ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ለሰው ዴንታ አይኑርህ አይባልም፡፡
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ስህተት ነው፡፡ የሰው ዋጋው በሰው ተለክቶ ነው፡፡ ማንም ሰው ለራሱ የመጠነውን ያህል ይኖራል፡፡ የልማድና ወግ መልክም ቀርጾ የሚኖር ስብስብ እንዲሁ ራሱን ያከብርበታል፡፡ ስለዚህ ለማንም ግዴለኝም እስከመሰለኝ በመሰለኝ እዋኛለሁ ብሎ መለቀቅ ከደመነብሰኝነት ማግስት የሚመጣ እክል እንዳይሆን ያስፈራል፡፡ የሰውነት ትርጉም የሚፈነጥቀው ከሰዎች ስብስብ ውስጥ ነው፡፡ ያደገንበት የኖርንበትና የምንኖርበት ከባቢ ሰውነትን የሚለካበትና የሚቀበልበት ዘየ አለው፡፡ የሚኖርበትና እንደማህበረሰብ የሚገለፅበት ብይን ነውና እሱን ካከበረ መጠይቅ መነሳት ለጥበብ መነሻ ነው፡፡

@write_event
"የኔልሰን ማንዴላ ..

☞ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው ። ስሙም ፒተር ይባላል ።

አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት
ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና ወፍ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" አላቸው ፣
ብልሁ ማንዴላም " አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ
እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ። በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል።

አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ ....
►"ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ ብር በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ ጥበብ ቢኖር በቅድሚያ የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ጠየቀው ፣
►ማንዴላም "ገንዘቡን አወስደዋለሁ" ብሎ መለሰለት ።
►ፕሮፌሰሩም በግልምጫ " አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ አወስድ ነበር" አለው፣
►ማንዴላ ፈገግ እያለ" ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው ።

በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል ። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ፣ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ " ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ፃፍልኝ"
"በማንም ላለመበለጥና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለማትረፍ ማስላት እያደረ ሰብዓዊ ፍቅርን ሊቀንስና ፈፅሞም ሊያጠፋ ይችላል። ይህ ባህር ስር ከሰደደ የስራ ሰዓትና የሰዎችን ሁኔታ ሳይለይ ቀ
በማንኛውም ጊዜ ከውስጥ ብቅ ብሎ ሊያፈጥ ይችላል። አንዳንዴም ይሉኝታና ምክንያታዊነትን ደምስሶ ሰዎችን ለጥቅም ብቻ የቆሙ አራዊት ያደርጋቸዋል። የሰው ፍቅር በፍቅረ ንዋይ ሲተካ ለማንም ለምንም ደንታ ያሳጣል።....


ያሳዝናል! ነጮቹን እንዲህ የሚያንጠባርራቸውና በበላይነት ስሜት የሚያስጋልባቸው የእኛ መጠጊያ ማጣት ነው። ሀገራችን መኩሪያ ና መመኪያ ልትሆነን አልቻለችም። በገዛ ሀገራችን ተዋርደንና ስራ አጥተን ከመኖር በስደት መኖርን መርጠን ነበር። ተሰድደን ስንኖር ደግሞ ፈረንጆቹ ይንቁናል። ...
ስለ እኛ ጥሩ ነገር መስማት አይፈልጉም። ምንጊዜም የሚያመሳስሉን ከችግር ከጦርነትና ከጉስቁልና ጋር ነው። ለዚህ አመለካከታቸው ደሞ እኛ ረድተናቸዋል። እርስ በእርሳችን እየተጣላን ሸሽተን እነርሱ ጉያ ስር እንሸጓጣለን፤ የምንዋጋበትን መሣሪያ እንዲሰጡን እንለምናቸዋለን ፤ ሳናጣ ያጣን ሆነን የልመና እጃችንን እንዘረጋላቸዋለን።

