ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
#እራስን መሆን ማለት እራሳችንን ከማንም ከምንም ጋር #አለማመሳሰል ማለት ነው። እራስን መሆን ቀላል ነገር አይደለም፤ ነገር ግን ሌሎችን እንደመምሰል አይከብድም። ሁላችንም ልዩ እንድንሆን ባይፈልግ ኖር አምላክ ተመሳሳይ አድርጎ በፈጠረን ነበር። ነገር ግን እኛን የሚመስል ፈጽሞ አይደገምም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ራሳቸውን በሌሎች የማንነት ሚዛን እየመዘኑ ነው የበታችነት ስሜት የሚያድርባቸው፡፡

Osho/ኦሾ

https://t.me/Write_Event
የዚህ ሙዚቃ ግጥም 👏👏👏
° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° °

አንተም ትላለህ - ምንም የለንም
እኔም እላለሁ - ምንም የለንም
ሀገር ግን ዛሬም - አላመነንም!
.
ዛሬም በኛ ጉዳይ - ዛሬም በኛ ነገር
ግራ እንደተጋባ - ውሎ ያድራል ሀገር
ከእህት ከወንድምነት - ያለፈ የለንም
ብለን ስንነግረው - ሰው እንዴት አያምንም።
.
ያለን ንፁህ ጓደኝነት
ባያውቅ ነው ወይ ወረት
አይቶን በአጉል መነፅሩ
ሁሉም መጠርጠሩ
እያሰበኝ ሰው ካንተ ጋር
ባሳጣህስ ትዳር?
ብዬ አንዳንዴ ቅር ይለኛል
ፍርሃት ይሰማኛል
ስጋት ይገባኛል።
.
ላንድ ራስ እውነትህ - ላንድ ራስ እውነቴ
አምነው ለማያምኑት - እምላለሁ ስንቴ
ወይስ ካይንህ አይኔ - አለ ድብቅ ፀባይ
ለኛ ተሰውሮ ለሌላው የሚታይ.......
°
°
°
°
ግጥም ፦ ናትናኤል ግርማቸው ና አንተነህ ይግዛው
ዜማ፦ ምህረታብ ደስታና ናትናኤል ግርማቸው
ሙዚቃ ቅንብር፦ Abel Paulos

@write_event
🙏🙏 #ሙላ_ነስረዲን_ሞኝ_ኮሚክ_ወፈላስፋ 👇

👉 አረቦች "ሙላ" እና" ሆጃ" የሚሉትን የክብር ስያሜወች እንደ ዝክር ዳቦ ለማንም በቀላሉ አይሰጡም። ሙላ የተከበረ የሀይማኖት ሊቅ፣ ሆጃ ደግሞ ታላቅና ጠቢብ መምህር እንደማለት ናቸው፤እንደኛው መምህር/አባ ወይም እንደ እብራይስጡ ራቢ።እኝህን ብርቅዬ ማዕረጋት ካገኙት ሰወች አንዱ ደግሞ ነስረዲን አቫንቲ ነው።ይህ በ1300 አካባቢ በአሁኗ ቱርክ እንደኖረ የሚገመት ሰው እጅግ በሚያስቁ ቀልዶቹ፣በእንግዳ ተግባሮቹና በግራ አጋቢ ስብዕናው ይታወቃል።

👉 ነስረዲን ይህ ነው ተብሎ ለመፈረጅ ከባድ ሰው ነው።ሞኝ፣ጠቢብ፣እብድ፣ለማኝ፣ዳኛ፣ፈላስፋ....ብቻ ሁሉንም ነው።ከ 25 በላይ ሀገራት የኛ ነው ብለው የሚከራከሩበት ነስረዲን ልክ እንደኛው አባ ገብረሀና የብዙ ቀልዶች ዋና ገፀባህርይ ነው።በመላው አለም እጅግ ከሚወደዱ ሰወችም አንዱ ነው፤የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የነስረዲን ቀን ብሎ እስኪሰይምለት ድረስ። በውብ ቀልዶቹ እየሳቃችሁ አንዳች ቁምነገር ትጨብጡ ዘንድ ጥቂቶቹን እነሆ፦

1.ሙላ ነስረዲን በአንድ ወቅት ከወዳጁ ትልቅ ማሰሮ ተበደረ።ልክ በ3ተኛው ቀን ማሰሮውን ሲመልስ ግን ከሌላ ትንሽዬ ማሰሮ ጋር ነበር።ግራ የተጋባው ጓደኛው ምን እንደሆነ ሲጠይቀው ነስረዲን ቀልጠፍ ብሎ"ማሰሮህ እኔ ጋር እያለች ልጅ ወልዳ ነው አሳድገው"አለው።በሞኝነቱ የተገረመው ጓደኛው በደስታ ተቀበለው። ልክ በሣምንቱ ነስረዲን በድጋሚ ትልቁን ማሰሮ ተበደረ፤አሁን ግን ሳይመልስ ቀረ። ይህ ያሳሰበው ጓደኛው ቤቱ ሄዶ ማሰሮውን መልስ ሲለው ሙላ እያዘነ"ማሰሮህን እኮ ሞታ ቀበርኳት"አለው። በንዴት የጦፈው ጓደኛው ለድብድብ ሲጋበዝ ነስረዲን እየሳቀ" ማሰሮህ ወለደች ስትባል ስቀህ ከተቀበልክ ሞተች ስትባል ምን አናደደህ?" ብሎ ጥሎት ገባ።

