ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
እኔና አንቺ
(ሜሪ ፈለቀ)

“አንተ ሴሰኛ አይደለህም፡፡”  ትዪኛለሽ። ሴሰኝነት ‘ስሜ’ መሆኑን አንቺም፣ እኔም፣ ከጎኔ የሚሻጡት ሴቶችም፣ እኔን የሚያውቁኝም ሁሉ እናውቃለን፡፡

ለራሴ ‘ያለማወቅሽን እና የዋህነትሽን’ ነገርኩት፡፡ ላንቺ ግን ዓይኖቼንም ልቤንም የጠለፈውን ህልም የመሰለ ውበት ያለው አካልሽን እያየሁ ጥርሴን ለመግለጥ ከንፈሬን አሸሸሁልሽ …….. ሚስጥር አዘል ወጋገን ያለው ፈገግታሽን መለስሽልኝ፡፡

“አንተ የእኔ በመሆንህ እድለኛ ነኝ::” አልሽኝ የሳምኩሽ እለት…….. በልቤ ሳቅኩብሽ…..  በጥርሴ ሳቅኩልሽ …..

“አንተ ከንቱ ሱሰኛ አይደለህም::”  አልሽኝ አስረኛ ሲጋራዬን እየተቀበልሽኝ ……. የሙሉ ጊዜ ስራዬ ሱስ መሆኑን ካንቺ በላይ የሚያውቅ አልነበረምና ግራ አጋባሽኝ፡፡

“አንተ እኮ ታታሪ ሰራተኛ ነህ፡፡ እንደማውቃቸው ሰዎች ሰነፍ አይደለህም፡፡ ለምን ስራ አትሰራም?”  ያልሽኝ ቀን
‘ትፎግራለች እንዴ?’ አልኩኝ ለራሴ …… በአንድ ዓይነት የትምህርት ዘርፍ ተመርቀን አንቺ ቤተሰብሽን ስታስተዳድሪ እኔ ቤተሰቤን ሳሳርር ዓመት እንዳለፈን ካንቺ በላይ እማኝ የለኝም፡፡

ከቋመጥኩለት ገላሽ ጋር መውደቅ አጓግቶኝ እንዳንቺ የወደድኳት ሴት ያለመኖሯን ምዬ ተገዝቼ  ስነግርሽ

“አምንሃለሁ፡፡ እኔን የምትዋሽበት ምክንያት አይኖርህም!!” ብለሽ ውሸታምነቴን አገዘፍሽብኝ፡፡

ማንም ወንድ ያልዘለቀው ገላሽን ስዘልቀው ………………. እድለኛነቴን ሳይሆን ‘ስላፈቀርሽኝ ራስሽን አሳልፈሽ በመስጠትሽ’ እድለኛነትሽን ነገርሽኝ እና ከደስታዬ ይልቅ ራስምታቴን አበዛሽው ………….

አብሬሽ ሆኜ ከሌሎች ብዙዎች ጋር አብሬያቸው መሆኔን ታውቂያለሻ !……….. ለቁጥር የሚታክቱ ጊዚያት ብልግናዬን ደርሰሽበታላ !……… ለተገለጠ ስድነቴ ብዙ ሰበብ ስደረድርልሽ

“ምክንያትህ አንተን ካሳመነህ ለኔ አትንገረኝ::”  ብለሽ ምንም ያልበደልኩሽ ያህል ከረሳሽው ቀናቶች ብቻ ናቸዋ ያለፉት!!

አንቺ በህይወቴ  እስከተከሰትሽበት ጊዜ ድረስ ሴት ልጅ …………. ልብ፣ ነፍስ፣ አዕምሮ፣ ስሜት ……..( ከሚታየው የሰውነት ክፍሏ ውጪ ያሉት የ’ሰው’ነት መለኪያ) አብሯት ስለመኖሩ አስቤ አላውቅም፡፡ የሴት ፍቺው - እኔጋ የሌለው የሴትነት አካሏ ነበር፡፡ …..  