መፅሐፍ - የቅናት ዛር
ደራሲ - ሲሳይ ንጉሡ



join
@write_event
ቃላዊ pinned a photo
ቃላዊ pinned «ሙላ ናስሩዲን አንዲትን ሴት እያማከረ ነው .. " ባለትዳር ነሽ ?" አዎ " " ስንት ልጆች አሉሽ ?" " 12 " አስራ ሁለት ! ምን መሆንሽ ነው ? ይሄን ሁሉ ልጅ መወለድ ምን የሚሉት ጉድ ነው .... ያውም በዚህ ዘመን " " እንዴ ተው እንጂ እንደዚህ አትበል .... ባሌን እኮ በጣም ነው የምወደው .." አለች ሴትየዋ። " አይይ በዛ ... እንዴ እኔም እኮ ሲጋራዬን እወደዋለሁ ... ቢሆንም…»
ዳኛቸው ወርቁ ስብእናው ይገዝፍብኛል። ጓደኛ አያበዛም፤ ወዳጆቹ ጥቂት ናቸው። ለቁስ እምብዛም ግድ የለውም። መፃህፍቱ በሃሳብ የተሞረዱ፣ ቋንቋው በለዛ የደለበ ነው።

ዳኛቸው ስለ ባእድ ፍልስፍና እንዲህ ይላል፦

"የንጉሱን መገርሰስ ተከትሎ የሰፈነው ስርአት በአንድ ሌት ማህበረሰቡን በማርክስ እና ሌኒን መንፈስ አጥምቆ ህዝቡን እምነት አልባ ሀገሩን ሃይማኖት አልባ ለማድረግ ተነሳ። ማህበረሰቡ ለሺህ አመታት ጠብቆ የቆየውን እሴት በአንድ ፋታ ለመደምሰስ ጭምር ነው። ይህ አጓጉል አካሄድ ብዙዎችን ወደ ሞት በመሸኘት ተጠናቀቀ።"

ለውጥ የህይወት ቅመም ነው። ህይወት በማያቋርጥ የለውጥ ሂደት ውስጥ ናት። ነገር ግን አስተማማኝ ለውጥ ግዜ ይመስዳል። እንደ ችግኝ ተተክሎ እንደ ዋርካ የሚያድግ ነው።

ከሌሎች እየተዋሱ ባህልን፣ ቄንቋን፣ ፍልስፍናን ማጎልመስ ያሻል። ነገር ግን መቼም ቢሆን መሰረቱ የራሳችን መሆን አለበት። ስንዋስም ብልጭልጩን ሳይሆን እሴት ያለውን ሊሆን ይገባል።

ሃይማኖት፣ ባህል ለማህበረሰብ የሚጨምሩት ግዙፍ እሴቶች አሏቸው። ትክክል ወይም ስህተት መሆናቸው አይደለም ቁምነገሩ። ለመሆኑ ማን ትክክል እና ስህተት መዛኝ አደረገን?! የሚያምኑት በገባቸው ልክ ነው። የማያምኑትም እንደዛ። ሁላችንም ግራ የተጋባን የምድር ጎስቋሎች ነን።

ሁላችንም እኩል ባንሆንም፣ ከመሀከላችን የበላይ ወይም የበታች የለም። ሁሉም በገባው መጠን በምድር ይመላለሳል። በዚህ አጭር ከንቱ ኑሮ ሁለት ነገሮች እርግጥ ናቸው—ፍቅር እና ሞት። በፍቅር እየኖርን አንዴ ብቻ እንሙት።በቁም ከመሞት የከፋ ነገር የለም። ፍቅር አልባ ህይወት በቁም ደጋግሞ መሞት ነው።

@write_event
ሙሉ ደስታ..!

ለሰዎች ብለህ ማስመሰሉ እኮ ነው ደስታህን የነሳህ! "ደስታ ማለት የምታስበው ከምትናገረውና ከምታደርገው ጋር አንድ ላይ ሲዋሀዱ ነው" ይለናል ማህተመ ጋንዲ።

ብቻህን ደስተኛ ካሎንክ ይመስልሀል እንጂ በሰዎች ብትከበብም ሙሉ ደስታ አይኖርህም፤ ሁልጊዜም ውስጥህ የሚነግርህን ህሊናህ የሚያዝህን አድርግ!

©Inspire Ethiopia | @write_event
ጓደኛ ማለት...!

1. እንደፈለክ በነፃነት የምትሰድበው
2. በጣም ጨንቆህ ስታማክረው እሱ የሚቀልድብህ
3. በጣም አስከፍቶህ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ በድጋሜ የሚሰድብህ ??

