ቃላዊ
342 subscribers
38 photos
6 videos
1 file
122 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
'ቀለም ና ቃል'
.
.
.
ገላዬ ለቀለም
ቀለም እኮ ነበረ
ከደም የተቀዳ
በቅብ የሰፈረ
ቃልዬ ቃልማ እኮ
በቃል ቃል ነበረ
እውነትን ሰባኪው
በቅኔው የኖረ
* * *
መች አጣነው ቃልን -- ከቃላቶች ጉያ
መቼ ጠፋ ቀለም -- ከሰው አምሳያ
'ቃል ና ቀለም' አሉ -- ከስሜቶች ቋያ
ውሃ ብንከልሰውም -- የንዳዱን መዋያ
* * *
ያሻው --- ቀለሙን
ያሻው --- ቃሉን

ብቻ ምን አለፋን --- ከፋፍለው ይመርጣሉ
ያሻቸውን ነቅለው --- ነጣጥለው ይወስዳሉ

ነው እንጂ ቃልዬ --- ቃልማ እኮ አለ
ገላ ታውቅያለሽ --- ቀለምም እንዳለ
* * *
አካል እንዳልሆነ
ብቻውን ሰውነት
ቃል እንደሆነ
ለሰው ዘውድነት
እኛ ካላወቅን
የቃልን ክቡድነት
ቃል ቀለም ምንም ነው
ያለ ህልውና ውህደት
* * *
ቀለምማ ደም ነው --- ቃል ደሞ መንፈስ
አሀዱ የነበር --- ህልውናን የምያድስ
* * *

ቃልኪዳን የአዮ ልጅ
01/03/2013 ዓ.ም
አርባምንጭ, ኢትዮጵያ
ከተባሉት ነገር --- አንድት ፍሬ ሳይረዱ
በልቤ ሙሉነት --- በደፈና ስፈርዱ
ለሰምው ተረት ነው --- የተረት ተረት
የማይሉት ቀርበው --- እቴ የመሰረት
2/3/13
IHMIS CLASS
◎ ኢትዮጵያዊነት 💚💛❤️!

ኢትዮጵያዊ...
የልቡ ባለሟል ህብረ ሰሚያዊ
ኢትዮጵያዊ....
ባመነው የሚያድር ክሱተ ህላዊ
ኢትዮጵያዊ....
እንደ ኩል የጠራ ፍፁም ሰላማዊ
ኢትዮጵያዊነት 💚!
አዛኝ እንደናቷ... ቆራጥ እንደ ዳዊት
ኢትዮጵያዊነት 💚!
ያገር አሳላፊ ... እንደንብ ሰራዊት
ኢትዮጵያዊነት 💚!
የመስኖ ዳር ፍሬ ጥዕሙ እንደ ሸዊት

ኢትዮጵያ.... 💛!
የአዳም ሞሰበ ወርቅ የግብር ማቅረቢያ
ኢትዮጵያ...💛!
የስብዕና ክብር ድርሳን መዘገቢያ
ኢትዮጵያ... 💛!
የተስፍ ጎህ ፀዳል የምስራቅ በር አጥቢያ
አንኪያስ.... !
ምንድነው ኢትዮጵያዊነት!

ኢትዮጵያዊነት💚💛❤️

ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
እልህ አለበት ሴራ ባያስቋጥር ለበቀል
በውህደት በህብረት እስከሚንቀለቀል
ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ደራ አለበት የጋለ ማረሻ የማያስውጥ
እንኳን እምነት ማተብ ቃል የማያስለውጥ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... !
ተስፍ አለበት የሩቁን አቅርቦ እሚያሳይ
ያንጀት የማጀቱን የሗላውን መሳይ
ኢትዮጵያዊነት....💚💛
◎ አንድም - በዕምነት 💚!
◎ አንድም - በዕውነት 💛!
◎ አንድም - በሰውነት !
◎ ኢትዮጵያዊነት ለኔ.......
አይኔ.. ብይኔ.. ሰባስቶፖል!

ኢትዮጵያዊነት 💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ዕዳ አለበት ያስራት መክሊቱ እየጎደለ
እንደ ቸርነቱ እሱ ያውቃል እሱ እየታደለ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ይሉኝታ አለበት ከሰው አፍ ላለመግባት
ለርኩስ ከሳሽ መንፈስ ቢያጣለት እልባት
◎ ኢትዮጵያዊነት... !
ፈውስ አለበት የስም ስብራት የሚጠግን
ምን ምላሽ ባይኖረው ምን ባያስመሰግን

ኢትዮጵያዊነት 💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
አርምሞ አለበት ግብ ግብ ከራስ ጋር ፋልሚያ
አደብ በከንፈሬ እድሜ ማራዘሚያ
ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ውል አለበት ለልቡ የገባው ቃል
ስፍርና ሚዛኑን ያስታጠቀው ያውቃል
ኢትዮጵያዊነት.... !
ብሂል አለበት የእልፍ ዘመናት ትውፊት
ምንግዜም ንቅደሚት ምንግዜም ወደ ፊት

ኢትዮጵያዊነት 💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ፀፀት አለበት እንደግር እሳት የሚያቃጥል
ትላንትን በነገ በዛሬ ሊቀጥል
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
እድር አለበት እንደ ሸረሪት ድር የሚስተሳስር
መርዶ የሚለፍፍ ንጋት የሚያበስር
◎ ኢትዮጵያዊነት.... !
ዘብ አለበት ለዛው ቀጥ እንደ ሰንደቅ
ግዳጁን ተወጥቶ መብቱን ሊያጠድቅ

ኢትዮጵያዊነት💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ጉዞ አለበት ቢሄዱት የማይዘለቅ
መልኩ የማይለወጥ ቀለሙ የማያልቅ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ጌጥ አለበት እንደ ቶጳዝዬን ፈርጥ
በጥበብ ይደምቃል ክፉ ደጉን ሳይመርጥ
ኢትዮጵያዊነት....!
ፀጋ አለበት ከፈጠረው የሚገናኝ ዘለበት
በናቱ ፈገግታ እሶን ባዘለበት
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ሞገስ አለበ በሰማዕት ገድል የደመቀ
እንዳአምባ ገሞራ የታመቀ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ፍቅር አለበት መቸም መቸ ነዶ የማያልቅ
በትህትና አጅቦ በሰላም የሚያዘልቅ
◎ ኢትዮጵያዊነት....!
ትንሳዔ አለበት የብሄረ ህያዋን ናፍቆት
ከእውነተኛው አገር ተገልጦ አሳውቆት

ኢትዮጵያዊነት💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ጫጉላ አለበት ከሰርግ ከምላሽ ጠብቆ
ወዶ ለፈወደው ሊያስተናግድ ታጥቆ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ጽናት አለበት በቀኝ በግራ የተፈተነ
እንኳንስ የቀልብ የእጅ ያልሰባተነ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... !
ዝማሬ አለበት ከፀጥታ ዜማ ቅኝት ጠልፎ
አሻግሮ እሚያሰግር ከቀዳበት አለሰፎ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ገና ብዙ አለበት. ብዙ ገና ብዙ አለበት
እንደአስተዳደሩ. ቀን እንደዋለበት

ሙሉጌታ ተስፍየ (አያ ሙሌ) የልቤ ሰው

t.me/Write_Event
በአረንጓዴ ቢጫ ~ በቀይ
የተዋበች
እምዬ ኢትዮጵያ ~ ጥበብ
ትመስላለች

ከሰሜን ተወልዳ ~ ጥጥ ፈታይ
እናቴ፣
ከደቡብ ጫፍ መጥቶ ~ ሸማኔው
አባቴ፣
ከምስራቅ ሲያስውበው ~
ስፌቱን አጎቴ፣
ከምዕራብ ተገኝቶ ~ ጥለት ሰሪ
አያቴ፣
መሃል አገር ሆና ~ ቋጨችው
አክስቴ፤
.
እንዲህ በአንድ አብረው ~
የሰሩትን ጥበብ
ቀላል ይሆናል ወይ?
እህት ወንድሞቼ ልነጥልህ ቢሉት
~ በሰበባ ሰበብ።
.
አይገርማችሁም ወይ?
ላጨልምህ ሲሉት
የአገራችን አርማ~ በሰማይ
ደመቀ
በአራቱም ማዕዘን
በሦስቱ ቀለማት ~ ምድር
ተጨነቀ ።

©ሜሮን ጌትነት

የተመቻችሁ 👍
ያልtመቻችሁ comment

ከ ሁለት አንዱን ተጠቀሙ ዝም ብሎ ማለፍ ያስቀጣል 😂
Join
•═════•••🍃🌺🍃•••═════•
🙏🙏 #Please_share 🙏🙏
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
""""ፍቅር ና በቀል""



ክፍል 1

ሁለት ልጆች ላስተዋውቃቹ ...ሀና እና ኪሩቤል በሰፈር ስሙ (ሳንቾ )

ሀና ለቤተሰቦቿ ሶስተኛ ልጅ ናት የመጀመሪያ ውንድሞ አግብቶ አንድ ልጅ የውለድ ነው። ሁለተናው ብዙ አይበላለጡም አንድ እድሜ ክልል ውስጥ ነው ያሉት እድሜዋ 22 ውስጥ ነው። ቤተሰቦቿ ሀብታም ከሚባሉት ውስጥ ይመደባሉ ። እቤት ውስጥ ሀናን እንደቁላል ነው የሚመለከቶት ምን ነገር ብትል ይደረግላታል ።

በትምህርቶ አሉ ከሚባሉት ትመደብ ነበር ነገር ግን የዩኒቨርሲቲ ውጤት መቶላት እቢ አልማርም በግል የነርሲንግ ድፓርትመንት መማር ጀምራለች ።
በረፍት ጊዜዋ የሙዚቃ እና ዳንስ ታዘውትራለች ቤተሰቦቿም ፍላጎታን ላለመጋፋት በዛ ላይ እንድትከፋ ስለማይፈልጉ ያለችውን ሁላ በእሽታ ነው የሚመሱሰላት ። ከታላቅ ውንድሞ ጋር በጣም ሚስጥረኞች ናቸው። በጣም ነው የሚዋደድት ።ምን የሚደባበኩት ነገር የለም እሱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እንጂነሪንግ ተማሪ ነው። በቀጣይ ይመረቃል ።.