የተናገርኳቸው ቃላትም ሆነ ያደረግኩት ድርጊት ሁሉ  የተለመደ ……. ቁጥራቸውን ለማላስታውሳቸው ሴቶች ሁሉ ያልኩትና ያደረግኩትን  ነበር፡፡

ከመቼ ወዲህ ነው የሴት ልጅ ነፍስ ይናፍቀኝ የጀመረው? መቼ ላይ ነው የሴት ልጅ ከንፈር ከመሳም አልፎ የሚያፈልቀው ቃል ይርበኝ የጀመረው?  …… ለስንተኛ ጊዜ አካልሽኝ ከተዋሃድኩት በኋላ ነበር ነፍስሽን የተዋሃድኳት?………..……… በሆነ በኔና ባንቺ ቀናት ውስጥ በአንዱ ቀን ወይም በሁሉም ቀን ነበር እንደዛ የተሰማኝ፡፡

መቼ ነው አንቺ ነህ የምትዪኝን እኔነቴን እየወደድኩት፣ የሆንኩት ራሴ እያስጠላኝ የመጣው? የትኛው ቀን ላይ ነው አንቺን ለማማለል ሳይሆን ትክክለኛ ስሜቴን ማውራት የጀመርኩት? ምን ካልሽኝ በኋላ ነው ራሴን ማረም እና ንግግሬን መቀባባት፣ ድርጊቴን መደበቅ ሳያስፈልገኝ ራሴን አሳይሽ የጀመርኩት? …….. የትኛው ቀን ላይ አንቺ ነህ ያልሽውን ሰው ለመሆን መወሰኔን አላውቅም፡፡ ከራሴ መማከሬም ትዝ አይለኝም፡፡

ብቻ…………… እግሮቼ ስራ ፍለጋ ሲኳትኑ፣ እጆቼ ሱሳቸውን ላለመከወን ሲታገሉ፣ ምላሴ ላለመዋሸት ከህሊናዬ ጋር ሲጣላ፣ ከሌላ ሴት ተኝቼ ይሰማኝ የነበረው ደስታ በበዛ ፀፀት ሲተካ………… ራሴን በቃልሽ ሳበረታ አገኘሁት፡፡

ክንዴ ሌላ ሴት አንተርሶ ሳለ ደወልሽልኝ፡፡ ‘የት መሆኔን’ ስትጠይቂኝ ለመዋሸትም ያለሁበትን ለመንገርም ቃል ከከንፈሬ አልወጣ አለኝ፡፡ ……

“ መጣሁ ህይወቴ የት ነሽ?”  ነበር ያልኩሽ ……

በስምሽ የጠራሁሽ ልቤ ውስጥ መከመርሽን የሚያሳንሱብኝን ቃላት ላለመጠቀም ነበር፡፡ …….ማሬ፣ ፍቅሬ፣ እናቴ ፣ውዴ…… ሁሉንም ቁልምጫዎች ለሌላ ሴት ብያቸዋለሁ …………….

“ስትጨርሽ ደውልልኝ!!”  ማለትሽ ለቸኮለች ነፍሴ አልገባትም፡፡

“ መጣሁ!!”  ስልሽም በአካሌ ብቻ አልነበረም ….. በሁለንተናዬ እንጂ

“ከኔ ጋር ሆነህ ሌላ ሴት ትቀጥራለህ? ….. ስድ ነህ!!!” ብላ እንደብራቅ ጮኸችብኝ ካንቺ ጋር ሳወራ ነፍሴ መሳቋ የገባት ሴት …..

“ከዛሬ በኋላ ስድ አልሆንም!!” ብዬ የመለስኩላት እውነቴን ነበር፡፡ ……

ካንቺ ውጪ ለመጨረሻ ጊዜ የተኛኋት ሴት መሆኗን ለራሴም እያረጋገጥኩለት ነበር፡፡ ……. ልቤም እግሬም አንቺጋ ለመድረስ ተጣድፈው ሸሚዜን እየቆላለፍኩ የሆቴሉን ክፍል ለቅቄ ስወጣ ነበር ሩቅ በማይባል ቦታ ተቀምጠሸ  ያየሁሽ ………… ካልሺኝ ሁሉ በጉልህ የሰማሁት ንግግርሽ

“መቼም የማትሻሻል ሴሰኛ ነህ!!”  የሚለውን ነው፡፡

ላስረዳሽ አልሞክርም፡፡ አንቺ ነህ ካልሺኝ በላይ የትኛውን መሆኔን ራሴም እርግጠኛ መሆን አልቻልኩማ ………

join
   ★ ★ @write_event   ★  ★
አይዞህ ልቤ

ድንገት ቢከፋ ባይቀና ኑሮ በዚች አለም
ጊዜ የማይፈታው ምንም የለም

ጊዜም አሁን ነው ትላንት ሆኖ ቀሪ
የነገን ቀን ሰሪ

አመት ያህላል ቀን እየዞረ
ዛሬም እራሱ ነገ ነበረ
የጊዜ ሚዛን አይላወስም
#ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም

ሳዝን አልውልም ሳላቅ ማደሬን
የኔነው በቃ አልሰጥም #ዛሬን

ቴዲ አፍሮ
Read more

share
@write_event
​​👉የሀበሻ መዝገበ ቃላት

•ዘመድ:- ባልተዘጋጁበት ቀን የሚመጣ ተጨማሪ ችግር

•ጫማ:- አብሮ የሚደክም እውነተኛ ፍቅረኛ 

•ደሞዝ :- ከወጣበት ዕለት ውጭ ቁም ነገር የሌለው

•ብድር:- በፍቅር የወሰዱትን በጦርነት የሚመልሱበት የዝርፍያ ሙከራ።

share n join
@write_event

      •═•••🍃🌺🍃•••═•
Book for ALL | Facebook (Facebook)

ኢትዮጸጵያ ውስጥ

የሙዚቃ ተንታኝ — ሰርፀ ፍሬስብሃት
የኳስ ተንታኝ — መንሱር አብዱልቀኒ
የስነጽሑፍ ተንታኝ — አለማየሁ ገላጋይ
የስእል እና ቅርፃቅርፅ ተንታኝ — በቀለ መኮንን
የህግ ተንታኝ—አብዱ አሊ ሂጂራ
የፖለቲካ ተንታኝ —100 ሚሊየን ህዝብ
share n join
@write_event
አስተናጋጁ..!


ባልና ሚስት ወደ አንድ ሬስቶራንት ለመገባበዝ ይሄዳሉ

ብዙ ጊዜ ባልና ሚስት ወደ ሬስቶራንት ሲሄዱ ከምግቡ ይልቅ ጨዋታቸውን ይደምቃል ከጥቂት ቆይታ በኃላ አስተናጋጁን ለመጥራት ያጨበጭባሉ

አስተናጋጁ አልመጣም.....

ድጋሚ አጨበጨቡ አሁንም አልመጣም....

ለሶስተኛ ጊዜ አጨበጨቡ ...ድንገት ከጥግ በኩል አንድ ቀብረር ያለ አስተናጋጅ ወደነሱ መጣ...

አስተናጋጅ፦ "ዝም ብሎ ጭብጨባ ምንድን ነው ? ሰርግ ቤት ነው እንዴ ያላችሁት ?
.....ና... ወንድሜ ታዘዝ ነው የሚባለው "
.
በጣም ይደነግጡና

ሚስት ፦"ሆቴል አስተናግደህ እንደዚህ የሆንክ የኣለም ዋንጫ ብታዘጋጅ ምን ልትሆን ነው "
.
አስተናጋጅ፦ " ዝም ብለሽ አትለፍልፊ የመጣሽበትን ብቻ ተናገሪ "
.
ሚስት ፦ " በቃ ታዘዘን ምን ምን አለ ? "
.
አስተናጋጅ፦ "ቋንጣ ፍርፍር አለ .... እንቁላል ፍርፍር አለ....ጥብስ አለ.. እንደገና ቋንጣ ፍርፍር አለ .... እንደገና ጥብስ አለ እንደገና ....."
.
በጣም ይናደዱና
"በቃ ጥብስ አምጣልን!! "
.
አስተናጋጁ፦ "ይመጣላችኃላ !! ይሄዳል ይደርስና ግን አያዝም ....ድጋሚ ወደ ተስተናጋጆቹ ጋር ይመጣና
" ጥብስ ነው ያላችሁኝ ኣይደል ? "
.
"አዎ ጥብስ ነው "
.
"በዳቦ ነው በእንጀራ ? "
.
በጣም ይናደዱና ..
"በእንጀራ አርግልን "
.
አሁንም አላዘዘም ይሄድና ይመለሳል ...
"የሚጠጣ ነገርስ ምን ላምጣ ? "
.
ስልችት ይለውና ባልየው
"ለሷ ፋንታ ለኔ ኮካ "
.
"ይመጣላችዋላ ታድያ ምንድን ነው ግልምጫው "

አሁንም ይሄዳል ግን ሳያዝ ድጋሚ ተመልሶ ይመጣል...
"ለስላሳው ከውጭ ነው ከውስጥ ? "
.
እጅግ ይናደዱና...
"ተወው በቃ ባለቤቱን ብቻ ጥራልን !"
.
"ይጠራላችዋላ ባለቤት መጥራት ብርቅ ነው እንዴ ! "
አሁንም ይሄዳል ተመልሶ ይመጣል ...
"ባለቤቱ ወንዱን ነው ሴቷን??

@write_event
ለፈገግታ ያህል..!