እንደዚህ አይነት ጓደኛ ካለህ.. እድለኛ ነህ💜

@write_event
ትንሽ ደሞ ፈገግ
አንዱ አይን አውጣ የእጮኛው ቤት  ይሄድና አባቷን አስጠርቶ

ጎረምሳው: -"ልጅዎን ለማግባት ነው"
.
.
አባት: - ልጄን ለጋብቻ ልትጠይቅ መጥተህ በአጠገቤ ማስቲካ ታኝካለህ ትንሽ እንኳን አታፍርም ? ክብረቢስ
.
ጎረምሳው: -"ይቅርታ ጌታዬ ስለጠጣው አፌ እንዳይሸት ብዬ ነው"
.
.
አባት: -"ጭራሽ መጠጥም ትጠጣለህ?"
.
ጎረምሳው: Read more ..
አንዳንድ አስገራሚ እውነታዎች
━━━━━✦━━━━━

• አብርሃም ሊንከን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆኑ በፊት የአገሩ የነፃ ትግል ሻምፒዮና ነበር፡፡ በ300 ገደማ የነፃ ትግል ግጥሚያዎች ላይ ተሳትፎ በአንዱ ብቻ ነው የተሸነፈው።

• ዝነኛው ሙዚቀኛ ኤልቪስ ፕሪስሊ 8ኛ ክፍል ሳለ፣ በሙዚቃ ትምህርት ዝቅተኛ ውጤት “C” ነበር ያገኘው።

• እ.ኤ.አ. በ1930 በሚያዝያ ወር አንደኛው ቀን ላይ ቢቢሲ ‹‹ዜና የለም›› ሲል አስታውቆ ነበር። በምትኩም የፒያኖ ሙዚቃ ለቋል።

• ፈረንሳይኛ፤ ከ600 ዓመታት በላይ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል።

• በ16ኛውና በ17ኛው ክ/ዘመን፣ ቱርክ ውስጥ ቡና ሲጠጣ የተያዘ ማንኛውም ሰው ለሞት ይዳረግ ነበር።

• የዛሬ 3ሺ ዓመት ገደማ፣ አብዛኞቹ ግብፃውያን የሚሞቱት በ30 ዓመት ዕድሜያቸው ነበር።

• ኮካኮላ መጀመሪያ ላይ ሲፈጠር ቀለሙ አረንጓዴ ነበር።

• በዓለም ላይ ከአምስት ሰዎች አንዱ (1.1 ቢሊዮን ሕዝብ) የቀን ገቢው ከ1 ዶላር በታች ነው።

• ገና የተወለዱ ሕጻናት ቢያንስ አንድ ወር እስኪሆናቸው ድረስ እንባ አያነቡም።

• አንድ የ4 ዓመት ሕጻን፣ በቀን በአማካይ ከ400 በላይ ጥያቄዎችን ይጠይቃል።

• ዝሆኖች መዝለል የማይችሉ ብቸኛ እንስሳት ናቸው።

• አንዳንድ ድመቶች ለሰዎች አለርጂክ ናቸው።

• ማር የማይበላሽ ብቸኛው ምግብ ነው። 3 ሺ ዓመት ያስቆጠረ ማር ያለችግር ሊበላ ይችላል።

• እንደ ጣት አሻራ ሁሉ፣ የእያንዳንዱ ሰው የምላስ አሻራ የተለያየ ነው።

━━━━━━━━
📰 አዲስ አድማስ
Saturday, 16 November 2019
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/write_event
እኔና አንቺ
(ሜሪ ፈለቀ)

“አንተ ሴሰኛ አይደለህም፡፡”  ትዪኛለሽ። ሴሰኝነት ‘ስሜ’ መሆኑን አንቺም፣ እኔም፣ ከጎኔ የሚሻጡት ሴቶችም፣ እኔን የሚያውቁኝም ሁሉ እናውቃለን፡፡

ለራሴ ‘ያለማወቅሽን እና የዋህነትሽን’ ነገርኩት፡፡ ላንቺ ግን ዓይኖቼንም ልቤንም የጠለፈውን ህልም የመሰለ ውበት ያለው አካልሽን እያየሁ ጥርሴን ለመግለጥ ከንፈሬን አሸሸሁልሽ …….. ሚስጥር አዘል ወጋገን ያለው ፈገግታሽን መለስሽልኝ፡፡

“አንተ የእኔ በመሆንህ እድለኛ ነኝ::” አልሽኝ የሳምኩሽ እለት…….. በልቤ ሳቅኩብሽ…..  በጥርሴ ሳቅኩልሽ …..