ትግስት ፣ ሜሮን ና ኮከቤ ጎደኞቾ ናቸው። ከአንድኛ እስከ 12 ክፍል አንድ ላይ ነው የተማሩት አንድም ቀን ሳይጣሉ በመካከላቸው የሚደባበቁት ነገር የለም። እና እናሱ እንደድል ሆኖ ውጤት አልመጣላቸውም ከዛ ነርሲግ በግላቸው እንማራለን ስላሉ ሀናም አልለያቸውም ብላ ነው የግቢው ውጤት እቢ ብላ እኩል የሆነችው ለእነሱ የተለየ ፍቅር እና ልዬ ቦታ አላት። በርግጥ በጣም ከጓደኞቿየሚያስቀኑ አንዳንቸው ላንዳቸው የሚተሳሰብ እና የሚያስቀኑ ናቸው ።
ትግስት ቀይ ብዙም ማውራት የማትውድ እረጋ ያለች ቆንጆ የምትባል ነው ። ሜሮን ከሁሉም ተስማሚ ናት ካበደው ጋር የምታብድ ከዝምተኛው እንደዛው። ኮከቤ ቀልቃላ እና ችኩል ግን በአፎ ብትናገርም ሆዶውስጥ ምን የሌለ የዋህ ፀይም ናት። በርግጥ ሀናም ትንሽ የመንቀልቀል እና የመቅበጥ ባህሪ አለባት ።

ከትምህርት እንደውጡ ውደ ሙዚቃ ዳንስ....የሚለማመድበት ያመራሉ እንደጨረሱ። ውደ ቤት ለመሄድ ሰዓቱ ስለመሸ ይርበተበታሉ። ድንገት የሀና ስልክ ጠራ "እየተነጫነጨች ስልኳን ስታየው የማታቀው ስል ነው። ላንሳው አላንሳው እያለች ማመንታት
"ሀኒ ስልኩን አንሺው ምነው?የማታቂው ነው? ትግስት ነበረች።
"አዎ ቁጥር ነው ግን ላንሳው ውድሜ ይሆናል ስላመሸው ብላ ስልኩን አንስታ
""ሄሎ ሄሎ ...ማን ልበል .....እይልለች ድምፆን ቀዝቀዝ አደረገችው:"
""ሀኒዬ እንዴት ነሽልኝ ?
ሀና ግራ በመጋባይ ...
"ይመስገነው ማን ልበል ይቅርታ አላውኩህም .....
""እንዴ አንቺ ቢጠፋ ቢጠፋ የኔ ድምፅ ይጠፋሻል ትገርሚያለሽ ..ሀና ግርማ አይደለሽ ?
ስልኩን ላውድ ላይ አድርጋውም ይቅርታ እኔ ሀና ጌታሁን እባላለው ተሳስተካል ""
""ኦ sorry...ብሎ ስልኩን ዘጋው ...
የሀና ጓደኞቾ ይሄ የዞረበት እያሉ መሳሳቅ ጀመሩ። ሀና በሀሳብ ተውጣለች ....

ስልክ የደውለው ኪሩቤል ነበር።
ኪሩቤል (ሳንቾ)ለቤተሰቦቹ አረተኛ ልጅ ነው የመጨረሻ አንድ ሴት እህትና ሁለት ውንድሞች አሉት። ከካናዳ የመጣው በሶስት ቀን በፊት ነው። ሁለቱ ውንድሞቹ እዛ ነበሩ። ውደዛ የሄደው እህቱና እናቱ ከሞቱ በኃላ አባቱና እሱ ውደ ካናዳ ሄድ። የመጣው የልጅነት ጓደኛው ጋር ነው ያረፈው። በርግጥ እሱ ተሳስቶ አልደውለም ለማውናበድ እንጂ ስልኩን ከዘጋው በኃላ ጎደኛው አማን ማን ጋር እንደደውለ ሲጠይቀው አይ ዝብዬ ቁጥር ስሞክር ነው አላቃትም ብሎ መለሰለት ።

"ሀና እቤት ስገባ ሁሉም እራት እየበሉ ነበር sorስላመሸው ማም ዳድ ብላ ግንባራቸውን ስማ እጆን ልትታጠብ ገባች። ውስጦ ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶታል ፉቶ ላይ ደስታ ይነበብ ነበር። ቤተሰቦቿ ግራ ቢጋብም ደስታዋን ውደውላታል ።
""ሀኒዬ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንዲ መፍለቅለቅ" እናቷ ነበሩ።.
"ምን እንዲሁ ነው መደሰት አይቻልም ....
"አረ ከፈለግሽ ጨፍሪ ማን ከለከለሽ
ብሎ መለሳላት ያቤት ምግብ ሰዓት ባጠቃላይ አንድ ላይ ሲሆኑ ጨዋታቸው አይጠገብም ።..ልክ እንደጨረሱ ...ሀና ክፍሎ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍታ አሻንጉሊት አቅፋ ተመስጣ ታደምጥ ጀመር። ድንገት የሙዚቃው መቆም እያበሳጫት የጨፈነችውን አይን ገለጥ ስታደርግ .....

ይቀጥላል!!

እንዲቀጥል ለወዳጆች Share ያድርጉ

share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
@kaliye06
''ፍቅር እና በቀል '' የተሰኘ ተከታታይ ታርክ መጀመራችን ይታወሳል ይሁን እንጅ ተቆርጦ ነበር ።
አሁን መጀመራችንን በይፋ እንገልፃለን ።
ታድያስ አንድ ሰው 3ሰውን በመጋበዝ እየሰፈን ታርኩን ከዛሬ ጀምሮ እንቀጥላለን ።
share and join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
""""ፍቅር ና በቀል""""
ሀዊ ጌታቸው (ሂዊ የጌቾ)
ክፍል 2
.
.
የጨፈነችውን አይኖን ገለጥ ስታደርግ እስራዬል ውንድሞ ነው ። ኡፍፍፍፍ ኢሱ ለም ዘጋከው ብላ እዛው ውደተኛችበት ተመለሰች..
"ወደ አልጋዋ እየተጠጋ ዛሬማ የሆነ ነገር ሆነሻል እእእ ምን ተገኘ እያላት ያቀፈችውን አሻንጉሊት ተቀበላት"። ።.".እንደመሳቅ እያለች ኢሱ ታውቃለክ omg ብላ ትራሱን አንስታ ፊቶ ላይ ሸፈነችው""
"እንዴ ምን ተናገሪ ከኔ የሚደበቅ የለም ፍቅር ነው አይደል እያለ ውደ እሱ አስጠግቶ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጦ እግሮቹ ላይ አስተኝቶት በይ እንዲ እያየሽ አዋሪኝ ።..ከሀ እስከ ፐ ...

"ወይ ከሀ እስከ ፐ ውዶ አይስኩ አሉ ጎረቤታችን ....ምን መሰለክ የሆነ ልጅ ተሳስቶ ደውለ ስልኬ ላይ ግን ኢሲዬ ያቺ ቅፅፈት ለምን የተለየ ስሜት እንደተሳማኝ ስልኩ ከተዘጋ በኃላ "ሀኒዬ እንዴት ነሽልኝ""ያላት ቃላት ውስጤ ውስጥ ይመላለስብኛል።
""እና መጨረሻው ምን ሆነ ?እንዴት ሀኒዬ አለሽ?
"ሀና ግርማ አይደለሽ ሲለኝ አይደለሁም ....ኦ sorry ብሎ ስልኩን ጥርቅም ..ይሄን ቃላት ስትናግረው በመናደድ ስሜት ነበር ።.
እስራዬል በሁኔታዋ መሳቅ ጀመረ። አያስቅም በትራስ እንደመምታት እያለች
እረ በደንብ ነው የሚያስቀው። እኔምልሽ
ቲጂ ጓደኛሽ ሰላም ናት?
"ከተኛችበት ተነስታ ምን ቲጂ ነው ያልከቅ አንተ ምነው እሷን ብቻ ጠየከኝ ለዛም አቆላምጠክ ...
"ከናንተ ውስጥ እሷ ናት ደና ሰው ብዬ ነዋ እንዳለ ወፈፌ ብቻ ነው።.. በዛ ላይ...
"ከት ብላ ስቃ በዛ ላይ ፍቅር ይዞኛል ልትል ባልሆነ !
""እንደመኮሳተር ብሎ ብልስ እኔ ውንድምሽ ለሷ አንሳለው ,?
" ከምርክ ከሆነ ደስ ይላል ቲጂዬ ምርጥ ናት ትበዛብሀለች እየሳቀች ።..
"ስልክ ተደውሎለት በይ ደና ደሪ ብሎ ከክፍሉ እንደውጣ ሀና በጀርባዋ ተኝታ በሀሳብ ባህር ትዋኛለች ድንገት የሞባይሎ ስልክ ካለችበት የሀሳብ ባህር አስበርግጎ አስወጣት ።

በንዴት ስልኩን ስታየው የቅድሙ ቁጥር ነው ።.ከእጆ ላይ ስልኩን አልጋው ላይ ውረውረችው ተነስታ በፍጥነት የመኝታ ቤቶን በር ቆለፈችው ማመን አቅቶት አንስታ ስታየው እራሱ ነው ተርበተበተች ቀልቃላዋ ቀበጦ ሀና ውድያው ፈሪ እና ዝምተኛ አደረጋት የልብስ ቁም ሳጥን ላይ ያለውን መስታውት እያየች ለምን ደውለ? ያውቀኛል?ወይስ ....ምን ፈልጎ ነው ?ለብቻዋ መለፍለፍ ስልኩ ጥሪውን አብቅቶ ከ አምስት ደቂቃውች በኃላ ድጋሚ ጠራ እየፈራች አንስታው ።..
ለስለስ ባለ ድምፅ "" ሄሎ ምነው አሁንም ተመሳሰልኩብክ እንዴ"
"እየሳቀ no ይቅርታ ልጠይቅሽ እና ከተፈቀደልኝ አንድ ነገር ልልሽ ነበር!?