ሙላ ናስሩዲን ሃጅ ወደሳውዲ ሄዶ ነው። ሰው ከመብዛቱ የተነሣ ናስሩዲን ማደሪያ ማግኘት አልቻለም፡፡ በመጨረሻ አንድ ሆቴል ውስጥ ጥንድ አልጋ ያለው እንድ ክፍል አግኝቶ ገባ። ብዙ ሳይቆይ ሁለተኛው አልጋ ተከራይቶ ሰውዬው መጣ። ናስሩዱን ሰውየውን ሲያየው ልክ እንደሱ ነበር የለበሰው። ቁርጥ እራሱን። መተኛት አልቻለም፡፡ ሰውየው ነቅቶ

“ወንድሜ፣ ለምን አትተኛም?” አለው።
“አንድ ችግር ገጥሞኝ ነው።”
“ምን?”
“እኔና አንተ ተመሳሳይ ነን። ተኝተን ስንነቃ እራሳችንን መለየት ቢያቅተንስ?” አለ ናስሩዲን። ሰውየው ለካ ተንኮልኛ ኖሯል። ዞር ዞር ሲል አንዲት አሻንጉሊት ጥግ ላይ ተቀምጣ ይመለከታል። ያነሳና እግሩ ላይ አስሮ...

“አሁን ተኛ፣ አሻንጉሊት እግሬ ላይ የታሰረው እኔ ነኝ ።” ይለዋል። ናስሩዲን ችግሩ ስለተፈታለት አመስግኖ ይተኛል፡፡ ሰውዬው በጠዋት ሲወጣ አሻንጉሊቱን ከእግሩ ላይ ፈቶ ናስሩዲን ላይ አስሮት ይሄዳል። ናስሩዲን ሲነቃ ደነገጠ። እየሮጠ ወደ አደባባይ በመውጣት እንዲህ አለ “አንድ ሰው ተሳስቶ እኔን ይዞ ሄዷል፡፡ እሱ እኔ ነውና የት ነው የማገኘው?” ...አለ ይባላል።

©አለማየሁ ገላጋይ

Join

@write_event
#ፈገግታ

#የለመደች_ጦጣ ...
አንድ ቀን ናስሩዲን አሀያዉን ጨው ጥርቅም አድርጎ ጭኖ ገበያ ወጣ ። በመንገዱ ላይ የነበርዉ ወንዝ ሞላ ብሎ ስላጋጠመው ሰፋ ያለ መልካ ፈልጎ
አሀያዉን እየጐተተ ለመሻገር ወንዝ ውስጥ ገባ ፡ ወንዙ መሐል እንደ ደረሰ ፡ አህያ ሆዬ አገሮቹን ወንዙ ውስጥ ተክሎ አልነቃነቅም አለ ፡ ናስሩዲን በመናደድ በያዘው ሽመል እሀያውን ይነርተዉ
ጀመር ፡ አሀያው ዱላ ሲበዛበት እየወደቀና አየተነግ ወንዙን ተሻገሩ ፡፡ ጨዉ ወንዙ ውስጥ ሟምቶ በመገባደዱ አሀያው ሸክሙ ስለቀለለው መንገዱን
በፍጥነት ማቀላጠፉን ተያያዘው ፡
በሌላ ጊዜ ናስሩዲን ያንኑ አህያ ጭኖ ገበያ ሲወጣ ከወንዙ ደረሰ ፡ ናስሩዲን አሀያዉን አየጐተተ ወንዙ ውስጥ ገባ ፡ መሐል እንደ ደረሱ እሀያው አሁንም ግትር ብሎ በመቆም ጭነቱን ወራጅ ውኃ
ያስመታ ጀመር ፡ በዚህ ጊዜ ናስሩዲን እሀያውን አልመታውም ፡ ለጥቂት ጊዜ አጠገቡ ዝም ብሎ
ከቆመ በኋላ መሳቢያውን ገመድ ጐተት ጐተት አደረገው ፡ አሀያወም እንደ ምንም ብሎ ወንዙን
ተሻገረ ፡ መንገዳቸውን ሊጀምሩ ሲሉ ከጭነቱ ክብደት የተነሣ የአሀያው ወገብ ተለምጦ መሬት ሊነካደረሰ ፡
ናስሩዲንም አሀያውን "የኛ ብልጥ ፡ ወንዝ
አቋርጠሀ ባለፍሀ ቊጥር እንደ ለመድከው የጭነትሀ ክብደት የሚቃለልልሀ መስሎሀ ነበር ፡ ዛሬ ጨው
ሳይሆን ጥጥ ነው የተጫንከው" አለው ፡
... #የለመደች_ጦጣ_ሁል_ጊዜ_ሸምጣጣ

@write_event
#ፈገግታ

#ነገር_በነገር_ይጠቀሳል ...

