝ ትዝ ስለኝ ቃሉን ሳልተፋው ለመዋጥ እገደዳለሁ።

ኦሾ እንድህ ተናግሮ ነበር ``የምትማሩት ለደመወዝ ብቻ ከሆነ ከሰላሳ ቀን በላይ አሻግራችሁ የምታዩት ራዕይ የላችሁም ማለት ነው'' ታድያ የሀገረ ሰው እውነት ይሄንን መመሪያ ተግባራዊ አድርጎ ነው ሳይታክት የምሰራው ? መቃዠት ጀመርኩኝ እንደ? ከመከላከያ ሰራዊት በስተቀር ማን አለ ሳይታክት የምሰራ? ማንም የለም መቸም የምኖር አይመስለኝም ። ሁለም ትንግርት የሆነች ቃል አለች ከጠዋቱ እስከ አመሻሽ በሁሉም መንግስት መስሪያ ቤት እንደ ስራ ቋንቋ የተሰየመች እሷም ማን ናት? ካላቹኝ ``ገና ለምሳ ወተው ነው'' ተብየ ናት። እኔስ በቀጣይ ስራ ቦታ አፈነግጥ ይሁን ? ለምሳ ወተው ነው ተብየ መለያ እደርበው ይሁን ? ብሎ ራስን መጠየቅ ከአሁኑ ይበጃል ።

ይህ ለምሳ ወተዋል የምትለው ቃል ምንም እንኳን መነሻው ከመንግስታዊ መስሪያ ቤት ብነሳም አሁን ላይ ግለሰባዊ ድርጅት ላይም ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል ። እሰይ ጥሩ ለውጥ ነው!! ማለት ይቅርታ ነውጥ ይሁን ? ምን አውቀ?

ከትላንት በስትያ አንድ ሱቅ ጎራ ብዬ ነበር። ሱቅ ከማለቴ [ሳልጨርሰው] አስቀድመው ሱ... እንዳልኩ
አበት አለች እናትየው ፤ ፍጥነቷ ገርሞኝ በውስጤም አበት የስራ ሰው ስል አደነኩኝ ግን እውነታው ወድያ ነበር ። ምክንያቱም ሱቁ ውስጥ በአካል ይቁሙ እንጂ መንፈሳቸው ለምሳ ወቷል።
ካርድ አልኳት ? ዝም አለች አልሰማችም ይሆናል ብዬ እናት ካርድ ብዬ አስር ብር ኪሎ ላይ አስቀምጬ ተቅለሰለስኩኝ አሁንም ዝም ዝም አለች አፍጥጨ ወደ ውስጥ ሳያቸው እነሱ ቡናቸውን እየቀሸሩ ነው ለካ !! ስትንቀራፈፍ ቆይታ ባለስንት አለችኝ ብሩን አሳየኋቸው። አሁንም ዝም ዝም አሉ!! ንዴቴ አይሎ ከኪሎ ላይ ብሩን ወስድኩና ለምሳ ወጥቻለሁ አይሉኝም ምነው ደንባችን ፣ ወግ ወጉን ዘነጉት ስል ዝቸ ሌላ ሱቅ ከነፍኩኝ።

አሁን አሁንማ ግፈኛ የሆንኩ እየመሰለኝ ነው። ታካሚ መቶ ዶክተሩ እኔን ያስቀምጠኝ እና ካፈ ነኝ እዝሁ ግብ ውስጥ በሽተኛ ከመጣ ለምሳ ወተው ነው በል አስቸኳይ ከሆነ ደውልልኝ...
አበት አበት የሰው ዝቅጠት የምሳ ሰዓት ሶስት ሰዓት ሆነ እንደ?
አንድ ቡና አዞ ቅጥ እስክደርቅ ድረስ መቀመጥ ምን የምሉት ብሂል ነው?