""ትንፋሾን አዘግይታ ... ይቅርታ አያስፈልገውም ደሞ አንዳንዴ ያጋጥማል አታስብ ስላከበርከኝ thanks.አንድ ነገር ያልከው ምንድነው?.
. ብላ አጠገባ ያለውን አሻንጉሊት እንደመንከስ እያለች ...
"ድምፅሽ ያምራል በዛ ላይ እርጋታሽ ድምፅሽ ሙዚቃ ትሞኪራለሽ እንዴ ?
"" ከት ብላ ስቃ ቀልደኛ ነክ ..በደረቶ ተኝታ እግሮቾን እያፈራረቀች አልጋው ላይ ታሳርፈዋለች ውስጦ ደስ ብሎታን ግን ለምን እንደሆነ እንዲ ልታናግረው እንደቻለች ለሯሷ ግርም ይላታል ...
ጫውታቸው ደራ በመሀል
" እንተዋውቅ አለማየው (አሌክስ)ብትይኝ አልጠላም ።.
ይህኔ የኪሩቤል ጓደኛ አማን አፈጠጠበት ..።ግን የአማን መቆጣት ማፍጠት ምን ሳይመስለው ...ውሬውን" ቀጠለ ..
""ሀና (ሀኒ ) ብትለኝ እጠላለው ስትለው
"እየሳቀ ተጫዋች ነሽ ሀኒዬ ...እንደዋውላለን ...ተባብለው ስልኩን እንደዘጉት
እሷ አልጋው ላይ መዝለል ጀመረች ከደቂቃዎች በኃላ እንዴ ምንድን ነው እንዲ የሚያረገኝ ....ለጓደኞቾ የዋትሳፕ ግሩፕ ላይ የተባባለችውን ሁላ voice አድርጋላቸው መብራቷን አትፍታ ተኛች

""ግን ያምሀል ስምህን ቀይረክ የምትተዋውቀው ቆይ ቆይ ልጅቶ ማናት?
"ኪሩ ይሄ ነገር አላማረኝም ..በጥርጣሬ አስተያየት እያየው .አማን ነበር
.
"አማንዬ ምን አታስብ ሰሞኑን አስተዋውቅሀለው ከንፈሮቹን እየነከሰ ሀኒ ማለት ጀመረ...

ይቀጥላል


share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

ለማንኛውም አስተያየት
@kaliye06
Sand and Foam
©Kahlil Gibran
≡≡≡≡≡≡≡
አንድ ፈላስፋ ለአንድ መንገድ ጠራጊ "የአንተ ስራ ከባድና ቆሻሻ ስለሆነ አዝንልሃለሁ" አለው።
መንገድ ጠራጊውም አመሰግናለሁ ጌታዬ። እስቲ ያንተን ስራ ንገረኝ " በሚል ይጠይቀዋል።
ፈላስፋውም መለሰ " እኔ የሰው ልጆችን አዕምሮ ግብሩንና ፍላጎቱን አጠናለሁ።"
መንገድ ጠራጊውም መጥረጉን በመቀጠል በፈገግታ "እኔም አዝንልሀለሁ " አለው።
"""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 3
.
.
"" አማንዬ አታስብ ሰሞኑን አስተውምውቅሀለው ከንፈሮቹን እየነከሰ ቲጂ ማለት ድምፆ የሚያምር .....
ለማንኛውም አሁን እንተኛ ..

"በተደጋጋሚ መደዋውል ጀምሩ። በእሷ በኩል ሳይደውል የዋለ ቁጥር እቤት ውስጥ መነጫነጭ እና በትንሽ ነገር የመበሳጨት ነገር ...ይህን ጉዳን ለጓደኞቾ ስነግራቸው ስቀው ግን ለምን አንድ ነገር አናደርግም አሉ።
"ማክዳ ሰው እንዴት ስልክ ተሳስቶ ደውሎ ከዛ ፍቅር ምነ ምን ያዘኝ ይላይ የንቀጥ እና የጥላቻ አክት እያሳየች አብሶ የዘንድሮ ውንዶች ጋር እውነት ፍቅር አለ"

""እንደዛ አታስቢ ደሞ ሁሉም አንድ አይደሉም በዛ ላይ ከሴትም አለ። ለገንዘብ ለውለታው...ብቻ ብዙ ፍቅሮች አሉ። አንቺ ዛሬአንድ ሰው ስለጎዳሽ ያው ናቸው አትበይ ...ቲጂ ማክዳን እያየች

""በይ እሱ ድሮ ቀረ እኔ ግን fb ...በስልክ ባጋጣሚ ምነምን አይመቸኝም አብሶ ኢንተርኔት ነክ። ፍቅር ማስጀመር እንጂ ማስጨረስ....


""ሀና የነሱክ ጭቅጭቅ እና ሙግታቸውን አንድም አልሰማችም በመሀል የስልኳ ጥሪ አባነናት ስታየው እሱ ነው። እሱ ነው ስትላቸው አንሺው ለምን አንገናኝም አትይውም አሏት

"No እሱ እስኪላት ትጠብቅ ...
""ፈገግታ በተሜው ድምፅ ሀይ አሌክስ እንዴት ነክ ...ጓደኞቾ ላውድ እንዳታደርገው በመልክት ነግራዋት አድርጋ ውሬአቸውን ቀጠሉ...

""በመሀል ሀኒ የት ነሽ?ለምን አንገናኝም?

" ደንግጣ መቼ ዛሬ አሁን በመደናነር ስሜት ውስጥ ሆና ...
""ምነው አይመችሽም ጓደኞችሽ አሉ እንዴ ..
"" አዎ ሌላ ቀን እንገናኛለን
ጓደኞቾ አፋቸው ላይ የመጣውን ሳቅ በእጃቸው ይዘው .
" እሺ ነገ ምሳ ልጋብዝሽ አስቢበት እቢ ማለት አይቻልም ....
"ካመነታች በኃላ የጓደኞቾን አይኖች አይታ እሺ እንደትለው ምልክት አሳዩያት
"እሺ...
"በቃ እንደዋውላለን ብሎ ስልኩን እንደዘጋው
"ለደቂቃ የያዙትን ሳቅ ሁሉም በነፃነት መሳቅ ጀመሩ ..
"እንደዘጋችው ኡፍፍፍ ብላ ተነፈሰች
"ነገ እንዴት ሆና መሄድ እንዳለባት መነጋገር ጀመሩ።..
ለምን እቤት አንሄድም ስትላቸው እኔ ና ማክዳ የምንሄድበት ቦታ አለ። እያውቃችሁት ባይሆን ቲጂ ጋር ሂድ ..ሜሮን ነበረች።

ትግስትና ሀና ወደ ሀና ቤት አመሩ ልክ ሲደርሱ የውጪውን በር ሲያንኳኩ እንደ ድንገት ውንድሞ ሲከፍት "እንዴ ዘበኛ ሆነክ ቀረክ" ስትለው ክው ብሎ ቀረ በርግጥ የደነገጠው በአለችው ነገር ሳይሆን ቲጂን ስላያት ነው።

""እብድ ከመምጣትሽ አትልከፊኝ ሰላም ነሽ ትግስት"
ሲል እየገባች ያለችው ልጅ ዞር ብላ ምን አልክ ትግስት ነው ያልከው። ይሄውልሽ ቲጂዬ ትላንት ቲጂ እያለ እያቄመጠ ስጠራሽ አምሽቶ አንቺን ሲያይ ....የመታውቂያ ስምሽን ይጠራል ።
በሁኔታዋ ፈንጠር ብለው የቆሙት አባቷ መሳቅ ጀመሩ። ቲጂ ያለችበትን እስከምትረሳ ትስቃለች ምን ውስጡ ቢናደድም ግን ደስ ብሎታል ።..
እየተሳሳቁ ውደ ውስጥ ገብ .።

""ሀኒ ክፍል ሆነው የልብስ ቁምሳጥኑን ከፍተው ልብስ እየሞከረች ቲጂ አልጋው ላይ እግሮን አውጥታ አስተያየት እየሰጠች ለክታ የጣለችውን ልብስ እያጣጠፈች ታስቀምጠለች ።..

""ቀይ አጠር ያለች ከጀርባው ክፍት የሆነ ልብስ ስታየው wowww ምርጥ ነው ፀጉርሽን ተሰርተሽ ስለቂው ይሸፈናል ይሄ ክፍተቱ ብላ በምርጫዋ ተስማምተው ሳሎን ሄደው ፊልም ማየት ጀመሩ። ድንገት ሀኒን አባቷ ጠርተዋት ሄደች። እስራዬል ና ቲጂ ቀሩ...ሰረቅ እያለ እያያት ተጫውቺ ...እንጂ..
"በእሽታ እራሶን እየነቀነቀች ....

አንድ ሁለት እያሉ ጫውታቸውን ደራ እየፈራም ቢሆን ነገ ለምን ሻይ ብና አንልም አላት።
እንደማሰብ ብላ እሺ ብላው ስልኮን ሰጠችው ።።...