ናስሩዲን የሚኖርበት አገር ንጉሥ ባለሟሎቹን ስብስቦ ፡ ከአገሬው ሕዝብ መካከል በጨዋነቱ የሚታወቀ ሰው ተፈልጎ እንዲቀርብለትና የዳኝነት ሹመት ሊሰጠው እንዳሰበ ያስታውቃቸዋል ። የንጉሡን ትእዛዝ የሚያስፈጽም አንድ የመልእከተኞች ቡድን ይሠየምና በአገሩ ውስጥ እየተዘዋወረ መስፈርቱን የሚያሟላ ተስማሚ ሰው ለማግኘት ሥራወን ይጀራል፡ የንጉሡ ፍላጐት ወሬም ከናስሩዲን ጆሮ ይደርሳል ፡ ናስሩዲን ከሚኖርባት ከተማ ነዋሪዎች መካከል
የንጉሡ መልእክተኞች አንዳያነጋግሯቸው ከተመረጡት ሰዎች መካከል እርሱ አንዱ ይሆናል ፡ ናስሩዲን ፡ በተያዘለት ቀጠሮ፡ ከለበሰው ልብስ ላይ የዓሣ ማጥመጃ መረብ ደርቦ መልእከተኞቹ ፊት ይቀርባል ፡ በናስሩዲን አለባበስ የተገረመው የመልእከተኞች መሪ ፤ "እስከ ዛሬ በያለበት ስንዘዋወር እንዳንተ የለበሰ ሰው ፈጽሞ አላጋጠመንም ፡ በልብስሀ ላይ የዓሣ ማጥመጃ መረብ የደረብክበት ምክንያት ምንድን ነው?" በማለት ይጠይቀዋል ።
"ከሥር ክመሠረቴ ድሃ የድሃ ልጅ በመሆኔ ፤ መተዳደሪያዬም ዓሣ ማጥመድ ነበር ፡ ይሀንን መረብ ዘወትር በልብሴ ላይ የምደርበው ያነን የድሮ ኑሮዬን አንዳልዘነጋ በማለት ነው።" ሲል ናስሩዲን ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ይሰጣል ፡ መልአክተኛቹ ተልአኮአቸውን ፈጽመው ለንጉሡ ባቀረቡት ሪፖርት የናስሩዲን ስም ከሁሉ ጐልቶ ይታያል ።
ንጉሡም ስለ ናስሩዲን የቀረበወን ዘገባ በመቀበል የዳኝነቱን ሹመት ይሰጠዋል ፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ ፡ ምርጫውን ካካሄዱት ባለሥልጣኖች አንዱ ፡ ናስሩዲን በታላቅ ችሎት ላይ ተሠይሞ አቤቱታ ሲሰማ ፡ የፍርድ ብያኔ ሲሰጥ ፡ ለተበደለው ሲፈርድና በደለኛወን ሲቀጣ ያገኘዋል ፡ ከችሎት መልስ ፡ ናስሩዲንና ባለሥልጣኑ ጥቂት ሲጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ፡
"ያን መረብሀን ምነው ዛሬ አላየሁትም"
በማለት ይጠይቀዋል ።
ናስሩዲንም ፡ "የምን መረብ ነው ደግሞ፡ ዓሣው ከተያዘ በኋላ መረቡ ምን ይፌይዳል" በማለት ይመልሳል ፡