ከራሴ ጋር እየተማገትኩ እያለ አንድት እናት ልጇን ይዛ መጣች በቃ ልቤን በላችው!! የሰው ልብ ይበላል እንደ?! ትሉኝ ይሆናል !!
ምንም ሳላንገራግር በጥድፊያ ደወልኩለት ።
ለምሳ ወተው ነው በል የምል ድምፅ ሰማሁ
``No no doctor this is priority wanna business " ስል ተሟገትኩ
"okay i will come" አለ!!
ይበል እንጂ የሱ መምጫ በግምት ከካፈ እሰከ ተመላላሽ ታካሚ ክፍል ሃያ አምስት ሜትር ብሆን ግን አዘገያየቱ የጌታ መምጫው አስመስለው ።

መምጣቱ አይቀርምና ኤሊዬ መጣ(ዶክተሩን ኤሊዬ ብዬ ልጠራው የተገደድኩት የአመጣጡን ፍጥነት ለክቼ ነው። ምን አልባት ኤሊ በሱ ትቀና ይሆናል ምክንያቱም አመጣጡ ኤሊን የምያሰንቅ ነው።) መግባቱን ያወኩት ደጅ እንደ ደረሰ በዘፈቀድ 'ምን አሟቸው ነው ?' በማለቱ ነው ። ያመማት ልጇን እሱ ግን ...?
እናትየው 'ወባ ነው መሰለኝ ' አለች ሀዘን እና ጥርጣሬ በተቀላቀለበት ድምፅ
'ታድያ ወባ ከሆነ መድኃኒት አትገዥም ነበር ለምን አዘልሽ አመጣሽ?' አለ ዶክተር ኤሊ
እናትየው 'አይ ልጄ እንድሁ ገምቸው ነው' ፍርሃት በተቀላቀለበት ድምፅ
'አንቺ ነሽ ወይስ እኔ ነኝ ዶክተር ?' ጓንቱን እያጠለቀ በንቀት አስተያየት እየተመለከተ ይነዘንዛል ዶክተር ኤሊ

ከእናትየው ይልቅ የኔ ስሜት ተጋጋለ በውስጤ ራሴን መነታረክ ተያያዝኩት ቆይ ይሄ ሆስፒታል ነው ወይስ እስር ቤት?
ቆይ ይሄ ተመላላሽ ታካሚ ክፍል ነው ወይስ የታራሚዎች መነዝነዣ ክፍል ?
ይሄ ዶክተር ነው ወይስ ፖሊስ ?
የለበስኩትን ጋዮነን አውልቀው ከክፍሉ ወጣሁና የክፍሉን ምንነት ማንበብ ተያያዝኩት ተመላላሽ ታካሚ ክፍል (opd) ይላል ።

እርግጠኛ ሆነን እናውራ ብንል "ድሮም ስም ግብሩን ግብር ስምን መች ገልጾት ያቃል(የድሃ ልጅ ሃብታሙ እየተባለ )" እናንተ እኮ አታፍሩም ከመቶ ፐርሰንት አሰር እጅ የምሆነው ይገልጻል ትሉኝ ይሆናል ፤ ያው ድስኩር ትደሰኩርና ህዝበ ለክቶት ለመገንዘብ ግዜ መፍጀት እንደማይፈልጉ ስለ ምትረዱ በፐርሰንት ትቀባጥራላችሁ።


ከኔ ጋር ለልምድ ልውውጥ ከግብ ወደ ሆስፒታል የተመደበው ልጅ ትከሻዬን ቸብ ቸብ ሲያደርገኝ ፈዝዠ ከቆምኩበት ነቃሁ ።
"ምነው ፍዝዝ ብለሃል " ልጁ ነው መፍዘዘ ገርሞት
አይ ምንም እንድሁ እያሰብኩኝ ነው
``የምሳ ሰዓት ነው እንውጣ'' አለኝ
በል አንተ ውጣ እኔ ትንሽ ቆያለሁ

ኦሯ በሚካኤል ሁሉ ቃዥቶ የለም ?!
ለመብላት ነው የምንኖረው ወይስ ለመኖር ነው የምንበላው ?!
ተምታታብኝ 'ኮ። ሆድህን ግዛው ወይስ ሆድህ ይግዛህ ተብሎ ነው የታወጀው ?!
ምነዋ ወዳጄ ቅጡ እና ቂጡን መለየት አቃታን?!