ሀና እየለፈለፈች መጣች ...

ምሽት ላይ ሀና ስልክ ሲደወልላት ወደ ክፍሏ ገብታ ማናገር ጀመረች። ኪሩቤል (አሌክስ) አናግራ እንደጨረሰች አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ተዘርግታ ታስብ ጀመር። የመኝታ ቤቶ በር ተንኳኳ....ይግብ ወንድሞ ነበር

"ዛሬ እንግዴ ስፈነጥዝ እደር ..እንደመሳቅ ብላ ...
""ማለት እንደመኮሳተር እያለ ውደ አልጋው እየተቀመጠ
"ልትዋሸኝ ባልሆነ ሁሉንም ሳዳምጥ ነበር እንድታውሩ ነው አውቄ እንዲያስጠራኝ ያረኩት..ስትለው

አንቺ ተንከሲስ ብሎ በትራስ እየመታት አቅፎ ሀኒዬ በጣም ነው የምውዳት ከምሬ ነው። የዛሬ እንዳይመስልሽ ከአመት በፊት ነው ፍቅር የያዘኝ....

""የምትፈልግክ ከሆነ ጥሩ ልጅ ናት ።ፍቅረኛ የላትም ....

መድረስ አይቀር የተቀጠረችበት ሰአት ደረሰ ...የለበሰቸውን ከለር ነገረችው ልትውጣ ስትል
ውንድሞ" ውዴት ነው"
"ኢሲዬ ስመጣ እነግርሀለው ....
""እሺ ግን እንዲ ሆነሽ....እራስሽን ጠብቂ ....
እሱም ቲጂን ስለቀጠረ ለምን አልሸኝሽም መኪና ይዛለው በሀሳብ ተስማምታ ከተቀጠረሽበት ሆቴን አድርሶት ሰዓት ስለረፈደበት በፍጥነት እየነዳ ሄደ ።.

""ልክ እንዳያት ሀኒ ብሎጠራት ልክ ስታየው...

ይቀጥላል...



share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 4
.
. "ልክ እንዳያት ሀኒ ብሎ ጠራት
የተበተነውን ፀጉራን ገለጥ አድርጋ ቀና ስትል ደነገጠች ."
"ከመቀመጫው ተነስቶ ልክ በፊት በአካል እንደሚተዋውቁ አቅፎ ሰላም አላት ግን እሷ ደንግጣ ብዙም ሰላም አላለችውም ከትንሽ ደቂቃ በኃላ
""ምን ሆነሻል እንደዚ አልጠበቅሽኝም ወይስ ....
""በመንተባተብ አይ ለዛ አይደለም ከሰው ጋር ተመሳስለክብኝ ነው"
Sorry ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ ሶፍት አውጥታ ግንባሯን እንደመጠራረግ አለች።
"ዝምታውን ለማፍረስ ብሎ "ከጠበኩሽ በላይ ቆንጆ። ነሽ ..
"አመሰግናለሁ አንተም ብላ እንደማቀርቀር አለች
"ምሳ አዘው እየበሉ ግን እሷ ውስጦ ብዙ ጥያቄዎች አደረባት ።.
"በልተው እንደጨረሱ እሱ
""በብርጭቆ ውስጥ ያለውን ውይን እየተጎነጨ ሀኒ ድፍረት አይሁንብኝ እና ቅድም ከማን ጋር ነው የተመሳሰልኩብሽ
""አይ የቆየ ታሪክ ነው እርሳው ...

"እንዴ ለምን ንገሪኝ ታሪክ መስማስ እወዳለው ...ስሙን ንገሪኝ ፍቅረኛሽ ነበር።

"አይ አይደለም የሰፈሬ ልጅ ነው በጣም ነበር የምንዋደደው ልጆች ነበርን ኪሩቤል ይባላል የሚገርምክ የቤት ስሙን በጣም ነው የምውድለት ((ሳንቾ))

"እሱ ክው ብሎ ቀረ እንዳይታውቅበት እና የት ሄደ sorry ግን ስሜትሽን እረበሽኩሽ ...
"በረጅሙ እንደመተንፈስ ብላ ካናዳ ሄዶል ይብቃን አናውራው አለችው ..

"ያኔ እሱ እንባው እንደመምጣት አለ ግን ሽንትቤት ብሎ ሄደ እራሱን በመስታውት እያየ ሀኒ በጥሩነትሽ እንዳትመጭብኝ
እያለ ውሀ እንደመርጨት ብሎ አደራርቆ። ወደ ቦታው ተመለሰ
እሺ ሀኒ ተጫውቺ ብሎ ግን ዳንስ አታለማምጅኝም?
" ችግር የለም ለምን ከኛጋር አትቀላቀልም...እንደመሳቅ እያለች .

ማታ ከተለያዬ በኃላ
ሀኒ ተሰምቶት የማያውቅ ስሜት ይሰማት ነበር ።በርግጥ ገና በስልክ እንዳናገራት ነበር ስለሱ ማሰብ የጀመረችው ዛሬ በአካል ስታገኛው ደሞ የበለጠ
እቤት ገብታ ሰላም ብላቸው በሆነው ባልሆነው ትስቅ ጀመር። እናቶ ሀኒዬ ምን ተገኝቶ እንዲ ፈንድሻ ያደረገሽ ዛሬ ..ምን ያው ደስታ ይከለከላይ እንዴ ብላ ውደ ሞባይሎ አቀረቀርች ..

""አይከለከልም ግን ያው አለ አይደል ...የደስታ አይነት አለው ብለን ነው አባቷ ከኮምፒውተር ላይ ገታ ብለው የሀኒን ደስታ ምክንያት ለማውቅ ።..
""እእእ ምን አልተገኛም ሰላም እደሩ ብላ ውደ ክላሷ በመግባት በደረቶ አሻንጉሊቶን አቅፋ ስሜቶን በዝምታ እንዴ በግርምት በሳቅ እያዋዛች ማዳመጥ .

"በኪሩቤል ከራሱ ጋር እንደተጣላ በሀሳብ ተውጦል ድንገት ጓደኛው ዛሬ ደሞ ብሶብካል የት እንደዋልክ ከማን ጋር እንደ ነበርክ ንገረኝ ብሎ ውጥር አድርጎታል ..

"አማን ሁሉም በጊዜው ትሰማዋለክ አሁን አትጠይቀኝ ብሎ ሌላ ውሬ ቀየረ ግን ኪሩቤል ሀናን እንዴት ውደ ፍቅር ውስጥ እንደሚከታት ነው የሚያስበው ።

"እጆቹን ወደ ስልኩ ሚሴጅ ላከ እና በረጅሙ ተንፍሶ ስልኩን ደረቱ ላይ አድርጎ ውደ ጣሪያው ተመለከት ግን ሳያስበው አይኖቹ በእንባ ተሞልተዋል

"ሀና እዛ እንቅልፍ ይዞት ስለነበር የስልኳ የቨይብሬት ጥሪ አስበረገጋት እንደማማተብ ብላ ...አይኖቾን እያሸች ስታየው የሱ ነው ያሁላ ድብርት በብርሀነ ፍጥነት ለቋት ማንበብ ጀመረች

""ሰላም ገባው አይባልም እንዴ ለማንኛውም አሪፍ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው ደና እደሪልኝ "" አብባ ስጨርስ መልስ ከመላክ ይልቅ ስልኩን ስማ አይኖቾን ጨፍና ስልኩን ደረቶ ላይ አድርጋ ስሜቶን ማዳመጥ ጀመረች ። ሳታውቀው በዛው እንቅልፍ ውስዶት ነበር ስትነሳ
ስልኳን ስትልየው
""good morning""""

ደነገጠች ባፀፋው መለሰችለት እና መልስ ስጠብቅ
ድንገት የመኝታ ቤቶን ሀኒ እያለ..
.

ይቀጥላል.....

|Share|Share|Share|


share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

t.me/Write_Event
"ላለህ ነገር ሁሉ የማመስገን ልማዱ ካለህ የበለጠ ታገኛለህ። ነገር ግን በሌለህ ነገር ላይ ብቻ የምታተኩር ከሆነ በምንም አይነት መልኩ በቂ ነገር ሊኖርህ አይችልም። "
ኦኘራ ዊንፍሬይ

"ጨለምተኛ ሰው በየትኛውም ጥሩ አጋጣሚ ውስጥ አስቸጋሪ ነገሮችን ሲመለከት ፤ የብሩህ ተስፋ ባለቤት የሆነ ሰው ግን ችግሮች ውስጥ መልካም አጋጣሚዎችን የሚመለከት ነው።"
ዊንስተን ቸርችል

Join:
t.me/Write_Event
የደስታ ዋጋው ስንት ነው?

💧ኢኮኖሚክስ ላይ 'Water & Diamond paradox' የሚባል እሳቤ አለ... ለኑረት ወሳኙ ነገር ውሃ ነው - ግን 'እርካሽ' ነው... አልማዝ ለህላዌ የሚያበረክተው ድንቡሎ የለም - ግን ውድ ነው... ለዚህም ይመስላል አንስታይን "The important things are always simple" ማለቱ...