... #ነገር_በነገር_ይጠቀሳል_እሾህ_በእሾ_ይነቀላል

@write_event
እዛች ወንዝ ዳር
በትዝታ ህመም
በተፈጥሮ ስካር.. .
ስቀመጥ ስጫወት
አይኔ ሲንከራተት በሰንሰሉ ውበት
ኩልል ካለው ውሀ ስወረውር ድንጋይ
ለአይኖቼ ሳይታይ ...
ከዛ ማዶ ሆኖ ዋሽንት የሚነፋ
ዜመኛ ነበረ !
ነፍሴን ያከበረ ... ቀኔን ያሳመረ ።
እናፍቀው ነበር ... እኩል እንደ ወንዙ
እኩል እንደ ውሀው...
በዜማው ነበረ ... ዛሬዬን የሰፋው ።
ዛሬ ከጉብታው.. . አቆልቁዬ እያየሁ
አምናን እያሰብኩኝ አንጎራጉራለሁ
እንደ ትናንት ሁሉ ድንጋይ እነዝራለሁ።
ወፎቹ ዝማሬ ዛሬም አላቆሙም
ለግጦሽ የወጡት በጎች አልቦዘኑም
መስኩና ጠሀዩ ሁሉም ተሰንደው
የውበት ወስከንባ ለአይኔ አበጅተው
እያየሁ አዕዋፉን እያየሁ አፀዱን
ነፍሴ ትለኛለች አንተ የሰው ብኩን
"ከመቅደስ ዝማሬ.. . ከሰከነ ነፋስ
ነገህን ስትዋስ.. .
ማንን ሰምተህ ነበር የምታሳርፈኝ?
ምን አድምጠህ ነበር ከህመም ያከምከኝ?"
ብላ ስትጠይቀኝ.. .
ያን ጊዜ አሰብኩት ያንን ባለዋሽንት
ቦታው አልነበረም ...
...ጥዑም ዜማው የለም !
አልጠይቅ ነገር አላውቀው አላየው
ዝምም አልል ነገር ነፍሴ ስትናፍቀው
እንጃ አልኩኝ እኔንጃ እኔን እየዋሸሁ
ትናንት የነበረ ዛሬን አይገኝም
ይሄንን አውቃለሁ !
የናፍቆት ምላሹ.. እህህ ብቻ ነው።
እህህህ.. .
እህህህ.. .
...... ትዝታና ናፍቆት
እህህህ..
....እህህህ
....ህመምና ናፍቆት
ጣቴን መሬት ሰዶት
አነሳሁ እንደ አምና ... አንዲት ፍሬ ድንጋይ
ነዘርኳት አርቄ ...
መድረሻዋን እንጃ ... እኔ ምን አውቄ ?

(ሚካኤል.አ)
❤️

"ሁሉን ነገር ካስተዋሉት ይገርማል
የኑሮ ትንሽ የለውም. . .

እዛ የወደቀች ሳር አስገራሚ ናት፤ ወፍ ለቅሞ ጎጆ ይሰራባታል . . . .

ጠዋት እዚህ ፀሀይ ስሞቅ የቆረጥኩት የአውራ ጣቴ ጥፍር ለስንት ጉንዳን እራት ይሆናል? ባላርስም አበላሁ ማለት አይደል? "

/መረቅ - አዳም ረታ/

❀:✧๑♡๑✧❀|
         @write_event
         @write_event
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
"ይታዩኛል ብዙ ሰዎች
ዕራፊ አልባ፣ ልብስ የለሾች፤
ይታዩኛል ብዙ ልብሶች
በውስጣቸው የሉም ሰዎች።"

በሩሚ

@write_event
@write_event
. አምራች እና ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡
በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡ ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት ተስማሙ፡፡

በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነጋዴ የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሄዱን አየ፡፡ በመጨረሻም ሚዛን ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም፡፡ ገበሬውንም አስጠራው፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ ‹ከተስማማነው ውጭ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው?› ሲል ጠየቀው፡፡

ገበሬውም ‹እኔ ፈጽሞ አልቀነስኩትም› ሲል በአግራሞት መለሰ፡፡ ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው፡፡ 150 ግራም ነው፡፡ ገበሬውም አዘነ፡፡ ‹እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም መለኪያ የለኝም፡፡ አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሐን ላይ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ቅቤውን በሌላኛው ሚዛን አስቀምጠዋለሁ፡፡ ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ እልክልሃለሁ› አለው፡፡ ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው፡፡ ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው፡፡

@write_event
🍁.... ወጣነት ማለት ፉሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ ማለት አይደለም ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አንደለም።
"ወጣትነት ውቂያኖስ ነው" ወጣነት ማለት አድማሠ ሀላፊነት
ነው ... ወጣትነት እውቀት ለማስፉት የምንጋደልቀበት ሠአት ነው ወጣትነት
ከፍርሀት፣ አይቻልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ
ነው።ወጣትነትለ አንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው።

ከ ኤጭ መፅሀፍ የተቀነጨበ ( አዘርግ)

◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🍁ሙሉጌታ ተስፉዬ የተባለ ገጣሚ
ምን ይላል መሠላችሁ! አለም ላይ ስትኖር ሁለት እድል አላችሁ ወይ ራሣችሁን ችላችሁ መቆም አለበለዚያ መቃብራችሁን ቆፍራችሁ መግባት። ሌላ አማራጭ የላችሁም ይላል..... የአለም ቁጥር አንድ ጀግና ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ጀግና ማለት ጦር ሜዳ ብዙ ገድሎች የሰራ አይደለም። ሠው መግደል ጀግንነት ሣይሆን ሠይጣናዊት ነው። ጀግና ማለት ብዙ ብሮች ያሉት ሀብታም አይደለም ጀግና ማለት ጫካ ውስጥ የሠራውን ገድል ከተማ ውስጥ መጥቶ እየተኮፈሰ ይህን አደረኩኝ የሚል አይደለም!
ትልቅ እውነተኛ ጀግና አምባገነን መሪ ፊት አንዳችም ሣይፈራ እውነቱን የተናገረ እና ውስጡ ያለውን ስንፍና ያሸነፈ ብቻ ነው።