“አንተ ከንቱ ሱሰኛ አይደለህም::”  አልሽኝ አስረኛ ሲጋራዬን እየተቀበልሽኝ ……. የሙሉ ጊዜ ስራዬ ሱስ መሆኑን ካንቺ በላይ የሚያውቅ አልነበረምና ግራ አጋባሽኝ፡፡

“አንተ እኮ ታታሪ ሰራተኛ ነህ፡፡ እንደማውቃቸው ሰዎች ሰነፍ አይደለህም፡፡ ለምን ስራ አትሰራም?”  ያልሽኝ ቀን
‘ትፎግራለች እንዴ?’ አልኩኝ ለራሴ …… በአንድ ዓይነት የትምህርት ዘርፍ ተመርቀን አንቺ ቤተሰብሽን ስታስተዳድሪ እኔ ቤተሰቤን ሳሳርር ዓመት እንዳለፈን ካንቺ በላይ እማኝ የለኝም፡፡

ከቋመጥኩለት ገላሽ ጋር መውደቅ አጓግቶኝ እንዳንቺ የወደድኳት ሴት ያለመኖሯን ምዬ ተገዝቼ  ስነግርሽ

“አምንሃለሁ፡፡ እኔን የምትዋሽበት ምክንያት አይኖርህም!!” ብለሽ ውሸታምነቴን አገዘፍሽብኝ፡፡

ማንም ወንድ ያልዘለቀው ገላሽን ስዘልቀው ………………. እድለኛነቴን ሳይሆን ‘ስላፈቀርሽኝ ራስሽን አሳልፈሽ በመስጠትሽ’ እድለኛነትሽን ነገርሽኝ እና ከደስታዬ ይልቅ ራስምታቴን አበዛሽው ………….

አብሬሽ ሆኜ ከሌሎች ብዙዎች ጋር አብሬያቸው መሆኔን ታውቂያለሻ !……….. ለቁጥር የሚታክቱ ጊዚያት ብልግናዬን ደርሰሽበታላ !……… ለተገለጠ ስድነቴ ብዙ ሰበብ ስደረድርልሽ

“ምክንያትህ አንተን ካሳመነህ ለኔ አትንገረኝ::”  ብለሽ ምንም ያልበደልኩሽ ያህል ከረሳሽው ቀናቶች ብቻ ናቸዋ ያለፉት!!

አንቺ በህይወቴ  እስከተከሰትሽበት ጊዜ ድረስ ሴት ልጅ …………. ልብ፣ ነፍስ፣ አዕምሮ፣ ስሜት ……..( ከሚታየው የሰውነት ክፍሏ ውጪ ያሉት የ’ሰው’ነት መለኪያ) አብሯት ስለመኖሩ አስቤ አላውቅም፡፡ የሴት ፍቺው - እኔጋ የሌለው የሴትነት አካሏ ነበር፡፡ …..  

የተናገርኳቸው ቃላትም ሆነ ያደረግኩት ድርጊት ሁሉ  የተለመደ ……. ቁጥራቸውን ለማላስታውሳቸው ሴቶች ሁሉ ያልኩትና ያደረግኩትን  ነበር፡፡

ከመቼ ወዲህ ነው የሴት ልጅ ነፍስ ይናፍቀኝ የጀመረው? መቼ ላይ ነው የሴት ልጅ ከንፈር ከመሳም አልፎ የሚያፈልቀው ቃል ይርበኝ የጀመረው?  …… ለስንተኛ ጊዜ አካልሽኝ ከተዋሃድኩት በኋላ ነበር ነፍስሽን የተዋሃድኳት?………..……… በሆነ በኔና ባንቺ ቀናት ውስጥ በአንዱ ቀን ወይም በሁሉም ቀን ነበር እንደዛ የተሰማኝ፡፡