💎ዘግይቶም ቢሆን የሚገባህ እውነት ነገሮችን በውድና ርካሽ የሚፈርጀው አስተሳሰብ እንጂ የነገሩ ወሳኝነት አለመሆኑ ነው... እርግጥ ማሕበረሰባዊ ስምምነቶች ለተፈጥሮ ህግ ከመገዛት ይልቅ መንጋነትን ያበረታሉ... ለምሳሌ:
-
ዋናው ቁምነገር አብሮነትና ፍቅሩ ቢሆንም ውዱ ግን ሰርጋችን ነው...
ትልቁ እውቀት ራስን ማወቅ ቢሆንም ውዱ ግን ከአስኳላ የምንገዛው ነው...
ጠቃሚው ውበት ጸጥታ ቢሆንም የምንከፍለው ግን ለሚበጠብጠን ጩኸት ነው...
ጤናችን ያለው ንጹህ ውሃ ውስጥ ቢሆንም ብዙ የምንከፍለው ግን ለመታመሚያችን አልኮል ነው... ወዘተ

🌊እልፍ ርቀት ሮጠህ ስታበቃ ቆም ብለህ 'ለዚህ ጉዳይ ይህን ያህል ዋጋ መክፈል ነበረብኝን?' ብለህ ብትጠይቅም መሮጥህን ግን አታቆምም...
~
💦በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ጡዘትህን እንጂ ቆምታህን አያበረቱም... ይልቁን በውድድር ውስጥ እንድትቆይ ይገፉሃል... ከጓደኛህ ትወዳደራለህ... ከጎረቤትህ ትወዳደራለህ... ከባልደረባህ ትወዳደራለህ... ከንግድ አቻዎችህ ትወዳደራለህ... እናም ማቆሚያ በሌለው ዙረት [Vicious circle] ውስጥ ትቧችራለህ...

💎ዛሬ የሆነ ነገር ለማግኘት ትሮጣለህ... ደርሰህ ስትይዘው ይቀልብሃል... ነገ ሌላ ለመጨበጥ ትዘረጋለህ... ደርሰህ ስታየው 'ለዚህ ነው በሬዬን ያረድኩት?' ያስብልሃል... እንደገና ሌላ ሩጫ... እንደገና ሌላ ፍለጋ... እንደገና ሌላ መባከን...

🌊እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም... በበርህ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም... ደስታን ከውጭ ከመፈለግ በላይ ጉድለት የሚመስለኝ ይህ ነው... እየፈለጉ መቀጠልን ማቆም ባይቻል በደረሱበት አለመብቃቃት ትልቅ ጉዳት ነው... የደረስክበት ደግሞ 'አሁን' ነው... ይህ ቅጽበት... አሁንና እዚህ...

🌊አንድ ጊዜ የምረቃ መጽሔት ላይ ከፎቶ ስር ለሚሰፍር ጽሑፍ 'የእኔ ቀን ነገ ናት' የሚል ቃል ሰጥቼ ነበር... አሁን ላይ ቆም ብዬ ሳስብ 'ምን ሆኜ ነው ግን' እላለሁ... እንዴት ሰው እርግጠኛ ከሚሆንበት ዛሬ ይልቅ በማያውቀው ነገ ላይ የደስታውን ውበት ያንጠለጥላል? ደስታ ኑረትን ግድ ይላል እኮ... 'ነገ እንትን ሳገኝ እደሰታለሁ' የምትል ከሆነ ለመደሰት ቀጠሮ እየሰጠህ ነው፣ ከዚያም በላይ ደስታህን በነገሩ መኖር አለመኖር ላይ እየመሰረትክ...

🌊ደግሞስ 'ለደስታ ምን ያህል ነው የሚበቃን?' ... ስንት ብር? ስንት መኪና? ምን ያህል ቁስ?... በዙሪያዬ ብዙ 'ያላቸው' - ተነጫናጮች እና 'የሌላቸው' ደስተኞች ሳይ... ብዙ ሃብታም የበሽታ ቋቶችና ድሃ ፍልቅልቅ ፊቶችን ሳስተውል ይሄ ጥያቄ ትዝ ይለኛል... መልሱ እኮ በአጭሩ "ደስታ ውስጣዊ እንጂ ቁሳዊ [ሰበባዊ] አይደለም" የሚለው ነው... ሆኖም በተግባባንበት መንገድ ሄጄ 'ለመደሰት ስንት ያስፈልገናል?' እላለሁ... ምንም አይበቃንም... ምናልባት ምድርን የሚያህል ሃብት ቢኖረን እንኳ ሌላ ፕላኔት ማሰሳችን አይቀርም... ደስታ ግን ከብዛትም ሆነ ከነገር ጋር አትቆራኝም...

🌊ሰውየው አንድ ቦታ ላይ እንዲህ ሲል ይጠይቃል..."A table, a chair, a bowl of fruit & a violin; what else does a man need to be happy?" ይህ አባባል ለዚህ ዘመን ኑረት ከስድብ በላይ ይመስላል... ይህን ያለው ግን አንስታይን ነው... በዘመናዊው የሳይንስ ዓለም ተስተካካይ የሌለው ተጽዕኖ ፈጣሪ... ሆኖም ከስኬት በላይ እሴት ስለሚመስጠው..."Try not to become a man of success, but rather try to become a man of value" ይላል...

💦ዲዮጋን ቀፎ መሳይ ቤት፣ ውሻና ውሃ መጠጫ ቅል ብቻ የነበረው ቢሆንም ወንዝ ሲሻገር አንድ ሰው አጎንብሶ በእጆቹ መዳፍ ውሃ ሲጠጣ ባየ ጊዜ 'ለካስ ቅልም ትርፍ ኖሯል?' ብሎ አሽቀንጥሮ ጥሏል...

🌊አንድ ቱሪስት በአንድ ዝነኛ የሱፊ መምህር ቤት ተገኝቶ ባየው ቁስ ተገርሞ ይጠይቃል... የሱፊው ንብረት አንድ ምንጣፍና ላምባዲና ብቻ ነው...
'የቤትህ ቁሳቁሶች የታሉ?'
'ያንተን ቁሳቁሶች አሳየኝ እስኪ ቀድመህ?'
'እኔማ እዚህ ጎብኚ ነኝ' መለሰ ቱሪስቱ
'እኔም እኮ ጎብኚ ነኝ'

💎ተረኮቹን ያመጣሁት በዚህ ዘመን እንዲህ መኖር አለብን ለማለት አይደለም መቼም... እንግዶች ሆነን በመጣንባት ምድር ለመኖር ቅድሚያ ያለመስጠታችን ለመሞገት እንጂ... የቁስ ጥማታችንን ለማሄስም ጭምር...

አዎን... ደስተኛ መሆን ካሻህ Be Contented እልሃለሁ!!

🌊'የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ የለውም' በሚል ከንቱ ስብከት እየተነዱ 'ያለኝ ይበቃኛል' ማለት እንደሚከብድ ግልጽ ነው... ያም ሆኖ በፍላጎታችን ላይ የምንሰለጥን እንጂ ፍላጎት የሚሰለጥንብን እንዳልሆንን ማወቅም ጠቃሚ ይመስለኛል... አግበስባሽነት በማግኘት ላይ እንድትመሰጥ እንጂ ባለህ ደስታ እንድትፈጥር ዕድል አይሰጥምና...

መልካም አሁን!!❤️

ደምስ ሰይፉ


Join:

t.me/Write_Event
📜ውብ ሐሳቦች🍂


ሰውዬው ራሱን ሊያጠፋ ነው፡፡ ደሃ ነው፣ አልተማረም፣ ሥራ የለውም - ሁሌ እየለመኑ መኖር ምርር አለው፡፡ ዘላለሜን እየለመንኩ ከምኖር ራሴን ባጠፋ ይሻላል አለ፡፡ እናም … ከትልቅ ኮረብታ ላይ ራሱን ወንዝ ውስጥ ወርውሮ፣ ሰጥሞ ለመሞት ወስኖ ኮረብታውን እየወጣ ሳለ … በአጋጣሚ … ኮረብታው ጫፍ፣ አንድ የሱፊ ተማላይ አገኘ፡፡

“እ … አጅሬ መጣህ ?” አለው ተማላዩ፣ “ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት ካልሆነ ወደዚህ ቦታ ድርሽ አይሉም፡፡ ይሄን ቦታ ለተመስጦዬ (Meditation) የመረጥኩትም ለዚሁ ነው፡፡ ማንም ስለማይመጣበት ፀጥ ያለ ቦታ ነው፡፡ እንደ አንተ አይነት ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ከስንት አንዴ ነው የሚመጡት - እንኳን ደህና መጣህ…”

“እንዴ…” አለ ሰውዬው፣ “ቃላት ሳይወጣኝ እንዴት ነው ራሴን ለማጥፋት መምጣቴን ያወቅከው ? በእርግጥ … እንዳልከውም ራሴን ለማጥፋት ነው የመጣሁት”

“መብትህ ነው፡፡ ራስህን ማጥፋት ትችላለህ፡፡ ግን አንድ መግዛት የምፈልገው ነገር አለኝ ካንተ - ሁለቱን ዓይኖችህን በስንት ብር ትሸጥልኛለህ ? ንጉሡ ሁለት የተዋቡ ዓይኖች ይፈልጋል፡፡ያንተ ዓይኖች ደግሞ እንደማየው እጅግ የሚያምሩ፣ የተዋቡ ናቸው፡፡ ንጉሡ፣ እኔ ሁሌ እዚህ የራስ ማጥፊያው ሰገነት - [አዎ የቦታው ስም ያ ነው ‘የራስ ማጥፊያ ሰገነት’ ነው የሚባለው] ላይ እንደምቀመጥ ስለሚያውቅ፣ ‘አደራ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን የሚያማምሩ የአካል ክፍሎች በጠየቁህ ገንዘብ ግዛልኝ’ ብሎኛል፡፡

ደግሞም ራስህን የምታጠፋ ከሆነ እነዚህ ውብ ዓይኖች ምን ያደርጉልሃል ! ለንጉሡ መሸጥ አይሻልም ?! ስለዚህ ዓይኖችህን የምትሸጥበትን ዋጋ ወዲህ በል፡፡ ሥንት ትላለህ ! የፈለግከውን ያህል ብር ጥራ፡፡ ችግር የለውም… ”

ሰውዬው በሐሳብ ተዋጠ - ስንት ብር ይበል ?! ማሰብ ተሳነው፡፡ 500 000 ብር ? አይይ ያንሳል፡፡ 1 ሚሊየንስ ? 5 ሚሊየን ብልስ ? .....የትኛውም ገንዘብ ለዓይኖቹ ዋጋ አልመጥልህን አለው፡፡ ቢሆንም በስተመጨረሻ እንደምንም ጨክኖ፣ “10 ሚሊየን ብር” አለ፡፡

“በጣም ጥሩ … በል ና እንሂድ” አለ ተማላዩ፤ “በመጀመሪያ ዓይኖችህን እናወጣቸውና እየመራውህ ይዤህ እዚህ እመጣለሁ - ከዛ ከዚሁ ቦታ ዘልለህ ራስህን ማጥፋት ነው”

“ግን … ሌሎች ደምበኞችም አሉኝ” አለ ተማላዩ ቀጠለና፤ “ለጭንቅላትህ ስንት ብር ትፈልጋለህ - ማለቴ ዓይኖቹ የወጡለት ጭንቅላት ?”