የቆሸሹ ሳቆች
(አዘርግ)


◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
እንደ ቶማስ በአይንህ ካላየህ በ እጅህ ካልዳሠሥክ አትረካም።
የትውልድ ሕመም ይህነው አንተንም የዚህ ሕመም ተጠቂ ትውልድ ምሣሌ ነህና ጫፉን ነግረንህ በዕምነት እንድትሆን ችላ ብንልህ ለማወቅ ትዳክራለህ። ያወቅከውን ደግሞ ትዘራዋለህ አንተ የትውልዱ ናሙና ነህ.. አንተ የተገዛከውን ገና ብዙዎች ይገዙታል ያወቅከውንና የደረስክበትንም መፃፍ ስለማይቀር ያንን ተከትለው ብዙዎች ይጓዛሉ። ግን ልብ በል! ብታገኙትም አታምኑም። እርሱ ራሱ ለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለ? ትላላችሁ አንተ በነገርካቸው መሠረት ሌሎች ካላመኑህ ደግሞ አንተም ዕምነትህ ይከዳሀል።


"ራሣችሁንና የራሣችሁን ዕውነት የምታረጋግጡት በምዕራቡ አለም መለኪያ ብቻ ነውና "

(እመጓ) በአለማየሁ ዋሴ ዶ/ር

• ◉ Join us share◉●••
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
ፍቅር እስከ መቃብር በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ
ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያን ፍቅርን
ይተርካል። ይህ ድርሰት ከሌሎች ልብወለድ ሥራዎች ለየት የሚያደርገው ደራሲው ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በፊደል አጠቃቀም ላይ ለውጥ አድርገው በማቅረባቸው ነው። ይኸውም
ለምሳሌ ያህል ሦስት «ሀ»ዎች፣ ሁለት «ሰ»ዎች፣ ሁለት «ኣ»ዎች የመሳሰሉትን
እንደ አንድ ወይም የመጀመሪያውን ብቻ በመያዝ ነው። በተጨማሪም ጠብቀው
በሚነገሩ ቃላት ላይ ከላይ አንድ ነጥብ በማስቀመጥ ይታወቃሉ። ሀዲስ ኣለማየሁ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሑፍ የራሳቸው ትልቅ አሻራ አኑረው ያለፉ አንጋፋ ደራሲ ናቸው።
• ◉ Join us share◉●••
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌

◌◉◎◦◈◦◎◉◌

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🌿ውስጣዊ ስሜቶች አይፃፉም፣ ቢፃፉ እንኳ ፍፃሜ የላቸውም። የአንዳንድ ነገሮች መሰባበር ሲሰማህ ትንሽ ራቅ በል። ንግግር ስሜትህን የመግለፅ አቅም ሲያጥረውም ትንሽ ዝም በል።

• ◉ Join us share◉●••
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
ከጥላቻ መንፈስ ፅዱ ሆነን እና በቅን መንፈስ ላይ ሆነን ስናየው እስልምና በራሱ እጅግ አስገራሚ የሆኑ ሰብአዊነትን የተላበሱ ህጎችን ተላብሶ እናገኘዋለን፡፡
...
በእስልምና ድሆችን ለመርዳት የሚሰጥ ማንኛውም እርዳታ "ምፅዋት" ወይም "ሰደቃ" ተብሎ ይጠራል፡፡ በእስልምና ህግ መሰረት "ደሀ ስለሆንኩ ሰውን መርዳት አልችልም" ብሎ ነገር በአላህ ፊት እንደ ምክንያት ማቅረብ አይቻልም... ምክንያቱም ሰውን ለመርዳት ሀብታም መሆን አይጠበቅብህም...
...
ይልቁንስ ብዙ አይነት ምፅዋቶች እንዳሉ እስልምና ያዛል... ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ፈገግታ ነው፡፡ አየህ መንገድ ላይ ነገ ስለምትበላው ቁራሽ ዳቦ እያሰብክ ስታዘግም "መሽናት ክልክል ነው" የሚል ፅሁፍ ከተፃፈበት ግንብ ስር ከአንተ የባሰ ምስኪን ተኮራምቶ ተኝቶ ታገኘዋለህ...
...
ታዲያ በእስልምና ህግ መሠረት ደሀ ነኝና ወይም ደግሞ በኪሴ ሰባራ ሳንቲም የለም ብለህ ሰውዬውን እያየህ ከንፈርህን እየመጠጥክ አታልፍም፡፡ ይልቁንስ አላህ በተፈጥሮ የሰጠህን ፈገግታ ለሰውዬው ትለግሰዋለህ፡፡
...
በቃ ይሄው ነው!!! ከጥርሶችህ ፍልቃቂ ውስጥ በሚወጣ ፈገግታ ካንተ ለባሰ ምስኪን ሰው የነገ ተስፈውን መፅውተኸው ጉዞህን ትቀጥላለህ... ፈገግታ ውስጥ ተስፋ አለ! ፈገግታ ውስጥ ፍቅር አለ! ፈገግታ ውስጥ ነገ አለ!
ሌላዉ መልካም ንግግር ነው የሞተን ተስፋ እንኳን እንኳን አፈሩን አራግፎ ሕይወት እንዲዘራ የማድረግ አቅም ያለው ነገር ነው!!