2.አዲስ የተሾመው አስተዳዳሪ ነስረዲንን አስጠራና"ሙላ እኔ ዋጋዬ ስንት ነው?" ሲለው ነስረዲን ፈጠን ብሎ"500ብር ከ15 ሳንቲም" አለው። የተናደደው አስተዳዳሪ"ያምሀል?የለበስኩት ልብስ እንኳን 500 ብር ነው እኮ" ብሎ ሲጮህበት ሙላ ፈገግ ብሎ"እሱንም ሂሳቡ ውስጥ አካትቸዋለው" አለው።

3.የከተማው ከንቲባ ጠቢባኑን ሰብስቦ የፃፈውን ግጥም ካነበበላቸው ቡሀላ አስተያየታቸውን ሲጠይቅ ነስረዲን ጮክ ብሎ"የማይረባ ከንቱ ግጥም ነው" ብሎ አፌዘበት።የተበሳጨው ከንቲባ ነስረዲንን ለ3 ቀን አሳሰረው።በ3ተኛው ቀን እልከኛው ከንቲባ ነስረዲንን ከ እስር ቤት አስጠራና አዲሱን ግጥሙን አነበበለት።ነስረዲን ትንሽ አሰበና ድንገት ብድግ ብሎ መውጣት ጀመረ።የተገረመው ከንቲባ"የት እየሄድክ ነው ሙላ?" ሲለው ነስረዲን ኮስተር ብሎ"ወደ እስር ቤት ክቡር ከንቲባ" ብሎ መለሰለት።

4.አንድ ፈላስፋና ሙላ ነስረዲን በብዙ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዙ። ፈላስፋው በቀጠሮው ቀን ሲመጣ ግን ነስረዲን በቤቱ አልነበረም።የተናደደው ፈላስፋ የነስረዲን በር ላይ "ደደብ ቂል" ብሎ ፅፎ ሄደ።የትም ሲዞር የዋለው ሙላ ማታ ሲመለስ የተፃፈውን አንብቦ የረሳው ቀጠሮ ትዝ አለው።ከዛም ወደ ፈላስፋው ቤት ሄደና በሩን አንኳኳ። ፈላስፋው በሩን ከፍቶ በንዴት ምን እንደፈለገ ሲጠይቀው ነስረዲን በትህትና"ቀጠሮአችንን ስለረሳሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ልክ ወደቤት ስመለስ ስምህ በሬ ላይ ተፅፎ ሳየው ነው እኮ ትዝ ያለኝ" አለው።

@write_event
"የተረጋጋ ህይወት እንዲኖርህ"

... መፅሀፍትን አንብብ ብዙ አታውራ ማውራት ሲኖርብህ ግን ዝም አትበል ፣ ምክር እና አስተያየት ለመቀበል አትፍራ ለተደረገልህ ጥሩ ነገር አመስግን

የማታውቀውን ጠይቅ በየወሩ ካለህ ገቢ ላይ ትንሹንም ቢሆን ቆጥብ ዛሬ መስራት የምትችለውን ዛሬውኑ ስራ

የሰው ልጅ ሲቸግረው ልብሱን ፣ የቤቱን ዕቃ ፣ ኩላሊቱንም ሳይቀር ሊሸጥ ይችላል ህሊናውን ከሸጠ ግን በጠና ቸግሮታል ማለት ነው።

ዶ/ር ምህረት ደበበ

@write_event
"ከተለያየን ምን አደርጋለሁ እችለዋለው
አብረን ባለን ጊዜ ብዙ አሳልፈን
አይቆጨኝም እኔ እሱ ይበቃኛል"

"አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም"

"የካብኩት ተናደ ባለማወቅ ስገነባው ፈርሶ
ባፀዳው ቆሸሸ እንደገና የፀዳው ደፍርሶ"

"በሚያስቀና ፍቅር ብዙ አመት ቆየን
ደግ ቀን አዋዶ ክፋ ቀን ለየን"

"ሰው ወዶ ሰው እንደመለየት ክፋ ነገር የለም
ልሸኝሽ የመጨረሻዬ በይ ይሁን ግድየለም"