“በጣም የምትገርም ሰው ነህ” አለ ሰውዬው፣ “ዓይን የሌለው የእኔን ጭንቅላት ማን የሚፈልግ አለ ?”

“ስለሱ አታስብ … አንድ ደምበኛ አለኝ፡፡ ምትሐተኛ (magician) ነው፡፡ የራስ ቅል አጥቶ ተቸግሯል፡፡ ‘የራስ ቅል አምጣልኝ ያልከውን ዋጋ እከፍላለሁ…’ እያለ ውጥር አድርጎ ይዞኛል፡፡ እድለኛ ነው ይሄው አንተን ጣለለታ፡፡ ለእሱ የራስ ቅሉ ዓይን ባይኖረውም ችግር የለውም፡፡ ለነገሩ እሱ ሙልጭ ያለ የራስ ቅል ነው የሚፈልገው፡፡ ስለዚህ አታስብ”

“የፈጣሪ ያለህ” አለ ሰውዬው ጭንቅላቱን ይዞ፣ “እና ጭንቅላቴን ሸጬ እንዴት ነው ተመልሼ መጥቼ…”

“እሱን በእኔ ጣለው” አለ ሱፊው፡፡

“እንግዲህ እንዳልክ … እኔ ጭንቅላቴ ስንት እንደሚያወጣ አላውቅም … እስቲ አንተው እርዳኝ … ስንት ብር ልበል ?”

“አይዞህ … አትፍራ … ራስሁ የፈለግከውን ብር ጥራ … የራስሁ ጭንቅላት አይደለ እንዴ ! እንዴ … ምን ይላል ይሄ” አለ ሱፊው… እናም ሰውዬው የራስ ቅሉን በ10 ሚሊየን ብር ሸጠ… ጥቂት እንደተጓዙ፣ “የተቀረውን አካልህንስ መሸጥ አትፈልግም ?!” ሲል ጠየቀ ሱፊው፤ “ምክንያቱም ምን ዋጋ አለው ? አንተ እንደሆነ አንዴ ሞተሃል፡፡

ዓይኖችህ፣ ጭንቅላትህ የለ… ምን ቀረህ ? ከዚህ በኋላ አካልህ ኖረ አልኖረ ምን ያደርግልሃል … እኔ ደምበኛ አለኝ፡፡ ሳይንቲስት ነው፡፡ ሬሳ እየቀደደ ምርምር ያካሄዳል፡፡ ሁሌ ባገኘኝ ቁጥር … ‘አስክሬን አምጣልኝ ነው !’ ፡፡ በተለይ አሁኑኑ የሞተ ሰው አስክሬን ባሉት ዋጋ ለመግዛት ዓይኑን አያሽም፡፡ ምክንያቱም ትኩስ አስክሬን አይገኝማ፡፡

በዕርግጥ ዓይኖችህ ወጥተዋል፡፡ ጭንቅላትህ የለም፡፡ ቢሆንም … ወዲያው እንደሞትክ፣ አስክሬንህ ሳይቀዘቅዝ ስለምሰጠው ደስታውን አይችለውም፡፡ አይገኝማ … ትኩስ ሬሳ፡፡ ልክ እኮ አሁኑኑ የተቆረጠ አበባ እንደማለት ነው፡፡ እስኪጠወልግ ሁለት ሶስት ቀን ይፈጅበት የለ - እንደዛ ነው፡፡

“አይይ በቃ ተውኩት - ራሴን አላጠፋም - ይቅርብኝ” አለ ሰውዬው ድንገት እርምጃውን ገትቶ…

“የግድ ራስህን ማጥፋት እኮ አይጠበቅብህም” አለ ሱፊው፣ “ዋናው ነገር ዓይኖችህን እና ጭንቅላትህን ሸጠህልኛል - እንዳትረሳ !”

“ቆይ ለመሆኑ … ብሩን ማነው የሚወስደው ?” ጠየቀ ሰውዬው…

“ብሩንማ እኔ ነኝ የምወስደው … ምክንያቱም አንተ የት አለህና ?” አለ ሱፊው፣ “እና ስታስበው - ብሩን ማን ይውሰደው ? ብሩ የእኔ የኮምሽን ክፍያ እንደሆነ ቁጠረው፡፡ ይዤው ልሙት ካልክም ብሩን ይዘኸው ሙት - ግን ምን ያደርግልሃል - አንተ እኮ የለህም - ሞተሃል”

ቤተመንግሥቱ አቅራቢያ ሲደርሱ ሰውዬው ሐሳብ ገባው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ … ዓይኖቹ ይሄን ያህል እንደሚያወጡ አያውቅም ነበር - 10 ሚሊየን ብር ! ይገርማል፡፡

‘ከራስ ቅሌ ጋር በአጠቃላይ ይሄ ተራ መሳዩ ጭንቅላቴ ብቻ 20 ሚሊየን ብር ያወጣል !! የተቀረው አካሌም እንዲሁ ! እና ይሄ ሰውዬ በእኔ አካል ሚሊየነር ሆኖ ሊከብር ነው ማለት ነው...’

“አልፈልግም … ትቼዋለሁ … እንደዚህ አይነት ቢዝነስ ይቅርብኝ”

“እሺ ራስ ማጥፋቱንስ ?” ጠየቀ ሱፊው…

“ራሴን ማጥፋትም አልፈልግም” አለ ሰውዬው ቁፍጥን ብሎ፣ “አሁን … በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐብታም መሆኔን ተረድቻለሁ፡፡ እስከዛሬ ራሴን እንደለማኝ ነበር እቆጥር የነበረው፡፡ ራሴን ላጠፋ የተነሳሁትም ምንም የለኝም ብዬ በማሰቤ ነበር - አሁን ግን ምን ያህል ትልቅ ሐብት እንዳለኝ ተረድቻለሁ”

“ያ ያንተ ውሳኔ ነው” አለ ተማላዩ፣ “እኔ እዛችው ኮረብታ ላይ ተቀምጬ ሌላ ሰው ልጠብቅ - አንተ ግን ብታስብበት ይሻላል - እንዲህ አይነት ደምበኞች መቼም አታገኝም…”

“አላግኝ !!! ተወኝ አልኩህ ሰውዬ - ልኑርበት” ተቆጣ ሰውዬው፣ “አንተ በጣም አደገኛ ሰው ነህ፡፡ ኮረብታው ላይ ሁሌ ተመስጠህ ሳይህ ኃይማኖተኛ ሰው ትመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ነው ምን አይነት ሰው እንደሆንክ የተረዳሁት - በጣም አደገኛ ሰው !!! ጨካኝ !!! አንድ በአንድ የአካል ክፍሌን ሸጠህ ብር ልትወስድ ! ብልጥ ! ሞኝህን ፈልግ፡፡
እስከዛሬ ስንቱን ሸጠክ ኪስህን እንዳደለብክ እግዜር ይወቀው፡፡ አሁን ግን ገብቶኛል… ለምን እዚያ ኮረብታ ላይ እንደምትቀመጥ ገብቶኛል፡፡ ቢዝነስህ ያለው እዛ ነዋ፡፡ ለከተማው ሰው ሁሉ ነው እየዞርኩ የምናገረው፡፡ ወደዚያ ኮረብታ እንዳትሄዱ፡፡ ኮረብታው ላይ አንድ አደገኛ ሰውዬ አለ ብዬ ሁሉንም አስጠነቅቃለሁ…”
“እኔ አንተኑ ለመርዳት ብዬ ነው” አለ ተማላዩ፣ “ይሄን ትልቅ ዋጋ ያለውን አካልህን በከንቱ ወንዝ ውስጥ ጨምሬ ካልገደልኩ ስትል ምን ላድርግ ?! ከገባህበት ክፉ ቅዠት ላነቃህ ነው የሞከርኩት፡፡ ተፈጥሮ ውድ ስጦታ ሰጥታሃለች፡፡ አንተ ግን እንደማመስገን በአስቀያሚ መንገድ መሄድን መረጥክ ! ደምበኛ አለኝ ያልኩህ ሁሉ ውሸት ነው፡፡ ንጉሡ ያንተ ዓይን ምን ያደርግለታል ? የሞቱ ዓይኖች ! ምትሐተኛውም የሚፈልገውን ያህል የራስ ቅል ከቀብር ቦታ ማግኘት ይችላል፡፡

በየቀኑ የማን እንደሆነ የማይታወቅ የባይተዋር ሰው አስክሬን
ወደ ሆስፒታል ይጎርፋል፣ ሆስፒታሎች ውስጥ በርካቶች ይሞታሉ፡፡ እና ለሳይንቲስቱ ምርምር ማካሄጃ የሚሆን ትኩስ አስክሬን መች ጠፍቶ ! ስለዚህ … ደምበኛ የሚባል ነገር የለም፡፡ ተፈጥሮ ምን ያህል ዋጋቸው በገንዘብ ሊተመን የማይችል ውድ ስጦታዎችን ሰጥታህ ሳለ አንተ ግን ምን ያህልvምስጋና ቢስ እንደሆንክ እንድታውቀው ብዬ ነው ! ተፈጥሮ ለሰጠችህ ውድ ስጦታዎች የምታቀርበው አንዳችም ምስጋና የለህም ? ራስን ማጥፋት ነው ያንተ ምስጋና ?!”