እስቲ ገንዘብ የለኝም ብለን ምናልፈቸውን ሰዎች አይዞን እንበላቸው ለኛ የአዕምሮ ዕረፍት ስናገኝ ለነሱ ደግሞ የመንፈስ ደስታ እንቸራቸዋለን!!!
መልካም ንግግር የነፍስ ምግብ ነው የልብ ፈገግታ ደግሞ የመንፈስ ዕረፍት የሌለንን እያሰብን ያለንን እየከለከልን እንደሆነ ልብ እንበል
ሰናይ ምሽት
• ◉ Join us share◉●••
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌

◌◉◎◦◈◦◎◉◌

"...ሰው ሲታመም የምንጠይቀው ከቋጠሮ ሰሐን ጋር ነው ... ሰው ( ሲታሰር ' እግዚአብሔር ያውጣህ' የምንለው ከፍትፍት አገልግል ጋር ነው ....አራስ የምትጠይቀው ከፔርሙዝ አጥሚት ጋር ነው ... የክርስትና አባታችን ለፋሲካ አክፋዩን የሚጠብቀው ድፎ ዳቦ ና አረቄ ነው ...እዝንተኛ የምናስተዛዝነው ሰባት እንጀራ ከአንድ ሰሐን ወጥ ጋር ነው ...ሟች የምንሸኘው ከገንቦ ጠላና ከለምለም እንጀራ ጋር ነው ...የቅዱሳንና የመልአክታት ተራዳኢነት የሚጎበኘን በስማቸው ከዘከርን ነው...ሰዕለታችን በሬ ወይም በግ ነው ...ሰርጋችን ፣ ልደታችን፣ እርቃችን፣ ሹመታችን፣ አምልኳችን፣ የሚበላ ነገርን ሙጥኝ ያሉ ናቸው።

...ሌላው ቀርቶ አንድ ሰው ተምሮ ሲመረቅ ይዘን የምንሄደለት ስጦታ ) ብዕር ወይንም መጽሐፍ አይደለም ፤ ኬክ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ... ነው :: - _ በሽተኛ ስትጠይቅ ከብርቱካንና ከሙዝ ይልቅ መጽሐፍ መውሰድ እንደማላገጥ ይቆጠራል ። ጊዜውን ይገፋበት ዘንድ መጽሐፍ ማበርከት በሽተኛው እንዳይድን ከመመኘት እኩል ነው ። _ ለኛ ለኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ከባዶ ገበታችን በስተዚያ የተቀመጡ ትርፍ ነገሮች ናቸው :: መጻሕፍት የሚያስፈልጉት ገበታችን ሞልቶ ከገነፈለ በኃላ ነው ብለን በይነናል። ገበታችንም አይሞላ ፤ መጻሕፍቱም አይነሱም ። ያልተረዳነው ቢኖር ለገበታ መትረፍረፍ ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ መጻሕፍት አቋራጭ መንገድ መሆናቸውን ነው ። እንዴት ታዲያ ማንበብ መብላትን ይቅደም ? መቼ ይሆን ከምንኮራባቸው ባህሎቻችን በላይ ማንበብ ባህላችን ሆኖ የምንታወቅበት ና የምንኮራበት?...."

አለማየሁ ገላጋይ


​​━━━━━✦🌺✦━━━━━

◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌


◌◉◎◦◈◦◎◉◌