ምን አለ ሳንበላ አንድ ሰዓት ብያመልጠን?! ይሄንን ነው መሸሽ !!
ቆይ እነዛ የጫካ አደሮች አንተ በቀን ሶስቴ እያገሳህ እንድትበላ እሱ በቀን አንዴ ለመብላት ስንት አሳሪ እንደምያይ ተገንዝበሃል ?! እውነት እውነት በዝህ አመጋገባችን ፈጣሪ ይታዘበናል።

ወቶ አደርን ተመልከት በበረሃ ስንቁ ደረቅ ብስኩት ነው። እሱ ደረቅ ይበላል ከአንጀቱ ጋር እየተሟገተ። ይህ ሁሉ ለምን ይመስልሃል ?! አንተ ለም ለምን ያለ ምንም መንጋጋት እንድትበላ ነው ። አንተ ጣፋጭ ጣፋጩን እንድት ጎነጭ ነው ። ግን አመድ አፋሽ አንሁን ምስጋና ያንሳቸዋል ይሄንን ፅሁፋ ስታነብ ባለህበት ቆመህ ለ1 ደቂቃ ብሆን ብቻ እስከ ምትችለው ድረስ ክፉ አይንካችሁ ስትል ፀልይ እና ለነሱ ያለህን ክብር ለራስህ አሳይ።

ይሄው እንዳልቆምክ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም የምሰራላትን ሳይሆን የምገላትን ነው እኛ የምናወድሰው። ቆምክ በል ፀልይ አመሰግናለሁ ።
ርዕሳችን ምን ነበር ?! ስለ ምሳ ሰዓት። ምነዋ ምሳ ባንበላ አንሞት ነገር?!
እኔ እንደው ሳስበው ግርም የምለኝ ነገር ቆይ ፈጣሪ አያድርገውና የሰባ ሰባቱ ድርቅ ብመጣስ?!
ያ መንገደኛው ባለቅኔ ``በሰባ ሰባት አንድ እንጀራ ለሰባት
እሱንም ከተገኘ ምን አልባት " ብለው እንዳቀነቀኑት የኛ ህይወት እንደዛ የምሆን አይመስለኝም ። አንድ እንጀራ ለሰባት ብገኝም ወይ የሃይማኖት ወይም የብሔር ግጭት ተፈጥሮ ሳንበላት ወደ መረት የምንሰዳት ነው የምመስለኝ። በእርግጥ ድርቅ ብጋረጥ ሁሉም አይተርፍም ሁሉም አያልቅም ። ይሄው ዛሬም ከጎናችን በቀን አንድ ጉርሽ የምያገኝ ስንቱ ተከምሯል ዳሩ የኛን መጥገብ እንጂ እሱ ምን በላ ማለቱን የት እናውቃለን ።
በዝህ ዘመን ወዳጅ የምመስለን የተጫማው ፣የለበሰው እና ያገጠው ብቻ ነው ።
ቡትርፍ ቡትቶ ለባሹ ሰው መሆኑን መለየት ካቃተን እኮ አያሌ ግዝያት እኮ ነጎዱ ።
የሰባአዊነት አንድምታ ህሊናችን ዝጎ ከረሳው ሰነባብቷል ። ሰው መሆን ካቃተን ቆይቷል ።
አሁን ሰው አይደለንም ስጋ ተሸካሚዎች ነን። ለመሸከም እንስሳትም ይሸከማሉ ። ፈጣሪ ይመስገን ሰው ጨርሶ አልጠፉም አንድ አንዶች አሉ ከአያሌ ሰው መሀ
ከል ሰው መሆንን የተገነዘቡት።

በሉ ከእናንተ ጋር እያወራሁ የምሳ ሰዓትን እየረሳሁ ነው ።
አታረሳሱኝማ የምሳ ሰዓት ነው ። እትዬ ስምተው ይሁን?! እትዬ የምሳ ሰዓት ነው።]