📚[Osho, The New Dawn, Ch 3, Q 3 (excerpt)]
ትርጉም:- ግሩም ተበጀ


||ይ🀄️🀄️ሉ||
http://t.me/Write_Event
ቃለ መጠይቅ ድሮና ዘንድሮ

(በእውቀቱ ስዩም)

📌ድሮ

ጋዜጠኛ:- ቁርስህን ምንድነው የበላህ?
ወጋየሁ:- "ዱለት"

ጋዜጠኛ:- የልብስ ምርጫህ?
ወጋየሁ:- "ቢትልስ ሹራብ"

ጋዜጠኛ:- በትርፍ ጊዜህ ምን ያዝናናሃል ?
ወጋየሁ:- "ካርታ ጨዋታ "
The end!


📌ቃለ -መጠይቅ ዘንድሮ

ጋዜጠኛ: - ዛሬ ቁርስህን ምን በላህ?

አርቲስት: -" ያው ሰው ሆነን ስንፈጠር ፤ ሰውነታችን እንደ ሰውነት ምግብ መጠየቁ አይቀርም ፤ አርቲስት ደሞ እንደማንኛውም ሰው ምግብ ያስፈልገዋል ፤ ምን ልልህ ፈልጌ ነው፤ ለኔ ትልቁ ነገር ለምግብ ሳይኖር ለህዝብ መኖር ነው ፤ ህዝብ እሚጠብቅብህን ነገር ካበረከትክ ቀኑን ሙሉ ባትበላ እንኩዋ የርሃብ ስሜት አይሰማህም ፤ ወደ ጥያቄህ ስመጣ ቁርሴን የበላሁት በቅርቡ የሚዳሰስና የሚቀመስ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበውን ጨጨብሳ ነው።"

ጋዜጠኛ:- የልብስ ምርጫህ ?

አርቲስት:-" እንግዲህ ሁላችንም ወዲዚህ ምድር ራቁታችንን ነው የመጣነው ፤ ራቁታችንን ሆነን ይሄንን ምድር እንቃለን ፤ ምን ልልህ ፈልጌ ነው፤ ርቃኔን ይሸፍንልኝ እንጂ የጣልያን ሱፍም ቢሆን ለመልበስ ዝግጁ ነኝ’

ጋዜጠኛ:- በትርፍ ጊዜህ ምን ያዝናናሃል?

አርቲስት:- "በዚህ አለም ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፤ ትርፍ ጊዜ ያላቸውና ከጊዚያቸው የሚያተርፉ፤ እኔ ከሁለተኛው ነኝ :: ያለችኝን ትንሽ የረፍት ጊዜ የማሳልፈው ከጉዋደኞቼ ጋር መስቀል አደባባይ ጉግስ በመጫወት ነው::"

ጋዜጠኛ:- ካነሳኸው ላይ የጉግስ ጨዋታን የፈጠረው ኢትዮጵያዊ ማን ይባላል?

አርቲስት:- "እንጃ!! የጥላሁን ጉግሳ አባት መሰለኝ"😂


||ይ🀄️🀄️ሉ||
https://telegram.me/Write_Event
📜ውብ ሐሳቦች🍂


በእየለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን።ያለፀፀት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁምነገር አሳልፍ።ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ልክ እንደገና በህይወት የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና የመወለድ ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውን ና ለማከናወን የምትመርጠውን አይነት ህይወት ለመኖር ሞክር።


📚ዝጎራ
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ

https://telegram.me/Write_Event
📜ውብ ሐሳቦች🍂



"ትልቅ ነገር አብዝተህ አትመኝ"

" ለምን?"

" ትንሽ ከትልቅ ስለሚበልጥ!"

"እንዴት"ልለው ስዘጋጅ "ወራጅ "ብሎ ወረደ::ከአንድ ዓመት በኃላ ታክሲ ላይ ተገናኘን:: ሰውየው በመስኮት አሾልኮ አተር ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ላከ:: የድመት ፊት የምታክለውን ፊቱን እንደስፖኪዮ ወደኔ ቀለበሰው::

" ከሰማይና ከፀሐይ በስፋት የሚልቀው ማነው?" አለኝ ከመቅፅበት::

"ሰማይ ነዋ!"

" ብርሀንን የምታጎናፅፈን ግን ትንሿ ፀሐይ ናት::" ገረመመኝ::

" ከዋክብት ኢምንቶች ናቸው አይደል?" ማታ ማታግዙፉን ሰማይ የሚያስውቡት ግን እነሱ ናቸው::

" ከበጋ እና ክረምት የሚረዝመው የቱ ነው ? ቡጋ ነው:: ዘር እየተዘራበት እህል እየታጨደበት የፍጥረትእስትንፋስ እንዳይቆም ሕይወት እንድትቀጥል እንድትቀጥል የሚያደርገው ግን ከበጋ የሚያንሰው ክረምት ነው:: ከጋንና ከጠጠር ጋን እንደሚተልቅ ሁሉም ያውቃል:: ትልቁን ጋን እንዲቀመጥ የሚያስችለው ትንሹ ጠጠር መሆኑን ግን አብዛኛው ሰው አያገናዝብም::


ከምጣድና ከጉልቻ ምጣድ ይሰፋል ግና ያለ ጉልቻ ምጣድ ማለት ጥቅም የለሽ ተራ ሸክላ ይሆናል:: እየሰማኸኝ ነው አይደል? ደሞ ስማኝ ብትፈልግም አትስማኝ ግን ስማ! ልለኔ አይደለም ለራስህ ስትል ስማ ! ልብ " ሰው" ሰው በሚባል ሀገር ውስጥ የወደቀች ብይ ናት :: ይቺ ትንሽ ብይ አምፃ ቀጥ ባለች ቅፅበት ግን ትልቁ ሰው ከሰውነት ወደ አድከሬንነት
ዜግነቱን ይቀይራል::


ከቅፅበትና ከዘልዓለም የሚረዝም የቱ እንደሆኑ ብጠይቅህ ዘለዓለም እንደሆነ እፍታ ሳትቆይ ትነግረኛለህ:: ዘልዓለም የተፈጠረው ትንሽ እንኳበማይገልፀው ትንሹ ቅፅበት ውስጥ መሆኑን አትነግረኝም:: ልንገርህ? ዘለዓለም ዝርጥርጥ ነው::የቅፅበት ጥበት ውስጥ ነው ውልደት ያለው: የቅፅበት ውልደት ውስጥ ሞት ያለው::


ዘመናት ከቀናት ቢረዝሙም ዘመናትና ፍጥረታት በሞላ የተፈጠሩት በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ ነው::
አሁንም ልንገርህትሪሊዮን ከአንድ ይበልጣል:: ከትሪሊዮን የሚበዙትን ፍጥረታት እና ዓለማት ጨምሮ ሰውን ከነኮተቶቹ የፈጠረው ግን አንድ ነው:: አንድ ፈጣሪ!!::


ወደ መፅሐፉ ተጎነበሰ እንደተጎነበሰ - " በብዙ ውስጥ ትንሽ ከመኖር በትንሽ ውስጥ ብዙ መኖት ይበልጣል::" ብሎ መፅሐፍ ውስጥ ተቀረቀር....🙇


📚[ጥቁር ሽታ]
ደራሲ:- መሐመድ ነስሩ( ሶፎንያስ አቢስ)

||ይ🀄️🀄️ሉ||
https://telegram.me/Write_Event
⭐️🌟⭐️ አብሪ ኮከቦች 💫💥💥

🇪🇹🇪🇹ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ🇪🇹🇪🇹

ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በደብረ ኤልያስ ቀበሌ፣ ጎጃም ተወልደው ሰኔ ፴ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. አረፉ) ስመ ጥር ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ለሕትመት አልበቁም። የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል።


ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ፲፱፻፴፭ ዓ/ም እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመታባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን እንዲሁም የደራስያን፤- ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ እና አቶ [[ተመስገን ገብሬን ምስል የተቀረጸባቸው ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል። (ዊክፕድያ)


ዮፍታሔ ንጉሴ፣ ብሔረ ነገዱ፣ ሀገረ ሙላዱ፣ ጎጃም፤ ቅኔ የተቀኘበት፣ ድጓ የተማረበት፣ ምስጢር ያገመረበት ደብረ
ኤልያስ ነበር። ጠይም ረዥም፤ ጠጉረ ሉጫ፤መልከ መልካም የቆንጆ ጠር፤ ቀጭን ዠርጋዳ ጣተ መልካም ፤ሽቅርቅር ጥዩፍ፤ ኮከቡ ሚዛን ነፋስ ነበር። ምዕ.1 ዮፍታሔ የቀለም ትምህርቱን ከመጀመሩ አስቀድሞ ምግበ አእምሮው የሆነውን የኤልያስን አየር እየተመገበ፣ ዝንጀሮ ያልቸውን ሁሉ ዘፈኑን፣ ስለምኑን፣ቁም ነገሩን፣ ወዘበሬታውን፣ ተረቱን፣ድርሳነ ባልቴቱን፣ ቀረርቶውን፣ልቅሶውን፣እማ በራዩን፣ ሙሻሙሾውን፣አይኮሉን፣ አረቦኑን፣ ወዘተ... እየሰማ ነበር ያደገው። ይኽ ሁሉ ኋላ ለተቀኘው ቅኔና ለደረሰው መዝሙር፣ ቲያትርና ስለምን ዐይነተኛ ዳራ ሁኖታል። ምዕ.1 የቅኔ ትምህርተ ተራውና ደረጃው ከፀዋትወ ዜማ ቀጥሎ ከትርጓሜ መጻሕፍት አስቀድሞ በጉልምስና ወራት ነው። ... ቅኔ የንባብና የጸዋትወ ዜማ ደጀን የትርጓሜ መጻሕፍት ፊታውራሪ ነው።