መቼ ነው አንቺ ነህ የምትዪኝን እኔነቴን እየወደድኩት፣ የሆንኩት ራሴ እያስጠላኝ የመጣው? የትኛው ቀን ላይ ነው አንቺን ለማማለል ሳይሆን ትክክለኛ ስሜቴን ማውራት የጀመርኩት? ምን ካልሽኝ በኋላ ነው ራሴን ማረም እና ንግግሬን መቀባባት፣ ድርጊቴን መደበቅ ሳያስፈልገኝ ራሴን አሳይሽ የጀመርኩት? …….. የትኛው ቀን ላይ አንቺ ነህ ያልሽውን ሰው ለመሆን መወሰኔን አላውቅም፡፡ ከራሴ መማከሬም ትዝ አይለኝም፡፡

ብቻ…………… እግሮቼ ስራ ፍለጋ ሲኳትኑ፣ እጆቼ ሱሳቸውን ላለመከወን ሲታገሉ፣ ምላሴ ላለመዋሸት ከህሊናዬ ጋር ሲጣላ፣ ከሌላ ሴት ተኝቼ ይሰማኝ የነበረው ደስታ በበዛ ፀፀት ሲተካ………… ራሴን በቃልሽ ሳበረታ አገኘሁት፡፡

ክንዴ ሌላ ሴት አንተርሶ ሳለ ደወልሽልኝ፡፡ ‘የት መሆኔን’ ስትጠይቂኝ ለመዋሸትም ያለሁበትን ለመንገርም ቃል ከከንፈሬ አልወጣ አለኝ፡፡ ……

“ መጣሁ ህይወቴ የት ነሽ?”  ነበር ያልኩሽ ……

በስምሽ የጠራሁሽ ልቤ ውስጥ መከመርሽን የሚያሳንሱብኝን ቃላት ላለመጠቀም ነበር፡፡ …….ማሬ፣ ፍቅሬ፣ እናቴ ፣ውዴ…… ሁሉንም ቁልምጫዎች ለሌላ ሴት ብያቸዋለሁ …………….

“ስትጨርሽ ደውልልኝ!!”  ማለትሽ ለቸኮለች ነፍሴ አልገባትም፡፡

“ መጣሁ!!”  ስልሽም በአካሌ ብቻ አልነበረም ….. በሁለንተናዬ እንጂ

“ከኔ ጋር ሆነህ ሌላ ሴት ትቀጥራለህ? ….. ስድ ነህ!!!” ብላ እንደብራቅ ጮኸችብኝ ካንቺ ጋር ሳወራ ነፍሴ መሳቋ የገባት ሴት …..

“ከዛሬ በኋላ ስድ አልሆንም!!” ብዬ የመለስኩላት እውነቴን ነበር፡፡ ……

ካንቺ ውጪ ለመጨረሻ ጊዜ የተኛኋት ሴት መሆኗን ለራሴም እያረጋገጥኩለት ነበር፡፡ ……. ልቤም እግሬም አንቺጋ ለመድረስ ተጣድፈው ሸሚዜን እየቆላለፍኩ የሆቴሉን ክፍል ለቅቄ ስወጣ ነበር ሩቅ በማይባል ቦታ ተቀምጠሸ  ያየሁሽ ………… ካልሺኝ ሁሉ በጉልህ የሰማሁት ንግግርሽ

“መቼም የማትሻሻል ሴሰኛ ነህ!!”  የሚለውን ነው፡፡

ላስረዳሽ አልሞክርም፡፡ አንቺ ነህ ካልሺኝ በላይ የትኛውን መሆኔን ራሴም እርግጠኛ መሆን አልቻልኩማ ………

join
   ★ ★ @write_event   ★  ★
አይዞህ ልቤ

ድንገት ቢከፋ ባይቀና ኑሮ በዚች አለም
ጊዜ የማይፈታው ምንም የለም

ጊዜም አሁን ነው ትላንት ሆኖ ቀሪ
የነገን ቀን ሰሪ

አመት ያህላል ቀን እየዞረ
ዛሬም እራሱ ነገ ነበረ
የጊዜ ሚዛን አይላወስም
#ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም

ሳዝን አልውልም ሳላቅ ማደሬን
የኔነው በቃ አልሰጥም #ዛሬን

ቴዲ አፍሮ
Read more

share
@write_event