"ዳገት ቁልቁለቱን ተመፀንኩት
አድርሰኝ ከልጄ እናት እያልኩት
የልቤም ባይሞላ ባላገኝሽ
እመጣለሁ በሳቤ ላጫውትሽ"

"ፍቅር ቸር ማድረጉ በኛ ታይቶ ታምኖ ተከበረ
ሰውን የሚያሳሳው ከነፍስ ወዲያ ሌላ ምን ነበረ"

-ማዲንጎ አፈወርቅ💛
ነፍስ ይማር...
ከኃይማኖትህ ፍሬ ያፈራህ ከሆንክ ፍሬህ ያስታውቃል። ማለዳ ተነስተህ ስለ እከሌ እንዲህ እላለሁ ብለህ አታቅድም። አንተን ፍጹም አድርገህ አትፈርድም። ጎጥ አትይዝም።

ሙስሊሙ፤
"ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" የሚለውን ክቡር ቃል እንዴት ተረዳኸው? እምነት ውስጥ ሆነህ ይህን ቃል በየቀኑ ስታስታውስ ለምን እንደምትለው ጠይቀህ ታውቃለህ?
ከብዙ ሙስሊም ጎራዎች አንዱ ላይ ሆነህ አትዳኝ። ልክነት ከላይ ነው። ፈቃዱን ላገኙ የእምነት ባለጸጎች የሚሰጥ ሽልማት።

ክርስቲያኑ፤
"እኔን እምትወዱ ከሆነ እኔን ተከተሉ..." የሚለው ቃል ጎሳ አለው እንዴ? "በስምህ አጋንንት አወጣን ስትሉኝ አላውቃችሁም" የሚለው ሀረግ ምን ሊነግርህ እንደሆነ አስበኸዋል?
ከብዙ የክርስትና ጎራዎች አንዱ ላይ ሆነህ አትዳኝ። ልክነት ከላይ ነው። ፈቃዱን ላገኙ የእምነት ባለጸጎች የሚሰጥ ሽልማት።

ኤቲስቱ(አምላክ የለም ባዩ)
ከታላላቅ ነቢያትህ አንዱ ሄዲጋር ነው። ''ኤግዚስታንሺያሊዝም" የተሰኘው ፍልስፍና ከጎመራመት የቀደመው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ቁጥራችሁ ጨምሯል። ቅዱስ ቃልህ ሳይንስ ወይም ዲያሌክቲክስ ነው። ታዲያ ጎጠኝነትን እንዴት አጠናኸው? ከፍልስፍናህ ታረቅ። ያላስተዋልከው እውነት አለ።

ብሔርተኛው፤
ያንተ ልማድ ልዩ ክብርህ እንደሆነው፤ ሌላውም ክብሩ የሆነ ልማድ አለው። እኔ በላጭ ነኝ ለማለት አእምሯዊ የሆነ የልማዱ ሚዛን በዓለም ታሪክ አልታየም። አይታይም።

ከስሜት ፖለቲካ ካልቀዳኸው በቀር ልማዱ ውስጥ ሳይንሳዊነት የለም። እያንዳንዱ የጎሳ ልማድ ግን በራሱ የጎሳ አባላቱን የሚያኖር ምልዓት አለው። ነፃነቱን ማክበርና መቀበል ስትችል አእምሮህ መስራት ጀምሯል ማለት ነው።
ፈላስፋ #መሐመድ_አሊ (ቡርሃን አዲስ)

@write_event
(ማለፌን 'ሚጠብቅ ፥
ትል ይናፍቀኛል
መውደቄ 'ሚያከስመው፥
ጥላ ያሳዝነኛል።)


ከመንደሪን... መንደሪን

@write_event
እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
💚💛
Join us

@write_event
ለሰው ዴንታ አይኑርህ አይባልም፡፡
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ስህተት ነው፡፡ የሰው ዋጋው በሰው ተለክቶ ነው፡፡ ማንም ሰው ለራሱ የመጠነውን ያህል ይኖራል፡፡ የልማድና ወግ መልክም ቀርጾ የሚኖር ስብስብ እንዲሁ ራሱን ያከብርበታል፡፡ ስለዚህ ለማንም ግዴለኝም እስከመሰለኝ በመሰለኝ እዋኛለሁ ብሎ መለቀቅ ከደመነብሰኝነት ማግስት የሚመጣ እክል እንዳይሆን ያስፈራል፡፡ የሰውነት ትርጉም የሚፈነጥቀው ከሰዎች ስብስብ ውስጥ ነው፡፡ ያደገንበት የኖርንበትና የምንኖርበት ከባቢ ሰውነትን የሚለካበትና የሚቀበልበት ዘየ አለው፡፡ የሚኖርበትና እንደማህበረሰብ የሚገለፅበት ብይን ነውና እሱን ካከበረ መጠይቅ መነሳት ለጥበብ መነሻ ነው፡፡

@write_event