... ቅኔን ከጸዋትዋ ዜማ በፊት ከትርጓሜ መጻሕፍት በኋላ ለመማር በፍጹም አይቻልም። ይኽውም ከዘር በፊት ቡቃያ ከባል በፊት ልጅ ይሆናል። የቅኔ ትምህርት...የትውልድ አገርን ትቶ ጋራ ዙሮ፣ ወንዝ ተሻግሮ ወጥቶ ወርዶ፣ከውሻ ተከላክሎ ፣ቁራሽ እንጀራ ለምኖ ፣ ደበሎና ማቅ ለብሶ፣ ተዋርዶ ተንከራትቶ፣ ብዙ ፈተና ተቀብሎ፣ አይመስሉ መስሎ፣ ቀይ የነበረው ጠቁሮ፣ ረዥም የነበረው አጥሮ፣ተርቦ ተጠምቶ ፣ ፀዋትወ መከራውን ሁሉ ታግሶ የሚማሩት የተባሕት ትምህርት ነው። "ምዕ.1፤ አለቃ ዕንባቆም ቃለ ወልድን ጠቅሶ" ስለደራሲው በጥቂቱ " ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ ክብሩ" የሚል የኖረ የግእዝ አባባል አለ:: አንዱ ኮከብ በብርሀኑ፤ በግዘፉ፤ መጠቅላላ ተፈጥሮው ከሌላው ኮከብ ይበልጣል::


እኔን የሚያስገርመኝ ይኽ አይደለም:: እንዳንድ ከዋክብት አሉ--በተለየ አጠራር ተወርዋሪ የምንላቸው:: በሌሊቱ ኅዋ ውስት ከአንዱ መአዘን ሰማይ ወደ ሌላው ተወርውረው ብልጭ ብለው ይጠፋሉ:: ይህ ሁሉ የሚሆነው በቀፅበት ነው::ያንን በጨለማው ግርማ የተዋጠውን ኅዋ በብርሃን ጎርፍ ሰንትቀው አጥለቅልቀውት ይጠፋሉ:: ተመልካችም ከመገረም በሚመነጭ ዝምታ ይዋጣል:: በኢትዮዽያም የሥነ ጽሑፍ ኅዋ ውስጥ ዮፍታሔ ንጉሤ አንድ ተወርዋሪ ኮከብ ነበር።


ብሩህ ነጸብራቁ፤
ውበቱና ድምጹ አንድነት ተሰማ
ተው አንድነት ቢበርቁ፤
የመያው ቅለት ጠፍቶ፤
ምስጢሩን አካቶ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በምናየው ሰማይ ነበረ በይፋ።


አዎን፤ ነበረ። በዚያን ቅጽበት በሆነው የጽሁፍ ዘመን ዮፍታሔ፤ የኢትዮዽያን የስነጽሁፍ ኅዋ በቅኔ ፤ በግጥም ፤በመዝሙርና በተውኔት የብርሃን ጎርፍ ሰንጥቆ አጥለቅልቆት ጠፍቷል። ዛሬ የሚያሳዝነው የዚህ ተወርዋሪ ኮከብ ተጽእኖ በዘመናችን
መጥፋቱ ነው። ስለ ዮፍታሔ ንጉሴ በሕፃንነቴ እናት አባቴ ሲያወጉ፤ ሲወያዩ፤ አንዳንዴም ሲከራከሩ እሰማ ነበርበተለይ አባቴ ከዮፍታሔ ንጉሴ ተውኔቶችና መዝሙሮች በቃሉ የሚያስታውሳቸውን ስንኞች ሲያንጎራጉር እየሰማሁ የዮፍታሔ ፍቅር በሕፃን ልቦናዬና ስሜቴ ተሳለብኝ ። ያኔ ከሰማኋቸው ትዝ የሚሉኝ "አንተ ባ...ጎራዴ ግዛ" እና "ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቻ ብላ እጅግ ሳይትሩባት ሳይዘሯት አብቅላ" የተባሉት መዝሙሮች ናቸው። ሁለተኛው በጣም ጠሊቅ መዝሙር ነው። ጠሊቅነቱ የተገነዘብሁት ካደግሁ በኋላ ነው። ያኔ መዝሙሩ ይመስጠኝ የነበረው በቃላቱ ጣእመ ዝማሬ ነበረ። የፊተኛውን መዝሙር ግጥሙን በሙሉ ላገኘው አልቻልሁም። የኋለኛው ግን "ብርሃንና ሰላም" ይባል በነበረው ጋዜታ በሙሉ ተጽፎ ስላገኘሁት ከዚህ ቀጥሎ ጽፌዋለሁ፤

ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቿብላ፤
እጅግ ሳይጥሩባት ሳይዘሯት አብቅላ፤
ስንዴውን ጠብቃ እንክርዳዱን ነቅላ፤
ስትመግበን አየን በፀሐይ አብስላ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናብ መንግሥታችን።
በመልካሙ ዘርእ ላይ እንክርዳቸ ሲዘራ፤
ታሳድገውና ከእንክርዳዱ ጋራ፤
ገለባ ሲቃጠል ገበሬ ሲያመራ፤
ታቃጥለዋልች እንክርዳዱን አብራ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
አይዞህ የኛ ጌታ ነገርህን አትርሳ፤
አለስልሰህ ዝራ የስንዴውን ማሳ፤
የተዘራችው ዘርእ ፈርሳና በስብሳ ፤
ታፈራልቸ ፍሬ ሙታ ስትነሣ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
በጊዜው የዘራ መልካም ዘር አትርፎ፤
ከበሮቹ ጋራ ማታ ከትላ አርፎ፤
ብርነት ታትቆ በቅን ተሰልፎ፤
በቸርነት ታጥቆ በቅን ተሰልፎ፤
ደግሞ ዘሩን ዘራ መክር አሳልፎ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።

………………
ማንም በዕድሜው ብዛት አያስጠራም ስሙን
በጥቂቱም ዕድሜው ይሠራል ሐውልቱን።
ታሪክ ሲያበላሸው ረጅሙም ያጥራል፣
ታሪክ ሲያሳምረው አጭሩም ይረዘማል፤
ብዙ ዘመን ቢኖር ዕድሜውም ቢበዛ፤
በሳቅ በጨዋታ ዋዛን በፈዛዛ፣
ሲለዋውጥ ኖሮ ሃሳቡን ሳይገዛ፣
እንዲሁ ይቀራል እንዲያው እንደዋዛ።

📖ከ "ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" መፅሀፍ የተወሰደ ፤ ደራሲ ዮሐንስ አድማሱ

🙏🙏ክብር ለታላቁ ደራሲና ገጣሚ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ
📜 ውብ ሐሳቦች🍂


« .....በአዕምሮህ ውስጥ ያለው ድብቅ ኋይል በዙሪያ ያለውን ዓለም የመቀየር ተአምራዊ ብቃት አለው! ካሰሩ ነገሮች በላይም የአዕምሮህ አቅም ይልቃል! ሕይወትህን ያለ ምንም ተስፋ መቁረጥ በብልሀት ኑራት! አሸናፊ ሆነህ ተፈጥርሀልና አሸናፊ ሆነህ ኑር። አሸናፊ ሆነህ እለፍ! ከውስጥህ የተሸናፊነት የአልችልም ባይነት የደካማነትንና የስንፍናን ስሜት አስወግድና ሕይወትህን በአሸናፊነት ኑራት!



አንተ ምንም አይነት ሰው ብትሆን እራስህን አክበር፤ እራስህንም ውደድ። ምክንያቱም ጨዋታውን እንድትጫወት የመረጠህና ብቃት አለው ብሎ ያመነብህ እንዲሁም ወደ ሜዳው እንድትገባ የፈቀደልህ አካልም እንዳንተ አይነት ስጋ የለበሰ ሰው ሳይሆን ሰማይና ምድርን በውስጧም ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ሀያል አምላክ ነው። አንተ በብቃትህና በችሎታህ የታመነብህና የተመሰከረልህ ድንቅ ተጫዋች ነህ እኔ ተራና ምስኪን ሰው ነኝ ብለህ በደምህ ውስጥ የሚሯሯጠውን በአዕምሮህ ውስጥ የሚንበለበለውን ሀያሉን እሳት ቀዝቃዛ ውኋ እየረጨህ አታጥፋው።



ያለህን እውቀትና ችሎታ ሸፍነህ ይዘህ አታዳፍነው። አይገርምም! ዛሬ በሀገር ውስጥና በአለም ላይ በሕይወት ካሉ ሀብታም ስኬታማ ታዋቂ ሰዎች እኩል 24 ሰዐት ተሰቶሃል። እሱንም ይህንን እድል ያገኙት እድለኛ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን በጊዜያቸው በንቃት በትጋትና በፍቅር ስለተጠቀሙበት ነው። ለካ ምድር ላይ ለውጥ ለመፍጠር ወሳኙ የቸሰጠን ጊዜ ብዛት
ሳይሆን የተሰጠንን ጊዜ ምን ያህል ተጠቅመንበታል የሚለው ነው።..."


📚[ የ'ኔ ስጦታ]
ደራሲ ብሩክ የሽጥላ


||ይ🀄️🀄️ሉ||
https://telegram.me/Write_Event